Joseph Math Tutor
رفتن به کانال در Telegram
Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/D8K0MVqynVA?si=y_uFeHG7awC1oX9Y Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580
نمایش بیشتر1 857
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+57 روز
+2130 روز
آرشیو پست ها
1 856
ምን ታያላችሁ ❓
እኔ ለማዳ ነኝ ፤ አልነካችሁም። ፍሬሾች ናችሁ መሰለኝ ... እኔ ምፈልገው ተከባብሮ አብሮ መኖርን ብቻ ነው።
— ከ ASTU ጅብ የተላለፈ መልዕክት 😂
1 856
በዓል ሲደርስ ከስንት ቀን በፊት ነው ምንወጣው ❓ 😅
You are about to join ASTU. But think you will celebrate your holidays. 🤔... maybe you might have listened to a motivational speaker saying "Think the impossible" 🤣🤣🤣
ምን መሰላችሁ ... ግቢው በዓል አያቅም። በእርግጥ ዝግጅት ግቢ ውስጥ ይዘጋጃል። ነገርግን ለበዓል ተብሎ የግቢው ካላንደር አይዛባም። ለምሳሌ በ 2017 ዓ.ም የሁለተኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስቴር ፋይናል ፈተና የሚሰጥበት ቀን በገና በዓል ላይ ይውላል። ለበዓል ብለው ትምህርት ይዘጋሉ የሚለውን አታስቡት።
1 856
Grade Calculate ማድረግ
Grade እንዴት Calculate እንደሚደረግ አናውቅም post ይደረግልን ስትሉ ለነበራችሁ እንሆ አሰራሩን ይዤ ከች ብያለሁ 😊
Grade calculate ለማድረግ በመጀመሪያ 3 ነገሮችን ማወቅ ይጠበቅባችኋል:- እነሱም
1. የ እያንዳንዱን የትምህርት አይነት Crh (credit hours)
In our case maths ብቻ ነው 4 crh ሌሎቹ 3 Crh ናቸው።
Applied 1 ----------------- 4Crh
English---------------------3Crh
Physics--------------------3Crh
Chemi----------------------3Crh
Logic------------------------3Crh
Python---------------------3Crh
2.በሁለተኛ ደረጃ ማወቅ የሚጠበቅባችሁ ነገር ደግሞ የእያንዳንዱ የ Grade ፊደላት ዋጋ ነው።
ይሄም እንደሚከተለው ይሆናል
A+ ---------- 4.0
A ------------ 4.0
A- ----------- 3.75
B+ ---------- 3.5
B ------------ 3.0
B- ----------- 2.75
C+ ---------- 2.5
C ------------2.0
C- -----------1.75
D ------------ 1
F ------------- 0
3. ሶስተኛ እና የመጨረሻው ደግሞ ማወቅ የሚጠበቅባችሁ ከመቶ ስንት ባመጣ እነዚህን ከላይ ነተጠቀሱትን Gradeኦች ይሰጠኛል የሚለውን ነው።
ይሄም እንደሚከተለው ነው።
90 እና ከዛ በላይ = A+
85 - 89 = A (85ትን እና 89ን ያካትታል)
80 - 84 = A- (80ን እና 84ትን ያካትታል)
75 - 79 = B+ (75ትን እና 79ን ያካትታል)
70 - 74 = B (70ን እና 74ትን ያካትታል)
65 - 69 = B-(65ትን እና 69ን ያካትታል)
60 - 64 = C+ (60ን እና 64ትን ያካትታል)
50 - 59 = C (50ን እና 59ን ያካትታል)
45 - 49 = C-(45ትን እና 49ን ያካትታል)
40 - 44 = D (40ን እና 44ትን ያካትታል)
39 እና ከዛ በታች = F
እሺ በስተመጨረሻ እንዴት አድርገን ነው Calculate ምናደርገው ❓...
እሺ ለምሳሌ ተማሪ አየለች ተመስገን የሚከተለውን ውጤት አመጣች እንበል
Maths 49.5 ( C- 🙆) መምህር ገነነ አዩን በጣም አበሳጭተዋታል😢
English 72 ( B 🐒)
Physics 66 (B- Oops🙄)
Chemi 94 ( A+... chemoን እማ ተክናበታለች
Logic 87 (A...አየሉ Logic ላይ ጥሩ ናት👏)
Python 78 ( B+...Wow!)
አሁን ምን እናረጋለን ... የ አዩን ውጤቶቾ በእያንዳንዱ ትምህርት Crh እናባዛቸዋለን
Maths => 1.75 × 4 = 7
English => 3 × 3 = 9
Physics => 2.75 × 3 = 8.25
Chemistry => 4 × 3 = 12
Logic => 4 × 3 = 12
Pyhton => 3.5 × 3 = 10.5
ከዛ ተባዝተው የሚመጡትን ውጤቶች እንደምራቸዋለን
7 + 9 + 8.25 + 12 + 12 + 10.5 = 58.75
ተደምሮም የመጣልንን ውጤት ለ Crhኦቹ ድምር እናካፍለዋለን
የ Crhኦቹ ድምር => 4 + 3 + 3 + 3 + 3 + 3 = 19
ስለዚህ 58.75/19 = 3.092 ( አየሉን እንዳይከፋት አስኪ 3.1 እንበልላት)
The End 🤗 🙌
1 856
📒 ማስታወሻ/ደብተር 📔
እዚህ እንደፈለጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። እንደ high school ለእያንዳንዱ ትምህርት አንድ ደብተር ካላችሁም መብታችሁ ነው። ሁሉንም በአንድ ካላችሁም ትችላላችሁ። ዋናው ነገር የሚፃፍ ነገርን በትክክል ትፅፋላችሁ ወይ በቂ የሆነ ማስታወሻስ ትወስዳላችሁ ወይ የሚለው ነው። እኔ ምመክራችሁ ግን ባለ ብዙ subject ደብተር ግዙ። ይሄ በአንድ ላይ አራት እና አምስት subject የሚይዘውን ከገዛችሁ ምርጥ ነው። አስፈላጊ ሲሆን ሌላ ትጨምራላችሁ። ፁሁፍ እንደየአስተማሪው ነው። አንዳንዱ ሞጁሉን ይገለብጣል 😏 ... አንዳንዱ ደግሞ ብትለምኑትም ምንም አይፅፍም። ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ሁሉ ማይፅፍ አለ። በቃ ዝም ብሎ ይገባል ያወራል ከዛ ይወጣል ... እሱ ሲወጣ ሁልጊዜ ሰሌዳው ፅድት እንዳለ ነው 😅...
እና እንደየራሳችሁ የንባብ ዘዴ ነው ማስታወሻ ሚያስፈልጋችሁ። በተለይ ደግሞ ወረቀት አስጠርዞ መጠቀም እዚህ ግቢ common ነው። ስለዚህ እንደሚመቻችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
Pls አትጨናነቁ ... feel free!🤗
1 856
#ASTU
#Grading_system (የ Grade ፊደላት ዋጋ)
#Mark #Letter_Grade #Grade_Pt
1. (90 - 100) A+ 4.00
2. (85 - 89) A 4.00
3. (80 - 84) A- 3.75
4. (75 - 79) B+ 3.50
5. (70 - 74) B 3.00
6. (65 - 69) B- 2.75
7. (60 - 64) C+ 2.50
8. (50 - 59) C 2.00
9. (45 - 49) C- 1.75
10. (40 - 44) D 1.00
11. (0 - 39) F 0.00
12. I Incomplete _
13. NG Non Grade _
1 856
መምህራን 👨🏫
በምንም አይነት ሁኔታ ከአስተማሪ ጋር የማይሆን ነገር ውስጥ አትግቡ ፤ አትነካኩ። አስተማሪ አንዴ ከጠመዳችሁ አይፋታችሁም። Pls pls pls pls ከአስተማሪ ጋር ያላችሁን ግንኙነት በተቻለ መጠን መልካም ብቻ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አድርጉ። አንዴ አይን ውስጥ ከገባችሁ ትቸገራላችሁ። አንዳንድ አስተማሪ ደግሞ መከራ በልታችሁ የምታመጡትን ግሬድ ሁሉ ገደል ሊከትባችሁ ይችላል። ስለዚህ ተጠንቀቁ። አስተማሪው በድሏችሁ እናንተ ይቅርታ ጠይቁ። "መብት አለኝ ፣ ሰርቼ ያገኘሁት ውጤቴ ነው ፣ ምን ያመጣል..." ምናምን የሚሉ ድንፋታዎች ገደል ከመክተት በስተቀር ምንም አይፈይዱም። በእርግጥ ብዙ ጊዜ የሚያናድድ ሁኔታ ሊገጥማችሁ ይችላል። ነገርግን እራሳችሁን በደንብ ተቆጣጠሩ። በሚገባ መምህራኖችን አክብሩ። ትልቅ ክብር ስጡአቸው። ትልቅ ሰው እየሆንኩ ነው 🫨 ፣ እራሴን መራለሁ እንጂ በማንም አልመራም 🫢፣ የራሴ ህግ ያለኝ 🤓 በራሴ ህግ የምመራ ሲግማ ነኝ 💀🤣... " ምናምን የሚሉ ቅዠቶች ውጤታቸው የማትፈልጉትን ነገር መማር ወይም ሻንጣ ተሸክሞ ወደ ቤት መሄድ ነው የሚሆነው።
ስለዚህ ጠንቀቅ በሉ ፣ መምህራንን (ምንም አይነት ቢሆኑ) አክብሩአቸው ለማለት ያክል ነው።
1 856
#ASTU
🚪 የበር ቁልፍ 🔑
የዶርማችሁ በር ቁልፍ የሲሊንደሩ ቁልፍ ሲሆን ሎከር የምትቆልፉበት ደግሞ እንዲህ 🔐 አይነቱ ቁልፍ ነው። እናም ጠንከር ያለ የሎከር ቁልፍ ቢኖራችሁ ጥሩ ነው። የመጋዘን ቁልፍ ገዝታችሁ ደግሞ አልገባም እንዳይል 😁 ... ስለዚህ መጠነኛ ቁልፍ ግዙ።
1 856
#ASTU
ፍሬሽማን ላይ ቻሌንጅ ሚያደርገው ብዙ ተማሪ ነው ወይስ ጥቂት ተማሪ ነው ❓
እውነት ለመናገር ሁሉም ተማሪ ማለት በሚቻል ደረጃ ጥሩ ውጤት ለማግኘት የማይፈነቅለው ድንጋይ ፣ የማይወጣው ተራራ ፣ የማይወርደው ሸለቆ የለም። ተኝቶ የሚያድር ተማሪ የለም።
አስባችሁታል ስምንት / ዘጠኝ ሰዓት ላይ ከላይብረሪ እየወጣችሁ በዛን ሰዓት ለማንበብ የሚገባ ተማሪ ስታገኙ ... 🫢🤭
ስለዚህ ቻሌንጅ አለ እናም ጠንከር ብላችሁ መዋጋት ነው።
🫡 በእርግጠኝነት ታሸንፋላችሁ 🔥
1 856
#ASTU
ክሊኒክ 🏥
ክሊኒክ የምትታከሙት በነፃ ነው። ምናልባት የግቢው ካፌ ምግብ ካሳመማችሁ እና ጨጓራችሁ ላይ ጉዳት የማስከተል እድል ካለው ግቢው ለጤንነታችሁ ቅድሚያ ስለሚሰጥ ስፔሻል ተመጋቢ እንድትሆኑ ያደርጋል።
ስፔሻል ተመጋቢ ማለት ተማሪዎች ከሚመገቡት መደበኛ ምግብ በጥራቱ እጅግ ከፍ ያለ ምግብ የሚመገብ ማለት ነው። የቤት ምግብ በሉት። እንደውም ከቤትም ይበልጣል ይላሉ 😁። ስፔሻል ተመጋቢ ትንሽ ስለሆነ እጥር ምጥን አድርገው መስራቱን አዘጋጆቹ ተክነውበታል 👌። ከመደበኛው ምግብ በጣም ይለያል ፤ ጣዕሙም እንዲሁም ሁሉ ነገሩ ይለያል።
1 856
#ASTU
ማታ ማታ እስከፈለጋችሁበት ሰዓት ድረስ ላይብረሪ መቆየት ትችላላችሁ። በእርግጥ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ይዘጋል እናም ጠዋት 2 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ማታ ላይ አንብባችሁ ስትመለሱ like 6 ፣ 7 ወይ 8 ሰዓት ላይ ብቻችሁን ባትሆኑ ይመረጣል። ሌባ አግኝቷችሁ ልትዘረፉ ትችላላችሁ (ይሄ ብዙም risk የለውም)። ምናልባት ጅቦቹ በብዛት አሉ በዛ ሰዓት። አይነኳችሁም። ግን ብቻችሁን ከሆናችሁ መፍራታችሁ እና መሸበራችሁ ስለማይቀር ከጓደኞቻችሁ ጋር ሆናችሁ አምሹ እንጂ ብቻችሁን አትሁኑ።
1 856
#ASTU
ወደ ቤት መሄድ /ከግቢ መውጣት
በፈለጋችሁት ሰዓት መሄድ ትችላላችሁ። ከምሽቱ 3 ሰዓት በኋላ ግን አይቻልም። አንዳንድ ተማሪዎች special case ሲኖርባቸው በትምህርት ቀናትም አስፈቅደው ይሄዳሉ። በተለይ የአዲስአበባ ልጆች ከተማው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ አብዛኞቹ weekend ላይ ወደቤት ይሄዳሉ። ዋናው ነገር ክላስ አለመቅጣት እንጂ መውጣት መግባቱ መብታችሁ ነው። ስትወጡ ግን ፕሮክተር ጋር ሄዳችሁ መውጫ ማስፃፍ ይኖርባችኋል። አለበለዚያ ከግቢ እቃ ይዛችሁ መውጣት አይቻልም።
1 856
#ASTU
ፀጉር 🙄
በእርግጥ ይከለከላል ማለት አይቻልም። ግን ባለፈው አመት ህዝቤ ሁሉ ሹሩባ የሚያሰራ ፀጉር ተሸክሞ ባለበት በድንገት ያልተጠበቀ አንድ ማስታወቂያ ወጣ ... የቀን ገደብ አስቀምጦ በዚህ ጊዜ ውስጥ እንድትስተካከሉ የሚል ነበር። እና ሁሉም ኖርማል በሚባል መልኩ ነበር የተስተካከሉት 💇💇♂። አንዳንዴ በተለይ ማታ ላይ ፀጉር ያሳደገ ሰው ግቢ ሲገባ ይይዛሉ። ደሞ ፌዴራል ፖሊስ ናቸው ... ስለዚህ ከስጋት ነፃ ለመሆን መጠነኛ/መካከለኛ ፀጉር ቢሆን ይመረጣል።
1 856
#ASTU
WiFi 🛜
ግቢው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች WiFi አለ። በየ ላይብረሪዎችም ይገኛል። ግቢው ውስጥ ያሉ ዋይፋይዎች የሚሰሩት በ IP address ነው እንጂ እንደማንኛውም በፓስወርድ አይደለም። ውጤታችሁን እና ሌሎች መረጃዎችን ምትከታተሉበት ፖርታል intranet ሲሆን የሚሰራውም በግቢው ዋይፋይ ብቻ ነበር አሁን ግን በ Data ይሰራል።
1 856
#ASTU
DStv 📺
ግቢው ውስጥ ተማሪ ሚሰበሰብበት amphi ሚባል ቦታ አለ። እዛ ቦታ አንድ ግዙፍ screen አለ። የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ተማሪዎች በሚገባ ይከታተላሉ። ግቢው በኳስ አፍቃሪ የተሞላ ነው። አንዳንዴ እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ ጨዋታውን ይከታተላሉ። ጎል ሲገባ ይጮኻሉ 😂። እዛው አከባቢ TV ምትመስልም screen አለች። አንዳንዴ ትልቁ ማይሰራ ከሆነ በዛም ይመለከታሉ።
1 856
#ASTU
ጂም 🏋🏻♂️
👉 ግቢው ውስጥ ያለ ሲሆን የሚገኘውም ስታዲየም ጋር ነው። በወር 400 ብር በቀን ከሆነ ደግሞ 20 ብር ነበር። ሴቶችም ይሰራሉ 🫢🤭።
@ASTU_Freshman_Channel
1 856
#ASTU
ክላስ መቅጣት 🥶
👉 በእርግጥ አንዳንድ አስተማሪዎች ምንም አይሉም። አንዳንዶቹ ደግሞ NG የሚሰጡ እና ተማሪውን ጠምደው እስከመጨረሻው ድረስ የማይፋቱ አሉ። ስለዚህ ክላስ መቅጣት አደገኛ ነገር ነው። መጀመሪያ ሲሆን ደግሞ የአስተማሪውን ፀባይ ስለማታውቁ ትቸገራላችሁ።
Attendance 👇
👉 ግቢው በአቴንዳንስ ጉዳይ ቀልድ አያቅም። አቴንዳንሳችሁ የግቢው ፖርታል ላይ ሁሉ ይሞላል። እናንተ ወረቀት ላይ ትሞላላችሁ ፣ አስተማሪዎቹ ወደ ፖርታል ያስገቡታል። ስለዚህ በአቴንዳንስ አትቀልዱ።
It's ASTU, the hell, not your high school 🫡
1 856
#ASTU
እስከ ስንት ሰዓት ግቢ ውስጥ መንቀሳቀስ እንችላለን ❓
👉 24Hrs ይቻላል። ሁሉም አንባቢ ነው ... Imagine አንተ ምሽት ስምንት ወይ ዘጠኝ ሰዓት ከላይብረሪ ስትመለስ የሆነ ሰው ለማንበብ እየሄደ ስታይ ..😁 .. ብቻ በፈለጋቹት ሰዓት መንቀሳቀስ ትችላላችሁ። ነገርግን አንዳንድ ቦታዎች ላይ አይፈቀድም። በተለይ ማታ ማታ ፌዴራል ፖሊሶች ናቸው ሚዞሩት እና መጠንቀቅ ማለት ግድ ነው።
ውጪ እስከ ስንት ሰዓት መቆየት ይቻላል ❓
👉 በሩ የሚዘጋው ከምሽቱ 3:00 ላይ ነው። ከዚህ በኋላ መግባት አይቻልም።
1 856
2. GENERAL PHYSICS
High school ላይ የተማራችሁት ነው። ግን እየሰፋ ይሄዳል። ምን ማንበብ እንዳለባችሁ አውቃችሁ ማንበብ ነው። በተለይ የ serway ጥያቄ መስራት። የ ASTU ን ጥያቄዎች በደንብ ካልሰራችሁ ልክ አይመጣም። ስለዚህ ብዙ ልፋት ይጠበቅባችኋል።
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .
1 856
1. APPLIED MATHEMATICS I
አንዳንዶች Interesting ነው ሲሉት ሌሎች ደግሞ boring ነው ይሉታል። ይዘቶቹ በዋናነት high school ላይ የተማራችኋቸው ሲሆኑ ፣ ብዙ የተጨመሩ ነገሮች አሉ።
🗂 Contents 👇
Chapter 1:
Vector
Chapter 2: Matrices
Chapter 3: Limit
Chapter 4: Derivation
Chapter 5: Integration
... እነዚህ ናቸው። መሰረት የሚያደርገው የ high school ትምህርት ላይ ሆኖ ግን ረጅም ርቀት ያስኬዳል። የሃይስኩሉ just መነሻ ብቻ ነው። ፈተናው በብዛት የሚያተኩረው የተግባር (applicable) ጥያቄዎች ላይ ነው። ፎርሙላ ሸምድዳችሁ🤓 ሳይሆን logical 🧠 ሆናችሁ ነው የምትሰሩት። Conceptual መሆን 👌...
ብዙ ተማሪዎች ውጤት ይወርድባቸዋል ፤ ስለማያውቁ ሳይሆን ፈተናው ትንሽ 💀 ስለሆነ 😁። እንደምታስቡት ላይሆንላችሁ ይችላል። በደንብ ማንበብ ይፈልጋል። ሁሌ ጥያቄ መስራት ፣ ሁል መፍለጥ ፣ አሁንም መፍለጥ ፣ ደግማችሁ መፍለጥ ፣ ከዛ መፈላለጥ በመጨረሻም መፈላለጥለጥለጥ ይፈልጋል። እየቀለድኩ አይደለም ፤ የምሬን ነው። ብዙ ተማሪ ያማርርበታል። እናንተ ግን ትችላላችሁ ✊🔥
Begashaw &University Mathematics reference bookochu
... ሲሆኑ አብዛኛው የግቢው ተማሪዎች የሚጠቀመው እነዚህን ነው። አስተማሪዎች ራሱ ፈተና ጭምር ያወጡባቸዋል ይባላል።
ይ ቀ ጥ ላ ል . . .