fa
Feedback
𝐁𝐞𝐧𝐚𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡𝐧𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲

𝐁𝐞𝐧𝐚𝐧 𝐓𝐞𝐜𝐡𝐧𝐨𝐥𝐨𝐠𝐲

رفتن به کانال در Telegram

💻የተማሩትን ማስተማር ያወቁትን ማሳወቅ ቅንነት ነው! ይህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ የምላቸውን ስለ ኮምፒውተር ትምህርቶች፤እንድሁም ከቴክኖሎጅ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እና እውቀቶችን የማካፍልበት ቻናሌ ነው! 📶ወንድማችሁ፦ሁሰይን አል-በናን(አቡ ሱፍያን)

نمایش بیشتر
1 696
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-4030 عوز

در حال بارگیری داده...

کانال‌های مشابه
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
دسامبر '24
دسامبر '24
+5
در 1 کانال‌ها
نوامبر '24
+9
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اڊتبع '24
+16
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '24
+62
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '24
+446
در 4 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '24
+9
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '24
+30
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '24
+158
در 3 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '24
+6
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مارس '24
+11
در 1 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '24
+33
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '24
+366
در 4 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '23
+3
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '23
+35
در 4 کانال‌ها
Get PRO
اڊتبع '23
+35
در 1 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '23
+29
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '23
+372
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '23
+87
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '23
+22
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '23
+35
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '23
+46
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '23
+44
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '23
+43
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '23
+69
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '22
+90
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '22
+144
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اڊتبع '22
+131
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '22
+169
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '22
+113
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '22
+60
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '22
+88
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '22
+95
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '22
+57
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '22
+99
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '22
+67
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '22
+67
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '21
+59
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '21
+46
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اڊتبع '21
+233
در 0 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشاعات
کانال‌ها
14 دسامبر0
13 دسامبر0
12 دسامبر+1
11 دسامبر0
10 دسامبر0
09 دسامبر+2
08 دسامبر0
07 دسامبر0
06 دسامبر0
05 دسامبر0
04 دسامبر+2
03 دسامبر0
02 دسامبر0
01 دسامبر0
پست‌های کانال
ስልክ ስንገዛ መጀመሪያ ማየት ያለብን ምንድነው!? ―መልሱ Processor ሲሆን፦ የስልክ Processor  ልክ እንደ ሰዉ አእምሮ  አድርጋቹ ማሰብ ትችላላችሁ።ስልኩ ላይ የምታደርጉት ማንኛውም ነገር የሚከናወነው በዚህ Processor አማካኝነት ነዉ። የተወሰኑትን እንመልከት :- ① Camera አንድ ስልክ አሪፍ Camera እንዲኖረዉ ከሚጠቀመዉ የ Camera Sensor በተጨማሪ ጥሩ Processor ሊኖረዉ ይገባል ይሄም የምታነሱት Photo እና የምትቀርፁት Video የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ያስችላል። ለምሳሌም:- -Low-light Performance -Faster Autofocus and Shutter Speed -Higher Resolution and Frame Rates -Video Stabilization -AI Features እነዚህ እና መሰል ነገሮችን በብቃት እንዲያከናውን ያስችላል። ② Battery አንድ ስልክ አሪፍ የሆነ የ Battery አጠቃቀም እንዲኖረው ጥሩ Processor ሊኖረዉ ይገባል ለምሳሌ ሁለት የተለያዩ ስልኮች ሁለቱም 5000mAh Battery Size ቢኖራቸውም Battery የሚጨርሱበት ፍጥነት ግን ሊለያይ ይችላል ይሄም የሚሆነው በ Processor የ Battery አጠቃቀም ነዉ። ጥሩ Processor ካለዉ ስልኩ ላይ ትልቅ ስራዎችን በምትሰሩ ሰአት ለምሳሌ Gaming ,multitasking ,እና መሰል ነገሮች ስታከናዉኑ የስልኩን Performance እና Battery አጠቃቀም Balance በማድረግ ሀይል እንዲቆጥብ ያስችለዋል። ③ Performance ሌላኛው Performance ሲሆን ይሄ በጣም ግልጽ የሆነ ነገር ነዉ ስልኩ ፈጣን እና የምታዙትን ነገሮችን በፍጥነት እንዲያከናውን ያለዉ Processor ቀልጣፋ መሆን ይኖሮበታል። Note! ስልክ ከመግዛታቹ በፊት መጀመሪያ እናንተ ምን አይነት የስልክ ተጠቃሚ እንደሆናቹ ማወቅ እና የምትገዙ ስልክ ከናንተ አጠቃቀም ጋር የሚሄድ መሆኑን ማወቅ አለባቹ። =t.me/Benan_Tech

2
ስልክ ስትገዙ መጀመሪያ ማየት ያለባቹ ምኑን ነዉ?
798
3
የ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ይፋ አድርጓል። ከላይ በጠቀስኩላችሁ አድራሻዎችም ከከፈት መልካም ነው። ሌላ ውጤት የምታዩበትንም መንገድ ይፋ ካደረገ ተከታተይ የማሳውቃችሁ ይሆናል።
1 169
4
ዛሬ ውጤት የምትጠብቁ የ12ኛ ክፍል የቻናላችን ቤተሰቦች አላችሁ!? በዚህ አጋጣሚ መልካም ዕድል ተመኝተናል። ነገር ግን ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በፀጋ ተቀብላችሁ በአዲስ አመት የወደፊት ህይወታችሁን አቅዳችሁ እንድትንቀሳቀሱ እንመክራለን። ጥሩ ውጤት ብታመጡ ደስ ይላል ግን ባታመጡም ህይወታችሁ እሱ ብቻ ነው ማለት አይደለም። ከጠነከራችሁ በዚህ ዘመን እራሳችሁን ልትለውጡባቸው የምትችሉባቸው በጣም ብዙ የስራ ዘርፎች አሉ። እድሜ ለቴክኖሎጂ!!! ስለዚህ አለፍን ብላችሁ ብዙ አትደሰቱ ዋናው ልፋት ገና ነው።  አላለፍንም ብላችሁም ብዙ አትከፋ ብዙ ዕድል ስላላችሁ። ስሜታችሁን በልክ አድርጉት። መልካም ዕድል!
1 343
5
• የ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ዛሬ ጳጉሜን 4 ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይታሰባል…ውጤቱ ይፋ ከተደረገ በነዚህ አድራሻዎች ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ፦ 1. በዌብሳይት https://result.eaes.et 2. በ6284 - SMS 3. በቴሌግራም - @eaesbot መልካም ዕድል! =t.me/Benan_Tech
1 541
6
🎖የኮምፒውተር ሶፍትዌር ለማውረድ የሚጠቅሙ ምርጥ ድረገጾች፥ 1. getintopc.com ይህ ድረገጽ ትላልቅ ሳይዝ ያላቸውን ሶፍትዌሮች ለማውረድ ተመራጭ ነው። ለምሳሌ ያህል driver pack(11GB size) ከዚህ ድረገጽ ማውረድ ይቻላል። በተጨማሪም ዊንዶውስ 10,8.1,8,7, እና ማይክሮሶፍት ኦፊስ ማውረድ ይቻላል። 2. oceanofgames.com 3. filehippo.com 4. cnet.com 5. softonic.com 6. download.com 7. softpedia.com 8. Tucows.com 9. freewareFiles.com 10. majorGreeks.com 11. snapfiles.com 12. filecluster.com 13. geardownload.com 14. soft32.com 15. softonic.com 16. freewarehome.com 17. freedownloadcenter.com 18. opensourcemac.org 19. lo4d.co 20. fileEagle.com 21. P30download.com
1 478
7
❖አንዳንድ የኮምፒውተር #ክፍሎች ማብራሪያ ❶. #RAM (Random Access Memory) ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል:: (1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB  በላይ ራም ይኖራቸዋል:: ❷. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot) ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን:: ❸. #Heat_sinker ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም #Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል:: ❹.#Fan ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው:: ❺ #CPU #CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን:: #CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው:: ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው:: #CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም : ▫️1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው:: : ▫️2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል:: : ▫️3. #Regster ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው:: ይሂም #Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው:: ❻ #Port (ፓርት) : port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው:: መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ:: የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ #ኤሌክትሪክ #ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው:: ❼ #Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል) power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው:: የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል:: ❽#ሞደም (Modem):- ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው:: : ❾#ኪቦርድ Keybord:- መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት ቁጥሮች ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን:: =t.me/Benan_Tech ❯❯
1 282
8
~በነገራችን ላይ…እንግሊዘኛ ቋንቋ መማር በዛሬው ዓለም ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ይህን እንድትረዱ ጥቂት ምክንያቶችን ልጠቅስላችሁ፡ ① ዓለም አቀፍ ቋንቋ፦ እንግሊዘኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ቋንቋ ነው። በንግድ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት እና በመዝናኛ ዘርፎች ሁሉ እንግሊዘኛ በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል። ② የሥራ እድል፦ እንግሊዘኛን መቆጣጠር የሥራ ገበያ ላይ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣችኋል። በብዙ ድርጅቶች ውስጥ እንግሊዘኛን መናገር መቻል የሥራ መስፈርት ነው። ③ ትምህርት፦ አብዛኛው የዓለም አቀፍ ትምህርት በእንግሊዘኛ ይሰጣል። በውጭ አገር ለመማር ወይም በዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ለመመዝገብ እንግሊዘኛን በደንብ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ④ መረጃ መድረስ፦በኢንተርኔት ላይ ያለው መረጃ አብዛኛው በእንግሊዘኛ ነው። እንግሊዘኛን መቆጣጠር ማለት በዓለም ላይ ካለው መረጃ ሁሉ ጋር በቀላሉ መገናኘት ማለት ነው። ⑤ ጉዞ እና ቱሪዝም፦በውጭ አገር በሚጓዙበት ጊዜ እንግሊዘኛን መናገር መቻል በጣም ጠቃሚ ነው። በብዙ አገሮች ውስጥ እንግሊዘኛ ሁለተኛ ቋንቋ ነው። ⑥ ግንኙነት፦እንግሊዘኛን መቆጣጠር ከተለያዩ አገሮች ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነት እንድትፈጥሩ ያስችላችኃል። በአጭሩ፣ እንግሊዘኛን መማር በዛሬው ዓለም ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው። በአላህ ፍቃድ ይህ ቋንቋ የእናንተን የሥራ እድል፣ የትምህርት እድል እና የግል እድገት ያሻሽላል። ✏️[ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን] =t.me/Benan_Tech
7 637
9
Telegram update!! ከዚህ በፊት telegram channel ላይ አድሚኖች post ሲያደርጉ ስማቸውን ብቻ ነበር የምናየው። በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት አንድ admin channel ላይ po
Telegram update!! ከዚህ በፊት telegram channel ላይ አድሚኖች post ሲያደርጉ ስማቸውን ብቻ ነበር የምናየው። በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት አንድ admin channel ላይ post ሲያደርግ ስሙ እና profile picture እንዲታይ ማድረግ የሚቻልበት feature telegram አስተዋውቋል። ይህ feature group ላይ ካለው chat system ጋር ይቀራረባል። በተጨማሪም አድሚኖች በራሳቸው profile ምትክ የቻናላቸውን profile መጠም ይችላሉ። ይህንን feature enable ለማድረግ Channel Settings ላይ በመግባት Administrators > Sign Messages እና Show Authors Profiles የሚሉትን ሁለቱንም on ማድረግ አንድ update እንጨምርላችሁ ይህኛው feature star subscription ሲሰኝ content creators special invite ፈጥረው ገንዘብ በየወሩ የሚያገኙበት feature ነው። Private invitation link ሲሆን ወደ private channel ለመግባት የቻናሉ ባለቤት ያስቀመጠልንን star ከፍለን የምንገባበት link ነው። ወደ channel ለመግባት star ከከፈልን አድሚኑ approve ሳያረገን በራሱ ያስገባናል። እንደዚህ አይነት ሊንክ ለመፍጠር በተመሳሳይ ወደ Channel Settings በመሄድ  > Channel Type > Manage Invite Links > Create a New Link በስተመጨረሻም Require Monthly Fee የሚለውን enable በማድረግ የምትፈልጉትን star መጠን ማስገባት። = t.me/Benan_Tech
1 575
10
Telegram update!! ከዚህ በፊት telegram channel ላይ አድሚኖች post ሲያደርጉ ስማቸውን ብቻ ነበር የምናየው። በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት አንድ admin channel ላይ post ሲያደርግ ስሙ እና profile picture እንዲታይ ማድረግ የሚቻልበት feature telegram አስተዋውቋል። ይህ feature group ላይ ካለው chat system ጋር ይቀራረባል። በተጨማሪም አድሚኖች በራሳቸው profile ምትክ የቻናላቸውን profile መጠም ይችላሉ። ይህንን feature enable ለማድረግ Channel Settings ላይ በመግባት Administrators > Sign Messages እና Show Authors Profiles የሚሉትን ሁለቱንም on ማድረግ አንድ update እንጨምርላችሁ ይህኛው feature star subscription ሲሰኝ content creators special invite ፈጥረው ገንዘብ በየወሩ የሚያገኙበት feature ነው። Private invitation link ሲሆን ወደ private channel ለመግባት የቻናሉ ባለቤት ያስቀመጠልንን star ከፍለን የምንገባበት link ነው። ወደ channel ለመግባት star ከከፈልን አድሚኑ approve ሳያረገን በራሱ ያስገባናል። እንደዚህ አይነት ሊንክ ለመፍጠር በተመሳሳይ ወደ Channel Settings በመሄድ  > Channel Type > Manage Invite Links > Create a New Link በስተመጨረሻም Require Monthly Fee የሚለውን enable በማድረግ የምትፈልጉትን star መጠን ማስገባት።
1
11
በስንት ልፋት የሰራችሁትን የMicrosoft Word ዶክመንታችሁን ማንም ሰው edit እንዳያደርገው በpassword መቆለፍ ከፈለጋችሁ። ▪️1. ዶክመንታችሁን ከከፈታችሁ በኋላ review የሚለውን t
በስንት ልፋት የሰራችሁትን የMicrosoft Word ዶክመንታችሁን ማንም ሰው edit እንዳያደርገው በpassword መቆለፍ ከፈለጋችሁ። ▪️1. ዶክመንታችሁን ከከፈታችሁ በኋላ review የሚለውን tab ክፈቱ። ▪️2. restrict editing የሚል option ይመጣላችኋል  እሱን ክፈቱ። ▪️3. በግራ በኩል formatting restriction እና Editing restrictions የሚሉትን ቼክ ቦክሶች check አድርጉ። ▪️4. start Enforcing Protection የሚለውን ትመርጣላችሁ። ▪️5. መጨረሻ ላይ የምትፈልጉትን password አስገብታችሁ ok ብላችሁ ትጨርሳላችሁ። save ካደረጋችሁት በኋላ ዶክመንቱን ለማንም ሰው ብትልኩ password ካላስገባ በስተቀር edit ማድረግ አይችልም። =t.me/Benan_Tech
2 020
12
በነፃ ምርጥ ምርጥ ሎጎዎችን የምትሰሩበት ዌብ ሳይት ነው! https://www.zarla.com/free-logo-maker
2 049
13
Restore point (system restore) ምንድን ነው? ጥቅሙስ? Restore point ማለት በዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ችግሮች ሲያጋጥሙ ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ የሚያስችል ፊቸር ነው። እነዚህ ችግሮች የsettingና የconfiguration መፋለስ ወይም በቫይረስ መጠቃት ሊሆኑ ይችላሉ። ኮምፒውተራችን ላይ restore point የሚፈጠርባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። የመጀመርያው የተለያዩ ሶፍትዌሮችን ስንጭን ኮምፒውተሩ በራሱ የሚፈጥረው ሲሆን ሌላው ደግሞ እኛ በራሳችን የምንፈጥረው ነው። በwindows 10 ላይ እንዴት መፍጠር እንደምንችል ላሳያችሁ። ✔️"Windows + E" ነክተን "This PC" የሚለው ጋ right click እናደርጋለን። ✔️ከዛ " properties" የሚለውን እንከፍታለን። ✔️በግራ በኩል "System protection" የሚለውን እንከፍታለን። ✔️የኮምፒውተራችን ድራይቮች ተዘርዝረው እናገኛለን ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ የተጫነበትን እንመርጥና(usually C: drive) create እንለዋለን። ✔️ገላጭ የሆነ ስም ከሰጠነው በኋላ create እናደርጋለን። አሁን በትክክል restore point ፈጥረናል ማለት ነው። ከላይ እንደተነጋገርነው restore point መፍጠር ብዙ ጥቅሞች አሉት። ⚫ጤነኛ የነበረ ኮምፒውተራችን ከጊዜ በኋላ በቫይረስ ቢጠቃ ቀድሞ ወደነበረበት የጤነኝነት ሁኔታ መመለስ ያስችለናል። ⚫የኮምፒተራችን ሲስተም ፋይሎች፣ setting እና configuration ላይ ብልሽት ወይም አላስፈላጊ ለውጥ ካለ በትክክል እየሰራ ወደነበረበት የቀድሞ ሁኔታ እንዲመልስ ያስችላል። ⚫የdriver ወይም የoprating system ብልሽት ቢያጋጥም አዲስ driver ወይም OS መጫን ሳያስፈልግ ወደቀድሞ ሁኔታው መመለስ ያስችለናል።
1 379
14
📃ጥናታዊ ጽሑፍ ለምታዘጋጁ ተመራቂ ተማሪዎች ስለምትሠሩት Proposal እና Research ትንሽ እገዛ! ~በመጀመሪያ ደረጃ የሚመርጡት የጥናት ርዕስ መነሻውና መድረሻውን ሥነ-ፍኖት በትክክል የተረዱትን መሆን ይገባዋል። ጥናታዊ ጽሑፍ መጨረሻ መታወቅ ያለበት ውጤቱ ነው እንጂ ሂደቱ መሆን የለበትም። ህደቱን ገና ከመጀመሪያው በትክክል እና በግልጽ (Accurately and clearly) መረዳትና ማወቅ ለውጤታማነት ተገቢ ነው። የጥናቱ ንድፈ ሀሳብ (Proposal) በሚገባ የሚመራ መንገድ መሆን አለበት። ጥናትን በተመለከተ ምሁራኑ የሚሉትን አንድ ታላቅ ገለፃ ላስታውሳችሁ "A research is as good as its propsal" -(የአንድ ጥናት ጥሩነት እንደ ንድፈ ሀሳቡ/ዕቅዱ/ ጥሩነት ይታወቃል) እንደማለት ነው። በመሆኑም የተወሰነ ምክረ ሃሳብ እገዛ ለማድረግ ጥቂት ነገር ላስታውሳችሁ። ልብ ሊባል የሚገባው ግን የግል ድጋፍ እንጂ የተቋም ይፋዊ format እያሳወቅሁ አለመሆኑን ነው። ✅ 1ኛ. Title፦ ርዕስ ለመመረጥ የመጀመሪያው ትኩረት ከሙያዎት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ያስተውሉ። ከዚህ ባለፈ ሙያዎትን ተጠቅመው በአካባቢዎ ባለው ማህበረስብ ውስጥ ያለውን ችግር በመፍታት አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉበት ቢሆን ይመረጣል። ከዚህ አንጻር "ይህንን አይነት መፍትሔ ብሠራለትስ" የሚሉትን ችግር መርጠው አጭር እና ገላጭ የሆነ የጥናት ርዕስ መምረጥ ነው። ከተቋሙ አካባቢ ወጣ ያሉ ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ርዕሶች መሆንም ይችላሉ። ✅ 2ኛ. Introduction_to_your_title ፦ በዚህ ርዕስ ሥር ስለ ጥናቱ ርዕስ ምንነት ገለጻ ማድረግ ነው። በዚህ ርዕስ ሥር የሚያካትቷቸው ይዘቶች defnitions, theories, materials used, tests, methods, constructions systems, types, ..... የመሳሰሉት ቢሆኑ መልካም ነው። ✅ 3ኛ. Background_to_your_title ፦ ይህ ደግሞ ስለሚያጠኑት ጥናት ታሪካዊ ዳራ/አመጣጥ (hisorical status) ገለጻ ማድረግ ነው። [who start investigate first, which country use, improvement (ማን ጀመርው? የት ቦታ? መቼ? በምን ተጀምሮ ወዴት ተሻሻለ all improvements፣ አሁን የት ደረሰ፣ .....) የሚሉትን የርዕሳችሁን ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስካለበት ድረስ ብቻ የምታስቀምጡበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ እርስዎ ሊጨምሩበት ወይም ሊቀይሩት ወይም ሊያስተካክሉት የሚችሉበትንም ጎን ጠቆም ማድረፍ መልካም ነው። ✅ 4ኛ. Statement_of_the_problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው። ✅ 5ኛ. Objectives {General and Specific}፦ ጠቅላይ/ዋና ዓላማ ከአንድ ዓረፍተ ነገር ባይበልጥ ከበዛ ደግሞ ከሁለት በላይ እንዳይሆንይመከራል። በዝርዝር ዓላማ (specific objectives) የሚቀመጡት ደግሞ በዋና ዓላማ ዉስጥ የሚገኙ በጥናቱ መከናወን የሚታወቁ የተለያዩ መልሶችን ታስቀምጣላችሁ። ✅ 6ኛ. Scope_of_the_Research፦ ይህ የሚገልጸው የጥናትችሁን ስፋተ-ሜዳ ነው። ምን ምን እንደሚያጠቃልል ወይም እንደሚዳስስ፣ ምን ምንን ደግሞ እንደሚተው /እንደማያጠቃልል/ ከነምክንያቱ፣ ለምን አይነት ተግባር የሚውል እንደሆነ ... በአጠቃላይ የጥናቱን መጠነ-ስፋት ወይም ይዘት የሚያስረዳ ይሆናል። ✅ 7ኛ.Litrature_review ፦ [በርዕሱ ዙሪያ እስካሁን የተጠኑ ጽሁፎች ምን ብለዋል?] “ማን የተባለው ሰው በየትኛው መጽሐፉ/ጥናቱ የትኛው ገጽ ላይ ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ምን ብሏል?“ የሚለውን መረጃ የያዘ ነው። በ"Litrature" ሥር የሚያካትቱት የቀደሙ ህትመቶች ማስረጃ ከእርስዎ ጥናት ጋር ተያያዥ ሀሳብ ያላቸውን ብቻ ነው። እርስዎ የማይዳሡትን ነገር በዚህ ርዕስ ሥር ማስገባት ከማንዛዛት እና ትርጉም አልባነት አያልፍም፣ ይልቁንም ሥራዎትን ውጤት (value) እና ተቀባይነት (acceptance) ሊያሳጣ ይችላል። በዚህ ሥር የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች reference specification [books, quastionary, journals, published apers, recorded interviews, vedio evidences] መሆን አለባቸው እንጂ guide specification [oral speeking, internet notes, handouts, non published documents] ላይ ያገኙትን ነገር ባይጠቀሙ ይመከራል። የተጠቀሙትን ምንጭም ከነመገኛ ገፁ አብረው ዋቢ ማስቀመጥም ተገቢ እና ግዴታ ነው። ✅ 8ኛ.METHODOLOGY፦ ይህ ደግሞ ዋናው የጥናት ሂደት መረብ ነው። ትናቱ የሚከናወንበት አካባቢ (study area)፣ ናሙና የሚወሰድበት የናሙና አወሳሰው ሥነዘዴ - ሥነዘዴው የተመረጠበትን ማስረጃ ምክንያት ጨምሮ (sampling system)፣ ከንድፈ ሀሳብ እስከ ፍጻሜ ያለውን የሚያሳይ የጥናቱ መነሻና መድረሻ ፍሰት (research deign - ብዙ ጊዜ በ"Chart" ሊገለፅ ይችላል) መካተት አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪ ቤተሙከራዊ ጥናት (Experimental research) ከሆነ የተለያዩ የቤተሙከራ ፍተናዎች (laboratory tests) የሚሠሩበት ስለሆነ የሚሰሩት ሙከራዎች (tests) የሚያስፈልጉ መሥሪያ ነገሪች (materials), መሥሪያ መሳሪያዎች (equipments), የሙከራ ሂደቶች (procedures to be used) የሚሉት ይዘቶች በግልፅ መታወቅ አለባቸው። ከቤተሙከራ ውጪ ከሆነ ደግሞ አንዳንዶቹ ተግባራዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፍልስፍናዎች ስለሆኑ የሚጠቀሙትን ሂደት ማስቀመጥ ተአቢ ነው። (ምሳሌ ~ መኪና መሥራት፣ በፀሀይ ጉልበት የሚሰራ ባቡር መሥራት ሊሆን ይችላል)። በሌላ በኩል Theoretical or statistical data analaysis ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች ከሆኑ ደግሞ የሚጠቀሟቸው የቃለመጠይቅ ጥያቄዎች (interiview questions)፣ የሚያስሞሉት የሰነድ ጥያቄ (questionair formats for data statistics)፣ የሚጠቀሟቸው የኮምፒዉተር ፕሮግራም (softwares to be used)፣ የሚፈልጉት ስታቲካዊ መረጃ (statistic data)፣ የሚሳተፉት ባለድርሳዎች (participants /responsible bodies)፣ የጥናት ማመዛዘኛ መንገድ (analaysis statics method..) የመሳሰሉትን ማካተት ተገቢ ሲሆን ይህ "Methodology" የሚባለው ክፍል አንድ ሰው በየትኛው ሥነዘዴ እንደሠራ የክንውን ሂደቱን የሚያስቀምጥበት ክፍል ነው። 🛑 NB፦ እነዚህ ከላይ ያሉት በሙሉ በንድፈ ሀሳብ ሰነድ (proposal document) ላይ ጭምር መስፈር ያለባቸው ናቸው። ይቀጥላል… ✏️―አቡ ሱፍያን― =t.me/Benan_Tech
602
15
ቴሌግራምና ዋትሳፕ ላይ ለሰዎች message መላክ ስንፈልግ ስልክ ቁጥራቸውን የግድ save ማድረግ ይኖርብናል። ይህም የስልክ ኮንታክታችን በማንፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ይሞላል። ይህን አፕሊኬሽን በመጠቀም ግን በቀላሉ ቁጥራቸውን save ማድረግ ሳይጠበቅብን message መላክ እንችላለን።
7 205
16
Video compressor pro እጅግ በጣም ቀላል Video ሳይዝ መቀነሻ አፕ ነው ። (Without losing quality) ● Premium is activated
761
17
Telegram hack‼ ቴሌግራማችሁን ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level • ማንኛውንም link ነክታችሁ Telegram login አድርጉ ቢላችሁ በፍፁም Login እንዳታደርጉ። • Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ። ይህን ለማስተካካል Settings - privacy and security - passcode • 2-step verification ተጠቀሙ። 2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው። Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት። ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ። • ከ2 በላይ device ላይ አትጠቀሙ። Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል። ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate sessions እያላችሁ ቀንሷቸው። • በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ። • ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ። • የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ። • ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው ካያቸው በኋላ የሚጠፉ) ሚሴጆችን ላኩ። • የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት። • በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ። Phone number - Nobody Last seen & online - My contacts Profile photos - My contacts Forwarded message - Nobody Calls - My contacts Group & channels - My contacts Hack የተደረገ account እንዴት እንደምናስመልስ በቀጣይ እናያለን። =t.me/Benan_Tech
910
18
Delete የተደረገ message እንዴት ማንበብ እንችላለን? Telegram፣ WhatsAppና 🌐Facebook Messenger ላይ ሰዎች ሚሴጅ ፅፈውላችሁ እናንተ ሳታዮት delete ቢያደርጉት እንዴ
Delete የተደረገ message እንዴት ማንበብ እንችላለን? Telegram፣ WhatsAppና 🌐Facebook Messenger ላይ ሰዎች ሚሴጅ ፅፈውላችሁ እናንተ ሳታዮት delete ቢያደርጉት እንዴት ማንበብ እንደምትችሉ ላሳያችሁ። ስልካችሁ Samsung ከሆነ • የስልካችሁ Settings ላይ ትገቡና Notifications የሚለውን ምረጡ። • Advanced settings የሚል አማራጭ ውስጥ Notification history የሚለውን on አድርጉት። በዚህ መሰረት ካስተካከላችሁት በኋላ ማንም ሰዉ message ፅፎላችሁ ካጠፋው እዚህ notification history ውስጥ ገብታችሁ ታገኙታላችሁ።
1 043
19
💻ላፕቶፕ ሲገዙ ማገናዘብ ያለብዎ አስፈላጊ ነገሮች⤵ ①.ምን ሊሰሩበት አስበዋል? ብዙ ሚፅፉ ከሆነ ኪቦርዱን ማየት ይገባል ጌም ሚያበዙ ከሆነ ግራፊክስ ካርዱንና ስፒከሩን ይመልከቱ። • ለቪዲዮ ቅንብር (editing or software Engineering) ከሆነ ከፍተኛ የፕሮሰሰር አቅም፣ትልቅ ሳይዝ ራም high definition (HD) ስክሪንመኖሩን ያረጋግጡ። ② አዲስ ከካምፓኒው እንደመጣ ( brand new ) ነውወይም በብልሽት ምክንያት ተመልሶ ካምፓኒው ገብቶ የተሰራ (Refurbished ) መሆኑን ያረጋግጡ። ③ የስክሪን ወይም የዲስፕለይ መጠን ለርሶዎ ትክክለኛዉን የስክሪን መጠን ይምረጡ (13.3” ,15.6”,17.3”) ④ ላፕቶፑን ስፔሲፊኬሽን በጥልቀት ይመርምሩ ፕሮሰሰር (intel core 2 dou, core i3, core i5, core i7 or AMD and others) • ራም (ስንት እንደሆነ 1GB,2GB,3GB,4GB , 8G and above) • ሀርድ ዲስክ (160 GB, 250GB, 320GB,500GB, 750GB and above) • ዲቪዲ ወይም ብሉሬይ ድራይቭ ( re-writable ) ⑤ የባትሪ ጉዳይም በጣም ወሳኝ ነው ። ሊደራደሩበትአይገባም! ቢያንስ 3 ሰአት እና ከዛ በላይ ቢሆን አሪፍ ነው። ⑥ የሚፈልጉት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይምረጡ: ማክሮሶት ዊንዶውስ (windows 7, windows8,windows10, windows11) , mac, Ubuntu,Linux…ዊንዶውስ 10 ወይም windows 11 ቢመርጡ ይመከራል! =t.me/Benan_Tech
956
20
💻ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው። ይህን ቻናል Join በማድረግ ምርጥ ምርጥ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን በቀላል አቀራረብ ያገኛሉ።
💻ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው። ይህን ቻናል Join በማድረግ ምርጥ ምርጥ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን በቀላል አቀራረብ ያገኛሉ።
808