fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 መዝሙር ዘሰንበት 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወብዙኃን ኖሎት መጽኡ ወስዕኑ ከሢቶታ ለዕብን እምአፈ አዘቅት እስከ ይመጽእ ያዕቆብ ዘክቡት ውስተ ሐቌሁ ዘሀሎ ይሠጎ እምሰብእ ከሠተ ወአስተየ መርዔቶ ወከማሁመ መጽኡ ብዙኃን ነቢያት ወስዕኑ ከሢቶታ ለጥምቀት እስከ ይመጽእ ዓቢይ ኖላዊ እምሰማይ ከሠተ ወአጥመቀ ብዙኃነ አሕዛበ በውስቴታ መንክር ተአምሪሁ ለመድኃኒነ በከመ ወጽአት በትር እምሥርወ ዕሤይ በአምሳለ በትረ ያዕቆብ በዘይርዒ አባግዒሁ ይእቲኬ ማርያም ይእቲ ወበእንተ ዘይቤ ትወጽእ በትር ወየዓርግ ጽጌ ውእቱኬ ዋህድ ውእቱ ውእቱኬ ወልደ አምላክ ውእቱ።

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ከመጋቤ ብሉይ ዮሐንስ እሸቱ ዛሬ በጉባኤው ላሉ ለቅኔ ደቀ መዛሙርት የተበረከተ ቅኔ ሥላሴ ምስጢረ ወለደቶ ከመ በአይነልብ ይርአይ ኩለሄ ህሊና አርድዕት ህፃና ይትራወፅ መንገለ ትርጓሜ ዘጳውሎስ ፍና ወይነስእ ካዕበ በእዱ ቀለመ ሰዋሰው ክዳና እንዘ እንዘ ይትረአይ በትህትና ውስተ ጽርሐ ቤቱ ለያሬድ ጉባኤቃና ድህረ ፀግበ ሰዋስወ መና ጸልዩ በእንቲአየ ወበእንተ ኩሎሙ አርድዕት 🙏🙏

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን ለተጋዳይ ለታላቁ አባት በቀንና በሌሊት ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ከስግደት ጋር እየጸለ ለአርባ ዓመት በገዳም ለኖረውና በኋላም ወደ በረሃ ከአንዲት ታናሽ ዋሻ ውስጥም ገብቶ እየተጋደለ ብቻውን ለኃምሳ ዓመት ለኖረ፤ ሁለት አንበሶች እንደሰው ለሚላኩለት ለባለ አንበሳው ለአባ አውሎግ ለዕረፍት በዓል፣ ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ ለአባት ለአባ በላትያኖስ በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ለአንድ ዓመት ያህል ተሰቃይቶ ኋላም አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለአባ ስልዋኖስ ረድእ ለአባ በትራ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኤጲስቆጶስ ከአባ አብርሃም፣ ከመነኰስ ከአባ መቃቢስና ከኮንቲ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን። + + + ❤ ባለ አንበሳው አባ አውሎግ፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆች ፍጹም በወርቅና በብርም የበለጸጉ ናቸው። በአንዲትም ዕለት "አውሎግ ያለህን ገንዘብህን ሁሉ ሽጠህ ለድኆች ሰጥተህ መከራ መስቀሉን ተሸክመህ ና ተከተለኝ" የሚለውን የከበረ የወንጌልን ቃል አሰበና ወዲያውኑ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ ወደ አባ አውሎጊን ሔደ እርሱም በደስታ ተቀበለው። ስለ እርሱ እንዲህ የሚለውን ራእይ አይቶ ነበር "እነሆ ወዳንተ ጐልማሳ ይመጣል ተቀበለውና ከሚያገለግሉ መነኰሳት ጋር ቀላቅለው"። እየፈተነውም ሦስት ዓመት ያህል ኖረ ፍጹም የሆነ ቅድስናውንም በአየ ጊዜ የምንኵስናን ልብስ የመላእክትንም አስኬማ አለበሰው። ከሰንበትም እስከ ሰንበት እየጾመ በብዙ ተጋድሎ ኖረ ምግቡም እንጀራና ጨው ነበረ በቀንና በሌሊትም ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ስግደት ጋር ይጸልያል በዚህም ተጋድሎ አርባ ዓመት ኖረ። ❤ ከዚያም በኋላ ያሰናብተው ዘንድ መምህሩ አባ አውሎጊንን ማለደውና ወደ በረሀ ሔደ ከአንዲት ታናሽ ዋሻ ውስጥም ገብቶ እየተጋደለ ኃምሳ ዓመት ኖረ። ለፍላጎቱም የሚያገለግሉት ሁለት አንበሶችን እግዚአብሔር ሰጠው በአንዲትም ዕለት ታመመ አንሶቹንም "እጠጣ ዘንድ የሞቀ ውኃ እሻለሁ" አላቸው። አንዱ አንበሳም ወደ ተራራ ሒዶ እረኛ አግኝት ወደ አባ አውሎግ አመጣው በአየውም ጊዜ ሰገደለትና "አባቴ ሆይ ምን ትሻለህ" አለው እርሱም "የሞቀ ውኃ ታጠጣኝ ዘንድ እሻለሁ" አለው እንዳለውም አደረገለት ከዚህም በኋላ አንበሳው እረኛውን ወደ ቦታው መለሰው። ያም እረኛ "ለእግሩ ተረከዝ ዓለሙ ሁሉ መጠኑ የማይሆን ጻድቅ ሰው አገኘሁ" ብሎ ለሰው ሁሉ ተናገረ በሰሙ ጊዜም ሰዎች ሁሉ ወደርሱ ተሰበሰቡ፡ በሽተኞችንም ሁሉ አመጡለትና ፈወሳቸው። ❤ በዚያም ወራትም መምህሩ አባ አውሎጊን ጣዖትን የሚያመልኩ የፋርስ ሰዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት ለመመለስ ወደ ፋርስ አገር ሊሔድ ፈለገ ዳግመኛም ልጁ አውሎግን ከእርሱ ጋር ሊወስደው ወደርሱ መልክተኛ ሊልክ ሽቶ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አንበሳውን አስገነዘበውና አጽፉንና ወንጌሉን አንሥቶ ተሸከመ። አባ አውሎግንም ጒዞን አመለከተው ተነሥቶም አንበሳውን ተከትሎ ወደ መምህር አውሎጊን ደረሰ እርሱም በደስታ ተቀበለው። ሲጓዝም ከጤግሮስ ወንዝ ደረሱ ውኃውም ተከፍሎላቸው ተሻገሩ ወደ አገሩም ውስጥ በደረሱ ጊዜ አስተማሩአቸው ወደ ቀናች ሃይማኖትም መለሷቸውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው። ❤ በአንዲትም ዕለት ደግሞ ቅዱሳን በተራቡ ጊዜ ምግባቸውን ይፈልጉላቸው ዘንድ አባ አውሎግ አንበሶችን አዘዘ ሒደውም እንጀራ በአህያ ላይ ጭኖ የሚጓዝ ሽማግሌ አገኙ ሕፃንም ከእንጀራው ጋር አለ። አህያውንም ወደ ቅዱሳን አመጡት ከድንጋጤም የተነሳ ብላቴናው ሞተ ቅዱሳንም ጸልየው ሕፃኑ ድኖ ተነሣ ቅዱሳንም ተመገቡ አንቦሶችም አህያውን ከእንጀራውና ከሕፃኑ ጋር ወደ ሽማግሌው መለሱት። ❤ ከዚህም በኋላ አባ አውሎግ ወደ በዓቱ ተመለሰና ጥቂት ታሞ የካቲት11 በሰላም ዐረፈ። በታላቅ ክብርም ተቀበረ እነዚያ አንበሶችም መቃብሩን እየጠበቁ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖሩ ከዚያም በኋላ ወደ ዱር ገቡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አውሎግ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። + + + ❤ አባ በላትያኖስ፦ ይህም ቅዱስ ብልህና አዋቂ የሆነ ታላቅ ተጋድሎን የሚጋደል ነው በሮሜ አገርም ሊቀ ጵጵስና ተሹሞ በቅዱስ ጴጥሮስ ወንበር ላይ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሰላም ኖረ ሕዝቡን የቀናች ሃይማኖትን እያስተማራቸው ሳለ መኰንኑ ፊልጶስ በንጉሥ ቀላውዴዎስ ላይ ተነስቶ በገደለው ጊዜ በርሱ ፈንታ ነገሠ በምእመናን ላይ ታላቅ መከራን አመጣ በዚህ በንጉሥ በዳኬዎስ እጅ ብዙዎች በሰማዕትነት ሞቱ። በዘመኑም ሰባቱ ደቂቅ ከእርሱ ሸሹ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ተኝተው ነቁ እርሱም በኤፌሶን ከተማ መስጊድ ሠርቶ በውስጡ ጣዖታትን አኖረ ሰዎችን ሁሉ ለጣዖታት እንዲሠዉ አስገደዳቸው ለጣዖታት ያልሠዉትንም ገደላቸው። ❤ ይህ የከበረ በላትያኖስም የጣዖታት አምልኮን እንደሚቃወም ሕዝቡም በክብር ባለቤት በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ እንደሚያስተምር ንጉሥ በሰማ ጊዜ ወደ ሮሜ አገር ልኮ ወደ ኤፊሶን ከተማ አስመጣውና ለጣዖታት እንዲሠዋ ለመነው። እርሱም ግን ቃሉን አልሰማም ተሣለቀበት አማልክቶቹንም ረገመ እንጂ ንጉሥም ተቆጣ አንዲት ዓመት ያህልም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ የካቲት11 ቀን በሰይፍ ራሱን ቆረጠው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በላትያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። + + + ❤ የአባ ስልዋኖስ ረድእ አባ በትራ፦ ይህም ቅዱስ በደብረ ሲና ካለች በዓቱ በነበረ ጊዜ ትርኅምትን ይጠብቅ ነበር በራትም ጊዜ ለሥጋው የሚያሻውን ይመገባል። ፈርኑ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስ በአደረጉት ጊዜ ትርኅምትን በማብዛት ሰውነቱን እጅግ አደከመ ደቀ መዛሙርቱ "አባታችን ሆይ በገዳም በበአትህ በነበርክ ጊዜ ትርኅምትን እንዲህ አላበዛህም ነበር" አሉት ይህም አባት እንዲህ አላቸው "ያን ጊዜ በገዳም በችግር ውስጥ ነበርኩ ዛሬ ግን ከብዙዎች መካከል በአንድነት አለሁ የምሻውም ሁሉ ብዙ አለኝ ነገር ግን ሥጋዬን ቀጥቼ ብገዛው ይሻላል" እንዲህም እየተጋደለ ኖረ ከዚህም በኋላ የካቲት10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በትራ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 11 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለበትራ ረድአ ስልዋኖስ ወምእኑ። ኤጲስቆጶሰ ዘኮነ በሀገረ ፈርኑ። ከመ እንግር ጽድቆ ወኂሩቶ እዜኑ። ለአፉየ ወልሳንየ በመጠኑ። ዘይረድአኒ መንፈሰ ይፈኑ"። አርከ ሥሉስ (አርኬ) የካቲት 11። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ ዚአየ ውእቱ ኵሉ አራዊተ ዘገዳም። እንስሳ ገዳምኒ ወአልሕምት። ወአአምር ኵሎ አዕዋፈ ሰማይ"። መዝ 49፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 4፥14-19፣ ያዕ 3፥5-11 እና የሐዋ ሥራ 14፥19-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ማር 1፥12-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችን ይሁንልን።

photo content
+2

❤ በአገሮችም ያሉ ሰዎች ስርሱ በሰሙ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ተማክረው ከኤጲስቆጶሳቱ ጋር ተስማሙ። በሌሊትም ወጥቶ ሸሸ ወደ ፈርማ ገዳም ደርሶ በዚያ መነኰሰ ከዚያም ወጥቶ ወደ አንዲት አነስተኛ ወሻ ገብቶ ብቻውን በውስጧ ብዙ ዘመናት ኖረ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ ከእርሳቸውም ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንት የደረሳቸው አሉ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍቶችን ብሉያትና ሐዲሳትን ተረጐመ። የመጻሕፍትም ቊጥራቸው ዐሥራ ስምንት ሺህ ነው እሊህም ድርሳናት ተግሣጻት ጥያቄዎችና መልሶች ወደ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት የተላኩ መልክቶች ናቸው ወደ ምእመናንም ወንዞች ውኃዎችን እንደሚያፈልቁ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ የሚያፈልቃቸው ሆኗልና። ❤ ይህንንም በጎ ሥራውን ሲፈጽም መልካም ጉዞውንም አከናውኖ ወደ በጎ ሽምግልና ደርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ የካቲት10 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኤስድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። + + + ❤ የፋርስ አገር ኤጲስቆጶስ አባ ፊሎ፦ ይህንንም ቅዱስ ለእሳት እንዲሠዋ ለፀሐይም እንዲሰግድ የፋርስ ንጉሥ አዘዘው እምቢ በአለውም ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይቶ የካቲት10 ቀን ራሱን በሰይፍ ቆረጠው በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊል ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይገባል አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት10 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ዕረፍተ ስሙ ጽዑጠ። እምብዝኀ ገድሉ እንዘ እንግር ኅዳጠ። ዐሠረ ክርስቶስ ይትሉ ሶበ ዮስጦሳ ተፈልጠ። መንገለ ወልዱ ወብእሲቱ ገጾ ኢሜጠ። ወአፍቅሮ ዘመድ ካዕበ በልቡ ኤሦጠ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 10። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦"አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 3፥8-ፍ.ም፣ 2ኛ 1፥8-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 10፥36-49። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥1-9። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ ሐዋርያት ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ለአንዱ ለእልፍዮስ ልጅ ለከበረ ሐዋርያ ለቅዱስ ያዕቆብ በንጉሥ ቀላውዴዎስ ዘመን በአይሁድ እጅ በድንጋይ ተወግሮ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለኢትዮያዊያኑ ጻድቅ ለአቡነ እንድርያስ ኤርትራ አገር የሚገኘው ታላቁ ገዳም ደብረ ጽጌ ሰፍኣ ለመሰረቱ ለዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ደቀ መዛሙርቶች በአረማውያን እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል (ታሪካቸውን የካቲት1 ይመልከቱ)፣ ለንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ለከበረ ለቅዱስ ዮስጦስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ፈርማ ከሚባል አገር በገድል ለተጠመደ ምሁር ለሆነ ዐሥራ ስምንት ሺህ መጽሐፍቶችን ተግሣጻትና ድርሳናት ለጻፈ ለዓለሙ ሁሉ መምህር ለአባ ኤስድሮስ ለዕረፍት በዓልና ለፋርስ አገር ኤጲስቆጶስ ለአባ ፌሎ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ ቅዱሳን ከኒቅላዎስና ከስምዖን ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ፦ ያስተምር ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ እንዲህ ሆነ። ከእርሱ ለሚሰሙትም ሁሉ ብዙ ተአምራትን አደረገ። ንጹሕ በሆነ ልቡናም በእግዚአብሔር አመኑ። ራሳቸውንም አጸኑ። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብም በልቡናው አሰበ። እንዲህም አለ። ሕዝቡ ከእርሱ ሰምተው እንዴት ያምናሉ አለ። እርሱም ሕዝቡ ወደተሰበሰቡበት ወደ ምኩራብ ገባ። ከአይሁድም የተቀመጡ የተሰበሰቡ ብዙ ሰዎችን አገኘ። በፍጹም ታላቅ ደስታ ያስምራቸው ዘንድም በመካከላቸውም ገባ። ለሁሉም በቃሉ ማስተማሩን አበዛ። ያለመፍራትም ሃይማኖቱን ገለጠ። አንድ ለሆነው ለእግዚአብሔር ልጅ ምስክር ሆነ። "የሕይወት ቃል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ አምላክ ነው። በእውነትም የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እርሱ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ ከአብ ጋር ነበርና። እርሱ በአብ አለ፤ አብም በእርሱ አለ። እርሱ የአብ ቃል ነው። እርሱ ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር አለ። እርሱ በሰማይ አለ። እርሱ ከአባቱ ጋር አለ። እርሱ በኪሩቤል ሰረገላ ይቀመጣል። ሱራፌልም ያመሰግኑታል። እርሱ በድንግል ማርያም ማሕፀን የተወሰነ በልዕልና በገናንነቱ ሥልጣን ነው። እርሱ ድንግል ማርያም የወለደችው ጌታችን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰው የሆነ አምላክ ነው"። አንድ ሰው ስንኳን ሳይፈራ በተሰበሰቡት መካከል የሐዋርያው ምስክርነት ይህ ነበር። በእውነት አንድ ለሆነው ለእግዚአብሔር ልጅ ልደትም ምስክር ሆነ። እርሱ ነበርና። በሞቱም፣ በትንሣኤውም፣ ወደ አባቱ ወደ ሰማይ ስለማረጉም ምስክ ሆነ። ለተሰበሰቡትም በክርስቶስ ስለማመን አስተማራቸው። ❤ የተሰበሰቡትም የሐዋርያውን ትምህርት በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ጋር ካለው ከአባታቸው ከሰይጣን የተነሳ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ላይ ፈጽመው ተቆጡ። ሁሉም ተሰብስበው ተቀመጡ። የተሰበሰቡት ሁሉ ደሙን ፈለጉ። ነገሩን የሰሙትም የተባረከ ሐዋርያን ያዙት። ከንጉሥ ከቀላውዴዎስም ወሰዱት። የሐሰት ምስክሮችንም በእርሱ ላይ አስነሡ። ለንጉሡም "ይህን ጥፋተኛ ሰው በሀገሩ በአውራጃው ይዘናል" አሉት፤ "እኔ የእግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነኝ ይላቸዋል። ለንጉሡ እንዳይገዙም ይከለክላል" አሉት። ስለተባረከው ሐዋርያ ይህን ነገር በሰማ ጊዜም እስከሚሞት ድረስ በድንጋይ ይወግሩት ዘንድ አዘዘ። አይሁድንም እግዚአብሔር ረገማቸው። ንጉሡ አይሁድን እንዳዘዛቸውም በድንጋይ ወገሩት። ከዚህ በኋላ ቡሩክ የሚሆን የእልፍዮስ ልጅ የሐዋርያው የቅዱስ የያዕቆብ ምስክርነት የካቲት ዐሥር ቀን ሆነ። በኢየሩሳሬም ቤተ መቅደስ ተቀበረ። ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይገባል። ከሐዋርያው ከቅዱስ ያዕቆብ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ገድለ ሐዋርያት። + + + ❤ "ሰላም ለጌርስጦስ (ለዮስጦስ) ወአቦሊ፡ ወልዱ"። ትርጉም፦ ለልጁ ለአቦሊና ለጌርስጦስና (ለዮስጦስ) ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ የንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮስጦስ፦ ይህም ቅዱስ በጦር ሜዳ እያለ እኅቱ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስን አግብታ ንጉሥም አደረገችው ከጦርነትም በተመለሰ ጊዜ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ አገኘውና እጅግ አዘነ። የአገሩም ሰዎች በአዩት ጊዜ ወደርሱ ተሰብስበው ዲዮቅልጥያኖስን "እኛ እንገድለዋለን አንተም ጌታችን በመንግሥትህ ዙፋን ላይ ትቀመጣለህ" አሉት እርሱ ግን ይህን ስለአልፈለገ እንዳይገድሉት ከለከላቸው ከምድራዊት መንግሥት ሰማያዊት መንግሥትን መርጧልና። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ቀርቦ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉሡም ፈርቶታልና "ጌታዬ ዮስጦስ ሆይ ይህን ታደርግ ዘንድ ያስገደደህ ማነው?" አለው የከበረ ዮስጦስም "በምስክርነቴ ደሜን እንዳፈስ ካልጻፍክ ሕዝቡን በአንተ ላይ አስነሥቼ ከመንግሥትህ እንደማስወጣህ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ነው" ብሎ ማለ። በዚያንም ጊዜ ንጉሡ ፈርቶ ከሚስቱ ከታውክልያ ከልጁ ከአቦሊ ጋር ወደ ግብጽ አገር እንዲወስዱአቸው አዘዘ የእስክንድርያንም ገዥ አብዝቶ እንዲሸነግላቸው ምናልባት ልባቸው ቢመለስ እንዳያሳዝናቸውም አለዚያ እያንዳንዱን እንዲለያያቸው አዘዘው። ❤ ወደ ግብጽ አገርም በደረሱ ጊዜ ከእርሳቸው ጋር የንጉሥ ደብዳቤ አገልጋዮችም አሉ። የእስክንድርያም ገዥ በአያቸው ጊዜ እጅግ ፈራ ሊሸነግለውም ጀምሮ ቅዱስ ዮስጦስን "ጌታዬ እንዲህ አታድርግ ክብርህ ይሻልሃል" አለው የከበረ ዮስጦስም "ነገር አታብዛ" አለው መኰንኑም ፈርቶ ቅዱስ ዮስጦስን ወደ ላይኛው ግብጽ ወደ እንዴናው ከተማ ሰደደው ልጁ አቦሊን ወደ አገረ ብስጣ ሚስቱ ታውክልያን ወደ አገረ ፃ ላካቸው ከአገልጋዮቹም የሚአገለግሏቸው አንዳንድ ሰጣቸው የከበረ ዮስጦስንም በእንዴናው ከተማ ብዙ ከአሠቃዩት በኋላ የካቲት10 ቀን ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ለበሽተኞችም ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕትነት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ ኤስድሮስ ዘአገረ ፈርማ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በምስር አገር የከበሩ ባለጸጎች ናቸው ለእስክንድርያ ሊቀነ ጳጳሳትም አባ ቴዎድሮስና አባ፡ ቄርሎስ ዘመዶች ናቸው ከእርሱም በቀር ልጅ የላቸውም መንፈሳዊ ትምህርትን ሁሉ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ሁሉ አስተማሩት ግልጽ አድርጎ አጠናቸው ጠበቃቸውም ዳግመኛም የዮናናውያንን የፍልስፍና ትምህርት የከዋክብትን አካሔድና ዓለምን መዞራቸውን ተማረ በእውቀቱና በጥበቡም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ በገድልም የተጠመደ ትሑትና የሚተጋ ሆነ።

ጉባኤ ቃና ዘወልደ ሐና ዘዲ/ን የአብስራ ወዲ/ን ቃለ አብ ጸብሐ ገሞራ ኢይቅረብ ለፀዋሚ ሀገረነነዌ መርድዕ እስመ በውስቴታ ተወድየ ነበልባለ ባቢሎን ቅብዕ ሰም፦ የገሞራ ወጥ ለሚፆም ለተማሪ ሀገረ ነነዌ አይቅረብ ለምን በውስጡ የባቢሎን እሳት ቅቤ ተጨምሮበታልና አይቅረብለት ወርቅ፦ ለሚፆም ሰው ቅቤ ያለው ወጥ እንደማይቀርብ ሁሉ በወጥ የተመሰለው ገሞራ ሲሆን በሰዶም እና በገሞራ በኃጢያታቸው ምክንያት እሳት ስለዘነበባቸው ከዚያ አንፃር ሲሆን የባቢሎን እሳትም በቅቤ የተመሰለው በዚሁ አንፃር ነው በባቢሎን ለሠለስቱ ደቂቅ የነደደውን እሳት ልብ ይሏልና ነው። በዚህም ቅኔ ላይ ሀገረ ነነዌ በሚፆም ተማሪ ሲመሰል እሳት በቅኔ ተመስሎ ወጡ ደግሞ እሳት በዘነበባት በሀገረ ገሞራ ተመስሎ ሲቀርብ ዋናው የቅኔ ጭብጥም የነነዌ ሰዎች በመፆማቸው ሊዘንብባቸው የነበረው እሳት እንደቀረላቸው ተመስጥሯል። ሙያ ፀብህ.......የቅኔ ባለቤት ገሞራ........የፀብህ ዘርፍ ኢ........አሉታ ሙያው አፍራሽ ይቅረብ.......ማሰሪያ ይስባል እንጂ አይሳብም ለ......አገባብ ፍቺው በቁም ቀሪ ሙያው ምስጢር አቀባይ ፀዋሚ........የሀገር ቅፅል ሀገር መርድዕ ......ምሳሌ መርድዕ ሰም ሀገር ወርቅ ተመስሎ የቅኔ ባለቤት ነነዌ.......የሀገር ዘርፍ እስመ........አገባብ ፍቺው ና ሙያው አስረጅ አስረጅነቱ ለይቅረብ በ......አገባብ ፍቺው በቁም ቀሪ ሙያው ማድረጊያ ውስቴታ......የማድረጊያ ባለቤት ነበልባል ቅብዕ ምሳሌ ቅብዕ ሰም ነበልባል ወርቅ ተመስሎ የአስረጅ ባለቤት ባቢሎን.......የነበልባል ዘርፍ

ሃይማኖታችንን እንወቅ ይህ ግሩፕ የተመሠረተው ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያለን እንድንጠያየቅ ነው ግሩፕን ሼር በማረግ ተባበሩን https://t.me/haymamot125

photo content
+1

በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም የሚደርስበትን ሥቃይ ሁሉ ነገረው "እነሆ ከአንተ ጋር እንድኖር እንዳጸናህም እግዚአብሔር አዞኛልና አትፍራ" አለው። ❤ በዚያንም ጊዜ ተነሥቶ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ በመኰንኑም ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ልብሱን አራቁተው ይገርፋት ዘንድ አዘዘ። ይህንንም አደረጉበት ከዚህም በኋላ በጐኖቹ ውስጥ መብራቶችን አስገብተው ለበለቡት እሳት ግን አልነካችውም መኰንኑም ለጣዖት እንዲሰግድ ብዙ ገንዘብ አመጣት የተመሰገነ ጳውሎስም "ወላጆቼ ሲሞቱ ዐሥራ ሰባት የወርቅ መክሊት ትተውልኝ ነበር። ስለ ክብር ባለቤት ክርስቶስ ፍቅር ትቼ ለድኆች መጸወትኩት ወደዚህ ወደተናቀ ገንዘብህ እንዴት እመለሳለሁ" አለው። ❤ መኰንኑም ሰምቶ ብረቶችን በእሳት አግለው በአፉና በጆሮዎቹ እንዲጨምሩ አዘዘ ይህንንም አደረጉበት ሱርያል መልአክም ወርዶ ዳሠሠውና አዳነው ሁለተኛም እባቦችን በላዩ ሰደዱ አልነኩም ምላሱንም ቆረጡ ጌታችንም አዳነው። መኰንኑም ወደ እስክንድርያ ከተማ በሚሔድ ጊዜ ከእርሱ ጋር ወሰደው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመርከብ ውስጥ ተገለጠለትና አጽናናው የዚህም ቅዱስ ኤሲም የሚባል ወዳጅ አለው እኅቱ ቴክላም። በጌታችንም ሥጋው ከሥጋቸው ነፍሱ ከነፍሱሳቸው ጋር እንደሚሆን ነገረው ያን ጊዜ እሊህ ቅዱሳን በእስክንድርያ ከተማ በእስር ቤት ነበሩ የከበረ ጳውሎስም ወደርሳቸው በደረሰ ጊዜ እርስበርሳቸው ተሳሳሙ በመገናኘታቸውም ነፍሳቸው ደስ ብሏት እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ❤ መኰንኑም ወደ እንዴናው ከተማ በሚመለስ ጊዜ የቅዱስ ጳውሎስን ራስ ቆርጠው ሥጋውን ከጥልቅ ባሕር ወረወሩ የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ ምእመናንም ሥጋውን በሥውር ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት በእርሱም ዘንድ አኖሩት ከእርሱም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በቅዱስ ጳውሎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት9 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለጳውሎስ ቅሡፈ ዘባን በተጠብጥቦ። ወበመኃትወ ነድ ውዑየ ገቦ። ሱርያል መልአክ እንዘ ይሜግቦ። በድሮ ፈጺሞ ወሃይማኖቶ ዐቂቦ። ዘምስለ ኤሲ ወቴክላ ተወፈየ ዐስቦ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 8። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ኵሉ ማዕበልከ ወሞገድከ እንተ ላዕሌየ ኃለፈ። ዓልተ ይኤዝዝ እግዚአብሔር ሣህሎ ወሌሊተ ይነግር። እምኀቤየ ብፅዐተ ሕይወትየ ለእግዚአብሔር"። መዝ 41፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥1-6፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 14፥21-24። የሚበበው ወንጌል ማቴ 16፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @EOTCW

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን ለከበረ በሶርያ አገር ላሉ መነኰሳት አባት ለሆነ እንደ ኢያሱ ፀሓይን ገዝቶ ላቆመ፣ ዝናብንም በጸሎቱ ላዘነበ፤ ሳይቀመጥ ሃምሣ አራት ዓመት ቁሞ ለኖረ ለታላቁ አባ በርሱማ ለዕረፍት በዓልና ለከበረ ለሶሪያዊ ከሃድያን ይዘው ምላሱን በመቁረጥ፣ በእሳት በማቃጠል፣ የብረት ችንካሮችን በእሳት አግለው በአፉና በጆሮዎቹ ለቸነከሩበትና በመጨረሻውም አንገቱን ለሰየፉት ለቅዱስ ጳውሎስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከከበረ ሰማዕት ከቅዱስ ጴጥሮስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ በርሱማ ዘሶርያ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ሳሚሳጥ ከሚባል አገር ሰዎች ውስጥ ናቸው አንድ በዋሻ ውስጥ የሚኖር ሰው በእርሱ ላይ ትንቢትን ተናገረ ከመወለዱ አስቀድሞ ለአባቱ እንዲህ አለው "የትሩፋቱ ዜና በሶርያ አገር ሁሉ የሚሰማ ጣዕም ያለው ፍሬ ከአንተ ይወጣል ከእርሱ የሚሆነውንም አሰረዳው"። ተወልዶም አድጎ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ በደረሰ ጊዜ ወላጆቹን ሸሽቶ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ደርሶ በዚያ ስሙ አብርሃም ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጠ እርሱም ወላጆቹን ስለፈራ ኪዚያ ገዳም ሰደደውና ሒዶ በአለት ውስጥ ኖረ በዚያም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ወሬውም በሶርያ አገሮች ሁሉ በተሰማ ጊዜ ብዙዎች ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ የዚያ ቦታ ውኃ ግን እጅግ መራራ ነበር በላዩ በጸለየ ጊዜ ተለውጦ ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቅች ተአምራቶችን አደረገ ከእርሳቸውም በአንዲት ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከበአቱ ርቆ ሳለ የፀሓይ መግቢያ ሰዓት ተቃረበ የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ወደ በአቱም እስቲደርስ ያን ጊዜ ፀሓይን አቆመለት። ❤ በሌላም ጊዜም እንዲህ ሆነ ረዓም የምትባል አገር ነበረች ሰዎቿም ከሀዲዎች ናቸው በላያቸውም ዝናብ ተከለከለ በተጨነቁም ጊዜ ወደ ከበረ አባ በርሱማ መጥተው ለመኑት እርሱም ገሠጻቸው እንዲህም አላቸው "ከክህደታቸሁ ተመልሳችሁ በእግዚአብሔር ብታምኑ እርሱ ብዙ ዝናብን ያወንብላችኋል" እነርሱም "እናምንበታለን አሉት"። በዚያን ጊዜ ጌታችንን ለመነውና ብዙ ዝናብ ዘነበላቸው የአገሩ ሰዎችም ሁሉ በጌታችን አመኑ። እዲሁም ሰዎቿ ከሀድያን የሆኑ ሌላ አገር ነበረች እነርሱንም ገሥጾ መክሮ አስተምሮ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የጣዖቶቻቸውንም ቤቶች አፈረሰ። ❤ ይህም ቅዱስ ለራሱ ቦታ አዘጋጅቶ በዚያ ሳይቀመጥ ሃምሣ አራት ዓመት ቁሞ ኖረ ከመትጋት የተነሣ ሲደክመው ከናሱ ግድግዳ ላይ ተደግፎ ያሸልባል በየሰባት ቀንም ይጾማል። የከበረ አባ ስምዖን ዘዓምድ ሊያየው ወዶ ወደርሱ ላከ የትሩፋቱንና የቅድስናውን ዜና ከብዙዎች ሰዎች ሰምቶ ነበርና እርሱም ወደ አባ ስምዖን መጥቶ እርስበርሳቸው በረከትን ተቀባበሉ ከዚያም በኋላ ወደ ገዳሙ ተመለሰ። በሶርያም አገርም አስተማረ በፊታቸው ተአምራትን በአደረገ ጊዜ በትምህርቱ ብዙዎች አመኑ። ዳግመኛም ወደ ታናሹ ቴዎዶስዮስ ንጉሥ ሒዶ በቀናች ሃይማኖት አጸናው ንጉሡም ብዙ ገንዘብን ሰጠው እርሱ ምንም ምን አልወሰደም በአንጾኪያም አገር በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዲኖረው ንጉሥ ጻፈለትና ኀቲም ቀለበትን ሰጠው። ❤ በከሀዲው ንስጥሮስ ምክንያት ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት በኤፊሶን ከተማ በተሰበሰቡ ጊዜ ከእሳቸው ጋር ይህ ቅዱስ አለ። ከእርሳቸውም ጋር ንስጡርን አወገዘው ዳግመኛም በአንጾኪያ አገር ያሉ መኳንንት መሳፍንትን ሹማምንት ሁሉም ይታዘዙለት ዘንድ ንጉሥ ደብዳቤን ጻፈለት እርሱም በጎ ሥራ እንዲሠሩ በሃይማኖት እንዲጸኑ የሚያዝዝ ደብዳቤ በመጻፍ በንጉሥ ኀቲም ቀለበት እያተመ ለአገሮች ሁሉ የሚልክ ሆነ። ክፋዎች ሰዎችም ጠሉት በንጉሥም ዘንድ ነገር ሠሩበት እንዲህም አሉት" እሆ አባ በርሱማ እንደ ዓለም ሰው ሁኖ ይበላል ይጠጣል መልካም ልብስንም ይለብሳል" ንጉሥም ስለ አባ በርሱማ የተነገረውን ያረጋግጥ ዘንድ ከባለሟሎቹ አንዱን ላከ። የንጉሡም ባለሟል ወደ አባ በርሱማ በደረሰ ጊዜ በእርሱ ላይ ከተነገረው ምንም ምን ያገኘው የለም ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ወሰደው ንጉሥም ቀድሞ ከሚያውቀው ከመንፈሳዊ ሥራው ልውጥ ሁኖ ያገኘው ነገር የለም ንጉሡም ታላቅ ክብርን አከበረው ወደ ቦታውም መለሰው። ❤ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያንም የኬልቄዶንን ጉባኤ በሰበሰበ ጊዜ የንጉሥ አማካሪዎች አባ በርሱማን እንዳያስመጣ ንጉሡን መከሩት እንደማይፈራና እንደ ማያፍር በሰው ፊትም እንደማያዳላ ተከራክሮ ረትቶ እንደሚሳፍራቸውም ስለሚያውቁ ነው። አንዱ ክርስቶስ ወደ ሁለት የከፋፈሉበት ይህ ጉባኤ በተፈጸመ ጊዜ የከበረ አባ በርሱማ ተጣላቸው ነቀፋቸው ቃላቸውንም በመሻር አወገዛቸው እርሱም ወደ ንጉሥ ወንጅለው በጽሑፍ ከሰሱት ንጉሡም ልኮ ወደርሱ አስቀረበው ግን በላዩ ስለ አደረ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሊቃወመው አልቻለም በሊቁ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ ስለ አደረገው ክፋት ንግሥቲቱን ረገማት ከጥቃት ቀንም በቀር አልኖረችም በክፉ አሟሟትም ሞተች። ከዚህም በኋላ መናፍቃን የሚቃወሙት ሆነ ምእመናን እንዳይታዘዙለት ወደ ሀገሮች ሁሉ ጽፈው የሚልኩ ሆኑ እነርሱ ግን አልተቀበሏቸውም እርሱ መታዘዛቸውንም አልተዉም። ዳግመኛም በጐዳና ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ ሁለት መቶ መናፍቃን ሰዎች ከመናፍቃን ኤጲስቆጶሳት ጋር ተስማምተው ወደ እርሳቸው እንዲመጣና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሚሔዱ ሁነው ላኩበት መጥቶም አብሮ በተጓዘ ጊዜ ደንጊያዎችን አንሥተው ጣሉበት ደንጊያዎታቸውም ወደ ራሳቸው የሚመለሱ ሆኑ በፍርሃትም ከእርሱ ሸሹ። ❤ እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም እሥረኛነት ሊአወጣው በወደደ ጊዜ መልአኩን ወደርሱ ልኮ ከአራት ቀን በኋላ ከዓለም እንሚፈልስ ነገረው በዚያንም ጊዜ በዙሪያው ወዳሉ አገሮች ምእመናንን ያጽናናቸው ዘንድ ረድኡን ላከው እርሱም ሲዞር የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ ወደምትኖርበት ቦታ ደረሰና የከበረች የቅዱስ ዮሐንስን ራስ እጅ ነሣት ስለ ከሀዲው ስለ ንጉሥ መርቅያን በማልቀስ ለመነ። እንዲህ የሚልም ቃል ከመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ወጣ " አባ በርሱማ ወደ እግዚአብሔር ስለ ከሰሰው ያ መርቅያን ሙቷልና አትፍራ"። የከበረ አባ በርሱማ ረድኡን ባረከው የካቲት9 በሰላ አረፈ። ከበአቱም ደጃፍ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታየ። ምእመናንም ሁሉ ከሩቅ አይተው ወደርሱ መጡ አርፎም አገኙት። ከሥጋውም ተባረኩ በላዩም አለቀሱ ከእርሱም ስለመለየታቸው እጅግ አዘኑ እደሚገባውም እየዘመሩና እያመሰገኑ ገንዘው በመቃብር አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በርሱማ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት9 ስንክሳር። + + + ❤ ሶርያዊው ሰማዕቱ ቅዱስ ጳውሎስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ የሶርያ ሰዎችና በእስክንድርያ ከተማ የሚኖሩ ነጋዴዎች ናቸው ከዚህም በኋላ በእስሙናይን ከተማ የሚኖሩ ሆኑ። ወላጆቹም ሲሞቱ ብዙ ገንዘብ ተውለት ከዚህም በኋላ ከሀድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቶስ የሚያምኑ ምእመናንን እንደሚያሠቃዩአቸውና እንደሚገድሏቸው ሰማ በዚያንም ጊዜ ተነሥቶ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በተነ። ከዚያም በኋላ የወደደውን መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ ጌታችንም መልአኩን ሱርያን ላከ እርሱም

🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵 ሥርዓተ ማኅሌት ዘየካቲት ኪዳነ ምሕረት 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ" ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል። @EOTCW መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። @EOTCW @EOTCW ዚቅ ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውልደ ስብእ፤ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኃኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኃኒተ ኵሉ ዓለም፤ ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት። @EOTCW ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። @EOTCW ዚቅ ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዶ ፍኖተ፤ ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ፤ መድኃኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ። @EOTCW @EOTCW ወረብ ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ ማርያም ድንግል/፪/ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን/፪/ @EOTCW መልክአ ኪዳነ ምሕረት ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማሰልዎ በኮከብ፤ ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤ ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኃኒት ዘዐርብ፤ ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ኅሊና ቀዳማይ አብ፤ አመ እምገነቱ ተሰደ በኀዘን ዕፁብ። @EOTCW ዚቅ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም፤ አመ ይሰደድ እምገነት። @EOTCW ወረብ አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አንቲ ውእቱ/፪/ አመ ይሰደድ እምገነት/፬/ @EOTCW @EOTCW መልክአ ኪዳነ ምሕረት ሰላም ለአዕዛንኪ እለ ተበስራ ኪዳነ፤ እምአፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤ አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ፤ እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ፤ ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ። @EOTCW ዚቅ ኪዳንኪ ኮነ ለኃጥአን ቤዛነ፤ ኪዳንኪ ኮነ ኪዳንኪ ኮነ፤ ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ። @EOTCW ወረብ ኪዳንኪ ኮነ/፮/ ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ/፬/ @EOTCW @EOTCW መልክአ ኪዳነ ምሕረት ሰላም ለመዛርዕኪ ወለኲርናዕኪ ምፅንጋዕ፤ እለ ሐቀፋሁ ለክርስቶስ ባሕርየ መለኮት ኅቡዕ፤ ማርያም ኅሪት እምነ መላእክት ወሰብእ፤ ተዝካረኪ ለእመ ገብረ በተአምኖ ጽኑዕ፤ በመንግሥት ሰማይ ምስሌኪ ይነግሥ ኃጥእ። @EOTCW ዚቅ አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን፤ ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን፤ ምስለ አባግዕ ቡሩካን። @EOTCW ወረብ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን አመ ይነግሥ ወልድ/፪/ ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን/፪/ @EOTCW ዓዲ (ወይም) ዚቅ መፍትው እንከ ንወድሳ ወንግበር ተዝካራ፤ ለቅድስት ድንግል ዓፀደ ወይን፤ መሶበ ወርቅ እንተ መና። @EOTCW መልክአ ኪዳነ ምሕረት ሰላም ለመልክዕኪ እመልክዐ ሐና ወኤልሳቤጥ፤ ዘብዑድ ስኑ ወልምላሜሁ ፍሉጥ፤ ማርያም ድንግል ድንግልተ፧ አፍአ ወውስጥ፤ ቤዛ ይኩነኒ ኪዳንኪ በገጸ ፈጣሪ ሥሉጥ፤ አመ ወርኀ ነጊድ የኃልቅ ወይጸራዕ ሤጥ። @EOTCW ዚቅ ቃለ እግዚአብሔር እምድንግል አስተርአየ፤ ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ፤ እስመ ወለደት ነቢየ። @EOTCW @EOTCW ወረብ እምድንግል አስተርአየ ቃለ ቃለ እግዚአብሔር/፪/ ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ"እስመ ወለደት ነቢየ"/፪/ /፪/ @EOTCW አንገርጋሪ ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ። @EOTCW አመላለስ 'አማን በአማን'/፪/ ኪዳንኪ 'አማን በአማን'/፪//፩/ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ/፬/ @EOTCW ወረብ ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ/፪/ አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ ምሥራቅ ደብረ ሕይወት/፪/ @EOTCW እስመ ለአለም ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዶ ፍኖተ፤ ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ፤ መድኃኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ። 👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 🌺 ሥርዓተ ዋዜማ ዘየካቲት ኪዳነ ምሕረት 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ዋዜማ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ርግብየ ይቤላ በእንተ የውሃታ፤ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ፤ ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤ ዳዊት ይሴብሕ፤ ወይዜምር ዕዝራ። @EOTCW ምልጣን እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ፤ ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ፤ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ። @EOTCW @EOTCW አመላለስ፦ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ/2/ ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ/4/ @EOTCW @EOTCW በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ ሰአሊ ለነ ማርያም፤ እንተ እግዚእ ኃረያ፤ ሰአሊ ለነ ማርያም። @EOTCW @EOTCW እግዚአብሔር ነግሠ እንተ ክርስቶስ በግዕት፤ እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤ በቤተ ልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ፤ ግሩመ ወለደት። @EOTCW @EOTCW በ፭ እግዚኦ ጸራሕኩ ኀቤከ ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን፤ ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን፤ ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን። @EOTCW ይትባረክ እግዝእትየ እብለኪ፤ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ። @EOTCW @EOTCW ሰላም ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ የሐንፁ አሕዛብ አረፋትኪ በዕንቊ ክቡር፤ ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ፤ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር በእንተ ዕበየ ክብርኪ፤ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ፤ ዘአድኃነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤ ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ። @EOTCW አመላለስ፦ ዘአድኃነኪ እምእደ ጸላዕትኪ እምእደ ጸላዕትኪ/2/ ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ/4/ 👇👇👇👇👇🇪🇹 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 👉@EOTCW👈 🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹 @EOTCW #Join & share

ሃይማኖታችንን እንወቅ ይህ ግሩፕ የተመሠረተው ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያለን እንድንጠያየቅ ነው ግሩፕን ሼር በማረግ ተባበሩን https://t.me/haymamot125

photo content
+2

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ የዕለቱ እግ.ነግ ዓራራይ ዜማ፦ "በቤተ ልሔም ተወልደ ወበናዝሬት ተሐፅነ ወስምዖን ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ ዳዊት ዘመሮ ወዮሐንስ ለንጸሮ ለሙሴ ገሃደ ተናገሮ"። ትርጉም፦ በቤተ ልሔም ተወለደ በናዝሬትም ሰገደ ስምዖን ተቀበለ (ሰብአ ሰገል) ሰገዱለት ልደቱ በእርግጥ ሆነ ዳዊት ዘመረለት ዮሐንስ ተመለከተው ለሙሴ በግልጥ ተናገረው። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለስምዖን ካህን ለወልደ እግዚአብሔር በእንግድዓሁ ዘተወክፎ፤ ለነበልባል ግሩም ሣዕር ድኩም ዘለከፎ"። ትርጉም፦ ደካማ ሣር ሲኾን የሚያስፈራ ነበልባልን ለነካው የእግዚአብሔርን፡ልጅ በደረቱ የተቀበለው ለኾነ ለካህኑ ስምዖን ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። @Eotcw

photo content

❤ ዳግመኛም አባቴ ሆይ "ለምን እግዚአብሔር ልጅ አልሰጠኝም" አለው አረጋዊውም "በምድር ላይ ሃይማኖት የሚከፋፈልበት ዘመን ይመጣል ከመናፍቃን ጋር አንድ እንዳይሆን ስለዚህ እግዚአብሔር ልጅን አልሰጠህም" አለው። ንጉሡም ብዙ ገንዘብን ሊሰጠው ወደደ እርሱ ግን አልተቀበለም። ወደ በአቱም እስተመለሰ ድረስ እህል እንዳልቀመሰ ስርሱ ተነገረ የካቲት8 ቀን በሰላምም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኤልያስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅድስት አመተ ክርስቶስ፡- ይህችውም ቅድስት ከቍስጥንጥንያ አገር የተገኘች ታላቅ እናት ናት፡፡ ከአገሪቱም የንጉሡ መሳፍንቶች ውስጥ አንዱን አግብታ ስትኖር ባሏ ሞተባት፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ ከመንግሥት ታላላቆች ውስጥ አንዱ ሊያገባት በፈለገ ጊዜ "ጽኑ ደዌ አለብኝና ትንሽ ጠብቀኝ" ብላው በማግሥቱ ንብረቷን ሁሉ ለድኆች መጽውታ ሁለት አገልጋዮቿን ይዛ በሌሊት ወጥታ ሄደች፡፡ ከኮረብታ በታች በሚገኝ በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብታ በዚያ 11 ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ ❤ ምግቧንም አእዋፋት የዕፅዋትን ፍሬ እያመጡላት እርሱን ከአገልጋዮቿ ጋር ትመገብ ነበር፡፡ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘመን አንዱ መኰንን ግብር ሊሰበስብ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ሄዶ ወደ አንድ ገዳም ደረሰ፡፡ መነኮሳቱም በፍቅር ተቀብለው አስገቡት፤ ከእነርሱ ጋር ሆኖ ሳለ ወፎች የዛፍ ፍሬዎችን ከነቅርንጨፉ እየቆረጡ ይዘው ሲበሩ አይቶ ይህ ነገር ምን እንደሆነ መነኮሳቱን ጠየቃቸው፡፡ መነኮሳቱም ወፎቹ እንዲህ 11 ዓመታቸው መሆኑንና እነርሱም ለምን እንደሆነ እንደማያውቁ ነገሩት፡፡ ❤ መኰንኑም ምናልባት በተራራ ውስጥ ለሚኖር አንድ ጻድቅ እየወሰዱለት እንደሆነ ግምቱን ሲነግራቸው በመሀል አንድ ቁራ መጥቶ የዛፉን ፍሬ ቆርጦ ሲሄድ አዩት፡፡ ከአበምኔቱም ጋር ሆነው ተከትለውት የሚገባበትን አዩት፡፡ በቦታውም ደርሰው ድንጋይ ሲጥሉ ከውስጥ ድምጽ ሰሙ፡፡ ከወዴት እንደሆኑ ሲጠይቋቸው "እኛን ለማየት ከፈለጋችሁ ራቁታቸንን ስለሆንን ሦስት ልብሶችን ጣሉልን" አሏቸው፡፡ ልብሳቸውንም ከጣሉላቸው በኋላ ጭንቅ በሆነች መንገድ ተጉዘው ወደ ውስጥ ገብተው ሴቶቹን እጅ ነሷቸው፡፡ አበ ምኔቱም ቅድስት አመተ ክርስቶስን "እናቴና እመቤቴ ሆይ ከወዴት ነሽ? ወደዚህስ አወጣጥሽ እንዴት ነው?" ብለው ጠየቋት፡፡ እርሷም ሥራዋን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ነገረቻቸው፡፡ አበ ምኔቱም "እናቴ ሆይ የምትፈቅጂ ከሆነ ከገዳም ምግብ እናምጣላችሁና ከእናንተ ጋር አብረን በአንድነት እንመገብ" አሏት፡፡ እርሷም ‹‹ወደዚህ ከመጣን ቅዱስ ቍርባንን አልተቀበልንምና የክርስቶስን ሥጋና ደም አምጥቶ እንዲያቀብለን ቄስ እዘዝልን›› አለቻቸው፡፡ እርሳቸውም ቄስ አዘዙላትና የለመነችው ተፈጽሞላት ሥጋ ወደሙን ተቀበሉ፡፡ በማግሥቱም ዓመተ ክርስቶስ ረጅም ጸሎትን ከጸለየች በኋላ የካቲት 8 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡ ሁለቱ አገልጋዮቿም ወዲያው ተከታትለው ዐረፉ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አመተ ክርስቶስና በሁለቱ አገልጋዮቿ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸው ከእኛ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምምንጭ፦ የየካቲት 8 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለሠላስ አንስት። ምንዳቤ ገዳም ዘፆራ እንዘ ዕሩቃት። እምድኅረ ነሥአ ቊርባነ እምእደ ካህናት። አዕረፈ ዮም በበአሐቲ ትልወት። አሐቲ እግዝእት ወክልኤቲ አእማት"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የየካቲት 8። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ዘያጸግባ እምበረከቱ ለፍትወትከ። ዘይሔድሳ ከመ ንስር ለውርዙትከ። ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር። መዝ 102፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥36-40። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ። ወአነ አየድዕ ግብርየ ለንጉሥ። ከመ ቀለመ ጸሐፊ ዘጠበጠበ ይጽሕፍ ልሳንየ"። መዝ 44፥1-2 ወይም 63፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 5፥5-11፣ ያዕ 5፥13-ፍ.ም እናጰ የሐዋ ሥራ የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥22-35 ወይም 11፥39-33። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ነው። መልካም የጌታችን በ40 ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት በዓል፣ የልደተ ስምዖን በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የካቲት8 ቀን። ❤ እንኳን ለጌታችን ለአምላካች ለመድኃኒታች ለኢየሱስ ክርስቶስ ከዘጠኙ ንዑስ በዓል ለአንዱ ከከበረ ልደቱ ከአርባ ቀኖች በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ለገባበት በዓል፣ በድሜው ላይ ጌታችን ተወልዶ እስኪያይ ድረስ ሦስት መቶ ዓመት ለተጨመረለት ለካህኑ አረጋዊ ቅዱስ ስምዖን ለልደቱ (ለዕረፍቱ) በዓል፣ ከአሴር ወገን ለሆነች ለፋሩኤል ልጅ ለነቢዪት ቅድስት ሐና ለዕረፍቷ በዓል፣ በትሩፉቱ ፍጹም ለሆነ ለታላቅ አረጋዊ ለገዳመ ሲሐቱ ለአባ ኤልያስ ለዕረፍት በዓልና ከቊስጥንጥንያ አገር ከነገሥታት ወገን ለነበረች ዓለምን ንቃ ዋሻ ውስጥ ገብታ 11ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ምግቧንም የሰማይ ወፎች ያመጡላት ለነበረችው ለከበረች ለእመቤት ቅድስት አመተ ክርስቶስ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአመተ ክርስቶስ ከሁለቱም አገልጋዮቿ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ስምዖን ተወክፎ ዳዊት ዘመሮ ነቢያት ቀደሙ አእምሮ ሐዋርያት ተራው አሠሮ ሰብአ ሰገል ሰገድ ሎቱ እሙነ ኮነ ልደቱ"። ትርጉም፦ ስምዖን ተቀበለው ዳዊት ዘመረለት ነቢያት አስቀድመው አወቁት ሐዋርያት ፍለጋውን ተከተሉ የጥበብ ሰዎች (ሰብአሰገል) ሰገዱለት ልደቱ በእርግጥ ሆነ። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ጌታችን በተወለደ በ40 ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት፦ ለዚህ ምሥጢር አገልጋይ ለሆነ ጻድቁ ዮሴፍና የወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የክብር ባለቤት እርሱ በእስራኤል ሕዝብ ላይ የሠራውን ሕግ ይፈጽሙ ዘንድ መሥዋትም ሊአቀርቡ መጡ። ጻድቅ ሰው ስምዖን ካህንም ሕፃኑን ተቀብሎ አቀፈው። ❤ እንዲህም ሆነ አባታችን አዳም ከተፈጠረ በአምስት ሺህ ሁለት መቶ ዓመት አሸናፊ የተባለ በጥሊሞስ በነገሠ ጊዜ የአይሁድ ወገኖች ከሥልጣኑ በታች ነበሩ። ወደ ኢየሩሳሌምም ልኮ ከሊቃውንቶቻቸው አዋቂዎች መምህራኖቻቸው ሰብዓ ሰዎችን መርጦ ወደርሱ ወሰዳቸው የኦሪትንም፡ መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ቋንቋ ወደ ጽርዕ ቋንቋ ይተረጒሙ ዘንድ አዘዛቸው። ይህም የሆነ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ከአይሁድ ሕጉና ሥርዓቱ እንደሚፈልስና በዓለም ሁሉ ላሉ ለክርስቲያን ወገን ይሆን ዘንድ አለውና። ዳግመኛም ሁለ ሁለት እያደረጉ እንዲለዩአቸው አዘዘ እነርሱ ሰባ ሁለት ስለሆኑ ሠላሳ ስድስት ድንኳን አዘጋጅቶ በዚያ ሁለት ሁለቱን አኖራቸው ተገናኝተው በመስማማት የሚጽፉትን የሕጉን ቃል እንዳይለወጡ በላያቸው ጠባቂዎችን አኖረ። እነርሱ በተንኰል ሥራ የታወቁ ናቸውና። ❤ ለዚህም ለስምዖን ይተረጒም ዘንድ የነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ደረሰውና "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ትወልዳለች"። ከሚለው አንቀጽ ደረሰ፤ድንግል፡በድንግልና ትፀንሳለች ብዬ ብጽፍ ስንኳን የአሕዛብ ንጉሥ የእስራኤል ንጉሥ ቢኾን ይቀበለኛል?ብሎ "ወለት ትፀንስ" ብሎ ጻፈ እንቅልፍ መጥቶበት ተኝቶ ቢነቃ የእግዚአብሔር መልአክ "ወለትን" ፍቆ "ድንግልን" ጽፎ አገኘ፤ ስምዖንም "ድንግልን" ፍቆ "ወለት" ብሎ ጻፎ በድጋሚ እንቅልፍ መጥቶበት ተኝቶ ቢነቃ "ወለትን" ፍቆ "ድንግልን" ጽፎ አገኘ፤ ሦስተኛም እንቅልፍ መጥቶበት ተኝቶ ቢነቃ "ወለትን" ፍቆ "ድንግልን" ጽፎ አገኘው እፍቃለኊ ሲል የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "የተጠራጠርከውን ከድንግል የሚወለደውን እስከምታየውና እስከምትታቀፈው ሞትን አትቀምስም" አለው ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከተወለደና በዚች ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ እስከ አስገቡት ድረስ ስምዖን ሦስት መቶ ዓመት ኖረ ሕፃኑን ጌታችንንም በታቀፈው ጊዜ ታውረው የነበሩ ዓይኖቹ ተገለጡ ሁለመናውም ሐዲስ ሆነ መንፈስ ቅዱስም "የምትጠብቀው የነበረው ሕፃን ይህ" ነው ብሎ ነግሮታልና እግዚአብሔርን አመሰገነው። እንዲህም አለ "ባርያህን በሰላም አሰናቡተው በአንተ ምክንያት በዚህ በኃላፊው ዓለም ሕይወት ታሥሬ ኑሬአለሁና እነሆ አሁን መጥተህ አየሁህ ወደ ዘላለም ሕይወት እሔድ ዘንድ አሰናብተኝ ዓይኖቼ ትድግናህን አይተዋልና። በወገኖችህ ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ለአሕዛብ ብርሃንን ለወገኖችህ እስራኤልም ክብርን ትገልጥ ዘንድ"። ❤ እመቤታችንን እናቱ ድንግል ማርያምንም እንዲህ አላት "ይህ ልጅሽ ከእስራኤል ውስጥ ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው በሚፈረድባቸው ገንዘብ ለምልክት የተዘጋጀ ነው"። ዳግመኛው በመከራው ጊዜ በልቧ የሚያድርባትን ኀዘን አስረዳት እንዲህ አላት "በአንቺ ግን በልብሽ የሚከፋፍል ፍላፃ ይገባል" ከዚህም በኋላ የካቲት8 ቀን በሰላም ዐረፈ። በዚያም የከበረ ወንጌል ያወሳት የፋኑኤል ልጅ ነቢዪት ሐና ነበረች እርሷም ስርሱ ትንቢት ተናገረች እግዚአብሔርን እያመሰገነች እርሱ ከሰይጣን ባርነት የሚያድናቸው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱና ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት8 ስንክሳርና መጽሐፈ ተአምኆ ቅዱሳን ንባብና ትርጓሜው መጋቢ ሐዲስ ሮዳስ ከጻፈው። + + + ❤ "ሰላም ለሐና ነቢይት"። ትርጉም፦ ለነቢዪት ሐናም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ነቢዪት ቅድስት ሐና፦ የእርሷም ዘመኗ አልፎ ነበር በድንግልና ከኖረች በኋላ ከባሏ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች። ሰማንያ አራት ዓመት ፈት ሁና ኖረች በጾምና በጸሎትም እያገለገለች ቀንም ሌሊትም ከምኵራብ አትወጣም ነበር። ጌታችን ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ በአርባ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በአስገቡት ጊዜ በዚያን ሰዓት ተነሥታ አመነች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው የኢየሩሳሌምን ድኅነት ተስፋ ለሚያደርጉ ሁሉ፡ስለርሱ ነገረች። ከዚያም በኋላ የካቲት 8 ቀን በሰላም ዐረፈች። + + + ❤ አባ ኤልያስ ዘገዳመ ሲሐት፦ ይህይ አባት የሚያረጋጋው በትሩፋቱ ፍጹም የሆነ፡ አረጋዊ መነኰሴ እንዲልኩለት በመለመን ጻድቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ወደ ገዳመ ሲሐት በላከ ጊዜ ይህን በትሩፋቱ ፍጹም የሆነ ኤልያስን ላኩለት ስርሱም እንዲህ ብለው ጻፉ "ንጉሥ ሆይ እነሆ በሥራው ኤልያስን የሚመስል ኤልያስ የሚባል ጻድቅ ሰው ልከንልሃል"። ወደ ንጉሥም በደረሰ ጊዜ ንጉሥ እንዲህ፡ አለው "አንተ በገድልህ ነቢይ ኤልያስን እንደምትመስል መነኰሳቱ ስለ አንተ ወደ እኔ ልከዋል" አረጋዊውም በየውሀትና በትሕትና እንዲህ አለ "ጻድቅ ንጉሥ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝ ሰው ሁሉ በጠባዩና በሥራው ይታወቃል የኤልያስም ገድሉ እንዲህ ነው ስለ ደግነቱ ምግቡን ቊራዎች ያመጡለት ነበር እኔ ግን ምግቤን በፀሐይ ውስጥ ባሰጣው ቊራ ይዞት ይሔዳል" ንጉሡም ሰምቶ ከቃሉ ጣዕም የተነሣ አደነቀ።