fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
photo content

photo content

photo content

አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን ጽረ ገጽ የተወሰደ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አድኅነኒ አግዚኦ ወተሠሃለኒ። እስመ በርዕቱ ቆመ እገርየ። በማኅበረ እባርከከ እግዚኦ። መዝ 25፥16-17። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥15-25። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥3-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1፥4-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 19፥17-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም (የብዙኀን ማርያም) በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን የእናታች የእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም (ለብዙኃን ማርያም)፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል በግሸን በመስቀለኛው ተራራ ላይ ገብቶ ለተቀመጠበት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለመወሰን፤ በኒቅያ ጉባኤ አርዮስን ለማውገዝ ከሩቅ ለተሰባሰቡበት ቀን በሰላም አደረሰን። + + + ❤የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ፦ ሃሌ ሉያ "ዓይ ይእቲ ዛቲ መድኃኒት እንተ ኀሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት ወይቤሎ ለኖህ አመ አይህ ግበር ታቦተ በዘትድኅን እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ። ትርጉም፦ ያች መድኃኒት ማን ናት ነቢያት የፈለጓት የዞርዋት በጥፋት ጊዜ ለኖህ አለው የምትድንበት ታቦት ሥራ በእርሷ አርአያ መስቀል ናትና እክሊል ተቀዳጅታ ትመላለሳለች። + + + ❤ የዕለቱ ዓራራይ (እግ ነግ) ዜማ፦ ሠለስቱ ምዕት ወሠርቱ ወሰመንቱ ኤጲስ ቆጶሳት ርቱዓነ ሃይማኖት እለ መሀሩ በስሙ በዕፀ መስቀሉ በውስተ ማኅበሮሙ ለቅዱሳን። ትርጉም፦ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ኤጲስ ቆጶሳት ሃይማኖታቸው የቀና በስሙ በዕፀ መስቀሉ በቅዱሳን ማኅበር ያስተምሩ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ። + + + ❤ ብዙኃን ማርያም፦ በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል "ብዙኃን ማርያም" በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ለጉባኤ ኒቅያ ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤ + + + ❤ ጉባዔ ኒቅያ፦ በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ "አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!" የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡ ❤ በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡ ❤ ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡ ❤ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡ + + + ❤ ዕፀ መስቀል፦ በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤ ❤ ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡ ❤ ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡ ❤ መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡ ❤ ከዚህ በኋላ ንጉሡ "መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!" ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ

20/1/2015 ዓ.ም (፲፰/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ መዝ ፹፫፥፮ እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ፤ ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል፤ ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን። #ትርጕም፦ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፤ ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን ለእስክንድርያ ሃያ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳሳት ለአትናቴዎስ ካልዕ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከድንግል መሊዳማ በሰማዕትነት ከዐረፈች፣ ከድንግል አቴና፣ ከፊና፣ ከፊላ፣ ከመነኰስ አብርሃም፣ ከታዴዎስ ከአቢናፍንዮስ፣ ከጻድቁ አርማንዮስ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከኤጲስቆጶሳት አለቃ ሰማዕት ከሆነ ከስምዖን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የእስክንድርያ ሃያ ስምንተኛ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ አትናቴዎስ፦ ይህም አባት አስቀድሞ የእስክንድርያ አገር ቤተክርስቲያን መጋቢ ነበር ከእርሱም በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ሁሉም ኤጲስቆጶሳት መኳንንቱና ሊቃውንቱ ሕዝቡም በአንድ ምክር ተስማሙ በእግዚአብሔር ሕግ በመጽናት ያደረገው መልካም ተጋድሎውና ቅድስናው ስለርሱ ስለተነገረ መንፈስ ቅዱስም እንደ አደረበት ስለ ተረዱ ያለ ፈቃዱም ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በምክሩ፣ በትምህርቱ፣ በጸሎቱ ከዲያብሎስ ተኵላዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው እሊህም ሃይማኖትን የሚለውጡ መናፍቃን ናቸው። ❤ በሊቀ ጵጵስናውም ፯ት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አትናቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 20 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለትናቴዎስ ለእስክንድርያ ሥዩማ። ወማኅቶት ብሩህ ዘይነብር ዲበ ተቅዋማ። ዓዲ ለፊላ ወመሊዳማ። አእዳወ ዝንቱ ወእማንቱ ይኩናኒ ግርማ። በማእተበ ሕይወት መስቀል ፍጽምየ ይኅትማ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 20። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት ቲቶ 1፥5-12፣ ያዕ 1፥2-13 እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳ ለኢትዮጵያ ንጉሥ ለናዖድ ልጅ ለከበረችና ለተባረከች ለቅድስት ሮማነ ወርቅ ለዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ለመስቀል ለበዓሉ መታሰቢያ፣ ያለ ደም ማፍሰስ ሰማዕት ለሆነ ለአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ከዐዘቅት ለወጣበት ለመታሰቢያ ቀን በዓልና በሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ዘመነ ለሆነ ለከበረ ለገዳማዊ ቂርቆስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ በዚችም ቀን ደግሞ የከበረ መስቀል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በተገኘ ጊዜ ሦስት ቀኖች ያህል በፍጹም ደስታ በዓልን አድርገውለት ነበርና እኛም እንዲሁ በታላቅ ደስታ የበዓሉን መታሰቢያ ልናደርግ ይገባናል ከጠላታችን ሰይጣን እጅ ድኅነታችን በእርሱ ተደርጎልናልና። ❤ በመስቀሉ ለአዳነን ለእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይሁን ሁላችንን የሐዋርያት የሆነች የከበረች የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለእኛ የተቀበለውን መከራውን የምናስበውን በባለሟልነትና በፍቅሩ ወደእርሱ ያቅርበን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ በዚችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ የናዖድ ልጅ የከበረችና የተባረከች ሮማነ ወርቅ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው። እርሷም መጾምና መጸለይን የምትወድ ድኆችንና ችግረኞችን የምትጎበኝ ነበረች እግዚአብሔር በቅድስት ሮማነ ወርቅ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የአርማንያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ጎርጎርዮስ ከዐዘቅት (ጉድጉድ) መውጣቱ፦ ይህም በንጉሥ ድርጣድስ ዘመን በአርማንያ አገር ራሱን ባሪያ አድርጎ ይኖር ነበር። ይህም ንጉሥ ከሀዲ ነበርና ዕጣን ሊዐሳርግ ወደ ጣዖቱ ቤት ሲገባ ቅዱስ ጎርጎርዮስን ጠርቶ ለአማልክት ዕጣን እንዲአሳርግ አዘዘው። ቅዱሱ ግን የንጉሡን ትእዛዝ አልሰማም ስለዚህም እጅግ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው በእሳትም አቃጠለው ከዚህም በኃላ ጥልቅ ከሆነ ጉድጓድ ውስጥ ጣለው በዚያም ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ። ❤ በንጉሡ አዳራሽ አቅራቢያም አንዲት አሮጊት ነበረች እርሷም "እንጀራ እየጋገርሽ ቅዱስ ጎርጎርዮስ በውስጡ ከአለበት ጉድጓድ ሁል ጊዜ ጣይለት" የሚላትን ራእይ አየች። ይችም አሮጊት እንዲህ እያደረገች እንጀራንም እየጣለችለት እስከ ዐሥራ አምስት ዓመት ፍጻሜ ኖረች። ❤ በዚያም ወራት ይህ ንጉሥ ድርጣድስ ደናግሎችንና ቅድስት አርሴማን ገድሎ ሥጋቸውም በተራራ ላይ ተጣለ። ሰይጣንም በንጉሥ ድርጣድስ ላይ ተጫነ እግዚአብሔርም የተፈጥሮ መልኩን ለውጦ እንደ እሪያ አደረገው እንዲሁም ከቤተ መንግሥት ሰዎች ብዙዎቹን ሰይጣን ተጫነባቸው በቤተ መንግሥት ውስጥ ታላቅ ኀዘንና ጭንቀት ሆነ። ❤ የንጉሡ እኅት ግን በሌሊት ራእይ "ጎርጎርዮስን ከጉድጓድ ውስጥ ካላወጣችሁት አለዚያ አትድኑም" እንደሚላት ሰውን አየች ለወገኖቿም ነገረቻቸውና እንርሱም ሒደው ቅዱስ ጎርጎርዮስን ከጎድጓድ አወጡት በዚያን ጊዜም ቅዱሳት ደናግልን ሥጋቸውን ገንዞ በመልካም ቦታ አኖራቸው ከዚያም በኋላ ንጉሡንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም ረወሳቸው። ዜናውም ሁሉ በዕረፍቱ ታኅሣሥ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል። ❤ ገዳማዊው ቅዱስ ቂርቆስ፦ ይህም ቅዱስ ሰው ከከሀዲው ንጉሥ ከመርቅያን በሸሸ ጊዜ በከፍተኛ ተራራ ላይ በብቸኛነት ተቀመጠ በውስጡም አራዊት የኖሩበታል ምግቡንም ከእግዚአብሔር ለመነ አጋዘንም በየሦስት ቀን ወደርሱ እንድትመጣ ወተቷንም እንዲጠጣ አዘዘለት በእንዲህ ያለ ሥራም ዐሥር ዓመታት ኖረ። ❤ የተረገመ ሰይጣን ግን በተጋድሎው በቀና ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ፈተና ሊፈትነው ጀመረ ያስፈራው ዘንድ በጥቁር ባሪያ አምሳል የሚመጣበት ጊዜ አለ ደግሞም በብዙ ሠራዊትና በፈረሰኞች አምሳል ሁነው ይዘው ያሥሩታል በጅራፍም ገርፈው በእግሮቹ ይጎትቱታል ሰይጣናት እንደሆኑ በአወቀ ጊዜ በመስቀል ምልክት በላያቸው ሲአማትብ ያን ጊዜ ሸሹ። ❤ በአንዲትም ዕለት በሌሊት ሲሰግድ በታላቅ ከይሱ አምሳል በአንገቱ ላይ ተንጠለጠለና በፊቱ ውስጥ ሊተነፍስበት ፈለገ ያን ጊዜም ከእግዚአብሔር ርዳታን ለመነ መልአኩን ልኮ አዳነው። ❤ የዕረፍቱም ጊዜ ሲቀርብ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ሒዶ ሥራውን ሁሉ ነገረው ከዚህም በኋላ ወደ በዓቱ ተመለሰ ሊቀ ጳጳሳቱም መገነዣውን እንዲያዘጋጁ ሦስት ኤጲስቆጶሳትን ወደርሱ ላከ ወደ በዓቱም በሔዱ ጊዜ ታሞ አገኙት ነፍሱም ከሥጋው በምትወጣ ጊዜ ለመነገር የማይቻል ታላቅ ክብርን ተመለከቱ በበዓቱም ውስጥ ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በገዳማዊው ቅዱስ ቂርቆስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 19 ስንክሳር። + + + ❤ ሰላም ለቂርቆስ ለነቢረ ገዳም ዘአፍቀራ ይሰቲ ሐሊበ ቶራ። ድኅረ አመከሮ ሰይጣን በዘዚአሁ መከራ። አዕይንቲሆሙ ለኤጲስቆጶሳት ነጸራ። በጊዜ ዕረፍቱ ዘኮነ ነከራ። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የመስከረም 19። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ተመየጥከኒ ወአሕየውከኒ። ወእምቀላየ ምድር አውፃእከኒ። ወአብዛኅኮ ለጽድቅከ"። መዝ 70፥20፥21። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ጴጥ 5፥1-5 እና የሐዋ ሥራ 10፥9-24። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥9-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅድስት ሮማነ ወርቅ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 15:8-10፡ "ከማሁ ብእሲትኂ ለእመ ባቲ ዐሥሩ " - "ዐሥር፡ድሪም፡ያላት፡አንድ፡ድሪም፡ቢጠፋባት፥መብራት፡አብርታ፡ቤቷንም፡ጠርጋ፡እስክታገኘው፡ድረስ፡አጥብቃ፡የማትፈልግ፡ሴት፡ማን፡ናት? ባገኘችውም፡ጊዜ፡ወዳጆቿንና፡ጎረቤቶቿን፡በአንድነት፡ጠርታ፦የጠፋውን፡ድሪሜን፡አግኝቼዋለሁና፡ከእኔ፡ጋራ፡ደስ፡ይበላችሁ፡ትላቸዋለች። እላችኋለሁ፥እንዲሁ፡ንስሓ፡በሚገባ፡ባንድ፡ኃጢአተኛ፡በእግዚአብሔር፡መላእክት፡ፊት፡ደስታ፡ይሆናል።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.38 KB

18/1/2015 ዓ.ም (፲፰/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 አንተ ትኳንን ኃይለ ባሕር። ወአንተ ታረምሞ ለድምፀ ማዕበላ። አንተ አሕሠርኮ ለዕቡይ ከመ ቅቱል። መዝ 88:9 🕯 ትርጉም የባሕርን ኃይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሠኘዋለህ። አንተ ረዓብን እንደ ተገደለ አዋረድኸው። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

18/1/2015 ዓ.ም (፲፰/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ መዝ ፹፫፥፮ እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ፤ ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል፤ ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን። #ትርጕም፦ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፤ ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል። https://t.me/Eotcw

photo content

ና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝዝሃለሁ" አለው። ሕፃኑም "አባቴ የእናቴ የአባቷ አገልጋይ እገሌ ነው" አለ የተሰበሰቡትም ሕዝብ ሰምተው አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ❤ ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲቀርብ ደቀ መዝሙሩን እንዲህ ብሎ አዘዘው "ከዚህ ዓለም የምለይበት ጊዜ ደርሷል በምሞትም ጊዜ ከአባ በርሳቦና ከልጀቹ ጋራ ቅበረኝ" ይህንንም ብሎ በሦስተኛው ቀን ዐረፈ መላእክትም ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ነፍሱን በክብር አሳረጉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በግብጻዊው በሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 18 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለያዕቆብ መስተጋድል ጽሙድ። እንተ ነበረ ዐሪጎ መልዕልተ ነዋኅ ማኅፈድ። ለአህጒሎ ንጉሥ ከሀዲ ዓጻሬ ሰማዕታት በምክያድ። አይኅአ በጸሎቱ ወዘንመ ነድ። ምስለ ደመና ጸሊም ወጸዩዕ በረድ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 18። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥1-17። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አንተ ትኴንን ኃይለ ባሕር። ወአንተ ታረምሞ ለድምፀ ማዕበላ። አንተ አኅሠርኮ ለዕቡይ ከመ ቅቱል። መዝ 88፥9-10። የሚነበቡት መልዕክታ ሮሜ 10፥11-ፍ.ም፣ 2ጴጥ 3፥14-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 14፥26-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ኤዎስጣቴዎስና የአቡነ አኖሬዎስ የዕረፍት በዓል ሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

እርሱንም ገድሎታልና" ጥቅም የሌለው ብዙ ነገርንም መከራቸው እነርሱም እርሱ እንደ አባ ሙሴ መስሏቸው ይመልሱለት ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ሰይጣን እንደሆነ ለሊቅ ያዕቆብ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘበው ደቀ መዛሙርቱንም የቁርባን ቅዳሴ እንዲቀድሱ አዘዛቸውና ሥጋውንና ደሙን ከተቀበሉ በኋላ ሰይጣን መሆኑን ለልጆቹ መነኰሳት ነገራቸው። ❤ ሁለተኛም በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አምሳል ወደርሳቸው መጣ ከእርሱም ጋር በኤጲስቆጶሳት አምሳል አሉ። በደረሰም ጊዜ በላያቸው ተኰሳተረ "ከዚህ ልትኖሩ ማን ፈቀደላችሁ" ብሎ አወገዛቸው ሊቅ ያዕቆብም አይቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እጆቹን ዘርግቶ ጸሎትን አደረገ። ወዲያውኑ ሰይጣን ተበተነ ግን መፈታተኑን አሁንም አልተወም በሚአስፈራ ዘንዶ አምሳልም ወደ አባ ያዕቆብ የሚመጣበት ጊዜ አለ። በንጉሥ አምሳልም ደም ግባታቸው በሚያምር ደናግል አምሳልም በአሞራዎችና በቁራዎች አምሳልም ሁኖ በጥፍሮቻቸው ፊቱን እየነጩ በእንዲህ ያለ ፈተና ሰባት ዓመት ተፈተነ ከዚህም በኋላ ትዕግሥቱንና ድካሙን እግዚአብሔር አይቶ መብረቅን ልኮ ሰይጣንን ቀጥቅጦ በተነው "ያዕቆብ ሆይ ከአንተ የተነሣ ወዮልኝ በጸሎትህ አቃጠልከኝ" እያለ ሸሸ ። ❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር አብዲን ወደሚባል ገዳም እንዲሔድ ሊቅ ያዕቆብን አዘዘው። እርሱም ለልጆቹ መነኰሳት ይህን ነገራቸው ከዚያም ግንብ ውስጥ እንዲኖሩ አማፀናቸው። እርሱ ግን ብቻውን ወደ ኢያሪኮ ባሕር ዳርቻ ሔደ መርከብንም በአጣ ጊዜ በባሕሩ ሞገድ ላይ ባረከ ገብቶም ወደ ተርሴስ አገር እስከ ገባ ድረስ በባሕሩ ላይ እንደ ደረቅ ምድር ሔደበት። ❤ በሀገሩ ጥጋጥግ አልፎ ሲሔድ በትል የተከበበ ቁስለኛ ሰው አገኘና ሊቅ ያዕቆብ "ስምህ ማነው" ብሎ ጠየቀው እርሱም "ስሜ እንጦኒ ነው አባቴም ለባለ መድኃኒቶች ብዙ ገንዘብ ሰጠልኝ ሊፈውሱኝ አልቻሉም"። መምህር ያዕቆብም ስለ ደዌው ተከዘ ጸሎትንም አድርጎ ሁለመናውን በመዳሰስ "ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጤነኛ ሁን" አለው ወዲያውኑ ዳነ ደቀ መዝሙሩም ሁኖ ተከተለው። ❤ ከዚህም በኋላ ከረድኡ ጋር ሲጓዝ ሀገረ ዐምድ ደረሱ የንጉሥ አንስጦስን ልጅ እየአበደ ራሱን በደንጊያ ሲደበድብ አገኙት እርሱን መያዝም የሚችል አልነበረም። ሊቅ ያዕቆብም ይዞ ያመጣለት ዘንድ ረድኡን አዘዘው በአቀረበለትም ጊዜ በከበረ መስቀል ምልክት አማተበበትና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሰውዬው ወጥቶ እንዲሔድ ሰይጣንን አዘዘው። ያን ጊዜም በጥቁር ባርያ አምሳል ወጣ የንጉሡም ልጅ በከበረ ሊቅ ያዕቆብ ጸሎት ዳነ አባቱና ወገኖቹ ሁሉ በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው ንጉሡም ለከበረ ሊቅ ያዕቆብ ብዙ ገንዘብ ሊሰጠው ወደደ እርሱ ግን አይሆንም አለ ምንም ምን አልተቀበለም። ❤ ክብር ይግባውና በእግዚአብሔርም ትእዛዝ አብዲን በሚባል አገር የገዳም አበ ምኔት ከሆነ ከአባ በርሳቦ ጋር ተገናኝተው በአንድነት ተጓዙ በጒዞ ላይም እያሉ እንጦኒ በሆድ ተቅማጥ በሽታ ታመመና በሦስተኛው ቀን ዐረፈ ቀበሩትም። ስሟ አውርሳ ከሚባል አገር በደረሱ ጊዜ የአገረ ገዥውን ልጅ ታሞ አገኙት በሊቅ ያዕቆብም ጸሎት ዳነ መኰንኑም ልጁ እንደ ዳነ አይቶ በታላቅ ደስታ ደስ አለው እስከ ዕለተ ሞቱ ረድዕ ይሆነው ዘንድ ለከበረ ያዕቆብ ልጁን ሰጠው የልጁም ስም ፍቁር ነው ። ❤ ወደ ሊቅ በርሳቦ ገዳምም በቀረቡ ጊዜ መነኰሳቱ ተቀበሏቸው በብዙ ምስጋናም እየዘመሩ አስገቧቸው በዚያችም አገር ጎን የታነፀ የጣዖት ቤት አለ ስሙ ሰሚር የሚባል የፋርስ ንጉሥ በየዓመቱ እየመጣ ለጣዖታት በዓልን ያከብራል የከበረ ሊቅ ያዕቆብም መነኰሳቱን እንዲህ አላቸው "እነሆ የፋርስ ንጉሥ እንደመጣ ሰምታችኋል የክብር ባለቤት ስለ ሆነ ክርስቶስ ስለ ስሙ ኑ ደማችንን እናፍስስ"። ❤ መነኰሳቱም በዚህ ምክር እየተስማሙ ሳሉ የንጉሡ ጭፍሮች ወደዚያ ገዳም ደረሱ መነኰሳቱንም ጥቁር ልብስን ለብሰው አዩአቸውና "እናንተ ምንድን ናችሁ? ከአምልክትስ ማንን ታመልካለችሁ?" አሏቸው። ቅዱሳን መነኰሳትም እንዲህ አሏቸው "እኛ ከሰማያት የወረደውን በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆነ የሕያው እግዚአብሔርን ልጅ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እናመልከዋለን" ጭፍሮችም ወደ ንጉሥ አቀረቧቸው። በደረሱም ጊዜ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ ስም በንጉሡ ፊት ታመኑ ንጉሡም ሀገራቸውን መረመረ አባ በርሳቦም የእኔና የወንድሞቼ መነኰሳት አገራችንም ሮም ነው አለ ። አባ ያዕቆብም የእኔ አገር ግብጽ ነው አለ ንጉሡም የአባ ያዕቆብን ቃል ሰምቶ ሊገድለው አልፈለገምና ብቻውን ገለል እንዲያደርጉት አዘዘ ። ከግብጽ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን ስላለው መነኰሳቱን ግን ደማቸው እስቲፈስ ገርፈው ከእሥር ቤት እንዲጥሏቸው አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ ፈወሳቸው ። ❤ በማግሥቱም ጤነኞች ሁነው በአገኛቸው ጊዜ ብዙ ሀብት እንደሚሰጣቸው ተስፋ ሰጣቸው እነርሱ ግን ቃሉን አቃለሉ። ንጉሡም በወይን መርገጫ ውስጥ በማስረገጥ በግርፋት ጥርሶችን የእጆችንና የእግሮች ጥፍሮችን በማውለቅ ሰባት ቀኖችም ያህል አፍንጫን፣ ከንፈርን፣ ጆሮዎችን በመቆረጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ። በስምንተኛውም ቀን ራሶቻቸውን ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ መምህራቸው ሊቅ በርሳቦም እየአንዳንዱን ለሰያፊ ከሰጣቸው በኋላ ዐሥሩ መነኰሳት ተቆረጡ የንጉሡ የፈረሶች ባልደራስ ያን ጊዜ ለቅዱሳኑ የወረዱትን አክሊሎች አየ ትጥቁንም ፈትቶ ጥሎ ክብር ይግባውና በጌታችን ክርስቶስ ታመነ እርሱንም አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት መምህር በርሳቦም ልጆቹ ከተቆረጡ በኋላ አንገቱን ዘርግቶ ሰያፊውን "የታዘዝከውን ፈጽም" አለው ያን ጊዜም ሰያፊው ቆረጠው ምስክርነታቸውንም ነሐሴ ሃያ ስምንት ቀን ፈጸሙ። ❤ ንጉሡም ሥጋቸውን በእሳት እንዲአቃጥሉ አዘዘ ምድርም ተከፍታ ሥጋቸውን ሠወረች ንጉሡም አፍሮ ወደ አገሩ ሊሔድ ወደደ። ያን ጊዜም አባ ያዕቆብ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ከሰማይም ከጠቆረ ደመና ጋርና ከሚከረፋ በረድ ጋር እሳት በንጉሡ ላይ ዘነመ ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ተቃጥሎ ጠፋ ከእነርሱ አንድ እንኳ አልቀረም ። ❤ የዚያች አገር ሰዎችም በሰሙ ጊዜ ሁሉም ወጥተው ፈረሶቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ገንዘባቸውንም ወሰዱ ወደ ሊቅ ያዕቆብም አምጥተው እሊህን ገንዘቦች ለምትሻው ሥራ ውሰድ" አሉት። እርሱም አልተቀበላቸውም ግን በሰማዕታት መቃብር ላይ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ አዘዛቸው ቤተ ክርስቲያኒቱም እስከ ዛሬ አለች። ❤ ከዘመናትም በአንዲቱ አገር ቸነፈር ሆነ ወደ ሊቅ ያዕቆብ እንዲጸለይላቸው ላኩ እርሱም ሰምቶ እጅግ አዘነ ማዕጠንትም ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ረጅም ጸሎት ጸለየ ዕጣንንም አሳረገ። ከዚያም ወጥቶ መልእክተኞችን "አትፍሩ አትጨነቁ በሰላም ሒዱ" አላቸው። በደረሱም ጊዜ አገሪቱን ጤነኛ ሁና አገኟት ደስ ብሏቸው የሊቅ ያዕቆብን አምላክ አመሰገኑት። ❤ ዳግመኛም ለከበረ ሊቅ ያዕቆብ ዳንኤል የሚባል ረድእ ነበረው ደግሞ ለቅዱስ ያዕቆብ ወዳጁ የሆነ አገር ገዥ አለ ለአገረ ገዥውም ወደ ቅዱስ ያዕቆብ ከአባቷ ጋር የምትመጣ ብላቴና አለችው ረዱን ዳንኤልን በኃጢአት ልትጥለው ፈለገችው እምቢ ባላትም ጊዜ ከአባቷ አገልጋይ ፀነሰችና በሊቅ ያዕቆብ ረድእ አመካኘችበት አባቷም ሰምቶ መምህር ያዕቆብንና ደቀ መዝሙሩን ሊገድል ሔደ በጒዞ ላይም ሳለ በላዩ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ ዐይኖቹን አሳወረው። ❤ የመኰንኑም ልጅ ከወለደች በኋላ ወደ ከበረ መምህር ያዕቆብ በጉባኤ መካከል "ሕፃኑን አባትህ ማን እንደሆነ ትናገር ዘንድ ክብር ይግባው

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ በሕንድ አገር ላደረገው ተአምር መታሰቢያ በዓል፣ በከሀዲው ዩልያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለ ሌላው ለቅዱስ መርቆሬዎስ ለዕረፍቱ በዓልና መስተጋድል ለሆነ ለግብጻዊው ሊቅ ለቅዱስ ያዕቆብ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ ከመስቀሉ በዓል መታሰቢያ፣ ከጻድቁ ንጉሥ ከቈስጠንጢኖስ እናት ከሆነች ከቅድስት ዕሌኒ ከመታሰቢያዋ፣ ከቀሲስ እስጢፋኖስና ከሰማዕት ቅዱስ ነኪጣ ከመታሰቢያቸው፣ ከቅዱስ ቶማስና ከሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ ዐፅማቸው ከተገኘበት ድንቅ ተአምራት ከሚያደርግ ከአባ ፊላታዎስና ከባሕታዊ አባ ኖብ ከቅዱስ አቦሊም ማኅበር ከሆኑ ከአርባ ወንዶችና ከሃያ ሴቶች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ በሕንደኬ አገር ያደረገው ተአምር፦ ቶማስም በሕንድ አገር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ለመሔድ በተነሣ ጊዜ "ወደዚያች አገር መግባትን እንዴት እችላለሁ" ብሎ አሰበ። ይህንንም ሲያስብ እነሆ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና "አትፍራ ቸርነቴ ከአንተ ጋር ትኖራለችና" አለው። ወዲያውኑ ከሕንደኬ የጎና ነጋዴ አቤኔስ መጣ ጌታችንም "ምን ትሻለህ" አለው ነጋዴውም "ሐናፂ የሆነ ባሪያ እሻለሁ" አለ። ጌታም "ይህን ባሪያዬን ገዝተህ ውሰድ እርሱ አናፂ ነውና" አለው ከዚህም በኋላ በሦስት ወቄት ወርቅ ሸጠው እንዲህም ብሎ ጻፈለት "የጠራቢ ዮሴፍ ልጅ የሆነ ባሪያዬን ለጎና ነጋዴ ለአቤኔስ ሸጨዋለሁ"። ❤ ከዚህም በኋላ አቤኔስ ቅዱስ ቶማስን ተረክቦ ወደ አገሩ ወሰደው ወደ ከተማውም በቀረቡና በደረሱ ጊዜ የእንዚራና፣ የመሰንቆ፣ የዛጉፍ፣ የእምቢልታ ድምፅ ሰምተው "ይህ ምንድን ነው" አሉ። ሰዎችም "ንጉሥ ለሴት ልጁ ሠርግ አዘጋጅቷል ወደ ንጉሡ ሠርግ ያልሔደውን እንዲቀጡት ንጉሥ አዟል" አሏቸው። ይህንን ሰምተው አቤኔስና ቅዱስ ቶማስ ወደ ሠርጉ ሔዱ ሁሉም ሲበሉና ሲጠጡ ሐዋርያ ቶማስ ምንም አልቀመሰም በዚያም ዕብራዊት የሆነች አዝማሪ አለች። በሠርጉ ምሳ ላይ ከሚያገለግሉ ውስጥ አንድ ሰው ሐዋርያ ቶማስን በጥፊ ፊቱን ጸፋው ሐዋርያውም በዕብራይስጥ ቋንቋ "ይቺን እጅ ውሾች ሲጎትቷት አያታለሁ" አለ አዝማሪዋም ብቻዋን ሰማችው። ❤ ይህም በጥፊ የመታው ውኃ ሊቀዳ ወደ ውኃ ጉድጓድ ወረደ አንበሳም መጥቶ ገደለውና በታትኖ ተወው አንድ ውሻም የቀኝ እጁን ይዞ ወደ ምሳ መካከል ወሰዳት ከዚያ ያሉትም "ማን ነው የሞተ" አሉ ሰዎችም "ይህን እንግዳውን በጥፊ የመታው ያ አሳላፊ" ነው አሏቸው። አዝማሪዋም በሰማች ጊዜ ወደ ሐዋርያው ሒዳ በአጠገቡ ቁማ "በጥፊ የመታችኝን እጅ ውሾች ሲጎትቷት አያታለሁ ሲል እኔ ስምቼዋለሁ" አለች በዚያ ያሉትም ሁሉ ይህን ሰምተው አደነቁ። ❤ ይህም ነገር በንጉሡ ዘንድ በተሰማ ጊዜ ንጉሡ ወደ ሐዋርያው መጥቶ "ዛሬ አጋብቻታለሁና ና በልጄ ላይ ጸሎት አድርግ" አለው። ሐዋርያው ቶማስም ወደ ጫጒላ ቤት ገብቶ ስለ ሙሽሮቹ ወደ ጌታችን ጸለየ የሃይማኖትንም ቃል አስተምሮ ባረካቸው በሐዋርያውም ቃል አመኑ። ጌታችንም ደግሞ በቶማስ አምሳል ተገልጦላቸው እርሱም ሃይማኖትን አስተማራቸው እነርሱም አመኑበት ጽምረታቸውንም ትተው ድንግልናቸውን ጠበቁ ንጉሥም ክብር ይግባውና በጌታችን ክርስቶስ አመነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሰማዕቱ ካልዕ ቅዱስ መርቆሬዎስ፦ እርሱም አስቀድሞ ክርስቲያን የነበረ ነው። የታላቁ ቈስጠንጢኖስ ልጅ ሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ በሞተ ጊዜ የቈስጠንጢኖስ እኅት ልጅ ዩልያኖስ ነገሠ እርሱ ግን ጣዖታትን አመለከ ሰገደላቸውም የክርስቲያን ወገኖችንም አሠቃያቸው ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ዐረፉ። ❤ የንጉሡም የልደቱ ቀን በሆነች ጊዜ የሳቅ የሥላቅ የሆኑ ተጫዋቾችን ሰበሰባቸው ይህ ቅዱስ መርቆሬዎስም ቁጥሩ ከእሳቸው ጋር ነበር ካህናት በቤተክርስቲያን እንደሚያደርጉት በክርስትና ሥርዓት እንዲጫወት ይህን መርቆሬዎስን ከሀዲው ንጉሥ አዘዘው እንዳዘዘውም በክርስትና ሥርዓት ሁሉ ተጫወተ ታላቅም ሳቅና ሥላቅ ሆነ። ❤ ሁለተኛም በክርስትና ጥምቀት ሥርዓት ሊጫወት ጀመረ በመስቀል ምልክት "አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያለ" በውኃው ላይ አማተበ። ያን ጊዜም መለኮታዊ ብርሃን በውኃው ውስጥ ወረደ እግዚአብሔርም የልቡናውን ዐይን ገልጦለት ያንን ብርሃን አየው ልብሱን ጥሎ ራቁቱን ወደ ውኃው ወርዶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ ተጠመቀ ። ❤ ከዚህም በኋላ ወጥቶ ልብሱን ለበሰ በንጉሡም ፊት ቆሞ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ንጉሡም በርሱ ላይ ተቆጣ እንዲህም ብሎ አስፈራራው ለእኔ በመታዘዝ ለአማልክት ዕጣንን ካላሳረግህ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይሃለሁ ትእዛዜን ከተቀበልክ ግን እኔ ብዙ ገንዘብ ሰጥቼህ እጅግ አከብርሃለሁ ። ❤ ቅዱስ መርቆሬዎስም የዚህን ዓለም ገንዘብ ሁሉና መንግሥትንም ብትሰጠኝ ጌታዬ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ብሎ መለሰለት ። ያን ጊዜም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ ንጉሡ አዘዘና ቆረጡት በሰማያዊት መንግሥትም የማይጠፋ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ካልዕ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ግብጻዊ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ፦ ወላጆቹም ደጎች ምእመናን ነበሩ ይህንንም ቅዱስ አገልጋይ ሊሆን ለእግዚአብሔር ሰጡት። ትምህርቱንም በአደረሰ ጊዜ በእስክንድርያ ወደ አለ ገዳም ወላጆቹ ወሰዱት ለአበ ምኔት አባ ገብርኤልም ሰጡት። እርሱም ተቀብሎ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሁኖ ሳለ አመነኰሰው። ❤ ከዚህም በኋላ ሃያ ዓመት ሲሆነው ለተጋድሎ ከመምህሩ ጋር ወደ በረሃ ወጡ ከፍታ ያላት ግንብንም አግኝተው አባ ገብርኤልና አባ ያዕቆብ ከላይዋ ላይ ወጡ። ከዚያም የውኃ ጉድጓድ አለ ከዚያም ጉድጓድ ውኃ እየቀዱ በገንዳዎች ላይ ያፈሳሉ የዱር እንስሶችም ሁል ጊዜ እየመጡ ከገንዳው ውኃ ይጠጣሉ አባ ያዕቆብም ያልባቸዋል ወተታቸውንም አይብ አድርጎ ከመምህሩ ጋር ይመገባሉ። ❤ አባ ገብርኤልም በዐረፈ ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ ዐሥራ ሁለት ገዳማውያን መጡ በጾምና በጸሎትም በመትጋት የእንስሶቹን ወተት በመመገብ ከእርሱ ጋር ተቀመጡ ለገዳሙ የሚያስፈልገውን ግን ነጋዴዎች ሥንዴን ከሩቅ ያመጣሉ። ❤ ከዕለታትም በአንዲቱ ዕለት እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ "አባ ሙሴ ጸሊምን ብናየው ከእርሱም ብንባረክ እንወድ ነበር"። ሰይጣንም በሰማ ጊዜ በመፋቀራቸው ቀንቶ በሙሴ ጸሊም አምሳል በክንፍ እየበረረ መጣ "ሽማግሌ ስሆን ከቦታዬ ለምን አናወጻችሁኝ" አላቸው። እነርሱም "የሕይወትን ቃል ከአፍህ ልንሰማ ከአንተም በረከትን ልንቀበል እንወዳለን" አሉት ደግሞ "ኑሮአችሁ እንዴት ነው" አላቸው። እነርሱም ለዱር እንስሶች በገንዳ ላይ ውኃን እንደሚቀዱ ውኃውንም ሊጠጡ ሲመጡ እንደሚአልቧቸውና ሁል ጊዜ በየማታው ከወተታቸው እንደሚመገቡ ነገሩት ። ❤ ሰይጣንም እንዲህ አላቸው "የአዘዝኳችሁን ትሰማላችሁን" አላቸው "አዎን እንሰማሃለን" አሉት ። ዳግመኛ እንዲህ አላቸው "የእንስሶቹን ወተት አትጠጡ እናንተ መነኰሳት ስትሆኑ አታምጡአቸው ጾምን ግን በየአርባ ቀን ጹሙ የዳዊትንም መዝሙር አትጸልዩ እርሱ በዐመፅ የኦርዮን ሚስት ነጥቋልና።

photo content

photo content