fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "አባ ዮሐኒ ጸገየ ሕይወተ። ፈረየ ሠላሳ ወስሳ ወምእተ። ብሔረ ሕያዋን ተመሥጠ ግብተ። ዘዐይን ኢርዕየ ነሥአ ዕሤተ"። ትርጉም፦ አባ ዮሐኒ ሕይወትን አብቦ፤ ሠላሳ፣ ስሳንና፣ መቶን አፈራ፤ ወደ ሕያዋን አገር በድንገት ተነጥቆ ዐይን ያላየውን ዋጋ አገኘ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ "ሶበ ዴገነኪ አርዌ በሊዐ ሕፃንኪ ዘኀለየ። በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጐዪየ። አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ። ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሓየ። ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ"። ትርጉም፦ ፀሐይን የምትለብሺ (እውነተኛ ፀሐይ የተባለ ጌታን የወለድሽ) የሰማይ እመቤት ማርያም ሆይ ልጅሽን ለመግደል ያሰበ አውሬ ሄሮድስ በተከተለሽና ወደ በረሀ ፈጥነሽ በምትሸሺበት ጊዜ ክንፍን እንዳወጣ እንደ አባ ዮሐኒ ክንፍን ስታወጪ ያየ ዮሐንስ፣ ተአምርሽን ጻፈ። ሊቁቆቹ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማኅሌተ ጽጌ ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content
+1

❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ክብር ይግባውና ጌታችን በዕጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን ለወጋው ለቅዱስ ለጊኖስ ራሱ ለታየችበት፣ ለሠራዊት አለቃ ለቅዱስ ቴዎድሮስም ከአገረ ሰጥብ ወደ አገረ አስዩጥ ሥጋው ለፈለሰበትና ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሰማዕት ጢሞቴዎስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግዕዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "በከመ አቡነ አብርሃም ኢሐነጸ ቤተ ወከማሁ አባ ዮሐኒ ነበረ አድባረ ወበዓታተ ገብ ኄር ዘወውኁድ ምዕመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ አሰይመከ"። ትርጉም አባታችንን አብርሃምን ቤትን እንዳልሰራ እንዲሁ አባ ዮሐኒ በበዓትና በተራራ ተቀመጠ ቸር ባርያ (አገልጋይ) በጥቂት የታመንህ ሆንክ በብዙ እሾምሀለሁ"። + + + ❤️ በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ ጐኑን የወጋ የቅዱስ ለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ነው። ይህም ቅዱስ በጌታችን ከአመነ በኋላ በቀጰዶቅያ አገር ወንጌልን የሚሰብክ ሆነ ከሀድያን አይሁድም በላዩ ተነሡበት በመኳንንት ዘንድ በሐሰት ወንጅለው በቀጰዶቅያ አገር ራሱን አስቆረጡት ራሱንም ብቻዋን ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱዋት። በኢየሩሳሌም የሚኖሩም አይሁድ በአዩዋት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ከዚህም በኋላ ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሩዋት። ❤ ከብዙ ቀኖችም በኋላ እንዲህ ሆነ በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች አንዲት ሴት በቀጰዶቅያ አገር ነበረች ራሱን ከቆረጡት ጊዜ ጀምራ በተቆረጠበት ቦታ በመቆም ስለርሱ ታለቅስ ነበር ክብር ይግባውና በእግዚአብሔርም ፈቃድ የዚያች ሴት ዐይኖቿ ታወሩ። ❤ ከዚህም በኋላ ምናልባት ዐይኖቿ ቢገለጡላት በማሰብ ከከበሩ ቦታዎችና ክብር ይግባውና ከጌታችን መቃብር ለመባረክና ለመለመን ተነሥታ ልጅዋን ይዛ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች። ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሰች ጊዜ በዚያ ልጅዋ ሞተ ኀዘንም ተጨመረባት ወደ አገርዋም መርቶ የሚያደርሳት አጣች ስለዚህም የመረረ ልቅሶን አለቀሰች ከኀዘኗምብዛት የተነሣ ተኛች። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞተው ልጅዋ ጋር በሕልሟ አየችው። "ዕገሌ ከሚባልም ቦታ ሒደሽ ራሴን ከዚያ ውሰጂ" አላት። ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ስለዚህ ቦታ ጠየቀች ሰዎችም ወደርሱ አደረሱዋት። ያንንም ቦታ በቆፈረች ጊዜ መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ ወጣ። ራሱ ወደአለችበት ስትደርስ ታላቅ ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿም በዚያን ጊዜ ተገለጡላት እግዚአብሔርንም አመሰገነች። ❤ ከዚህም በኋላ ከልጅዋ ሥጋ ጋር የቅዱስ ለንጊኖስን ራስ ወደ አገርዋ ወሰደቻት። በታላቅ ክብርም በአማረ ቦታ አኖረቻት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ለጊኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 5 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለከ ጢሞቴዎስ ቡሩክ። ሰማዕተ አምላክ። ብእሲ ሰማያዊ ወምድራዊ መልአክ። ኅብአኒ በክነፊከ በዕለተ ምንዳቤ ወሀውክ። እምነ ልሳን ምዑክ ወእምዐይን ድሩክ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 5። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ኃጢአትየ ዘበንስየእ ወዕበድየ ኢትዝክር ሊተ። ወበከመ ሣህልከ ተወከረኒ። በእንተምሕረትከ እግዚኦ"። መዝ 24፥7። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥8-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥9-13 እና የሐዋ ሥራ 26፥12-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 19፥31-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ዮሐኒ ከሞት የተሰወሩበት (የስዋሬ) በዓል፣ የአባ አሞኒ የዕረፍት በዓልና የተፈፀመ ጽጌ ማኅሌት። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content
+1

❤ አባ አሞኒ ካረፉ ከ12 ዓመት በኋላ የአባ ዮሐኒ ወላጅ እናታቸው የልጇን ነገር ስታጠና ኖራ ነበርና አሁን ባሏም ስለሞተ አባ አሞኒም ስላረፉ ልጇን ልታይ ከ 32 ዓመት በኋላ መጣች፡፡ ቀሚስ ለብሳ ፀጉሯን ተሠርታ በሴትነቷ ልጇ ካለበት ቦታ በመሄድ ማነጋገር እንደማትችል ስላወቀች ፀጉሯን ተላጭታ የወንድ ልብስ ቁምጣ ለብሳ በሁለመናዋ ወንድ መስላ ወደ ደብረ ዓሣ ተራራ አመራች፡፡ እዚያም እንደደረሰች በቅዱሳን ሥርዓት መሥረት ሦስት ጊዜ "አውሎግሶን፣ አውሎግሶን፣ አውሎግሶን" አለች፡፡ ሰይጣን ይህን ስም ሲሰማ 40 ክንድ ይርቃል፡፡ የደብረ ዳሞ መነኰሳት እንደ ሰላምታ መለዋወጫ ይጠቀሙበታል፡፡ አባ ዮሐኒም ይህን ድምጽ ከውጭ በሰሙ ጊዜ "አንተ ማነህ?" አሉ፡፡ እርሷም "ዓመተ መንፈስ ቅዱስ ነኝ" አለቻቸው፡፡ አባታችንም አንድም ድምፁዋ ወትሮ ከሚያውቁት ድምፅ ስተለየባቸው ደግሞም ትዝ ሲላቸው እነዚያ እንስራ አዝለው ደረታቸው ላይ ቀንድ ያላቸው ሆነው ውኃ ቀድተው ሲሄዱ በመነገድ ያዩአቸው ሴቶች ድምፅ ሆነባቸው፡፡ ደግሞም "ወልደ እከሌ፣ ክንፈ እከሌ" ሲባል እንጂ "ዓመተ፣ ወለተ" ሲባል ሰምተው አያውቁም ነበርና አባታቸው አባ አሞኒ የነገሯቸው ትዝ አላቸው፡፡ በዚያውም ቅጽበት የሚጽፉባትን ብዕር ጆሮአቸው ላይ እንደሰኩ 500 ሜትር ርዝመት ካለው ትልቅ ተራራ ላይ ራሳቸውን ቁልቁል ወረወሩ፡፡ ነገር ግን መሬት ሳይደርሱ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአየር ላይ እንዳሉ ተቀበላቸው፡፡ ብዕራቸው ግን መሬት ላይ ወድቃ ሸምበቆ ሆነች፡፡ ወዲያውም አባ ዮሐኒ ክንፍ አውጥተው ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ጎን ለጎን ሆነው በዛሬው ዕለት ኅዳር 5 ቀን ወደ ብሔረ ሕያዋን ይዟቸው ገባ፡፡ ❤ ብሔረ ሕያዋን ያሉ እነ ሄኖክና ኤልያስም "ሰው ከሚሞትበት ሀገር ሞት ወደሌለበት አገር ማን አመጣው?" አሉ፡፡ መልአኩም በዚህ ጊዜ "እግዚአብሔር ባዘዘኝ ጊዜ እኔ ገብርኤል ነኝ ያመጣሁት" አላቸው፡፡ ቀጥሎም መልአኩ "አንተ ሄኖክ ምንም ንጹሕ ብትሆን በሥርዓተ ሥጋ ተወልደህ በሥርዓተ ሥጋ አድገህ ሚስት አግብተህ ወልደሃል፣ እግዚአብሔርም እዚህ ያደረሰህ በንፅህናህ ነው፤ አንተም ኤልያስ ምንም ድንግል ብትሆን በሥርዓተ ሥጋ ተወልደህ በሥርዓተ ሥጋ አድገህ ከዚህ ደርሰሃል፤ ይህ አባ ዮሐኒ ግን ከተወለደ ጀምሮ የእናቱን ጡት አልቀመሰም፣ ቀን ቀን ሰሳ እያጠባችው ሌሊት ሌሊት ንስር አሞራ በክንፎቹ እያለበሰው አድጓል እንጂ" ብሎ ነገራቸው፡፡ ቀጥሎም መልአኩ የአባ ዮሐኒን ገድል ዘርዝሮ ከነገራቸው በኋላ ሊሞት ያለበትንም የአሟሟቱን ነገር ከነገራቸው በኋላ "ታዲያስ እንዲህ ያለውን አምጥቼ ከብሔር ሕያዋን ባስገባው ፍርዴ እውነት አይደለምን" አላቸው፡፡ ሄኖክና ኤልያስም ይህን ጊዜ "ይገባዋል" ብለው አባ ዮሐኒን በምስጋና ተቀበሉት፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ደብረ ዓሣ ተመልሶ መጥቶ ለአባ አበይዶ ተገለጠላቸውና አባ ዮሐኒን ብሔረ ሕያዋን እንዳስገባው ነገራቸው፡፡ በመጀመሪያ ሄኖክና ኤልያስ አላስገባ ብለው እንደነበርና በኋላም መልአኩ ራሱ የአባ ዮሐኒን ገድላቸውን ከነገራቸው በኋላ በምስጋና እንደተቀበሉት ለአባ አበይዶ ነገራቸው፡፡ ቀጥሎም መልአኩ የአባ ዮሐኒን ገድላቸውን እንዲጽፉትና እንዲያስተምሩበት ለአባ አበይዶ አዘዛቸውና ዐረገ፡፡ አባ አበይዶም አባ ዮሐኒ ከገደሉ ተወርውረው ሲወደቁ አንድ ደስ የሚል ወንድ ሲቀበለው አይተው ነበርና አሁን መልአኩ ሲነግራቸው እጅግ ደስ አላቸው፡፡ አባ አበይዶም በታዘዙት መሠረት የአባ ዮሐኒን ገድል ጻፉት፡፡ እርሳቸውም ትናንት ኅዳር 4 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ ❤ በፎቶው ላይ እንደምታዩት ተንቤን የሚገኘው የአባ ዮሐኒ ቤተ ክርስቲያን አቀማመጡ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ ተራራው መሀል ላይ ወደሚገኘው ቤተ ክርስቲያኑ ለመውጣት 150 ሜትር ተራራውን መውጣት ይጠይቃል፡፡ ሽቅብ ከተወጣ በኋላ አፈ ጽዮንን ትገኛለች፡፡ ከአፈ ጽዮን በኋላ ከድንጋይ የተፈለፈለ 12 መድረክ ያለው የውስጥ ለውስጥ የጨለማ መንገድ አለ፡፡ በመጨረሻ ብርሃን ወዳለብ ስፍራ ሲወጣ በስተግራ በኩል 12 ሜትር ርቀት ላይ ቤተ መቅዱሱ ይገኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ 13 ጉልላቶች አሉት፡፡ ገዳሙ ጥንት 58 ዓምደ ወርቅ ነበረው፡፡ በአንድ ወቅት በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት 22ቱ ሲሰባበሩ አሁን ያሉት 36ቱ ብቻ ናቸው፡፡ ገዳሙ ውስጥ ሦስት ቤተ መቅደሶች ያሉ ሲሆን አንዱን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይቀድሱበት የነበረው ነው፡፡ ገዳሙ ደብረ ዓሣ እየተባለ ይጠራል፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያኑ በመሬት መንቀጥቀጥ ከመፍረሱ በፊት ጣራው የዓሣ አንበሪ ቅርጽ ነበረው፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀልም በወቅቱ በዚህ ዓሣ ምስል ያሠሩት ቅዱስ መስቀል በገዳሙ ውስጥ ይገኛል፡፡ አንድም ደግሞ በመጀመሪያ ዐፄ ገብረ መስቀል እና ሌሎቹም ቅዱሳን አበው በገዳሙ ውስጥ ሱባኤ ገብተው ሳለ ቅዱሳን በዓሣ ተመስለው ሲወጡና ሲገቡ በማየታቸው ነው ገዳሙ "ደብረ ዓሣ አባ ዮሐኑ" የተባለው፡፡ ❤ ሌላው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ ድንቅ በሆነው በዚህ ገዳም ውስጥ አስገራሚ የመቃብር ጉድጓዶች አሉት፡፡ መቃብሮቹ የተፈለፈሉ ዋሻዎች ናቸው፡፡ አንዱ ዋሻ በአንድ ጊዜ ከ6 ሰዎችን ጎን ለጎን አስተኝቶ መያዝ አይችልም ነገር ግን በጣም የሚገርመው የመቃብር ጉድጓዶቹ እስከዛሬም ድረስ አልሞሉም፡፡ አንድ ሰው ከተቀበረ ከዓመት በኋላ አስክሬኑ ይጠፋል፣ አጥንቱም አይገኝም፡፡ ሰሌኑ ግን እስከ ሁለት ዓመት ይቀመጣል፡፡ ለአባ ዮሐኒ ለዚህ ገደማቸው ዕጣን ጧፍ ዘቢብ የሰጠ ሰው ቢኖር ስጦታውን እንደ አቤል መሥዋዕት አድርጎ ጌታችን እንደሚቀበልለት ለጻድቁ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከአባቶቻችን ከአባ አሞኒ ከአባ ዮሐኒና ከአባ አበይዶ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ከገድላት አንደበት። + + + ❤ "ሰላም እብል ለዘኮነ ሱቱፈ። ምስለ እለ ገብሩ ሰብእ ብሔረ ሕያዋን ምዕራፈ። እምሥርዓተ መላእክት ዮሐኒ ምንተኒ ኢያትረፈ። ከመ ሕይወቶሙ ሕይወተ ተጸገወ ዘልፈ። ወከመ ክንፎሙ አብቈለ አክናፈ"። ትርጉም፦ ብሔረ ሕያዋንን ማረፊያን ካደረጉ ሰዎች ጋር ኅብረትን ያደረገ ለኾነ ሰላም እላለኍ፤ ዮሐኒ ከመላእክት ሥርዐት ምንም ምን አላስቀረም፤ እንደ ሕይወታቸው ሕይወትን ተቀበለ (ተቸረ)፤ እንደ ክንፋቸውም ክንፎችን አበቀለ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 5። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፭ (5) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ለታላቁ አባት ለአቡነ ዮሐኒ እንደ መላእክት ክንፍ አብቅለው (ተሰቷቸው) ወደ ብሔረ ሕያዋን በመግባት ከሞት ለተሰወሩበት ለመታሰቢያ በዓላቸውና አባ ዮሐኒን ላሳደጉ ላስተምረው ለታላቁ አባት ለአቡነ አሞኒ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ሰላም ለአባ ዮሐኒ ከመ ንህብ ዘተመሰለ፤ እምኵሎሙ ቅዱሳን ዘአስተጋብአ ገድለ"። ትርጉም፦ እንደ ንህብ የተመሰለ ኾኖ ከቅዱሳን ኹሉ ገድልን የሰበሰበ ለኾነ ለአባ ዮሐኒ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤️ አቡነ አሞኒና ልጃቸው አቡነ ዮሐኒ ደቀ መዝሙራቸው አባ አበይዶ፡- የአባ ዮሐኒ አባታቸውን መጽሐፍ ዘስዩመ ተንቤን እሁሁ ይላቸዋል፡፡ እናታቸው ደግሞ ዓመተ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ ደገኛ ምግብራቸው ያማሩ ሀገር ወዳድ ናቸው፡፡ አቡነ አሞኒ የካቲት 5 ቀን አክሱም ውስጥ ሲወለዱ ሰይጣናት የወላጆቻቸውን ቤት ከበው በማየታቸው እንደተወለዱ በእጃቸው ቢያመለክቱ በአንድ ጊዜ 60 ሰይጣናት ተሸንፈው እንደጢስ በነው ጠፍተዋል፡፡ አሞኒ ማለት አሸናፊ ማለት ነው፡፡ ❤ አባ አሞኒ የራስ ፀጉራቸው ልብስ መጎናጸፊያ ሆኖላቸው የኖሩ ታላቅና ቀደምት አባት ናቸው፡፡ በደመና ተጭነው ደብረ ዘይት ድረስ በመሄድ ከአባ እብሎይ ጋር ተገናኝተው ብዙ ምሥጢርን አውርተዋል፡፡ አባ ዮሐኒን ያሳደጉት አስተምረው ያሳደጓቸው አባ አሞኒ ናቸው፡፡ የእናቱን ጡት ፈጽሞ ጠብቶ የማያውቀውን የመንፈስ ቅዱስ ልጃቸውን አባ ዮሐኒን እሳቸው እያጫወቱት የታዘዘ አሞራ በክንፎቹ እያለበሰው ቶራ (ሰሳ) እያጠባችው ነው ያደገው፡፡ መነሻ ታሪኩም እንዲህ ነው፦ የተንቤን አውራጃ ገዥ የነበረው ሰው በዘመኑ ዐፄ ካሌብ የነበሩበት ዘመን ነበርና አብሯቸው ወደ ምድረ ኖባ ሄደው ሰባት ዓመታትን የፈጀ የጦር ዘመቻ ክርስያኖችን በሚያሠቃዩ ነገሥታት ላይ አዳሄዱ፡፡ የተንቤኑ አውራጃ ገዥም ወደ ዘመቻው ከሄደ ቆይቶ ነበርና ታናሽ ወንድሙ የገዥውን ሚስት "ወንድሜ የቀረው ሞቶ ነው እንደ ኦሪቱ ሕግ እኔው ላግበሽና ልጆቹን ላሳድግ" አላት፡፡ እርሷም "ባሌ ቢሞት ይነገረኝ ነበረ ዘመቻ የሄደው ሁሉ አልተመሰም" ብላ እምቢ ብትለው በግድ ተገናኛት፡፡ በዚህም ጊዜ አባ ዮሐኒ ተፀነሱ፡፡ በሚያዝያ 5 ቀንም ተወለዱ፡፡ ❤ ከዘጠኝ ወር በኋላ ባሏ ከዘመቻ መጣና ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ የአካባቢውም ሰው ወጥቶ በክብር ሲቀበለው ሚስቱ ግን ምጥ ተይዛ ታማ ስለነበር ወጥታ አልተቀበለችውም፡፡ "የት ሄደች? ምንስ ሆነች?" ብሎ ሲጠይቅ ልጅ አይደብቅምና አንድ ሕፃን "አርግዛ ልትወልድ በምጥ ላይ ትገኛለች" አለው፡፡ የአውራጃውም ገዥ ያለችበት ድረስ ሄዶ ቢያያት ያማረ ወንድ ልጅ ታቅፋ አገኛት፡፡ ከዚህም በኋላ ከቤቱ ምሰሶ ጋር ጥፍንግ አድርግ አስሮ እየገረፋትና እያስጨነቃት ከማን እንዳረገዘች ጠየቃት፡፡ እርሷም የወንድሙን ምሥጢር ለመጠበቅና ወንድማማቾቹን ላለማጣላት ሥቃዩን ታግሳ ዝም አለች፡፡ በዚህ ቅጽበት የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል 40 ዓመት ሙሉ ዘግተው በበረሃ ለሚኖሩት ለአባ አሞኒ ተገለጠላቸው እንደ አውሎ ነፋስ አምዘግዝጎ ወስዶ አውራጃ አገረ ገዥው ቤት አደረሳቸው፡፡ ❤ እንደደረሱ ዓመተ መንፈስ ቅዱስ በጽኑ ድብደባና ግርፋት እየተሠቃየች እያለ አባ አሞኒ የጸጉራቸውን አጽፍ ለብሰው ራቁታቸውን ደጇ ላይ ቆመው አየቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ለባሏ "ያውና ከዚህ መነኲሴ ነው የወለድኩት" አለቸው፡፡ የተንቤኑ አውራጃ አገረ ገዥውም አባ አሞኒን ይዞ ጽኑውን ግርፋት በወታደሮቹ አስገረፋቸው፡፡ በመቀጠልም ገና የእናቱን ወተት እንኳን ያልቀመሰውን ጨቅላ ሕፃን አንሥቶ "እንካ ልጅህን ይዘህ ጥፋ ከዚህ" ብሎ ሰጣቸው፡፡ አባ አሞኒም በዚህ ጊዜ "ዮ ሀበኒ ዮ ሀበኒ" አሉ፡፡ በትግርኛ እሽ ስጠኝ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ነው ሕፃኑ በኋላ ላይ "አባ ዮሐኒ" የተባሉት፡፡ አባ አሞኒም ሕፃኑን ተረክበው ወደ ደብረ ዓሣ ተራራ ሥር ሄደው ልጁን ከወይራ ዛፍ ሥር አስተኝተው "አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ኃጢአቴን ተመራምረህ ይህንን ሕፃን የሰጠኸኝ አላጠባው ጡት የለኝ አላበላው እህል የለኝ" ብለው የጨቅላው ሕፃን ነገር እጅግ ቢያስጨንቃቸው ምርር ብለው አለቀሱ፡፡ ጸሎታቸውንም እንደጨረሱ ተራራውን በመስቀል ምልክት ቢባርኩት በተራራው መሐል ላይ እንደመደብ ያለ አልጋ በተአምራት ተሠርቶ አገኙት፡፡ ሕፃኑንም ከዚያ አስተኝተው ድጋሚ ጸሎት ሲጀምሩ ቶራ (ሰሳ) መጥታ እግርና እግሯን አንፈራጣ ሕፃኑን አጠባችውና ሄደች፡፡ ❤ አባ አሞኒም በዚህ ደስ ተሰኝተው ሕፃኑን "የምግብህ ነገር ከተያዘ ግዴለም" ብለው ሌሊቱን ሙሉ ሲጸልዩ አድረው መለስ ቢሉ ዳግመኛም ሕፃኑን የታዘዘ ንስር አሞራ በክንፎቹ ጋርዶ አልብሶትና አቅፎት እንዳደረ ተመለከቱ፡፡ አባታችንም እጅግ ደስ ተኝተው እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ቀን ቀን ቶራዋ እያጠባችው ሌሊት ሌሊት ንስር አሞራው አልብሶት እያደረ ሕፃኑ ሦስት ዓመት ሆነው፡፡ አባ አሞኒም ከሰባት ዓመቱ ጀምረው እስከ 12 ዓመቱ ድረስ ፊደል፣ ንባብ ከነትርጓሜው፣ ብሉይንና ሐዲስን፣ ምግባር ሃይማኖትን ሥርዓተ ቤተ ክርስያንን ሁሉ አስተማሩት፡፡ ❤ አባ አሞኒ ልጃቸው አድጎ 12 ሲሆነው ከዚህም በኋላ ዲቁና ሊያሾሙትና አክሱም ጽዮን ወስደው ሊያስባርኩት ቤተ ካህናት ከተባለው ቦታ ይዘውት ሲሄዱ ልዩ ስሙ ሲሂታ ከሚባለው ቦታ ሲደርሱ ከወገባቸው በላይ እራቁታቸውን የሆኑ እንስራ የተሸከሙ ዓሥር ሴቶች አገኙ፡፡ አባ ዮሐኒም አባታቸውን "አባቴ እነዚህ ደረታቸው ላይ ቀንድ ያላቸው ጽጉራቸው የረዘመ ምንድናቸው? እንደእኛ የሆኑ መስህታን የሚባሉት እነዚህ ናቸውን?" አሏቸው፡፡ አባ አሞኒም "አይደሉም ልጄ ዝም ብለህ ሂድ" አሏቸው፡፡ በኋላ ግን ትዝ ሲላቸው "በዱር እንስሳት ያሳደኩት ልጄ ወንድና ሴት ለይቶ ሲያውቅ በዚያው ሊሳሳት አይደልምን?" ብለው በማሰብ ዲቁናና ክህነቱ ይቅርበት ብለው ተመልሰው ወደ በዓታቸው ይዘውት ገቡ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ አባ አበይዶ ወደ አባ አሞኒ መጣና እሳቸውን ከአባ ዮሐኒ ጋር እያገለገሏቸው ተቀመጡ፡፡ ዮሐኒ እየጻፈ አበይዶ የሚጻፍበትን ቆዳ እያዘጋጁ ሦስቱም በአንድነት በተጋድሎ መቀመጥ ጀመሩ፡፡ ❤ አባ ዮሐኒ 20 ዓመት አባ አሞኒ ደግሞ 40 በሆናቸው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለአባ አሞኒ ተገለጠላቸውና "አሞኒ ሆይ ከእንግዲህስ እግዚአብሔር ወደኔ ና ብሎሃል" አላቸው፡፡ እሳቸውም ልጆቻቸውን አባ ዮሐኒንና አባ አበይዶን ጠርተው "በሉ እንግዲህ እኔ ወደ እግዚአብሔር መሄዴ ነውና ጸልዩልኝ" አሏቸው፡፡ ከማረፋቸውም በፊት አባ ዮሐኒን ለብቻቸው ጠርተው "አንተ አባ ዮሐኒ ካሁን በፊት ሲሂታ ላይ ያየሃቸው ሴቶች ናቸው፣ አዳምንም ከገነት ያስወጡ ናቸው፡፡ ወደፊትም እንደ እነርሱ ያለ የደረሰብህ እንደሆነ ካለህበት ገደል ተወርውረህ ውደቅ በባሕር ውስጥ ጥለቅ" ብለው ነግረዋቸው በዛሬዋ ዕለት ኅዳር 5 ቀን በሰላም ዐረፉና ወደ ጠራቸው እግዚአብሔር ሄዱ፡፡

photo content

ማኅሌቱን የምትቆሙ ማኅሌታውያን መልካም አገልግሎት🤲🤲🤲

ማኅሌቱን የምትቆሙ ማኅሌታውያን መልካም አገልግሎት🤲🤲🤲

🌹🌹🌹🌹🌹🌷🌷🌷🌷🌷 ሥርዐተ ማሕሌት ዘሣድስ  ሳምንት በዓለ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ተፈፀመ) 💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐 ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ   ሉያእመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡ @EOTCW @EOTCW ✨መልክዐ  ሥላሴ ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም። @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም በዝ መካን መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጎላት ዘቔላት ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት ለዘቀደሳ ለሰንበት /ለዘአክበሮ ለቂርቆስ/ ኪያሁ ፍርህዎ ወሰብሕዎ ወተማኅፀኑ ኀቤሁ። @EOTCW 🔸🌱ዓዲ ዚቅ፦ ኀበ ጸገየ ወይን ወፈርየ ሮማን ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት፤ ዬዬዬ ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት ብሂል ውስተ ርስቶሙ ለኩሎሙ ሐዋርያት ብሂል @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡ @EOTCW ❣❣❣ወረብ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/2/ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡ @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሀ በቃለ ስብሐት ፀውኡ/2/ ጸልዩ ቅድመ ስዕል ለቅድስት ድንግል እመ በግ ወመርዓተ አብ/2/ @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ። @EOTCW ❣❣❣ወረብ፦ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/2/ ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ፤እንተ ሐዋርያት ይሴብሑኪ፤መላእክት ይትለአኩኪ፣ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ ሶበ ዴገነኪ አረዌ በሊዓ ሕፃንኪ ዘኀለየ፤በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጎይየ፤አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤ተአምርኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ @EOTCW @EOTCW ❣❣ወረብ፦ አመ አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ/2/ ተአምርኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ዘርእየ ተአምርኪ/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ፦ በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ፤ምስለ ዮሴፍ አረጋ፤ነገደት ቁስቋመ ናዛዚት ኃዘን ወብካይ @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡ @EOTCW ❣❣❣ወረብ፦ ክበበ ጌራ ወርቅ  ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ/2/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ፦ ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤ አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ፤ ወትምክሕተ ቤቱ ለ፳ኤል። @EOTCW @EOTCW ✨ማኅሌተ ጽጌ፦ ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡ @EOTCW @EOTCW ❣❣❣ወረብ ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/2/ አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/2/ @EOTCW @EOTCW 🌱ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡ @EOTCW @EOTCW ✨ሰቆቃወ ድንግል ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡ @EOTCW ❣❣ወረብ ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/2/ ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/2/ @EOTCW 🌱ዚቅ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ። @EOTCW @EOTCW ❄️መዝሙር ፦ በ6 ሃሌታ- ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት፤ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት ወጸገወነ ዕረፍት ከመ ንትፌሳሕ ኅቡረ።አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረይ፤ማ- ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤ከመ አሐዱ እምእሉ @EOTCW 🔹አመላለስ፦ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ/2/ ከመ አሐዱ እምእሉ/4/ https://t.me/Eotcw     # Join & share

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 የህዳር ፬ ምስባክ ፮ኛ እሁድ መዝሙር ክርስቶስ ሠርዐ ሰንበተ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ዘቅዳሴ ምስባክ ቆላስይስ፦፩፥፩-፲፪ ያዕቆብ ፦፩፥፩-፲፫ ግብ.ሐዋ፦፲፫፥፮-፲፮ ወንጌል ፦ማቴ ፮፥፳፭ ቅዳሴ፦ዘእግዚእትነ ወይከውን ከመ ፅፅ እንተ ትክልት ኀበ መጎዝ ማይ፣ አንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ፣ ወቆጽላኒ ኢይትነገፍ።                 ✝            ✝🇪🇹✝ መዝ ፩፤፫                 ✝

photo content
+2

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን ለሮሜ አገር ለሆኑ ለቅዱሳን አቢማኮስና አዛርያኖስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ የሐርመዝ ልጅ በሆነ በፋርስ ንጉሥ በሳቦር እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለቅዱስ ያዕቆብና ለአገረ ፋርስ ኤጲስቆጶስ ለአባ ዮሐንስ፣ በግብጽና በሶርያ እስላሞች በነገሡ ጊዜ ሰማዕትነት ለተቀበለ ለደማስቆ ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ ቶማስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከታላቁ አባት ከዘካርያስ፣ ከእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ ከመታሰቢያቸውና ከሰማዕታት ጉባዔ ከሆነ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ቅዱሳን አቢማኮስና አዛርያኖስ፦ እሊህም ቅዱሳን ክርስቶስን የሚያምኑ እንደሆኑ ከሀዲ ንጉሥ መክስምኖስ በሾመው መኰንን ዘንድ ወነጀሏቸው እርሱም አስቀርቦ ስለ ሃይማኖታቸው ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። ❤ እርሱም መኰንኑንም ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ እውነተኛውን አምላክ ማምለክ ትቶ የሰይጣን መንፈስ በውስጣቸው ያደረባቸውን የማያዩ የማይሰሙ በሰው እጅ የተሠሩ የረከሱ ጣዕታትን ስለማምለኩ ዘለፉት። ❤ መኰንኑም ከድፍረታቸው የተነሣ አደነቀ ቸብቸቧቸውንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የምስክነት አክሊል ኅዳር 4 ቀን ተቀበሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት አቢማኮስና አዛርያኖስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ ያዕቆብና የአገረ ፋርስ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ፦ እሊህም ቅዱሳን የሐርመዝ ልጅ በሆነ በፋርስ ንጉሥ በሳቦር እጅ በሰማዕትነት ያዐረፉ ናቸው። እርሱም ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ለእሳትም እንዲሰግዱ አዘዛቸው ትእዛዙንም ባልሰሙ ጊዜ በጽኑዕ ሥቃይ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ። በሥቃይም ውስጥ እያሉ ሕዝቡን በማስተማር ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ያጸኑአቸው ነበር። ❤ የልባቸው ጥንካሬ በሥቃይም ውስጥ መታገሣቸውን ማስተማርንም አለመተዋቸውን በአየ ጊዜ ከእሳት ውስጥ እንዲጥሏቸው አዘዘ። በዚያንም ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ነፍሳቸውን ሰጡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ያዕቆብና በአገረ ፋርስ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ በጸሎታቸው ይማረን። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የደማስቆ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቶማስ፦ ይህ ቅዱስ በግብጽና በሶርያ እስላሞች በነገሡ ጊዜ በሰማዕትነት ያዐረፈ ነው። ይህንንም ቅዱስ ቶማስ ከመምህራኖቻቸው ውስጥ አንድ እስላም በተከራከረው ጊዜ ቅዱስ ቶማስ በረታበት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ አምላክ እንደሆነ በማስረዳት አይሎ ረታው። ❤ ያም እስላም በዐፈረ ጊዜ ወደ መኰንናቸው ሒዶ "ይህ ክርስቲያናዊ ቶማስ ሃይማኖታችንን ረገመ" ብሎ ወነጀለው። መኰንኑም ወደርሱ አስቀርቦ "በውኑ ሃይማኖታችንን ትረግማለህን?" አለው። ቅዱሱም "መርገምስ ከአፌ አልወጣም ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ከእርሱም ሕግ በኋላ ሌላ ሕግ እደማይመጣ አጽንቼ አስረዳሁት እንጂ" ብሎ መለሰለት። ❤ መኰንኑም "የእኛስ ሕግ ከእግዚአብሔር ነውን? ወይስ አይደለም?" አለው ቅዱሱም "ከእግዚአብሔር አይደለም" አለው። በዚያንም ጊዜ መኰንኑ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቅድስት ራሱን ቆረጡት። በመንግሥተ ሰማያትም የምስክርነት አክሊልን ኅዳር 4 ቀን ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በኤጲስቆጶስ በቅዱስ ቶማስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 4 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለቶማስ ቢጸ ዘካርያስ መምህር። ኢጲስቆጶስ ዘደማስቀ ሀገር። እንዘ ተስፋ ሰማይ ይሬኢ በአይነ ምስጢር። ከመ ያኅድግዎ ስእኑ አፍቅሮተ ክርስቶስ ፍቁር። በመጥባሕት ስሑል ወበኵሉ ፃዕር"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 4። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፬ (4) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ የዚህን ዓለም ሥራ ለተዉ ለአባ ዮሐኒ ደቀ መዝሙር ለሆኑት ለታላቁ አባት ለአባ አበይዶ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ብፁዕ ውእቱ አባ አበይዶ ረድአ ዘኮኖ ለአባ ዮሐኒ ብፁዕ ብእሲ በትዕግሥቱ ዘፈጸመ ገድሎ"። ትርጉም፦ ለአባ ዮሐኒ አገልጋይ የኾነው አባ አበይዶ ንኡድ ክቡር ነው፤ ተጋድሎውን በትዕግሥቱ የፈጸመ የኾነ ርሱም ንኡድ ክቡር ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለአባ አብይዶ ለጸላኢ ዘኬዶ"። ትርጉም፦ ጠላትን የረገጠው ለኾነ ለአባ አበይዶ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ የአባ አበይዶ ታሪክ ከአባታቸው ከአባ ዮሐኒ ጋር ነገ በኅዳር 5 አብሮ ይቀርባል። + + + ❤ "ሰላም ለአበይዶ መጠነ ዮሐኒ መጠኑ። እስመ ውእቱ ረድኡ ወውስተ ኵሉ ምእመኑ። ለዝ ፃማዊ ወፈጻሜ መልእክት ዘበበበይኑ። ጼና አልባሲሁ ከመ ጼና ስሂን ይጼኑ። ወይበርህ እምፀሐይ ምስብዒተ ስኑ"። ትርጉም፦የማዕርጉ መጠን እንደ ዮሐኒ ማዕርግ መጠን ለኾነ ለአባ አበይዶ ሰላምታ ይገባል እርሱ አገልጋዩና በኹሉም ውስጥ ታማኙ ነውና፤ በየወገኑ አገልግሎትን ለሚፈጽምና ለዚኽ ትጉህ ለኾነ ሰው የልብሶቹ ሽታ እንደ ዕጣን መዐዛ ይሸታል፤ የልብሱ ሽታ እንደ ዕጣን ጢስ ይሸታሉ፤ ደም ግባቱም ከፀሓይ ሰባት እጅ ይበራል። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 4። https://t.me/Eotcw

photo content

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 12:9-14፡ "ወፈሊሶ እምህየ" - "ከዚያም፡ዐልፎ፡ወደ፡ምኵራባቸው፡ገባ። እንሆም፥እጁ፡የሰለለች፡ሰው፡ነበረ፤ይከሱትም፡ዘንድ።በሰንበት፡መፈወስ፡ተፈቅዷልን፧ብለው፡ ጠየቁት። እርሱ፡ግን፦ከእናንተ፡አንድ፡በግ፡ያለው፡በሰንበት፡በጕድጓድ፡ቢወድቅበት፥ይዞ፡የማያወጣው፡ሰው፡ማን፡ነው? እንግዲህ፡ሰው፡ከበግ፡ይልቅ፡እንደምን፡አይበልጥም! ስለዚህ፡በሰንበት፡መልካም፡መሥራት፡ተፈቅዷል፡አላቸው። ከዚያም፡በኋላ፡ሰውየውን፦እጅህን፡ዘርጋ፡አለው። ዘረጋትም፥እንደ፡ሁለተኛዪቱም፡ደኅና፡ሆነች። ፈሪሳውያን፡ግን፡ወጥተው፡እንዴት፡አድርገው፡እንዲያጠፉት፡ተማከሩበት።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨