fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
❤ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በአገልግሎታቸው ለሚያምኑ እያጽናኑና እያበረቱ፣ ለማያምኑ ደግሞ አሳምነው እያጠመቁ እስከ ማዕርገ ክህነት አድርሰው ቤተ ክርስትያን ይሠሩላቸው ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ቅዱስ አባታችን በብዙ ተጋድሎ ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውንና አገልግሎታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከእግዚአብሔር የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለው ጥቅምት 19 ቀን 1722 ዓ.ም በ96 ዓመታቸው ራሳቸው በመሠረቱም በገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስ ሥላሴ ዐርፈዋል፡፡ ❤ የአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤልን መንገድ የተከተሉ የዚህ ገዳም መነኰሳትም በጸምና በጸሎት ተወስነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሑሩ ወመሐሩ" (ማቴ 28፡19) ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሐዋርያዊ ተልኮአቸውን እየፈጸሙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናን ከከረን እስከ ኦምሓጃር ከዛ አልፎም እስከ ከሰላ ሱዳን አንጸዋል፡፡ በፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም ሐምሌ 7 ቀን የሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል በዓለ ዕረፍታቸው ጥቅምት 19 ቀን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በእነዚህ ክብረ በዓላት ላይ በርካታ ምእመናን ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ከበረከቱ ይሳተፋሉ፡፡ ከአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ኤርትራ አገር የሚገኘውን በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ አስደናቂውን ፃዕዳ ዓምባ ቅድስት ሥላሴ ገዳምን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት ለአቡነ ሰይፈ ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል፦ እኚህ ጻድቅ በ1669 ዓ.ም የገደሙት ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ ገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስት ሥላሴ ከኤርትራ በዓንሰባ ዞን ከከረን 25 ኪ.ሜ እርቆ በደቡባዊ ምዕራብ ከባሕር ጠለል በላይ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ወደዚህ ድንቅ ገዳም የሚያደርሰው መንገድ ዳገትና ቁልቁለት የበዛበት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሣ ብርቱ ትዕግሥትና መንፈሳዊ ጽናት ይጠይቃል፡፡ ገዳሙ ለመድረስ ከከረን ከተማ በደቡባዊ ምዕራብ በኩል ወንዞችንና ጋራ ሸንተረሮችን ማቋረጥ ግድ ነው፡፡ ከዚያም "ድንጃ ወርቅ" በተባለ ከገዳሙ እግር ሥር በሚገኘው ረጅሞ ተራራ ከተደረሰ በኋላ ከድንጃ ወርቅ የአንድ ሰዓት ተኩል ዝግዛግ የእግር ጉዞ ያስኬዳል፡፡ ከዚያም "ማዕዶዋይ" ከተተባለው ቦታ ይደረሳል፡፡ ትርጓሜውም በርቀት የሚታይ ማለት ነው፡፡ ከማዕዶዋይ ወደ ገዳሙ ውስጥ ለመግባት ከእግር መረገጫ የማያልፍ ስፋት የሌላት በቀኝና በግራ የምታስፈራ በጭንቅ የሚሻገርዋት "ጸናፌ ጽልመት" ተብላ የምትጠራዋን አስጨናቂ ገደል ማለፍ ግድ ይላል፡፡ ይህቺን ለመሻገርም ሆነ ለማለፍ አስቸጋሪ የሆነችን መንገድ ለብዙ ጊዜ የተመላለሱባት ምእመናን ግን ከባድ እቃ በሸክም ይዘውም ቢሆን ያለ ምንም ፍርሃት ይሻገሩባታል፡፡ በጭንቅ የሚሻገርዋትን ይህችን አስጨናቂ ገደል ከታለፈ በኋላ ቀጥሎ "ደገ ሰላም" ና "መንገደ ሰማይ" የሚባል ወደ ገዳሙ የሚያስገባ ዝግዛግ መንገድ አለ፡፡ ❤ አባታችንን ወደዚህ ድንቅ ገዳም እየመራ ይዞአቸው የገባው የታዘዘ መልአክ ነው፡፡ ወደ ገዳሙ ቅጥር ውስጥ ከተገባ በኋላ ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ልዩና መንፈሳዊ ሐሴትን የሚሞሉ በርካታ ተአምራት የተፈጸመባቸውን ነገሮችን መመልከት ይቻላል፡፡ተአምራቶቹም "ድሮ እንዲህ ነበር፣ እንደዛ ተደረገ…" ተብሎ በአፈ ታሪክ ብቻ የሚወራ ሳይሆን አሁንም ድረስ በዐይን የሚታዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገዳሙ አጠገብ የሚገኙት ዛፎች ብዙ ዕድሜ ከማስቆጠራቸው የተነሣ በንፋስ ኃይል ሲወድቁ ወደ ታች መውደቅ ሲገባቸው በተቃራኒው ግን ዛፎቹ የሚወድቁት ወደ ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ገዳሙ ውስጥ በላዔ ሥጋ ሥጋን የሚበላ ንስር ሳይቀር እንኳን የሞተ እንስሳም ቢያገኝ ሥጋ የሚባል ነገር አለመብላቱ አሁንም ድረስ በዐይን የሚታይ እውነታ ነው፡፡ ❤ እንዲሁም እዚህ ድንቅ ገዳም ውስጥ መርዛማ እባብም ነድፎ ሰው ሊገድል አይችልም፡፡ በእባቡ የተነደፈ ሰው እንኳን ቢኖር በጉንዳን የተነከሰ ያህል ይሰማዋል እንጂ ፈጽሞ አይሞትም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ ላይ "ለሚያምኑ እነዚህ ምልክቶች ይከተሉዋቸዋል፡- በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣ እባቡን ይይዛሉ፣ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳን ከቶ አይጎዳቸውም" ያለው አምላካዊ ቃል እዚህ ገዳም ውስጥ ባለንበት ዘመን በግልጽ በተግባር ይታያል፡፡ ማር 16፡16-18፣ ሐዋ 28፡3-6፡፡ እንዲሁም በዚህ ገዳም ውስጥ ከነበሩ ዛፎች ውስጥ አንዱ ዳዕሮ የተባለ ትልቅ ዛፍ አለ፡፡ ከዚህ ልዩ ዛፍ ተጠምቆ የሚዘጋጀው መጠጥ ከወይን የሚጥም ኅሊናን የሚመስጥና ሕመምን የሚፈውስ ነበር፡፡ ሌላው በገዳሙ ውስጥ በዐይን ከሚታዩትና ከሚያስደንቁት ተአምራቶች ውስጥ አንዱ በክረምት ወቅት ኃይለኛ ዝናብ ሲጥል በወረደ መብረቅ ምክንያት ገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ዐለት ተሰንጥቆ የሀገሪቱ ምስል ተስሎበት ተገኝቷል፡፡ እነዚህና ሌሎችም በርካታ ተአምራት እስከ አሁን ድረስ ጸንተው የሚገኙት የዚህ የፃዕዳ ዓምባ ቅድስት ሥላሴ ገዳም መሥራች በሆኑ በአቡነ ሠይፈ ሚካኤል የምሕረት ቃልኪዳን ነው፡፡ ❤ አቡነ ሠይፈ ሚካኤል ከአባታቸው ከዓምደ ሚካኤልና ከእናታቸው ከኅሪተ ማርያም ተወለዱ፡፡ ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩና በጾም ጸሎት የተወሰኑ የዋኆች ስለነበሩ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል፡፡ አባታቸው ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩላቸው ልጃቸውን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ወስደው ለመምህር ሰጧዋቸው፡፡ መምህሩም በደስታ ተቀብለው ቅዱሳት መጻሕፍትንና ያሬዳዊ ዜማን አስተማሯቸው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ አቡነ ሠይፈ ሚካኤል "እኔን ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ" የሚለውን ጌታችንን ቃል ለመፈጸም ዓለምን ከነምኞቷ ንቀው ትተው መስቀሉን ተሸክመው ጌታችን ተከተሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ዋሻዎችና ገዳማት እየሄዱ በአድያቦ ቤተ ቂርቆስ የሚባል ገዳም ደርሰው ከአቡነ ኖላዊነኄር ግብረ ምንኵስና እየተማሩ በገዳሙ ውስጥ የነበሩ መነኰሳት እስከሚደነቁ ድረስ በጽኑ ትጋትና በብዙ ትሩፋት በተጋድሎ አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ከጽኑ ተጋድሏቸው የተነሣ ሰውነታቸው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት አቡነ ዕንቆ ብርሃን ልብሰ ምንኵስናና አስኬማ መላእክት አለበሷቸው፡፡ እንዲህ ባለ ጽኑ ገድል በኣድያቦ ከመንፈስ አባታቸው ከአባ ዕንቆ ብርሃን ብዙ ዓመታትን ቆይተው በኋላ ወደ ዋልድባ ሄዱ፡፡ ዋልድባ ከገቡም በኋላ እዛ ከነበሩ ቅዱሳን ተባርከው ጽኑ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡ ❤ ከዚያም በዋልድባ ቅዱሳን ፈቃድ ወደ ወገሪቆ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሄደው አበምኔትና መምህር ሆነው አገለገሉ፡፡ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ወንጌልን እያስተማሩና ሕሙማን እየፈወሱ እስከ ጋሽ ባርካ ደብረ ሳላ የሚባል ቦታ ዞሩ፡፡ ይሄን አገልግሎታቸው ከፈጸሙ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እየመራ ማረፍያ ቤታቸው ወደሆነችው ፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም በደብረ ከባቦ አደረሳቸው፡፡ በዚያም በጾምና በጸሎት ተጠምደው እግዚአብሔርን አገለገሉ፡፡ሲጸልዩም እስከ ሰማይ ድረስ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ ይታያቸው ነበር፡፡ ❤ አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ አጋንንት በእባብና በንብ እየተመሰሉ ይፈታተኗቸው ነበር ነገር ግን አባታችን በጾምና በጸሎት ድል ይነሷቸው ነበር፡፡ በደብረ ከባቦ ቤተ ክርስትያን አንጸው ማኅበር አቋቁመው ለ9 ዓመት ከ6 ወር አገልግሎታቸውን እየፈጸሙና መከራ እየተቀበሉ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን በሰርክ ጸሎት እየጸለዩ ሳለ መልአክ መጥቶ "…ወደ ገዳሙ አስገባሃለሁና ተከተለኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም ከኋላው እየተከተሉ መልአኩ ወደ ዛሬይቱ ወንዶች ብቻ ወደሚገቡባት ገዳም አስገባቸው፡፡ ያቺን ለማየትም ጭምር የምታስፈራዋን መንገድ አባታችን "ጸናፌ ፅልመት"ብለው ሰየሟት፡፡ ከገቡም በኋላ በገዳሙ ውስጥ ቤተ ክርቲያን አንጸው ቤተ ማኅበር አቋቋሙ። ❤ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ርኲሳን መናፍስትን ከሕሙማን ያወጡ ስለነበር እነዚያ አጋንንትም "እዚህ እንድትኖር አንፈቅድልህም" እያሉ በገሃድ ለሞት እስከሚደርሱ ድረስ ዐይናቸውን አፈሰሱባቸው ሆኖም ግን መልአከ እግዚአብሔር ዳስሶ ዐይናቸውን መልሶ አበራላቸው፡፡ እንዲሁም አጋንንቶቹ በማደርያ ቤታቸው እሳት እያቀጣጠሉ በላያቸውም ትላልቅ ድንጋዮችን እየወረወሩ ከበፊቱ በእጅጉ ይፈታተኗቸው ነበር፡፡ እነዚያ የተወረወሩባቸው ድንጋዮች ግን አቡነ ሰይፈ ሚካኤል ይጸሉዩበት በነበረ ቦታ በደቡብ አቅጣጫ ተተክለው ቀርተዋል፡፡ ድንጋዮቹ እስከ አሁን ድረስ አሉ፡፡

አዘክሪ ድንግል.mp31.49 MB

ዘሐምስ ዓመት ወዘራብዕ ሰንበት @EOTCW

ዘሐምስ ዓመት @EOTCW

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ማህሌተ ጽጌ ዘራብዕ ሳምንት ☘☘☘☘☘☘☘☘☘ ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ (፪) እመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡ @EOTCW @EOTCW ✴️ነግስ፦ ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም። @EOTCW 🌱ዚቅ ሃሌ ሉያ ይኬልልዋ መላእክት በውስጠ ውሳጤ መንጦላእት ለቅድስት ማርያም ነቢያት ወሐዋርያት ወሰማእትኒ ያሰምኩ ባቲ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ወማህደሩ ለልዑል @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ ናሁ ጸገየ ወወሀበ መአዛ፤ ተአምርኪ ናርዶስ ለቤተክርስቲያን ዘይሔውዛ፤እንዘ ታረውጽኒ ሊተ ማርያም በፍኖተ ሎዛ፤ አጕይዪኒ ከመ ወይጠል ወከመ ኃየል ወሬዛ፤እምገጸ ኃጢአት እኅተ አርዌ ዘይቀትል ሕምዛ @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ናሁ ጸገየ ወወሀበ መአዛ  ናሁ ጸገየ/2/ ተአምርኪ ናርዶስ ለቤተክርስቲያን ዘይሔውዛ ለቤተክርስቲያን/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ ነፍሳተ ጻድቃን አውያን አመ ይሁቡ መአዛ ለዘምግባረ ጽድቅ አልብነ ይኩነነ ቤዛ ንግደትኪ ማርያም እስከ ደብረ ቊስቋም እምሎዛ @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ ሰመዩኪ ነቢያት እለ ርእዩ ኅቡአት፤ገነተ ጽጌ ዕፁተ ወኆኅተ ምስራቅ ኅትመተ፤ እግዚአብሔር ወሀበ ለቤተ ዳዊት ትንቢተ፤ከመ ትጸንሲ ድንግል ወትወልዲ ሕይወተ፤ ኢሳይያስኒ ነገረ ክሡተ @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ነቢያት ሰመዩኪ እለ ርእዩ ኅቡአት ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ/2/ ገነተ ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወኆኅተ ምስራቅ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ መሰንቆሁ ለዳዊት ወአክሊሉ ለሰሎሞን ገነት ዕፁት አዘቅተ ኅትምት መሶበ ጽንስ ምስለ ድንግልና ዘኢሳይያስ @EOTCW @EOTCW 🔹🌱ዓዲ ዚቅ፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ  ገነት ዕፁት ገነት ዕፁት አዘቅት ሕትምት፤ተሰውጠ ዲቤሃ ምዑዝ ዕፍረት @EOTCW @EOTCW ❣❣ማህሌተ ጽጌ፦ ፄነወኒ ተአምርኪ ሶበ ይነፍሑ ነፋሳት፤ ከመ ጼና ገነት ዘይፄኑ እምርኁቅ ፍኖት፤ መዓዛ አፈዋት ማርያም ወጽጌ መንግሥት ቡርክት፤  ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት፤ጽጌ ጽጌ ጽጌ አሮን ዘክህነት @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት/2/ መዓዛ አፈዋት ማርያም መዓዛ አፈዋት ወጽጌ መንግሥት ቡርክት/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ ሠርፀ መንግስት ዘእምሥርወ ዕሤይ ወጽጌ ንጽሕት ዘእምጕንደ ዳዊት፤ወብኪ ይትሜዓዙ ኲሎሙ ቅዱሳን @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል  ከማኪ ርኅሩኅ ፡፡  @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ/2/ ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኤልያስ ወኤልሳዕ ነቢያተ እስራኤል፤ወምስለ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋዓ ልቡና ዘአስተዮ ዑርኤል @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ ክበበ ጌራ ወርቅ  ጽሩይ  እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ  ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ  ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ  ታሰግዲ  ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ/2/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ ለጊዮርጊስ  መንግሥቱ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ፦ በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት @EOTCWW @EOTCWW ✨ሰቆቃወ ድንግል ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ። @EOTCW ❣❣ወረብ ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/2/ ማርያም ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ፤ወለመላትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ። @EOTCW @EOTCW ❄️መዝሙር በ6፦ በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት፤ ቆመ በረከት ናሁ ጸገዩ ጽጌያት፤ናርዶስ ፈረየ በውስተ ገነት፤ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ ምስለ ዕንጎታት ማ፦ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ነአኩቶ ለዘፀግወነ ሠናይቶ። https://t.me/Eotcw   # Join & share #

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 22:15-22፡"ወፈነዉ ኅቤሁ እምፈሪሳውያን" - "ስለዚህ፥ፈሪሳውያን፡ሄዱና፥እንዴት፡አድርገው፡በነገር፡እንዲያጠምዱት፡ተማከሩ። ደቀ፡መዛሙርታቸውንም፡ከሄሮድስ፡ወገን፡ጋራ፡ላኩበት፥እነርሱም፦መምህር፡ሆይ፥እውነተኛ፡እንደ፡ሆንህ፡በእውነትም፡የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡እንድታስተምር፡እናውቃለን፥ለማንምም፡አታደላም፥የሰውን፡ፊት፡አትመለከትምና፤ እንግዲህ፡ምን፡ይመስልኻል፧ንገረን፡ለቄሳር፡ግብር፡መስጠት፡ተፈቅዷልን፡ወይስ፡አልተፈቀደም፧አሉት። ኢየሱስም፡ክፋታቸውን፡ዐውቆ፦እናንተ፡ግብዞች፥ስለ፡ምን፡ትፈትኑኛላችሁ? የግብሩን፡ብር፡አሳዩኝ፡አለ።እነርሱም፡ዲናር፡አመጡለት። እርሱም፦ይህች፡መልክ፡ጽሕፈቲቱስ፡የማን፡ናት?አላቸው። የቄሳር፡ነው፡አሉት። በዚያን፡ጊዜ፦እንኪያስ፡የቄሳርን፡ለቄሳር፡የእግዚአብሔርንም፡ለእግዚአብሔር፡ አስረክቡ፡አላቸው። ይህንም፡ሰምተው፡ተደነቁ፥ትተውትም፡ኼዱ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.28 KB

18/2/2015 ዓ.ም (፲፰/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወይረውዩ እምጠለ ቤትከ። ወትሠቅዮሙ እምፈለገ ትፍሥሕትከ። እስመ እምኀቤከ ነቅዐ ሕይወት። መዝ 35÷8 🕯 ትርጉም ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ። ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ። የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማር. 12:13-19፡"ወፈነዉ ኅቤሁ እምፈሪሳውያን" - "በንግግርም ሊያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑትን ወደ እርሱ ላኩ። መጥተውም፦ መምህር ሆይ፥ የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን፤ ለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? እንስጥን ወይስ አንስጥ? አሉት። እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆ፦ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ አላቸው። እነርሱም አመጡለት። ይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው፤ እነርሱም፦ የቄሣር ናት አሉት። ኢየሱስም መልሶ፦ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው። በእርሱም ተደነቁ። ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው ጠየቁት እንዲህም አሉት፦ መምህር ሆይ፥ ሙሴ፦ የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.45 KB

18/2/2015 ዓ.ም (፲፰/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ዘአመከሩኒ አበዊክሙ። ፈተኑኒ ወርእዩ ምግባርየ፡፡ አርብዓ ዓመተ ተቆጣዕከዋ ለይእቲ ትውልድ። መዝ. 94፥9 🕯 ትርጉም የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ። ፈተኑኝ ሥራዬንም አዩ። ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለቴዎፍሎስ ቀዋሚ ለቤተ ክርስቲያን ዘሰመየቶ ማርያም ፈረሳዊ ዘይጸብእ በእንተ ክርስቲያን"። ትርጉም፦ ስለክርስቲያን የሚዋጋ (አርበኛ) ጋላቢ (ፈረሰኛ) ብላ ማርያም የሰየመችው ለቤተ ክርስቲያን የሚከራከር ለኾነ ለቴዎፍሎስ ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ "ሰላም ለሮማኖስ ሰማዕተ ክርስቶስ፤ ኪያሁ በዴግኖ ዘአውቀዩ ልሳኖ"። ትርጉም፦ ርሱን በመከተሉ ምላሱን የቈረጡት ለኾነ የክርስቶስ ሰማዕት ለሮማኖስ ሰላምታ ይገባል"። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው "እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ እውነት ነገርን ብታውቅ ለእግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ ይገባ እንደሆነ ወይም ለአማልክት እንዲነግረን ሕፃን ልጅ እንዲአመጡ እዘዝ" መኰንኑም ታናሽ ሕፃንን እንዲአመጡ አዘዘ መኰንኑም ሕፃኑን "ስግደት ለማን እንዲገባ ዕውነቱን ንገረን" አለው። ሕፃኑም "ልብ የሌለህ ደንቆሮ መኰንን በአንዲት ቃል ዓለሙን ሁሉ ለፈጠረ ለሕያው እግዚአብሔር ስግደትና አምልኮ እንዲገባ አታውቅምን" አለው። ❤ መኰንኑም ሕፃኑን ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ የሕፃኑም እናት ልታየው መጣች ሕፃኑም እናቱን "ተጠምቻለሁና ውኃ አጠጭኝ" አላት። እናቱም "ልጄ ሆይ ከዚህ ውኃ የለም ነገር ግን ወደ ሕይወት ውኃ ሒድ" አለችው። ❤ በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ። ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ። ወታደሩንም ጠርቶ "ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው" አለው ወታደሩም "የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ" አለው አምጥተውለትም አይቶ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን ፈጽሞ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመስተጋድል በመኰስ ቅዱስ ሮማኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለሮማኖስ ሰማዕተ ኢየሱስ ዋሕድ። ምቱረ ልሳን በመጥባሕት ወሕኑቀ ካሣድ በእድ። ስምዐ ዚአሁ አግሀደ ንኡስ ወልድ። እንተ ነበበ ወይቤ እምነ አምልኮ ለባዕድ ለእግዚአብሔር ይደሉ ወይትዕ ሰጊድ"። ትርጉም፦ አንገቱ በእጅ የታነቀና ምላሱን በሰይፍ የተቈረጠ ተቀዳሚ ተከታይ ለሌለው ለኢየሱስ ምስክር ለኾነ ሮማኖስ ሰላምታ ይገባል፤ ባዕድን ከማምለክ ይልቅ ለእግዚአብሔር መስገድ የሚቀናና የሚገባ ነው ብሎ የተናገረ ታናሽ ልጅ የርሱን ሰማዕትነት ገለጠ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 18። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወይረውዩ እምጠለ ቤትከ። ወትሠቅዮሙ እምፈለገ ትፍሥሕትከ። እስመ እምኀቤየ ነቅዐ ሕይወት"። መዝ 35፥8-9 የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥7-12፣ 1ኛ ጴጥ 1፥6-10 እና የሐዋ ሥራ 20፥30-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 22፥15-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ቴዎፍሎስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክድርያ ሃያ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ ለታላቁ አባት ለአቡነ ቴዎፍሎስና ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፋ ለከበረ ለመነኰስ ሮማኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት ዮሐንስ፣ ከአድራኒ፣ ከአርቴማዎስ፣ ከአርስጦስ ከሉዲኖስ፣ ከአስማኒትና ከሰባቱ ልጆቿ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የእስክንድርያ ሃያ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ቴዎፍሎስ፦ ይህም አባት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በነገሠ በስድስተኛ ዓመት ተሾመ በወንጌላዊ ማርቆስም ወንበር ሃያ ስምንት ዓመት ኖረ። ❤ በዘመኑ ብዙ መጻሕፍትን የተረጎመ ከእሳቸውም የወንጌላዊ ዮሐንስን ራእይና የሐዋርያ ጳውሎስን መልእክት የተረጎመ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ተነሣ ዳግመኛም ለደሴተ ቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ የሆነ ኤጲፋንዮስ ነበረ። ❤ በዘመኑም ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ከአንቀላፉ በኋላ ተነሡ። ይህም አባት የሐዋርያዊ ሊቀ ጳጳሳት አባት አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር ነው የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍትና ሥርዓቱን ሁሉ እየተማረ በእርሱ ዘንድ አደገ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስም በዐረፈ ጊዜ ይህ አባት በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ አዋቂና አስተዋይም ስለሆነ ስለ ፍቅር ስለ ርኅራኄ ከንሰሐ በፊት ሥጋውንና ደሙን ከመቀበል መጠበቅ ስለ ሚገባ ስለ ሙታን መነሣትና ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ ስለዘላለማዊ ሥቃይ ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ። ❤ ቅዱስ ቄርሎስም ለዚህ አባት ቴዎፍሎስ የእኅቱ ልጅ ነው እርሱም በበጎ አስተዳደግ አሳደገው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት አስተማረው።ከዚያም በኋላ ወደ አባ ሰራብዮን ላከው አባ ሰራብዮንም መንፈሳዊ ተግባርን ሁሉ አስተማረው። ❤ በአትናቴዎስም ዘመን አስቀድሞ እንዲህ ሆነ "በጎ ዘመን ባገኝ ይህን ኮረብታ ባስጠረግሁት ነበር። ለከበሩ ለመጥምቁ ዮሐንስና ለነቢይ ኤልሳዕም ቤተ ክርስቲያን በሠራሁም ነበር" ሲል ይህ አባት ቴዎፍሎስ አባ አትናቴዎስን ይሰማው ነበር። በሹመቱ ወራትም ይህን ነገር አስታውሶ የሚያዝንና ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን የሚጸልይ ሆነ። ❤ በዚያ ወራትም ባሏ ብዙ ገንዘብ ትቶላት የሞተ አንዲት ባለጸጋ ሴት ከሮሜ አገር መጣች ሁለት ልጆቿም ከእርሷ ጋር አሉ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስንም ሲያዝን አየችውና "ክብር አባት ሆይ ምን ያሳዝንሐል" አለችው። እርሱም "ብዙ ወርቅ በዚህ ኮረብታ ውስጥ እያለ ድኆች ይራባሉና" አላት እርሷም "አንተ ስለ እኔ ጸልይ እኔም አስጠርገዋለሁ" አለችው። ❤ ይህንንም ብላ ያን ኮረብታ አስጠረገችው በውስጡም በደንጊያ ሠሌዳ እየአንዳንዱ የተከደኑ ሦስት ሣጥኖች ተገለጡ። በላያቸው ቴዳ ቴዳ ቴዳ የሚል ተጽፎባቸዋል አባ ቴዎፍሎስም በአየው ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ምሥጢራቸውን አውቆ "ቴዳ ማለት የጌታ ስም ነው ይህም ለድኆች ይገባል" አለ "ሁለተኛውም ቴዳ የንጉሥ ቴዎዶስዮስ ነው ሦስተኛውም ቴዳ ቴዎፍሎስ ማለት ነው። የእኔ ገንዘብ ስለሆነ በዚህም አብያተ ክርስቲያናትን እሠራለሁ" አለ። እሊህም ሣጥኖች በመቄዶንያዊው ፊልጶስ ልጅ በንጉሥ እስክንድር ዘመን እንደ ተቀበሩ የዘመን ቊጥር ተገኘ እርሱም ሰባት መቶ ዘመናት ነው። ❤ ከዚህም በኋላ ያን የወርቅ ሣጥን ለንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላከለት ስለዚያም የወርቅ መዝገብ አስረድቶ ቦታውን መጥቶ እንዲያይ አሳሰበው እርሱም በመርከብ ተጭኖ ወደ እስክንድርያ አገር መጥቶ ሁሉንም አየ የዚያንም ወርቅ እኵሌታ መለሰለት አባ ቴዎፍሎስም ብዙዎች አብያተ ክርስቲያንን ሠራ። አስቀድሞም በቅዱሳን በመጥምቁ ዮሐንስና በነቢይ ኤልሳዕ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራ ሥጋቸውንም ከእስራኤል አገር አፍልሶ አምጥቶ በውስጧ አኖረ እርሷም የታወቀች ናት ዴማስ በሚባል ቦታ ሁለተኛም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሀገሩ ምሥራቅ በኩል ሠራ ከዚህም በኋላ በሊቀ መላእክት ሩፋኤል ስም በደሴት ውስጥ ሠራ ሌሎችንም ብዙዎች አብያተ ክርስቲያን አሳነፀ። ❤ ንጉሡም አብያተ ክርስቲያናትን ለመሥራት ያለውን የሊቀ ጳጳሳቱን ፍቅር አይቶ በግብጽ አገር ያሉትን የጣዖታት ቤቶችን ሁሉንም ሰጠው እርሱም ተቀብሎ አፈረሳቸውና በቦታቸው አብያተ ክርስተከያናትንና የእንግዶች ቤቶችን ሠራ ሁለተኛም ምድራቸውን ሁሉ ሰጠው። ይህም አባት ቴዎፍሎስ የክርስትና ጥምቀትን በሚያጠምቅ ጊዜ የብርሃን በትረ መስቀል በሚጠመቁት ላይ በመስቀል ምልክት ሲያማትብ ያይ ነበር። ❤ ይህ አባት ቴዎፍሎስና ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ልጆች በሆኑበት ጊዜ ሁለቱም በአንዲት ሌሊት አንዲት የሆነች ራእይን እነርሱ እንጨቶችን እንደሚለቅሙ አዩ። ከእነርሱም አንዱ ንጉሥ እንደሚሆን ሁለተኛውም ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ያቺን ራእይ ተረጎሟት እንዲሁም ሆነ። ይህም አባት ቴዎፍሎስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመባት በመጀመሪያዪቱ ዓመት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሃይማኖትን እናስተምራለን የሚሉ ሁሉ ሃይማኖታቸውን በመጽሐፍ ጽፈው ወደርሱ እንዲአቀርቡ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ። ❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡና ሊቀ ጳጳሳቱ ተነሥተው እነዚያን ጽሑፎች በመሠዊያው ላይ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ጌታም ወልድ በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው ብሎ ከሚታመን በቀር ከውስጣቸው በቀናች ሃይማኖት የጸና እንደ ሌለ ገለጠላቸው። በዚያንም ጊዜ እሊህን የመናፍቃን መጻሕፍትን እንዲአቃጥሏቸው እነዚያንም መናፍቃን ከሚገዛው አገር እንዲአሳድዷቸው ንጉሥ አዘዘ። ❤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም መጻሕፍትን ማንበብና መመርመር ያበዛ ነበር ስለዚህም የአውጋርዮስን መጻሕፍት አወገዘ ያወግዙ ዘንድም ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ወደዚህ አባት ወደ ቴዎፍሎስ ወደ ቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ ወደ ኤጲፋንዮስ ወደ ኤዺስቆጶሳት ሁሉ በየሀገሩ ላከ። ❤ ከዚህም በኋላ መልካም ጒዞውን በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥቅምት 18 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቴዎፍሎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ መነኰስ ቅዱስ ሮማኖስ፦ ይህም ቅዱስ ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን ሰማዕት የሆነ ነው። የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው። ❤ አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ አስቅልጵያኖስ "በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን?" አለው ቅዱሱም "የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን ክርስቶስ ነው" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ ጉንጮቹንም ሲሰነጣጥቁት ምንም አልተናገረምና መኰንኑ ትዕግሥቱን አደነቀ።