Arganon type• *¨*••*¨*•.🖌
رفتن به کانال در Telegram
ንግግሮቻችን የስብዕናዎቻችን መለኪያዎች ናቸው ፥ በመልካምነት የሚለኩ ፥ በጥሩነት የሚዳኙ ቃሎችን እንናገራለን ። 👉👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👉Contact... @Arganon12 👈 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
نمایش بیشتر1 458
مشترکین
-324 ساعت
-127 روز
-3130 روز
آرشیو پست ها
እኛ የዛሬ ትጋታችን ነገ ከነገ_ወዲያ ደስታና ስኬት ሆኖ እንደምናገኘው የምናምን ሰዎች ነን ፥ ይብዛም ይነስም አሁን ላይ ያሉ የመኖር ትግሎቻችን ህይወት ላይ ተስፋ እንዳለን ማሳያዎች ናቸው ።
ከጥረቶቻችን ጋር እንቆይ ፥ የተስፋዎቻችን ክፍያዎችም ይመጣሉ
እነሱ ንግግሮቻቸውን ማደራጃት የሚችሉት ፥ አንደበቶቻቸው ከቁጥጥራቸው የማይወጡባቸው ሰዎች ፥ በቅንነትም እንበለው በሞኝነት ከአንደበቶቻችን አፈትልከው በወጡ ቃሎቻችን ከምንጸጸትና ከምንቆጭ ሰዎች የተሻለ የተረጋጋ ህይወት አላቸው ።
ደኝነቶችና ፍርዶች በንግግሮቻቹህ ዙሪ የሚሆኑበት ጊዜ ስለሚበዛ የምትከበሩበትን ቃል ምረጡ ።🤗@Arganon_type @Arganon_type
"አንድ ጊዜ ምን ሆነ መሰላችሁ? ሀገራችን ላይ ዝናብ ጠፋና የድርቅ ወሬ እዚህም እዚያም ሆነ፡፡ ሙስሊሙም በመስጅዱ፤ ከርስቲያኑም በመቅደሱ ወደ ፈጣሪ ሊጮህ በነቂስ ወጣ። አንድ አባወራ ሕፃን ልጁን ና ወደ መስጅድ እንውጣ ፥ ሙስሊም ከርስቲያኑ ሁሉ ተሰብስበን ዝናብ እንዲሰጠን ወደ እላህ ልንፀልይ ነው::" ይልና የሕፃኑን እጅ ይዞ ከቤት ይወጣል። ገና ደጃፉን እንደተራመዱ ህጻን ልጅ ቆይ ፥ ቆይአባዬ መጣሁ ይልና እየሮጠ ወደ ቤት ይመለሳል፡፡ ወደ መስጅድ ለመሄድ የተቻኮለው አባት ምን ፈልጎ ነው?” እያለ በር በሩን ያያል፡፡ ሕፃኑ አፍታም ሳይቆይ እየሮጠ ይመለስና “ዣንጥላ ረስተን ልንሄድ ነበር::* አለው በእጁ የያዘውን ዣንጥላ እያመለከተው:: የዚያ ሕፃን ልጅ ቀልብ ከሁሉም የተሻለ መሆኑን ተመልከቱ እንግዲህ፡ አላህን ተሰባስበን ዝናብ ከጠየቅነውማ ዝናቡ በእርግጥም ይዘንባል ብሎ የሚጠለሉበትን ዣንጥላ ይዞ ወጣ፡፡
ከአለማየሁ ደመቀ ዮቶር(ኮብላይ ካህን) ከሚለው መጽሀፍ ከገጽ 55_56 የተወሰደ
“ፍቅረኛዬ እጅጉን ውብ ነበረች፡፡" ብሎ ጀመረ ወጣቱ፡፡ “ዓይኖቿ ከተፈጠረችበት ዕለት ጀምሮ ማየት አይችሉም ነበር፡፡ ዓይነ ስውር በመሆኗ ሳቢያ ብቻ ራሷን ጨምሮ፣ ሁሉንም ሰው ትጠላ ነበር፡፡ ለእሷ የነበረኝን ፍቅር መግለፅ ይከብደኛል፡፡ እሷም ብትሆን በማንኛውም ሁኔታ ሁሌም ከጎኗ የማልለየው እኔ ብቻ ነበርኩና ትወደኝ ነበር፡፡
“ዓለምን በዓይኖቼ ማየት ብችል አገባህ ነበር' ትለኛለች ደጋግማ፡፡አንድቀን ጥንድ ዓይኖች ተለገሷት፡፡እኔን ጨምሮ የጓጓችለትን ብርሃን ማየት ቻለች፡፡ 'የኔ ውድ፣ አሁን ዓለምን ማየት ችለሻል፡፡ እንደ ቃልሽ እንጋባ፡፡' ብዬ ጠየቅኳት፡፡ ያኔ ግን በድንጋጤ ተንቀጠቀጠች፡፡ እኔ ፍቅረኛዋም ዓይነ ስውር መሆኔን ስታይ ከፉኛ ተንቀጠቀጠች፡፡ እንኳን ልታገባኝ አብራኝ መሆን እንኳ እንደማትፈልግ አረዳችኝ፡፡
“ፍፁም ያልጠበቅኩት ነገር ነበርና የምገባበት እስካጣ ድረስ ደነገጥኩኝ፡፡ ግን ምን ማድረግ እችል ነበር? በዕንባዬ እየታጠብኩ ሄድኩ፣ ራቅኳት፡፡ ከቀናት በኋላ ጥቂት ቃላት የያዘ ደብዳቤ ላኩላት፡፡ 'ውዴ፣ ዓይኖቼን
አደራ ተንከባከቢልኝ፡፡' የሚል ደብዳቤ፡፡ የዚያኑ እለት ያን እምነት የጣልኩበትን ዓለም ትቼ ሩቅ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡
"
እንግዲህ ሁኔታዎች ሲለወጡ የሰው ልጅ አዕምሮም አንዲህ አብሮ ይለወጣል፡፡ አየህ የሰው ልጆች ስንባል እንዲህ ነን፡፡ ጥቂት የታደሉ ሰዎች ብቻ ናቸው በእነዚያ እጅጉን በከፉ የጨለማና የስቃይ ዘመናት ውስጥ ሁሌም ከጎናቸው ያልተለዩ ሰዎችን የማይረሱ፡፡”ብሎ የፍቅር ገጠመኙን በአጭሩ አጫወተን፡፡
ከአለማየሁ ደመቀ ዮቶር(ኮብላይ ካህን) ከሚለው መጽሀፍ ከገጽ 48_49 የተወሰደ@Arganon_type @Arganon_type
ማደር መክረማቸውን የማያውቁ ቅን ልቦች ፥
ነገ ከነገ በስቲያ ፍሬ አፍርተው እንደሚያገኟቸው ለተማመኑባቸው ሳቅና ደስታ
ዛሬያቸውን ለመታገል አይሰንፉም ።@Arganon_type @Arganon_type
በጊዜ ሒደት ቀናት ፥ ሳምንታት ፥ ወራትና አመታት እራሳቸውን ያድሳሉ ፥
እኛ ሰዎች በአንዳንድ ነገሮች ላይ የጸና ሀሳብና ውሳኔ እናሳልፍና ከጊዜ ጋር የማንታደስ አይነት እንመስላለን ፥
ግን አንዳንዴ ከጊዜ እኩል ተለውጠን ከተውነውም ከረሳነውም ጉዳይ ላይ መገኘት ያለ ነገር ነው ፥ መሸነፍም ዝቅ ማለትም ሊሰማን አይገባም ።
@Arganon_type
@Arganon_type
https://t.me/spell_wallet_bot/wallet?startapp=r-spell1k38jj79a9jfe2ydhfrxxh3ptz5ynuhakkjeqpr__utm-friendsTabRef
Join me in Spell Wallet! Claim Mana and unlock access to upcoming crypto airdrops!
መጥቀሙን ባላውቅም የተናገርኩት ቃል
ክፋት ግን የለውም ማለቴ ቀን ያውቃል
ተስፋ ያዙ ማለት በከንቱ አትድከሙ
ነገ ቀናቹህ ነው ባይሆንም ትርጉሙ
ነገ ይሻል እንደው ምን አልባት ከዛሬ
ስተት ግን የለውም ከዚህ ንግግሬ ።
ቀን ያውቃል ለራሱ ነገም ነገን ያውቃል
ፈጥሬ አላልኩትም እንዲህ አይነቱን ቃል ።
ስለነገ አትጨነቁ ለነገ ክፋቱ ይበቃዋል ። ነገ ለራሱ ይጨነቃል
ቢመሽም ቀኑ ቢጨልም ለብርሃን እጅ አልሰጥ ቢልም ጊዜ ቡዙ ያረጋል ቻል አርገው ይነጋል . . . ቻል ሆድህን አስፋ ተው አትቁረጥ ተስፋ !!@Arganon_type @Arganon_type
አንዳንዴ በህይወት መመረጥ እንጂ ጥረት ዋጋ ላይኖረው ይችላል ። " ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም " ይሉት የሀገራችን ቢህል ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ነው ። ዛሬ የለኝም ነገንስ ምን እሆናለው በማለት አትጨነቁ ።
ለህይወት ተመራጮች ልትሆኑ ትችላላቹ@Arganon_type @Arganon_type
ማሰብ በራሱ ሊሰለች ሊያደክም ይችላል የተግባር ሰው መሆን ደግሞ በጣም ፡ ህይወት በጥረቱ መለወጥ ለሚፈልግ ከምተሰጠው በጎ ነገር ይልቅ ፈተናዋና መከራዋ ይበልጣል ።
ዛሬም በልባችን ተስፋ እንዲኖር ..ነገን መለወጥ ስለመቻላችን እናስብ !!
ሁሉም ለበጎ ነው...!@Arganon_type @Arganon_type
ሰው ማሰቡን ሲያጣ ተግባሩ የስሜት
የት እደርሳለው አይል መሔድ እንደላኩት
ደመ ነፍስ አለቃው ደም ፍላት ወዳጁ
በቁጣ ይሞላል ፍቅር የለም ደጁ
ያይኑን ጣላት ላጥፉ የቃል ስተት ልግደል
አመል እንኳን ያጣል ሰውን የሚያስመስል
መኖር ኗሪን መቅበር መሞት ይዞ መሔድ
ሰው መሽት አይሸትም ሰውነትን መውደድ
@Arganon_type
@Arganon_type
ዛሬን ከትላንት የተሻለ ለማድረግ እቅዳቹህን እና ተስፋቹህን ጠብቃቹ ላደራቹህ ንቁ የማለዳ ሰዎች..
ቀናቹ በመልካም አጋጣሚዎች የተሞላ እንዲሆን ተመኘንላቹህ ።@Arganon_type @Arganon_type
ቀን አድባሩን ሌት ሲቀማውከእንቅልፌ ጋር መች ተስማማው አያሰብኩሽ እየነጋ እንቅል ይሉት ባይኔ ሳይዞር ቅዠት እንኳ ይናፍቃል አንቺን ማምጣት ህልም ሲያስቀር በቀንማ አትመጪም ሀሳብ እንጂ ቅርብ ያረገሽ ለሞኝ ልብ ብሎሽ እንጂ ልብልጡማ የሩቅ ሰው ነሽ ተፈቃሪን በመለመን ልብ አይገኝ በተማፅኖት ቀን ሲከዳ ሌት አያውቅም የት እንዳለሽ በህልም ቤት ። @Arganon_type @Arganon_type
ፍቅር ምስሎ ላታለለኝ ለኮልታፋው ለዛ ቃልሽ
ተሰብሬ ስለቀረው ከሀዘኔ ምን አገኘሽ
ንፁህ ልብ እንዳደለው አስመስሎ በቃል መጽደቅ
ልምድሽ ነበር እኔን መጣል በውበትሽ መመጻደቅ
ብትዋቢ ከሰው በላይ አማርሽና ለመፈቀር
አለም ከንቱ...ቆንጆ ገላም ሲሞት ያፈር ...
የወደዱት ነፍስ አልሰጠ ከሱ ቆርጦ እድሜ አይቀጥል
የተረፈኝ ስሜን ማጣት ላጠራሩ ያንቺ መባል
የኔ መሆን ፈራ ተባ ግማሽ እውነት ግማሽ ክደት
ያሳሳሻል ከንቱ መልክሽ ቆንጆ ሲሉሽ በዋልሽበት
አመል ጎድሎት ለስያሜ ስምሽ ጠፍቶ ከደግነት
ውብ ገላሽን የተመኘ ሰው ሲጠራሽ የኔ እመቤት
መጥፎን መርጦ በጎን ጥሎ ድንቄም መኖር ባንቺ ልኬት
ሲሸበሸብ ፊትሽ መልኩ አለኝ ያልሽው ወዳጅ መሳይ ሲያልፍ አታይም ባለፍሽበት
ቀኑ ሲደርስ ለመካካድ ከውበት ጋር ውል ከመያዝ
ስም ነበረው የሚወደድ ደግነት ይዞ መጓዝ !!
@Arganon_type
@Arganon_type
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=uSCSAQwf
LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾
https://t.me/major/start?startapp=1104785352
👑 Join me in @Major game and earn $MAJOR token soon!
⭐️ 750 rating bonus for you.
⭐️ 1000 rating bonus if you are Premium.
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=uSCSAQwf
LFG!
PAWS is the new top dog! 🐾
በጥቂት ቀናት ውስጥ ብዙ User ማፍራት የቻለውን ይሔን Airdrop መስራታቹህን እንዳትረሱ ፥ በተጀመረ ጥቂት ቀናት ውስጥ Veriefy መሆን ችሏል ።
