fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1.45 KB

3/3/2015 ዓ.ም (፫/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኀዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ። መዝ 1፥2 🕯 ትርጉም ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውሃ ፈሳሾች ዳር እንደተተከለች፤ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ ዛፍ ይሆናል። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 24:27-33፡ "ወአኀዘ ይፈክር ሎሙ" - "ከሙሴና፡ከነቢያት፡ሁሉ፡ጀምሮ፡ስለ፡እርሱ፡በመጻሕፍት፡ሁሉ፡የተጻፈውን፡ተረጎመላቸው። ወደሚሄዱበትም፡መንደር፡ቀረቡ፥እርሱም፡ሩቅ፡የሚሄድ፡መሰላቸው። እነርሱ፦ከእኛ፡ጋራ፡ዕደር፥ማታ፡ቀርቧልና፥ቀኑም፡ሊመሽ፡ጀምሯል፡ብለው፡ግድ፡አሉት፤ከእነርሱም፡ጋራ፡ሊያድር፡ገባ። ከእነርሱም፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡እንጀራውን፡አንሥቶ፡ባረከው፥ቈርሶም፡ሰጣቸው፤ ዐይናቸውም፡ተከፈተ፥ዐወቁትም፤እርሱም፡ከእነርሱ፡ተሰወረ። እርስ፡በርሳቸውም፦በመንገድ፡ሲናገረን፡መጻሕፍትንም፡ሲከፍትልን፡ልባችን፡ይቃጠልብን፡አልነበረምን፧ተባባሉ። በዚያችም፡ሰዓት፡ተነሥተው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ፥ዐሥራ፡አንዱና፡ከእነርሱ፡ጋራ፡የነበሩትም፦ጌታ፡በእውነት፡ተነሥቷል፡ ለስምዖንም፡ታይቷል፡እያሉ፡በአንድነት፡ተሰብስበው፡አገኟቸው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.58 KB

3/3/2015 ዓ.ም (፫/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወዘሂ ገበርኩ ርእያ አዕይንቲከ ። ወኲሉ ይጸሐፍ ውስተ መጽሐፍከ። መዓልተ ይትፈጠሩ ወአይሄሉ እንከ አሐዱ እምኔሆሙ፡፡ መዝ. 138፥16 🕯 ትርጉም ያልተሠራ አካሌን ዐይኖችህ አዩኝ። የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ፤ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ከቆሮንቶስ አገር ለሆነ ከኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ ቄርሎስም በመሆን የክብር ባለቤት የሆነ መንፈስ ቅዱስን ስለ አቃለለ መቅዶንዮስ መቶ ሃምሳው የኤጲስቆጶሳት አንድነት ጉባኤ በቊስጥንጥንያ በተደረገ ጊዜ አብሮት ለሆደ ለቅዱስ አባት ኪርያቆስ ለዕረፍት በዓል፣ ለአባ አትናቴዎስና ለእህቱ ለቅድስት ኢራኢ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ከቆሮንቶስ አገር የሆነ ቅዱስ አባት ኪርያቆስ፦ የዚህም አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና የከበሩ ናቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩት ከዚህም በኋላ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነ ወደ አባ ጴጥሮስ አቀረቡት እርሱም በላዩ ጸልዮ አናጒንስጢነት ሾመው ለአባ ጴጥሮስም የወንድሙ ልጅ ነው። ❤ ከዚህም በኋላ ዘወትር መጻሕፍትን የሚያነብ የቃላቸውንም ትርጓሜ የሚመረምር የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓቷንና ሕጓን የሚያጸና ሆነ በትምህርቱና በእውቀቱም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ ኤጲስቆጶሱም መጻሕፍት ማንበብን እንዳያቋርጥ ያዝዘው ነበር እነርሱም በሕዝቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለኢጲስቆጶሱ በእርሱ ደስ ይለው ነበርና። ❤ ዕድሜውም ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነ ጊዜ ሚስትን ያጩለት ዘንድ ወላጆቹ ጠየቁት እርሱ ግን ይህን አልወደደም ግን ከገዳማት ወዳንዱ ይሔድ ዘንድ እንዲአሰናብቱት ወላጆቹን ለመናቸው። ከዚያም በኋላ አዘውትሮ ወደ ገዳማት የሚሒድና ወደ ወላጆቹ የሚመለስ ሆነ። መመላለሱም ከበዛ ዘንድ የከበረች የምንኲስናን ልብስ ሊለብስ ወደ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ከኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ ከአባ ቄርሎስ ጋር ተገናኝቶ ስለ ምንኲስና ኀሳብን ሁሉ ነገረው። እርሱም "በጎ ሥራን ወደሃል" አለው ታላቅ አባትም እንደሚሆንና በእርሱም የብዙዎች ነፍሳት ብሩሃን እንደሚሆኑ ትንቢት ተናገረለት። ❤ ከዚህም በኋላ የመነኰሳት አባት ወደ ሆነ በፍልስጥዔም ወደ ሚኖር ወደ ክቡር አባ ሮማኖስ ላከው እርሱም በደስታ ተቀብሎ የምንኲስናን ልብስ አለበሰው። የምንኲስናንም ሥርዓት ያስተምረው ዘንድ የሰይጣንንም ተንኰል ያስረዳው ዘንድ በዚያው ገዳም ለሚኖር አንድ አረጋዊ ሰጠው። ከዚህም በኋላ በጾም በጸሎት በስግደት በመትጋት በታላቅ ድካም በቀንና በሌሊት በገድል ተጸምዶ በትዕግሥት በትሕትና በቅንነት ኖረ። ❤ እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጥቶት ወደርሱ የሚመጡትን በሽተኞች ሁሉ የሚፈውሳቸው ሆነ የትሩፋቱና የቅድስናውም ዜና በሁሉ ቦታ ተሰማ። የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ ቄርሎስም የክብር ባለቤት የሆነ መንፈስ ቅዱስን ስለ አቃለለ መቅዶንዮስ መቶ ሃምሳው የኤጲስቆጶሳት አንድነት ወደሚሰበሰቡበት ወደ ቊስጥንጥንያ በሚሔድ ጊዜ ይህን አባት ኪርቆስን አባ ቄርሎስ ከእርሱ ጋር ወሰደው በላያቸው በአደረ መንፈስ ቅዱስ ስም ተከራክረው ከሀዲ መቅዶንዮስን ረቱት ከምዕመናንም ለይተው አሳደዱት። ❤ ከዚህም በኋላ በመልካም ሽምግልና እግዚአብሔርን አገልግሎ ኅዳር 3 ቀን በሰላም ዐረፈ። ከዕረፍቱም በኋላ እግዚአብሔር ድንቆች የሆኑ ብዙ ተአምራትን ከሥጋው ገለጠ ከእርሳቸውም አንዱ ከኢየሩሳሌም ገዳማት በአንዱ ሥጋው ይኖራል። ከዐረፈበት ጊዜ ጀምሮ እሰሰከ ዛሬ ሥጋው አልተለወጠም ወደ ኢየሩሳሌም የሚሔዱ ሁሉ ያዩታል እነርሱም በቅርብ ጊዜ እንዳረፈ ያስባሉ እርሱ ግን ያረፈው ለአኖሬዎስና ለአርቃዴዎስ አባታቸው በሆነ በታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኪርያቆስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ አትናቴዎስና እኅቱ ቅድስት ኢራኢ፦ እሊህንም ቅዱሳን ከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃያቸው። በማሠቃየትም በደከመ ጊዜ ዕራቁታቸውን ከጒድጓድ ጨመራቸው በላያቸውም የጒድጓዱን አፍ ዘጋ በውስጧም ነፍሳቸውን አሳለፉ የሰማዕታት አክሊልንም ተቀበሉ በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 3 ስንክሳር። ❤ "ሰላም ወአምኃ ለኪርያቆስ አፌኑ። ወተአምሪሁ እዜኑ። ለእለ ይምጽኡ ሕዝብ ይርአይዎ ውስተ መካኑ። ይትረከብ ከዊኖ ሐዲሰ በድኑ። እንዘ ሰዓ ሞቱ ርኁቅ ወጒዱንይ ዘመኑ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 3። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content
+4

+ + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ"። መዝ 1፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 4፥6-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥15-22፣ የሐዋ ሥራ 19፥8-11። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥9-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። የጻድቁ ንጉሥ የቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ከሞት የተሰወረበት (የስዋሬ) በዓል፣ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ የአቡነ ፍሬ ካህን፣ የአቡነ ዓምደ ሚካኤል የዕረፍታቸውና የጾም ጊዜ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባንም አመንኵሰው መርቀው ሲሸኟቸው እንዲያገለግሏቸው አንበሶችን ከጫካ ጠርተው ያዘዙላቸው አባታቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ከመነኰሱ በኋላ በደብረ በንኰል 12 ዓመት አባታችንን ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ እሳት እስከማያቃጥላቸው ድረስ ከብቃት ደረጃ ላይ ሲደርሱ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ መርቀው በማሰናበት በዓት እንዲያጸኑ ሲያደርጓቸው አቡነ ሳሙኤል በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ጣና ደሴት ገብተው ሱባኤ ያዙ፡፡ በዚያም ሳሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ማረፋቸውን በመንፈስ ዐውቀው ሲያለቅሱ ጌታችን የአቡነ መድኃኒነ እግዚእን ነፍስ በእቅፉ አድርጎ ወደ ገነት ሲያሳርጋት አሳያቸው፡፡ ወዲያውም ጌታችን በብርሃን ሰረገላ አድርጎ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን ደብረ በንኰል አድርሷቸዋል፡፡ በዚያም እስከ 40ኛው ቀን ከቆዩ በኋላ በዚሁ ዕለት ሲቀድሱ ክንድ ከስንዝር ከመሬት ከፍ ብለው ቅዱሳን ሐዋርያት እየተራዱዋቸው ከቀደሱ በኋላ ወደነበሩበት መልሷቸዋል፡፡ የጻዲቁ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ቀን 1360 ዓ.ም ሲሆን ጠቅላላ ዕድሙያቸውም 180 ዓመት ነው፡፡ ❤ ዐፄ ፋሲል ጻድቁ የተከሏቸውን የጥድ ዛፎች በሙሉ ተቆርጠው የአክሱም ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራበት አዋጅ አወጁና መልእክተኞች መጥተው ዛፎቹን ሲቆርጡ መነኰሳቱ ግን "ጻድቁ አባታችን የተከሏቸው የጥድ ዛፎች መቆረጥ የለባቸውም" ብለው ቢከራከሩም ሰሚ አላገኙም፡፡ መነኰሳቱም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱ ጩኸታቸው ተሰምቶላቸው ወዲያው እየተቆረጡ ያሉት የጥድ ዛፎች በሙሉ በተአምራት ወደ ወይራ ዛፍነት ተለወጡ፡፡ የወይራ ዛፎቹም ለዐፀድ እንጂ ለሕንፃ የማይመቹ ጎባጣ ሆኑ፡፡ የዚህም ምልክቱ ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ግንዱ ጥድ ዛፉ ግን ወይራ የሆነ ትልቅ ዛፍ "ወይራ ዘገብረ ተአምር" በሚባል ቦታ አሁንም ድረስ ቆሞ ይታያል፡፡ ❤ ጻድቁ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ በ1312 ዓ.ም የመሠረቱት ገዳማቸው ደብረ በንኰል ከአክሱም በእግር ሦስት ሰዓት ያስኬዳል፡፡ ይኸውም በንግሥተ ሳባ ቤተ መንግሥት አድርጎ የቀዳማዊ ሚኒሊክን መቃነ መቃብር አልፎ በመሄድ ነው፡፡ ወይም በመኪና ለመጓዝ አክሱም ጉበዱራን አቋርጦ ውቅሮ ማራይ ከተማን አልፎ በስተ ሰሜን አቅጣጫ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በስተ ምዕራብ የአቡነ አላኒቆስ ዘማይበራዝዮን ገዳም፣ በስተ ምሥራቅ የአቡነ ሰላማን ገዳም እየተለመከቱ እንደተጓዙ ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነውን ደብረ በንኰልን ያገኙታል፡፡ ኅዳር 20 ጻድቁ ስለሚነግሱ ገዳሙም ለአክሱም ቅርብ ስለሆነ ይህ ለአክሱም ጽዮን ተጓዦች ተጨማሪ ትልቅ በረከት ነው፡፡ ❤ ደብረ በንኰል ማለት "ሙራደ ቃል" ማለት ነው፡፡ ትርጉሙም የምሥጢር መውረጃ ማለት ነው፡፡ በቦታው ላይ ሱባኤ ለያዘ ሰው እንደ ቅዱስ ያሬድና እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ምሥጢር እንደሚገለጥለት የሚጠቁም ነው፡፡ በ14ኛው መ/ክ/ዘ የነበሩት ደጋግ መነኰሳት ሕይወታቸውን በሙሉ በምንኵስና፣ በጸሎትና በታላቅ ተጋድሎ መኖር ሲፈልጉ ከደብረ ዳሞ፣ ከሐይቅ እስጢፋኖስ፣ ከደብረ ሊባኖስና ከሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች እየተነሡ ወደ ደብረ በንኰል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነበር የሚሄዱት፡፡ ❤ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ቃልኪዳን፡- ጻድቁ ባርከው ያፈለቁት ጸበላቸው ላበደ ሰው መድኃኒት ነው፡፡ ከመቃብራቸው ላይ የሚነሣውን አፈር ጻድቁ ባርከው ባፈለቁት ጸበላቸው ታሽቶ በእጃቸው መስቀል ተባርኮና ታሽቶ የሚዘጋቸውን የአቡነ መድኃኒነ እግዚእን እምነታቸውን በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው ንብረቱን ሌባ ቀማኛ ዘራፊ አይሰርቀውም፤ የመኪና አደጋ አይደርስበትም፤ ጥይት አይመታውም፡፡ "በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው" መባሉን ልብ ይሏል፡፡ ይኸውም ለጻድቁ የተሰጣቸው ታላቅ ቃልኪዳን ነው፡፡ ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። + + + ❤ አቡነ ዓምደ ሚካኤል፡- ትውልዳቸው ወሎ ቦረና ነው፡፡ ወላጆቻቸው ገላውዲዮስና ኤልሳቤጥ ሁለቱም በሃይማኖትና በዓለም ገንዘብ የበለጸጉ ናቸው፡፡ ይህንንም ጻድቅ ልጃቸውን የአርባዕቱ እንስሳ በዓል ዕለት ወለዱትና ስሙን ዓምደ ሚካኤል ብለው ጠሩት፡፡ ለዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ ለዐፄ በእደ ማርያምና ለዐፄ እስክንድር የሠራዊት አለቃ የነበረ ጻድቅ ነው፡፡ በአንድ ዓመቱ ወላጆቹ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይዘውት እንደሄዱ ከወላጆቹ ተለይቶ ጠፍቶ ሳይገኝ ቀረ፡፡ መልአክም ከቤተ መቅደስ አግብቶ እየመገበው 3 ቀን አቆይቶታል፡፡ በ3 ኛው ቀን ቄሱ ሊያጥን ሲገባ በከርሰ ሐመሩ ውስጥ ሕፃኑን አገኘውና ወስዶ ለወላጆቹ ሰጣቸው፡፡ ❤ ባደገም ጊዜ በመመጽወትና አብያተ ክርስቲያናትን በማደስ የሚተጋ ሆነ፡፡ ለድኆችም በቅንነት በመፍረድ በታላቅ ተጋድሎ የሚኖር ሆነ፡፡ ለነገሥታም ገዥ ከሆነ በኋላ በጸሎቱና በበረከቱ በሀገራችን ላይ ሁሉ ሰላም ሆነ፡፡ ጠላቶችም ሁሉ ለነገሥታቱ ተገዝተው ይገብሩ ነበር፡፡ በበጎ ምግባሩ የቀኑ ዐመፀኞችም በክፋ ተነሡበት፡፡ ጻድቁ በመንፈስ አድጎ መንኵሶ በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር ነገር ሠሪዎች በሐሰት ወንጅለው ከሰሱት፡፡ ንጉሡም እጅግ ስለሚወደው የራራለት ቢሆንም በነገራቸው ባስጨነቁት ጊዜ ወደ ሩቅ አገር አስሮ አጋዘው፡፡ አባታችንም በግፍ ታስረው ሳሉ በእስር ቤቱ ውስጥ ብርሃን ወረደላቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ሰማያዊ መና እያመጣ ይመግባቸው ነበር፡፡ የጌታችንንም ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ነበር፡፡ ነገረ ሠሪዎቹ ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሡን ለመኑት፡፡ በዓመፃቸውም ብዛት ወደ ፍርድ ሸንጎ አምጥተው ገደሏቸው፡፡ ❤ አንድ ጻድቅ መነኩሴ የቅዱስ ዓምደ ሚካኤልን ሥጋ ሦስት ቅዱሳን መላእክት ሲያጥኑ አገኛቸውና ያየውን ለሕዝቡ ተናገረ፡፡ በሌላም ጊዜ የብርሃን ፋና ከሰማይ ሲወርድላቸው ብዙ ቀን የተመለከቱ ብዙ ቅዱሳን ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡ ንጉሡም ይህንን ሁሉ ሲሰማ በአሳቾቹ ልበ ደንዳናነትና ክፋት እጅግ ተጸጽቶ በሞት ቀጣቸው፡፡ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤልንም በአባቶች መቃብር በክብር አስቀበራቸው፡፡ ስማቸውንም በበጎ እንጂ በክፋ ማንም እንዳያነሳቸው በአዋጅ አስነገረ፡፡ መታሰቢያም አቆመላቸው፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ የአባቱን የበእደ ማርያምን ቃል ኪዳን ሰምቶ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋም ጻድቁ ሲያርፉ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተቀበሩ ቢሆንም ከብዙ ዘመን በኋላ ዐፅማቸውን አፍልሰው በተድባበ ማርያም እንደቀበሯቸው ጽፈዋል፡፡ ከአቡነ ዓምደ ሚካኤል እግዚአብሔር አምላክረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ። + + + ❤ "ሰላም ለእርስከ ዘተከለለ ቆብዐ። አርአያ አክሊሉ ለክርስቶስ በዲበ መስቀል ሶበ ተመርዐ። መድኃኒነ እግዚእ አፋየ አመ ስመከ ጸውዐ። ነዓ ነዓ ምስለ ሳሙኤል ነዓ። ምስሌየ ትግበር ሰላም ወስንዓ። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 3።

❤ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ንጉሥ በሰላምና በበረከትና በፍቅር 40 ዘመን፡፡ ከነገሠ በኋላ የቅዱስ ላሊበላ ልጅ ዐፄ ይትባረክ ትምህርት ቤት ሆዶ ስለ ነበር ከአለበት አስፈልጎ አስመጥቶ አነገሠው እርሱም የቀኖና የቱሩፍት ስራውን በበለጠ አጠጋክሮ በጽሞና በጸሎት ተወስኖ ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ "ከአይነ ሞት የምትሰወርበት ጊዜ ስለደረሰ ቃል ኪዳን ልስጥህ ዘንድ የምትፈልገው ለምነኝ" አለው። እርሱም ለቅዱሳን የሰጠው ምክንያተ ድኅነት የሆነው ልመና ስራቀረበ የሚከተለው ቃል ኪዳን ተቀብላል። ❤ "ዝክረ ስዋሬህን በማሰቡ በየወሩና በየዓመቱ ያከበረ ስምህ የጠራ ዝክርህን የዘከረ ቤተ መቅደስህ የሠራ ያሠራ መጽሐፈ ገድልህን ያጻፈንና የተረጐመውን የሰማውንና ያሰማውን እስከ 7 ትውልድ ምሕረትን እሰጠዋለሁ። ❤ ስለ እኔ ፍቅር መከራ መስቀሌን በማሰብ ስለፈፀምከው መከራ አንድ ክረምት የበቀለውን ቡቃያ የሚያህል ነፍሳትን ምሬልሃለሁ። ❤ መላ ዘመንህን ሁሉ ከአይንህ እንባ ሳታቋርጥ ያፈሰስከውን ምሳሌ ከቤተ መቅደስህ የሚጠባጠብ ጠበልን እሰጠዋለሁ። ይህም የእምባህ ምሳሌ ነው። ጠበልህ ብዙ ድውያንን እስከ ዕለተ ምጽዓት ሲፈውስ ይኑር። ❤ በቃል ኪዳንህ የተማፀኑ ሁሉ የአንተን ልጆችና ወዳጆች መሆናቸው እንዲታወቅ በቅዱስ ገብርኤል እጅ ቀኝ ግራ እጃቸው ታትሞ መንግሥተ ሰማያት ይግብልህ። እድል ፈንታቸው ፅዋ ተርታቸው ከአንተ ጋር ይሁንልህ" በማለት ቃልኪዳኑን አደረገለት (ከሰጠው በኋላ) ከአይነ ሞት የምትሰወረው ኅዳር 3 ቀን ነው ብሎ ወደ ሰማይ ዐረገ። ❤ እንደተባለውም በሰባ ዓመቱ ኅዳር 3 ቀን ማዕጠንት በማጠን ላይ እያለ በ7 ሰዓት ገብረ ክርስቶስ የተባለው ዲያቆን በመስቀሉ ባርኮት ኤልሳዕ ኤልያስን እያየ ወደ ሰማይ እንደወጣ እርሱ እያየው ከአይነ ሞት ተሰውሯል። ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ነአኵቶ ለአብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ቅዱሳንና ሥራቸው የአራቱ ቅዱሳን ነገሥታት ታሪክ ከሚለው መጽሐፍ። + + + ❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፡- ከደጋግ ክርስቲያኖች ከቀሲስ ሰንበት ተስፋነ እና ከኅሪተ ማርያም በ 1180 ዓ.ም በሥዕለት የተወለዱት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅግ አስደናቂ ገድልና ትሩፋት ያላቸው ጻድቅ ቢሆኑም ብዙው ሕዝበ ክርስቲያን እንደሚገባቸው መጠን ያላወቃቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጩን አባቶች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የደብረ በንኰሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ እስቲ ቀጥሎ ስማቸውን የጠቀስኳቸውን እነዚህን ቅዱሳን አባቶች ታሪካቸውንና የጽድቅ ሕይወታቸውን አስታውሱት፡- እነርሱም አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን አስተምረውና አመንኵሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አባት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ ❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እነዚህን ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኵሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን ደብረ በንኰልን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ላይ የመነኰሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን "ሰባቱ ከዋክብት" እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ በእግራቸውም እየረገጡ ባሕሩን የተሻገሩ አሉ፡፡ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፡፡ ❤ በደብረ ሊባኖሱ ሐዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኰሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኰሷቸው መነኰሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ "ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን" በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን ያመኰሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ፡፡ ❤ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ልጆች ዛሬ ግሸን ላይ በክብር ተቀምጦ ሀገራችንን ከመዓት እየጠበቀ ያለውን የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ያመጡትም እነርሱ ናቸው፡፡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ረኃብ ስለነተሳ የደብረ ቢዘኑን አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማከሯቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስም "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን መርጠው ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ በጽድቅ ሥራቸውና ተአምራትን በማድረግ በወቅቱ ታዋቂ የነበሩትና ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዐሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡ ❤ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ተአምራታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ አራዊት ሁሉ እንደሰው ያገለግሏቸው የነበር፡፡ ውኃ የሚያመላልስላቸውንና የሚያገለግላቸውን አህያ አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ አንበሳውን ድፍን 7 ዓመት ለገዳማቸው ውኃ አስቀድተውታል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ለአባታችን ውኃ የሚያመላልስላቸውና የሚያገለግላቸው አንድ አህያ ነበራቸው፡፡ ውኃው የሚገኘው እርሳቸው ካሉበት በጣም እርቆ በእግር የሦስት ሰዓት መንገድ ከተሄደ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን አህያቸው እንደ ሰው እየተላላካቸው ይቀዳላቸው ነበር፡፡ አንድ ግን ከመንገድ አንበሳ አግኝቶት ግማሽ አካሉን በልቶት ሄደ፡፡ አባታችንም የአህያቸውን ተረፈ በድን አግኝተው በማዘን "ውኃ የሚያመላልስልኝ ረዳቴ ይህ አህያ ብቻ ነበር፣ አሁንም አህያዬን የበላህ አውሬ እንድታነጋግረኝ እፈልጋለሁ" ቢሉ በአንበሳ ተበልቶ የሞተው የአህያው ግማሽ አካል አፍ አውጥቶ አንድ አንበሳ እንደበላው ነገራቸው፡፡ ❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በዚህ እጅግ ደስ ተሰኝተው ፈጣሪያቸውን ካመሰገኑ በኋላ አህያቸውን የበላውን አንበሳ ከጫካው ውስጥ ጮኸው ጠሩት፡፡ አንበሳውም ከሌሎቹ አንበሳ ተለይቶ ወደ እርሳቸው በመምጣት እግራቸው ሥር ወድቆ ሰገደ፡፡ አባታችንም "አህያዬን የበላኸው አንተ ነህን?" ብለው ሲጠይቁት አንበሳውም በሰው አንደበት "ዎ እኔ ነኝ" አላቸው፡፡ እርሳቸውም ፈጣሪያቸውን በድጋሚ ካመሰገኑ በኋላ አንበሳውን "በል ና ተከተለኝ በአህያዬ ምትክ ታገለግለኛለህ" አሉት፡፡ አንበሳውም ተከትሏቸው ወደ በዓታቸው በመግባት ለ7 ዓመታት እንደ አህያቸው ውኃ እየቀዳ አገልግሏቸዋል፡፡ የአንበሳው ቆዳ ዛሬም በገዳማቸው ደብረ በንኰል በክብር ተቀምጠቷል፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን አኲሱም አካባቢ የሚነኘውን ታላቁ ገዳም ደብረ በንኰልን ለመሰረቱት ሰባቱን ከከዋክብት የተባሉት እነ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን አስተምረው ላመነኰሱትና ውኃ ይቀዳላቸው የነበረውን አህያቸውን አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ አንበሳውን 7ዓመት ለገዳማቸው ውኃ ላስቀዱት ለታላቁ አባት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ ለጻድቁ የኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለቅዱስ ነአኵቶ ለአብ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ፈንታ ለተሰወረው ዕለት ለመታሰቢያ በዓሉና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መና ሲመግባቸውና የጌታችንንም ቅዱስ ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ለነበሩት ሰማዕቱ አቡነ ዓምደ ሚካኤል ለዕረፍታቸው በዓል ሰላም አደረሰን። + + + ❤ ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ፦ ከዐሥራ አንዱ ነገሥታተ ዛጕዬ መካከል በዐሥረኛ የሚገኝ ቅዱስ ስመ ጥሩ ንጉሥ ነው። አባቱ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም ሲሆን እናቱ ደግሞ ቅድስት መርኬዛ ትባላለች። ቅዱሱ ፍጥረት ነአኵቶ ለአብ ከነዚህ ቅዱሳን ሰዎች የተወለደው በብስራተ መልአክ ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ወጥቶ ከወንድምህ የሚወለደው ልጅህ ቅዱስና ደግ ነው የአንተም ወራሽ እርሱ ነው አለው። ቅዱስ ላሊበላም ይህን ሰምቶ "ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክ እስራኤል ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ ቅዱስ" እያለ ጸልዮ ሲጨርስ ወደ ነአኵቶ ለአብ እናት "ሰላም ለኪ ወሰላመ እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌኪ ኢትፍርሂ ወኢትህዝኒ በከመ ዐወፀ ማሕፀኖን ለሣራ ወለሐና ከማሁ ሀወፀ እግዚአብሔ ማህፀንኪ በፍሬ ሰናይ" ብሎ ላከ እርሷም ይህን ስትሰማ መካን ሆና ትኖር ነበርና በእውነት ፈጣሪ በማህፀኔ ፍሬ ሊያሳድርብኝ ይሆን እያለች ብትጠረጥር ቅዱስ ገብርኤል እራሱ ለቅዱስ ላሊበላ እንደነገረው መልእክተኛው አረጋግጦላት ሲሆድ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤ እንደ ገና ለእናቱ ተገልጦ ልጅ እንደምትወልድ አበሰራት። ❤ በዚህም መሰረት ቅድስት መርኬዛ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብን በብስራተ መልአክ ልክ ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን ወለደችው። ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ አባቱም እናቱም በህፃንነቱ ነበር የሞቱት በሆኑም ቅዱስ ላሊበላና ቅድስት መስቀል ክብራ በቤተ መግሥታቸው በጥበብና በሞገስ እንዲሁም በእንክብካቤ አሳደጉት ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ አባ ይስሐቅ የተባሉ መምህር ተቀጥረውለት ሲማር መንፈስ ቅዱስ ያደረበት በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጨርሶ ተማረ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ላሊበላ ሞግዚትም ጓደኛ እንዲሆንና የቤተ መግሥት ሥርዓት እንዲያስተምረው ገብረ ክርስቶስ የሚባል አገልጋይ ሰጠው። ❤ ነአኵቶ ለአብም በዚህ ሲኖር ዲቁና ተቀብሎ ፈጣሪው እያገለገለ በቅድስና ኖረ ሃያ ዓመት ሲሆነው በፍቃደ እግዚአብሔር ቅዱስ ላሊበላ በሱባኤ ጠይቆ የጥንት ስሟ አምባጌ የዛሬ እምባጽዮን በመባል ከምትታወቀው አካባቢ ቄስ እስጢፋኖስና አቅሌስያ ከሚባሉ ደናግ ሰዎች የምትወለደው ንጽሕት የምትባ ልጅ ለሚስትነት አጩለት፡፡ የሠርጉ ስርዓትና ቁርባን ከተፈጸመ በኋላ ሕገ መርዓዊ ወመርዓት ይፈጽሙ ዘንድ መጋረጃ ጥለውላቸው ሲወጡ "እህቴ ወይ እባክሽ ድንግልናችንን እንደነ ድሜጥሮስ እንጠብቅ ብሎ ለባለቤቱ ነገራት በዚሁም ተስማምተው እሰከ ሃያ አምስት ዓመት ድረስ በድንግልና ኖሩ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብም በዘመኑ ሁሉ ከመላእክት ጋር ይነጋገር ነበር። በየቀኑም ብረትና ድንጋይ ተሸክሞ ሺህ ጊዜ ይሰግድ ነበር። በዚህም የቅድስና ተግባሩም የአባቶቹ በረከት አደረበት። በተለይም ቅዱስ ላሊበላ ላይ የነበረው ጸጋና ስጦታ በእርሱም ላይ አደረ። በዚህ መሠረት አባቱን ቅዱስ ላሊበላን አስፈቅዶ እርሱ ጀምሮት የነበረውን የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያንን እንደሰራ በገድሉ ተጽፏል። ያነጻትንም ቤተ ክርስቲያን ደብረ ጽዮን ብሎ ሰይሞ ህዳር 21 ቀን ታቦቷ ገባች። ❤ ከዕለታት አንድ ቀን እቴጌይቱ ቅድስት መስቀል ክብራም በመንፈስ ቅዱስ ተመርታ ለቅዱስ ላሊበላ እንዲህ አለችው። "እንግዲህ የመግሥትህ ፍፃሜ እየደረሰ ነውና ለነአኵቶ ለአብ ትሰጠው ዘንድ ከወዲሁ አስተዳደር እንዲማር የአንድ አውራጃ ገዥ አድርገህ ሹመው አለችው። ቅዱስ ላሊበላም ነአከኵቶ ለአብን ጠርቶ መርቆ ሥርዓተ ንግሥና ፈጽሞ ሾመው ነአኵቶ ለአብ ግን አይገባኝም በማለት አብዝቶ ከተከራከረ በኋላ በሐዘንና በለቅሶ ተሾመ ቅዱስ ላሊበላ ባርኮ መርቆ ከሠራዊት ጋር ወደ ቆቅህና (ብሔረ ቆቅህና) ሰደደው። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ላሊበላ ሊያርፍ አቅራብያ ነአከኵቶ ለአብን እንደገና አስጠርቶ ይስሐቅ ያዕቆብን እንደመረቀው መንበረ ዙፋኑን አስቀምጦ በመሉ መንግስቱ በኢትዮጵያ ላይ አነገሠውና ከቅዱስ ላሊበላ ጥቂት ቀይቶ ሞተ፡፡ ነአኵቶ ለአብም እስከዚህ ድረስ እርሱም ሚስቱም በድንግልና ሲኖሩ ቅዱስ ሩፋኤል በራዕይ ተገልጦ ልጅ ተወልዳላችሁ ብሎ አበሰረው ነአከኵቶ ለአብም ድግልናው እንዳይሻርበት እያዘነ እያለቀሰ ሲጸልይ እመቤታችን ተገልጻ በራዕይ ድንግልናው እንደ ማይሻር ገልጣ አጽናናችው። ስለዚህ ለመጀርያ ጊዜ ሚስቱን ንጽሕትን አወቃት እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙም በሀይለ መስቀል ተባለ ይህ ልጅም በደምግባቱና በውበቱ የሚመስለው የሌለ በጣም መልከ መልካም በመሆኑ ነአኵቶ ለአብ ይህ "ልጅ በመልኩ እየተመካ ኃጢያት ሰርቶ የሞት ሞት ከሚሞትብኝ እባክ ፈጣርዬ ዛሬውኑ ውሰድልኝና በአንተ ስም ኄሮድስ ከአስፈጃቸው ሕፃናት ጋር ጨምርልኝ" ሲል በማልቀስ ፈጣሪን ለመነው ጌታም ልመናውን ተቀብሎ የካቲት 16 ቀን በሞት ለይቶ ወሰደው በዚህም ጊዜ ነአከኵቶ ለአብ ደስ ብሎት ታላቅ ግብዣ አደረገ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ነአከኵቶ ለአብ ከባለቤቱ ጋር ከአንድ ቀን በስተቀር ከዚያን በፊት ከዚም በኋላ ግኑኙነት አላደረጉም ምግብም ቢሆን ቀዳሚትና እሑድ እንዳይሻሩ የቤተ ማርያምን አፈርና ጥቂት የዘንጋዳ ቂጣ ይቀምስ ነበር እንጂ ዘወትር የሚዘጋጀውን የቤተ መንግሥት ምግብ አይመገብም ነበር። ❤ ከዚምህ በኋላ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ በተጋድሎው እየጨመረ በመሄዱ 30ሰው የማይችለው ድንጋይ በአንገቱ ላይ በማሰር ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም ብሎ የፈጸመውን ፀዋትኦ መከራ እያሰበ ላቡ ከምድር ወርዶ እስኪ ረጋ ድረስ ይሰግድ ነበር። አይሁድም እየተሳለቁበትና እየተዘባበቱበት የነበረውን መከራ በማስታወስ ዘወትር ያለቅስ ነበር። ቀን ከወርቅ ወንበር ሆኖ ሲታይ ህጋዊ ንጉሥ ይምሰል እንጂ በውስጡ ግን ማቅ ታጥቆ የከሸሎ እሾህ ከሰውነቱ በማስገባት ሲዋጋ ይኖር ነበር። ❤ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ እንደ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ የጌታን ሕማምና ሞት በማሰብ በፊቱ ሳቅ ቀርቶ ፈገግታ እንደማያውቅ ቅዱስ ገድል ያስረዳል። በዕለተ ዐርብ የችሎቱን ዙፋኑን አይዘረጋም ከ6 እስከ 9ሰዓት እጁን ዘርግቶ በ9 ሰዓት መራራ ነገር ይቀምስ ነበር። በሥግደትም ጊዜ በፊት በኋላ በቀኝ በግራ የሚዋጉ ጦሮችን በማድረግ የጌታ መወጋትን ያስታውስ ነበር።

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፫ (3) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ከኢየሩሳሌም አፈር አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኰሳቱ "ገዳሙ በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ ላደረጉት ለታላቁ አባት ለአቡነ ፍሬ ካህንና ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ፍሬ ካህን፡- ጻድቁን በመጀመሪያ ከጎጃም ተነሥተው በታዘዘ መልአክ መሪነት ትግራይ ደብረ በንኰል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ሄደው መንነው መነኰሱ፡፡ ጻድቁ ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው ሲሆኑ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ይታወቃሉ፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን ወንጌልን ሲሰብኩ ሙታንን እያስነሡ በሲኦል ውስጥ ስላለው መከራና ሥቃይ እንዲመሰክሩ ያደርጓቸው ነበር፡፡ ጻድቁ ሐይዳ ገዳም ታቦት ተቀርጾላቸው ገድል የተጻፈላቸው ቢሆንም ሙሉ ገድላቸው ታትሞ ለምእመኑ አልተዳረሰም፡፡ አቡነ ቶማስ ካረፉ በኋላ አቡነ ፍሬ ካህን ገዳማቸውን ተረክበው በጽድቅ መንገድ መነኰሳቱን አስተዳድረዋል፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኰሳቱ "ገዳሙን በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ አድርገዋቸዋል፡፡ ❤ አባታችን ሽሬ ደብረ ሐይዳ አቡነ ፍሬ ካህን የተባለ ትልቅ ገዳም አላቸው፡፡ ገዳሙ ከአቡነ ቶማስ ዘሐይዳ ገዳም ጋር አንድ ነው፡፡ ወደዚህ ገዳም ውስጥ ሥጋና ቅቤ ተበልቶም ሆነ ተይዞ መውጣት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ አልታየሁም ተብሎ በድብቅ ሥጋ ተይዞ ቢገባ ሥጋው ይተላል፡፡ ሥጋና ቅቤ የበላ ሰውም ዕለቱን በድፍረት ወደ ገዳሙ ቢገባ ሆዱ በኃይል ይነፋል በዚህም ይታወቅበታል፡፡ ከብቶችም ቢሆኑ ወደ ገዳሙ አይወጡም፣ ማንም ሳይመልሳቸው ራሳቸው ይመለሳሉ፡፡ የአቡነ ፍሬ ካህን ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ነው፡፡ ከአቡነ ፍሬ ካህን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን። https://t.me/Eotcw

ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡ 💚
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡ 💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️

❣❣❣የዚቅ ወረቦች @EOTCW

❣❣❣ተመየጢ ተመየጢ@EOTCW

❣❣❣ናሁ ተፈፀመ@EOTCW

❣❣❣ክበበ ጌራ ወርቅ @EOTCW

❣❣ብእሲተ ሰማይ@EOTCW