fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጳጒሜን ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ ለተጋዳይ አባት ለአባ ባይሞንና ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አርዮሳውያንን በመቃወም በማውገዝ ብዙ ለደከመ ሃይማኖትን ለጠበቀ ላጸና ለታላቅ አባት ለአባ ሊባርዮስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታቡ፦ ከአባ ባይሞን ከስድስቱ ወንዱሞቹ መነኰሳት፡ሰማቸው ከዮሐንስ፣ ከኢዮብ፣ ከዮሴፍ፣ ከላስልዮስ፣ ከያዕቆብና አብርሃም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ ባይሞን፦ ይህም ቅዱስ ከምስር ሀገር ነው ስማቸው ዮሐንስ፣ ኢዮብ፣ ዮሴፍ፣ ላስልዮስ፣ ያዕቆብ፣ አብርሃም የሚባል ስድስት ወንድሞች አሉት ሁሉም መነኰሳት ሁነዋል። ከእሳቸውም ዮሐንስ ይልቃል ነገር ግን በእውቀትና በጥበብ ባይሞን ይበልጣል። ሁሉም ተስማምተው ከዓለም ወጡ ከሰውም ሩቅ በሆነ ቦታ የሚኖሩ ሆኑ የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ቀንበር ተሸክመው ከዘመድም ተለይተው በጠባብ መንገድ ተጓዙ። ❤ እናታቸውም ልታያቸው ወዳ ወደ በዓታቸውም ደርሳ በውጭ ቆመች ወደርሷም መጥተው እንድታያቸው ላከችባቸው እነርሱም ወደርሷ እንዲህ ሲሉ ላኩ "በዚህ በኃላፊው ዓለም ልታይን ከወደድሽ በወዲያኛው ልታይን አትችይም" እርሷም አስተዋለች አልመለሰችላቸውም መንገዷን ተጓዘች። ❤ ይህም አባት ባይሞን በአስቄጥስ ገዳም ለሽማግሌዎችም ለጐልማሶችም አረጋጊ ወደብ ሆነ። ከጠላት ሰይጣን ፈተና የሃይማኖት ጥርጥር ወይም ደዌ ያገኘው ሁሉ ወደርሱ ይመጣል ወዲያውኑ ያረጋጋዋል ከደዌውም ይፈውሰዋል። ይህም አባት በምንኲስና ሕግ ስለ መጋደል ስለ አምልኮም ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ። በትምህርቱም እንዲህ አለ "የተሰነካከለ ወንድምን ብታይ ስለርሱ ተስፋ አትቁረጥ ልቡን አንቃለት እንጂ ከወደቀበትም እንዲነሣ አጽናንተህ ሸክሙን አቃልለት። አፍህ የተናገረውን ይሠራ ዘንድ ልብህን አስተምረው" አለ። ❤ አንድ ወንድም እንዲህ አለው "ሥራው መልካም የሆነ ወንድም ያየሁ እንደሆነ ደስ ይለኛል ወደቤቴም አስገብቼ ባለኝ ነገር ደስ አሰኘዋለሁ። ግን ሥራው ብልሹ የሆነ ወንድም ያየሁ እንደሆነ አልፈቅደውም ወደ ቤቴም አላስገባውም"። አባ ባይሞንም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ሥራው በጎ ለሆነው እንዳረግኸው ለዚህም ሥራው ብልሹ ለሆነው ዕጥፍ አድርገህ በመሥራት ደስ አሰኘው ለታመመ መድኃኒት ያደርጉለት ዘንድ ይገባልና"። ❤ ከዚህም በኋላ ለዚያ ከርሱ ጋር ለሚነጋገር ወንድም እንዲህ ብሎ ነገረው "በመነኰሳት ገዳም ስሙ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ በኃጢአትም ወድቆ "አቤቱ ይቅር በለኝ" እያለ የሚጮህና የሚያለቅስ ሆነ። ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "አንተ ወንድምህን በመከራው ጊዜ ቸለል ያልከው ባትሆን እኔ ባልጣልኩህም ነበር"። ❤ ይህ አባት ደግሞ እንዲህ አለ "እኛ የወንድማችን በደል ብንሰውር እግዚአብሔርም በደላችንን ይሠውርልናል"። ይህም አባት ዕድሜውን በተጋድሎና በትሩፋት ሥራ ከፈጸመ በኋላ ወደ መልካም ዕርግና ደርሶ እግዚአብሔርን አገልግሎ ጳጒሜን 4 ቀን በሰላም አረፈ። + + + ❤ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሊባርዮስ፦ ይህም አባት አርዮሳዊ በሆነ በሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ ዘመን ተሾመ። የቈስጠንጢኖስም ወንድሙ ቊንስጣ በሮሜ ነግሦ ነበር። ❤ ሐዋርያዊ አትናቴዎስንና ጳውሎስን ከመንበረ ሢመታቸው በአሳደዳቸው ጊዜ እነርሱም ወደዚህ አባት ሊባርዮስ መጡ። ይረዳቸውም ዘንድ ለመኑት እርሱም ተቀበላቸው ከደብዳቤ ጋርም ወደ ንጉሥ ቊንስጣ ላካቸው ንጉሡም ደብዳቤያቸውን ተቀብሎ በጎ ነገር እንዲያደርግላቸው ወደ መንበረ ሢመታቸውም እንዲመልሳቸው ወደ ወንድሙ ቈስጠንጢኖስ ደብዳቤ ጻፈላቸው። እርሱም የወንድሙን ደብዳቤ በአነበበ ጊዜ አትናቴዎስን ወደ መንበረ ሢመቱ እስክንድርያ፣ ጳውሎስንም ወደ መንበረ ሢመቱ ቊስጥንጥንያ መለሳቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ቊንስጣ ንጉሥ በዓመፀኞች በተገደለ ጊዜ ቈስጠንጢኖስ ወደዚህ አባት ሊባርዮስ መልእክት ላከ ሐዋርያዊ አትናቴዎስን ያሳድደው ዘንድ የአርዮስንም ወገን እንዲቀበላቸው ብዙ ቃል ኪዳናትንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም በምክሩም ከእርሱ አልተስማማም። ስለዚህም ይህን አባት ሊባርዮስን ሩቅ አገር አጋዘው። ❤ ከዚህም በኋላ ወንዱሙ ቊንስጣን የገደለውን ጭፍራ ልኮ ገደለው። ከዚህም በኋላ ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ሔደ ስለዚህ አባት ሊባርዮስም የገዳማትና የአድባራት ሊቃውንት ካህናቱም ሁሉ ወደ መንበረ ሢመቱ ይመልሰው ዘንድ ንጉሡን ለመኑት እርሱም ምልጃቸውን ተቀብሎ ወደ መንበረ ሢመቱ መለሰው። ❤ ይህ አባት ወደ መንበሩ በተመለሰ ጊዜ በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ሁልጊዜ መንጋዎቹን ማስተማር ጀመረ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ የአርዮስ ወገኖችንም እየተቃረናቸው ኖረ ያወግዛቸውና ያሳድዳቸውም ነበር። ከስደት ከተመለሰ በኋላ በሰባት ዓመት በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሊባርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳጒሜን 3 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዕብል በልሳንየ መዋቲ። ፯ተ አኃወ ኅዱራነ በአት አሐቲ። ሶበ ፈቀደት እሞሙ ትርእዮሙ ይቤልዋ ላቲ። ኢትክሊ ትርአዪነ በዓለም ሰማይ እንታክቲ። ለእመ በዝየ ርኢክነ አንቲ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጳጉሜን 4። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ክላክ ልሳንከ እምእኩይ። ወከናፍሪከኒ ከመ ኢይንብባ ጒኅሉተ። ተሐገሥ እምእኩይ ወግብረ ሠናየ"። መዝ 33፥13-14። የሚነበቡት መልክዕታት 2ኛ ጢሞ 2፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-6 እና የሐዋ ሥራ 15፥19-25። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥23-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

ስለዚህ የዕለታት ተውሳክ ቀሪዎቹን በመያዝ ይታወቃል። መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን የዕለት ተውሳክ በመደመር ነው። መባጃ ሐመር= 21+8=29 መባጃ ሐመር ከ30 ስለሚያንስ ራሱ 29 ይያዝና መጥቅዕ መስከረም ላይ ስለወደቀና መጥቅዕ የወደቀበት ዕለት ቅዳሜ ስለሆነ የዘመኑ መጥቅዕ 21 የቅዳሜ ተውሳክ 8 ድምር 29 ስለሆነ ጾመ ነነዌ ጥር 29 ቀን በዕለተ ሰኞ ይውላል ማለት ነው። • ጾመ ነነዌ፦ መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ በመደመር በ30 ገድፈን እናገኛለን፡፡ይህ ጾም ተውሳክ የለውም የሚወጣውም በደረቅ መባጃ ሐመር ነው፡፡ ሌሎችን አጽዋማትና በዓላት ተውሳካቸውን ጾመ ነነዌ የዋለበትን የቀን ቁጥር (መባጃ ሐመር)ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን ከ30 በታች ከሆነ ደግም ራሱን በመጠቀም እናገኛለን። ••• ፩፦ ከነነዌ ጾም እስከ ዐቢይ ጾም 14 ቀናት አሉ። ስለዚህ የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ይሆናል፡፡ ፪፦ ከነነዌ እስከ ደብረዘይት 41 ቀኖች አሉ፡፡ 41 ÷ 30 = 1 ደርሶ ቀሪው 11 የደብረዘይት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፫፦ ከነነዌ እስከ ሆሣዕና 62 ቀኖች አሉ፡፡ 62 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 2 የሆሣዕና ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፬፦ ከነነዌ እስከ እስከ ስቅለት 67 ቀኖች አሉ፡፡ 67 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 7 የስቅለት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፭፦ ከነነዌ እስከ ትንሣኤ 69 ቀኖች አሉ፡፡ 69 ÷ 30 = 2 ደርሶ ቀሪው 9 የትንሣኤ ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፮፦ ከነነዌ እስከ ርክበ ካህናት 93 ቀኖች አሉ፡፡ 93 ÷ 30=3 ደርሶ ቀሪው 3 የርክበ ካህናት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፯፦ ከነነዌ እስከ ዕርገት 108 ቀኖች አሉ፡፡ 108 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀሪው 18 የዕርገት ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፰፦ ከነነዌ እስከ ጰራቅሊጦስ 118 ቀኖች አሉ፡፡ 118 ÷ 30 = 3 ደርሶ ቀርው 28 የጰራቅሊጦስ ተውሳክ ይሆናል፡፡ ፱፦ ከነነዌ እስከ ጾመ ሐዋርያት 119 ቀኖች አሉ፡፡ 119 ÷ 30 =3 ደርሶ ቀሪው 29 የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ ነው፡፡ ፲፦ ከነነዌ እስከ ጾመ ድኅነት 121 ቀኖች አሉ፡፡ 121 ÷ 30 = 4 ደርሶ ቀሪው 1 ሲሆን የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ይሆናል፡፡ ••• ከዚህ ተነስተን አጽዋማትንና በዓላትን ተውሳኮቻቸውን ከነነዌ ጋር (ከዘመኑ መባጃ ሐመር) ጋር እየደመርን እናገኛለን፡፡ ስለዚህ የ2015 የነነዌ ጾም መግቢያ ጥር 29 ቀን ይሆናል፡፡ 21+8= 29 ስለሆነ ነው፡፡ ★ ዐቢይ ጾም ተውሳኩ 14 ነው = 14 +29= 43 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 13 ሲሆን ስለዚህ ዘንድሮ በዘመነ ሉቃስ ዐቢይ ጾም የካቲት 13 ይገባል ማለት ነው፡፡ * ደብረ ዘይት፡ ተውሳኩ 11 ነው፡፡ 11+29 = 40 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 10 ይሆናል፡፡ የካቲትን ስላለፍን በመጋቢት 1ዐ እሁድ ደብረዘይት ይሆናል። ★ ሆሣዕና ተውሳኩ 2 ነው፡፡ = 2+29 =31 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 1 ስለሆነና መጋቢትን ስላለፍን ሆሳዕና ሚያዚያ 1 ቀን በዕለተ እሁድ ይሆናል፡፡ ★ ስቅለት ተውሳኩ 7 ነው፡፡ 7+29= 36 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 6 ሲሆን ዘንድሮ በሚያዝያ 6 ዓርብ ስቅለት ይሆናል፡፡ ★ ትንሣኤ ተውሳኩ 9 ነው፡፡ 9 +29 = 38 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 8 ሲሆን ሚያዝያ 8 በዓለ ትንሣኤ ይውላል። ★ ርክበ ካህናት ተውሳኩ 3 ነው፡፡ 3 +29 = 32 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 2 ስለሚሆንና በሚያዝያ ስላለፍን በግንቦት 2 ረቡዕ ርክበ ካህናት ይሆናል። ★ ዕርገት ተውሳኩ 18 ነው፡፡ 18 +29 = 47 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 17 ሲሆን ዘንድሮ ግንቦት 17 ሐሙስ በዓለ ዕርገት ይሆናል። ★ ጰራቅሊጦስ ተውሳኩ 28 ነው፡፡ 28 +29= 57 በ30 ገድፈን ቀሪው 27 ስለሆነ በግንቦት 27 እሁድ በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል። ★ ጾመ ሐዋርያት ተውሳኩ 29 ነው፡፡ 29 +29=58 ይህን በ30 ገድፍን ቀሪው 28 ሲሆን በግንቦት 28 ሰኞ የሐዋርያት ጾም ይገባል። ★ጾመ ድኅነት ተውሳኩ 1 ነው፡፡ = 1 + 29 =30 በመሆኑም ጾመ ድኅነት(የረቡዕና ዓርብ ጾም) ግንቦት 30 ይገባል። አምላካችን እግዚአብሔር በዲሱ ዓመት አዲስ ልብና ቀና መንፈስ ያድለን የስደት፣የርኃብ፣የጦርነትና የጭንቅ ጊዜያትን ያሣጥርልን። ዐውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዐውደ ዓመት ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣኅል። ሼር # ሼር # ሼር https://t.me/Eotcw

የ2015 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት ▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰ ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምሕረት + ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) = 2015 + 5500 =7515 ወንጌላዊ ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡ ዓመተ ዓለም፥4 7515 ÷ 4 = 1878 1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡ 1878×4=7512 7515-7512=1341 ደርሶ ቀሪ 3 ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ቀሪው ' 0 ' ከሆነ (ያለ ቀሪ ከተካፈለ)ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል። ስለዚህ ቀሪው '3' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ሉቃስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ይባላል። ••• ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡ ዕለተ ቀመር= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7 = 7515 + 1878 =9393 = 9393 ÷ 7 = 1341 ደርሶ ቀሪ 6 ይሆናል ቀሪው '0 'ከሆነ ሰኞ ቀሪው '1' ከሆነ ማክሰኞ ቀሪው '2 'ከሆነ ረቡዕ ቀሪው '3 'ከሆነ ሐሙስ ቀሪው '4 'ከሆነ ዓርብ ቀሪው '5 'ከሆነ ቅዳሜ ቀሪው '6 'ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው '6' ስለሆነ ዕለተ ቀመር እሑድ ይሆናል። ••• መደብ = ዓመተ ዓለምን በዐቢይ ቀመር(532) በማዕከላዊ ቀመር(76) እና በንዑስ ቀመር(19) በማካፈል ማግኘት እንችላለን 1.7515፥532=14 ደርሶ ቀሪ 67 2.67 ለ ማዕከላዊ ቀመር ወይም ለ 76 መካፈል ስለማይችል ቀጥታ ለንዑስ ቀመር (19) ይካፈላል። 67 ፥19=3 ደርሶ 10 ይቀራል። ስለዚህ መደብ 10 ይሆናል፡፡ ••• • ወንበር =መደብ ሲቀነስ አንድ ነው(አሐደ አእትት ለዘመን የሚል አዋጅ አለና ላለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ) ። መደብ - 1=ወንበር (10 - 1= 9) ይሆናል። በዚህም መሠረት ወንበር 9 ነው እንላለን • አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በዘመኑ ወንበር አባዝተን ከ 30 በላይ ከሆነ በ30 ገድፈን ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም እናገኛለን። አበቅቴ =11×9=99 99፥30= 3 ደርሶ ቀሪው 9 ይሆናል ስለዚህ የዘንድሮው አበቅቴ 9 ነው እንላለን። አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈው ዘመን አበቅቴ ላይ ጥንተ አበቅቴን (11) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን ከ30 በታች ከሆነ ደግሞ የመጣውን ቁጥር በመጠቀም ማግኘት እንችላለን ። ይህም ማለት የ2014 ዓ.ም አበቅቴ 28 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም አበቅቴን ለማግኘት 28+11=39 ይህን በ30 ገድፈን ቀሪው 9 ስለሆነ አበቅቴ '9' ይሆናል ማለት ነው። • መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በዘመኑ ወንበር አባዝተን በ 30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን። መጥቅዕ = 19×9 = 171 171 ÷ 30= 5 ደርሶ ቀሪው '21 'ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ '21 'ይሆናል። መጥቅዕን ለማግኘት ሌላው አማራጭ ያለፈውን ዘመን መጥቅዕ ከጥንተ መጥቅዕ ላይ( 19 ) በመጨመር የሚገኘው ቁጥር ከ30 በታች ከሆነ ራሱ ከ30 በላይ ከሆነ ለ 30 ተካፍሎ ቀሪው የዘመኑ መጥቅዕ ይሆናል። ይህም ማለት የ2014 ዓ.ም መጥቅዕ 2 ነበር፤ ስለዚህ የ2015 ዓ.ም መጥቅዕን ለማግኘት 2+19=21 ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ '21' ይሆናል ማለት ነው። “አበቅቴ ወመጥቅዕ ክልዔሆሙ ኢይበዝኁ እም ሠላሳ ወኢይውኅዱ እም ሠላሳ ወትረ ይከዉኑ ሠላሳ ፤ አበቅቴ ቢበዛ መጥቅዕ ቢያንስ መጥቅዕ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከሠላሳ አይበዙም ከሠላሳ አያንሱም” ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አበቅቴ ተደምረዉ ውጤቱ ከሠላሳ መብለጥና ማነስ የለበትም፤ ሁልጊዜ ሠላሳ ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ የ2015 ዓ.ም = 9+21= 30 መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ይዉላል፤ መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይዉላል፤ መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ በየካቲት ይውላል። ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 21 ስለሆነ ከ14 ይበልጣል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በመስከረም ይዉላል፤ ••• ስለዚህ የ2015 መጥቅዕ መስከረም 21 ሲሆን መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት (ዕለተ መጥቅዕ) ቅዳሜ ይሆናል፡፡ ••• መባጃ ሐመር= የዘመኑ መጥቅዕ + መጥቅዕ የወደቀበት የዕለት ተውሳክ በመጠቀም የሚገኘው ቁጥር ከ 30 በላይ ከሆነ ለ 30 በማካፈል ቀሪውን መባጃ ሐመር እንላ ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡ የቅዳሜ---8 የእሑድ---7 የሰኞ------6 የማክሰኞ--5 የረቡዕ------4 የሐሙስ----3 የዓርብ ------2 ነው የዕለታት ተውሳክ የአመጣጥ ስሌቱም የሚከተለውን ይመስላል። ከዕለተ መጥቅዕ ጀምረን እስከ ነነዌ ጾም መግቢያ ስንቆጥር 128 ቀን ይሆናል፡፡ በ30 ብንገድፈዉ 4 ደርሶ ቀሪ 8 ይሆናል፡፡ ይህም የቅዳሜ ተውሳክ ነው። በዚህ ዓይነት ስሌት ስንሄድ መጥቅዕ የሚወድቅበት ዕለት • ቅዳሜ ከሆነ ፡- 128፥30= 4 ቀሪ 8 • እሁድ ከሆነ፡127፥30= 4 ቀሪ 7 • ሰኞ ከሆነ፡ 126፥30=4 ቀሪ 6 • ማግሰኞ ከሆነ፡ 125 ፥30= 3 ቀሪ 5 • ረቡዕ ከሆነ ፡124 ፥30= 2 ቀሪ 4 • ሐሙስ ከሆነ ፡ 123፥ 30= 2 ቀሪ 3 • ዓርብ ከሆነ ፡122፥ 30= 2 ቀሪ 2

መምህር_ዘለዓለም_ወንድሙ_ቀን_03_13_13_በጽርሐ_አርየም_ቅዱስ_ሩፋኤል_ት_ት.m4a33.40 MB

ውእቱ_ሊቆሙ_ወመልአኮሙ_ስሙ_ሩፋኤል_ወረብ.m4a23.10 MB

photo content

photo content

photo content

photo content

ነገር ቢያደርግ እኔ በመከራው በችግሩ ረዳዋለሁ ወይም የሹመቴን ነገር የሚጽፍ ወይም ከቅዱሳን ጋራ ስሜን የሚያስብ ወይም በስሜ ለቊርባን የሚሆነውን የሚሰጥ ወይም በበዓሌ ቀን ምጽዋትን የሚሰጥ ይኸውም እግዚአብሔር በሊቃነ መላእክት ክብር የሾመኝና ያከበረኝ ጳጕሚን ሦስት ቀን ነው። ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እስከማስገባው በብርሃን ሠረገላ እኔ እሸከመዋለሁ በምድር ላይ ከቶ እንደርሱ ያለ የማይገኝ መዐዛው እጅግ ጣፋጭ በሆነ ሽቱ ነፍሶቻቸው እርሱን በማሽተት ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ። ❤ ሐዋርያት ሆይ በእግዚአብሔር ፊት እስከምትቆሙ እጠብቃችሁ ዘንድ ከእኔ ርዳታን ሹ። የዚህ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሩፋኤል ተአምራቶቹ ብዙ ናቸው ስለእኛ ይማልድ ዘንድ የበዓሉን መታሰቢያ ልናደርግ ይገባናል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለመልከ ጼዴቅ ዐቢይ ካህን አምሳሊሁ ለወልደ እግዚአብሔር፤ ዘእእመረ ምስጢሮ ኅቡአ ዘሀሎ ይትገበር"። ትርጉም ሊከናወን (ሊፈጸም) ዘንድ ያለውን ስውር (ድብቅ) ምስጢሩን ያወቀ፤ ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው ለኾነ ለታላቁ ካህን ለመልከ ጼድቅ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው የሆነ ካህኑ ቅዱስ መልከጼዴቅ፦ መልከጼዴቅም ዐሥራ አምስት ዓመት በሆነው ጊዜ ከአዳም ሥጋ ጋር እንዲልከውና በምድር መካከል እንዲያኖረው እግዚአብሔር ኖኅን አዘዘው እርሷም ቀራንዮ ናት። የዓለም መድኃኒት ክርስቶስም መጥቶ በዚያ እንደሚሠዋ አዳምንም ከልጆቹ ሁሉ ጋር እንደሚያድነው አመለከተው። ❤ ከዚህም በኋላ በአባቱ በኖኅ ትእዛዝ ሤም መልከጼዴቅን በሥውር ወሰደው የእግዚብሔርም መልአክ እየመራቸው ሔደው ወደ ቀራንዮ ተራራም አደረሳቸው መልከጼዴቅም ክህነትን ተሾመ። ዐሥራ ሁለት ደንጊያዎችንም ወስዶ መሠዊያ ሠራ ከሰማይ የወረደለትንም ኅብስትና ወይን መሠዊያ በሠራቸው ደንጊያዎች ላይ መሥዋዕትን አሳረገ። ❤ ምግቡንም መላእክት ያመጡለታል ልብሱም ዳባ ነው በአባታችን አዳም ሥጋ ዘንድ ሲያገለግል ኖረ። አብርሃምም ከጦርነት ነገሥታትን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ኅብስትንና ወይንን አቀረበለት አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው እርሱ ካህንም ንጉሥም ሁኖ ተሹሟልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በካህኑ ቅዱስ መልከጼዴቅ በአማላጅነቱ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ ሰራጵዮን፦ ይህም ቅዱስ ሰንዱን ከሚባል አገር ነው። ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ትርጓሜያቸውንም ተማረ የዚህንም ዓለም ገንዘብ ሁሉ ትቶ ወደ አረሚ አገር ሔደ ራሱንም በሃያ ብር ሸጦ ማገልገል ጀመረ የሽያጩንም ዋጋ ጠበቀው። እንጀራ ሳይበላ ውኃ ሳይጠጣ ከስሕተታቸው ይመልሳቸው ዘንድ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ አሳመናቸው ሕግንና ሥርዓትንም ሁሉ አስተማራቸው ከዚህም በኋላ ስለርሳቸው ራሱን ባሪያ አድርጎ እንደሸጠ እንጂ እርሱ ባሪያ እንዳልሆነ ነገራቸው ሽያጩንም ለድኆች እንዲሰጡት ሰጣቸው። ❤ ከዚህም በኋላ መንካያውያን ወደሚባሉ ሕዝቦች ሒዶ ለነርሱም ራሱን ሸጠ የክብር ባለቤት ወደሆነ ክርስቶስ እምነት እስከመለሳቸው ድረስ ተገዛላቸው። ከዚህም በኋላ ደግሞ ወደ ሮሜ አገር ሒዶ በሰላም እስከ አረፈ ድረስ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳጒሜን 3 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ ዓራራይ ዜማ፦ "ይቤሎ ለጦብያ አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሐዱ እምሰብዓቱ (ተሰዓቱ) ሊቃ መላእክት ዘተፈኖኩ ኀበ ጦቢት"። ትርጉም፦ ለጦብያ ከሰባቱ (ዘጠኙ) ሊቃነ መላእክት አንዱ ወደ ጠቢት የተላኩኝ ሩፋኤል መልአክ እኔ ነኝ አለው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "መሐለ እግዚአብሔር ወኢይኔስሕ። አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከጼዴቅ። እግዚአብሔር በየማንከ"። መዝ109፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 17፥20-31። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እግዚአብሔርሰ ገሃደ፡ይ መጽእ። ወአምላክነሂ ኢያረምም። እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"። መዝ 49፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 7፥1-7፣ ይሁ 1፥11-17 እና የሐዋ ሥራ 5፥16-26። የሚነበው ወንጌል ማቴ 25፥31­46። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው። መልካም የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤለ በዓል ለሁላችን ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጳጒሜን ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሩፋኤል ለተሾመበት፣ ጦቢትን ዐይኑን ለአበራለትና ልጁ ጦብያን ለረዳበት፣ የራጉኤልን ልጅ ሣራን ተቆራኝቷት የነበረው አስማንድዮስ ጋኔን ላወጣላት በዓል(ታሪክ በጽሐፈ ጦብት ላይ ያንብቡ)ና ለሊቀ ካህን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ለሆነ ለካህኑ መልከፄዴቅ ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን በስንክሳሩ ከሚታሰበው፦ ሰንዱን ከሚባል አገር ከቅዱስ ሰራጵዮን ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግዕዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ይሰግዱ በብረኪሆሙ ወያሌዕሉ ህሊናሆሙ በጥንቃቄ ወበኅሢሥ ኀበ እግዚኦሙ ንጉሥ ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት ዑራኤል ወሩፋኤል ይትፌነው፡ለሣህል እምኀበ ልዑል"፡፡ ትርጉም፦ ወደ ጌታቸው ንጉሣቸው ይሰግዳሉ ህሊናቸውንም በጥንቃቄ ከፍ ከፍ ያደርጋሉ ለነፍሳት የሚቆሙ እነዚህ አለቆች ዑራኤልና ሩፋኤል ከልዑል ለይቅርታ ይላካሉ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለሩፋኤል መልአከ ነፍስ"። ትርጉም፦ የነፍስ (የሰውነት) መልአክ ለኾነ ለቅዱስ ሩፋኤል ሰላምታ ይገባል"። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለአፃብኢከ አዕይንተ ጦቢት ዘፈሳ። ወለ አፅሪከ ደርገ ዘኵሕላ ሐሞት ዓሣ። መልአከ ምሥጢር ሩፋኤል ወዘውገ ርቡዓን እንስሳ። አዕይንትየ እግዚኦ አፃአብከ ይግሥሣ። ከመ እደ መልአክ ገስሳ ለነቢይ ዘሱሳ"። ትርጉም፦ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ የጦቢትን ዐይኖች ለፈወሱ ጣቶችህ ሰላም እላለሁ። ለመፈወሱ በመተባበር የዓሣ ሐሞትን ለኳሉ ጥፍሮችህም ሰላም እላለሁ። ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ የኪሩቤል ወገን­ የምትሆን መለኮዊ ምሥጢርን የምትነግር ነህና። የሕይወት መልአክ እጅ የሱሳን ነቢይ እንደ ዳሰሰ። አቤቱ ጣቶችህ ዓይኖቼን ይዳስሱልኝ። መልክአ ቅዱስ ሩፋኤል። + + + ❤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል፦ እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው። ደግሞም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት ነው። ❤ ይህም እንዲህ ነው ሀብታም ሴት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ መጥታ ሳለ ከእርሷ ጋርም ብዙ ሰው ነበረ። ከባሏም የወረሰችው ብዙ ገንዘብ አላት በሊቀ ጳጳሳቱ ቤት አንጻር ያለውን ኮረብታ አስቆፈረችው በጥቅምት ወር ዐሥራ ስምንት ቀን እንደጻፍን የወርቅ መዝገብ ተገለጠ። በዚያም ወርቅ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትን አነፀ ከእርሳቸውም አንዲቱ የመላእክት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ ሩፋኤል በስሙ የታነፀች ይህች ናት። ሥራዋንም በፈጸመ ጊዜ እንደዛሬው በዚች ቀን አከበራት። ❤ ብዙ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈጽማ ተናወጸች ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና። የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ ያን ጊዜ ይህ የከበረ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው "እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም"። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ። ❤ ይቺም ቤተ ክርስቲያን እስላሞች እስከተነሡበት ዘመን ኖረች ከዚህም በኋላ ሁለተኛ ያ አንበሪ ተናወጸ ደሴቲቱም በላይዋ ከሚኖሩ ብዙ ሕዝብ ጋራ ሠጠመች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የመልአክ ቅዱስ ሩፋኤል በረከቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ዳግመኛም የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ ጻድቅ ለሆነ ንጉሥ አኖሬዎስ ተናገረ። እንዲህም አለው "ንጉሥ ሆይ እኛ ወዳንተ ልንመጣ በመርከብ እንደተሳፈርን ዕወቅ በጒዞ ላይ ሳለንም በቀዳሚት ሰንበት ቀን በደሴት ውስጥ ታናሽ ቤተ ክርስቲያን አየን ወደ ወደቡም ደርሰን በዕለተ እሑድ ሥጋውን ደሙን እንቀበል ዘንድ ወደርሷ ሔድን። ❤ ለዚያች ቤተ ክርስቲያንም በጐኗ ታናሽ ገዳም አገኘን በውስጧም ወንድሞች መነኰሳት አሉ በክብር ባለቤት ጌታችንም ፈቃድ ወደ ርሳቸው ደረስን። መነኰሳቱንም "በቀደሙ አባቶች ዘመን የተጻፈ አሮጌ መጽሐፍ በእናንተ ዘንድ እንዳለ እጽናናበት ዘንድ እርሱን ሰጡኝ" አልኳቸው። ❤ እንዲህም ብለው መለሱልኝ "እኛ ትርጓሜያቸውን የማናውቀው መጻሕፍቶች በዕቃ ቤት አሉ"። እኔም "አያቸው ዘንድ ወደዚህ አምጡልኝ" አልኳቸው። በአመጡአቸውም ጊዜ መረመርኳቸው ጌታችንም በደቀ መዛሙርቱ ፊት ያደረጋቸውን ኃይሎችና ድንቆች ተአምራቶችን ስለ ሰማይና ምድርም ጥንተ ተፈጥሮ አገኘሁ። ❤ ሁለተኛም ስመረምር ስለ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሹመትና መዐርግ አባቶቻችን ንጹሐን ሐዋርያት የጻፉትን አገኘሁ ይኸውም ጌታችን በደብረ ዘይት ከእሳቸው ጋራ እያለ የመለኮቱን ምሥጢር በገለጠላቸው ጊዜ። ሐዋርያትም እንዲህ ብለው እንደለመኑት "ጌታችንና ፈጣሪያችን ሆይ የከበረ የሩፋኤልን ክብሩን ታስረዳን ዘንድ እንለምንሃለን በየትኛው ዕለት በየትኛው ወር ሾምከው"። ከባልንጀሮቹ የመላእክት አለቆችም ትክክል ነውን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ዘንድ በዓለም ውስጥ ስለርሱ እንድናስተምር እርሱም በመከራቸው ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ በአማላጅነቱም በአንተ ዘንድ ይቅርታን ያገኙ ዘንድ። ❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዘዘና ከሦስተኛው ሰማይ ሦስቱ የመላእክት አለቆች ሚካኤል፣ ገብርኤልና ሩፋኤል መጡ በታላቅ ደስታም ለክብር ባለቤት ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰገዱ። ጌታችንም ሩፋኤልን እንዲህ አለው "የክብርህን ገናናነት የባልንጀሮችህንም ልዕልናቸውን እንዲያውቁ ለሐዋርያት ንገራቸው"። ያን ጊዜም ለጌታችን ሰገደ ይነግራቸውም ዘንድ ጀመረ እንዲህም አላቸው "ደገኛው የመላእክት አለቃ ሚካኤል ለሁሉም መላእክት አለቃቸው ነው ስሙም ይቅር ባይ ይባላል"። ❤ "ሁለተኛም የመላእክት አለቃ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ አገልጋይም ጌታም የሆነ የዓለሙ ሁሉ እመቤት የሆነች አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሠራት ነው"። "የእኔም ስሜ ሩፋኤል ነው ይህም ደስ የሚያሰኝ ቸር መሐሪ ቅን የዋህ ማለት ነው እኔም ኃጢአተኞችን በእግዚአብሔር ዘንድ አልከሳቸውም ከኃጢአታቸው በንስሓ እስኪመለሱ ስለ ቅንነቴ በእነርሱ ላይ እታገሣለሁ እንጂ። በሃያ ሦስቱ የመላእክት ነገድ ሠራዊት ላይ እግዚአብሔር የሾመኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ እግዚአብሔር አብን ይቅር ባይ ልጁን አጽናኝና አዳኝ የሆነ መንፈስ ቅዱስን እናመሰግነው ዘንድ። ❤ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሺህ ዓመት ተድላ ደስታ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክብር ጽዋን በሚሰጣቸው ጊዜ ለቅዱሳኖቹ በጎ ነገርን እንድሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ። ደግሞም በዚች ቀን ከዕፀ ሕይወት ዐጽቅ ወስጄ ለተመረጡ ክርስቲያኖች በእጄ እንድሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ። የሰማያት መዛግብትም ከእጄ በታች ተጠብቀው የሚኖሩ እኔ ሩፋኤል ነኝ። እኔም እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እከፍታቸዋለሁ እዘጋቸዋለሁም። ❤ በምድር ሰው ለባልንጀራው ስለ ስሜ በጎ

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጳጒሜን ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ታላቁን ቀብጽያ ገዳምን ለመሠረቱት፤ መልአከ ሞትን የማያሳይ ታላቅ ቃልኪዳን ላላቸው ለታላቁ ለአባት ቀፀላ ጊዮርጊስ ለዕረፍታቸው በዓልና ለኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ላለው ለአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለዕረፍቱ ቀን መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ቀፀላ ጊዮርጊስ፦ ትውልዳቸው አገው ሲሆን ከብዙ ጽኑ ተጋድሎአቸው በኋላ እንደ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው ታላቅ አባት ናቸው። አቡነ ቀፀላ ጊዮርጊስ በ16ኛው መ/ክ/ዘ የነበሩ ሲሆን ታላቁን ቀብጽያ አንድነት ገዳምን የመሠረቱት ናቸው። ጻድቁ በመጀመሪያ የአባ አሞኒን ገዳም ለመገደም ወደ ትግራይ ቀብጽያ ሲሄዱ በእግዚአብሔር ታዘው የአቡነ አሞፅን ገዳም በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም መሠረቱ። ገዳሙም "ቀብጽያ አሞፅ ወቀፀላ ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም" ተባለ። ❤ አቡነ ቀፀላ ጊዮርጊስ 200 ተከታይ መነኰሳትን አስከትለው ሌሎች 6 አስደናቂ ገዳማትን ገድመዋል። ገዳማቱም ማይወኒ ቅዱስ ሚካኤል፣ ውጅግ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ ጅል ውኃ ቅዱስ ማርቆስ፣ ዶቅላኮ አርባእቱ እንስሳ፣ አንጓ ቅድስት ማርያም እና ድቁል ማርያም ይባላሉ። ❤ ጻድቁ ስድስት ክንፍ እስኪሰጣቸው ድረስ ብዙ ተጋድሎ ያደረጉት በቀብጽያ ገዳም ነው። ዕረፍታቸውም ጳጒሜን 3 ቀን ነው። በዘንዶዎች የሚጠበቀው ይህ አስደናቂ ገዳም በብዙ መልኩ ከሌሎች ገዳማት የተለየ ነው። የገዳሙን አፈር ቅዱሳን መላእክት ናቸው ከገነት ያመጡት። ጌታችን 12 እልፍ መላእክቱን ልኮ ከገነት አፈር አምጥተው በዝናብ አምሳል በቀብጽያ ገዳም ላይ እንዲነሰንሱት አዟቸዋል። ❤ ገዳሙን የተሳለመ ሰው ኢየሩሳሌም በጎልጎታን እንደተሳለመ የሚቆጠርለት ሲሆን በገዳሙ ውስጥ የተቀበረ ሰው ወቀሳ የለበትም። ከአካሉም ላይ ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን ቆርጦ በገዳሙ ክልል ውስጥ የቀበረ ሰው ቢኖር መልአከ ሞትን ፈጽሞ እንደማያይና ገዳሙ የሚገኝበት አካባቢ በእግር ለመጓዝ አስቸጋሪ ቢሆንም ቦታውን የረገጠ እስከ 15 ትውልድ ምሕረትን እንደሚያገኝ ጌታችን በቃል ኪዳን አጽንቶታል። ❤ ቀብጽያ ገዳምን ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፈዋሹ ጠበል ከጻድቁ አቡነ አሞፅ መቃነ መቃብር ሥር የሚፈልቅ መሆኑ ነው፡፡ ከዋሻው ሥር የተንጠባጠበው ጠበል ወደ ጠንካራ ዐለትነት የሚቀየር ሲሆን እርሱን ለእምነት የተጠቀሙበት ሰዎች ከተለያዩ በሽታዎች ተፈውሰዋል፡፡ በቅርቡም ከ6 ዓመት በፊት በዚህ እምነት የተሻሸች አንዲት ሴት ከዘመኑና መድኃኒት ካልተገኘለት ከHIV በሽታና ከመካንነቷ ተፈውሳ ልጅ ወልዳለች፡፡ ይህ አስደናቂ ቀብጽያ ገዳም ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ቢሆንም ከጊዜና ብዛት ጉዳት ስለደረሰበትና የሚያድሰው አካል ስላላገኘ በአሁኑ ወቅት ሌላ አዲስ ቤተ መቅደስ እየታነጸ ይገኛል፡፡ ❤ በቀብጽያ ገዳም ውስጥ 336 ዓመት የሆነው የወይራ ዛፍ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ ስውራን የሆኑ ቅዱሳን ሦስት ጊዜ ደወል ሲደውሉበት ተሰምቷል፡፡ ገዳሙን አቡነ ቀፀላ ጊዮርጊስ ይገድሙት እንጂ በቦታው ላይ አቡነ አሞፅ አስቀድመው መቶ ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ኖረውበታል። አቡነ አሞፅ ትውልዳቸው ሸዋ ሲሆን የመነኰሱት ደብረ ሊባኖስ በአቡነ ዮሐንስ ከማ እጅ ነው፡፡ አቡነ ዮሐንስ ከማ በመልአክ ታዘው 10 መነኰሳት 500 ሕዝብ ተከትሏቸው ወደ ትግራይ ሲሄዱ ሳምረ ወረዳ ላይ ሲደርሱ ሕዝቡ ቢራብ ዋርካ ዕለቱን አብቅለው ባርከው መግበውታል፣ ውኃም አፍልቀው አጠጥተውታል፡፡ ከዚኽም በኋላ የበቁትንና ቅዱሳን የሆኑትን ዓሥሩን መነኰሳት ገዳም እንዲገድሙ ወደተለያዩ ቦታዎች ላኳቸው፡፡ ከእነዚኽም ዓሥር ቅዱሳን መነኰሳት መካከል አቡነ አሞፅ አንዱ ናቸው፡፡ እርሳቸውም ጽላተ ማርያምን ይዘው በቅዱሳን መላእክት ታጥራ ወደምትገኘው ምድረ ቀብጽያ መጥተው መቶ ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ። ❤ አቡነ አሞፅ ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን የእመቤታችን መከራ የሚተርከውን ድንቅ ድርሰት ሙሉውን ክፍል በብራና ላይ በሥዕል ገልጸው በክብር አስቀምጠውታል፡፡ ከሰማይ የወረደላቸው የወርቅ መስቀላቸውም በገዳሙ ይገኛል፡፡ ❤ አቡነ አሞፅ በ1592 ግንቦት 26 አርብ ቀን ሲያርፉ ጌታችን ከድንግል እናቱ ጋር ተገልጾላቸው ከላይ ያየናቸውን አስደናቂ ቃልኪዳኖች ከሰጣቸው በኋላ ነፍሳቸውን እመቤታችን አቅፋ አሳረገቻቸው፡፡ ዐፅማቸው ያረፈበትን መካነ መቃብር ታላላቅ ዘንዶዎች ይጠብቁታል፡፡ ጠበላቸውም የፈለቀው ከመቃብራቸው ሥር ነው፡፡ ቦታው በስውራን ስለሚገለገል የከበሮ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን የእጣንም ሽታ ይሸታል፡፡ ከአባታች ከአቡነ ቀፀላ ጊዮርጊስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ከገዳሙ ካሳተመው ስዕል ጀርባ የተገኘ ታሪክና መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ። + + + ❤ በዚች ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ያለው ዘርዐ ያዕቆብ ዐረፈ። እርሱም በመንግሥቱ ግዛቶች አገሮች ሁሉ ያማሩ ሥርዓቶችን የሠራ ሃይማኖትንም ያቀና ነው እግዚአብሔርንም አገልግሎ ደስ አሰኝቶ ጳጒሜን 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳጒሜን 3 ስንክሳር። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

​​ጳጉሜን ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡ የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ተፅሕፈ ፡ እም ዲ/ን የአብስራ ጌታሁን

ቅዱስነታቸው በሰላም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ተመልሰዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሀገረ አሜሪካ ሲያደርጉ የነበረውን ሕክምናቸውን አጠናቀው ዛሬ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው በሰላምና በመልካም ጤና ተመልሰዋል። የቅዱስነታቸውን ወደ ሀገርና ወቅዱስ መንበራቸው መመለስን ተከትሎ በአሁን ሰዓት የአቀባበል ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተካሄደ ነው። የፎቶ ባለቤት : የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ጷጉሜ 🌼 እንኳን አደረሳቹ 🌼 ሰላም እንዴት ናቹ ጓደኞቼ በቅድሚያ እንኳን ለጷጉሜ (13)ኛ ወር አደረሳቹ!!!እስኪ ዛሬ ስለ የጷጉሜ (Qaammee) ወር አመጣጥ ትንሽ ልበላቹ!ለመሆኑ የጿጉሜ ወር አመጣጥ እንዴት ነው? መረጃውን ያገኘውት ከመምህር ሮዳስ ታደሰ ሲሆን የጷጉሜን አመጣጥ እንዲ ያስረዱናል፦ "❤️ጷጉሜ የተባለችው 13ኛዉ ወር በፅርዕ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል፡፡የአምስት (5) ቀናትን ጷጉሜን አመጣጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጠንቅቀው ቀምረው በባህረ ሃሳብ ብራናቸው ላይ ፅፈውልናል፡፡" "❤️ይኽውም ከመስከረም 1 እስከ ነሃሴ 30 ያሉት 12ቱ ወራት ባጠቃላ ያላቸው360 እለታት ነው፡፡ በቀደምት ኢትዮጲያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ትንተና 1 ቀን የሚባለው 24 ሰአት 52 ካልኢት ከ31 ሳልሲት ነው፡፡" "❤️ 1 ካልኢት ማለት 24 ሰኮንድ ሲሆን 52 ካልዒት ማለት 1248 ሰከንድ ነው፡፡31 ሳልሲት ማለት 12.4 ሰከንድ(ቅፅበት) ይሆናል፡፡ በመሆኑም በአንድ ቀን ውስጥ 1 ደቂቃ ከ 0.4 ሰከንድ ትርፍ መኖሩን ያስረዳል፡፡" "❤️በመሆኑም ከመስከረም 1 እስከ ነሃሴ 30 ባሉት 360 ቀናት ያሉትን 52 ካልዒት ወይም1248 ሰከንድ እንደዚ እናባዛቸዋለን 52 ካልዒት×360 ዕለታት=18,720 ካልዒት ወይም 449,280ሰከንድ ይሆናል፡፡ ወደ ደቂቃ ስንለውጠው 7488 ደቂቃ ወይም 5 ዕለት ይሆናልና፡ የጷጉሜ አመጣጥ ይች ናት፡፡" : : : እኔን በጣም ያስገረመኝ እና ያስደነቀኝ የጳጉሜ 5 ሚስጥር 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 "❤️አራት የአመት ወቅቶች ማለትም፦መፀው፣ሐጋይ፣ፀደይ እና ክረምት 91,91 የሚሆኑት ከጷጉሜ 1 ቀን እየተሰጣቸው ሲሆን ባጠቃላይ 364 ቀናት ወይም 52 ሳምንት ኾኖ አንዲት እለት ትተርፋለች ፤ይቺኽም ጷጉሜ 5 ስትሆን በኢትዮጵያ ቀደምት የዘመን ቀመር ሊቃውንት "እለተ ምርያ አዕዋዲት" ትባላለች፡፡ "❤️እለተ ምርያ ማለት እለተ መድኃኒት ማለት ነዉ፤ ምክኒያቱም ጷጉሜን አምስት (5) የመዳኍኒታን የእየሱስ ክርስቶስ ልደትን የምናውቅባት ስለሆነች ነው፤ይኽውም ጷጉሜ 5 በዋለችበት ዕለት የክርስቶስ ልደት ዕለት በተመሳሳይ መልኩ ይውላል፡፡😁 ለምሳሌ፦የዚህ ዓመት ጿጉሜ 5 ዕለተ ቅዳሜ ናት በተመሳሳይ የ2015 የክርስቶስ ልደት ታሕሳስ 29 ቅዳሜ ትውላለች ፡፡😀😀😀 በዚ ምክኒያት ነው ዕለተ ምርያ የሚል ስያሜ ሊሰጣት ችሏል፡፡" "❤በተጨማሪ ጷጉሜ አምስት(5) የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የአዲሱ አመት መንደርደሪያ ዕለት እንደ ሆነች የክርስቶስ ልደትም የአመተ ፍዳ ማቆሚያ️ የአመተ ምህረት መጀመሪያ በመሆኑ እለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ መዋሉ እጅጉ ይገርማል፣ይደንቃልም፡፡ " ምንጭ፦ከመምህር " ሮዳስ ታደሰ "የተወሰደ በመጨረሻ ትንሽ ነገር ልበላቹ ❤️❤️ይችን ቀን ቀምረው ላስቀመጡልን ሊቃውንት አባቶቻችን ክብር🙏🙏🙏 ክብር ይገባቸዋል!!! በ2014 ያስቀየምኳችሁ ይቅርታ!!!🙏 ዘመኑን በይቅርታ (ይቅር በመባባል እንሸኘው !!!) አዲሱ አመት የሰላም፣የፍቅር እና የአንድነት ያድርግልን !!! "አሜን" "ፍቅር ይስጠን!!! አሜን"❤️❤️❤️ : : " ሃገራችን ሰላምሽ ብዝት ይበልልን" ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቃት!!!🙏