fa
Feedback
𝐁𝐞𝐧𝐚𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡𝐧𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲

𝐁𝐞𝐧𝐚𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡𝐧𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲

رفتن به کانال در Telegram

💻የተማሩትን ማስተማር ያወቁትን ማሳወቅ ቅንነት ነው! ይህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ የምላቸውን ስለ ኮምፒውተር ትምህርቶች፤እንድሁም ከቴክኖሎጅ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና እውቀቶችን የማካፍልበት ቻናሌ ነው! 📶ወንድማችሁ፦ሁሰይን አል-በናን(አቡ ሱፍያን)

نمایش بیشتر
1 696
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-4030 عوز
آرشیو پست ها
​​✳️ Cloud Storage ምንድነው❓ 🔺 ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የ
​​✳️ Cloud Storage ምንድነው❓ 🔺 ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡ 🔺በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዩ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋሉ፡፡ 🔺መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጅ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን ማግኘት እንችላለን። 🔺ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡  🔺በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን እና ብዛት ነው፡፡

✳️ ስልኮ እየተጠቀሙበት በመሃል መስራት ያቆማል? ለምን? መፍትሄውስ: ◻️ስልኮ በጣሙን የሚዘገይ አልያም አልታዘዝ ካሎት ስልኮ የሆነ ችግር ገጥሞታል ማለት ሲሆን ለዚህ አይነት ችግር መንስዔ የሚሆኑ መነሻዎችን ከነመፍትሄዎቻቸዉ ጋር እንደሚከተሉት አቅርበንሎታልና ይተግብሯቸዉ፡፡ 🔺ከስልኮ ላይ የአላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መኖር ከስልኮ ላይ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ያጥፉ፡፡ ለምሳሌ ጌሞች የፎቶ እና ቪዲዮ ማሳመሪያ ኤዲትኢንግ ሶፍትዌሮች የተለያዩ የሙዚቃም ይሁን የቪዲዮ ማጫወቻ ፕሌየሮች ስልኮ ላይ ካለ በተቻለ መጠን የሚፈልጉትን አፕሊኬሽን ብቻ ትተዉ ሌላዉን በአብዛኛዉ የማይጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች ያጥፉ፡፡        🔺የስልኮ ዳታ መያዣ ስቶሬጅ በፋይሎች መጨናነቅ በስልኮ ሜሞሪ ላይ ብዛት ያላቸዉ ሙዚቃዎች ቪዲዮች አፕሊኬሽኖች የማያስፈልጋችሁን አስቀምጠዉ ከሆነ በተቻለ መጠን የማይፈልጉትን ቢያጠፉ አልያም ከቆይታ በኋላ ብፈልጋቸዉ አላገኛቸዉም ካሉ በሌላ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ሜሞሪ ያስቀምጡት፡፡ 🔺የስልኮን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ስልክዎ ላይ ያለን ሶፍትዌር አለማደስ: ስልኮ ያሉትን ሶፍትዌሮች እና ስልኮን ያለማደስ ስልኮን ለሌላ ቫይረስ አልያም ጎጂ ሶፍትዌር ያጋልጣል ይህም የስልኮን ፕሮግራሞች ሳይዘጉ ከኋላ እንዲነሳ (background play) ስለሚያደርገዉ ስልኮንና የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ያድሱት፡፡ 🔺ካች (Cache) ዳታን አለማፅዳት ካች ዳታ የምንላዉ አብዛኛዉን ጊዜ የምንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮችና ፋይሎች ስልካችን የሚያስቀምጥበት ቦታ ሲሆን ስልካችንን መረጃን በማመላለስ (loading data) ጊዜን እና ቦታ ተጣቦ ከመዘግየትና ከመቆም ያደናል ስለዚህ የስላካችንን ካች ማፀዳት ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡ #Tech_Tips

​✳️ የኮምፒውተር ቫይረስ ሰለባ መሆንዎን እንዴት ማወቅ ይችላሉ? 🔺ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቋረጥ፡ ከዚህ ቀደም ድንገተኛ የሆነ የአገልግሎት መቆራረጥ አጋጥሞዎት በተደጋጋሚ ሰማያዊ ቀለም ያለው ገጽታ የሚያሳይ ከሆነ ኮምፒውተርዎ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቋሚ ነው፡፡ 🔺የኮምፒውተር ስርዓት ማዝገም Slow System በሲስተምዎ ላይ ብዙ ቦታ የማይፈልጉ መተግበሪያዎችን (Apps) ሳይጠቀሙ የኮምፒውተር ስርዓቱ ዝግ ማለት የኮምፒውተርዎ ስርዓት በቫይረስ መጠቃትን አመላካች ነው። 🔺ከልክ ያለፈ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴ (Excessive Hard Drive Activity) ምንም እንኳን ኮምፒተርዎ ስራ እየሰራ ባይሆንም ጥቂት የማይባሉ የሃርድ ድራይቭ እንቅስቃሴን ካስተዋሉ ይህ ምናልባትም በቫይረስ ስለመጠቃትዎ የማስጠንቀቂያ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ 🔺ያልተለመዱ የዊንዶው ምልክቶች ሲስተዋሉ ኮምፒውተርዎን በሚከፍቱበት ወቅት እንግዳ የሆኑ ነገሮች ብቅ ካሉ እና በተለይ በኮምፒተርዎ ላይ የተለያዩ ድራይቭዎች Drive ከጠፉ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡ 🔺መጥፎ የፕሮግራም እንቅስቃሴ ፕሮግራሞችዎ ከጠፉ ፣ ከተበላሹ ፣ ወይም ያለ እርስዎ ፍቃድ እራሳቸውን በራሳቸው መክፈት ከጀመሩ ፣ እንዲሁም ያለ እርስዎ ትእዛዝ ኢንተርኔት ለመድረስ እየሞከረ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከደረሰዎ ይህም የቫይረስ ሰለባ መሆንዎን ጠቋሚ ነው፡፡ 🔺የዘፈቀደ አውታረ-መረብ እንቅስቃሴ Random Network Activity ምንም ጉልህ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወደስራ ሳያስገቡ አልያም ከፍተኛ የበይነ-መረብ ዳታን በማይጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ ራውተር በቋሚነት ብልጭ ድርግም የሚል ምልክት የሚያሳይ ከሆነ፣ የሆነ ችግር መፈጠሩን አመላካች ነው፡፡ #Antivirus_Tips

​​✳️ ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች! ◽️ ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶወች (ዋልፔፐር) አይጠቀሙ፡፡ ◽️ ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡ ◽️ አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡ ◽️ የማይጠቀሙበት አፕሊኬሽን ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት። ◽️ ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡ ◽️ ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ። ◽️ Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ:: ◽️ ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡ ◽️ ብዙ አፕሊኬሽን ባንዴ አይክፈቱ:: =t.me/Benan_Tech

ቴሌግራም ላይ story የምታደርጉ ከሆነ ልታውቋቸው የሚገቡ ቲፖችን 1. story ላይ ፎቶ add ስታደርጉ የፎቶውን background remove ማድረግ ትችላላችሁ። ይህን ለማድረግ add ያደረጋችሁት ን ፎቶ ጫን አድርጋችሁ ይዛችሁ Cut Out የሚለውን መንካት ነው። 2. የትኛውም የቴሌግራም ቻናል ላይ ያለ post story ማድረግ ትችላላችሁ። ይህን ለማድረግ የፖስቱ ጫፍ ላይ የቀስት (share) ምልክቱኑን ነክታችሁ Repost to story የሚለውን በመንካት story ማድረግ ትችላላችሁ። ስቶሪውን የሚያይ ሰው Read more የሚለውን በመንካት ወደ original የቻናሉ ፖስት ሄዶ ሙሉውን ማንበብ ይችላል። ቻናል ካላችሁ ቻናላችሁን ለማስተዋዎቅ ይጠቅማችኋል። (ለመሞከር ይህን ፖስት ተጠቀሙ።) 3. story ያደረጋችሁትን ፖስት ያልፈለጋችሁት ሰው እንዳያይ ማድረግ ትችላላችሁ። ይህን ለማድረግ ስቶሪውን ካስተካከላችሁ በኋላ next ብላችሁ "Who can view your story" ከሚለው ስር "Select people who will never see your stories." የሚል አለ ያልፈለጋችሁትን ሰው መምረጥ ትችላላችሁ። 4. story area ላይ የማትፈልጉትን ሰው story ማየት ካልፈለጋችሁ ጫን አድርጋችሁ ይዛችሁ "Hide Stories" ብላችሁ Hide ማድረግ ትችላላችሁ። 5. Story የሆነ ረጅም video የምታዩ ከሆነ ቪዲዮውን ጫን አድርጋችሁ በመያዝ fast forward ማድረግ ትችላላችሁ።

🌐AI |አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ | ምንድን ነው? AI በ5 ደቂቃ ለመረዳት! =t.me/AbuSufiyan_Albenan

ከዚህ በሁዋላ በሲቢኢ ፌክ Screenshot መታለል ቀረ - CBE Payment Checker bot. ~ይህ ቦት በሲቢኢ የተላከላቹን Screenshot Forward አድርጋችሁ በመላክ ትክክል እንደሆነና
ከዚህ በሁዋላ በሲቢኢ ፌክ Screenshot መታለል ቀረ - CBE Payment Checker bot. ~ይህ ቦት በሲቢኢ የተላከላቹን Screenshot Forward አድርጋችሁ በመላክ ትክክል እንደሆነና እንዳልሆነ Scan አድርጎ ያሳያችኋል። ቦቱ ይህ ነው 👉 @CBECheckerBot ⚠️ ይህ ቦት ለሚያስፈልጋቸው ሰው ሼር ማድረግ እንዳይረሱ። =t.me/AbuSufiyan_Albenan

እነዚህን ዌብሳይቶች ይጠቅሟችኋል። ቼክ አድርጓቸው። 1. pdfescape.com – quickly edit PDF in the browser without Acrobat. 2. wetransfer.com – for sharing really big files online. 3. web.skype.com — make voice and video calls in your browser with Skype. 4. snapdrop.com - Share files directly between devices in the same network without having to upload them to any server first. 5. privnote.com – create text notes that will self-destruct after being read. 6. youtube.com/webcam — broadcast yourself live over the Internet without any complicated setup. 7. onlineocr.net – recognize text from scanned PDFs 8. tinychat.com – setup your own private chat room in micro-seconds. 9. faxzero.com - send an online fax for free 10. urbandictionary.com – find definitions of slangs and informal words. 11. typingweb.com – master touch-typing and improve your typing speed. 12. stackblitz.com — a playground for building web projects in HTML, CSS and JavaScript. 13. todo.microsoft.com — a beautiful todo app and task manager.

Whatsapp ልክ እንደ Telegram ሁሉ channel create ማድረግ የምንችልበትን አሰራር ጀመረ። ዋትሳፕ ከቴሌግራም ጋ ለመፎካከር የሚያስችሉትን የተለያዩ ፊቸሮች እየጨመረ ይገኛል። ከነዚህ ውስጥ  Screen share Username Message editing አሁን ደግሞ የተለያዩ ሃሳቦችን ለተከታታዮቻችን share ማድረግ የምንችልበትን Whatsapp channel ይዞ ብቅ ብሏል። አሁን ያላችሁን Whatsapp application update አድርጉና updates የሚል ፎልደር አለ እሱ ውስጥ ታገኙታላችሁ። =t.me/Benan_Tech

ኑ! በዚህ ግሩፕ ዛሬ አድ የማድረግ ዘመቻ ነው! ⇘⇘ መጀመሪያ ጆያን ይበሉና ሌሎችንም አድ አድ አድርጉ! https://t.me/Benan_Group https://t.me/Benan_Group

☞አንድ በጣም ድንቅ የ YouTube Channel ልጠቁማችሁ ከ 6million በላይ Subscribers ያለው ከ Computer ጋር በተያያዘ በዚህ ቻናል የፈለጋችሁት መማር ትችላላችሁ የሚሰጡት Top
☞አንድ  በጣም ድንቅ የ YouTube Channel ልጠቁማችሁ ከ 6million በላይ Subscribers ያለው ከ Computer ጋር በተያያዘ በዚህ ቻናል የፈለጋችሁት መማር ትችላላችሁ የሚሰጡት Top Tutorials ⇛HTML Tutorial ⇛CSS Tutorial ⇛JavaScript Tutorial How To Tutorial ⇛SQL Tutorial ⇛Python Tutorial ⇛W3.CSS Tutorial ⇛Bootstrap Tutorial ⇛PHP Tutorial ⇛Java Tutorial ⇛C++ Tutorial ⇛jQuery Tutorial እነዚህ እና ሌሎችንም ለመማር ከፈለጋችሁ  ይሄንን ቻናል ብቻ ጎብኙት!⇙ https://youtube.com/c/Freecodecamp

ይህ ግሩፕ ማንኛውም ከ ቴክኖሎጁ ጋር የተያያዘ ጥያቄና ሐሳብ የምታቀርቡበት፣ እንድሁም ግልፅ ያልሆኑ ትምህርቶች ማብራሪያ የምትጠይቁበት ግሩፓችሁ ነው። ሁላችሁንም አድ አድ አድርጉ!⇘⇊ https://t.me/Benan_Group https://t.me/Benan_Group

✳️ ቴክኖሎጂያዊ እውነታዎች፡ ◽️ የመጀመሪያው እ.ኤ.አ. በ 1971 የተፈጠረው የኮምፒዩተር ቫይረስ “CREEPER” ተብሎ ይጠራ ነበር። ◽️ Google ፍየሎችን ይከራያል ፣ ይህ ቀልድ አይደለም!. በGoogle HQ ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ሳር የሚያጭዱት 200 ፍየሎች ናቸው። ◽️ አፕል እ.ኤ.አ. በ2014 የሚያስገባው ገቢ ሩብ ከጎግል ፌስቡክ እና አማዞን ተደምረው ከሚያገኙት ገቢ ጋር እኩል ነበር። ◽️ HP ፣ Google ፣ Microsoft እና Apple የአይቲ ኩባንያዎች ከመሆናቸው ውጭ አንድ የሚያመሳስላቸው ነገር ሁሉም የተጀመሩት በጋራጅ ውስጥ ነበር። ◽️ የጆሮ ማዳመጫ ወይም Earphone ለአንድ ሰዓት ብቻ ማድረግ በጆሮዎ ውስጥ የሚገኙትን ባክቴሪያዎች በ700 እጥፍ ሊጨምር ይችላል። ◽️ ከAndroid 1.0 እና 1.1 በስተቀር ሌሎች ሁሉም የAndroid ስሪቶች ጥቂቶችን ለመጥቀስ እንደ ጄሊ ቢን ፣ አይስክሬም ሳንድዊች ፣ ማር ማርብ በመሳሰሉ ጣፋጭ ምግቦች የተሰየሙ ናቸው። ◽️ Internet ለአንድ ቀን ቢዘጋ 196 ቢሊዮን ኢሜሎች ፣ 3 ቢሊዮን የጉግል ፍለጋዎች ፣ 12 ቢሊዮን የፌስቡክ እና የዩቲዩብ ቪዲዮ ዕይታዎች እና 500 ሚሊዮን ትዊቶች ሳይላኩ ይቀራሉ። =t.me/Benan_Tech

የኮምፒውተራችንን Hard Drive እንዴት በቀላሉ ፓርቲሽን(partition) መክፈል እንችላለን? 📍በመጀመሪያ ፓርቲሽን በመክፈላችን ምናገኛቸው ጥቅሞች ምንድናቸው ብለን ስናስብ እንደየ ፍላጎታችን ሚለያይ ሲሆን ለሁላችንም ሚሰጠን ዋናው ጥቅም ቢኖር ፉይላችንን ከ ሲስተም ፋይል ያሉ ፋይሉችንን ለይተን በማስቀመጥ በተላያዩ ምክንያት ቡት ማረግ ወይም ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን መነሳት ሲያቅተው ልናጣ ምንችለውን ፉይል ለመከላከል የምንጠቀምበት መንገድ ነው 📍ለምሳሌ ከፋብሪካው እንደመጣው በ C: partiton ብቻ እየተጠቀምን ቢሆንና በ ቫይረስ ምክንያት ሲስተም ፋይል ቢጠፋ ሌሎች ፐርሰናል ፉይሎችን አጣን ማለት ነው። 📍ስለዚህ በቀላሉ እዛው ፓርቲሽን በመፍጠር የግል ፉይል ለብቻ C: ፓርቲሽን ለብቻ አድርገን በመጠቀም ፋይላችንን መከላከል እንችላለን ይህን ካልን ስለ ፓርቲሽን እንዴት ዊንዶውስ ባዘጋጀልን disk managment በ መጠቀም እንዴት መስራት እንችላለን ሚለውን ላሳያችሁ ወደድኩ 📍በመጀመሪያ ባክአፕ መውሰድ አስፈላጊ ነው ምንም እንኳ ፕሮሰሱ ፋይል ባያጠፋብንም ለጥንቃቄ ሲባል ወስደን መጀመር አለብን 📍በመቀጠል ወደ my computer iconላይ ራይት ክሊክ አርገን manage ሚለውን ክለክ ስናደርግ አዲስ ዊንዶው ይከፈትልናል ማለት ነው። 📍በግራ ባለው ዝርዝር ውስጥ disk managment ሚል በመፈለግ ያንን እንከፍታለን በመቀጠልም በሚከፈተው ዊንዶው ውስጥ መሀል ላይ ሁኖ ከታች ባለው ቦታ ላይ 📍 ያልተከፈለው ፓርቲሽን በ ሰማያዊ ይታየናል ስለዚህም ማድረግ የፈለግነውን ፓርቲሽን ላይ ራይት ክሊክ በማድረግ በሚመጡት ዝርዝሮች ውስጥ shrink volume የሚል ን በመምረጥ በሚከፈትልን ዊንዶው መሰረት እንደምን ፈልገው ሳይዝ በማስገባት ሌላ አዲስ ፓርቲሽን እንፈጥራለን። ⚠️ ማሳሰቢያ የ disk size ስባስገባ ቁጥሩ በ Mega byte(MB) ነው የሚቀመጠው ስለዚህ ለምሳሌ 100 GB ማድረግ ከፈለግኩኝ 1024,000 ብየ ቁጥሩን ማስገባት አለብኝ ማለት ነው ወይም 200GB ማድረግ ብፈልግ 2048,000 ማለት አለብኝ። የ 1 GB ማለት 1024 MB ስለሆነ።⚠️ ይህንን finish ብለን ከጨረስን በኋላ የከፈትነው ፐርቲሽን እዛው disk managment ውስጥ በጥቁር ከለር ይታየናል ስለዚህ ይህንን ፓርቲሽን ላይ ራይት ክሊክ በማድረግ የጀመረነውን ፓርቲሽን መፍጠር ለመጨረስ እንጀምራለን። 📍ስለዚህ ራይት ክሊክ ስናደርግ new volume የሚለውን ስንነካ አዲስ ዊንዶ ይመጣል ስለዚህ ምንም ነገር ሳንነካ nextን ብቻ በመጫን መጨረሻም ላይ finish ን ስንጫን አዲሱ ፓርቲሽን my computer ውስጥ መታየት ይጀምራል ማለት ነው ። ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ እንደተለመደው በመጠየቅ አበረታቱን ስል እላለው አመሰግናለው።

📲የዚህ ወንድም አድራሻ ያላችሁ? https://t.me/AbuSufiyan_Albenan

በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ! ይሄኔ በዚህ ሰዓት የሆነ ሰው ስላንተ ስኬት እየፀለየልህ ነው ! ያ ሰው ቤተሰብህ አይደለም በአካልም አያውቅህም አታውቀውም ! ግን ደግሞ ድጋፍህ ያስፈልገዋል ያንተ አላማ መሳካት ለእርሱ ህይወት እጅግ በጣም ጥልቅ ተፅዕኖ አለው ህልምህን ስታሳካ አንተ ብቻ ሳትሆን ብዙ ሰዎች ይድኑበታል !