fa
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

رفتن به کانال در Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite

نمایش بیشتر
3 607
مشترکین
-324 ساعت
-77 روز
+1130 روز
آرشیو پست ها
የጥቅምት_ወር_2018_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ_11.PDF3.15 MB

ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኖች ኪራይ ጨረታ

🚨የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስባቸው አራት ምክንያቶች በፌደራል ግዥ አዋጅ 1333/2016 መሠረት በማንኛውም ተጫራች የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ሊወረስ ይችላል። 1⃣ ጨ
🚨የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስባቸው አራት ምክንያቶች በፌደራል ግዥ አዋጅ 1333/2016 መሠረት በማንኛውም ተጫራች የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ሊወረስ ይችላል። 1⃣ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ጨረታው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ካገለለ ወይም፣ 2⃣ ጨረታው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ ተጫራች መሆኑ በፅሑፍ ተገልጾለት፣ ውል ለመፈረም፣ የገዛውን ንብረት ለማንሳት ወይም የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ፣  3⃣ በተጫራቹ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ላይ የሂሳብ እርማት ተደርጎ ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ፤ 4⃣ ተጫራቹ የማጭበርበር ወይም የማታለል ወይም ከሌሎች ተጫራቾች ጋር የመመሳጠር ወይም መረጃ የመደበቅ ድርጊቶችን መፈፀሙ ሥልጣን ባለው አካል የተረጋገጠ ከሆነ ናቸው። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👵 Discussion: @procinsightet2

የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ አቅራቢው ባውሚት ኦስትሪያ ወደ ኢትዮጵያ ገባ ▭‼️➖ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ባውሚት ኦስትሪያ መካከል በነበረው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቃቸው የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ  ኮርፖሬሽኑና ባውሚት ኦስትሪያ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ስምምነት ፈጽመዋል። ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ሚስተር ኤድዋርድ አርትነር ተፈራርመዋል፡፡ የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ እና የባውሚት አፍሪካና ኤዥያ ብቸኛ ወኪል የሆነው የካሳ ዲ አርጂላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሮላንድ ጃንሰን የጫካ ሳተላይት ከተማ ፕሮጀክትን፣ በአዲስ አበባ ከተማ እተከናወኑ ያሉትን ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ለማድረግ ያከናወነውን የቅድመ ዝግጅት ስራም ተዘዋውረው ተመልተዋል፡፡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ሁለንተናዊ አመራር ሰጭነት ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ተምሳሌት ሀገር በመሆኗ በቤት ልማት  ዘርፍ በቴክኖሎጂ አቅርቦት ጠንካራ ተሳትፎ እንደሚያደርግም ነው የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ የገለጹት፡፡ ተዘዋውረው በተመለከቱት አስደናቂ አገራዊ የልማት ሥራና ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ለማድረግ በኮርፖሬሽኑ በኩል በተከናወኑት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መደሰታቸውን ገልጸው፣ የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ አቅርቦት በአጭር ጊዜ ለመፈጸም ስምምነት  ላይ ለመድረስ ኩባንያቸው መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
የ3D ተክኖሎጂ ቤትን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በአጭር ጊዜ በማቅረብ የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ከመሰረቱ እንደሚቀይረው ያላቸው እምነት የገልጹት ሚስተር ኤድዋርድ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ ለሚገነቡት ቤቶችን  ባውሚት ኦስትሪያ የገንዘብና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
 የባውሚት ኦስትሪያ አፍሪካና የኢዥያ ወኪል ካሳ ዲ አርጅላ በአንድ ዓመት ውስጥ የ3D ኮንክሪት ቴክነኖሎጂን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም  ሚስተር ኤድዋርድ ተናግረዋል፡፡
የባውሚት ኦስትሪያ 3D ኮንክሪት ተክኖሎጂ አቅርቦትና ተከላ፣ የእውቀት ሽግግር እና ሥልጠና ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን  የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ የወቅቱ የከተሞች ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ከመሰረቱ ለመቅረፍ ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው፡፡ ቤት ከመገንባት ወደ ማምረት የሚያስችለንን የ3D ኮንክሪት ቴክኖሎጂን ትግበራን በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ ሙሉ ሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ ከባውሚት ኦስትሪያ ጋር እንደሚሠራም ተናግረዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ እና የአገራዊ ቤት ልማት እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነቱ ትልቅ ሚና እንሚኖረው አቶ ረሻድ ተናግረዋል፡፡

የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ አቅራቢው ባውሚት ኦስትሪያ ወደ ኢትዮጵያ ገባ ▭‼️➖ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እና ባውሚት ኦስትሪያ መካከል በነበረው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቃቸው የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑና ባውሚት ኦስትሪያ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ስምምነት ፈጽመዋል። ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማልና የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ አርትነር ተፈራርመዋል፡፡ የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ እና የባውሚት አፍሪካና ኤዥያ ብቸኛ ወኪል የሆነው የካሳ ዲ አርጂላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ሮላንድ ጃንሰን የጫካ ሳተላይት ከተማ ፕሮጀክትን፣ በአዲስ አበባ ከተማ እተከናወኑ ያሉትን ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ለማድረግ ያከናወነውን የቅድመ ዝግጅት ስራም ተዘዋውረው ተመልተዋል፡፡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ሁለንተናዊ አመራር ሰጭነት ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ተምሳሌት ሀገር በመሆኗ በቤት ልማት ዘርፍ በቴክኖሎጂ አቅርቦት ጠንካራ ተሳትፎ እንደሚያደርግም ነው የባውሚት ኦስትሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ኤድዋርድ የገለጹት፡፡ ተዘዋውረው በተመለከቱት አስደናቂ አገራዊ የልማት ሥራና ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ለማድረግ በኮርፖሬሽኑ በኩል በተከናወኑት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መደሰታቸውን ገልጸው፣ የ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ አቅርቦት በአጭር ጊዜ ለመፈጸም ስምምነት ላይ ለመድረስ ኩባንያቸው መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
የ3D ተክኖሎጂ ቤትን በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት በአጭር ጊዜ በማቅረብ የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ከመሰረቱ እንደሚቀይረው ያላቸው እምነት የገልጹት ሚስተር ኤድዋርድ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በ3D ኮንክሪት ፕሪንት ቴክኖሎጂ ለሚገነቡት ቤቶችን ባውሚት ኦስትሪያ የገንዘብና የቴክኖሎጂ አቅርቦት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
 የባውሚት ኦስትሪያ አፍሪካና የኢዥያ ወኪል ካሳ ዲ አርጅላ በአንድ ዓመት ውስጥ የ3D ኮንክሪት ቴክነኖሎጂን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ሚስተር ኤድዋርድ ተናግረዋል፡፡
የባውሚት ኦስትሪያ 3D ኮንክሪት ተክኖሎጂ አቅርቦትና ተከላ፣ የእውቀት ሽግግር እና ሥልጠና ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ የወቅቱ የከተሞች ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ከመሰረቱ ለመቅረፍ ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ነው፡፡ ቤት ከመገንባት ወደ ማምረት የሚያስችለንን የ3D ኮንክሪት ቴክኖሎጂን ትግበራን በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ ሙሉ ሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ኮርፖሬሽኑ ከባውሚት ኦስትሪያ ጋር እንደሚሠራም ተናግረዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ እና የአገራዊ ቤት ልማት እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነቱ ትልቅ ሚና እንሚኖረው አቶ ረሻድ ተናግረዋል፡፡ ▪️▫️▪️ ኢንፍራኮን ሚዲያን ፎሎው እና ሼር ያድርጉ! የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ t.me/infraconmedia

ⓂIRACLE METAL SHOP _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ ምን ለመገንባት እያሰቡ ነው መኖሪያ ቤት ወይንስ ህንፃ ለየትኛውም ግንባታ ወሳኝ የሆነውን የአርማታ ብረት ፌሮ በከ
+9
ⓂIRACLE METAL SHOP _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _   ምን ለመገንባት እያሰቡ ነው መኖሪያ ቤት ወይንስ ህንፃ ለየትኛውም ግንባታ ወሳኝ የሆነውን የአርማታ ብረት ፌሮ በከፍተኛ ጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ የት እንደሚያገኙ ሀሳብ ሆኖብዎታል ? እንግዲያውስ እኛ ጋር ይምጡ በደስታ ተቀብለን በምቾት እናስተናግዶታለን ሚራክል ፌሮ አከፋፋይ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ በሀገራችን ባሉ ፋብሪካዎች የተመረቱ እና ከቱርክ የመጡ  ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግሬድ 75 የሆኑ ፌሮዎችን እንሸጣለን የምንሸጣቸው ፌሮዎች         ለ 1=Beam(ቢም) 2=Column(ኮለን) 3=Slab(ስላቭ ) 4=Mesh(ሜሽ) የሚሆኑ ናቸው ከእኛ ጋር ሲገበያዩ 1= አስተማማኝ(ሰፊ) አቅርቦት 2= ተመጣጣኝ ዋጋ 3=ምቹ ቀላልና አስተማማኝ የአከፋፈል ሁኔታ 4=ነፃ የትራንስፖርት አቅርቦት በተጨማሪም ለኮንትራክተርና ለቸርቻሪ ነጋዴ ልዩ ቅናሽ እናደርጋለን። አብረን እንስራ ለሚሉ ደላላዎች በራችን ክፍት ነው። አድራሻችን:- ቁ.1= ተክለሃይማኖት                    ቁ.2=ጎጃም በረንዳ ስልክ ~     +251955868655                  +251955878755 ዋጋ ለማየት በዚህ ሊንክ ይጠቀሙ https://t.me/miraclemetalshop ሁሌም በጥራት!

የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ ሰነድ እየተሸጠ ነው እንዳይዘናጉ ፈጥነው ይግዙ
የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ ሰነድ እየተሸጠ ነው እንዳይዘናጉ ፈጥነው ይግዙ

የ ሙያ ፍቃድ / professional license🪪 /ለማውጣት ምን ያስፈልጋል http://www.eservices.gov.et 🌎 ከላይ በተቀመጠው ዋብሳይት በመግባት user Account በመክፈት የ
የ ሙያ ፍቃድ / professional license🪪 /ለማውጣት ምን ያስፈልጋል http://www.eservices.gov.et 🌎 ከላይ በተቀመጠው ዋብሳይት በመግባት user Account በመክፈት የ ሙያ ፍቃድ ማውጣት ትችላላችሁ። ይህ የ ሙያ ፍቃድ ዲዛይን ስታደርጉ Title block ላይ ከ ስማችሁ ጎን Registration Number / የምዝገባ ቁጥር ይያያዝላችኋል ። https://constructionproxy.com/construction-certification-and-registration-regulation-directive-no-648-2021/

موقعیت جغرافیایی

🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱 Red brick:- This is the classic brick color that you see Quality with affordable price 🧱ጥራ
🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱 Red brick:- This is the classic brick color that you see Quality with affordable price 🧱ጥራት ያላቸውን እና ለተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የቀይ ሸክላ (ጡቦችን) እናመርታለን። 🧱 ለሙሉ የቤት ግንባታ፣ 🧱ለባንክ ቤት ካዝና፣ 🧱 ለግቢ አጥር ማጠሪያ፣ 🧱 ለመንገድ ዳር ጠርዞች፣ 🧱  ለሆቴሎች፣ሬስቶራንት፣እና ካፌዎች ማሳመሪያ ፣ 🧱 ለx-ray ክፍሎች፣ 🧱 ለፍሳሽ ማንዋሎች፣ 🧱 ለኪችን ሲንክ ማስቀመጫ ፣ 🧱 ለሻወር ገንዳ ማሰቀመጫ፣ 🧱 የPBC ፍሳሽ ማስወገጃ ለመሸፈን፣ 🧱 ለአበባ መትከያ 🧱 ለብረት ማቅለጫ ፈርኒስ፣ 🧱 ለፒዛ ኦቭን፣ 🧱 ለምድጃ፣ 🧱 ለቆሻሻ ማቃጠያ፣ *We produced High quality clay bricks for various construction purposes. 🧱 For building construction, 🧱 For bank vaults, 🧱 Fence for the yard, 🧱 For road edges, 🧱 For Hotels,Restaurants,and Cafes decoration, 🧱 For x-ray rooms, 🧱 For manuals, 🧱 For kitchen, 🧱 For shower tray 🧱 To cover PBC drains, 🧱 For garden, 🧱 Furnace For steel factory, 🧱 For pizza oven, 🧱 For waste incinerator.... 🧱 For more information join our telegram channelhttps://t.me/+d8A-rQlF5p5lZThk & Ticktok account @newpointbricksfactory 🧱Order now 📲0912854327,0902378888 🧱"Quality is our first priority" Thank you 谢谢🧱

የአርማታ ሙሌታ (Concrete Compaction) ቁጥጥር 1. የግብአት ጥራትን (Materials Quality)፦ በአርማታ ሙሌት ሥራ ሂደት ውስጥ የሚጠቀማቸውን የማምረቻ ግብአቶች ጥራት በተገለጸው መስፈርት መሰረት የሚያሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ይህ ማለት የቀረበው ሲሚንቶ (Cement) አይነትና የምርጥ ጥራት፣ የአሸዋ (sand or Fine aggregate) እና ጠጠር (Coarse Aggregate)ሳይንሳዊ ምዘናን ማሟላቱን፣ የማቅጠኛ ውሀ (Water) የኮንክሬት ስትራክቸሩን ሊጎዳ የሚችል ኬሚካልና ቆሻሻ የሌለው የጠራ ውሃ መሆኑን እና ሌሎች ተጨማሪ ኬሚካል (Admixture) መለያ አይነት የተሟላ መሆኑን ሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ ተደግፎ የማረጋገጥ ሂደትን መተግበር ማለት ነው። በዚህ ረገድ የግብአት መሐንዲሱ (Materials Engineer) ለሳይቱ በቀረበው የቤተሙከራ ክፍል ውስጥ በመስራት የማረጋገጥ አልያም በቅርቡ በሚገኝ የቤተሙከራ አገልግሎት ሰጪ ተቋማ በማሰራት የግብአቶችን ጸባይ የመለየትና ማረጋገጫ የመስጠት ግዴታ ይኖርበታል። 2. የግብአቶችን ልኬት (Batching of materials):- በተለይ በሀገራችን የግንባታ ልምድ ኮንክሬት በሚመረትበት ሰዓት ያለው የአሸዋ፣ የጠጠር እና የውሃ ልኬት ለችግር የተጋለጠ ነው። አንድ 1፡2፡3 ምጥጥንን መሰረት አድርጎ ዲዛይን የተሰራ አርማታ አንድ እጅ ሲሚንቶ፣ ሁለት እጅ አሸዋ፣ ሦስት እጅ ጠጠር መጠቀም አለበት ማለት ቢሆንም የመቀላቀያ ማሽኑ ተቆጣጣሪ (Mixer Operator) ይህንን ምጥጥን ጠብቆ አምራታ የማምረት ልምድ ቸልተኝነት የተሞላበት እንደሆነ ይስተዋላል። ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በምጥጥን (Proportion) መሰረት እየተመረት መሆኑን መቆጣጠር የግድ ነው። 3. የማሽን እና መሳሪያ ደህንነት (Equipments Security):- የኮንክሬት ድብልቅ ማምረቻ ማሽኖች (mixers) ደህንነታቸው የተረጋገጠ ወይም በአግባቡ የሚሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የኮንክሬት ግብአቶችን መለኪያ ሳጥኖችን (box) ርዝመት ወርድ እና ቀመት (L, W, H) አግባብነት ያለው መሆኑን (ለምሳሌ፦ 18*40*50)፣ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ብሎም የካሳ ሙግትና የሥራ ማቆም መሰናክል እንዳይፈጠር የሰራተኞች ደህንነት መጠበቂያ አልባሳት የተሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። 4. በአግባቡ መጠቅጠቁን፦ የሚሞላው አርማታ በተለይ ምሰሶ (column) እና የምሰሶ ጫማ (Footing Pad) በክፍልፋይ ላየሮች ከፋፍሎ እያንዳንዱ የላየር ክፍል ጫፍ ላይ ሲደርስ በኤሌክትሪክ መንዘሪያ (Vibrator) በደንብ መጠቅጠቅ መቻል አለበት። የአርማታ መጠቅጠቅ እያንዳንዱ የግንባታ ግብአት በአግባቡ የተሰራጨ እንዲሆን እና የቀጠነው አርማታ ወደታች ወርዶ ጠጠራማው ወደላይ እንዳይቀር በማድረግ የትኛውም የስትራክቸር ክፍል ተመሳሳይ አይነት ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርጋል። 5. የአርማታ ድርቀት እንዳይኖር መቆጣጠር፦ የአርማታ ሙሌት ሂደት ላይ አዲስ የተመረተ አርማታ አላስፈላጊ ደቂቃዎችን ሳይሞላ መቆየት የለበትም። አርማታ ሳይሞላ ከሚክሰር እንደተገለበጠ የሚቆይ ከሆነ በፎርምወርክ ውስጥ ሆኖ መያዝ ያለበትን የመጀመሪያ ጥንካሬ (Initial Setting) መያዝ ስለሚጀምር ከዚያ በኋላ ሙሌትን ለማከናወን አዳጋች ከመሆኑም በላይ የሚፈለገውን የኮንክሬት ስትራክቸር ጥንካሬ ለማግኘት አዳጋች ይሆናል። https://t.me/ethioengineers1

የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም /CRIS/ ማስጀመሪያ መረሀ ግብር ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ሚንስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካ
+1
የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም /CRIS/ ማስጀመሪያ መረሀ ግብር ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ሚንስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የዲጅታል ሬጉላቶሪ ሲስተም ትግበራ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በሳይንስ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል። https://t.me/ethioconradio

UPVC ከአልሙኒየም ይልቅ ተመራጭ የሚያደርገው ውበቱ ብቻ ሳይሆን፣ ለረጅም ጊዜ ሳይዝግ፣ ቀለሙ ሳይለቅ፣ ሳያረጅ መቆየቱ እና በዋጋ ተመጣጣኝ መሆኑም ጭምር ነው! የUPVC ማቴሪያሎችን በመጠቀም በተ
UPVC ከአልሙኒየም ይልቅ ተመራጭ የሚያደርገው ውበቱ ብቻ ሳይሆን፣ ለረጅም ጊዜ ሳይዝግ፣ ቀለሙ ሳይለቅ፣ ሳያረጅ መቆየቱ እና በዋጋ ተመጣጣኝ መሆኑም ጭምር ነው! የUPVC ማቴሪያሎችን በመጠቀም በተለያዩ ዲዛይኖች በሮች፣ መስኮቶችና ፓርቲሽኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ አምርተን በራሳችን ባለሙያዎች ያሉበት ቦታ ድረስ መጥተን እንገጥማለን! 📍 Location: ጋዜቦ አደባባይ፣ ሙልሙል ዳቦ ቤት አጠገብ 📞 Call us: 0930099146,0930099145 The door is the face of a home; beauty begins there

በ40/60 የጋራ ሕንፃዎች ላይ የሚገኙ የንግድ ቤቶች ጨረታ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ ➖▭‼️▭➖ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክ/ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀቁ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ ከነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከጨረታ ተሳታፊዎች ፍላጎት በመነሳት እና ለዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መመለሻ በቂ ጊዜ ለመስጠት ሲባል የጨረታ ሰነድ መሸጫና መመለሻ ጊዜን ማራዘም አስፈላጊ መሆኑ በኮርፖሬሽኑ ስለታመነበት ከመስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር/10 ተከታታይ የሥራ ቀናት/ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ/የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፤ ጨረታው ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በጨረታ መመሪያው በተገለጸው ቅደም ተከተል መሠረት ከጥቅምት 08 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን