cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Hossana Gospel Movment

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
275
مشترکین
-124 ساعت
-17 روز
-430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ቀን 2 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 ለትግራይ የሕዝብ ክፍል እንጸልይ! የትግራይ ህዝብ መነሻውን ከብዙ ሺህ አመታት በፊት መቁጠር ይችላle። በቀይ ባህር በአፍሪካ በኩል በአባይ ደልታ እና ከሸለቆው በምስራቅ እስከ የኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች ድረስ ኑሮውን ያደረገ ማህበረሰብ ነው። እንደ ሳባ/ሳባ እና አክሱም ያሉ ታላላቅ መንግስታትን መስረቱ፡፡ ኑሮአቸው ምን ይመስላል? የትግራይ ህዝብ በዋናነት አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ናቸው። በጥንት ጊዜ በትግራይ ክልል ውስጥ በአቢሲኒያ መካከለኛው ዘመን ብዙ ክርስቲያናዊ ጥበብን የፈጠሩ በርካታ ትላልቅ የከተማ ማህበረሰቦች የነበሯቸውም ናቸው፡፡ የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ላለፉት ዓመታት በጦርነት ውስጥ ቆይቷል የትግራይ ሕዘብም በዚህ ጦርነት አስከፊ ጊዜ ውስጥ አልፏል ዛሬ ላይ ከዚህ ጦርነት ጠባሳዎች፣ አካለዊ እና አዕምሯዊ ጉዳቶ ለማገገም እና ወደ ቀደመው ኑሮአቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ እየተካሄደበት ያለ አካባቢ ነው፡፡ እምነታቸው ምንድን ነው? ክርስትና ወደ ትግራይ የመጣው በኮፕቲክ ሚሲዮናውያን አማካኝነት ነው። በትግራይ ክልል ውስጥ በምትገኘው በተቀደሰችው ነጋሽ ከተማ የመሐመድን ተከታዮች በመካ ከሚገኙት ጠላቶቻቸው ከተጠለሉ በኋላ ትግራይ እና ሌሎች ሀበሻዎች የመጀመሪያዎቹ አፍሪካውያን እስልምናን የተቀበሉ ናቸው። የተመለሱት ሀበሻዎች (በተለይ የትግራይ ሙስሊሞች) ጀበርቲ (በፈጣሪ የተመረጠ) በመባል ይታወቃሉ። ዛሬ አብዛኛው የትግራይ ተወላጆች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዮች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ የሱኒ/ሱፊ ሙስሊም ናቸው። የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏼 በትግራይ ያለውን የክርስትና መልክ የሚያጠራ የመንፈስ ቅዱስ ሃይል እንዲገለጥ እንጸለይ፡፡ 👉🏼 ብዙ ስሜታዊ እና አካላዊ ቁስል በገጠማቸው በዚህ ሰዓት የኢትዩጵያ ቤተ-ክርስትያን ለፈወስ እና ለህይወት በሚሆን ከህዛባችን ጎን በአብሮነት እንድትቆም ፤ ሁሉን መለወጥ የሚችለውን ኢየሱስ መስበክ እንድትችል ጌታ በጸጋው እንዲረዳን እንጸልይ ፡፡ 👉🏼 ቤተክርስቲያኖች የወንጌል ተልእኮ እንቅስቃሴዎችን በትግራይ ሕዝብ መካከል በትጋት መስራት እንዲችሉ ፣ ሚሲዮናዊያንን እንዲልኩ እንጸልይ፡፡ 👉🏼 ኢየሱስን ከሃይማኖታዊ ወጎች ይልቅ የሚያስቀድም ትውልድ እንዲቀሰቀስ እንተልይ፡፡
نمایش همه...
ቀን 1 🙏🏽እንጸልይ🙏🏽 ለአማራ የሕዝብ ክፍል እንጸልይ በምድራችን ኢትዮጵያ ቀደምት ወንጌል ከተሰበከባቸው አካባቢዎች የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዋናው ነወ፡፡ ወንጌል ወደምድራችን የገባባቸው ሁነቶች እንደሚሳዩት የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የወንጌል መልእክት በእውነተኛ መሰረት የተሰበከበት ስፍራ እንደነበር እንመለከታለን፡፡ በታሪክ ሂደት የወንጌል እውነት በብዙ መልኩ በዚህ አካባቢ ያለፈ ሲሆን ከሰሜኑ ክፍልም የአማራ የሕዝብ ክፍል የክርስትና እምነት በስፋት ተከታይ ያለበት አካባቢ ነው፡፡ የአማራ የሐዝብ ክፍል የተለያዩ የማህበረሰቦችን ያቀፈ ነው፡፡ የቀድሞ በዝዙ ዋጋ መክፈል የተሰበከ የወንጌል እውነት በዛሬ ዘመንም እንደገና እንዲያብብ በእግዚአብሔር ፊት አብዝተን እንጸልይ፡፡ ዛሬ ላይ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የወንጌል እንቅስቃሴዎች በበዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ያልፋሉ፣ የክርስቲያኖች ስደት ዛሬም አለ፣ የተልእኮ እንቅስቃሴዎች በአንድ ወቅት እንደነበረው ትኩረት አሁን ላይ በዛ ልክ እየተሰራ አይደለም፡፡ የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏼 እግዚአብሔር በአማራ ክልል ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች ላይ ጣልቃ እንዲገባ እንጸለይ፡፡ 👉🏼 ቤተክርስቲያኖች የወንጌል ተልእኮ እንቅስቃሴዎችን በትኩረት ወደ መስራት እንዲመጡ፣ ሚሲዮናዊያን እንዲላኩ እንጸልይ፡፡ 👉🏼 የተሃድሶ እንቅስቃሴዎች ጉልበት እንዲያገኙ፤ ተጽእኖአቸው እንዲሰፋ እንጸልይ፡፡
نمایش همه...
👍 1
ለሰሜን ኢትዮጵያ የወንጌል ንቅናቄ እንጸልይ ! በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡— መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፡ አላቸው። ማቴዎስ ወንጌል 9: 37 – 38 በዚህ ሳምንት እስከ አርብ ድረስ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ የወንጌል ንቅናቄ እና ተሃድሶ እንጸልያለን፤ በየቀኑ በሚለቀቁት የጸሎት ርዕሶች አበራችሁን እንድጥጸልዩ እንጋብዛለን፡፡
نمایش همه...
ለሰሜን ኢትዮጵያ የወንጌል ንቅናቄ እንጸልይ ! በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡— መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፡ አላቸው። ማቴዎስ ወንጌል 9: 37 – 38 በዚህ ሳምንት እስከ አርብ ድረስ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ የወንጌል ንቅናቄ እና ተሃድሶ እንጸልያለን፤ በየቀኑ በሚለቀቁት የጸሎት ርዕሶች አበራችሁን እንድጥጸልዩ እንጋብዛለን፡፡
نمایش همه...
ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል እንጸልይ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡— መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፡ አላቸው። ማቴዎስ 9፡ 37 - 38 ሰላም  የሚሽን ሞቢላይዜሽን ኢትዮጵያ ቤተሰቦች! ዛሬ አርብ ምሽት ከ3:30 ጀምሮ በቴልግራም ላይቭ ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል  በህብረት የምንፀልይበት ጊዜ ስለሚኖረን ከታች ባለዉ የቴሌግራም ቻናል ሊንክ በመግባት አብራችሁን እንድትጸልዩ እንጋብዛችኋለን። https://t.me/MobilizationEthiopia
نمایش همه...
ቀን 4 🙏🏾 እንጸልይ 🙏🏾               ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል በእግዚአብሔር ቃል ተደግፈን እንጸልይ! እግዚአብሔር ሆይ አንተ ታላቅ አምላክ ነህ! በምድር በሰማይ ከፍ ከፍ በል! እናመሰግንሀለን; ተመስገን አርሲ ኦሮሞ ሕዝቦች ከማንም ቀድመህ ስለምታቃቸው ስለምትወዳቸው፣ እንደቃልህም ስለምታስባቸው እናመሰግንሃለን። የጸሎት ርዕሶች 🤲 👉🏾 እነሆ፥ የአርሲ ኦሮሞ ሕዝብን በእጅህ መጻፍ ቅረጻቸው፥ ቅጥራቸም ሁልጊዜ በፊትህ ይሁን። ልጆቻቸው ይፍጠኑ፤ የሚያፈርሱዋትና ሊያወድሙዋት የሚጥሩ እግዚአብሄር ሆይ አስወጣቸው ። ትንቢተ ኢሳይያስ 49: 16-17 👉🏾ንስሐ እና የኃጢአት ስርየት በኢየሱስ ስም ለሁሉም  አርሲ ኦሮሞ ሕዝብ እንዲሰበክ እንጸልያለን። ሉቃስ 24፡47 👉🏾እንግዲህ ምሕረትን የአርሲ ኦሮሞ ሕዝቦች እንዲቀበሉ በሚያስፈልጋቸውም ጊዜ የሚረዳቸውን ጸጋ እንድትሰጣቸው ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት ስለእነሱ ቀርበን እንለምንሃለን። ወደ ዕብራውያን 4፤16
نمایش همه...
ቀን 3 🙏🏾 እንፀልይ 🙏🏾 ለአርሲ ኦሮሞ ህዝብ ክፍል እንጸልይ! ከአንድ አምላክ እግዚአብሔር ውጪ ዛሬም ብዙዎች ብዙ አማልክት እና ሀይላትን እያመለኩ ይኖራሉ፡፡ ስፍራ እና ቦታ የተሰጣቸው በስም የሚጠሩ አማልክት አሉ እግዚአብሔር ይህን እንዲቀይር እንጸልይ፡፡ 👉🏾 የመከሩ ጌታ ሚስዮናውያን በዚህ ሕዝብ መካከል እንዲልክ አጥብቀን እንጸልይ። 👉🏾 በአምልኮ እና በምልጃ ምድሪቱ ለወንጌል ለም መሬት እንድትሆን፣ የጸሎት ቡድኖችን የሚጀምሩ ቡድኖችትን እግዚአብሔር እንዲያነሳ ለምኑት።
نمایش همه...
1
ቀን 2 🙏🏾 እንጸልይ 🙏🏾 ለአርሲ ኦሮሞ ህዝብ ክፍል እንጸልይ! የአርሲ ኦሮሞ ሕዝብ ለቤተሰብ ልዩ ቦታ ያለው ማህበረሰብ ነው፤ ወንዶች የቤተሰብ መሪዎች እና አስተዳዳሪዎች ሲሆኑ አብዛኛው ወንዶች በአንድ ሚስት ተወስነው ቤተሰባቸውን ይመራሉ፤ ሆኖም ከአንድ በላይ ሚስት ያላው እና የተለያዩ ቤተሰቦችን የሚያስተዳድሩ አባወራ ወንዶች አሉ፡፡ አንድ አባወራ ብዙ ልጆች ሲኖሩት ክብሩ ይጨምራል፡፡ አርሲ ኦሮሞ ለቤተሰብ ልዩ ቦታ ያለው ሕዝብ ከመሆኑ አንጻ ከወለዷቸው ልጆች በተጨማሪ የራሳቸው ያልሆኑ ልጆችን በማሳደግ የሕይወታቸው አካል በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏾 ግብርና የሚተዳደሩበት የማህበረሰቡ መተዳደሪያ ስለሆነ እግዚአብሔር በስራቸው አማካኝነት ከሚያምኑ እና ወንጌልን ሊነግሯቸው ከሚችሉ ክርስቲያኖች ጋር እንዲገናኙ እንጸልይ። 👉🏾 የተተረጎመው የእግዚአብሔር ቃል ተደራሽ እንዲሆን አስፈላጊው አቅርቦት ሁሉ እንዲሟሉ እንጸልይ።
نمایش همه...
👍 1
አርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል የሕዝብ ብዛት - 6,944,000 • ዋነኛ ቋንቋ- ኦሮሚኛ ቦረና-አርሲ-ጉጂ • ብዙ ተከታይ ያለው ሐይማኖት - እስልምና (82.00%) • ክርስትና - 10.00% • ወንጌላዊያን አማኞች - 3.80% • የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም - ሙሉ ተተርጉሟል • ወንጌል ተኮር ቅጂዎች - አሉ የአርሲ ኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሕዝብ ክፍሎች መካከል ናቸው፤ በማዕከላዊ ምዕራበ የኢትዮጵያ ክፍል አብዛኞቹ ይኖራሉ፡፡ አርሲዎች የጦረኛነት ባህል ያላቸውና እረኛ ማህበረሰቦች ናቸው። የአንድን ሰው ደረጃ የሚለካውም ባለው የእንስሳት ብዛት እና በሚያሳየው የድፍረት እና የወንድነት ባህሪያት ናቸው፡፡ ደፋርነት እና ውጊያ አዋቂነት ላይ ትኩረት ይሰጣሉ ፈረስ መጋለብ፣ ጦር መወርወር እና መዋጋትየማንነት መገለጫ አካል ናቸው፡፡ አብዛኛው የአርሲ ሕዝብ እስልምናን የሚከተል ነው፤ ነገር ግን ባህላዊ ኃይማኖቶችም ከከፊሉ በላይ በሆነው ሕዝብ ይተገበራሉ። እነዚህ የጎሳ ኃይማኖተኞች ዋቃ የሚባል ታላቅ ፍጡርን ያመልካሉ፤ ከዛም ውጪ ብዙ ስያሜ ለሚሰጣቸውን አማልክት ግብርን የሚገብሩ እና አምልኮን የሚያቀርቡ አሉ፡፡ በዚህ ሳምንት ለአርሲ ኦሮሞ እንጽልያለን እግዚአብሔር ይህን ሕዝብ እንዲጎበኝ አጥብቀን እንጸልይ፡፡ የጸሎት ርዕሶች 🤲🏽 👉🏼 እግዚአብሔር በአርሲ ሕዝብ መካከል ራሱን እንዲገልጥ አጥብቀን እንጸልይ፡፡ 👉🏼 የወንጌል ደጆች እንዲከፈቱ አጥብቀን እንጸልይ፡፡ 📖 መዝሙር 2: 8 ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።
نمایش همه...