ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መጋቢት፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን ለእስክንድርያ አርባ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳሳት በተሾሙ ጊዜ ለሦስት ቀናት ስለ ቅድስናቸው እግዚአብሔር ዝናብን ላዘነበላቸው፤ በግብፅ አገር አሕዛብ በእሥራትና በስደት ብዙ ላሠቃዩአቸውና የኢትዮጵያው ንጉሥ ሦስት መቶ ሺህ ሠራዊት አዝምቶ ከዚህ ሥቃያቸው ታድጎ ነፃ ላወጣቸው ለከበሩ አባት ለአባ ሚካኤል ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አባ ሚካኤል፦ ይህም አባት በእስክንድርያ ከተሾሙ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ሰባተኛ ነው፡፡ በአስቄጥስ በአባ መቃርስ ገዳም መንኰሶ ኖረ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎድሮስ በዐረፈ ጊዜ በላዩ የትንቢት መንፈስ ያደረበት አንድ ጻድቅ ሰው እስከ ሚያስረዳቸው ድረስ ለዚች ሹመት ስለሚሻል ሲመክሩና ሲመረምሩ ብዙ ቀኖች ኖሩ።
❤ ከዚህም በኋላ ያ ሰው እኔ በአባ መቃርስ ገዳም በነበርኩ ጊዜ ስጸልይ "የሊቀ ጵጵስና ሹመት ለሚካኤል ይገባዋል ለዚች ሹመት የሚሻል እሱ ነውና የሚል ቃልን ከሰማይ ሰማሁ" አላቸው። ሁሉም ስለ ትሩፋቱ ተናገሩ ስለ እርሱም ተስማምተው ከገዳሙ ወደ እስክንድርያ ሊያመጡት ከምስር ገዥ ዘንድ ደብዳቤ አጽፈው ያዙ። ሊያመጡትም ሲሔዱ ስለ ገዳሙ አገልግሎት ከሽማግሌዎች መነኰሳት ጋራ ወደ ጋዛ ከተማ ሲመጣ በመንገድ አገኙት ይዘውም አሠሩት። ወስደውም በመስከረም17 ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ያቺም ዕለት በጌታ ደም የከበረ መስቀል በዓሉ የሚከበርባት ናት።
❤ ይህም የሆነው ከዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በኋላ የሐሚድ ልጅ እልሲድ በሚገዛበት ዘመን ነው። በሹመቱ ወራትም መርዋን አልጋዲን ነገሠ። የእስክንድርያም አገር ሰዎች ከጥቂት ካፊያ በቀር ብዙ ዝናብ ሳይዘንብላቸው ብዙ ዓመታት ኖሩ። በዚች እርሱ በተሾመባት ቀን በሁለተኛውም በሦስተኛውም ብዙ ዝናብ ዘንቦላቸው እጅግ ደስ አላቸው።
❤ በዚህም አባት ዘመን በክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራ ደረሰ ከምዕመናንም ብዙዎች ሸሹ የክብር ባለቤት ክርስቶስም የካዱት ሰዎች ቁጥራቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነ። ለዚህለመለካውያን ነገር ምክንያት የሆነውን ከእርሱ እግዚአብሔር እስከአጠፋው ድረስ ይህ አባት ስለዚህ በታላቅ ኀዘን ውስጥ ነበር።
❤ ዳግመኛም በዚህ አባት ዘመን ቆዝሞስ ሊቀ ጵጵስና ተሹሞ ሳለ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ክርስቶስ ተዋሕዶ ከዚህ አባት ከአባ ሚካኤል ጋራ ተከራክሮ ይህ አባት አባ ሚካኤል እንዳስረዳው አመነ። እንዲህም ብሎ በእጁ ጻፈ "የክብር ባለቤት ክርሰቶስ በተዋሕዶ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት ቄርሎስ እንደተናገረ የመለኮቱና የትስብእቱ አንድ ባሕርይ በመሆን ጸንቶ ይኖራል ሲል ኤጲስቆጶሳቱም እንዲሁ ከተዋሕዶ በኋላ ክርስቶስ የተለያዩ ሁለት ባሕርያት ሁለት ገጻት አሉት ይሉ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲሉ ጻፈ። ሐዋርያትም በሰበሰቧት በከበረች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት ጸንተው ሊኖሩ ተስማሙ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእስክንድርያ ሰዎች መለካዊ የሆነ ስሙ አንስጣስዮስ የሚባል ሰው በላያቸው ጥፋትን አመጣ እርሱ ኤጲስቆጶስነት እንዲሾሙት ሽቶ አልሾሙትምና። ስለዚህ ወደ እስላሞች ንጉሥ ሒዶ በአባ ሚካኤል ነገር ሠራበት ከዐመፀኞች የነገሥታትም ብዙ መከራ ደረሰበት ጽኑዕ የሆነ ሥቃይም አሠቃዩት ብዙ ግርፈትም ገርፈው ለረጂም ጊዜ በእግር ብረት አሠሩት። አንገቱንም በሰይፍ ሊቆርጡ ወደ መኰንኑ አቅርበውት ነበር ስለ መንጋዎቹም ጥበቃ እግዚአብሔር አዳነው።
❤ ዳግመኛም በመዋርዋን አልጋዲ ዘመነ መንግሥት የሙሴ ልጅ በሆነ በንጉሥ አገልጋይ አደባባይ ታላቅ ሥቃይ አሠቃዩት፡፡መኰንኑም ገንዘብ እንዲሰጠው ሽቶ ሊቀ ጳጳሳቱን አባ ሚካኤል አሠረው ሰዎች መጥተው ዋስ ሁነው አወጡት። ምጽዋትም ጠይቆ ለመኰንኑ ብዙ ገንዘብ አምጥቶ እንዲሰጠው ወደ ላይኛው ግብጽ ወሰዱት። ይህ አባትም ወደ ላይኛው ግብጽ በሔደ ጊዜ በዚያ ብዙ ተአምራትን አድርጎ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የካዱትን ምዕመናን ብዙዎቹን ወደቀናች ሃይማኖት መልሶ አስገባቸው።
❤ የኢትዮጵያ ንጉሥም ይህን አባት የእስላሞች መኳንንት እንዳሠቃዩት በሰማ ጊዜ ፍጹም ኀዘንንም አዘነ። መንፈሳዊ ቅናትንም ቀንቶ ወደ ግብጽ አገር ዘምቶ ከላይኛው ግብጽ ደረሰ። ከርሱ ጋርም መቶ ሺህ ፈረሰኞች አርበኞች፣ መቶ ሺህ በበቅሎ የተቀመጡ አሁንም በግመል የተቀመጡ መቶ ሺህ አርበኞች ነበሩ ብዙ አገሮችንም አጠፋ ብዙዎችንም ማረካቸው።
❤ የግብፁ ንጉሥም ይህ ሁሉ የሆነው ስለ ሊቀ ጳጳሳቱ ስለ አባ ሚካኤል እንደሆነ ዐውቆ ከእስራቱ ፈታው፡፡ ታላቅ ክብርንም አከበረው፡፡ የክርስቲያንን ወገኖች ሁሉ እጅግ አከባረቸው። ከዚህም በኋላ ለኢትዮጵያ ንጉሥ ደብዳቤ ጽፎ ይልክ ዘንድ ወደ አገሩም እንዲመለስ ያዝዘው ዘንድ የግብጽ ንጉሥ ይህን አባት አባ ሚካኤል ለመነው።
❤ ይህም አባት ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ እርሱንና መኳንንቱን መሳፍንቱንና ሠራዊቱን እየባረከና እየመረቀ ደብዳቤ ጽፎ ላከ። እንዲህም አለው "እንሆ በአንተ ምክንያት ከአሥራትና ከሥቃይ ሁሉ እግዚአብሔር አድኖናልና አሁን ወደ አገርህ በሰላም በፍቅር ተመለስ ስለ እኔና ስለ ክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ስለ ደከምክ መልካም ዋጋ እግዚአብሔር በመንግሥተ ሰማያት ይስጥህ"። የኢትዮጵያ ንጉሥም የዚህን አባት የሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልን ደብዳቤ በአነበበ ጊዜ ፈጥኖ ተነሥቶ ወደ አገሩ በሰላም በፍቅር አንድነት ተመለሰ።
❤ አባ ቆዝሞስና ወገኖቹም ከሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋር በተስማሙ ጊዜ አባ ቆዝሞስ በውዴታው ለምስር ኤጲስቆጶስ ሁኖ ተሹሞ ከዚህ አባት ከአባ ሚካኤል ሥልጣን በታች ሆነ።
❤ ይህም አባት መልካም ተጋድሎውን በፈጸመ ጊዜ ወደ ወደደው እግዚአብሔር መጋቢት16 ሔደ። የአባ ሚካኤል አማልጅነቱ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት16 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለሚካኤል እንተ ነበረ ገዳመ። እንዘ ይትጋደል ፍጹመ። ሊቀ ጳጳሳት ዝንቱ በዕለተ ተሠይመ። መልዕልተ ምድር ገብረ ሰላመ። ሰማይኒ ወሀበ ዝናመ"። ትርጉም፦ በገዳም ፍጹም ገድልን ሲጋደል ለነበረ ለአባ ሚካኤል ሰላምታ ይገባል፤ ሊቀ ጵጵስናን በተሾመበት በዚች ዕለት (ቀን) በምድር ላይ ሰላም ሆነ፤ ሰማይም ዝናብን ሰጠ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት16።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ዝርዎሙ ለአሕዛብ እለ ይፈቅዱ ቀተለ። ይምጽኡ ተናብልት እምግብፅ። ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር"። መዝ67፥30-31። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ14፥28-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መጋቢት ፲፭ (15) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረች ተጋዳይ ለመነኰሳዪት ሰይጣንን በትሕትና ድል ላደረገች ለቅድስት ሣራ ዘላዕላይ ግብጽ ለዕረፍት በዓልና ለቅድስት አስጠራጦኒቃ እጮኛዋ ለሆነ ለቅዱስ ሰለፍኮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ናህስ ከሚባል አገር ከሆኑ ከሰማዕቱ ከከበረ ከአባ ሕልያስ፣ ከሰፍንዮስና ከአዲስ ጊዮርጊስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅድስት ሣራ፦ ይቺም ቅድስት ከላይኛው ግብጽ ናት ወላጆቿም የክብር ባለቤት ክርስቶስን የሚያመልኩ ክርስቲያን ናቸው። እጅግም ባለጸጎች ነበሩ። ነገር ግን ከእርስዋ በቀር ልጆች የሏቸውም በመልካም አስተዳደግም አሳደጓት ለክርስቲያን የሚገባ ትምህርትን ሁሉ አስተማሩዋት ደግሞም ጽሕፈትን አስተማራት ሁሉጊዜም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ታነባለች ይልቁንም የመነኰሳትን ዜና ታነብ ነበር። መጻሕፍትንም አዘወትራ ስለምታነብ የምንኵስና ልብስ ለመልበስ ፈለገች በላይኛው ግብጽ ከሚገኙ ገዳማትም ወደ አንዱ ገዳም ሒዳ ገባች ብዙ ዘመናትም ደናግልን እያገለገለች ኖረች።
❤ ከዚህም በኋላ የምንኵስና ልብስን ለበሰች ሰይጣንን ድል እስከ አደረገችው ድረስ። ሰይጣን የሚያመጣውን ሥጋዊ ፍትወት እየታገለች ዐሥራ ሦስት ዓመት ኖረች። ንጽሕናን ከመውደዷ ጽናት በተሸነፈ ጊዜ በትዕቢት ሊጥላት ወዶ በቤት መዛነቢያ ልትጸልይ ቁማ ሳለች ተገልጦ "ሣራ ሆይ ሰይጣንን ድል አደረግሽዋልና ደስ ይበልሽ" አላት እርሷም መልሳ "እኔ ደካማ ሴት ነኝ ከክብር ባለቤት ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ድል አድርጌ ላበረው አልችልም" አለችው።
❤ ይህችም ቅድስት አብረዋት ላሉ ደናግል ጥቅም ያላቸውን ብዙ ትምህርቶችን ታስተምራቸው ነበር። እንዲህም ትላቸዋለች "ከቀን ብዛት ጠላት እንዳያስተኝ እኔ እንደምሞት አስቀድሜ ሳላስብ እግሬን ከአንዱ መወጣጫ ደረጃ ወደ ሁለተኛዋ አውጥቼ አላኖራትም"። ዳግመኛም "ለሰው ርኅራኄ ማድረግ በተሻለው ነበር ይህንንም በሚያደርግ ጊዜ የኋላ ኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ይኖራል" በዜና አረጋውያን መነኰሳት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉ ሌሎች ብዙ ቃሎችንም ተናግራለች።
❤ ታላቅ ተጋድሎም እየተጋደለች በዓቷም በባሕር ዳርቻ ሁኖ ሰባት ዓመት ኖረች አንዲት ቀን እንኳን ከሰው አንዱም አላያትም እርሷ ግን ሁሉን ታይ ነበር። ሸምግላ እስከ ሰማንያ ዓመት በደረሰች ጊዜ ከዚህ ዓለም የሕይወት ማሠሪያ ተፈትታ የዘላለም ተድላ ደስታ ወደሚገኝበት መጋቢት15 ቀን ሔደች። የቅድስት ሣራ ጸሎቷ በረከቷ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ሰለፍኮስ፦ የዚህን ቅዱስ ዜና ክርስቲያን እንደሆነ ከሃዲ ንጉሥ በሰማ ጊዜ ያመጡት ዘንድ አዘዘ ወደርሱም ሲቀርብ "የአስጠራጦኒቃ እጮኛዋ ሰለፍኮስ የተባልክ አንተ ነህን" አለው "አዎን ነኝ" አለ። ዳግመኛም "ማንን ታመልካለህ" አለው እርሱም እኔ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልከዋለሁ" ብሎ መለሰ። ንጉሡም መርዝ ያላቸው እባቦች ወዳሉበት እንዲጨምሩት አዘዘ እግዚአብሔርም አዳነው።
❤ ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዝዞ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊል ተቀበለ። የቅዱስ ሰለፍኮስ በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት15 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለሕልያስ ሰማዕት ሐዲስ። ዘአገረ ናህስ። ብቊዓኒ ሊተ በእንተ ክርስቶስ። ከመ ተሀበኒ መድኃኒት ሥጋ ወነፍስ። እምነ ብዕልከ እስእል ጽኑስ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 15።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ጻድቃንሰ ይወርስዋ ለምድር። ወይነብሩ ውስቴታ ለዓለመ ዓለም። አፉሁ ለጻድቅ ይትሜሐር ጥበበ"። መዝ 36፥29-30። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥19-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ።
minte
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ መጋቢት ፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረ ተጋዳይ ለሆነ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጦ በጌታችን ማመን ላስተማለው በሐዋርያት እጅ ለተጠመቀ፤ ወላጆቹን በሚያደርገው ተዓምራት ላሳመነ፤ የጣዖት አምልኮን ላጠፋና ሰይጣንን ድል ላደረገ ለጽኑ አባት ለአባ ኩትን ለዕረፍት በዓል፣ ለከበሩ ቅዱሳን ለእድርያኖስና ለሚስቱ፣ አውሳብዮስና አርማ ሌሎች አርባ ሰዎችም ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ ኖብ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ ከሁለት ሺህ ሰዎች ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ አባ ኩትን፦ እርሱም በሶርያ አገር ስሟ በንጣንዮስ ከምትባል ቦታ የሚኖር ነው። አባቶቹም ከዋክብትን ያመልኩ ነበር የአባቱ ስም ንስጣር የእናቱም ስም ቴዎድራ ይባላል። በአደገ ጊዜም ወላጆቹ ሊያጋቡት ፈለጉ እርሱ ግን አልወደደም ግድ ብለው ያለ ውዴታው ሚስትን አጋቡት ሊገናኛትም አልፈለገም ስለ ሥጋ ድካም ወይም ስለ ጽድቅ ሳይሆን የሥጋ ፍትወትን ስለሚጠላት ነው እንጂ። ደናግልም እንደሆኑ ሁለቱ ሁሉ ከሚስቱ ጋር በአንድነት ኖረ።
❤ "አምላክ ሆይ ወደ ዕውቀትህ ምራኝ" በማለት ጸሎትና ምልጃን ያዘወትር ነበር። ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለቆርኔሌዎስ እንደተገለጠ ተገለጦ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን አስተማረው ከሐዋርያትም ወደ አንዱ ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን እንዲጠመቅ አዘዘው። የሐዋርያት የስብከታቸው ወራት ነበርና ሒዶ ተጠመቀ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሁሉ ሕጉን ሥርዓቱንም ሁሉ ተማረ መለኮታዊ ምስጢርንም ተቀበለ። በየቀኑ ሁሉ የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት ይሰማ ነበር። የጽድቅን ሥራ መሥራትና ንጽሕና፣ ለበጎ ሥራ መጠመድ ትጋት፣ ቅንነት፣ የዋህነት፣ ጾም፣ ጸሎትና ሰጊድ በላዩ ተጨመረ። በእነዚህ ሁሉ የሚተጋ ሆነ እግዚአብሔርም አስደናቂ ተአምራቶችን እንዲያደርግ በርኵሳን አጋንንት ሥልጣንን ሰጠው።
❤ በሚያደርገው ተአምራትም ወላጆቹን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ማመን ስቦ አስገባቸው ደግሞ ሚስቱንና ወላጆቿን አሰገባቸው። ከከሀድያን አንዱ ለሰይጣን ሊሠዋ ወደ ጣዖቱ ቤት በገባ ጊዜ ቅዱስ ኩትን አውቆ በሰይጣን ላይ ጮኸ እርሱ ሰይጣን እንጂ አምላክ እንዳልሆነ በሰው ፊት ያምን ዘንድ አዘዘው። ሰይጣንም እንዳዘዘው ራሱን ገለጠ በዚያ የነበሩ ሁሉም "የቅዱሰ ኩትን አምላክ አንድ እርሱ ብቻ ነው" እያሉ ጮኹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ።
❤ ከዚህ በኋላ ከቀላውዴዎስ ቄሣር የተላከ መኰንን የቅዱስ ኩትንን ዜናውን በሰማ ጊዜ ወታደር ልኮ አስቀረበው ስለ ሥራውም ጠየቀው እርሱም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ መኰንኑም ጽኑ ግርፋት ገርፈው እንዲሥሩት አዘዘ ይህንንም አደረጉበት።
❤ የአገር ሰዎችም ቅዱስ ኩትንን አሠቃይተው እንዳሠሩት በሰሙ ጊዜ ሁሉም ወደርሱ ተራወጡ መኰንኑንም ሊገሉት ወደዱ መኰንኑም ሸሸ። ቅዱስ ኩትንንም ከማሠሪያው ፈትተው ከደሙም አጥበው ተሸክመው ወደቤቱ ወሰዱት ከዚህም በኋላ ብዙ ዘመናት ኑሮ የወደደው እግዚአብሔርን አገልግሎ ደስ አሰኝቶ በፍቅር አንድነት መጋቢት 9 ቀን ዐረፈ።
❤ ከዕረፍቱም በኋላ ቤቱን ቤተ ክርስቲያን አድርገው ሥጋውን በውስጥዋ አኖሩ ጌታችንም ከሥጋው ብዙዎች ታላላቅ ተአምራቶችን አሳየ። አባ ኩትን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትሁን አሜን።
+ + +
❤ የከበሩ ቅዱሳን እድርያኖስና ሚስቱ፣ አውሳብዮስና አርማ፣ ሌሎች አርባ ሰዎችም ሰማዕትነት፦ እሊህንም ምርጦች ለረከሰ ከወርቅና ከብር ለተሠራ ጣዖት ማምለክን እምቢ ስላሉ የክብር ባለቤት ለሆነ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለስሙ ዐላውያን ጽኑ የሆነ ሥቃይን አሠቃዩአቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን መጋቢት 9 ቀን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦የመጋቢት 9 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለኩትን በእደ ሐዋርያት ዘተጠምቀ። እመልአከ ሰማይ ትምርተ ከመ ተጠየቀ። ሶበ አገበርዎ እንተ ሕሊናሁ ኢጽሕቀ። በፍትወተ ሥጋ ኢተሞዐ ወበሥምረቱ ኢወድቀ። ምስለ ብእሲቱ ሰኪቦ ዘአኮ ርኁቀ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት9።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ፈሪሃ እግዚአብሔር እምሀርክሙ። መኑ ውእቱ ብእሲ ዘይፈቅድ ሐይወ። ወያፈቅር ይርአይ መዋዕለ ሠናያት"። መዝ 33፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 1፥1-11፣ ያዕ 2፥1-14 እና የሐዋ ሥራ 4፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማር 1፥23-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። በሁላችንም ይሁንልን።
1 161
አመ ፭ቱ ለመጋቢት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥርዓተ ማህሌት
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።
ዚቅ
ላህም መግዝዕ ተጠብሐ፤ ጽዋዓ መድኃኒት ተቶስሐ፤ አግብርት አግብርት አግብርት ይረፍቁ፤ ውስተ ሕፅኑ ለመርዓዊ፡፡
መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።
ዚቅ
ወይሁቦ ጸሎቶ ለዘጸለየ፤ ወባረከ ዓመተ ጻድቃኑ፡፡
ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኃኒት፤ እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት።
ዚቅ(ሌላ)
ማርያም ቤዛ ብዙኃን፤ ሕይወተ ኮነት ለኲሉ ዓለም፤ ፍሥሐነ ለእለ አመነ፡፡
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።
ዚቅ
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ ከመ አዕዋፍ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ጽሑፍ፡፡
ወረብ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ/፪/
'ኀበ ዓምደ ወርቅ'/፪/ ስሙ ጽሑፍ/፪/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፉከ ሰላም፤ ዓቃቤ ሥርዓት ዘሤመ ወማዕፆ ሕግ ዘዓቅም፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መነኮስ በምግባረ ሠናይ ፍጹም፤ እንበለ መብልዕ ወስቴ እንዘ ትትጋደል በጾም፤ ነጺራ ትዕግሥተከ አንከረት ገዳም
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ፤ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ፤ ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ።
ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ/፪/
ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ/፬/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከርሥከ ዘተሴሰየ ኅብስተ፤ አኮ ኅብስተ ምድራዌ እንተ ያመጽዕ ሐኬተ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኲሉ ይንዕዱከ ከሡተ፤ ብርሃነ ለዕውራን ወለሐንካሣን ፍኖተ፤ ወለበሐማን ቃለ ዘኮንኮሙ አንተ፡፡
ዚቅ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይከ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘበስለ፤ ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይከ፤ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድሐ።
ወረብ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ዘተሴሰይከ ኅብስተ ምድራዌ ኅብስተ/፪/
አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት/፪/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ እንተ ረሰየ ህላዌ፤ ኀበ ኢሰማዕ ቦቱ ዜና ሞት ወዝክረ ደዌ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንተ ዘገዳማውያን ሠርዌ፤ ወረዱ ጊዜ ሞትከ ዑፁፋነ ፅዱል ሥርጋዌ፤ ከመ ይትቀበሉ ኪያከ መርዓዌ፡
ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፤ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡
ወረብ
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት/፪/
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለገብረ ሕይወት/፪/
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ ብርሃነ ሰማይ ዘአገቶ፤ እለ ያዕቆብ ወዮሴፍ እስከነ ፈርሁ ቀሪበቶ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ባዕል ለብዕለ ጸጋከ ዘያስተቶ፤ ኃያል ብእሲ ይንሣእ ሢመቶ፤ ወበዓለ ዕዳ ይበርብር ንዋዮ ወቤቶ፡፡
ዚቅ
ፀሐይ ፀሐይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ፤ ዘያበርህ ስኑ በውስተ ቀላይ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ዘባረኮ አግዚእ አዶናይ።
መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም መቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ፤ ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ፤ ዜና መቃብርከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ፤ ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም ዓፀድ፤ ወቦ ዘይቤ ሀለወ በከብድ፡፡
ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ ጸሎቱ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ፡፡
ወረብ፦
ወረደ ብርሃን ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤
ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ ጸሎቱ ለገብረ ህይወት፤
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ፦
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘእግዚአብሔር ገብር በእደ መላእክት ቅቡር፤ በኢየሩሳሌም ሀገር፤ ኀበ ኢይበጽሕ ሰብእ በእግር፤ እንበለ ዳዕሙ ዖፍ ዘይሠርር
ምልጣን፦
ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል፤ እለ አክናፊሆሙ ነበልባል፤ ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።
አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል/፬/
ወረብ
'ግሩማን መላእክት'/፪/ ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል/፪/
ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል አማን ገብረ ህይወት/፪/
አመ ፭ቱ ለመጋቢት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥርዓተ ማህሌት
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።
@eotcww
@eotcww
@eotcww
1 161
ወረብ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ/፪/
'ኀበ ዓምደ ወርቅ'/፪/ ስሙ ጽሑፍ/፪/
@EOTCmahlet
👇👇🇪🇹
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹
@eotcww
#Join & share
ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ/፪/
ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ/፬/
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹
@eotcww
#Join & share
ወረብ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ዘተሴሰይከ ኅብስተ ምድራዌ ኅብስተ/፪/
አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት/፪/
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@eotcww
#Join & share
ወረብ
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት/፪/
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለገብረ ሕይወት/፪/
👉@eotcww
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@eotcww
#Join & share
ወረብ
'ግሩማን መላእክት'/፪/ ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል/፪/
ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል/፪/
👇👇🇪🇹
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
👉@eotcww👈
🇪🇹👆👆👆👆🇪🇹
@eotcww
#Join & share
1 161
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)
እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡
ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10)፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡
ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-
☑️ እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
☑️ ዕለተ ሥጋዌ ናት። ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
☑️ ዕለተ ትንሣኤ ፥ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት ናትና
☑️ የቤተ/ክ የልደት ቀን፥ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያገኙባት ዕለት ናትና
☑️ ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት(1ኛ ቆሮ 16፤1)
☑️ የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7) በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት
ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡
ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር። (ራዕ 1፡10)
በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)
ከሰንበት ረድኤት በረከት ይካፍለን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የካቲት ፲፬ (14) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት ሃይማኖታቸው ለቀና ምዕመናን መምህራቸው ለሆነ ለአንጾክያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ አባት ለአባ ሳዊሮስ ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክንድርያ ለኃምሳኛ ሊቀ ጳጳስ በጸሎቱ አንድ ሙት ላስነሳ ለከበረ አባት ለአባ ያዕቆብና ሰባ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ አባት ለአባ ቄርሎስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ከዳርዮስ፣ ከጳውሎስ፣ ከአኩደራስና ከሊድና ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለሳዊሮስ ሊቀ ጳጳሳት ዘተጰጰሰ በሃይማኖት"። ትርጉም፦ በቀናች ሃይማኖት የጳጳሳት አለቃን ኾኖ ለተሾመ ሳዊሮስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ አባ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ፦ የዚህ ቅዱስ ዘመዶቹ ከሮሜ አገር ናቸው አባቱም ስሙ ሳዊሮስ የሚባል ኤጲስቆጶስ ነው። እርሱም ስለ ንስጥሮስ በኤፌሶን ከተማ ጉባኤ በሆነ ጊዜ ከሁለት መቶ አባቶች ኤጲስቆጶሳት ጋር መጣ በዚያም እንዲህ የሚለውን ራእይ አየ "ከአንተ የሚወለድ ልጅህ ስሙም እንደ ስምህ ሳዊሮስ ተብሎ የሚጠራ እርሱ ለቀናች ሃይማኖትን" ያጸናታል።
❤ ይህም ኤጲስቆጶስ በዐረፈ ጊዜ ልጁን ሳዊሮስ ብለው ጠሩት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ የሆነውን ጥበብን ሁሉ ተማረ። ከመምህሩም ወጥቶ ወደ አንድ ቦታ ሲጓዝ በዋሻ ራሱን እሥረኛ አድርጎ የሚኖር ጻድቅ ሰው ተገናኘው በእርሱም ደስ ብሎት "የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሃይማኖታቸው ለቀና ምዕመናን መምህራቸው የሆንክ ሳዊሮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው" አለው። ሳዊሮስም ከቶ ሳያውቀው በስሙ በጠራው ጊዜ የሚደረግለትንም ከመሆኑ አስቀድሞ በመናገሩ አደነቀ።
❤ ከዚህም በኋላ ሳዊሮስ ትሩፋት በመሥራት አደገ መልካም ስም አጠራሩና ዜናው ተሰማ በአባ ሮማኖስ ገዳም መንኵሶ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ በትሩፋትም ሥራ እጅግ የተጠመደ ሆነ የከበረ ወንጌል "በተራራ ላይ የተሠራች መንደር መሠወር አትችልም" እንዳለ ዜናው በሁሉ ዘንድ ተሰማ። የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳትም በዐረፈ ጊዜ አዋቂዎች ኤጲስቆጶሳት ይህን የከበረ ሳዊሮስን ይሾሙት ዘንድ ተስማምተው ያለ ውዴታው ወስደው በአንጾኪያ አገር ላይ ጵጵስና ሾሙት በሹመቱም እስከ ዓለም ዳርቻ ያለች ቤተ ክርስቲያን ብርሃን ሆነላት በአገሮች ሁሉ ወዳሉ መናፍቃን ከሀድያን ትምህርቱ በሚደርስ ጊዜ ሁለት አፍ እንዳለው ስለታም ሰይፍ ሥራቸውን ይበጥሳልና።
❤ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ አማኒ ንጉሥ ሙቶ በርሱ ፈንታ ስሙ ዮስጥያኖስ የሚባል መናፍቅ ነገሠ ንግሥቲቱ ሚስት ግን ሃይማኖቷ የቀና ነው ስማ ቴዎድራ ይባላል። ንጉሡም የኬልቄዶን ወደ ሆነች ወደረከሰች ሃይማኖቱ ይህን የከበረ አባት ያስገባው ዘንድ ያስፈራራው ነበር እርሱ ግን ፈርቶ አይትዘዝለትም ቊጣውንም የሚፈራ መስሎት በእርሱ ላይ አብዝቶ ተቆጣ ቊጣውንም ባልፈራ ጊዜ በሥው፡ ሊያስገድለው መከረ ንግሥቲቱም አውቃ ከንጉሡ ፊት ይሸሽ ዘንድ ሊቀ ጳጳሱን መከረችው እርሱም በሥውር ወጥቶ ገለል አለ። እግዚአብሔር የዚህን አባት ሞት አልፈቀደምና ስለ ምእመናንም ጥቅም ጠበቀው። በአንድ ተራ መነኵሴ አምሳል ሁኖ፡ በቦታዎችና በገዳማት የሚዘዋወርና ምእመናንን የሚያጠናክራቸው ሆነ ስካ በሚባል አገር ስሙ ዶርታኦስ ከሚባል ደግ ምእመን ባለ ጸጋ ሰው ዘንድ ተምጦ ሳለ ጌታችን በእጆቹ ብዙ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ ስካ በተባለ አገር እስከ ዐረፈ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ሁሉንም ያስተምራቸው ነበር ከዚህም በኋላ ወደ ዝጋግ ገዳም አፈለሱት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሳዊሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ቄርሎስ፦ ይህም አባት ፍዩም ከምትባል አገር ነው። በእርሷም ቅስና ተሹሞ ኖረ ከዚህም በኋላ ከዚያ፡ ለቆ ከምስር ከተማ ውጭ ወደ ሆነች የኢትዮጵያውያን የጒድጓድ ውኃ ወዳለበት ወደ ቅዱስ ፊቅጦር ገዳም ደረሰ በውስጡም ታላቅ ተጋድሎን እነተጋደለ ብዙ ዘመናትን ኖረ።
❤ የዕውቀቱና የቅድስናው ዜና በተሰማ ጊዜ ያለ ውዴታው ይዘው በእስክድርያ አገር ሊቀ ጵጵስና ሾሙት መንጋውንም በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ በቊርባንና በጸሎት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊሠሩት የሚገባቸውን ለካህናት ሦርዓትን ሠራ። በሹመቱም ሰባት ዓመት ከዘጠኝ ወር ከሃያ ሰባት ቀን ኑሮ የካቲት14 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ያዕቆብ፦ ይህም አባት እልመቱዝ ለተባለ የግብጽ ንጉሥ በነገሠ በ17 ዓመት ተሾመ እርሱም ለመኰንኑ ለወልደ ኀሮን ረሽድ ወንድም የሆነ ነው፡ በዚህም አባት ዘመን የአስቄጥስ ገዳማት ታድሰው መነኰሳቱ ወደሳቸው ተመለሱ።
❤ አፎን በሚባል አገር ስሙ መቃርስ የሚባል ሰው ነበር ወደዚህ አባት ወደ ያዕቆብ መጥቶ ወደቤቱ በመሔድ ቤቱን ይባርክለት ዘንድ ለመነው እርሱም አብሮት ሔደ ታሞ የነበረ ልጁም ሞተ ወደ አባ ያዕቆብ አቅርቦ እንዲህ ብሎ ለመነው "ከርሱ በቀር ልጅ የለኝምና አባቴ ሆይ ራራልኝ እርሱም እነሆ ሞተ ስርሱ፡ ወደ እግዚአብሔር ትማልድ ዘንድ እለምንሃለው" አለው። አባ ያዕቆብም "እንደ እምነትህ ይሁንልህ አትፍራ" አለው። ሕፃኑንም ከአባቱ ተቀብሎ ታቀፈውና በላዩ ጸለየ በመስቀል ምልክትም አማተበበት ስለርሱም ወደ እግዚአብሔር ለመነ ጌታችንም ልመናውን ተቀበለው የሕፃኑ ነፍስ ተመልሳ ዐይኖቹን ገለጠ ከሞትም ድኖ ተነሣ አባቱንም "ልጅህን ውሰድ የሞተ አይደለም ያንቀላፋ ሁን ነው እንጂ" አለው። የሕፃኑም አባት ይህን ድንቅ ሥራ በአየ ጊዜ እጅግ ፈራ የገንዘቡንም እኩሌታ ለምጽዋት ብሎ ሰጠው እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ ሃይማኖታቸው ለቀና ምእመናን ሁሉ ወደርሷ በመጡ ጊዜ መጠጊያ ይሆን ዘንድ ቤተ ክርስቲያንን ሠራበት።
❤ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ዲዮናስዮስም ወደ ምስር በመጣ ጊዜ ከአባ ያዕቆብ ጋር ተቀምጦ ወደ አገሩ ተመለሰ። ይህ አባት ያዕቆብ በሹመቱ ዐሥር ዓመት ከስምት ወር፡ ከሦስት ቀን ኑሮ የካቲት14 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ያዕቆብ በጸሎቱ ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 14 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለያዕቆብ ለእግዚአብሔር ቅዱሱ። ዘአድባረ ገዳም ኵሉ በመዋዕሊሁ ተሐደሱ። እስከ አቡሁ ገነየ ለብዕለ ጸጋሁ ወዕበየ ሞገሱ። በግሠተ እዱ ወበጽላሎታ ለእርሱ። ውስተ በድነ ሕፃን ገብአት ዘወጽአት መንፈሱ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 14።
@Eotcw @Eotcw
@Eotcw @Eotcw
1 161
የዕለቱ ምስባክ
#ምስባክ፦
መዝ፵፮፥፫
አግረረ ለነ አሕዛበ ወሕዝበ ታሕተ እገሪነ፤
ወኀረየነ ሎቱ ለርስቱ፤
ሥኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ።
#ትርጕም፦
አሕዛብን ከእኛ በታች ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን፤
ለርስቱ መረጠን፤
የያዕቆብን ውበት የወደደ እርሱ ነው።
1 161
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ የከበረ ሰርግዮስን በመንኰራኵር ውስጥ ያሠቃዮት ዘንድ በጆሮዎቹ የእሳት መብራቶችን እንዲጨምሩ የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች እንዲነቅሉ በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠልጥለው ከብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን እንዲያነዱ አውህዮስ አዘዘ እንዳዘዘውም አደረጉበት ጌታችን ኢየሱስ ያጸናውና ያለ ጥፋት በጤና ያስነሣው ነበር። የሠራዊት አለቃ አውህዮስም ማሠቃየቱን በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ፡አዘዘ የከበረ ሰርግዮስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ወደ አባቱና ወደ እናቱ ወደ ወንድሞቹም ላከ ዘመዶቹ ሁሉም የእርሱ የሆኑ ሰዎችም መጡ በአፋም ልጓም ለጒመው ቸብቸቦውን ወደሚቆርጡበት ሲስቡት አገኙትና መኰንኑን የረከሱ ጣዖታቱንም ረገሙ መኰንኑም ከከበረ ሰርግዮስ ጋር ሁሉንም ቸብቸቧቸውን እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
❤ እንዲህም ሆነ ከሕዝቡ ውስጥ አንድ ታናሽ ሕፃን እግዚአብሔር ዐይኖቹን ገልጦለት የቅዱሳን ሰማዕታትን ነፍሶቻቸውን መላእክት ወደ ሰማያት ሲያወጧቸው አይቶ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅር በለኝ" እያለ በከፍተኛ ቃል ጮኸ እናትና አባቱም መኰንኑ ሰምቶ ስርሱ እንዳያጠፋቸው አፋን የሚዘጉ ሆኑ እርሱ ግን እንዲህ እያለ መጮኹን አልተወም በላዩ እስከ ተኙበትና ነፍሱን እስከ አሳለፈ ድረስ ከሰማዕታትም ጋር የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕታት በጸሎቱ ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት13 ስንክሳር።
+ + +
❤ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሁለተኛ ነው። ይህንንም አባት ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራና ችግር ደርሶበታል ። እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስ ወደ ግብጽ አገር መጣ እርሱም ከዚህ አባት ጢሞቴዎስ ጋር ምእመናንን እያጽናና ከሀገር ወደ ሀገር ከገዳም ወደ ገዳም ከቦታ ወደ ቦታ የሚዘዋወር ሆነ።
❤ በዚህም አባት ጢሞቴዎስ ዘመን ከቊስጥንጥንያ የመጡ ክፉዎች ሰዎች በግብጽ አገር ተገለጡ እነርሱም የክርስቶስን ተዋሕዶ ምትሐት በሚያደርግ መከራውንና ትንሣኤውንም በሚክድ በረከሰ በአውጣኪ ትምህርት የሚያምኑ ናቸው ይህም አባት አውግዞ ከግብጽ አገር አሳደዳቸው።
❤ ዳግመኛም በዘመኑ ምእመን ንጉሥ አንስጣስዮስ አረፈና በርሱ ፈንታ ኬልቄዶናዊ መናፍቅ ዮስጣትያኖስ ነገሠ እርሱም በአባ ጢሞቴዎስ ፈንታ ሊናርዮስን ሊቀ ጵጵስና ሾመው ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናንን ሁሉ በኬልቄዶን ግባኤ ወደተወሰነ ሃይማኖት ሊመልሳቸው ወዶ በቅስጥንጥኒያ ጉባኤ ሰብስቦ የአንጾኪያውን ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስን ከኤጲስቆጶሳቶቹ ጋር አስመጣው።
❤ በኬልቄዶን ጉባኤ በተወሰነች በተበላሸች ሃይማኖቱ ያምኑ ዘንድ አስገደዳቸው እነርሱ ግን አልተቀበሉትም ትእዛዙንም አልሰሙም ስለዚህም ሃይማኖታቸው በቀና ምእመናን ሁሉ ታላቅ መከራ አደረሰባቸው።
❤ ይህም አባት ጢሞቴዎስ በመንበረ ሢመቱ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኑሮ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጢሞቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም እብል ጢሞቴዎስሃ ሰባኬ። ወሊቀ ጳጳሳት ዝኬ። ዘበመዋዕሊሁ ተውህበ ለመሃይምናን ቡራኬ። ወውዕዩ በነደ ቃሉ ከመ አገዳ ሐመል ወመሎኬ። እለ ተአመኑ በትምህርቱ ለዕልው አውጣኬ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 13።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "አግረረ ለነ አሕዛበ ወሕዝበ ታሕተ እገሪነ። ወኀረየነ ሎቱ ለርስቱ። ሥኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ"። መዝ 46፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥1-17፣ 1ኛ ጴጥ 2፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 11፥1-14። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 4፥1-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@Eotcw
1 161
+ + +
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ አውሳብዮስ ዘሀገረ ሶርያ፦ ይኽም ቅዱስ የሶርያው መስፍን ልጅ ነው፡፡ ለርሱም መንፈስ ቅዱስን የተመላች ስሟ አውሎፊያ የምትባ እኅት አለችው ይህንንም በተግሣጽና በጥበብ በማስተማር ካሳደጉት በኋላ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ በታላቅ ክብር አጋቡት፡፡ በሠርጉም ዕለት ወደ ቅድስት ወደሆነችው ወደ እኅቱ ዘንድ ገብቶ "እስቲ ምከሪኝ ልቤ ይህን ጋብቻ አይሻውም ዓለምን ንቆ መተውን እንጂ" አላት፡፡እኅቱም "የዚህ የኃላፊው ዓለም ጣዕም ምን ይጠቅምሃል?እንደ ሊቀጳጳሳት ድሜጥሮስ በድንግልና መኖር ይሻልሃል" አለችው፡፡ ምሽትም በሆነ ወደ ሙሽራይቱ ጫጉላ ቤት ገብቶ የእነርሱ ውበትና ደምግባት እንደሚጠፋ ከዚህም ይበልጥ የሚጠቅማቸውን የጽድቅ ሥራ በመሥራት ድንግልናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ሙሽራይቱን አዋያት፡፡ ሙሽራይቱም በሀሳቡ ተስማምታ ድንግልናቸውን በመጠበቅ በጾም በጸሎት እየዋሉ ሌሊትም ከባሕር ውስጥ፡ገብተው፡ቆመው ሲጸልዩ ያድሩ ጀመር፡፡ አትራ ወደምትባል ቤተ ክርስቲያን ሄደው አራት እልፍ ይሰግዳሉ፡፡
❤ በአንዲት ዕለት የሶርያው ንጉሥ ሚስት ቅዱስ አውሳብዮስን አይታው እጅግ ወደደችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ ሁለቱን ልካ ካስመጣችው በኋላ በወርቅ አጊጣ በሐር በተነጠፈ አልጋ ላይ ሆና ጠበቀችው፡፡ከእርሷም ጋር እንዲተኛ ስትጠይቀው "እኔስ ሚስቴንም እንኳን በግብር ያላወኩ ነኝና ተይኝ ንጉሡ ባልሽ በቤት ባይኖር ሰውም ባያየን እግዚአብሔር ግን ያየናልና እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ? "በማለት ትቷት ሊወጣ ሲል ልብሱን ያዘችው፡፡ እርሱም ሮጦ በማምለጥ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ እርሷ ግን በመጮህ ባሮቿ ሲመጡላት" ክፉ ነገርን አድርጎብኝ ሄደ" ብላ በሐሰት ተናገረች፡፡ ጭፍሮቿም ቅዱስ አውሳብዮስን ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው እየደበደቡ ወደ ንግሥቲቱ አመጡት፡፡ እጆቹንና እግሮቹንም አሥረው ከከተማ ውጭ በአራት ዕንጨቶች ላይ አሰቀለችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ አንዲቱ በንግሥቲቱ ተልካ ሄዳ አውሳብዮስን "ከተሰቀልክበት እንዲታወርድህ ለእመቤቴ ያለችህን እሺ በላት" አለችው፡፡ እርሱም "የአመንዝራን ቃል አልሰማም" አላት፡፡ ንግሥቲቱም እሺ እንዳላላት ስታውቅ አንገቱን በገመድ አሳንቃ 160 ፍላጻዎችን በሰውነቱ ውስጥ እንዲጭምሩበት አደረገች፡፡ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮለት ፍላጻዎቹን ከሰውነቱ ውስጥ አወጡለትና ፍጹም ጤነኛ ሆነ፡፡
ንጉሡም ከሄደበት ሲመለስ ንግሥት ሚስቱን አውሳብዮስን ለስቅላትና ለሞት ያበቃችው በምን ምክንያት እንደሆነ ሲጠይቃት አንተ በሌለህበት ወደ መኝታ ቤቴ ገብቶ ሊናገሩት የማይገባ ነገር ጠየቀኝ በከለከልኩትም ጊዜ በሥራዩ አሳመመኝ" አለችው፡፡ንጉሡም ተቆጥቶ ቅዱስ አውሳብዮስን ከተሰቀለበት አስወርዶ ካስመጣው በኋላ ለምን ይህን እንዳደረገ ጠየቀው፡፡ አውሳብዮስም እውነቱን በነገረው ጊዜ ጭፍሮቹን ምስክር ይሆኑ ዘንድ ሲጠይቃቸው ንግሥቲቱ ስትጮህ ወደ ውስጥ ሲገቡ ያጋጠማቸውን መሰከሩ፡፡ ንጉሡም የሚስቱን ነገር አምኖ በመቀበል በንዴት የቅዱስ አውሳብዮስን ሰውነቱን በሰይፍ አስቆርጦ ሥጋውን እንደ ላም ሥጋ ቆራርጦ በምንቸት አድርጎ በእሳት እንዲበስል አደረገው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከምቸቱ አውጥተው ከሞትም አድነው በማስነሣት ፍጹም ጤነኛ አደርገው አቆሙት፡፡
❤ ከሞት ከተነሣም በኋላ በአገሩ ውስጥ ሲሄድ ሰዎች አይተውት ለንጉሡ ስለነገሩት ንጉሡ ድጋሚ ካስመጣው በኋላ አራት ዛንጅሮች በአካላቶቹ ውስጥ በማስገባት እጅና እግሩን አሳስሮ በእሳት ውስጥ ጨመረው፡፡ የከበሩ ሁለቱ ቅዱሳን መላእክት አሁንም መጥተው ፈወሱት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14ዓመት ኖረ፡፡ ከዚያም ወደ ምድር ተመልሶ መጥቶ ወንጌልን እያስተማረ 40 ዓመት ኖረ፡፡ በእርሱም ትምህርት 85ሺህ አረማውያን አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ቅዱስ አውሳብዮስ በመጨረሻ ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን ፈጽሞ የካቲት13 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡ጌታችንን፡ኢየሱስም ስሙ ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ እስከ ሰባት ትውልድ ሊምርለት ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አውሳብዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ሰርግዮስ፦ የዚህ ቅዱስ አባቱና እናቱ ደጎች ናቸው። የአባቱ ስም ቴዎድሮስ የእናቱም ስም ማርያም ነው። ዕድሜውም ሃያ ዓመት ሲሆነው በክብር ባለቤት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አሰበ ወደ መኰንኑ ቆጵርያኖስም ቀርቦ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩት ዘንድ ያሥሩትም ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሰማይ አምጥቀው የቅዱሳን ሰማዕታትን መኖርያ ያሳዩዋት ዘንድ አዘዘ አይታም ተጽናናች ከሥቃይ ከሕማሙም ፈወሰው።
❤ ቀሲስ አባ መጹንና ሁለት ዲያቆናትም ተጋድሎውን ሰሙ ያን ጊዜም ተነሥተው ወደ አትሪብ አገር ገዥ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ የጸና ግርፈትም ይገርፋቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ሕዝቡም ሁሉ በዙርያቸው ሁነው ይመለከቷቸው ነበር ስለ ቄሱና ከእርሱ ጋር ስላሉትም አዘኑ ቄሱ ግን ፊቱን ወጀርሳቸው መልሶ ገሠጻቸው አስተማራቸውም "በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ በቀናች ሃይማኖት እንዲህ ጽኑ" አላቸው ከዚህም በኋላ በውኋ ላይ ጸልዮ በላያቸው ረጨ በዚያንም ጊዜ በላያቸው ወርዶአልና የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀበለው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ቆረጧቸው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከዚያም በኋላ ቄሱን ከውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሩት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ እግዚአብሔርም ከእሳት አዳነው። ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጠለትና እርሱ ስለ ክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ሦስት ጊዜ ምስክር እንደሚሆን አሰረዳው ከእሳት ማንደጃው ውስጥም አወጣው። መኰንኑም ወደ እስክድርያ አገር ላከው ተጋድሎውንና ምስክርነቱን በዚያ ፈጸመ የምስክርኘቱን አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
❤ ከዚያም በኋላ መኰንኑ ቆጵርያኖስ የከበረ ሰርግዮስን ያቀርቡት ዘንድ አዘዘ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው የነሐስ መንኰራኵሮችንም አምጥተው ከውስጣቸው አስገብተው አበራዩት ሕዋሳቱም አራት ክፍል ሁኖ ሥጋው ሁሉ ተቆራረጠ ጌታችንም አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው። ዳግመኛም እንዲሰግድለት ጣዖትን አመጡ ቅዱሱ ግን ሲረግጠው ወድቆ ተቀጥቅጦ ደቀቀ መኰንን ቆጵርያኖስም አይቶ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ "አምላክ ቢሆን ራሱን ማዳን በቻለ ነበር" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ የጭፍራ አለቃ ስሙ አውህዮስ የሚባል የከበረ ሰርግዮስን ፈልጎ ያዘው ቆዳውንም ገፈው በተቀላቀለ ኮምጣጤና ጨው ቊስሉን ያሹት ዘንድ አዘዘ ጌታችን ግን በሥቃዮች ላይ ያጸናውና ያበረታው፡ ነበር። እናቱና እኅቱም ሰምተው ወደርሱ መጡ በአዩትም ጊዜ በላዩ አለቀሱ ከኀዘንም ብዛት እኅቱ ነፍሷን አሳለፈች የከበረ ሰርግዮስም ስለ እኅቱ ወደ ጌታችን ጸለየ ከሞትም ድና በሕይወት ተነሣች። ያን ጊዜ የሰማዕታትን ገድል የሚጽፍ የአቅፋስ፡አገር ሰው የከበረ ዮልዮስ መጣ ገድሉንም ሁሉ ከእርሱ ተረዳ ለሥጋውም እንደሚያስብ ቃል ገባለት።
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤
❤ የካቲት ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን መልካም ስም አጠራርና ጣፋጭ ዜና ላለው ለሶርያ መስፍን ልጁ ለሆነ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከሞት አስነሥተውት፤ ቅዱስ ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14ዓመት ለኖረ፤ ተመልሶ ወደ ምድር መጥቶ 40ዓመት ለኖረ በተአምራቱና በትምህርቱ 85ሺህ አረማውያንን አሳምኖ ላጠመቀ ለተመሰገነ ለሁለተኛው ለቅዱስ አውሳብዮስ ለምስክርነቱና ለዕረፍቱ በዓል፣ ለከበረ ለቅዱስ ሰርግዮስ ከአባቱና እናቱ ከወድሞቹም ከሌሎችም ብዙ ሰዎች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለኅርማኖስ ልጅ ለታላቁ ሰማዕት ለቅዱስ ፊቅጦር ለልደቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ አባት ከእስክድርያ አገር ሠላሳ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ ከአባ ጢሞቴዎስ ዕረፍት፣ ከቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ ከቅዱስ ቴዎድሮስ ከምስክርነቱ መታሰቢያ፣ ከአባ ክፍላና ከአባ ኅብስት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "ወብዙኃን ኖሎት መጽኡ ወስዕኑ ከሢቶታ ለዕብን እምአፈ ዐዘቅት እስከ ይመጽእ ያዕቆብ ዘክቡት ውስተ ሐቋሁ ዘሀሎ ይሠጐ እምሰብእ ከሠተ ወአስተየ መርዔቶ ወከማሁመ መጽኡ ብዙኃን ነቢያት ወሰስዕኑ ከሢቶታ ለጠጥምቀት እስከ ይመጽእ ዐቢይ ኖላዊ እምሰማይ ከሠተ ወአጥመቀ ብዙኃነ አሕዛበ በውስቴታ መንክር ተአምሪሁ ለመድኀኒነ በከመ ወፅአት በትር እምሥርወ ዕሤይ በአምሳለ በትረ ያዕቆብ በዘይርዒ አባግዒሁ ይእቲኬ ማርያም ይእቲ ወበእንተ ዘይቤ ትወፅእ በትር ወየዐርግ ጽጌ ውእቱኬ ዋሕድ ውእቱ ውእቱኬ ወልደ አምላክ ውእቱ። ትርጉም፦ ብዙ እረኞች መጡ ከጉድጓድ ውኃ ላይ የተገጠመው ድንጋይ ማንከባለልና በጎቻቸውን ውኃ ማጠጣት አልቻሉም ያዕቆብ ሲመጣ ግን ድንጋዩን ከጉድጓዱ ላይ አንሥቶ መንጋዎቹን አጠጣቸው፣ እንዲሁም ብዙ ነቢያት ቢመጡም ከሰማይ የሚመጣው ታላቅ እረኛ ክርስቶስ እስኪመጣና የጥምቀት ምሥጢር ከፍቶ ብዙ አሕዛብን በውኃ እስከያጠምቅ ድረስ የጥምቀትን ምሥጢር ሊገልጧት አልተቻላቸውም።
+ + +
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር፦ ለዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ኅርማኖስ ነው እርሱም ለዲዮቅልጥያኖስ የአማካሪዎቹና የሠራዊቱ አለቃ ነው ስለ አምልኮ ጣዖት ሥራ ምክሩና ንግግሩ ሁሉ ከእርሱ ጋራ ነበር የእናቱም ስም ማርታ ይባላል በክርስትናዋ የጸናች ብፅዕት ናት።
❤ ቅዱስ ፊቅጦርም በአደገ ጊዜ አባቱ ወደ ንጉሥ አቀረበው ንጉሡም በመንግሥቱ ውስጥ ሦስተኛ ማዕርግ አድርጎ ሾመው በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበረ። እርሱም የዚህን ዓለም ክብር ናቀ ሥጋ አይባላም ወይን አይጠጣም ዘወትርም ይጾማል ጸሎትንም ባለማቋረጥ በቀንና በሌሊት ይጸልያል። በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም የታሠሩትን ይጐበኛቸዋል ለድኆችና ለምስኪኖችም ይመጸውታል።
❤ የቅዱስ ቆዝሞስና ድምያኖስ እናት ቅድስት ቴዎዳዳን በገደሉዋት ጊዜ ንጉሡም ስለ መፍራት ሊቀብራት ማንም አልደፈረም። ይህ ቅዱስ ፊቅጦርም መጥቶ ሥጋዋን ወሰደ ከንጉሥ ስለሚመጣው ቅጣት ሳይፈራ ቀበራት። ጣዖት ስለ ማምለኩ አባቱን ዘወትር የሚገሥጸውና ብዙ ጊዜም የሚመክረው ሆነ አባቱም ወደ ንጉሥ ከሰሰው እንጂ አልሰማውም። ተከሶም ወደ ንጉሥ በአቀረቡት ጊዜ "አማልክት ያልሆኑ ርኲሳን ጣዖታትን ለሚያመልክ ሰነፍ ዝንጉ ልብ የለሽ ለሆነ ንጉሥ አላገለግልም። ከዛሬ ጀምሮ ለሕያው ንጉሥ ክርስቶስ እገዛለሁ የሰጠኸኝንም ገንዘብህን ንሣ" ብሎ በፊቱ ትጥቁን ፈትቶ ጣለለት።
❤ አባቱ ኅርማኖስም ወደ እስክንድርያ እንዲልከውና በኄርሜኔዎስ መኰንን ዘንድ በዚያ ፊቅጦር እንዲቀጣ ንጉሡን መከረው። በዚያን ጊዜም ከአደባባይ አወጡት እናቱም በብዙ ልቅሶ ልትሸኘው መጣች። እርሱም ሲመግባቸው ስለ ነበረ የታሠሩ ምዕመናን ስለ ድኆችና ምስኪኖች ስለ ሙት ልጆችና ስለ ባልቴቶች የሚሹትን በመስጠት እንድትጐበኛቸው አዘዛት ከዚያም አፉን ለጉመው ወሰዱት።
❤ በእስክንድርያ አገር ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስ ዘንድ በደረሰ ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ሰማያት አውጥቶ ስለ ክብራቸው ለመናገር የሚያስጨንቁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳይቶ ወደ መኖሪያው መለሰው። መኰንኑም በእሳት በአፈሉት በዝፍት፣ በዲን ደግሞ አሠቃየው ከዚያም በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ። ደግመው ከውሽባ ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃዩት የክብር ባለቤት ጌታችንም ያጸናውና ከሥቃዩ ያስታግሠው መልአኩንም ልኮ ከቊስሉ ይፈውሰው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ እንዴናው ከተማ ላከው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ምላሱን ቆረጡ። በእሳት ያጋሉዋቸውን ችንካሮች በጐኖቹ ውስጥ ጨመሩ እግዚአብሔር ግን አጽንቶ አስታግሦ ያለ ጉዳት በደኅና ያነሣዋል። ከዚህም በኋላ በዚያ በረኃብ እንዲሞት ከዱር ባለ ግምብ ውስጥ አሠሩት። እርሱ ግን መጥረብ የሚያውቅ ስለሆነ ላይዳዎችን በመጥረብና በመሸጥ በየጥቂቱ እየተመገበ የቀረውን ለድኆች እየሰጠ ኖረ። አንድ መኰንንም መጥቶ በዚያ ግምብ አቅራቢያ አደረ ስለ ቅዱስ ፊቅጦርም እርሱ የንጉሥ የሠራዊት አለቃ የሆነ የኅርማኖስ ልጅ እንደሆነ ነገሩት። መኰንኑም ወደርሱ አቅርቦ ብዙ ሸነገለው ባልሰማውም ጊዜ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ጅማቶቹን መዘዙ አፋን መቱት ቊልቊል ሰቀሉት በእጆቹ ላይ ከባድ ደንጊያ አንጠልጠሉ። ከዚያም ከሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት ሙጫ፣ አደሮ፣ ማርና ዘይትን አፍልተው በላዩ ደፉበት በማበራያም አበራዩት አፉንም በአሞትና በእሬት አመረሩት ዐይኖቹንም አወለቁት ደግመውም ዘቅዝቀው ሰቀሉት። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾለት አጸናው አረጋጋው። ሥሮቹንም ሕዋሳቶቹን በቦታቸው መለሰለትና አዳነው።
❤ አንዲት ዓሥራ አምስት ዓመት የሆናት ብላቴና ነበረች ቅዱስ ፊቅጦርን ሲአሠቃዩት በቤቷ መስኮት ታየው ነበር። መላእክትም በእጆቻቸው አክሊሎችን ይዘው እነርሱም በቅዱስ ፊቅጦር ራስ ላይ ሲያኖሩአቸው አይታ እንዴት እንዳየች ለአሕዛብ ነገረቻቸው እጅግም አደነቁ ከእርሳቸውም ብዙዎች በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ። ያቺም ብላቴና በጌታችን አመነች መኰንኑም ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። የሕይወት አክሊልንም ተቀበለች ሁለተኛም የአመኑትን ሁሉ ራሳቸውን እንዲቆርጡአቸው አዘዘ የሕይወትንም አክሊል ተቀበሉ።
❤ ከዚህም በኋላ የከበረች የቅዱስ ፊቅጦርን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ተጋድሎውንም ሚያዝያ27 ፈጽሞ የሕይወትና የድል አክሊል ተቀበለ። ምዕመናን ሰዎችም ሥጋውን ወስደው በከበሩ ልብሶች በድርብ በፍታ ገነዙት። እናቱ ማርታም ከአንጾኪያ እስክትመጣ በንጹሕ ቦታ አኖሩት በመጣችም ጊዜ ከዚያ ወሰደችው። ውብ ቤተ ክርስቲያንም ሠርታ ሥጋውን በውስጥዋ አኖረች ከእርሱም ታላላቅ
ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ፊቅጦር በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ27 ስንክሳር።
1 161
ሚካኤል ለኃይልከ ኃይለ ሰብዕ ኢይትማሰሎ
ዝርዎሙ ለአጽራርየ እለ ይብሉኒ ንቅትሎ
ፈኒወከ ላዕሌሆሙ ቆባረ ወአውሎ
ሚካኤል ሆይ ኃይልክን የሰው ኃይል የማይመስለው
የሚመክሩብኝን ጠላቶቼን ብለው እንግደለው
በላያቸው ላይ ጭጋግ እና አውሎን ልከክ በትናቸው
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የካቲት ፲፪ (12) ቀን።
❤ እንኳን ለመላእክት አለቃ ለከበረ ለቅዱስ ሚካኤል ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ተልኮ ኃይልን ሰጥቶት ጠላቶቹን ድል እንዲያደርግ ለረዳበት ወራዊ መታሰቢያ በዓል፣ ተጋዳይ ፍጹም የዋሕና ትሑት ለሆነው ለከበረ አባት ለአባ ገላስዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከዶርቃስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የከበረ ቅዱስ ሚካኤልን በዚች ዕለት እግዚአብሔር ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ላከው የፍልስዔም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስከ አደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ ረዳው ኃይልንም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ ከእርሳቸው አንድ ሺህ ሰዎችን ገደለ። ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠለትና አጸናው እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ።
❤ ዳግመኛም ከሚስቱ ጋር ተስማምተው ዐይኖቹን አሳውሩ የራሱንም ጠጒር ላጩ አሠሩትም ከዚያም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን በአዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ወሰዱት በዚያም ሦስት ሽህ ያህል ሰዎች ተሰብስበው ነበር የከበረ ቅዱስ ሚካኤልም ተገለጠለትና ኃይልን መላው የዚያንም ቤት ምሰሶዎች ነቀላቸው ቤቱም በላያቸው ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ገላስዮስ፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምዕመናን ናቸው በጥበብንና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩትና ዲቁና ተሾመ። ከታናሽነቱም ጀምሮ ይህን ዓለም ንቆ ተወ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስንም ቀንበር በመሸከም በምንኵስና ሁኖ በትጋት እየጾመ እየጸለየና እየሰገደ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ እግዚአብሔር መርጦት በአስቄጥስ ገዳም ባሉ መነኰሳት ላይ ቅስና ተሾመ። ተጋድሎውንና አገልግሎቱን እየፈጸመ ሳለ ለአባ ጳኵሚስ እንደ ተገለጠ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና መነኰሳትን ሰብስቦ ፈሪሀ እግዚአብሔርን የምንኵስናንም ሕግ ያስተምራቸው ዘንድ አዘዘው በዚያንም ጊዜ ብዙዎች መነኰሳትን ሰበሰበ መንፈሳዊ የሆ የአድነት ማኅበርራዊ ኑሮንም ሠራላቸው እርሱ በመካከላቸው እንደ መምህር አልሆነም ከእርሳቸው እንደሚያንስ አገልጋይ እንጂ።
❤ ይህ አባት የዚህ ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ የተወ ሆነ እጅግም የዋህና ቸር ሆነ ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍቶችም የተሰበሰበ አንድ ታላቅ መጽሐፍን አጻፈ ለማጻፊያውም ዋጋ ዐሥራ ስምንት የወርቅ ዲናር አወጣ ከርሱ ሊጠቀሙ በሚፈልጉ ጊዜ መነኰሳቱ እንዲያነቡት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአትሮንስ ላይ አኖረው። አንድ መጻተኛ ሰውም አረጋዊ አባ ገላስዮስን ሊጎበኝ በገባ ጊዜ ያንን መጽሐፍ አየውና አማረው በጭልታም ከዚያ ሰርቆ ወጣ ወደ ከተማ ውስጥም በገባ ጊዜ ሊሸጠው ወደደ አንድ ሰውም ዋጋው "ምን ያህል ነው" አለው እርሱም "ዐሥራ ሰባት የወርቅ ዲናር ስጠኝ" አለው። ያ የሚገዛውም ሰው "ያልከውን እሰጥሃለሁ ነገር ግን ለወዳጄ እስካሳየው ታገሰኝ" አለው ያሳየውም ዘንድ ወደ አባ ገላስዮስ ወሰደውና "ተመልከትልኝ መልካም ከሆነ እገዛዋለሁ" አለው አባ ላስዮስም "ያመጣውን ሰው ከአንተ ምን ያህል ፈለገ" አለው "ዐሥራ ሰባት የወርቅ ዲናር" አለው ቅዱስ ገላስዮስም "መጽሐፉ መልካም ነው ዋጋውም ቀላል ነው ግዛው" ብሎ መለሰለት። ወደ ሌባውም በተመለሰ ጊዜ አባ ገላስዮስ የነገረውን ሠውሮ "ለአባ ገላስዮስ አሳየሁት እርሱም ዋጋው በዝቷል አለኝ" አለው፡ሌባውም "ያ ሽማግሌ ሌላ የተናገረህ ነገር የለምን" አለው "አዎን የለም" አለው። ሌባውም "እንግዲህ እኔ አልሸጠውም" ብሎ ወደ አባ ገላስዮስ ሒዶ ከእግሩ በታች ወድቆ ለመነው "ሰይጣን አስቶኛልና ይቅር በለኝ መጽሐፍህንም ውሰድ" አለው የከበረ ገላስዮስም "እኔ መጽሐፉን መውሰድ አልሻም" አለው። ሌባውም በፊቱ እያለቀሰና እየሰገደ ብዙ ለመነው በብዙ ድካምም መጽሐፉን ተቀበለው ማንም ያወቀ የለም። እግዚአብሔር ትንቢት የመናገርን ሀብት ሰጥቶት ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ።
❤ በአንዲትም ዕለት ለገዳሙ መነኰሳት ዓሣ አመጡ ባለ ወጡ ዓሣን አብስሎ በቤት ውስጥ አኑሮ አንዱን ብላቴና ጠባቂ አድርጎ ወደ ሥራው ሔደ ብላቴናውም ከዚያ ዓሣ በላ። ባለ ወጡ በመጣ ጊዜ ተበልቶ አገኘውና በብላቴናው ላይ ተቆጥቶ "አረጋዊ አባቶች፡ ሳይባርኩት እንዴት ደፍረህ በላህ" አለው የቊጣ መንፈስም በልቡ አደረና ብላቴናውን ረገጠው ወዲያውኑ ሞተ እንደሞተም አይቶ ደነገጠ ታላቅ ፍርሀትንም ፈራ ሒዶ ለአባ ገላስዮስ የሆነው ሁሉ ነገረው እርሱም "ወስደህ ከቤተ መቅደሱ ፊት አስተኛው" አለው ሰውየውም እንዳዘዘው አደረገ ወደ ማታ ጊዜም አረጋውያን መነኰሳት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው የማታውን ጸሎት አድርሰው ወጡ አረጋዊ አባ ገላስዮስም በወጣ ጊዜ የሞተው ብላቴና ተነሥቶ በኋላው ተከተለው ከመነኰሳትም ማንም አላወቀም እርሱም የገደለውን ባለ ወጥ ለማንም እንዳይናገር አዘዘው።
❤ የተመሰገነ አባ ገላስዮስም ያማረ ትሩፋቱንና ተጋድሎውን ፈጽሞ አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ይህንንም በጎ መታሰቢያን ትቶ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም የሚለይበት ሲደርስ የካቲት12 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ገላስዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦የየካቲት12 ስንክሳር።
+ + +
❤የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥31-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ እኋልቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"። መዝ 138፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥6-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥9-19 እና የሐዋ ሥራ 38፥30-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 20፥24-29። የሚቀደሰው ቅዱስ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል የቅዱስ ሚካኤልና የአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
@Eotcw
