fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 21:1-7፡ "ወነጸረ ወርእየ አብዕልተ" - "ዓይኑንም አንሥቶ መባቸውን በመዝገብ የሚጥሉ ባለ ጠጎችን አየ። አንዲትም ድሀ መበለት ሁለት ሳንቲም በዚያ ስትጥል አየና፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህች ድሀ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብልጣ ጣለች፤ እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አለ። አንዳንዶቹም ስለ መቅደስ በመልካም ድንጋይና በተሰጠው ሽልማት እንዳጌጠ ሲነጋገሩ፦ ይህማ የምታዩት ሁሉ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል አለ። እነርሱም፦ መምህር ሆይ፥ እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.42 KB

17/2/2015 ዓ.ም (፲፯/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወጽንሐሐኒ ኢትሠምር። መስዋዕቱ ለእግዚአብሔር መንፈስ የዋህ። ልበ ትሑተ ወየዋህ ኢይሜንን እግዚአብሔር። መዝ 50÷16 🕯 ትርጉም የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሠኝህም። የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው። የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዮሐ. 1:35-41፡"ወበሳኒታ ካዕበ እንዘ ይቀውም" - "መልአኩም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላት፦መንፈስ፡ቅዱስ፡ባንቺ፡ላይ፡ይመጣል፥የልዑልም፡ኃይል፡ ይጸልልሻል፡ስለዚህ፡ደግሞ፡ከአንቺ፡የሚወለደው፡ቅዱስ፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ይባላል። እንሆም፡ዘመድሽ፡ኤልሳቤጥ፥እርሷ፡ደግሞ፡በእርጅናዋ፡ወንድ፡ልጅ፡ፀንሳለች፥ለርሷም፡መካን፡ትባል፡ ለነበረችው፡ይህ፡ስድስተኛ፡ወር፡ነው። ለእግዚአብሔር፡የሚሳነው፡ነገር፡የለምና። ማርያምም፦ እንሆኝ የጌታ፡ባሪያ፡እንደ፡ቃልህ፡ይኹንልኝ፡አለች።መልአኩም፡ከርሷ፡ኼደ። ማርያምም፡በዚያ፡ወራት፡ተነሥታ፡ወደ፡ተራራማው፡አገር፡ወደይሁዳ፡ከተማ፡ፈጥና፡ወጣች፥ ወደዘካርያስም፡ቤት፡ገብታ፡ኤልሳቤጥን፡ተሳለመቻት። ኤልሳቤጥም፡የማርያምን፡ሰላምታ፡በሰማች፡ጊዜ፡ፅንሱ፡በማሕፀኗ፡ውስጥ፡ዘለለ፤በኤልሳቤጥም፡መንፈስ፡ ቅዱስ፡ሞላባት፥" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.51 KB

17/2/2015 ዓ.ም (፲፯/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 አሐተ ሰእልክዎ ለእግዚአብሔር ወኪያሃ አኀሥሥ። ከመ እኅድር ቤቶ ለእግዚአብሔር። ወከመ ያርእየኒ ዘያሠምሮ ለእግዚአብሔር፡፡ መዝ. 27፥4 🕯 ትርጉም እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት። እርሷንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኘውንም አይ ዘንድ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለእስጢፋኖስ በኵረ ሰማዕታት ሊቀ ዲያቆናት ዐምደ ሃይማኖት ቅድስተ ሥላሴ ዘርእየ በዐይኑ ወልዱ ለአብ እንዘ ይነብር በየማኑ ተቃውሞቶ መዋግድ ዘስእኑ ነባቤ ጥበብ በልሳኑ ጽጉያተ ወጽዱላተ አቅማኀ ቃሉ ማዕከለ አይሁድ በውስተ ዐውድ ዘኮነ ሰማዕተ ወልድ"። ትርጉም፦ የሰማዕታት መዠመሪያ የዲያቆናት አለቃ፣ የሃይማኖት ምሰሶ፤ የተለየች ሦስትነትን በዐይኑ ያየ፤ የአብ የባሕርይ ልጁ በቀኙ ተቀምጦ ያየ፤ መከራከሩን ጨፋጮች አይሁድ ያልቻሉ በአንደበቱ ጥበብን የሚናገር የቃሉ ፍሬዎችም ብርሃናውያትና ያበቡለት፤ በአይሁድ መኻከል በዐደባባይ ውስጥ የወልድ ምስክርን ኾኖ ለተገኘ ለእስጢፋኖስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን ለሀገረ ቀምስ ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ ፊልያስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለነቢዩ ለቅዱስ ሳሙኤል እናት ለነቢይት ለቅድስት ሐና ለልደቷ መታሰቢያ በዓል፣ ለቅዱስ ባስልዮስ ወንድም ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለእስክንድር አገር ሠላሳ አንደኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ ዲዮስቆሮስ ካልዕ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በቆዳ ገመድ ከታሠሩ ከደጋጋጎች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የሀገረ ቀምስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ፊልያስ፦ ይህንንም ቅዱስ በመኰንኑ ቊልቊልያኖስ ዘመን ወደ ፍርድ አደባባይ አቀረቡት ቊልቊልያኖስም "ለአማልክት ሠዋ" አለው። ፊልያስም "እኔ ከብቻው እግዚአብሔር በቀር ለአማልክት አልሠዋም" አለ። ቊልቊልያኖስም "እግዚአብሔር ምን አይነት መሥዋዕት ይሻል" አለ ፊልያስም "ቅን ትሑት የሆነ ንጹሕ ልቡናን ዕውነተኛ ፍርድን ቁም ነገርን እንዲህ ያለ መሥዋዕትን እግዚአብሔር ይወዳል" አለው። ❤ ቊልቊልያኖስም "የምትጋደል ስለ ነፍስ ነው ወይስ ስለ ሥጋ" አለ ፊልያስም "ስለ ነፍስና ስለ ሥጋ ነው እነርሱ በአንድነት ይነሣሉና" አለ። ቊልቊልያኖስም "የምትወዳት ሚስት የምትወዳቸው ልጆች ወይም ወንድምና ዘመድ አለህን" አለው ፊልያስም "ከሁሉም የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለ። ቊልቊልያኖስም "እግዚአብሔር ከበጎ ሥራ የሠራው ምንድን ነው?" አለ ፊልያስም "እግዚአብሔር ያደረገልን ይህ ነው ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ ፈጠረልን። ዳግመኛም ከጠላታችን ከሰይጣን እጅ ያድነን ዘንድ ከሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሁኖ ተወለደ የሕይወት መንገድንም በዓለም ውስጥ ተመላልሶ አስተማረ መከራንም በሥጋው ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ በሦስተኛውም ቀን ተነሥቶ በአርባ ቀን ዐረገ ዳግመኛም ለፍርድ ይመጣል ይህን ሁሉ ስለ እኛ አደረገ"። ❤ ቊልቊልያኖስም "አምላክ ይሰቀላልን ይሞታልን?" አለ ፊልያስም "አዎን የዘላለም ሕይወትን ይሰጠን ዘንድ ስለ እኛ ፍቅር ሞተ" አለው። ቊልቊልያኖስም እንዲህ አለው "እኔ እንዳከበርኩህ ልጣላህም እንዳልፈለግሁ አላወቅህምን አንተ በወገን የከበርክ እንደሆንክ አውቃለሁና አሁንም ለአማልክት ሠዋ በክፉ አሟሟት እንዳትሞት" አለው። ፊልያስም "እኔን ደስ ማሰኘት ከወደድክ እንዲያሰቃዩኝና እንዲገድሉኝ እዘዝ" አለው በዚያንም ጊዜ በሰይፍ ራሱን እንዲቆርጡት አዘዘ። ❤ ሊገድሉት ሲወስዱትም ዘመዶቹና የሀገር ታላላቆች ወደርሱ መጡ ለመኰንኑም በመታዘዝ ለአማልክት እንዲሠዋ እጆቹን እግሮቹን እየሳሙ ለመኑት። እርሱ ግን "የጌታዬ ክርስቶስን መከራ መስቀልን ልሸከም እሔዳለሁና እናንተ አሳሳቾች ከእኔ ወግዱ" ብሎ ገሠጻቸው። ❤ ከሚገድሉበትም ሲደርስ ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ እጆቹን ዘርግቶ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ ሕዝቡን አደራ ወደ ጌታ አስጠበቀና ተሰናበተ ከዚህም በኋላ ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ፊሊያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ የባስልዮስ ወንድም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፦ ይህም ቅዱስ ጎርጎርዮስ እጅግ የተማረ አዋቂ ነበረ በደሴቶችም ላይ ኤጲስቆጶስነት ተሾመ እነሆ በዚህ ወር በዐሥራ አምስት ቀን የሆነውን ከገድሉ ጥቂት እንጽፋለን። ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ መሥዋዕቱን ለማክበር በሚቀድስ ጊዜ በመሠዊያው ላይ ሲወርድ መንፈስ ቅዱስን የሚያየው ሆነ ከዚህም በኋላ ኪሩብን አየው በደረቱም ውስጥ አቀፈው በመሠዊያውም ላይ ሳለ ወደ ዝምታና ተደሞ አደረሰው ሰዎችም ሁሉ ሥጋዊ እንቅልፍ የሚያንቀላፋ ይመስላቸው ነበር። ❤ በኤጲስቆጶስነት ሹመት ሠላሳ ሦስት ዘመናት በተፈጸሙለት ጊዜ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ ሊጠይቀው መጣ እርሱ ከተጋድሎ ብዛት የተነሣ በጽኑ ደዌ የሚታመም ሁኖ ነበርና በቅዱስ ባስልዮስ መምጣት ደስ አለው። ❤ ቅዱስ ጎርጎርዮስም እንደ ልማዱ ሊቀድስ ወደ መሠዊያው በወጣ ጊዜ የከበረች ድንግል እመቤታችን ማርያም ተገለጸችለትና "ዛሬ ወደኔ ትመጣለህ" አለችው የቊርባኑንም ቅዳሴ ሲጨርስ ሕዝቡ በቀናች ሃይማኖት ጸንተው እንዲኖሩ ይመክራቸውና ያስተምራቸው ዘንድ ወንድሙን ባስልዮስን ለመነው እርሱም እንደሚያንቀላፋ ሆነ በቀሰቀሱትም ጊዜ ሙቶ አገኙት ቅዱስ ባስልዮስም ሣጥን እንዲሠሩለት አዘዛቸው። ጸሎታትንም በመጸለይ መዝሙራትንም በመዘመር በማመስገንም እንደሚገባ ገንዞ በመቃብር ውስጥ አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጎርጎርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር 21 ስንክሳር። + + + ❤ የእስክንድርያ አገር ሠላሳ አንደኛ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮስቆሮስ ካልዕ፦ ይህም አባት በዘመኑ ካሉ ትውልድ እርሱን የሚመስል ያልተገኘ በጠባዩ ቅን የዋህ በእውቀቱ አስተዋይ በበጎ ሥራው ፍጹም የሆነ ነው። ❤ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ መልእክትን ጽፎ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጰሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ላካት። እርሱም ልዩ ሦስት የሆኑ ሥላሴ በመለኮት አንድ እንደሆኑ እየገለጠና እያሳሰበ ነው። ስለ ወልደ እግዚአብሔርም ሰው መሆን እርሱ ፍጹም ሥጋን ነባቢትና ለባዊት ነፍስን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ነሣ በመለኮቱና በትስብእቱም አካል ያለው አንድ ልጅ እንደሆነ ከተዋሕዶውም በኋላ በሥራው ሁሉ የማይለያይ ጭማሪ ወይም ጉድለት የሌለው ነው። መልእክቱም ወደ ቅዱስ አባት ሳዊሮስ በደረሰች ጊዜ አነበባትና ፈጽሞ ደስ ተሰኘባት ለአንጾኪያም ሕዝብ አስተማረባት ሁሉም ደስ አለቸው። ❤ ከዚህም በኋላ አባ ሳዊሮስ ለአባ ዲዮስቆሮስ የመልእክቱን መልስ እንዲህ ብሎ ጻፈ። "በኒቅያ ከተማ ተሰብስበው ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ቅዱሳን አባቶቻችን በቀናች ሃይማኖት አጽንተው የሠሩዋትን ቤተ ክርስቲያኑን እንድትጠብቅ ለዚች ለከበረች አገልግሎት የመረጠህ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። ዳግመኛም በዚሁ እንዲጸና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ እንዳይል አስገነዘበው ደግሞም በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን ሁል ጊዜ አስተምራቸው" አለው። ❤ የአባ ሳዊሮስም መልእክት ወደ አባ ዲዮስቆሮስ በደረሰች ጊዜ ደስ ተሰኘባት በሁሉ ቦታም እንዲአስተምሩባት አዘዘ ይህም አባት ሕዝቡን ሁል ጊዜ የሚያስተምራቸው ሆነ። ሁል ጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸዋል ኤጲስቆጶሳቱንና ካህናቱንም መንጋዎቻቸውን ስለ መጠበቅ ያዛቸዋል መልካም አገልግሎቱንም አድርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዲዮስቆሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለልደተ ሐና እመ ሳሙኤል ክብር። ጊዜ ትጼሊ ለልባ በኢከናፍር። ሶበ አምሰላ ስክርተ ካህነ ምስጢር። ኢይጻእ እምአፋክሙ ዐቢይ ነገር። እስመ አምላክነ ትቤ ፈታሒ ማእመር"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 17። የቅዱስ ሐና ታሪክ ጥቅምት 6 ቀን ላይ ያንብቡ።

photo content

photo content

photo content

❤ የእለእስክንድሮስም ሚስት በመርከብ ስትጓዝ ጣዕም ያለው የመላእክትን ዝማሬ ሰማች፡፡ ልታየውም በተነሣች ጊዜ ሣጥኑ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት መሆኑን ዐወቀቸ፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም ለመመለስ አልተቻላትም ይልቁንም ይህ እንዲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ዐውቃ ለዚህ ክብር ስላበቃት አመሰገነች፡፡ ቊስጥንጥንያም እንደደረሰች ለሊቀ ጳጳሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ ይዛ እንደመጣች ላከችበት፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ሁሉ በታላቅ ደስታ ወጥተው በክብር ተቀበሏት፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ሥጋውን በበቅሎ ጭነው ሲጓዙ ቊስጣንጢኖስ ከሚባል ቦታ ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የያዘችው በቅሎ አልንቀሳቀስ አለች፡፡ እግዚአብሔር የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው በዚህ ቦታ እንዲኖር የፈቀደ መሆኑን ዐወቁ፡፡ ሥጋውን የተጫነው በቅሎም በሰው አንደበት "የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ ይገባል" ብሎ ተናገረ፡፡ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉ እጅግ አደነቁ፡፡ የበለዓምን አህያ ያናገረ አምላክ አሁንም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከመችውን በቅሎ እንዳናገራት ዐውቀው ደስ አላቸው፡፡የሀገሪቱም ንጉሥ በቦታው ላይ ውብ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ በክብር አኖሩ፡፡ ከሥጋውም ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ከቅዱስ እስጢፋኖስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከቱ ያሳትፈን በጸሎቱ ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱስ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደና ከገድላት አንደበት። + + + ❤ "ሰላም ለእስጢፋኖስ እንተ ነጸረ በዐይኑ። እንዘ ወልድ ይነብር ለአብ ውስተ የማኑ። ከመ ኖትያዊ ጠቢብ ኃዳፌ ሐመር በኪኑ። ባሕረ መጻሕፍት አመ ጸበተት ልሳኑ። ተቃውሞቶ መዋግድ ስእኑ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 17። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አሐተ ሰአልክዎ ለእግዚአብሔር ወኪያሃ አኀሥሥ። ከመ እኅድር ቤቶ ለእግዚአብሔር በኵሉ መዋዕለ ሕይወትየ። ወከመ ያርእየኒ ዘያሠምሮ ለእግዚአብሔር"። መዝ 26፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥35-41። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወጽንሐሐኒ ኢትሠምር። መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር መንፈስ የዋህ። ልበ ትሑተ ወየዋሃ ኢይሜንን እግዚአብሔር"። መዝ 50፥16-17 ወይም መዝ 50፥10። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 1፥3-15፣ 1ኛ 5፥2-5 እና የሐዋ ሥራ 7፥54-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥1-7። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ እስጢፋስ የሲመት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ ቅዱሱም በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ከጌታችን የተማረውን "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው" እያለ ስለ ገዳዮቹ ምሕረትን ይለምን ነበር፡፡ ሰማይም ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይኸውም የቀድሞው ሳውል ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት የገዳዮቹን ልብስ ይጠብቅና ድንጋይ ያቀብል ነበር፡፡ "የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ" ብሎ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ መስክሯል፡፡ ሐዋ 22፥20፡፡ ❤ የቅዱስ እስጢፋኖስ መምህር የነበረው ምሑረ ኦሪቱ ገማልያልና ልጁ አቢብ በእስጢፋኖስ ትምህርትና የሞቱ ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት አይተው ከይሁዲነት ተመልሰው በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- "እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ የነፃ አውጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም፡፡ በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ፡፡ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና "ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና" የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ፡፡ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት"፡፡ የሐዋ ሥራ 6፥8-15፡፡ ❤ የአይሁድ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ ያቀረቡት የክሳቸው ምክንያት ጌታችንን ከከሰሱት ክስ ጋር በሁለት ነጥቦች ይመሳሰላል፡፡ የመጀመሪያው ክሳቸው "የሙሴን ሕግ ሽሯል" የሚል ነው፡፡ "የሙሴን ሕግ በመሻር ኦሪት አትጠቅምም አትመግብም አታድንም፤ ሐዲስ ኪዳን (ወንጌል) ግን ትመግባለች ታድናለች" ብሏል ብለው ከሰሱት፡፡ የሐዋ ሥራ 6፥13፡፡ ሁለተኛው ክሳቸው "እግዚአብሔርንም ይሰድባል" የሚል ነው፡፡ የሐዋ ሥራ 7፥50፡፡ አይሁድም የቅዱስ እስጢፋኖስን የወንጌል ቃል ንግግሮች በእግዚአብሔር ላይ እንደተሰነዘሩ ስድቦች በመቁጠር ነበር የወነጀሉት፡፡ የኦሪት የካህናት አለቃውም ቅዱስ እስጢፋኖስ ለተከሰሰበት መልስ ይሰጥ ዘንድ ሲጠይቀው እርሱ ግን ለተከሰሰበት መልስ ከመስጠት ይልቅ ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፍ በዝርዝር በሚገባ ተረከላቸው። ❤ ቅዱስ እስጢፋኖስም እንዲህ አላቸው፡- "ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም፡፡ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት፡፡መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡፡ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፣ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፡፡ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ፡፡ እስጢፋኖስም "ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል" ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር፡፡ ተንበርክኮም "ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው" ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ይህንም ብሎ አንቀላፋ፡፡ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡ የሐዋ ሥራ 7፥52-60፡፡ ❤ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለንጽሕናው ስለድንግልናው፣ ስለሰማዕትነቱ ስለተጋድሎው እና ስለስብከቱ ስለተአምራቱ ሦስቱ አክሊላት ተቀዳጅቷል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ አምላኩን ክርስቶስን በብዙ ነገር መስሏል፡፡ በመጨረሻዋ የመሞቻው ሰዓት ላይ እንኳን ሆኖ አምላኩን አብነት አድርጎ ተገኝቷል፡፡ ጌታችን "ነፍሴን ተቀበላት" እንዳለ ሁሉ ቅዱስ እስጢፋኖስም "አቤቱ ጌታ ሆይ ነፍሴን ተቀበላት" ብሏል፡፡ ጌታችን "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" እንዳለ እስጢፋኖስም "ጌታ ሆይ ይህን ኃጥአት አትቁጠርባቸው የሚያደርጉትን አያውቁምና" በማለት ለገዳዩቹ ምሕረትን ለምኗል፡፡ በጌታችን ጸሎት እነ ፊያታዊ ዘየማንን ጨምሮ እልፍ ነፍሳት ወደ ንስሐ ተመልሰው ገነት መንግስተ ሰማያትን እንደወረሱ ሁሉ በቅዱስ እስጢፋኖስም ጸሎት ብዙ ነፍሳት ድነው ገነት መንግስተ ሰማያትን ወርሰዋል፡፡ ❤ የጌታችን ቅዱስ መስቀል እልፍ ሙታንን ያስነሣ ድውያንን ይፈውስ እንደነበር ሁሉ የቅዱስ እስጢፋኖስም ዐፅም ሙታንን ያስነሣ ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውበታል፡፡የቅዱስ እስጢፋኖስ ልደቱና ዕረፍቱ ጥር 1 ቀን ነው፡፡ መእመናንም ሥጋውን ወስደው በክብር ቀበሩት፡፡ ጥቅምት 17 የተሾመበት ነው፡፡ መስከረም 15 ቀን ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ ቅዱስ ዐፅሙ ሙትን ያስነሣ ድውይን ይፈውስ ነበርና አይሁድ በቅናት ተነሥተው እንደ ጌታችን ቅዱስ መስቀል የቅዱስ እስጢፋኖስን ዐፅም አርቀው በመቆፈር ቀብረው በላዩም ቆሻሻ በመጣል ለ300 ዓመታት ያህል ተቀብሮ ኖሮ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር እንደ ቅዱስ መስቀሉ ተቆፍሮ በመውጣት መስከረም 15 ቀን ቅዱስ ዐፅሙ ወጥቶ በክብር በስሙ በታነጸው ቤተ ክርስቲያን በክብር ተቀምጧል፡፡ ❤ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመት በላይ በሆነ ጊዜ ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሲነገሥና ሃይማኖትን በመላው ዓለም አቀና፡፡ ተዘግተው የነበሩ ገዳማትና አብያተ ክርስያናት ተከፈቱ፡፡ በዚህም ወቅት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው በሚገኝበት በኢየሩሳሌም አካባቢ ሉክያኖስ ለሚባል ሰው ቅዱስ እስጢፋኖስ በራእይ ተገለጠለትና "እኔ እስጢፋኖስ ነኝ፣ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሯል" በማለት ሥጋውን ያወጡ ዘንድ አዘዘው፡፡ ሉክያኖስም ለኢየሩሳሌሙ ኤጰስ ቆጶስ ሄዶ ነገረውና ወደ ቦታው ሄደው ሲቆፍሩ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነና ሳጥኑ ተገኘ፡፡ ከሳጥኑ እጅግ ደስ የሚል በዓዛ ወጣ፡፡ በዚያ ቦታም ቅዱሳን መላእክት ሲያመሰግኑ ተሰሙ፡፡ ኤጲስ ቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በክብር በታላቅ ዝማሬ ወስደው አስቀመጡት። ❤ ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፡- በኢየሩሳሌም የሚኖር የቁስጥንጥንያ ተወላጅ የሆነ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር፡፡ እርሱም ለቅዱስ እስጢፋኖስ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው በዚያ በክብር አኖሩት፡፡ ከ5 ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ ዐረፈና ሚስቱ በቅዱስ እስጢፋኖስ አስክሬን ጎን ቀበረችው፡፡ ከሌሎች ከ5 ዓመቶችም በኋላ ሚስቱ የባሏን አስክሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሄድ አስባ ወደ መቃብሩ ስትሄድ የባሏን አስክሬን የወሰደች መስሏት በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ድረስ ተሸከመችውና በመርከብ ተሳፍራ ወደ ቁስጥንጥንያ ሄደች።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን ለዲያቆናት አለቃ ለሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ ለቅዱስ እስጢፋኖስ ለተሾመበት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የዕለቱ መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ሊቃነ ካህናት ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን እለ ሎሙ ሕግ ወሎሙ ሥርዓት ብፁዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን ለከ የዓርጉ ስብሐት እግዚኣ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በስነ ጽጌያት ወሠራዕከ ሰንበት ለሰብእ ዕረፍተ ወብውህ ለከ ትኅድግ ኃጢአተ ረቢ ንብለከ ረቢ ሊቅ ነአምን ብከ። ትርጉም፦ ሕግና ሥርዓት ያላቸው የካህናት አለቆች የቤተ ክርስቲያን ሹማምንት፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስትና ጳጳሳት እስጢፋኖስ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ምስጋናን ያሳርጉልሃል፣ የሰንበት ጌታ ምድርን በአበቦች ውበት አስጌጥካት፣ ለሰው ዕረፍትን ሰንበትን ሠራኽ ኃጢአትን ትተውለት ዘንድ መምህር እንልሃለን፣ ሊቅ መምህር ሆይ እናምንብሃለን። + + + ❤ የዕለቱ እግ ነግ፦ "ሮድዎ ወሰሐብዎ በአሕባል አግብርት እኩያን ወአብጽሕዎ ኀበ ዐውደ ቅስት ወስዕኑ ተቃውሞቶ ለእስጢፋኖስ። ትርጉም፦ ገረመሙት በሐብል ሳቡት ክፉዎች ባርያዎች ወደ ሞት አደባባይ አደረሱት እስጢፋኖስን በጽኑ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ። + + + ❤ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፦ እስጢፋኖስ ማለት "መደብ" ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ "አክሊል" ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከነቢያትና ከጻድቃን ወገን ናቸው፡፡ በመጀመሪያ ሁለት ወንድ ልጆችን ወለዱ፡፡ አንዱ ይሁዳ ሲባል ሁለተኛውም ቅዱስ እስጢፋኖስ (አስተፓኖስ) ነው፡፡ ❤ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወለደው ጥር 1 ቀን በእስራኤል ሃገር ውስጥ ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለች ቦት ነው፡፡ የተወለደውም በስለት ነው፡፡ እርሱም ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡ በኋላም ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመሄድ ይላላካቸውና ያገለግላቸው ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ከተሾሙት ከ7ቱ ዲያቆናት አንዱ ሲሆን የዲያቆናት አለቃ እርሱ ነው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን በማስተማሩና ብዙዎችን ክርስቶስን ወደማመን ስለመለሳቸው ክፉዎች አይሁድ በጠላልትነት ተነስተውበት ጥር 1 ቀን በ34 ዓ.ም ከጌታችን ቀጥሎ ከምእመናን ወገን የመከራውን ገፈት ስለተቀበለ (በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ስላረፈ) "ቀዳሜ ሰማዕት" ተሰኘ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ "ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ" እየተባለ ይጠራል፡፡ ይኸውም የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት በሰባቱ ዲያቆናት ላይ አለቃ አድርገው በሾሙት ጊዜ የተሰጠው ስያሜ ነው። ❤ የመጀመሪያ ክርስቲያኖች የአማኞች ቊጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በሄደ ጊዜ የማኅበራዊው ኑሮ አስተዳደር ማለትም የምግብንና የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች (ገንዘብም ጭምሮ) በትክክልና በእኩልነት የማከፋፈሉ ሥራ በሐዋርያት ዘንድ አስቸጋሪ ሆኖ ተገኘ፡፡ እነርሱም ደግሞ ዋና ተግባር አድርገው በትጋት ለመያዝ የፈለጉት ማስተማርን ነበር፡፡ ስለዚህም አማኞችን ሁሉ ሰብስበው ከመካከላቸው በመልካም ጠባያቸው የተመሰገኑ በመንፈስ ቅዱስና በጥበብ የተሞሉ ሰባት ሰዎችን እንዲመርጡ አሳስቧቸው፡፡ አማኞችንም ነገሩ አስደስቷቸው ሰባት ሰዎችን መረጡ፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ እስጢፋኖስ (ዕረፍቱ ጥር 1)፣ ቅዱስ ጵሮኮሮስ (ሰኔ 8)፣ ቅዱስ ጢሞና (ሚያዝያ 16)፣ ቅዱስ ፊልጶስ (ጥቅምት 14)፣ ቅዱስ ጰርሜና (መስከረም 1)፣ ቅዱስ ኒቃሮና (3 ጊዜ ሞቶ የተነሣ)፣ ቅዱስ ኒቆላዎስ (ሚያዝያ 15) ናቸው፡፡ ሐዋ 6፡5፡፡ ❤ እነዚህንም ቅዱሳን በከበሩ ሐዋርያት ፊት ባቆሟአቸው ጊዜ ጸልየው እጃቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው፡፡ በከበሩ ሐዋርያት ጫንቃ ላይ ተጭኖ የነበረው ከባድ ሸክም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ደሀ አደጎች በመርዳት ችግሮቻቸውን አቃለሉላቸው፡፡በከበሩ ሐዋርያት ከተመረጡት ሰባቱ ዲያቆናት መካከል ሊቀ ዲያቆናት ተደረጎ የተመረጠው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ሌሎቹም ዲያቆናት እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ወንጌልን በማስተማርና የመጀመሪያ ክርስቲያኖች በማስተዳደር በጽናት ተጋድለዋል፡፡ እነዚህም ሰባቱ ዲያቆናት ከአባቶቻቸው ከከበሩ ሐዋርያት አይተው የእነርሱንም መንፈስ ተቀብለው ያልተማሩ አህዛብን ልቡናቸውን ለመስበርና የእግዚአብሔርን ኃይልነት ተረድተው እንዲገነዘቡ በማሰብ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡ ❤ ከእነርሱም ውስጥ በዋነኛነት ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ ፊት ያደረጋቸው ተአምራት እጅግ ድንቅ ናቸው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ መካከል ቆሞ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ አንድ አንደበቱ ዲዳ የሆነ ሰው አጠገቡ ቢመጣ በጆሮው የሕይወት እስትንፋስ እፍ ቢልበት መስማት የማይችለው መስማት ቻለ፡፡ በዚህም ጣኦት አምላኪው ናኦስ እና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመለሱ፡፡ ጣኦት አምላኪው ናኦስ በድርጊቱ በጣም ከመናደዱ የተነሣ በአጠገቡ የቆመውን በሬ ጠንቋዩ ናኦስ በጆሮው እፍ ብሎ ቢተነፍስበት በሬው በምትሃት ለሁለት ተሰንጥቆ በመሞቱ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተመለሱት በናኦስ ምትሃታዊ ድርጊት በመሳባቸው እንደገና ወደ ናኦስ ተመለሱ፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስም በዚህ ጊዜ የአህዛብ ልቡና ወላዋይ እንዳይሆንና እንዳይጠፉም በማሰብ ናኦስ እፍ ብሎ ለሁለት ሰንጥቆ የገደለውን በሬ መልሶ በሕይወት እንዲያስነሣው ናኦስን ጠየቀው፡፡ ነገር ግን ናኦስ ያንን ማድረግ አልቻለም፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ "ናኦስ ዳግመኛ ሕይወት ዘርቶ ማስነሣት ካልቻለ ነገሩ ሐሰተኛ ነው ማለት ነው፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ኃይልና ድንቅ ሥራ ይህን ለሁለት ተሰንጥቆ የሞተውን በሬ ዳግመኛ ሕይወት ዘርቶ እንዲነሣ አደርገዋለሁ" በማለት ወደ እግዚአብሔር ከጸለየ በኋላ በሬውን አስነሣው፡፡ ይህንንም ተአምር አድርጎ በማስተማር ልቦናቸው ወላውሎ ወደ ናኦስ የተመለሱትን አህዛብ ገንዘቡ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ኃይልነት እንዲያምኑ አድርጓል፡፡ ናኦስ በአልሸነፍ ባይነትና በአጋንንት ረዳትነት ራሱን ወደ ላይ እንዲንሣፈፍ አድርጎ በአየር ላይ ቢወጣ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ተአምር በማሳየት በትዕግስት ጠብቆ በአጋንንት ረዳትነት ወደ ላይ የተነሳውን ናኦስ በትምዕርተ መስቀል ቢያማትብበት ይዘውት የነበሩት አጋንንት ሁሉ ለቀውት ሲበተኑ ናኦስም ምድር ደርሶ ተንኮታኩቶ በመውደቁ በጣኦት አምላኪነት የነበሩ ሁሉ ዳግም ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመልሰዋል፡፡ ❤ የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በትምህርቱና በተአምራቱ ብዙዎችን ወደቀናች ሃይማኖት ስለመለሰ ክፉዎች አይሁድ ቀኑበትና የሐሰት ምስክር አዘጋጁበት፡፡ "በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል" ብለው በሐሰት ከሰሱትና በሸንጎአቸው አቆሙት፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ያለውን ሁሉንም እየጠቀሰ የሃይማኖትን ነገር አስተማራቸው፡፡ ነቢያትን ስለማሳደዳቸውና ስለመግደላቸው እየወቀሰ ሲናገራቸው በትምህርቱ ተናደው ጆሮአቸውን ይዘው በመጮህ በድንጋይ ወግረው ይገድሉት ዘንድ እየጎተቱ ከከተማው ውጭ አወጡት፡፡

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክድርያ አርባ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ያቃቱ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን መቊሮፍዮን፣ ከእብሎ፣ ከባሕታዊ ኢሳይያስ ረድእ ከጴጥሮስ፣ ከፋሩ ከድርቄ አገር ከሆኑ ከአርባ አምስት ጻድቃን፣ ከቃርቡ ከአናልዩ ከአባ ጳውሊ ከመስተጋድል ማርቆስ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የእስክንድርያ አርባ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳሳት አባ ያቃቱ፦ ከርሱ በፊት የነበረ አባ ብንያሚን በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም ብዙ ችግር ደርሶበታል ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል አንድ መለካዊ ሰው ነበረ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ወደ ዘይድ ሒዶ ብዙ እጅ መንሻ ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሁኖ ተሾመ። ❤ ይህንንም አባት አባ ያቃቱን ሊአስጨንቀው ጀመረ በየዓመቱ ግብር ሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከእርሱ እስከተቀበለ ድረስ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ ይህን አባት እንዲህ አሠቃየው። በዘመኑም የብዙዎች ቅዱሳን አባቶች አባት የሆነ የአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃዋ ተፈጸመ። ❤ በአንዲት ሌሊትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዚህ አባት ተገለጸለት ፍዩም በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ ሰው መነኰስ እንዳለ ነገረው። ሕዝብን በማስተማርና በመምከርም ይረዳው ዘንድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲአስመጣውም አዘዘው ሁለተኛም ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ገለጠለት። ❤ በዚያንም ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሥራውንም ሁሉ አስረከበው ይህንንም አባት ከብዙ ድካም የሚያሳርፈው ሆነ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ ከዚህም በኋላ ጥቅምት 16 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ያቃቲ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 16 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለክሙ መቊሮፍዮን ወእብሎ ብፁዓዊ። ወጴጥሮስ ረድኡ ለኢሳይያስ ባሕታዊ። ደናግል ዕደው እምነ ፍትወት ምድራዊ። ሀቡኒ እምቅብዕክሙ ፈትለ ማኅቶትየ አርዊ። አመ በውውዓ ሌሊተ ይመጽእ መርዓዊ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት16። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ኪያከ ተወከሉ አበዊነ። ተወከሉከኒ ወአድኀንኮሙ። ኀቤከ ጸርሑ ወድኅኑ"። መዝ 21፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 6፥13-19፣ 1ኛ ጴጥ 3፥10-18 እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥1-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ኢያሱና የአቡነ አሮን የዕረፍታቸው በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw