fa
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

رفتن به کانال در Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite

نمایش بیشتر
3 595
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+47 روز
-2030 روز
آرشیو پست ها
ማስታወቂያ፦ ለተከበራችሁ የማኅበራችን አባላት! ከዚህ ቀደም ሲል የ “Claims Management” ሥልጠና በማኅበራችን በኩል ለመስጠት ታስቦ ፍላጎት ያላችሁ አባላት እንድትመዘገቡ ጥሪ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡ በዚሁ ጥሪ መሠረትም የየአባል ድርጅቶቹ ባለቤቶች በእራሳቸው ሥልጠናውን ለመውሰድ በመሻት የተመዘገቡ እንዳሉ ሁሉ በየአባል ድርቶቹ ውስጥ የሚገኙ በተለያየ የሥራ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሙያተኞችም ሥልጠናውን እንዲወስዱ ስማቸው እንደተላለፈልን ይታወቃል፡፡ ይሁንና ይህን ሥልጠና በመጀመሪያ እንዲወስዱ በማኅበራችን በኩል የታቀደው እራሳቸው የየአባል ድርጅቶቹ ባለቤቶችን ሲሆን ይህም ሲታቀድ ተከታታይነት ያለው ሰፊ ሥራ ለመሥራት በማሰብና የሥራ መመሪያ (Working Manual) እንዲዘጋጅ ለማድረግ በማለምም ነው፡፡ ይህም ማኅበሩን ወጪ የሚያስወጣው ሆኖ ስለተገኘ የየአባል ድርጅቶቹ ባለቤቶች አሁን በታቀደው ሥልጠና ላይ እንዲካፈሉ ሆኖ ዓላመውን በተጨባጭ በመረዳት ከዚህ አንፃር ለምናደርገው የሥራ እንቅስቃሴም ማኅበሩን በፋይናንስ እንዲያግዙ አስበን በመሆኑ የየአባል ድርጅቶቹ ባለቤቶች ትመዘገቡ ዘንድ በታላቅ አክብሮትና ትህትና ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር

በአዲስ_አበባ_ቤቶች_ልማትና_አስተዳደር_ቢሮ_የአዲስ_አበባ_ቤቶች_ልማት_ኮርፖሬሽን.pdf9.39 KB

በአዲስ_አበባ_ቤቶች_ልማትና_አስተዳደር_ቢሮ_የአዲስ_አበባ_ቤቶች_ልማት_ኮርፖሬሽን.pdf9.39 KB

ማስታወቂያ: ለነባር እና ለአዳዲስ ስራ ተቋራጮች እና ማህበራት በሙሉ ፡- የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከቤት ልማቱ ጎን ለጎን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር በኢኮኖሚው ተጠቃሚ ሲያደርግ የቆየና እያደረገም ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ በሚኖረው የግንባታ ፕሮጀክቶች በዘርፉ የተሠማሩ ስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን አሳታፊ አድርጎ ለመስራት ያሰበና ለዚህም ይረዳው ዘንድ በከተማችን ያሉትን የስራ ተቋራጮችንና ማህበራትን በመመዝገብ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ እና መመልመል አስፈላጊ ሆኖ ማግኘቱን በቅርቡ በተቋሙ ማህበራዊ ድረ-ገጽ አሳውቋል፡፡ በዚህም መሰረት ለነባር እና አዳዲስ ተመዝጋቢዎች ከቀን 13/10/2015 - 27/10/2015 ዓ.ም ድረስ ለለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት online ምዝገባ ማካሄድ እንደሚጀመር እየገለጽን ከዚህ በታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) https://www.aahdc.gov.et በመጫን እና የሚጠይቀውን መረጃ በአግባቡ በማስገባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡- በነባር፡- በተቋማችንና በተለያዩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ትስስር ተደርጎላችሁ ስትሠሩ የነበራችሁ ስራ ተቋራጮችና ማህበራት ነባር በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማድረግ ያለባችሁ ሲሆን፤ በአዲስ፡- ከዚህ በፊት በተቋማችንም ሆነ በቅርንጫፍ ፅ/ቤቶቻችን ስር ምንም ዓይነት የስራ ትስስር ያልተደረገላችሁ አዲስ በሚለው ስር ምዝገባችሁን ማካሄድ ትችላላችሁ፡፡ ለምዝገባ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በድጋሚ ለማስታወስ ያህል፡- - የታደሰ ንግድ ፍቃድ - የግበር መክፈያ መለያ ቁጥር( Tax        Identification Number- TIN.) - የስም ስያሜ ምዝገባ ሰርተፊኬት - የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት - የስራ ልምድ ከ1-2 ገፅ በማይበልጥ   በዝርዝር ይጠቀስ - የስራ ልምድ ክብደት በገንዘብ ሲቀየር     የሚያሳዩ መረጃዎች -  እና ሌሎች ስራ ተቋራጩን እና    ማህበራቱን የሚገልጹ ሰነዶችን   ናቸው ማሳሰቢያ፡- ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ከሚመለከተው አካል በሚላከው መረጃ መሠረትና በተቋማችን ባለው መረጃ መሠረት ወደ ስራ ሲገባ በነባር መመዝገብ እያለባችሁ በአዲስ ተመዝግባችሁ የተገኛችሁት ላይ እንዲሁም በሁለቱም (በነባርም፣በአዲስም) ተመዝግቦ የሚገኝ ስራ ተቋራጭም ሆነ ማህበራት ላይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

INVITATION FOR  RETENDERING IFB No. ECWCT/NCB/PW-128/2015 1. The Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) hereby invites registered eligible bidders for TO SUPPLY AND FIX OF METAL WORKS  2. Interested Potential Bidders are required to present renewed relevant Trade License for the Ethiopian fiscal year, VAT Registration Certificate, Tax Clearance Certificate and Online Supplier list Registration Certificate together with their offer. 3. Bidding document should be prepared in English language. 4. Interested Potential Bidders obtain a complete set of bidding document from the office of Procurement Department against payment of none refundable fee of Birr 300.00 upon presentation of Trade License renewed for the fiscal year. 5. This invitation of bid is open to all interested potential bidders regardless of their nationality and the bid evaluation and award shall be determined in accordance with the provision indicated in bidding document. 6.  The deadline for bid Submission shall be on June 28, 2023, at 08:00 (Local Time) 7. Bid must be accompanied with a Bid Security of an amount of Birr Birr 300,000.00 ETB (Three hundred thousand) in the form of certified cheque (CPO) or Bank guarantee. Bid Bond in the form of insurance bond or in any other form shall not be accepted. 8. Bids must be delivered or deposited in the Tender Box situated at the office of the Procurement Department on June  28, 2023, at 08:30 (Local Time). in Ethiopian Construction Works Corporation Procurement Department conference room, in the presence of bidders and/or their representatives who choose to attend. 10. The Ethiopian Construction Works Corporation reserves its rights to reject any or all bids. 11. Bidders may get further information at the following address: Ethiopian Construction Works Corporation Address: - Gurd shola behind Athletics Federation Building In front of Andinet International school Telephone No.011 8 72 29 58/ 0118 72 30 86/011 896 29 91

ማስታወቂያ: ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት! የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ከመጪው ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል በመንግሥት የተወሰነውን የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት የተመለከተ የውይይት መርኃ-ግብር አዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በመጪው ሰኔ 13 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል በሚዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በዚህ የግዥ ሥርዓት የተመዘገባችሁ አባላትም ሆናችሁ ያልተመዘገባችሁት የማኅበራችን አባላት እንዲሁም መላው የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች በዚሁ የውይይት መርኃ-ግብር ላይ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡ በተለይ በዚህ በአዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ያልተመዘገባችሁት የማኅበራችን አባላትም ሆናችሁ ያልተመዘገባችሁት መላው ሥራ ተቋራጮች ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የመንግሥታዊ ግዥ ሥርዓት ውስጥ ተሳታፊ መሆን የሚችሉት በአዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ውስጥ የታቀፉ ሥራ ተቋራጮች ብቻ መሆናቸውን ከወዲሁ ተገንዝባችሁ በመርኃ-ግብሩ ላይ ተሳታፊ እንድትሆኑ አጥብቀን እንመክራለን፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር

A_Groundbreaking_Journey_with_the_Ethiopian_Securities_Exchange.pdf6.22 KB