ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
#ማህደረ_መለኮት
ማህደረ መለኮት 2×
ማርያም እመ ብዙሃን
አዝ........
መለኮት ያደረብሽ ከፍጥረት ተለይተሽ
ከሁሉ የተወደድሽ ንፅህት ክብርት ነሽ
ከቃል በላይ ቃል አለ ለክብርሽ መግለጫ
ገናንነትሽ ከዓለም ድንግል ሆይ አለው ብልጫ
ማርያም እመ ብዙሃን
አዝ..........
አላወዳድርሽም በማንም በምንም
ወልደሽ ስለሰጠሽኝ ፍቅርና ሰላም
ማርያም ማርያም እልሻለው ደግሜ ደጋግሜ
በወለድሺው መድኃኒት ስለቀለለ ሸክሜ
ማርያም እመ ብዙሃን
አዝ.........
ተወስኗል በሆድሽ ያልቻሉት ሰማያቱ
በማህፀንሽ ሀኖ ያስገርማል መታየቱ
ሰባአ ሰገል ተደንቀው ቤተልሔም ተገኙ
ወርቅ ዕጣንና ከርቤ ሊገብሩ ለአዳኙ
https://t.me/Eotcw
1 161
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማኅሌት ዘመስከረም ብዙኃን ማርያም
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
❄️ሥርዓተ ነግሥ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ፤ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@EOTCWW
@EOTCWW
✨መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCmahlet
🌱ዚቅ
ንባርኮ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ንፍሑ ቀርነ በጽዮን፤ ስብኩ በዓለ ማርያም ወበዓለ መስቀል ዘዮም።
@EOTCWW
@EOTCWW
✨መልክአ ማርይም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
@EOTCWW
@EOTCWW
🌱ዚቅ
ፍጽመነ ንዕትብ በዕፀ መስቀሉ፤ ነግሀ ነቂሐነ እምንዋም በከመ ይቤሉ አዕማደ ሰላም፤ ዘዮም መስቀል አሠነየ ዓለመ እንተ በልየ፤ በስነ ማርያም አዋከየ፤ ለክርስቲያን ኮኖሙ ዕበየ።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ዮም መስቀል አሠነየ እንተ በልየ ዓለመ አሠነየ/፪/
በስነ ማርያም አዋከየ በስነ ማርያም/፪/
@EOTCWW
✨መልክአ ማርያም
ሰላም ለጒርዔኪ ሠናይ እምወይን፤ በከመ ይቤ ሰሎሞን፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ብርሃን፤ ክድንኒ ገርዜነ ጸጋ ኢያዕጽበኒ ዕርቃን፤ ዘኢአነምዎ ጠቢባን በኪን።
@EOTCWW
@EOTCWW
🌱ዚቅ
በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም፤ ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ጽጌ ደመና፤ መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም፤ ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን፤ ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን፤ አጽገዩ ሕዝበ ወመሐይምናን፤ በቤተ መርዓ ተመልዑ ክርስቲያን።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን/፪/
ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን/፪/
@EOTCWW
@EOTCWW
✨መልክአ ማርያም
ሰላም ለመልክዕኪ ዘተሠርገወ አሚረ፤ ዘያበርሕ ወትረ፤ ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ፤ አርእይኒ ገፀ ዚአኪ ማርያም ምዕረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ
@EOTCWW
🌱ዚቅ
አብርሂ አብርሂ ማርያም አብርሂ፤ መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትትሞጥሒ፤ ጽዮን ዮም ተፍሥሒ።
@EOTCWW
❣❣ወረብ
አብርሂ አብርሂ ማርያም አብርሂ አብርሂ/፪/
መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትትሞጥሒ ጽዮን ዮም ተፈሥሒ/፪/
@EOTCWW
@EOTCWW
❣❣አንገርጋሪ
ዓይ ይእቲ ዛቲ መድኃኒት፤ እንተ ኃሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት፤ ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኅ፤ ግበር ታቦተ በዘትድኅን፤ እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ፤ አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ።
@EOTCWW
@EOTCWW
@EOTCWW
🍀🍀እስመ ለዓለም
ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል፤ ይእቲኬ ቤተ ምስአል፤ ዘአስተዓጸቡ ታቀልል፤ ለኲሉ ፍጥረት ትተነብል፤ በአክናፈ መላእክት ትትኬለል፤ ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፤ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፤ መንክር ወመድምም ዕበያ ወክብራ ለድንግል፤ ጽሕፍት ውስተ ወንጌል፤ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።
@EOTCWW
@EOTCWW
🔸🔸አመላለስ
ጽሕፍት ውስተ ወንጌል/፪/
ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል/፪/
@EOTCWW
❣❣ወረብ
ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል ይእቲኬ ቤተ ምስአል/፪/
ለኲሉ ፍጥረት ትተነብል ለኲሉ ፍጥረት/፪/
https://t.me/Eotcw
# Join & share #
1 161
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሥርዓተ ዋዜማ ዘመስከረም ብዙኃን ማርያም
☘☘☘☘☘☘☘☘
ዋዜማ
በ፩: አስተጋብዖሙ እምበሐውርት እምጽባሕ ወእምዓረብ፤ ወመስዕ ወባሕር፤ በዕፀ መስቀሉ አተቦሙ፤ ወአውዓዩ ሥጋሆሙ በእሳት፤ ተለዓሉ በክብር ደናግል፤ እለ ውስተ ርእሶሙ ክብር።
@EOTCWW
🔹ምልጣን
ወአውዓዩ ሥጋሆሙ በእሳት፤ ተለዓሉ በክብር ደናግል፤ እለ ውስተ ርእሶሙ ክብር።
@EOTCWW
@EOTCWW
✴️በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
ሤሞሙ አብ ጳጳሳተ ቀሳውስተ ወዲያቆናተ ሤሞሙ አብ ጳጳሳተ።
@EOTCWW
@EOTCWW
✴️እግዚአብሔር ነግሠ
፫፻፲ወ፰ቱ ኤጲስ ቆጶሳት ርቱዓነ ሃይማኖት፤ እለ አምኑ በስሙ፤ በዕፀ መስቀሉ፤ በውስተ ማኅበሮሙ ለቅዱሳን።
@EOTCWW
@EOTCWW
✴️በ፭ እግዚኦ ጸራሕኩ ኀቤከ
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን፤ ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን፤ ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን።
@EOTCWW
@EOTCWW
💎ይትባረክ
ወእምዝ መሐሩ ወአስምዑ ቃለ እግዚአብሔር፤ ውስተ ብሔረ ከነዓን እግዚአብሔር መርሖሙ።
@EOTCWW
@EOTCWW
🔹፫ት
ሮማ አስተጋብዖሙ እምበሐውርት፤ ለብዙኃን አኃው ውስተ ፩ዱ ቤት፤ እንዘ ሀለዉ ውስተ ማኅበሮሙ፤ ብርሃነ ከሠተ ሎሙ።
@EOTCWW
@EOTCWW
👋ሰላም
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።
https://t.me/Eotcw
# Join & share
1 161
መስከረም 21 (ለብዙኃን ማርያም)
በቅዳሴ ጊዜ
#ምስባክ
መዝ ፵፬ ቊ፱-፲
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ።
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት።
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወጽምዒ እዝነኪ።
#ትርጉም
የንግሥት ሴቶች ልጆች ለክብርህ ናቸው፣
በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ተቆማለች፣
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው ለቅዱስ ጢባርዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ለቅዱስ ቆጵርያኖስና ለድንግሊቱ ቅድስት ዮስቴና ሰማዕትናት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ በዚችም ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት የአንዱ ሐዋርያ የቅዱስ ጢባርዮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። የሐዋርያው ቅዱስ ጢባርዮስ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ቅዱስ ቆጵርያኖስና ድንግሊቱ ቅድስት ዮስቴና፦ ይህም ቅዱስ ቆጵርያኖስ አስቀድሞ ከሀዲና ሥራየኛ ነበር እርሱም ለሥራየኞች ሁሉ አለቃቸው ነው።
በሥራዩም ሥራ ከመመካቱ ብዛት የተነሣ በሥራይ የሚበልጠው ካለ ሊያይና ከዚያ ሊማር ከሌለ ግን በእነርሱ ላይ ሊመካባቸው ወደ አንጾኪያ አገር ሔደ።
❤ ቆጵርያኖስም ወደ አንጾኪያ ከተማ በደረሰ ጊዜ ወሬው ተሰማ በአንጾኪያም ከተማ ከሀገር ታላላቆች ተወላጅ የሆነ አንድ ጐልማሳ አለ እርሱም ላህይዋ የሚያምር አንዲቷን ድንግል ብላቴና ተመኛት ወደ ቤተ ክርስቲያን በምትሔድ ጊዜ እያያት በእርሷ ፍቅር ልቡ እንደ እሳት ተቃጠለ በምንም በምን ሊአገኛት አልተቻለውም ገንዘብ በመስጠትም ቢሆን ወይም በማስፈራራት ወይም በሥራይ ሥራ አልሆነለትም።
❤ የቆጵርያኖስም ወሬው በተሰማ ጊዜ እርሱ ከሥራየኞች ሁሉ እንደሚበልጥ ስለርሱ ተነግሮአልና ያም ድንግል ዮስቴናን የተመኛት ጐልማሳ ወደ ቆጵርያኖስ ሒዶ በልቡ ያለውን ጉዳዩን ድንግሊቱን ዮስቴናን እንደተመኛትና እርሷን ማግኘት እንደተሳነው ነገረው ቆጵርያኖስም እኔ የልብህን ፍላጎት እፈጽምልሃለሁ አትዘን አለው።
❤ ከዚያም በኋላ ያን ጊዜ ዮስቴናን ወደርሱ ያመጧት ዘንድ በሥራዩ የአጋንንትን ሠራዊት ወደርሷ ላከ እነዚያም አጋንንት ወደርሷ በቀረቡ ጊዜ እርሷን መውሰድ አልቻሉም ከጸሎቷ የተነሣ ይቃጠላሉና እንዲህም ብዙ ጊዜ ላካቸው ግን ወደርሱ ሊያመጧት አልቻሉም ቆጵርያኖስም ሁሉንም አጋንንት ጠርቶ ድንግል ዮስቴናን ካላመጣችሁልኝ እኔ ከእናንተ ተለይቼ ክርስቲያን እሆናለሁ አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ የሰይጣናት አለቃ ሊሸነግለው አሰበ አንዱንም ሰይጣን ከሰይጣናት ውስጥ በዮስቴና አምሳል ተመስሎ ለቆጵርያኖስ እንዲታየው አደረገ። ሰይጣኑም አለቃው እንዳዘዘው እንዲህ አድርጎ ተዘጋጀ እነሆ አሁን የዮስቴናን መምጣት ለቆጵርያኖስ ነገረው እርሱም እውነት መስሎት እጅግ ደስ አለው ሊቀበላትም ተነሣ። በእርሷ አርአያ የተመሰለውንም ምትሐት በአየ ጊዜ "የሴቶች እመቤት ዮስቴና መምጣትሽ መልካም ሆነ" አለ ይህንንም ስሟን በጠራ ጊዜ ያ በእርሷ አምሳል የተመሰለ ሰይጣን እንደ ጢስ ሁኖ ተበተነ።
❤ በዚያንም ጊዜ የሽንገላው ምክንያት ምትሐቱም ከንቱ እንደሆነ ቆጵርያኖስ አወቀ አስተዋለም በልቡም እንዲህ አለ። "ስሟን በጠሩበት ቦታ እንደ ጢስ የሚበተኑ ከሆነ በፊቷ ሊቆሙ ሊሸነገሏትስ እንዴት ይቻላቸዋል" ይህንንም ብሎ ወዲያውኑ የጥንቆላ መጻሕፍቶቹን አቃጠለ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠምቆ የምንኲስና ልብስን ለበሰ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ዲቁና ሾመው። ዳግመኛም ቅስና ሾመው በትሩፋት ሥራና በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ለሀገሩ ምዕራብ ለሆነች ቅርጣግና ለምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ ተገባው ያን ጊዜም ቅድስት ዮስቴናን ወስዶ ለደናግል ገዳም እመ ምኔት አደረጋት።
በቅርጣግናም የቅዱሳን የአንድነት ስብሰባ በሆነ ጊዜ ከጉባኤው አባላት እርሱ አንዱ ነው።
❤ ከብዙ ወራት በኋላም ከሀዲው ንጉሥ ዳኬዎስ ስለእነርሱ ሰማ ወደርሱም አስቀረባቸውና የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ለጣዖቶቹ እንዲሰግዱ አዘዛቸው። ትእዛዙንም ባልሰሙ ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ብዙ ሥቃይንም ከአሠቃያቸው በኋላ የቅዱስ ቆጵርያኖስንና የቅድስት ደንግል ዮስቴናን የሦስት ወንዶችንም ራሳቸውን አስቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱስ ቆጵርያኖስና ድንግሊቱ ቅድስት ዮስቴና በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 21 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ሰላም ለጢባርዮስ ስንዕ። ምስለ ፸ወ፪ቱ አርድእተ እግዚእ። በዕለተ ዕረፍትከ ዮም ብሔረ ተድላ ወፍግዕ። ባርከነ ለደቂቅከ በውስተ ዛቲ ምሥዋዕ። እስመ ለመምህር ቡራኬ ሥሩዕ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 21።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
