cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر

ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው። አስተያየት ለመስጠት= @esmael9

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 416
مشترکین
+424 ساعت
+277 روز
+6330 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
📢 ለዓረፋ ዚያራ ... በምንችለው ሁሉ ኢስላምን አደራ !!! ... ያንተ አባቶች ጋራ ሸንተረሩን ሞፈርና ቀንበር አጥምደው በመቆፈር ፊደል ሳይቆጥሩ በጣታቸው እየፈረሙ አንተን ለማሳደግና ከተሜ ስልጡን ለማድረግ ከነበራቸው መስዋዕትነት በተጨማሪ የተለያዩ ማማለያዎችንና የተጠኑ ስልቶችን በመጠቀም ሀገሬውን ለማክፈር የመጣውን ኃይል ሸሪዓዊ ዕውቀትን ባልተሞረከዘ ጥበብና ተፈጥሯዊ በሆነ ማንነት ላይ ሆነው በከፈሉት ተጋድሎ ሕዝበ ሙስሊሙን በአላህ ፍቃድ ከክህደት ታድገውት አንተንም ዛሬ ላይ ላለክበት ማንነት አበቁክ❗ 💐 አንተ ግን ይህን ወደር የማይገኝለት የአባትና እናት ውለታ ረስተክ ... እነዚያው ካፊሮች ከብዙ ዓመታት የሴራ ቆይታ በኋላ ትላንት እጅ ባለመስጠት ፊት ነስቶ ጠላቱን ያባረረና ዕምነቱን የጠበቀ ጀግና አባትና እናትን ደከም ብለው ወገባቸው በጎበጠና ከልቡ የሚጦራቸው የአብራካቸወ ክፋይ ኖሮ እንደሌለ ነገር ያጡ የሆነ ጊዜ ...በአላህ ምድር ላይ ክህደትን የማንገስ "ፕሮጄክት" ነድፈው ለየት ያለና የተጠናከረ ተልዕኮ በመያዝ ወደ እያንዳንዱ ሙስሊም ቤት በስውርና በግልጽ እያንኳኩ ነው። በናቅናቸውና ኋለ ቀር አርገን በምንቆጥራቸው ወላጆቻችን ጀግንነት ያልተደፈረ ዕምነት ስልጡንና ዘመናዊ በመሰልነው ከንቱ ኩፍሶች ተናቀ !!! ፊደል ሳይቆጥሩ የጠበቁት "ዲን" ፊደሉን አተራምሰን ለይተን የተማርነው እኛ አስደፈርነው ! እነሱም የአባቶቻችንን የጀግንነት ተጋድሎ ድል ለመቀልበስና ለመበቀል ፍርኀት የዋጠውን የሙስሊም ትውልድ ሴት ወንድ እፃን አዋቂ ሳይሉ ለሁሉም በሚስማማው መልኩ ኩፍርን አበጅተው እያሳደዱት ነው !!!!! ስለዚህ ፦ እንንቃ በደንብ እንንቃ !!! 👉 ጥቂት የማይባሉ ሰዎች በኛው ወንጀል ምክንያት የመጣውን ይህን አስከፊ የኑሮ ውድነትና መከራ ለማለፍ ሲሉ በሩን እየከፈቱ ነው !!! የአንተስ ቤተሰቦች በራቸውን ላለመክፈታቸው ምን ማስተማመኛ (ዋስትና) አለክ ? 👉 ሰሞኑን ከተወሰኑ ወንድሞች ጋር ሆነን ለዚሁ ለዳዕዋ ጉዳይ በሚል ወደ ደቡብ ክልል ወደምትገኘው ስልጤ ዞን ሄደን ነበር። በአከባቢው ያለው ማህበረሰብ በአላህ ቸርነት መታደል ሆነና እስልምናን ዕምነት ከመሠረቱ በመጎናፀፍ እስካሁን ድረስ በትውልድ ሽግግር አላህ ጠብቆለት ከላይ ያወሳውላቹ እናት አባቶች በአላህ ዕርዳታ በከፈሉት መስዋዕትነት እዚህ ደርሶ ነበር። 👉 አሁን ላይ ግን የኩፍር አይሎች ትላንት ወላጆቻችንን ለማማለል የተጠቀሙበት " ልጆቻችሁን ትምህርት እናስተምርላችዋለን ... ! " በሚልለው ዘዴ ሳይሆን... ዛሬ ኑሮ ተወዷል አይደል ...??! ጊዜውም እንደምታዩት ከፍቷል ...‼️ ደሞም ወልዳቹ እንዳልወለዳቹ ነገር ልጆቻቹም ጠፉ !!! "እውነተኛ በሰማይ ያለው አባት በሩን ከፍቶ ነው እኛን ወደ እናንተ የላከን..." የቸገራቹን ነገር ንገሩን የምትፈልጉትን ነገር ይዘን እንመጣለን !!! እያሉ እኛ የነፈግናቸውን ዱቄትና ዘይት ... ለመስጠት እየሞከሩ ነው‼️ ልክ ሰለፎቹ እንደሚሉት ፦ « ሆድ ከበላ ዓይን ያፍራል » እውነት ነውና የገጠር ወገኖቻችንም ይህን አደጋ የሚታደጉበት ኢማን ተሸርሽሮ ጫፍ የደረሱ ይመስል አንዳንድ ለሆዱ አደር የሆነ ማይረባ የፖለቲካ ጉዳይ አስፈፃሚና ከንቱ የሆነውን ተራ ሰው ተጠቅመው እጅ መንሻ በመስጠት ኩፍራቸውን በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ። አዎ ! እኛም በሄድንበት ያየነውና የሰማነው ይህንኑ ነው። ከሄድን በኋላ እንግድነት ከተቀበሉን ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት እከሌ እዚህ ቦታ እከሌ እዚህ መንደር ላይ እከሊትም በዚህ ምክንያት ከፈሩ "እየሱስ ጌታ ነው ‼️" ማለት ጀመሩ። በማለት እያዘኑ ነገሩን። ሌላኛው አንድ ወንድማችንም እንዲህ በማለት አስከትሎ በቤተሰቡ የሆነውን እውነተኛ ክስተት ነገረን « ከአለፈው ዐረፋ በፊት አዲስ አበባ ዚያራ መጥቶ በሰላም ሸኝተነው ነበር።ለዐረፋም ስንመጣ በነበረበት ነበር።ሰሞኑን ስመለስ ግን ከፍሮ "አላህ ጬኛል" (አላህ ወልዷል‼️) እያለ ተቀበለን !!! ያሳዝናል ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ገብቶናል‼️!!! ያሳዝናል !!! ተጠያቂው ማነው ‼️??? ሁላችንም ነን !!!!! አዎ እኛ ሰራን ካልን የሚታየን ትልቁ ስራ ከኩፍር ወደ ኩፍር አስተምህሮ የሚቀባበለንን ት/ቤት ነው። አዎ ! ለዚህ ነው ብዙ ሺህ ብር ዶላርና ሪያል ለማሰባሰብ እየሮጥን ያለነው ይህን ደሞ ቀዳማዊቷም እየተገበረችው ነው። የርሷ ትግበራ ግን እጅግ በረቀቀ ሰው ሰራሽ ስሌት የተቀነባበረ ነው !!! የእናንተ እና የእርሷ ዕቅድ በመነሻ አሳቡ አንድ ሆኖ ድንቁርናን ማጥፋት የሚለው ነው‼️ በማሳረጊያውና በመጨረሻው ውጤት ግን... የእናንተው ዕምነቱን እየሸራረፈም ቢሆን ሊቅ ማግኘት ሲሆን የርሷና የመሰሎቿ ግብ ግን ሊቅ እያፈሩ በአላህ ምድር ላይ ኩፍርን ማፅናት ነው !!! ይህ ደግሞ በቀጥታና በተዘዋዋሪ እስልምናን መዋጋት ነው ‼️እኛም አብረናቸው እስልምናን እየተዋጋን ይሆን !!?‼️ አዎ ! ጥርጥር የየውም !!! አይተናነቀን አምነን እንቀበል !!! 👉 ይህ ደሞ ሳይታለም የተፈታ መሆኑ ገና ከጅምሩ ገብቶናል !!! እንዴት አይግባን የውዱ ነብይ ሱና ተከታይ ሆነን ???!!! 👉 ሙስሊሞች ሆይ ሁላችንም በደንብ ይግባን !!! 👉 ቆም ብለን እራሳችንን በአስተውሎት እንጠይቅ !! 👉 ስለዚህ ማንቀላፋቱ ይብቃ ! ትክክለኛ የ"ዐቂዳ"ና "ሱና" ፍሬ ላላቸው መስጂዶች ፣ መርከዞች ፣ መድረሳዎች... ብራችንን እንምዘዝ እላለሁ ።ይህን በማድረግ የክህደት ኀይሎችን እንዋጋ አላፊነታችንን ተወጥተን ወገኖቻችንን እንታደጋቸው !!! አንተ እንደሆነ የገጠሩን መሬት እትብትክን እንዳልቀበርክበት ነገር ትተከዋል !! ረስተከው የተውከው የገጠሩ ሰውም በዓመት አንዴ ብቻ ተመግቦ እንደሚፀዳዳ ነገር ...ጋዝ ሳሙናና ጨው... አንጠልጥለክ ደሟን አፍስሳ ፥ ስጋዋ ተተልትሎ የወለደችክ ሳያንሳት በድጋሚ ጡቷን መዝምዘክ ፥ በሽንትክ አቃጥለካት ፥ ወገቧን አጉብጠክ ያስቀራካትን ውዷን እማምዬ ወግ ነውና ሰው ለመምሰል ስትል "ለዐረፋ" ብቻ ሄደ ታያታለህ❗ ያለመታደል ሆነና አብዛኞቹ የገጠር እናቶች እናትነታቸው በዓመት አንዴ ለዐረፋ ብቻ ሆነ❗ አንተና አንቺ እኔንም ጨምሮ ሁላችንም የኢስላም ልጆች ሆይ ! የአላህንና የመልዕክተኛውን "ሐቅ" በከባዱ ይይዘናል !!! እንዲሁም የእናትና አባት ሐቅን አለመወጣታችን በታማኙ መልዓክ "ጅብሪል" አስረግሞናል...!!! በታላቁ ነብይ አንደበት "አሚን" ባይነት ይሁንታን አግኝቷል !!! ለፍርድ በማይቾክለው አምላክ ፈራጅነት "ጀነት" እርም እንዳይሆንብንም ያስፈራልናል !!! 📢 ስለዚህ አላህ ፊት ቀርበክ ሳትጠየቅ በፊት ከሆዳቸው በላይ ዕምነታቸውም አደጋ ተጋርጦበታልና በዕውቀትክ በጉልበትክ በገንዘብክ ብቻ በቻልከው ሁላ ለወላጆችክም ለወገኖችክም ድረስ እላለሁ ! “ ከተሜ መባል የሆነ ነገር ቢኖረውም ቅሉ ገጠሬ መባል ግን ልዩ ጥበብ አለውና ” 👉 እትብትክ የተቀበረበትን ገጠር አስታውስ !!! … ኢስማኤል ወርቁ... https://t.me/amr_nahy1
2226Loading...
02
الدرس الثامن قول الناظم:  وإلى السماء بغير كيف ينزل 🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-08 ♻️ ክፍል-ስምንት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة።   ١٤٤٥/هـ4 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1330Loading...
03
📮 ዓረፋ በገነንዳ በምሩ ኽሮት ያነወ📮⤵️ በሚል ርዕስ ወቅታዊ የሆነ መደመጥ ያለበት በጉራጊኛ ቋንቋ የተደረገ ሙሐደራ⤵️ 📍👇ሙሐደራው ላይ ከተወሱ ነጥቦች ውስጥ በከፊሉ⤵️👇 💥አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ቱሩፋትና በልዩ መልኩ ከዙልሂጃ ዘጠነኛው ቀን። 💥 ኡዱሒያ የተደነገገበት ጥበብ {ሂክማ} እና ሁክሙ ምንድነው? 💥ክፍለ ሀገር ላይ ከዒደል ዓድሀ ዓረፋ ጋር በተያያዘ አንዳንድ  የሚፈፀሙ ሙንከራቶች 💥 የዒድ ቀን ለኡዱሒያ(እርድ) የሚዘጋጀው ማሟላት ያለበት መስፈርቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ... 💥 ሲታረድም ሆነ ከታረደ በኋላ የሚባል ዱዓ ወይም ሌላ ነገር አለን? 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ሲሄዱ የሚያደርጉት የተለየ ዒባዳ አለን? 💥 ዒድ የሚሰገድበት ሰዓት {ጊዜ} እና የሚያበቃበት ሰዓት {ጊዜ}። 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ በምን አይነት ሁኔታ ነው መሄድ ያለባቸው? 💥 የዒድ ሰላት አሰጋገድ ሁኔታ በተግባር ምን ይመስላል ተክቢራስ ስንቴ ነው ሚባለው? 📌 ሌሎችንም ነጥቦች የተዳሰሰበት በጉራጊኛ ቋንቋ የተደረገ ሙሓደራ። 🎙 በኡስታዝ አቡ የሕያ ኢልያስ ቢን አወል አላህ ይጠብቀው። 📅 ሀሙስ 30/10/2014E.C 📅 📎https://t.me/Adamaselefy/8013
1431Loading...
04
ለሞተ ሰው ኡዱሒያ... *الأضحية عن الميت؟.* 🏷️ قال الإمام ابن باز رحمه الله تعالى : فإﻥ ﻛﺎﻥ قد ﺃﻭﺻﻰ ﺑﻬﺎ ﻓﻲ ﺛﻠﺚ ﻣﺎﻟﻪ ﻣﺜﻼﺃﻭ ﺟﻌﻠﻬﺎ ﻓﻲ ﻭﻗﻒ ﻟﻪ ﻭﺟﺐ ﻋﻠﻰ اﻟﻘﺎﺋﻢ ﻋﻠﻰ اﻟﻮﻗﻒ ﺃﻭ اﻟﻮﺻﻴﺔ ﺗﻨﻔﻴﺬﻫﺎ ﻭﺇﻥ ﻟﻢ ﻳﻜﻦ قد ﺃﻭﺻﻰ ﺑﻬﺎ ﻭﻻ ﺟﻌﻞ ﻟﻬﺎ ﻭﻗﻔﺎ ﻭ ﺃﺣﺐ ﺇﻧﺴﺎﻥ ﺃﻥ ﻳﻀﺤﻲ ﻋﻦ ﺃﺑﻴﻪ ﺃﻭ ﺃﻣﻪ ﺃﻭ ﻏﻴﺮﻫﻤﺎ ﻓﻬﻮ ﺣﺴﻦ. 📝 مجموع الفتاوى ٤٠/١٨. ጥያቄ ፦ 👉 ለሞተ ሰው ኡዱሒያ ማረድ ይቻላልን ? መልስ ፦ 🌴 ሟቹ ከገንዘቡ 1/3ኛ ላይ ተናዞ ከሆነ ወይም ለራሱ "ወቅፍ" አድርጎት ከነበረ አላፊነቱን በወሰደው አካል ላይ መፈፀሙ ግዴታ ይሆናል !!! 👉 ነገር ግን (ሟች) ያልተናዘዘም ወቅፍም ያላደረገ ሆኖ እያለ (ከቤተሰቡ የሆነ አካል) ለአባቱ ወይም ለእናቱ ወይም ለሌሎች ቤተሰቦቹ "ኡዱሒያ" ልረድ ቢል ይህ ያማረ ተግባር ነው !!! (መጅሙዓ ፈታዋ 18/40) ታላቁ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ https://t.me/amr_nahy1 … ኢስማኤል ወርቁ …
4212Loading...
05
የዘር ፍሬው የተኮላሸ... *ذبح الخصي في الأضحية؟* 📚 " الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله يجوز أن يذبح الخصي في الأضحية حتى إن بعض أهل العلم قد فضَّله على الفحل لأن لحمه يكون أطيب. 📝 مجموع الفتاوى ٢٥/ ٤٩/٥٠. ጥያቄ ፦ 👉 የዘር ፍሬው የተኮላሸ (የተቆረጠ) እንሰሳ ለኡዱሒያ እርድ ይበቃልን ? መልስ ፦ 👉 የዘር ፍሬው የተኮላሸ (የተቆረጠ) እንሰሳ ለኡዱሒያ እርድ ይበቃል። 👉 እንደሁም ከፊል ዑለማዎች (ጠንካራ) የዘር ፍሬ ካለው እንሰሳ አስበልጠውታል። ምክንያቱም ፦ ሥጋው የበለጠ ያማረ ነው በሚል ነው !!! (መጅሙዓ ፈታዋ 49፥50/25) (ታላቁ ኢማም ሸይኽ መሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) https://t.me/amr_nahy1 ... ኢስማኤል ወርቁ ...
1 6432Loading...
06
(አል-ኒሳእ (142)) አላህ ይጠብቀን !!!!! ይህው የሀገሬ ሰው ወግ ነውና "ሐጅ" አርጎ ሲመለስ ጥቂቱ ካልሆነ በስተቀር "ሐጂ" እና "ሐጀት" መባል ይወዳል‼️ካልተባለ ወይም እሱ "ሐረምን" እደዘየረው ሁላ እሱም ካልተዘየረ የሚከፋውም በርካታ ነው‼️ ወጣቱ ጋርም ስትመጣ ጥቂቱ አላህ ያዘነለት ሲቀር የሐረምን ቆይታ በፎቶና በድምፅ ቀርፆ ለወዳጆቹ በማጋራት አድናቆት እየተቸረ ሲኩራራ ይታያል‼️ 🔥 እንግዲህ ይህ ሁሉ ታይታና በራስ መደነቅ የሚያመጣው መዘዝ አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ አማኙ ባሪያ አላህን በአምልኮትና በመታገዝ ውስጥ ብቸኛ እንዳያደርግ ያደርገዋል❗️ ይህ ደሞ ሽርክ ላይ የሚጥል የልብ ህመም ነው። ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተሚያ ስለ ታይታና በራስ መደነቅ አስከፊነት ሲገልፅ እንዲህ ይላል ፦ قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله - 🔥 ... « فالرياء : من باب الإشراك بالخلق. والعجب : من باب الإشراك بالنفس. وهذا حال المستكبر ؛ فالمرائي لا يحقق قوله : «إياك نعبد»، والمعجب لا يحقق قوله : «وإياك نستعين»، فمن حقق قوله: «إياك نعبد»، خرج عن الرياء، ومن حقق قوله: «إياك نستعين»، خرج عن الإعجاب». [مجموع الفتاوى (١٠/ ٢٧٧)]. 👉 « ... (ሪያእ) "فالرياء" በፍጥረታት ከማጋራት አኳያ የሚሆን ሲሆን » 👉 « (ወል-ዐጀብ) " والعجب " « በነፍስ ከማጋራት አኳያ የሚሆን ነው። » ይህ ዓይነቱ ሰው ሁኔታው ኩራተኛ (እንደሆነ) ሰው ነው ‼️ 👉 (ፈል-ሙራኢ) "فالمرائي " ታይታን የሚፈልግ የሆነው ሰው «إياك نعبد» (አንተን ብቻ እንገዛለን። (እናመልካለን !!!) የሚለውን የአላህ ንግግር አያረጋግጥም‼️ 👉 (ወል-ሙዓጂብ) " والمعجب " በራሱ ነፍስ የሚደነቅ የሆነ ሰው «وإياك نستعين» ( በአንተ ብቻ እንታገዛለን !!! ) የሚለውን የአላህ ንግግር አያረጋግጥም‼️ 👉 (በእርግጥም) « إياك نعبد » የሚለውን የአላህ ንግግር ያረጋገጠ የሆነ ሰው ከ"ታይታ" ነፃ ወጥቷል !!! 👉 (በእርግጥም) «إياك نستعين» የሚለውን የአላህ ንግግር ያረጋገጠ የሆነ ሰው "በራስ ነፍስ ከመደነቅ" ነፃ ወጥቷል !!! [ሸኸል ኢስላም ኢብን ተሚያ] (መጅሙዓ ፈታዋ (277/10)) 👉👉👉 ወንድም እህቶች እንዲሁም እናት አባቶች “ሐጅ” ማለት ከ5ቱ የእስልምና መሠረቶች አንዱ ነው። ስለዚህ የእስልምናችን መሠረት እንዳይናጋ እንጠንቀቅ። ይህን ብዙ ሚልዮኖች እየቋመጡት ያላገኙት ዕድል እናንተ አግኝታቹታልና በአግባቡ ከታይታ እርቃቹ አላህን በመፍራት ተጠቀሙት። በባለፈው "ሐጅ" ይህን አጥፍቼ ፣ ስቼ ፣ ተሳስቼና ባለማወቄ "ሐጅ" የሰራው አልመሰለኝምና ዳግም ሌላ ጊዜ እደግመዋለሁ ብንል ሞትን ጨምሮ በሌሎች ብዙ ምክንያቶች ላይሆን ይችል ይሆናል ! ስለሆነም ይህ ሁሉ ታይታና ስሙልኝ ለማናችንም አይበጅምና ተደብቀን ለመኖር ጥረት እናድርግ በማለት አደራ እያልኩ ሰፊውን የተውሒድና የ“ሐጅ” አደራረግ ስርዓተ- ትምህርቶችን ጥረት በማድረግ እንማር እያልኩ በመልዕክተኛው ሐዲስ አጭሩን መልዕከቴን አበቃው‼️ وقال ﷺ : (من حج فلم يرفث ولم يفسق رجع كيوم ولدته أمه) 🌺 ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ፦ « (ከባለቤቱ ጋር) ግብረ-ሥጋ ግንኙነት ሳያደርግና "ወንጀልን" ሳይሰራ "ሐጅ" ያደረገና (ከዚያም አጠናቆ) የተመለሰ የሆነ ሰው ልክ እናቱ እንደወለደችሁ ዕለት ይሆናል !!! ይህ "ሐጁ" የነፃ (ተቀባይነት) ያለው ነው !!! » ታላቁ ኢማም ኢብን ባዝ ይህን ሐዲስ ሲቶረግሙ ተከታዩን አሉ ፦ 🌱 « ይህም "ሐጅ" ማለት እውነተኛ "ተውበት" ማድረግ አብሮት ያለው ማለት ነው። ወንጀልና ( ከባለቤቱ ጋር ) ግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አብሮት የለውም‼️ ይህ "ሐጅ" ንፅት ያለ ነው !!!!! ይህም ሰው በወንጀል ላይ ችክ ብሎ ከመዘውተር ሰላም የሆነ ነው !!! ... አዎ ! " አል-ሐጁ መብሩር " ሲባል የተፈለገበት በእርግጥም "ሐጅ " የሚያደርገው ሰው በወንጀል ላይ ሳይዘወትር አላህ ለሱ የስህተቱን " ተውበት " የተቀበለው ሰው ማለት ነው !!! (الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة) 👉👉👉 ታዲያ ወንጀል ሳይቀላቀልበትና ተሰርዞለት "ሐጅ" አርጎ “ጀነት” መግባት የሚጠላ አለን ? " እንዴታ ?? የለም እንጂ ... !!! " ስለዚህ በዚህ የተከበረ ስፍራ አላህን ማስወደድ ሲገባን አስቆጥተን ፎቶ (ቪዲዮ) መነሳትም ይሁን ማንሳት ተገደን ካልሆነ በስተቀር "ሐራም" ነው‼️ አላህ ለስራችን ኢኽላስን ይግጠመን !!! https://t.me/amr_nahy1 (… ኢስማኤል ወርቁ …)
3264Loading...
07
🕋 "ሐጅ" እና አስደንጋጩ "ሪያ"🔥 "ሪያ" ማለት ድቅድቅ ባለ ጥቁር ጨለማና ጥቁር ድንጋይ ላይ እንደሚሄድ ጥቁር ጉንዳን ድካው ስውር ነው ‼️‼️‼️ ታላቁ ሼይኽ ዶክተር ሷሊሕ ቢን ፈውዛን አል–ፈውዛን ሐጅ ላይ ፎቶ ስለመነሳት ተጠይቀው ሲመልሱ ተከታዩን ምክር ይሰጣሉ ፦ 👉 « ይህ ድርጊት እዩልኝ ከሚለው (የሽርክ ዓይነት) ውስጥ ይገባል !!! ያ "ሙሕሪም" ሆኖ የገዛ ራሱን ምስል የ"ዐረፋ" (ተራራ) ላይና "ካዕባ" (🕋) ዘንድ የሚቀርፅ የሆነ ሰው በ"ሐጅ" እና "ዑምራ" ላይ የሚሰራውን ስራና ትዕዛዛቶች ለሰዎች ማሳየት (የሚፈልግ) ሰው ነው‼️ የሰው ልጅ በተቻለው ያህል ስራውን መሰወር ነው ያለበት !!! (ስራውን) በእርሱና በአላህ መካከል ብቻ ያድርገው !!!!! » የሸይኽ ንግግር አበቃ። 👉 መቼስ ዐዋቂ ይናገር አይደለም የሚባለው ?‼️እኔ ተናግሬው ቢሆን እንኳን እሺ... ነብዩም ቢሆን የሰው ልጆችን ልብ ከፍተው ስላዩ ሳይሆን ከልዕለ አያሉና የሩቁን ዐዋቂ ከሆነው አምላክ አላህ የተገለጠላቸውን ነው የተናገሩት !!! 👉 ሸይኹም ቢሆን ከላይ እንዳየከው ለመምከር የሞከሩት ሐጅ ላይ ስላለው የሰዎች ሁኔታ በማስቀመጥ ጥቅል ምክር ነው የሰጡት እንጂ የሐጅ አምልኮት ላይ ፎቶ የሚነሱ ሰዎች ሽርክ ላይ ወድቀዋል አይደለም ያሉት !!! 👉 ነገር ግን በዒባዳ ቦታ ላይ "ዕዩኝ ማለት" አደገኛ ስለሆነ ይህን የመሰለ "ዒባዳ" በታይታ እንዳያበላሹትና ለቅጣት እንዳይዳረጉ እያስጠነቀቁ ነው‼️ 👉 ዑለማዎች ደሞ ከዚች አታላይ ዓለም ክፋት አስጠንቃቂ ባይሆኑ ኖሮ አንድም መልካም ሰው በምድር ላይ ባልኖረ ነበር !!! (( " قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِثْلُكُمْ يُوحَى إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَهُكُمْ إِلَهٌ وَاحِدٌ فَمَنْ كَانَ يَرْجُوا لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلاً صَالِحاً وَلا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَداً " )) [الكهف: 110]. « እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው ፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ (አል-ከህፍ (110)) (( " وعن أبي هريرة مرفوعا: قال تعالى: أنا أغنى الشركاء عن الشرك؛ من عمل عملا أشرك معي فيه غيري تركته وشركه " )) (رواه مسلم.) ከአቡ ሁረይራ እንደተወራው "መርፉዕ" በሆነ ሐዲስ አል-ቁድሲይ ላይ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ ፦ (( እኔ ከአጋሪዎችና ከሚያጋሩበት ሽርካቸው የተብቃቃው ነኝ !!! አንድ ስራን የሰራና በሰራው ስራ ውስጥ ከእኔ ጋር ሌላን ነገር ያጋራ የሆነ ሰው እሱንም ያጋራበትን ስራውንም እተወዋለሁ‼️)) (ሙስሊም ዘግቦታል።) (( " وعن أبي سعيد مرفوعا: ألا أخبركم بما هو أخوف عليكم عندي من المسيح الدجال؟ قالوا: بلى، قال: الشرك الخفي؛ يقوم الرجل فيصلي فيزين صلاته لما يرى من نظر رجل. ( رواه أحمد. ) ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ እንደተወራው "መርፉዕ" በሆነ ሐዲስ ላይ ነብዩ ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ፦ (( " አዋጅ ! እኔ ዘንድ ከመሲሕ አል-ደጃል የበለጠ አስፈሪ ስለሆነው ነገር አልነግራችሁምን ? (ሰሓባዎቹም እንዲህ አሉ ፦) እንዴታ ! ንገሩና ! እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦ « ስውሩን ሽርክ ነው‼️» ( ይህም ማለት ፦) « ሰውዬው ተነስቶ ይቆማል ! ሶላቱንም ይሰግዳል ! ለሚመለከተው ሰው እይታ ሲል ሶላቱን ያጌጠዋል‼️» 👉 ወንድሜ "ሪያ" ቀላል ወንጀል እንዳይመስለን... በጣም አደገኛ ነው‼️ ለዚህም ነበር ሰለፎች "ታይታን" እጅግ በጣም ከመፍራታቸው የተነሳ ይሰሩት የነበረውን መልካም ስራ በመደበቃቸው ማን እንደሰራው ይታወቅ የነበረው ከሞቱ በኋላ የነበረው። ለምን ??? ስራቸውን ሰዎች ማወቃቸው ኢኽላሳቸውን ያበላሽብናል በማለት ስለሚፈሩ ነው‼️ 👉 ከእውነተኛ ዒማን የሚመነጭ ድርጊት ከሆነ በትክክልም መልካም ስራን መደበቅ ነው !!! 👉 እኛ ግን እንደምንታየው የሰራናትን እያንዳንዷን መልካም ስራ ሰው እንዲያይልን እንፈልጋለን !!! 👉 በዚህም የተነሳ በምንሰራው ዒባዳ ልክ የልብ ጥፍጥና አጥተን ግራ ተጋብተናል !!! ምፅዋት እንሰጣለን እርካታ አይሰማንም‼️ ሶላት እንሰግዳለን እርካታ አይሰማንም‼️ "ሐጅ" እና "ዑምራ" እናረጋለን እርካታ አይሰማንም‼️... 👉 ግን ለምን ??? ሲባል። አብዛኞቻችን ሰርተን አላህን ከማስደሰት ይልቅ ለሰው ልጆች አሳይተን ጊዜያዊ ደስታን መጎንጨት ነው የምንፈልገው‼️ ለዚህም ነው ረሱል እንደነገሩን ዕለተ-ትንሳዔ በሚያሳቅቅ ሁኔታ የሰዎችን አድናቆትና ሙገሳ ፈልገክ ሰርተክ የምትፈልገውን አግኝተካልና ከኔ ዞር በል ተብሎ በኪሳራ ይመለሳል ያሉት ‼️ 👉 ታዲያ አላህ ፊቱን ያዞረበት ሰው ምን መሄጃ ይኖረው ይሆን ?‼️ 👉 መቼስ ውድ ወንድሜ እንዲሁም እህቴ እኔንም አንተንም አንቺንም ጨምሮ በምንሰራው ስራ "ሙኽሊስ" ነን ? ወይንስ አይደለንም ? ብለን ለራሳችን (ለነፍሳችን) ማለትና መጠየቅ (መገምገም) የሚችል ስነ-ልቦና እንኳን የለንም !!! 👉 ከቀደምት ሰለፎች ውስጥ የአንዳንዳቸውን ታሪካቸውን ስትሰማ " እኔ ለአላህ ብዬ ጥርት አርጌ ሶላትን አስተካክዬ ለመስገድ 20...ዓመትና ከዚያ በላይ ፈጀብኝ" ሲሉ ትሰማለክ !!! እኛስ አንድ ወር አከታትለን ከሰገድን... ነገሩ አበቃ !!! 👉 ይልቁንስ አንዳንድ የ"ዐቂዳ"ን ጥፍጥና በስሱም ቢሆን ያልቀማመሱ ሞኝ ወገኞች እንደሚሞግቱት " ኢማን በልብ ነው ! " እያልን የልብ ኢማን በውጫዊ ማንነት እንደማይገለፅ ነገር ከራሳችን አልፈን ለሰው ልጆች አመፅ ጠበቃ እንቆማለን !!! ጥሩም አይደል !!! ሞኝነት ይቅር !!! ተውሒድን እንማር !!! 👉 በአብዛኛው የ"ሐጅ" ስርዓትን የሚፈፅሙ ሰዎችን ስናይ በ"ዐረፋ" ተራራ ላይ ፥ በካዕባ ዙሪያ ... ፎቶ ሲነሱ የፈለጉበት ምንድነው ??? ፎቶውን በፍሬም አሰርተው ማስለቀሻ ማድረግ ፣ ወይም ልክ በአምልኮታቸው ግራ ተጋብተው እርካታ እንዳጡት ካፊሮች ቤታቸው ለመጣው ወዳጅ ዘመድ አልበም አሰርተውለት እንግድነቱን በፎቶ መቀበልና አድናቆትን ማግኘት ነው !!! 👉 ካልሆነ ፎቶ መነሳትና እዩልኝ እያሉ በሞባይል ላይ " ፕሮፋይል" ማድረግ በ"ሐጅ " ስነ-ስርዓት ላይ እንደሚፈፀሙት "ጠዋፍ" ማድረግ ፥ "ሰዒይ" ማድረግና ጠጠር የመወርወር ዓይነት የሚተገበር አንዱ ተግባር ሆኖ አይደለም‼️ ለዚህም ነው ጠቢቡ አምላክ እዩኝ የማለትን አደገኝነት ሲያወሳ መናፍቃኖች "ዒባዳ" ሲሰሩ የሚያሳዩትን ባህሪ በመግለፅ የመሰለው... (( " إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا " )) ((መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ (ይቀጣቸዋል)፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም፡፡ " ))
2602Loading...
08
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-3 ♻️ ክፍል ሦስት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
940Loading...
09
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-4 ♻️ ክፍል አራት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1100Loading...
10
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-² ♻️ ክፍል ሁለት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1080Loading...
11
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚 تيسر العلام في توضيح نواقض الإسلام               جمع وترتيب أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🌹ለሴቶች ከኅስር በኋላ የሚሰጥ ደርስ🌹 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ.³ ♻️ ክፍል-አንድ 🕋በመስጂደ ሱና{ወራቤ} حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/٢ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1560Loading...
12
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-¹ ♻️ ክፍል አንድ 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1200Loading...
13
ሌሎችንም ደርሶችን በአሏህ ፈቃድ በኡስታዝ -አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አል-ሐበሺይ አሏህ ይጠብቀውና በወራቤ ሱና-መስጅድ እየተሰጡ ያሉ ትምህርቶችን በቅደም ተከተል እንለቃለን።              🔍ተጠባበቁን🌐 -ሌላ ማሳሰቢያ ዛሬ እሁድ ከዙዑር በኋላ ወንዶችንም ሴቶችንም የሚያሰትፍ ልዩ የሆነ የሙሓደራ ፕሮግራም ይኖረናልና ሁላችሁም እንድትገኙ ከወዲው እናሳስባለን። የልቻለ 📡እንሞ https://t.me/mesjidalsunnabewerabe
1010Loading...
14
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚 المختصر في الآداب شرعية            للناشئين                                 جمع وترتيب أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى وأم سلمان الحبشية حفظهما الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ.³ ♻️ ክፍል-ሦስት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1380Loading...
15
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚 المختصر في الآداب شرعية            للناشئين                                 جمع وترتيب أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى وأم سلمان الحبشية حفظهما الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-² ♻️ ክፍል ሁለት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1170Loading...
16
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚 المختصر في الآداب شرعية للناشئين                                 جمع وترتيب أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى وأم سلمان الحبشية حفظهما الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-¹ ♻️ ክፍል አንድ 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1250Loading...
17
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-5 ♻️ ክፍል አምስት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
1070Loading...
18
ጆሮና ቀንዱ ከተቆረጠስ...??? *حكم الأضحية مقطوعة الأذن أو القرن ؟.* 📚 " الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله جائزة مجزئة لكنها مكروهة ؛ لأنها ناقصة الخلقة. 📝 مجموع الفتاوى ٤٠/٢٥. ጥያቄ ፦ 👉 "ጆሮው" ወይም "ቀንዱ" የተቆረጠ የቤት እንሰሳ ለ"ኡዱሒያ" እርድነትነት ያብቃቃልን ? መልስ ፦ 👉 ይቻላል ያብቃቃል። ነገር ግን የተጠላ ነው። ምክንያቱም ፦ አፈጣጠሩ ጎዶሎነት ያለው በመሆኑ ነው !!! (መጅሙዓ ፈታዋ 25/40) (ታላቁ ኢማም ሸይኽ መሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) https://t.me/amr_nahy1 ... ኢስማኤል ወርቁ ...
1480Loading...
19
🕋 ኡዱሂያና ድንጋጌዎቹ 🕋 💥 አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ቱሩፋት... 💥 ኡዱሂያ ምን ማለት ነው?...... 💥 የኡዱሂያ አራቱ ስሞች እነማን ናቸው ሁክሙስ ምንድነው?..... 💥 የኡድሂያ መስፈርቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ... 💥 ኡዱሂያ የተደነገገበት ጥበብ {ሂክማ} 🔖 የነብዩላህ ኢብራሂም እና ኢስማኢል ታሪክ በሰፊው የተዳሰሰበት መካሪ የሆነ ሙሓደራ። 🎙 በኡስታዝ አቡ ሙሰየብ ሃምዛ ቢን ረሻድ አላህ ይጠብቀው። 📅 እሁድ 26/10/2014E.C 📅 🕌 በፉርቃን መስጂድ {አለም ባንክ} ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇 📎 https://t.me/Adamaselefy/8010
1500Loading...
20
📢 ማሳሰቢያ ! ለ“ኡዱሒያ” ከብት ... ለምትገዙ ሁሉ... 📢 ለ"ኡዱሒያ" ከብት... ስትገዙ አስገዳጅ የሆኑት ቅድመ-ሁኔታዎችን እንዳትረሱ !!! 📚 " الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله أن تكون من بهيمة الأنعام : وهي الإبل والبقر والغنم أن تبلغ السن المعتبر شرعًا في الضأن : ستة أشهر وفي الماعز : سنة وفي البقر : سنتان وفي الإبل: خمس سنوات أن تكون سليمة من العيوب المانعة من الإجزاء وهي : العوراء البيِّن عورها... والمريضة البيّن مرضها والعرجاء البيِّن عرجها والعجفاء التي لا تُنقي ( ليس فيها مُخ ، لهزالها و ضعفها ). 📝 مجموع الفتاوى ٢٥/ ١٢-١٣. 👉 ለ"ኡዱሒያ" እርድ የሚሆነው የቤት እንሰሳ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው። 👉 “ግመል” “በሬ” “ላም” “ በግና ፊየል ” ናቸው። 🌴 በሸሪዓው ተቀባይነት ያለው ዕድሜ ላይ የደረሱ (መሆን አለባቸው !!!) 👉 በግ ( 6 ወር ) 👉 ፊየል ( 1 ዓመት ) 👉 በሬና ላም ( 2 ዓመት ) 👉ግመል ( 5 ዓመት ) ናቸው። 🌺 ለ"ኡዱሒያ" እርድነት እንዳይሆን ከሚከለክል ነውር ነገር (ጉድለት) ነፃ መሆን አለበት‼️ እነሱም ፦ ❌ በዓይኑ ላይ ግልፅ የሆነ (የመታወር) ችግር ካለበት... ❌ ግልፅ የሆነ በሽታ ያለበት ከሆነ ... ❌ ግልፅ የሆነ ስብራት (የአካል ጉድለት) ያለበት ከሆነ ... ❌ ደካማ ከመሆኑ የተነሳ መቅኔ የሌለው ሆና የሚያብቃቃ አጥጋቢ ሰውነት ከሌለው ... ለ"ኡዱሒያ" እርድነት አይበቃም‼️ (ታላቁ ኢማም ሸይኽ መሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) https://t.me/amr_nahy1 ... ኢስማኤል ወርቁ ...
4458Loading...
21
الرابع : الحرية ؛ فالرقيق المملوك لا يجب عليه الحج ؛ لأنه مملوك مشغول بسيده ، فهو معذور بترك الحج ، لا يستطيع السبيل إليه . 4ኛ. “ አል-ሑሪየቱ” ከባርነት ነፃ መሆን አለበት። ❌ ባሪያ የሆነ ሰው በእርሱ ላይ "ሐጅ" ግዴታ አይሆንበትም። ምክንያቱም ፦ በአስተዳዳሪ አለቃው ጉዳይ የተወጠረ ስለሆነ ነው። 👉 ለዚህ ሰው "ሐጅ" ላለማድረጉና ለመተው (በአለቃው ጉዳይ መወጠሩ) "ዑዝር" ምክንያት ይደረግለታል። "ሐጅ"ን ለማድረግ መንገዱን (ጣጣውን) አልቻለም ማለት ነው። الخامس : القدرة على الحج بالمال والبدن ؛ فإن كان الإنسان قادراً بماله دون بدنه ، فإنه ينيب من يحج عنه ؛ لحديث ابن عباس رضي الله عنهما : أن امرأة خثعمية سألت النبي صلى الله عليه وسلم فقالت : يا رسول الله ، إن أبي أدركته فريضة الله على عباده في الحج ، شيخا كبير لا يثبت على الراحلة ، أفأحج عنه ؟ قال (( نعم )) (208)، وذلك في حجة الوداع ففي قولها : أدركته فريضة الله على عباده في الحج ، وإقرار النبي صلى الله عليه وسلم إياها على ذلك ، دليل على أن من كان قادراً بماله دون بدنه ، فإنه يجب عليه أن يقيم من يحج عنه ، أما إن كان قادراً ببدنه دون ماله ، ولا يستطيع الوصول إلى مكة ببدنه ، فإن الحج لا يجب عليه . ومن القدرة : أن تجد المرأة محرما لها ، فإن لم تجد محرما ، فإن الحج لا يجب عليها ، لكن اختلف العلماء : هل يجب عليها في هذه الحال أن تقيم من يحج عنها أو يعتمر ، أو لا يجب ؟ على قولين لأهل العلم ؛ بناء على أن وجود المحرم هل هو شرط لوجوب الأداء ، أو هو شرط للوجوب من أصله ، والمشهور عند الحنابلة رحمهم الله : أن المحرم شرط للوجوب ، وأن المرأة التي لا تجد محرما ليس عليها حج ولا يلزمها أن تقيم من يحج عنها . فهذه شروط خمسة لوجوب الحج ، أعيدها فأقول : هي الإسلام ، والعقل ، والبلوغ ، والحرية ، والاستطاعة ، وهذه الشروط تشمل الحج والعمرة أيضا . فتاوى الحج الشيخ محمد بن صالح ابن عثيمين (أكثر من 300سؤال وجواب في المناسك 5ኛ. “ አል-ቁድረቱ ” ( "ሐጅ" ለማድረግ በገንዘብና በአካል መቻል ነው። 👉 አንድ ሰው ከአካሉ ውጪ በገንዘቡ ብቻ የቻለ ከሆነ ሌላ ሰው ይወክልና በውክልና "ሐጅ" ያስደርጋል። ይህም የሚሆነው ለኢብን ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ሐዲስ ሲባል ነው ፦ « አንዲት ከ"ኹስዓሚየተ" የሆነች ሴት ነብዩን ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ በማለት ጨየቀቻቸው።. አባቴ አላህ በባሪያው ላይ የደነገገው የ"ሐጅ" ግዴታ ደረሰችበት። በእርጅና ላይ ነው ያለው በመጓጓዣ ላይ እራሱን ችሎ አይቀመጥም። እኔ "ሐጅ" ላድርግለትን ? እርሳቸውም " አዎ ! (አድርጊለት) " አሏት። » ይህንንም ያሏት የመሰናበቻው "ሐጅ" ወቅት ላይ ነው። እቺ ሴት « አባቴ አላህ በባሪያው ላይ የደነገገው የ"ሐጅ" ግዴታ ደረሰችበት።» ማለቷና ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)ም የሷን ንግግር ማረጋገጣቸው አንድ በገንዘቡ "ሐጅ" ማድረግ የቻለ የሆነ ሰው በአካሉ "ሐጅ ማድረግ ባይችል ሌላን ሰው ወክሎ "ሐጅ" ማስደረግ ግዴታ እንደሚሆንበት አመላካች ነው። 👉 በአካሉ የቻለ ፤ ገንዘብ የሌለውና ወደ "መካ" በአካሉ መድረስ ያልቻለ ከሆነ በዚህ ሰው ላይ "ሐጅ" ግዴታ አይሆንበትም። ⛔️ ሌላው ከመቻል ውስጥ የሚገባው ፦ አንዲት ዕንስት "መሕረም" ማግኘቷ ነው። "መሕረም" ያላገኘች ከሆነ "ሐጅ" ግዴታ አይሆንባትም። ነገር ግን ዑለማዎች በዚህ ጉዳይ ተለያይተውበታል። ማለትም ፦ አንዲት ሴት "መሕረም" አጥታ በዚህ ሁኔታ ላይ ስትሆን "ሐጅ" እና "ዑምራ" የሚያደርግላት ሰውን ታድርግ ወይንስ ማድረጉ ግዴታ አይሆንባትም በሚል በዑለማዎች መሀል ሁለት ዓይነት ንግግር አለ። 👉 "ሐጅ"ን መፈፀም ግዴታ ለመሆኑ "መሕረም" የመገኘቱ መስፈርትነት ግዴታ ይሆናልን ? በሚልና (ለሴቲቱ) "መሕረም" መገኘቱ ከመሰረቱ ግዴታ የሆነ ነው በሚል ልዩነት ተገኘ። 👉 ( በዚህ ጉዳይ ላይ ) "ሐናቢላዎች" ዘንድ ( አላህ ይዘንላቸውና ) የሚታወቅ የሆነው አቋም ፦ "መሕረም" መገኘቱ ለ"ሐጅ" ግዴታነት መስፈርት ነው። አንዲት "መሕረም" የማታገኝ የሆነች ሴት በእርሷ ላይ "ሐጅ" ግዴታ አይሆንባትም። እንዲሁም "ሐጅ" የሚያደርግላት ሰው በማድረግ ላይም ግዴታ አይደረግባትም። 👉👉👉 እነዚህ አምስት መስፈርቶች "ሐጅ"ን ግዴታ የሚያደርጉ ናቸው። 🕋 በድጋሚ እንዲህ እላችዋለሁ ፦ 1ኛ. “ አል-ኢስላሙ ” ( ሙስሊም መሆን ) 2ኛ. “ አል-ዐቅሉ” ( አይምሮ ጤናማ መሆን ) 3ኛ. “ አል-ቡሉጉ ” ( ዕድሜው የደረሰ መሆን ) 4ኛ. “ አል-ሑሪየቱ ” ( ከባርነት ነፃ የሆነ መሆን) 5ኛ. “ አል-ኢስቲጣዓ ” ( ችሎታ ያለው መሆን ናቸው። ) 👉 እነዚህ መስፈርቶች ሐጅንም ይሁን ዑምራን የሚያካትቱ ናቸው። ((( ታላቁ ኢማም መሐመድ ሷሊሕ ኢብን ዑሰይሚን))) https://t.me/amr_nahy1 … ኢስማኤል ወርቁ …
3121Loading...
22
🕋 5. የ“ሐጅ” እና “ዑምራ” መስፈርቶች... شروط وجوب الحج والعمرة  السؤال (210 ) : فضيلة الشيخ ، ما هي شروط وجوب الحج والعمرة ؟ ጥያቄ ፦ የ“ሐጅ” እና “ዑምራ” መስፈርቶች ምንድናቸው ? الجواب : شروط وجوب الحج والعمرة خمسة ، مجموعة في قول الناظم : الحج والعمرة واجبـان        في العمر مرة بلا تواني بشرط إسلام كذا حرية            عقل بلوغ قدرة جليــة  فيشترط لوجوبه أولا : الإسلام ، فغير المسلم لا يجب عليه الحج ، بل ولا يصح منه لو حج ، بل ولا يجوز دخوله مكة ؛ لقوله تعالى : ( إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَذَا)(التوبة: 28 )، فلا يحل لمن كان كافراً بأي سبب كان كفره ، لا يحل له دخول حرم مكة . ولكن يحاسب الكافر على ترك الحج وغيره من فروع الإسلام على القول الراجح من أقوال أهل العلم ، لقوله تعالى : (إِلَّا أَصْحَابَ الْيَمِينِ) (39) ( فِي جَنَّاتٍ يَتَسَاءَلُونَ) (40) (عَنِ الْمُجْرِمِينَ) (41) (مَا سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ) (42) (قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ) (43) (وَلَمْ نَكُ نُطْعِمُ الْمِسْكِينَ) (44) (وَكُنَّا نَخُوضُ مَعَ الْخَائِضِينَ) (45) (وَكُنَّا نُكَذِّبُ بِيَوْمِ الدِّينِ) (46) (حَتَّى أَتَانَا الْيَقِينُ) (المدثر: 39 ، 47 ). መልስ ፦ 🕋 ግዴታ የሆኑ የ“ሐጅ” እና “ዑምራ” መስፈርቶች አምስት ናቸው። 👉 (እነሱም) በገጣሚው ስንኝ ውስጥ ተጠቃለው እንዲህ ተወስተዋል ፦ « “ሐጅ” እና “ዑምራ” ያለክፍተት (ያለመዘናጋት) በዕድሜ ውስጥ አንድ ጊዜ ግዴታ ናቸው። ( እሱም የሚሆነው ) በእስልምና መስፈርትነት እንዲሁም ከባርነት ነፃ መሆን ፤ የአይምሮ ጤነኝነት ፤ የዕድሜ መድረስና ግልፅ የሆነ ችሎታ ናቸው። 1ኛ. “አል-ኢስላሙ” እስልምና ግዴታ በመሆኑ መጀመሪያ መስፈርት ይደረጋል። ❌ ከሙስሊም ውጪ የሆነ ሰው ላይ "ሐጅ" ግዴታ አይሆንበትም። ❌ "ሐጅ" ቢያደርግም ትክክል አይሆንለትም❗️ ❌ እንደሁም "መካ" መግባት አይፈቀድለትም‼️ (ይህም የሆነው) ለአላህ ንግግር ሲባል ነው ፦ ((( እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፡፡ ))) (አል-ተውባ (28)) ❌ የክህደቱ ምክንያት ምንም ቢሆን "ካፊር" ከሃዲ የሆነ ሰው "ሐጅ ማድረግም ሆነ "ሐረም" (መካ) መግባት አይቻልለትም‼️ 👉 ይሁን እንጂ "ሐጅ"ንም ይሁን ሌሎች የእስልምና ድንጋጌዎችን ባለመተግበሩና በመተው የተነሳ በላጭ በሆነው የዑለማዎች ንግግር አላህ ዘንድ ይጠየቅበታል !!! (ይህም የሆነው) ለአላህ ንግግር ሲባል ነው ፦ ((( የቀኝ ባለቤቶች ብቻ ሲቀሩ፡፡ (እነርሱስ) በገነቶች ውስጥ ይጠያየቃሉ፡፡ ከአመጸኞቹ ኹነታ፡፡ (ይሏቸዋልም) « በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ ? » (እነርሱም) ይላሉ « ከሰጋጆቹ አልነበርንም፡፡ « ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡ « ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡ « በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡ « እርግጠኛው (ሞት) እስከ መጣን ድረስ፡፡ » አል-ሙደሲር 39/47 الشرط الثاني : العقل ؛ فالمجنون لا يجب عليه الحج ، فلو كان الإنسان مجنوناً من قبل أن يبلغ حتى مات ، فإنه لا يجب عليه الحج ولو كان غنياً . 2ኛ. “አል-ዐቅል” አይምሮው ጤናማ የሆነ ሰው መሆን አለበት። "እብደት" ያለበት የሆነ ሰው "ሐጅ" ግዴታ አይሆንበትም ! 👉 አንድ ሰው ዕድሜው ሳይደርስ በፊት ጀምሮ እስኪሞት ድረስ የአይምሮ ህመምተኛ ከሆነ "ሐጅ" ግዴታ አይሆንበትም። 👉 ይህ ሰው ሀብታም ቢሆንም "ሐጅ" ግዴታ አይሆንበትም !!! الثالث : البلوغ ؛ فمن كان دون البلوغ فإن الحج لا يجب عليه ، ولكن لو حج ، فحجه صحيح ، إلا أنه لا يجزئه عن فريضة الإسلام ، لقول النبي صلى الله عليه وسلم للمرأة التي رفعت إليه صبياً وقالت : ألهذا حج ؟ قال : (( نعم ولك أجر ))(207) ، لكنه لا يجزئه عن فريضة الإسلام لأنه لم يوجه إليه الأمر بها حتى يجزئه عنها ؛ إذا لا يتوجه الأمر إليه إلا بعد بلوغه . وبهذه المناسبة أحب أن أقول : إنه في المواسم التي يكثر فيها الزحام ، ويشق فيها الإحرام بالصغار ، ومراعاة إتمام مناسكهم ، فالأولى ألا يحرموا لا بحج ولا بعمرة ، أعني هؤلاء الصغار ؛ لأنه يكون فيه مشقة عليهم وعلى أولياء أمورهم ، وربما شغلوهم عن إتمام نسكهم ، أي : ربما شغل الأولاد آباءهم أو أمهاتهم عن إتمام نسكهم ، فبقوا في حرج ، وما دام الحج لا يجب عليهم ، فإنهم في سعة من أمرهم . 3ኛ. “አል-ቡሉግ” ለአቅመ- አደም የደረሰ መሆን አለበት። 👉 ዕድሜው ያልደረሰ ከሆነ ሐጅ" ግዴታ አይሆንበትም። ✅ ነገር ግን "ሐጅ" ቢያደርግ "ሐጁ" ትክክል ነው። ከእስልምናው ግዴታነት ግን አያብቃቃውም። ይህም ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ዕፃን ልጅን ይዛ ወደ እርሳቸው ልትጠይቃቸው ለሄደችው ዕንስት ለተናገሩት ንግግር ሲባል ነው ፦ እንዲህም አለቻቸው ፦ « “ ለዚህ ልጅ "ሐጅ" ይደረግለታልን ? ” እሳቸውም “ አዎ ! ምንዳው ለአንቺም ነው። ” አሏት። » ነገር ግን ከእስልምናው ግዴታነት ግን አያብቃቃውም። ምክንያቱም ፦ ( የእስልምና ድንጋጌው ) እስከ ሚያሰመነዳው ድረስ አይቅጣጨውምና ነው። (ይህም ማለት ፦) የእስልምና ድንጋጌው አይቅጣጨውም ዕድሜው ከደረሰ በኋላ ቢሆን እንጂ...(ማለት ነው።) 🌱 እኔም ከዚህ በመነሳት እንዲህ ማለት እወዳለሁ ፦ 👉 ይህ ቦታ (ጊዜ ) ግፊያ መጨናነቅ ከሚበዛባቸው ቦታዎች ውስጥ ነው። ዕፃናትን "ኢሕራም" ማስደረጉ ይከብዳል። አምልኮታቸውን አሟልተው እንዲያደረጉ መጠባበቁም አስቸጋሪ ነው። 👉 በላጭ የሚሆነው እነኚህን ዕፃናት "ሐጅ"ንም ይሁን "ዑምራ"ን “ኢሕራም” አለማስደረጋቸው ነው። ምክንያቱም ፦ ይህ ነገር በእነርሱም ላይ ይሁን በቤተሰቦቻቸው ላይ አስቸጋሪ ነገር አለው። አንዳንዴም አባትና እናታቸውን አምልኮታቸውን አሟልተው እንዲያስደርጉአቸው ይወጥሯቸዋል። በዚህም የተነሳ ወላጆች የተቸጋገሩ ሆነው ይቀራሉ ! "ሐጅ" እስከ ቀጠለ ጊዜ ድረስ በእነርሱ ላይ ግዴታ አይሆንም። እነርሱ በጉዳያቸው ሰፋ ያለ ሁኔት ላይ ናቸው።
2741Loading...
23
📻 تسجيلات مسجد السنة  بورابي   في الحبشة: يسرها أن تقدم لكم هذه المادة وهي عبارة عن خطبة جمعة 🎧 የመስጂደል ሱና ወራቤ የጁመዓ ኹጥባ 🔖 بعنوان:  عشر ذي الحجة وفضائلها 🔖 የዙልሂጃ እስር ቀናት  ደረጃ 🔜 በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ የጁመዓ ኹጥባ። 🎙 للأخ الفاضل الداعي إلى الله أبي سلمان فارس بن عبدالله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙️ በኡስታዝ አቡ ሰልማን ፋሪስ ብን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። 🗓️ سجلت يوم الجمعة في ٠١ ذي الحجة ١٤٤٥هـ في مسجد السنة ورابي في الحبشة حرسها الله تعالى 🗓️ ዙልሂጃ { 01-1445 ሂጅሪያ } አርብ በወራቤ መስጂድ ሱና  አላህ ይጠብቃት።
1341Loading...
24

25
📩 መልዕክት ⤵️⤵️⤵️ 🚘 ለዐረፋ በዓል ወደ ክፍለ ሀገር ተጓዦች። 🤝 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🔖 አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ እንኳን የ1445 ዓመተ ሒጅራ የዙልሒጃ የመጀመሪያ አስሩ ቀናቶች በሰላም አደረሳችሁ በማለት በተለያዩ የዒባዳ አይነቶች እንድትጠናከሩ ለማስታወስ ይወዳል። 💥 በመቀጠል አመት በዓሉን አስመልክቶ ለዚያራና ቤተሰብ ጥየቃ ወደ ተለያየ ቦታ እና ክፍለ-ሀገር የምትጓዙ ወንድምና እህቶች በሙሉ ስንጓዝ ሸሪዐን በጠበቀ መልኩ ሊሆን ይገባል። ወደ ቤተሰብ በምንጓዝበት ጊዜ ዓላማችን መብላትንና መጠጣት ላይ ብቻ ትኩረት ልናደርግ አይገባም። 💥 ስለዚህ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ትክክለኛውን እስልምና በሰለፎች ግንዛቤ ላልደረሳቸው ማህበረሰቦች የማድረስ ግዴታ ይጠበቅብናል። 💥 በመሆኑም የተለያዩ አጫጭርና ጠቃሚ የሆኑ ሪሳላዎች ማስቀራት የምንችል ኪታቦቹን በመያዝ ማህበረሰባችንን ልናስገነዝብ ይገባል። 💥 ይህንን ማድረግ የማንችል ከሆነ አልፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ እንደተለመደው ወቅቱን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኡስታዞቻችን ደርሶች ሙሀደራዎችንና እንዲሁም የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶችን በሚሞሪና በፍላሽ አዘጋጅቶ የሚጠብቃችሁ መሆኑን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው። 📮 ማሳሰብያ በራሳቸው ሚሞሪም ይሁን ፍላሽ በፈለጉት አይነትና መጠን ሲያስጭኑ ምንም አይነት ክፍያ የሌለው መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን። {ምንም እንኳን በራሳችን መጣራትንና ማድረስ ባንችል በሌሎች ወንድሞች በኩል እንዲደርስ ሰበብ ሆነን የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!} 🕌 አድራሻ አዲስ አበባ አለም-ባንክ ከፉርቃን መስጂድ ጎን ለጎን እንገኛለን። 💻 አልፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ የሰለፊዮች ልሳን!⤵️ 📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/16562
550Loading...
26
✅ ማታ በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ የነበረው ሙሓደራ ⤵️ 🔖 10ሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ‼️ 📌 በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት መካሪ የሆነ ሙሓደራ። 🎙 በኡስታዝ አቡ ሰልማን አብድልመጂድ አላህ ይጠብቀው። 🗓️ ዙል ሂጃ 01/1445 ሂ 🕌 በሱና መስጂድ #አዳማ ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇 https://t.me/Adamaselefy/7992
1753Loading...
27
በአስሩ ሌሊቶች እምላለሁ‼️ بسم الله الرحمن الرحيم 🌴 የአስሩ ቀናቶች ትልቅነት መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው !!! ወደ ኋላ ዘመን ተሻግሮ በታላቁ ነብይ ኢብራሂም ያማረ ጥሪና መስተንግዶ ደምቆ አምሮ ተውቦ ነበር !!! (( " وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ " )) (( " ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» (ባልነው ጊዜ አስታውስ)፡፡ " )) (አል-ሐጅ (26)) 👉 ይህ ለነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ብቻ ሳይሆን ለህዝባቸው ለኛም ጭምር የተሰጣ አስደማሚ ትውስታ ነው !!! እንዳንረሳ !! ውለታው ብዙ ተቆጥሮ የማይዘለቅ ነውና‼️ 👉 እኛ ግን ከዓለማት ሁሉ መርጦ የሰጠንን ፀጋ (ውለታን) ክደን ትዕዛዛቱን ከመፈፀም ወደ ኋላ አልን‼️ (( " وَآتَاكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ ۚ وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَتَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ الْإِنسَانَ لَظَلُومٌ كَفَّارٌ " )) (( " ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡፡ የአላህንም ጻጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ ሰው በጣም በደለኛ ከሓዲ ነው፡፡ " )) 🌺 አዛኙ አምላክ አላህ ለኛ ካለው እዝነትና ፣ ውዴታ የተነሳና ሊጠቅመንም በመፈለጉ ምንዳዉና ችሮታው የሚነባበርባቸዉን ቀናትና ጊዜያት አመላከተን፡፡ አስተዋይ ልቦና የሰጠው ሰው በትኩረት ይጠቀምባቸዋል፡፡ እንደዋዛ አያሳልፋቸዉም፡፡ 👉 ስለዚህ እኛም ከበዳይነትና የቸሩን አምላክ ስጦታ ከመካድ ወጥተን እንጠቀምባቸው !!! 👉 አስሩ ምርጥ ቀናቶችና ሌሊቶች ሊጀምሩ ቀናቶች ቀሩት፡፡ ስለ ምርጥነታቸው በቁርኣን ተመስክሮላቸዋል !!! አሸናፊው አምላክ አላህ ምሎባቸዋል ! « ... وَلَيَالٍ عَشْرٍ » « ... በአስሩ ሌሊቶች » ( እምላለሁ ፡፡ ) 🌴 የአላህን ቤት ጎብኚዎችም ወደ ተከበረዉና የተቀደሰው ሥፍራ መካ እና ዙርያው በመጉረፍ የሐጅን ስነ-ሥርዓት ያከናውኑባቸዋል፡፡ (( " وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ " )) « ... (አልነውም) ፦ በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡ » (አል-ሐጅ (27)) 👉 ከልብ ተፀፅቶ ወደ አላህ በመመለስ አላህን ማውሳት 👉 ፆም በመፆም ኢስቲግፋር ማብዛት ... 👉 ሰደቃ በማብዛት (መመጽወት...) 👉 "ዱዓ" በማድረግ (አላህን መለመን) ሶላትን በወቅቱና በጀመዓ በመስገድ ከተለያዩ ወንጀሎች መራቅ... 👉 ወደ አላህ መንገድ መጣራት ፤ ዝምድናን መቀጠል ! ለጎረቤት መልካም መዋል ! ወላጆችን ማስደሰት አስቸጋሪን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ፤ የታመሙ ሰዎችን መጎብኘት ፤ ወንድም እህቶችን በሌሉበት በዱዓ ማስታወስ ፤ የባለዕዳን ዕዳ መሰረዝ ወይም መክፈል ፤ የተቸገረን መርዳት ፤ የታሰረን መጠየቅ ፤ ሰዎችን አለማስቸገር ፤ ቤተሰብን መንከባከብ ፤ ለሠራተኞች ማዘን ... ላይ አደራ እንበርታ !!!!! 👉 ለመሆኑ እስልምና በዓመት ውስጥ ያሉትን ወራቶች እንዴት ነው የገለፃቸው ? (( " إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ وَقَاتِلُوا الْمُشْرِكِينَ كَافَّةً كَمَا يُقَاتِلُونَكُمْ كَافَّةً ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ " )) (( " የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ኾነው እንደሚዋጉዋችሁ በአንድ ላይ ኾናችሁ ተጋደሉዋቸው፡፡ አላህም ከሚፈሩት ጋር መኾኑን ዕወቁ፡፡ " )) (አል-ተውባ (36)) 👉 አላህ በዚህ ንግግሩ መገዳደልን እርም ያደረገባቸው የተከበሩ አራት ወራቶች ያላቸው ተከታዮቹ ናቸው ፦ « ረጀብ » « ዙል-ቃዒዳ » « ዙል-ሐጅ » እና « ሙሓረም » ናቸው !!! 👉 ዑለማዎች ሲያወሱ በነዚህ ወራቶች ውስጥ መገዳደልን ሐራም በማድረግ ያወጀበት ምክንያት ለአማኞች በተረጋጋ መንፈስ ሰላማዊ ሆነው ያለስጋት "ዑምራ" እና "ሐጅ" ... ለፈጣሪያቸው የሚዋደቁና የሚያጎበድዱ ሲሆን እንዲተገብሩም ነው !!! ታላቁ ኢማም ቢን ባዝ እንዲህ ይላሉ ፦ « ... فدل ذلك على أنه محرم فيها القتال، وذلك من رحمة الله لعباده؛ حتى يسافروا فيها، وحتى يحجوا ويعتمروا... » نشرت في مجلة (التوعية الإسلامية) العدد التاسع عام 1401هـ. (مجموع فتاوى ومقالات الشيخ ابن باز 18/ 433). « ...( በነዚህ ወራቶች) ውስጥ በሰው ልጆች መሀል መገዳደል እንዳይኖር በማድረግ የተከበሩ ወራት የመደረጋቸው ምክንያት አላህ ለባሪያዎቹ ካለው እዝነት በመነሳት በሰላም እንዲጓዙ ሐጅ እና ዑምራንም እንዲተገብሩም ነው... ( ኢማም ኢብን ባዝ... ) ( ለአማኞች ምቾትን ላደላደለው አዛኙ አምላክ ምስጋና ይገባው !!! )... 🌴 ዙል-ሐጅ ብሎ ማለት ደግሞ በዐረበኛ ወር አቆጣጠር 12ኛ ወር ሲሆን የዚህ ወር አስር ቀናት ልዩ ትሩፋት እንዳላቸው ነቢያችን ﷺ ተናግረዋል። እንደዚሁም ቁርአን ላይም እነዚህ ቀናቶች ተወስተዋል። 🌺 አላህ ጥራት የተገባው አምላክ ከፈጠራቸው ፍጡር ውስጥ አንዱን ከሌላኛው አበላልጧል። የረመዷን ወር ከወሮች ሁሉ በላጭ ነው። የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ሌሊቶች ከሌሊቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ምክንያቱ ደግሞ " ለይለተል ቀድር " በውስጧ ስላለ ነው። 🌴 የዙልሒጃ አስሩ ቀናት ደግሞ ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ለዚህም ነው ሸይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያ ረሒመሁላህ ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶች የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናቶች እንደሚበልጡና ከዙልሒጃ አስር ሌሊቶች ደግሞ የረመዷን አስር የመጨረሻ ለሊቶች እንደሚበልጡ የተናገረው። (መጅሙዓል ፈታዋ 25/287) 🌴 አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) በተከበረው ቁርአን ላይ እንዲህ ይላል ፦ { لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ }
3543Loading...
28
(( ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ )) (አል-ሐጅ (28)) 🌴 እነዚህ ቀናት ብሎ ማለት ዐብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንደገለፁት አስሩ የዙልሒጃ ቀናት እንደሆኑና በነሱም ላይ አላህን በጣም ማውሳት እንዳለብን ተናግረዋል። 🌴 ከዚህም በተረፈ ዐብደላህ ኢብን ዓባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ ባስተላለፈው ነቢያችን ﷺ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦ 🌴 [ ከዙልሒጃህ አስር ቀናቶች የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም። በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን ?! ተብለው ሲጠየቁ ፦ አዎ ! በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] (አል-ቡኻሪ 969) 🌴 ኢብኑረጀብ ረሒመሁላህ እነዚህ አስር ቀናት ከሌሎቹ ሊበልጡ የቻሉበት ምክንያት ሲናገሩ ፦ በጣም ዋና የሚባሉት የዒባዳ አይነት በአንድ ላይ ስለ ሚሰባሰቡበት ነው እነሱም ሰላት ፣ ፆም ፣ ሰደቃ እና ሐጅ ናቸው ብለዋል። (ፈትሑልባሪ ፥ 2/460) ◾️ዋና ዋና በዚህ ወር ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ውስጥ ፦ 🌺 ፈርድ ሰላትን ወቅት ጠብቆ መስገድ ይኖርብናል። ሱጁድ በማብዛት ወደ አላህ ( ሱብሓነሁ ወተዓላ) መቃረብ ተገቢ ነው። ነቢዩም ﷺ [ ሱጁድ በማብዛት ላይ አደራ አንተ እኮ ምንም ሱጁድ አታደርግም በሱጁዱህ ልክ አላህ ዘንድ ማዕረግህ ከፍ ቢል እና ወንጅልክም ቢራገፍልህ እንጂ ብለዋል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል). 👉 ሱና ሰላቶችንም ማብዛት ይጠበቅብናል። በተለይም 12ቱ "ራቲባ" የሚባሉትን እነሱም ፦ ከሱብሂ በፊት 2 ረከዓ ፣ ከዙሁር በፊት 4 ረከዓ , በኋላ 2 ረከዓ ፣ ከመግሪብ በኋላ 2 ረከዓ እና ከዒሻእ በኋላ 2 ረከዓ ናቸው። 🌺 ፆም መፆምም ተገቢ ነው። ከነዚህ አስር ቀናቶች የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆንባቸው ቀናቶች የሉም ! ፆም ደግሞ ከመልካም ስራ ስለሚገባ መፆም ተገቢ ነው። ኢማሙ ነወዊም አስሩ የዙልሂጃን ቀናት መፃም የጠበቀ ሱና ነው ብለዋል። 🌺 ሰደቃ በመስጠት ላይም መጠናከር ይኖርብናል። ምክንያቱም ፦ ወቅቱን መጠቀም ስላለብን ነው። ከምንሰጠው ሰው አንፃር ደግሞ ችግር ፣ መከራ ፣ ረሀብ ፣ መፈናቀል ፣ መሰደድ ፣ መታረዝ ፣ መታመም ... የበዛበት ጊዜ ላይ ነው ያለነውና በምፅዋት ላይ እንበርታ !!! 👉 ከንፉግነትና ስስታምነት በአላህ እንጠበቅ ለጋስ እንሁን !! እንድንድን ዘንዳ የነፍሳችንን ስስት እንጠንቀቅ‼️ይህ ደሞ አንሳሮች የተወደሱበት ልዩ ስብዕና ነው !!! (( " وَالَّذِينَ تَبَوَّءُوا الدَّارَ وَالْإِيمَانَ مِن قَبْلِهِمْ يُحِبُّونَ مَنْ هَاجَرَ إِلَيْهِمْ وَلَا يَجِدُونَ فِي صُدُورِهِمْ حَاجَةً مِّمَّا أُوتُوا وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ ۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ " )) (( " እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት ወደእነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡ " )) (አል-ሐሽር (9)) 🌺 " ተክቢር " እና " ተህሊልል"ን ማብዛትም ተገቢ ነው። ሰሓባዎችም በነዚህ ቀናት ውስጥ ተክቢርና ተህሊልን ያበዙ ነበር። በአሁን ሰአት ግን በጣም ከተረሳ ሱናዎች ውስጥ አንዱ ይህ ነው። ኢማም አል-ቡኻሪም እንዲህ ብለዋል ፦ ኢብኑ ዑመርና አቡ ሁረይራ ወደ ገበያ ቦታ በመውጣት በነዚህ ቀናቶች ውስጥ "ተክቢር" ይሉ ነበር። ሰዎችም በነሱ "ተክቢራ" ማለት ተነሳስተው " ተክቢራ" ይሉ ነበር። አባባሉም እንደሚከተለው ነው ፦ " አሏሁ አክበር " " አሏሁ አክበር " " ላኢላሀኢለላህ " " አሏሁ አክበር " " አሏሁ አክበር " " ወሊላሂል ሐምድ " 👉 ሌሎችንም በትክክለኛ ሐዲስ የተዘገቡ ተክቢራዎችን በማረጋገጥ ማለት ይቻላል። 🌺 ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀን ማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ ስለ ዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ (( " ያለፈውን ዓመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው " )) (ሙስሊም ዘግቦታል) 👉 በዚህም ቀን ላይ "ዱዓ"ን ማብዛት አስፈላጊ ነው። 🌺 ሌላኛው 10ኛው ቀን ላይ ሚተገበሩ ተግባሮች ናቸው። እነሱም ፦ ዒድ ሰላት መስገድ ፣ "ኡድሒያ"ን ማረድ ... ሐጅ ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ " ጀመራት " ይወረውራሉ ፣ ፀጉራቸውን ይላጫሉ ፣ "ሀድይ" የያዙ ሰዎች ሀድያቸውን ያርዳሉ ፣ ወደ መካ ተመልሰው " ጠዋፈል ኢፋዷ " ያደርጋሉ። በአጠቃላይ 10ኛው ቀን አላህ ዘንድ በጣም ትልቅ ነው !!! 🌺 ስለዚህ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በምናገኝበት ጊዜ ተውበት አድርገን ራሳችንን ለኸይር ስራ ዝግጁ አድርገን ከወንጀላችን ታቅበን ሌሎችንም ከዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ይሄን እድል እንዲጠቀሙ መገፋፋት ያስፈልጋል ። እንደዚህ አይነት ዕድል በሚመጣ ጊዜ ሳናውቀው ስለሚያልፈን መስነፍ አያስፈልግም መጠንከር እና ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። 🌺 በመጨረሻም አላህ የዙል-ሐጅ ቀናቶችን ተጠቅመው ምንዳ ከሚበዛላቸው ባሪያዎቹ ያድርገን !!! 🕋 የረቢ ! የተከበረውን ቤትክን አዘይረን !!!!! …ኢስማኤል ወርቁ… https://t.me/amr_nahy1
3111Loading...
29
በአስሩ ሌሊቶች እምላለሁ‼️ بسم الله الرحمن الرحيم 🌴 የአስሩ ቀናቶች ትልቅነት መገለጫዎቹ ብዙ ናቸው !!! ወደ ኋላ ዘመን ተሻግሮ በታላቁ ነብይ ኢብራሂም ያማረ ጥሪና መስተንግዶ ደምቆ አምሮ ተውቦ ነበር !!! (( " وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ " )) (( " ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» (ባልነው ጊዜ አስታውስ)፡፡ " )) (አል-ሐጅ (26)) 👉 ይህ ለነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ብቻ ሳይሆን ለህዝባቸው ለኛም ጭምር የተሰጣ አስደማሚ ትውስታ ነው !!! እንዳንረሳ !! ውለታው ብዙ ተቆጥሮ የማይዘለቅ ነውና‼️ 👉 እኛ ግን ከዓለማት ሁሉ መርጦ የሰጠንን ፀጋ (ውለታን) ክደን ትዕዛዛቱን ከመፈፀም ወደ ኋላ አልን‼️ (( " وَآتَاكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ ۚ وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَتَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ الْإِنسَانَ لَظَلُومٌ كَفَّارٌ " )) (( " ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡፡ የአላህንም ጻጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ ሰው በጣም በደለኛ ከሓዲ ነው፡፡ " )) 🌺 አዛኙ አምላክ አላህ ለኛ ካለው እዝነትና ፣ ውዴታ የተነሳና ሊጠቅመንም በመፈለጉ ምንዳዉና ችሮታው የሚነባበርባቸዉን ቀናትና ጊዜያት አመላከተን፡፡ አስተዋይ ልቦና የሰጠው ሰው በትኩረት ይጠቀምባቸዋል፡፡ እንደዋዛ አያሳልፋቸዉም፡፡ 👉 ስለዚህ እኛም ከበዳይነትና የቸሩን አምላክ ስጦታ ከመካድ ወጥተን እንጠቀምባቸው !!! 👉 አስሩ ምርጥ ቀናቶችና ሌሊቶች ሊጀምሩ ቀናቶች ቀሩት፡፡ ስለ ምርጥነታቸው በቁርኣን ተመስክሮላቸዋል !!! አሸናፊው አምላክ አላህ ምሎባቸዋል ! « ... وَلَيَالٍ عَشْرٍ » « ... በአስሩ ሌሊቶች » ( እምላለሁ ፡፡ ) 🌴 የአላህን ቤት ጎብኚዎችም ወደ ተከበረዉና የተቀደሰው ሥፍራ መካ እና ዙርያው በመጉረፍ የሐጅን ስነ-ሥርዓት ያከናውኑባቸዋል፡፡ (( " وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ " )) « ... (አልነውም) ፦ በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡ » (አል-ሐጅ (27)) 👉 ከልብ ተፀፅቶ ወደ አላህ በመመለስ አላህን ማውሳት 👉 ፆም በመፆም ኢስቲግፋር ማብዛት ... 👉 ሰደቃ በማብዛት (መመጽወት...) 👉 "ዱዓ" በማድረግ (አላህን መለመን) ሶላትን በወቅቱና በጀመዓ በመስገድ ከተለያዩ ወንጀሎች መራቅ... 👉 ወደ አላህ መንገድ መጣራት ፤ ዝምድናን መቀጠል ! ለጎረቤት መልካም መዋል ! ወላጆችን ማስደሰት አስቸጋሪን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ፤ የታመሙ ሰዎችን መጎብኘት ፤ ወንድም እህቶችን በሌሉበት በዱዓ ማስታወስ ፤ የባለዕዳን ዕዳ መሰረዝ ወይም መክፈል ፤ የተቸገረን መርዳት ፤ የታሰረን መጠየቅ ፤ ሰዎችን አለማስቸገር ፤ ቤተሰብን መንከባከብ ፤ ለሠራተኞች ማዘን ... ላይ አደራ እንበርታ !!!!! 👉 ለመሆኑ እስልምና በዓመት ውስጥ ያሉትን ወራቶች እንዴት ነው የገለፃቸው ? (( " إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ ۚ وَقَاتِلُوا الْمُشْرِكِينَ كَافَّةً كَمَا يُقَاتِلُونَكُمْ كَافَّةً ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ " )) (( " የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ኾነው እንደሚዋጉዋችሁ በአንድ ላይ ኾናችሁ ተጋደሉዋቸው፡፡ አላህም ከሚፈሩት ጋር መኾኑን ዕወቁ፡፡ " )) (አል-ተውባ (36)) 👉 አላህ በዚህ ንግግሩ መገዳደልን እርም ያደረገባቸው የተከበሩ አራት ወራቶች ያላቸው ተከታዮቹ ናቸው ፦ « ረጀብ » « ዙል-ቃዒዳ » « ዙል-ሐጅ » እና « ሙሓረም » ናቸው !!! 👉 ዑለማዎች ሲያወሱ በነዚህ ወራቶች ውስጥ መገዳደልን ሐራም በማድረግ ያወጀበት ምክንያት ለአማኞች በተረጋጋ መንፈስ ሰላማዊ ሆነው ያለስጋት "ዑምራ" እና "ሐጅ" ... ለፈጣሪያቸው የሚዋደቁና የሚያጎበድዱ ሲሆን እንዲተገብሩም ነው !!! ታላቁ ኢማም ቢን ባዝ እንዲህ ይላሉ ፦ « ... فدل ذلك على أنه محرم فيها القتال، وذلك من رحمة الله لعباده؛ حتى يسافروا فيها، وحتى يحجوا ويعتمروا... » نشرت في مجلة (التوعية الإسلامية) العدد التاسع عام 1401هـ. (مجموع فتاوى ومقالات الشيخ ابن باز 18/ 433). « ...( በነዚህ ወራቶች) ውስጥ በሰው ልጆች መሀል መገዳደል እንዳይኖር በማድረግ የተከበሩ ወራት የመደረጋቸው ምክንያት አላህ ለባሪያዎቹ ካለው እዝነት በመነሳት በሰላም እንዲጓዙ ሐጅ እና ዑምራንም እንዲተገብሩም ነው... ( ኢማም ኢብን ባዝ... ) ( ለአማኞች ምቾትን ላደላደለው አዛኙ አምላክ ምስጋና ይገባው !!! )... …ኢስማኤል ወርቁ… https://t.me/amr_nahy1 🌴 ዙል-ሐጅ ብሎ ማለት ደግሞ በዐረበኛ ወር አቆጣጠር 12ኛ ወር ሲሆን የዚህ ወር አስር ቀናት ልዩ ትሩፋት እንዳላቸው ነቢያችን ﷺ ተናግረዋል። እንደዚሁም ቁርአን ላይም እነዚህ ቀናቶች ተወስተዋል። 🌺 አላህ ጥራት የተገባው አምላክ ከፈጠራቸው ፍጡር ውስጥ አንዱን ከሌላኛው አበላልጧል። የረመዷን ወር ከወሮች ሁሉ በላጭ ነው። የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ሌሊቶች ከሌሊቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ምክንያቱ ደግሞ " ለይለተል ቀድር " በውስጧ ስላለ ነው። 🌴 የዙልሒጃ አስሩ ቀናት ደግሞ ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ለዚህም ነው ሸይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያ ረሒመሁላህ ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶች የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናቶች እንደሚበልጡና ከዙልሒጃ አስር ሌሊቶች ደግሞ የረመዷን አስር የመጨረሻ ለሊቶች እንደሚበልጡ የተናገረው። (መጅሙዓል ፈታዋ 25/287) 🌴 አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) በተከበረው ቁርአን ላይ እንዲህ ይላል ፦
10Loading...
30
{ لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ } (( ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ )) (አል-ሐጅ (28)) 🌴 እነዚህ ቀናት ብሎ ማለት ዐብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንደገለፁት አስሩ የዙልሒጃ ቀናት እንደሆኑና በነሱም ላይ አላህን በጣም ማውሳት እንዳለብን ተናግረዋል። 🌴 ከዚህም በተረፈ ዐብደላህ ኢብን ዓባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ ባስተላለፈው ነቢያችን ﷺ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦ 🌴 [ ከዙልሒጃህ አስር ቀናቶች የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም። በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን ?! ተብለው ሲጠየቁ ፦ አዎ ! በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] (አል-ቡኻሪ 969) 🌴 ኢብኑረጀብ ረሒመሁላህ እነዚህ አስር ቀናት ከሌሎቹ ሊበልጡ የቻሉበት ምክንያት ሲናገሩ ፦ በጣም ዋና የሚባሉት የዒባዳ አይነት በአንድ ላይ ስለ ሚሰባሰቡበት ነው እነሱም ሰላት ፣ ፆም ፣ ሰደቃ እና ሐጅ ናቸው ብለዋል። (ፈትሑልባሪ ፥ 2/460) ◾️ዋና ዋና በዚህ ወር ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ውስጥ ፦ 🌺 ፈርድ ሰላትን ወቅት ጠብቆ መስገድ ይኖርብናል። ሱጁድ በማብዛት ወደ አላህ ( ሱብሓነሁ ወተዓላ) መቃረብ ተገቢ ነው። ነቢዩም ﷺ [ ሱጁድ በማብዛት ላይ አደራ አንተ እኮ ምንም ሱጁድ አታደርግም በሱጁዱህ ልክ አላህ ዘንድ ማዕረግህ ከፍ ቢል እና ወንጅልክም ቢራገፍልህ እንጂ ብለዋል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል). 👉 ሱና ሰላቶችንም ማብዛት ይጠበቅብናል። በተለይም 12ቱ "ራቲባ" የሚባሉትን እነሱም ፦ ከሱብሂ በፊት 2 ረከዓ ፣ ከዙሁር በፊት 4 ረከዓ , በኋላ 2 ረከዓ ፣ ከመግሪብ በኋላ 2 ረከዓ እና ከዒሻእ በኋላ 2 ረከዓ ናቸው። 🌺 ፆም መፆምም ተገቢ ነው። ከነዚህ አስር ቀናቶች የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆንባቸው ቀናቶች የሉም ! ፆም ደግሞ ከመልካም ስራ ስለሚገባ መፆም ተገቢ ነው። ኢማሙ ነወዊም አስሩ የዙልሂጃን ቀናት መፃም የጠበቀ ሱና ነው ብለዋል። 🌺 ሰደቃ በመስጠት ላይም መጠናከር ይኖርብናል። ምክንያቱም ፦ ወቅቱን መጠቀም ስላለብን ነው። ከምንሰጠው ሰው አንፃር ደግሞ ችግር ፣ መከራ ፣ ረሀብ ፣ መፈናቀል ፣ መሰደድ ፣ መታረዝ ፣ መታመም ... የበዛበት ጊዜ ላይ ነው ያለነውና በምፅዋት ላይ እንበርታ !!! 👉 ከንፉግነትና ስስታምነት በአላህ እንጠበቅ ለጋስ እንሁን !! እንድንድን ዘንዳ የነፍሳችንን ስስት እንጠንቀቅ‼️ይህ ደሞ አንሳሮች የተወደሱበት ልዩ ስብዕና ነው !!! (( " وَالَّذِينَ تَبَوَّءُوا الدَّارَ وَالْإِيمَانَ مِن قَبْلِهِمْ يُحِبُّونَ مَنْ هَاجَرَ إِلَيْهِمْ وَلَا يَجِدُونَ فِي صُدُورِهِمْ حَاجَةً مِّمَّا أُوتُوا وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ ۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ " )) (( " እነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት ወደእነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡ " )) (አል-ሐሽር (9)) 🌺 " ተክቢር " እና " ተህሊልል"ን ማብዛትም ተገቢ ነው። ሰሓባዎችም በነዚህ ቀናት ውስጥ ተክቢርና ተህሊልን ያበዙ ነበር። በአሁን ሰአት ግን በጣም ከተረሳ ሱናዎች ውስጥ አንዱ ይህ ነው። ኢማም አል-ቡኻሪም እንዲህ ብለዋል ፦ ኢብኑ ዑመርና አቡ ሁረይራ ወደ ገበያ ቦታ በመውጣት በነዚህ ቀናቶች ውስጥ "ተክቢር" ይሉ ነበር። ሰዎችም በነሱ "ተክቢራ" ማለት ተነሳስተው " ተክቢራ" ይሉ ነበር። አባባሉም እንደሚከተለው ነው ፦ " አሏሁ አክበር " " አሏሁ አክበር " " ላኢላሀኢለላህ " " አሏሁ አክበር " " አሏሁ አክበር " " ወሊላሂል ሐምድ " 👉 ሌሎችንም በትክክለኛ ሐዲስ የተዘገቡ ተክቢራዎችን በማረጋገጥ ማለት ይቻላል። 🌺 ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀን ማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ ﷺ ስለ ዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ (( " ያለፈውን ዓመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው " )) (ሙስሊም ዘግቦታል) 👉 በዚህም ቀን ላይ "ዱዓ"ን ማብዛት አስፈላጊ ነው። 🌺 ሌላኛው 10ኛው ቀን ላይ ሚተገበሩ ተግባሮች ናቸው። እነሱም ፦ ዒድ ሰላት መስገድ ፣ "ኡድሒያ"ን ማረድ ... ሐጅ ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ " ጀመራት " ይወረውራሉ ፣ ፀጉራቸውን ይላጫሉ ፣ "ሀድይ" የያዙ ሰዎች ሀድያቸውን ያርዳሉ ፣ ወደ መካ ተመልሰው " ጠዋፈል ኢፋዷ " ያደርጋሉ። በአጠቃላይ 10ኛው ቀን አላህ ዘንድ በጣም ትልቅ ነው !!! 🌺 ስለዚህ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በምናገኝበት ጊዜ ተውበት አድርገን ራሳችንን ለኸይር ስራ ዝግጁ አድርገን ከወንጀላችን ታቅበን ሌሎችንም ከዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ይሄን እድል እንዲጠቀሙ መገፋፋት ያስፈልጋል ። እንደዚህ አይነት ዕድል በሚመጣ ጊዜ ሳናውቀው ስለሚያልፈን መስነፍ አያስፈልግም መጠንከር እና ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። 🌺 በመጨረሻም አላህ የዙል-ሐጅ ቀናቶችን ተጠቅመው ምንዳ ከሚበዛላቸው ባሪያዎቹ ያድርገን !!! 🕋 የረቢ ! የተከበረውን ቤትክን አዘይረን !!!!! …ኢስማኤል ወርቁ… https://t.me/amr_nahy1
10Loading...
31
📢 ለሙስጠፋ ምክር ከዐዋቂ... ሙስጠፋ አል-ሐበሺይ አላህ ያስተካክለው! አላህ ይምራው! ወደ ዑለማዎች በመመለስ ወገንተኛ ባለመሆን የማይመለከተውን ነገር መፍራት (ሲገባው) ወደ ጉዳት በሚመልሰውና ዝምታ በሚሰፋው ርዕስ ላይ የገዛ ነፍሱን ፈተነ!...(እሱ) ተማሪ ነው! ወደ ዑለማዎች ፈላጊ ሲሆን...ዕውቀትን ሊማር ይገባዋል! ዕውቀትን ፍለጋ ሊጓዝ ይገባል! 👉 ወደ ዕውቀት ባለቤቶች የተጓዘና ጉልበቱን ከዑለማዎች ፊት ያንበረከከ የሆነ ሰው የዕውቀትንና የራሱን ልክ ያውቃል! እንዲሁም የዑለማዎችን የመሻይኾችንና የተጣሪዎችን ልክም ያውቃል! ነገራቶችን ስርዓት ያሲዛል! ንግግሩን ይመዝናል! ከኋላ ተከትሎ የሚመጣውንም ያውቃል! 🔥 በውስጡ ማሽሟጠጥ መቀለድና ማነወር ያለበት የሆኑ ንግግሮች (ተንፀባርቀውበታል።) ⛔️ በኢማሙ አልባኒ በሸይኽ አቡ ቢላልና በሌሎች የሱና መሻይኾች ላይ እንዳላገጠ ተረጋግጧል❗️ የምንመክረው ሲሆን እንፈልገዋለን! ...እንዲመለስ የምንከጅል ሲሆን እንመክረዋለን! በሩ ክፍት ነው! ምክር ሊሰማ ይገባዋል! ወደ ሱኒዮች ረድፍ ይመለስ! ከሌላው ይልቅ በእርሱ ላይ የራሩለትና የሚያዝኑለት ወደ ሆኑት ወንድሞቹ ይመለስ! ለእርሱ ጥቂት ተካቶዮች አሉት ይሁንንና በዙ ተከታይ ያለው ቢሆንም... የበላይነት አትያዘው! ወደ “ሐቅ” መመለስ ብልጫ ነው! ለ“ሐቅ” ባልተቤቶች ለ“ሐቅ”ና ለዕውቀት ባልተቤቶች ይተናነስ! መጨረሻው መልካም ነውና። ⛔️ ሁኔታው (ሲታይ) ምላሽ ይፈልጋል ይሁን እንጂ እንዲመለስ እንመክረዋለን። 👉 በገዛ ነፍሱና በዳዕዋው ላይ አላህን ይፍራ! የሱና ባለቤቶች ይመክራሉ ይራራሉም! ከዚያ ግን በጥፋቱ ... ይዋረድና ይኮላሻል! ⛔️ አንድም ሰው አህሉል ሱናና ሊያነውር አይችልም‼️ (ሸይኽ አድናን) https://t.me/amr_nahy1 … ኢስማኤል ወርቁ …
2318Loading...
32
🕋 4. ሐጅን በፍጥነት ወይንስ ... السؤال (209 ) : فضيلة الشيخ ، وجوب الحج هل هو على الفور ، أم على التراخي؟ ጥያቄ ፦ የ"ሐጅ" ግዴታነት (ተፈፃሚ የሚደረገው) በፍጥነት ነውን ወይንስ በጊዜ ክፍተት ውስጥ ነው ? الجواب : الصحيح أنه واجب على الفور ، وأنه لا يجوز للإنسان الذي استطاع أن يحج إلى بيت الله الحرام أن يؤخره ، وهكذا جميع الواجبات الشرعية ، إذا لم تقيد بزمن أو سبب ، فإنها واجبة على الفور . فتاوى الحج الشيخ محمد بن صالح ابن عثيمين (أكثر من 300سؤال وجواب في المناسك መልስ ፦ 🕋 ትክክለኛው የሚሆነው “ሐጅ”ን በፍጥነት መተግበር ነው። ❌ ለሰው ልጅ ወደ አላህ ቤት "ሐጅ" ማድረግ እስከቻለ ድረስ ማዘግየት አይቻልለትም‼️ 👉 ግዴታ የተደረጉ አጠቃላይ ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች ልክ እንደዚሁ ናቸው !!! 👉 በግዜ ወይም በምክንያት የተገደበ ካልሆነ በስተቀር (እቺህ አምልኮት) በፍጥነት መተግበሯ ግዴታ ነው !!! ((( ታላቁ ኢማም መሐመድ ሷሊሕ ኢብን ዑሰይሚን))) https://t.me/amr_nahy1 … ኢስማኤል ወርቁ …
2401Loading...
33
🌼 የምድራችን ምርጥ ቀኖች... 👉 1️⃣0️⃣ ሩ የዙል-ሐጅ ውድ ቀኖች ዛሬ ጀመሩ !!! (ለዓለማቱ ጌታ አላህ ምስጋና ይገባው ! ... « አላህ ዘንድ በዱኒያ ዓለም በላጭ የሆነው ቀን የዙል-ሒጃ 10 ቀናቶች ናቸው !!! »... (((ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም))) ( አቢ ማሊክ ሳቢር አል-ሊሒጂ) https://t.me/amr_nahy1 … ኢስማኤል ወርቁ …
4112Loading...
34
لدخوله في الأعمال الصالحة؛ ✍" فعن هنبدة بن خالد عن امرأته عن بعض أزواج النبي صلى الله عليه وسلم قالت: «كان النبي صلى الله عليه وسلم يصوم تسع ذي الحجة، ويوم عاشوراء، وثلاثة أيّام من كل شهر».  رواه أحمد وأبو داود والنسائي وغيرهم رحمهم الله . ✍" وقال الإمام النووي رحمه الله عن صوم أيّام العشر أنّه مستحب استحباباً شديداً. 2ኛ. ፆም 👉 (ፆም ከመልካም ስራዎች ውስጥ የሚካተት በመሆኑ ነው።) « ሀንበደተ ቢን ኻሊድ ከባለቤቱ እርሷ ደሞ ከከፊል የረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ባልተቤቶች በመያዝ እንዲህ አለች ፦ 👉 « " ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የዙል-ሒጃን ዘጠነኛውን (9ኛውን) ቀን ፥ የዐሹራን ቀን እና በየወሩ ሦስት ቀን ይፆሙ ነበር። " » ኢማሙ አሕመድ ፣ አቡ ዳውድ ፣ ነሳኢ ሌሎችም (አላህ ይዘንላቸውና) ዘግበውታል ። 👉 ኢማሙ ነወዊ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ አሉ ፦ " የዙል-ሒጃን አስር ቀናቶች መፆም ጠንከር ያለ መወደድን ይወደዳል !! " 3⃣  التكبير والتهليل والتحميد: 👈 "  لما ورد في حديث ابن عمر رضي الله عنهما السابق: «فأكثروا من التهليل والتكبير والتحميد» 3ኛ. " አላህ ዋክበር " " ላሂላሂለላህ " እና " አልሓምዱሊላሂ " ማለት (ይገባል።) ያሳለፍነው የሆነው የኢብን ዑመር "ሐዲስ"ም ስለመጣ... 👉 « " ላሂላሂለላህ "  " አላህ ዋክበር " እና " አልሓምዱሊላሂ " ማለት አብዙ !! » ✍"  وقال الإمام البخاري رحمه الله: "كان ابن عمر وأبو هريرة رضي الله عنهما يخرجان إلى السوق في أيّام العشر يكبران ويكبر النّاس بتكبيرهما"، ኢማሙ ቡኻሪ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ አሉ ፦ 👉 " ኢብን ዑመርና አቡ ሁረይራ በአስሩ የዙል-ሒጃ ቀናቶች ውስጥ ወደ ገበያ ቦታ ይሄዱና " ተክቢራ " ያደርጉ ነበር። ( " አላህ ዋክበር " ይሉ ነበር።) ሰዎችም አብረዋቸው ይላሉ። " ✍ " وقال أيضًا: "وكان عمر يكبر في قبته بمنى فيسمعه أهل المسجد فيكبرون ويكبر أهل الأسواق حتى ترتج منى تكبيراً". ኢማሙ ቡኻሪ በድጋሚ እንዲህ አለ ፦ 👉 « ዑመር "ሚና" ላይ በቁባ ውስጥ "ተክቢራ" ያደርግ ነበር። የመስጂዷም ሰዎች ይሰሙታል ፤ (ከዚያም) እነሱም "አላህ ዋክበር" ይላሉ ፤ ግብይይት ቦታ ላይም ያሉትም ሰዎች (ይሰሙና) "ሚና" በተክቢራው እስከ ምትንቀጠቀጥ ድረስ  አብረው ይላሉ !!! » 👈" وكان ابن عمر رضي الله عنهما يكبر بمنى تلك الأيّام، وخلف الصلوات وعلى فراشه، وفي فسطاطه، ومجلسه، وممشاه تلك الأيّام جميعا، والمستحب الجهر بالتكبير لفعل عمر وابنه وأبي هريرة رضي الله عنهم أجمعين .. ኢብን ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) በነዚህ ቀናቶች ውስጥ በሚና ላይ "ተክቢራ" ያደርግ ነበር ። 👉 « እንዲሁም ከሶላት በኋላ ምንጣፉ ላይ (ባለበት) ፥ በድንኳኑ ውስጥ ፥ በሚቀመጥበት ቦታውና በሚሄድበት ቦታ ባጠቃላይ በነዚህ ቀናቶች ውስጥ "ተክቢራ" (ያደርግ ነበር ።) » ዑመር ፣ የዑመር ልጅ (አብደላ) ፣ አቡ ሁረይራ አጠቀላይ ሁላቸውም አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና የተገበሩት ከመሆኑ የተነሳ (ተክቢራው ሲደረግ) ድምፅን ከፍ ማድረግ ይወደዳል። 👈 " وحري بنا نحن المسلمين أن نحيي هذه السنة التي قد أضيعت في هذه الأزمان، وتكاد تنسى حتى من أهل الصلاح والخير -وللأسف- بخلاف ما كان عليه السلف الصالح .. 👉 በእኛ ላይ የተገባ ይሆናል !! እኛ ሙስሊሞች ነን !!! በእርግጥም በዚህ ዘመን የጠፋች የሆነችውን "ሱና" ሕያው ልናረጋት የተገባ ይሆናል !!! 👉 ከሚያሳዝነው ነገር (እቺ "ሱና" " ተክቢራዋ " ) የጥሩነትና የመልካምነት ባልተቤት የሆኑ ሰዎች ዘንድ (ሳይቀር) ቀደምት ደጋግ ሰዎች ከነበሩበት በተቃራኒው ልትረሳ ቀርባለች !!! ‼️ 👈 " صيغة التكبير : ورد فيها عدة صيغ مروية عن الصحابة والتابعين منها: ☝ - الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر كبيرًا. ☝ - الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلاّ الله، والله أكبر، والله أكبر، ولله الحمد. ☝ - الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلاّ الله، والله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد. 👉 (ተክቢራ አደራረጉን (በተመለከተ) ከሰሃባዎችና ከተሃቢዮች የተወራ ሲሆን የተወሰነ የአደራረግ ዓይነት መጥቷል። ከነሱ ውስጥም ☝ " አላህ ዋክበር " , " አላህ ዋክበር " , " አላህ ዋክበር ከቢራ !!! " ☝ " አላህ ዋክበር " , " አላህ ዋክበር " ," ላሂላሂለላህ " , " ወላሁ አክበር " , " ወላሁ አክበር " , " ወሊላሂል ሐምድ !!! " ☝ " አላህ ዋክበር " , " አላህ ዋክበር " , " አላህ ዋክበር " , " ላሂላሂለላሁ " , " ወላሁ አክበር " , " ወላሁ አክበር " , " ወሊላሂል ሐምድ !!! " 4⃣ صيام يوم عرفة: 👈"  يتأكد صوم يوم عرفة، لما ثبت عنه صلى الله عليه وسلم أنّه قال عن صوم يوم عرفة: «أحتسب على الله أن يكفر السنة التي قبله والسنة التي بعده» رواه مسلم رحمه الله . 4ኛ. የ"ዐረፋ" ዕለት ፆም 👉 የ"ዐረፋ" ዕለትን መፆም ጠንከር ይደረጋል !! ከረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተረጋግጦ ለመጣው "ሐዲስ " ሲባል ፤ እሳቸውም የ" ዐረፋ" ዕለትን መፆም በተመለከተ እንዲህ አሉ ፦ (( " ከ" ዐረፋ" በፊትና በኋላ ያለውን ዓመት ወንጀል እንዲሰርዝ አላህን እተሳሰባለሁ ! " )) ኢማሙ ሙስሊም (አላህ ይዘንላቸውና) ዘግበውታል። ✋ " لكن من كان في عرفة حاجاً فإنّه لا يستحب له الصوم، لأنّ النبي ﷺ وقف بعرفة مفطراً. ✋ ነገር ግን በዐረፋው ጊዜ ሐጅ ላይ ከነበረ ለርሱ መፆሙ አይወደድም !! ምክንያቱም ፦ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ያፈጠሩ (ያልፆሙ) ሲሆን " ዐረፋ " ላይ ቆመው ነበር። ☝ وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين. 📚 " الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله የአላህ ሶላትና ሰላም በነብያችን ሙሐመድ እንዲሁም ባጠቃላይ ቤተሰቦቻቸውና ባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን !!! ታላቁ ኢማም ሸይኽ መሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) https://t.me/amr_nahy1 ... ኢስማኤል ወርቁ ...
6407Loading...
35

190Loading...
36
🌱 የምድራችን ምረጥ ቀናቶች... بسم الله الرحمن الرحيم #خير_ايام_الدنيا_اقبلت 📝 فضل العشر من ذي الحجة !!! السؤال ✍ ما هو فضل أيّام عشر ذي الحجة؟ ጥያቄ ፦ አስሩ የዙል-ሒጃ ቀናት ያለው ብልጫ ምንድነው ? "الإجابــة ":- ✍ " الحمد لله ربّ العالمين، والصلاة والسلام على سيد المرسلين وبعد . 👈 " فإنّ من فضل الله ومنته أن جعل لعباده الصالحين مواسم يستكثرون فيها من العمل الصالح، ومن هذه المواسم عشر ذي الحجة. 🌺 ለዓለማቱ ጌታ አላህ ምስጋና ይገባዋል ! ሶላትና ሰላም የመልዕክተኞች አለቃ በሆኑት (ነብይ) ላይም ይሁን !!! 👉 ከዚህም በማስከተል ፦ 🌴 ከአላህ ትሩፋትና ፀጋ ውስጥ ለመልካምና ደጋግ ባሪያዎቹ መልካም ሥራን የሚያበዙትን ጊዜ ማድረጉ ነው። 👉 ከነዚህም ጊዜያቶች ውስጥ አስሩ የዙል-ሒጃ ቀናቶች (ተጠቃሽ ናቸው።) 👈 " فضـلها ✍ وقد ورد في فضلها أدلة من الكتاب والسنة منها: 👉 ያለው ብልጫ ፦ በእርግጥም በ"ቁርአን"ና በ"ሐዲስ" ውስጥ ( አስሩን የዙል-ሒጃ ቀናቶች ) (አስመልክቶ) ያላቸውን ብልጫ መረጃ መጥቷል። 👉 ከነዚህም መረጃዎች ውስጥ ፦ 1⃣ قال تعالى: {وَالْفَجْرِ . وَلَيَالٍ عَشْرٍ} [الفجر ١٢]، 📮" قال ابن كثير رحمه الله: "المراد بها عشر ذي الحجة كما قاله ابن عباس وابن الزبير رضي الله عنهما ومجاهد وغيرهم رحمهم الله ". 1ኛ. አላህ እንዲህ ይላል ፦ (( " በዐሥሩ ሌሊቶችም (እምላለሁ።)) (አል-ፈጅር (2)) ኢብን ከሲር አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ ፦ 👉 በዚህ (የቁርኣን አንቀፅ) የተፈለገበት አስሩን የዙል-ሒጃ ቀናቶች ነው። ልክ ኢብን ዐባስና ኢብን ዙበይር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲሁም ሙጃሂድና ሌሎችም እንዳሉት (ማለት ነው።) 2⃣ عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : « ما العمل في أيّام أفضل في هذه العشرة»، قالوا: ولا الجهاد، قال: «ولا الجهاد إلاّ رجل خرج يخاطر بنفسه وماله فلم يرجع بشيء» رواه البخاري رحمه الله في صحيحه. 2ኛ. ኢብን ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አሉ በማለት አለ ፦ 👉 " ከነዚህ አስር ቀናቶች የበለጠ ቀን የለም ! " ሰሃባዎችም እንዲህ በማለት (ጠየቁ) ፦ 👉 " በአላህ መንገደ ላይ መታገልም ቢሆን ? " ነብዩም እንዲህ በማለት (መለሱ) ፦ 👉 " አዎ ! በነፍሱና ገንዘቡ የሚታገል ሆኖ ወጥቶ ሳይመለስ በዚያው የቀራ ሰው ሲቀር በአላህ መንገድ ላይ መታገልም ቢሆን (ይበልጣል !!!!! " ) » (ቡኻሪ (አላህ ይዘንለትና) ዘግቦታል።) 3⃣ قال تعالى: {وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ} [الحج:٢٨]، 📮" قال ابن عباس رضي الله عنهما وابن كثير رحمه الله يعني : "أيام العشر". 👉 (( " ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ " )) አል-ሐጅ (28) ኢብን ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲሁም ኢብን ከሲር (አላህ ይዘንለትና) فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ} (በሚለው ቃል) ማለት የተፈለገው (አስሩን የዙል-ሒጃ ቀናቶች) ነው። (አሉ።) 4⃣ عن ابن عمر رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : « مامن أيّام أعظم عند الله سبحانه ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر، فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد» رواه الطبراني رحمه الله في المعجم الكبير. 4ኛ. ኢብን ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አሉ በማለት አለ ፦ 🌺 « ጥራት የተገባው አምላክ አላህ ዘንድ ከነዚህ አስሩ የዙል-ሒጃ ቀናቶች የላቀ እንዲሁም በውስጡ በሚተገበሩት ስራዎች የተወደደ ቀን የለም !!! 👉 (ስለዚህ) "ላሂላሂለላህ" " አላህ ዋክበር " እና " አልሓምዱሊላሂ " ማለት አብዙ !! » ኢማሙ ጠበራኒይ " አል ሙዕጀሙል ከቢር " ውስጥ ዘግቦታል። 5⃣ كان سعيد بن جبير رحمه الله إذا دخلت العشر اجتهد اجتهاداً حتى ما يكاد يُقدَر ُ عليه رواه الدارمي رحمه الله . 5ኛ. ሰዒድ ኢብን ጁበይር (አላህ ይዘንለትና) የዙል-ሒጃ አስሩ ቀናቶች የገቡ ጊዜ መቻል እስኪያቅተው ድረስ አላህን በማምለክ ላይ መታገልን ይታገላል ነበር !!! አል-ዳረሚይ (አላህ ይዘንለትና) ዘግቦታል። 6⃣ قال ابن حجر رحمه الله في الفتح: "والذي يظهر أنّ السبب في امتياز عشر ذي الحجة، لمكان اجتماع أمهات العبادة فيه، وهي الصلاة والصيام والصدقة والحج، ولا يأتي ذلك في غيره". 6ኛ. ኢብን ሐጀር "ፈትሑል ባሪ" ውስጥ እንዲህ አለ ፦ 👉 " ያ የዙል-ሒጃን አስሩ ቀናቶች የሚለዩበት መሆኑን ግልፅ የሚያደረገው ምክንያት ፦ በውስጡ ዋና የአምልኮት (ዓይነቶች) የሚሰባሰቡበት ቦታ (ጊዜ) በመሆኑ ነው። እሱም ፦ "ሶላት" ፣ ፆም ፣ "ሰደቃ"ና "ሐጅ" ናቸው። እነዚህ ዒባዳዎች በሌላ ጊዜ (አንድ ላይ ተሰባስበው) አይመጡምና ። ✍" ما يستحب في هذه الأيام :- 1⃣ الصلاة: 👈 " يستحب التبكير إلى الفرائض، والإكثار من النوافل فإنّها من أفضل القربات. ✍" روى ثوبان رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: «عليك بكثرة السجود لله فإنّك لا تسجد لله سجدة إلاّ رفعك إليه بها درجة، وحط عنك بها خطيئة» رواه مسلم رحمه الله 👈 " وهذا في كل وقت. 👉 በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የሚወደዱ ነገሮች ፦ 1ኛ. ሶላት 👉 ወደ ግዴታ ሶላት መቅደም ይወደዳል ፤ ሱና ሶላቶችን ማብዛትም ይወደዳል።ይህም ከትላልቅ መቃረቢያዎች ውስጥ ነው !! 👉 ከሰውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተወራው ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሲሉ ሰማዋቸው በማለት አለ ፦ 👉 « " አደራህን ! ለአላህ "ሱጁድ" በማብዛት ላይ አንተ ለአላህ አንዲትን "ሱጁድ" አትደፋም ! አላህ (በሱጁዷ) የተነሳ ደረጃክን ወደ እሱ ከፍ ቢያደርግልክና ወንጀልክን የሚሰርዝልክ ቢሆን እንጂ..." » ኢማሙ ሙስሊም (አላህ ይዘንለትና) ዘግቦታል። 👉 ይህም (የሚሆነው) በሁሉም ወቅት ነው። 2⃣ الصيام:
6077Loading...
37
🚧ይደመጥ ይደመጥ🚧 📩 ገሳጭ ሙሃደራ በተለይ ለባለ ትዳሮች 🌸ሴት ልጅን ከመበደል መጠንቀቅ… ❌👉🏼ሴት ልጅን መምታት!! ❌👉🏼በፍቺ ማስፈራራት!! ❌👉🏼ፍቺ ላይ መቸኮል!! ❌👉🏼ሚስትን አንጠልጥሎ መተው!! ❌👉🏼ሴት ልጅን መጨቆን!! 🔖 እነዚህ እና ሌሎችም ነጥቦች የተዳሰሱበት እጅግ መካሪ እና ገሳጭ የሆነ ሙሃደራ ነውና እንዳያመልጣችሁ!!! 🎙በኡስታዝ አቡ ሙሰየብ ሀምዛ ቢን ረሻድ አላህ ይጠብቀው። 📅 ጁማዓ /20/01/2015 Ec 🕌 በሱና መስጂድ አላህ ይጠብቃት። 👇👇👇➖➖➖➖➖➖➖➖ https://t.me/Adamaselefy/7962
2558Loading...
📢 ለዓረፋ ዚያራ ... በምንችለው ሁሉ ኢስላምን አደራ !!! ... ያንተ አባቶች ጋራ ሸንተረሩን ሞፈርና ቀንበር አጥምደው በመቆፈር ፊደል ሳይቆጥሩ በጣታቸው እየፈረሙ አንተን ለማሳደግና ከተሜ ስልጡን ለማድረግ ከነበራቸው መስዋዕትነት በተጨማሪ የተለያዩ ማማለያዎችንና የተጠኑ ስልቶችን በመጠቀም ሀገሬውን ለማክፈር የመጣውን ኃይል ሸሪዓዊ ዕውቀትን ባልተሞረከዘ ጥበብና ተፈጥሯዊ በሆነ ማንነት ላይ ሆነው በከፈሉት ተጋድሎ ሕዝበ ሙስሊሙን በአላህ ፍቃድ ከክህደት ታድገውት አንተንም ዛሬ ላይ ላለክበት ማንነት አበቁክ❗ 💐 አንተ ግን ይህን ወደር የማይገኝለት የአባትና እናት ውለታ ረስተክ ... እነዚያው ካፊሮች ከብዙ ዓመታት የሴራ ቆይታ በኋላ ትላንት እጅ ባለመስጠት ፊት ነስቶ ጠላቱን ያባረረና ዕምነቱን የጠበቀ ጀግና አባትና እናትን ደከም ብለው ወገባቸው በጎበጠና ከልቡ የሚጦራቸው የአብራካቸወ ክፋይ ኖሮ እንደሌለ ነገር ያጡ የሆነ ጊዜ ...በአላህ ምድር ላይ ክህደትን የማንገስ "ፕሮጄክት" ነድፈው ለየት ያለና የተጠናከረ ተልዕኮ በመያዝ ወደ እያንዳንዱ ሙስሊም ቤት በስውርና በግልጽ እያንኳኩ ነው። በናቅናቸውና ኋለ ቀር አርገን በምንቆጥራቸው ወላጆቻችን ጀግንነት ያልተደፈረ ዕምነት ስልጡንና ዘመናዊ በመሰልነው ከንቱ ኩፍሶች ተናቀ !!! ፊደል ሳይቆጥሩ የጠበቁት "ዲን" ፊደሉን አተራምሰን ለይተን የተማርነው እኛ አስደፈርነው ! እነሱም የአባቶቻችንን የጀግንነት ተጋድሎ ድል ለመቀልበስና ለመበቀል ፍርኀት የዋጠውን የሙስሊም ትውልድ ሴት ወንድ እፃን አዋቂ ሳይሉ ለሁሉም በሚስማማው መልኩ ኩፍርን አበጅተው እያሳደዱት ነው !!!!! ስለዚህ ፦ እንንቃ በደንብ እንንቃ !!! 👉 ጥቂት የማይባሉ ሰዎች በኛው ወንጀል ምክንያት የመጣውን ይህን አስከፊ የኑሮ ውድነትና መከራ ለማለፍ ሲሉ በሩን እየከፈቱ ነው !!! የአንተስ ቤተሰቦች በራቸውን ላለመክፈታቸው ምን ማስተማመኛ (ዋስትና) አለክ ? 👉 ሰሞኑን ከተወሰኑ ወንድሞች ጋር ሆነን ለዚሁ ለዳዕዋ ጉዳይ በሚል ወደ ደቡብ ክልል ወደምትገኘው ስልጤ ዞን ሄደን ነበር። በአከባቢው ያለው ማህበረሰብ በአላህ ቸርነት መታደል ሆነና እስልምናን ዕምነት ከመሠረቱ በመጎናፀፍ እስካሁን ድረስ በትውልድ ሽግግር አላህ ጠብቆለት ከላይ ያወሳውላቹ እናት አባቶች በአላህ ዕርዳታ በከፈሉት መስዋዕትነት እዚህ ደርሶ ነበር። 👉 አሁን ላይ ግን የኩፍር አይሎች ትላንት ወላጆቻችንን ለማማለል የተጠቀሙበት " ልጆቻችሁን ትምህርት እናስተምርላችዋለን ... ! " በሚልለው ዘዴ ሳይሆን... ዛሬ ኑሮ ተወዷል አይደል ...??! ጊዜውም እንደምታዩት ከፍቷል ...‼️ ደሞም ወልዳቹ እንዳልወለዳቹ ነገር ልጆቻቹም ጠፉ !!! "እውነተኛ በሰማይ ያለው አባት በሩን ከፍቶ ነው እኛን ወደ እናንተ የላከን..." የቸገራቹን ነገር ንገሩን የምትፈልጉትን ነገር ይዘን እንመጣለን !!! እያሉ እኛ የነፈግናቸውን ዱቄትና ዘይት ... ለመስጠት እየሞከሩ ነው‼️ ልክ ሰለፎቹ እንደሚሉት ፦ « ሆድ ከበላ ዓይን ያፍራል » እውነት ነውና የገጠር ወገኖቻችንም ይህን አደጋ የሚታደጉበት ኢማን ተሸርሽሮ ጫፍ የደረሱ ይመስል አንዳንድ ለሆዱ አደር የሆነ ማይረባ የፖለቲካ ጉዳይ አስፈፃሚና ከንቱ የሆነውን ተራ ሰው ተጠቅመው እጅ መንሻ በመስጠት ኩፍራቸውን በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ። አዎ ! እኛም በሄድንበት ያየነውና የሰማነው ይህንኑ ነው። ከሄድን በኋላ እንግድነት ከተቀበሉን ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት እከሌ እዚህ ቦታ እከሌ እዚህ መንደር ላይ እከሊትም በዚህ ምክንያት ከፈሩ "እየሱስ ጌታ ነው ‼️" ማለት ጀመሩ። በማለት እያዘኑ ነገሩን። ሌላኛው አንድ ወንድማችንም እንዲህ በማለት አስከትሎ በቤተሰቡ የሆነውን እውነተኛ ክስተት ነገረን « ከአለፈው ዐረፋ በፊት አዲስ አበባ ዚያራ መጥቶ በሰላም ሸኝተነው ነበር።ለዐረፋም ስንመጣ በነበረበት ነበር።ሰሞኑን ስመለስ ግን ከፍሮ "አላህ ጬኛል" (አላህ ወልዷል‼️) እያለ ተቀበለን !!! ያሳዝናል ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ገብቶናል‼️!!! ያሳዝናል !!! ተጠያቂው ማነው ‼️??? ሁላችንም ነን !!!!! አዎ እኛ ሰራን ካልን የሚታየን ትልቁ ስራ ከኩፍር ወደ ኩፍር አስተምህሮ የሚቀባበለንን ት/ቤት ነው። አዎ ! ለዚህ ነው ብዙ ሺህ ብር ዶላርና ሪያል ለማሰባሰብ እየሮጥን ያለነው ይህን ደሞ ቀዳማዊቷም እየተገበረችው ነው። የርሷ ትግበራ ግን እጅግ በረቀቀ ሰው ሰራሽ ስሌት የተቀነባበረ ነው !!! የእናንተ እና የእርሷ ዕቅድ በመነሻ አሳቡ አንድ ሆኖ ድንቁርናን ማጥፋት የሚለው ነው‼️ በማሳረጊያውና በመጨረሻው ውጤት ግን... የእናንተው ዕምነቱን እየሸራረፈም ቢሆን ሊቅ ማግኘት ሲሆን የርሷና የመሰሎቿ ግብ ግን ሊቅ እያፈሩ በአላህ ምድር ላይ ኩፍርን ማፅናት ነው !!! ይህ ደግሞ በቀጥታና በተዘዋዋሪ እስልምናን መዋጋት ነው ‼️እኛም አብረናቸው እስልምናን እየተዋጋን ይሆን !!?‼️ አዎ ! ጥርጥር የየውም !!! አይተናነቀን አምነን እንቀበል !!! 👉 ይህ ደሞ ሳይታለም የተፈታ መሆኑ ገና ከጅምሩ ገብቶናል !!! እንዴት አይግባን የውዱ ነብይ ሱና ተከታይ ሆነን ???!!! 👉 ሙስሊሞች ሆይ ሁላችንም በደንብ ይግባን !!! 👉 ቆም ብለን እራሳችንን በአስተውሎት እንጠይቅ !! 👉 ስለዚህ ማንቀላፋቱ ይብቃ ! ትክክለኛ የ"ዐቂዳ"ና "ሱና" ፍሬ ላላቸው መስጂዶች ፣ መርከዞች ፣ መድረሳዎች... ብራችንን እንምዘዝ እላለሁ ።ይህን በማድረግ የክህደት ኀይሎችን እንዋጋ አላፊነታችንን ተወጥተን ወገኖቻችንን እንታደጋቸው !!! አንተ እንደሆነ የገጠሩን መሬት እትብትክን እንዳልቀበርክበት ነገር ትተከዋል !! ረስተከው የተውከው የገጠሩ ሰውም በዓመት አንዴ ብቻ ተመግቦ እንደሚፀዳዳ ነገር ...ጋዝ ሳሙናና ጨው... አንጠልጥለክ ደሟን አፍስሳ ፥ ስጋዋ ተተልትሎ የወለደችክ ሳያንሳት በድጋሚ ጡቷን መዝምዘክ ፥ በሽንትክ አቃጥለካት ፥ ወገቧን አጉብጠክ ያስቀራካትን ውዷን እማምዬ ወግ ነውና ሰው ለመምሰል ስትል "ለዐረፋ" ብቻ ሄደ ታያታለህ❗ ያለመታደል ሆነና አብዛኞቹ የገጠር እናቶች እናትነታቸው በዓመት አንዴ ለዐረፋ ብቻ ሆነ❗ አንተና አንቺ እኔንም ጨምሮ ሁላችንም የኢስላም ልጆች ሆይ ! የአላህንና የመልዕክተኛውን "ሐቅ" በከባዱ ይይዘናል !!! እንዲሁም የእናትና አባት ሐቅን አለመወጣታችን በታማኙ መልዓክ "ጅብሪል" አስረግሞናል...!!! በታላቁ ነብይ አንደበት "አሚን" ባይነት ይሁንታን አግኝቷል !!! ለፍርድ በማይቾክለው አምላክ ፈራጅነት "ጀነት" እርም እንዳይሆንብንም ያስፈራልናል !!! 📢 ስለዚህ አላህ ፊት ቀርበክ ሳትጠየቅ በፊት ከሆዳቸው በላይ ዕምነታቸውም አደጋ ተጋርጦበታልና በዕውቀትክ በጉልበትክ በገንዘብክ ብቻ በቻልከው ሁላ ለወላጆችክም ለወገኖችክም ድረስ እላለሁ ! “ ከተሜ መባል የሆነ ነገር ቢኖረውም ቅሉ ገጠሬ መባል ግን ልዩ ጥበብ አለውና ” 👉 እትብትክ የተቀበረበትን ገጠር አስታውስ !!! … ኢስማኤል ወርቁ... https://t.me/amr_nahy1
نمایش همه...
الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر

ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው። አስተያየት ለመስጠት= @esmael9

👍 5
الدرس الثامن قول الناظم:  وإلى السماء بغير كيف ينزل 🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-08 ♻️ ክፍል-ስምንት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة።   ١٤٤٥/هـ4 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
نمایش همه...
الدرس_الثاني_فتح_رب_الأنام_بتوضيح_لامية_شيخ_الإسلام_بعد_صلاة_الظهر.mp33.74 MB
الدرس_التاسع_فتح_رب_الأنام_بتوضيح_لامية_شيخ_الإسلام_.mp313.80 MB
الدرس_السادس_المختصر_في_الأداب_الشرعية.mp35.82 MB
الدرس_الرابع_الدرس_في_اللغة_العربية.mp32.75 MB
👍 1
📮 ዓረፋ በገነንዳ በምሩ ኽሮት ያነወ📮⤵️ በሚል ርዕስ ወቅታዊ የሆነ መደመጥ ያለበት በጉራጊኛ ቋንቋ የተደረገ ሙሐደራ⤵️ 📍👇ሙሐደራው ላይ ከተወሱ ነጥቦች ውስጥ በከፊሉ⤵️👇 💥አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ቱሩፋትና በልዩ መልኩ ከዙልሂጃ ዘጠነኛው ቀን። 💥 ኡዱሒያ የተደነገገበት ጥበብ {ሂክማ} እና ሁክሙ ምንድነው? 💥ክፍለ ሀገር ላይ ከዒደል ዓድሀ ዓረፋ ጋር በተያያዘ አንዳንድ  የሚፈፀሙ ሙንከራቶች 💥 የዒድ ቀን ለኡዱሒያ(እርድ) የሚዘጋጀው ማሟላት ያለበት መስፈርቶች ሰፋ ያለ ማብራሪያ... 💥 ሲታረድም ሆነ ከታረደ በኋላ የሚባል ዱዓ ወይም ሌላ ነገር አለን? 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ሲሄዱ የሚያደርጉት የተለየ ዒባዳ አለን? 💥 ዒድ የሚሰገድበት ሰዓት {ጊዜ} እና የሚያበቃበት ሰዓት {ጊዜ}። 💥 ወንዶችም ሴቶችም ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ በምን አይነት ሁኔታ ነው መሄድ ያለባቸው? 💥 የዒድ ሰላት አሰጋገድ ሁኔታ በተግባር ምን ይመስላል ተክቢራስ ስንቴ ነው ሚባለው? 📌 ሌሎችንም ነጥቦች የተዳሰሰበት በጉራጊኛ ቋንቋ የተደረገ ሙሓደራ። 🎙 በኡስታዝ አቡ የሕያ ኢልያስ ቢን አወል አላህ ይጠብቀው። 📅 ሀሙስ 30/10/2014E.C 📅 📎https://t.me/Adamaselefy/8013
نمایش همه...
ዓረፋንዳ በገነንዳ.mp312.85 MB
ለሞተ ሰው ኡዱሒያ... *الأضحية عن الميت؟.* 🏷️ قال الإمام ابن باز رحمه الله تعالى : فإﻥ ﻛﺎﻥ قد ﺃﻭﺻﻰ ﺑﻬﺎ ﻓﻲ ﺛﻠﺚ ﻣﺎﻟﻪ ﻣﺜﻼﺃﻭ ﺟﻌﻠﻬﺎ ﻓﻲ ﻭﻗﻒ ﻟﻪ ﻭﺟﺐ ﻋﻠﻰ اﻟﻘﺎﺋﻢ ﻋﻠﻰ اﻟﻮﻗﻒ ﺃﻭ اﻟﻮﺻﻴﺔ ﺗﻨﻔﻴﺬﻫﺎ ﻭﺇﻥ ﻟﻢ ﻳﻜﻦ قد ﺃﻭﺻﻰ ﺑﻬﺎ ﻭﻻ ﺟﻌﻞ ﻟﻬﺎ ﻭﻗﻔﺎ ﻭ ﺃﺣﺐ ﺇﻧﺴﺎﻥ ﺃﻥ ﻳﻀﺤﻲ ﻋﻦ ﺃﺑﻴﻪ ﺃﻭ ﺃﻣﻪ ﺃﻭ ﻏﻴﺮﻫﻤﺎ ﻓﻬﻮ ﺣﺴﻦ. 📝 مجموع الفتاوى ٤٠/١٨. ጥያቄ ፦ 👉 ለሞተ ሰው ኡዱሒያ ማረድ ይቻላልን ? መልስ ፦ 🌴 ሟቹ ከገንዘቡ 1/3ኛ ላይ ተናዞ ከሆነ ወይም ለራሱ "ወቅፍ" አድርጎት ከነበረ አላፊነቱን በወሰደው አካል ላይ መፈፀሙ ግዴታ ይሆናል !!! 👉 ነገር ግን (ሟች) ያልተናዘዘም ወቅፍም ያላደረገ ሆኖ እያለ (ከቤተሰቡ የሆነ አካል) ለአባቱ ወይም ለእናቱ ወይም ለሌሎች ቤተሰቦቹ "ኡዱሒያ" ልረድ ቢል ይህ ያማረ ተግባር ነው !!! (መጅሙዓ ፈታዋ 18/40) ታላቁ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ https://t.me/amr_nahy1 … ኢስማኤል ወርቁ …
نمایش همه...
الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر

ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው። አስተያየት ለመስጠት= @esmael9

የዘር ፍሬው የተኮላሸ... *ذبح الخصي في الأضحية؟* 📚 " الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله يجوز أن يذبح الخصي في الأضحية حتى إن بعض أهل العلم قد فضَّله على الفحل لأن لحمه يكون أطيب. 📝 مجموع الفتاوى ٢٥/ ٤٩/٥٠. ጥያቄ ፦ 👉 የዘር ፍሬው የተኮላሸ (የተቆረጠ) እንሰሳ ለኡዱሒያ እርድ ይበቃልን ? መልስ ፦ 👉 የዘር ፍሬው የተኮላሸ (የተቆረጠ) እንሰሳ ለኡዱሒያ እርድ ይበቃል። 👉 እንደሁም ከፊል ዑለማዎች (ጠንካራ) የዘር ፍሬ ካለው እንሰሳ አስበልጠውታል። ምክንያቱም ፦ ሥጋው የበለጠ ያማረ ነው በሚል ነው !!! (መጅሙዓ ፈታዋ 49፥50/25) (ታላቁ ኢማም ሸይኽ መሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) https://t.me/amr_nahy1 ... ኢስማኤል ወርቁ ...
نمایش همه...
الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر

ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው። አስተያየት ለመስጠት= @esmael9

👍 1
(አል-ኒሳእ (142)) አላህ ይጠብቀን !!!!! ይህው የሀገሬ ሰው ወግ ነውና "ሐጅ" አርጎ ሲመለስ ጥቂቱ ካልሆነ በስተቀር "ሐጂ" እና "ሐጀት" መባል ይወዳል‼️ካልተባለ ወይም እሱ "ሐረምን" እደዘየረው ሁላ እሱም ካልተዘየረ የሚከፋውም በርካታ ነው‼️ ወጣቱ ጋርም ስትመጣ ጥቂቱ አላህ ያዘነለት ሲቀር የሐረምን ቆይታ በፎቶና በድምፅ ቀርፆ ለወዳጆቹ በማጋራት አድናቆት እየተቸረ ሲኩራራ ይታያል‼️ 🔥 እንግዲህ ይህ ሁሉ ታይታና በራስ መደነቅ የሚያመጣው መዘዝ አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ አማኙ ባሪያ አላህን በአምልኮትና በመታገዝ ውስጥ ብቸኛ እንዳያደርግ ያደርገዋል❗️ ይህ ደሞ ሽርክ ላይ የሚጥል የልብ ህመም ነው። ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተሚያ ስለ ታይታና በራስ መደነቅ አስከፊነት ሲገልፅ እንዲህ ይላል ፦ قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله - 🔥 ... « فالرياء : من باب الإشراك بالخلق. والعجب : من باب الإشراك بالنفس. وهذا حال المستكبر ؛ فالمرائي لا يحقق قوله : «إياك نعبد»، والمعجب لا يحقق قوله : «وإياك نستعين»، فمن حقق قوله: «إياك نعبد»، خرج عن الرياء، ومن حقق قوله: «إياك نستعين»، خرج عن الإعجاب». [مجموع الفتاوى (١٠/ ٢٧٧)]. 👉 « ... (ሪያእ) "فالرياء" በፍጥረታት ከማጋራት አኳያ የሚሆን ሲሆን » 👉 « (ወል-ዐጀብ) " والعجب " « በነፍስ ከማጋራት አኳያ የሚሆን ነው። » ይህ ዓይነቱ ሰው ሁኔታው ኩራተኛ (እንደሆነ) ሰው ነው ‼️ 👉 (ፈል-ሙራኢ) "فالمرائي " ታይታን የሚፈልግ የሆነው ሰው «إياك نعبد» (አንተን ብቻ እንገዛለን። (እናመልካለን !!!) የሚለውን የአላህ ንግግር አያረጋግጥም‼️ 👉 (ወል-ሙዓጂብ) " والمعجب " በራሱ ነፍስ የሚደነቅ የሆነ ሰው «وإياك نستعين» ( በአንተ ብቻ እንታገዛለን !!! ) የሚለውን የአላህ ንግግር አያረጋግጥም‼️ 👉 (በእርግጥም) « إياك نعبد » የሚለውን የአላህ ንግግር ያረጋገጠ የሆነ ሰው ከ"ታይታ" ነፃ ወጥቷል !!! 👉 (በእርግጥም) «إياك نستعين» የሚለውን የአላህ ንግግር ያረጋገጠ የሆነ ሰው "በራስ ነፍስ ከመደነቅ" ነፃ ወጥቷል !!! [ሸኸል ኢስላም ኢብን ተሚያ] (መጅሙዓ ፈታዋ (277/10)) 👉👉👉 ወንድም እህቶች እንዲሁም እናት አባቶች “ሐጅ” ማለት ከ5ቱ የእስልምና መሠረቶች አንዱ ነው። ስለዚህ የእስልምናችን መሠረት እንዳይናጋ እንጠንቀቅ። ይህን ብዙ ሚልዮኖች እየቋመጡት ያላገኙት ዕድል እናንተ አግኝታቹታልና በአግባቡ ከታይታ እርቃቹ አላህን በመፍራት ተጠቀሙት። በባለፈው "ሐጅ" ይህን አጥፍቼ ፣ ስቼ ፣ ተሳስቼና ባለማወቄ "ሐጅ" የሰራው አልመሰለኝምና ዳግም ሌላ ጊዜ እደግመዋለሁ ብንል ሞትን ጨምሮ በሌሎች ብዙ ምክንያቶች ላይሆን ይችል ይሆናል ! ስለሆነም ይህ ሁሉ ታይታና ስሙልኝ ለማናችንም አይበጅምና ተደብቀን ለመኖር ጥረት እናድርግ በማለት አደራ እያልኩ ሰፊውን የተውሒድና የ“ሐጅ” አደራረግ ስርዓተ- ትምህርቶችን ጥረት በማድረግ እንማር እያልኩ በመልዕክተኛው ሐዲስ አጭሩን መልዕከቴን አበቃው‼️ وقال ﷺ : (من حج فلم يرفث ولم يفسق رجع كيوم ولدته أمه) 🌺 ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ፦ « (ከባለቤቱ ጋር) ግብረ-ሥጋ ግንኙነት ሳያደርግና "ወንጀልን" ሳይሰራ "ሐጅ" ያደረገና (ከዚያም አጠናቆ) የተመለሰ የሆነ ሰው ልክ እናቱ እንደወለደችሁ ዕለት ይሆናል !!! ይህ "ሐጁ" የነፃ (ተቀባይነት) ያለው ነው !!! » ታላቁ ኢማም ኢብን ባዝ ይህን ሐዲስ ሲቶረግሙ ተከታዩን አሉ ፦ 🌱 « ይህም "ሐጅ" ማለት እውነተኛ "ተውበት" ማድረግ አብሮት ያለው ማለት ነው። ወንጀልና ( ከባለቤቱ ጋር ) ግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ አብሮት የለውም‼️ ይህ "ሐጅ" ንፅት ያለ ነው !!!!! ይህም ሰው በወንጀል ላይ ችክ ብሎ ከመዘውተር ሰላም የሆነ ነው !!! ... አዎ ! " አል-ሐጁ መብሩር " ሲባል የተፈለገበት በእርግጥም "ሐጅ " የሚያደርገው ሰው በወንጀል ላይ ሳይዘወትር አላህ ለሱ የስህተቱን " ተውበት " የተቀበለው ሰው ማለት ነው !!! (الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة) 👉👉👉 ታዲያ ወንጀል ሳይቀላቀልበትና ተሰርዞለት "ሐጅ" አርጎ “ጀነት” መግባት የሚጠላ አለን ? " እንዴታ ?? የለም እንጂ ... !!! " ስለዚህ በዚህ የተከበረ ስፍራ አላህን ማስወደድ ሲገባን አስቆጥተን ፎቶ (ቪዲዮ) መነሳትም ይሁን ማንሳት ተገደን ካልሆነ በስተቀር "ሐራም" ነው‼️ አላህ ለስራችን ኢኽላስን ይግጠመን !!! https://t.me/amr_nahy1 (… ኢስማኤል ወርቁ …)
نمایش همه...
الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر

ይህ ቻናል በመልካም ማዘዝንና ከመጥፎ መከልከልን ዓላማው በማድረግ ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በመመርኮዝ የተለያዩ አስተማሪና ገሳጭ ምክሮች የሚተላለፍበት ነው። አስተያየት ለመስጠት= @esmael9

🕋 "ሐጅ" እና አስደንጋጩ "ሪያ"🔥 "ሪያ" ማለት ድቅድቅ ባለ ጥቁር ጨለማና ጥቁር ድንጋይ ላይ እንደሚሄድ ጥቁር ጉንዳን ድካው ስውር ነው ‼️‼️‼️ ታላቁ ሼይኽ ዶክተር ሷሊሕ ቢን ፈውዛን አል–ፈውዛን ሐጅ ላይ ፎቶ ስለመነሳት ተጠይቀው ሲመልሱ ተከታዩን ምክር ይሰጣሉ ፦ 👉 « ይህ ድርጊት እዩልኝ ከሚለው (የሽርክ ዓይነት) ውስጥ ይገባል !!! ያ "ሙሕሪም" ሆኖ የገዛ ራሱን ምስል የ"ዐረፋ" (ተራራ) ላይና "ካዕባ" (🕋) ዘንድ የሚቀርፅ የሆነ ሰው በ"ሐጅ" እና "ዑምራ" ላይ የሚሰራውን ስራና ትዕዛዛቶች ለሰዎች ማሳየት (የሚፈልግ) ሰው ነው‼️ የሰው ልጅ በተቻለው ያህል ስራውን መሰወር ነው ያለበት !!! (ስራውን) በእርሱና በአላህ መካከል ብቻ ያድርገው !!!!! » የሸይኽ ንግግር አበቃ። 👉 መቼስ ዐዋቂ ይናገር አይደለም የሚባለው ?‼️እኔ ተናግሬው ቢሆን እንኳን እሺ... ነብዩም ቢሆን የሰው ልጆችን ልብ ከፍተው ስላዩ ሳይሆን ከልዕለ አያሉና የሩቁን ዐዋቂ ከሆነው አምላክ አላህ የተገለጠላቸውን ነው የተናገሩት !!! 👉 ሸይኹም ቢሆን ከላይ እንዳየከው ለመምከር የሞከሩት ሐጅ ላይ ስላለው የሰዎች ሁኔታ በማስቀመጥ ጥቅል ምክር ነው የሰጡት እንጂ የሐጅ አምልኮት ላይ ፎቶ የሚነሱ ሰዎች ሽርክ ላይ ወድቀዋል አይደለም ያሉት !!! 👉 ነገር ግን በዒባዳ ቦታ ላይ "ዕዩኝ ማለት" አደገኛ ስለሆነ ይህን የመሰለ "ዒባዳ" በታይታ እንዳያበላሹትና ለቅጣት እንዳይዳረጉ እያስጠነቀቁ ነው‼️ 👉 ዑለማዎች ደሞ ከዚች አታላይ ዓለም ክፋት አስጠንቃቂ ባይሆኑ ኖሮ አንድም መልካም ሰው በምድር ላይ ባልኖረ ነበር !!! (( " قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِثْلُكُمْ يُوحَى إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَهُكُمْ إِلَهٌ وَاحِدٌ فَمَنْ كَانَ يَرْجُوا لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلاً صَالِحاً وَلا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَداً " )) [الكهف: 110]. « እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው ፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ (አል-ከህፍ (110)) (( " وعن أبي هريرة مرفوعا: قال تعالى: أنا أغنى الشركاء عن الشرك؛ من عمل عملا أشرك معي فيه غيري تركته وشركه " )) (رواه مسلم.) ከአቡ ሁረይራ እንደተወራው "መርፉዕ" በሆነ ሐዲስ አል-ቁድሲይ ላይ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ ፦ (( እኔ ከአጋሪዎችና ከሚያጋሩበት ሽርካቸው የተብቃቃው ነኝ !!! አንድ ስራን የሰራና በሰራው ስራ ውስጥ ከእኔ ጋር ሌላን ነገር ያጋራ የሆነ ሰው እሱንም ያጋራበትን ስራውንም እተወዋለሁ‼️)) (ሙስሊም ዘግቦታል።) (( " وعن أبي سعيد مرفوعا: ألا أخبركم بما هو أخوف عليكم عندي من المسيح الدجال؟ قالوا: بلى، قال: الشرك الخفي؛ يقوم الرجل فيصلي فيزين صلاته لما يرى من نظر رجل. ( رواه أحمد. ) ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ እንደተወራው "መርፉዕ" በሆነ ሐዲስ ላይ ነብዩ ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ፦ (( " አዋጅ ! እኔ ዘንድ ከመሲሕ አል-ደጃል የበለጠ አስፈሪ ስለሆነው ነገር አልነግራችሁምን ? (ሰሓባዎቹም እንዲህ አሉ ፦) እንዴታ ! ንገሩና ! እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦ « ስውሩን ሽርክ ነው‼️» ( ይህም ማለት ፦) « ሰውዬው ተነስቶ ይቆማል ! ሶላቱንም ይሰግዳል ! ለሚመለከተው ሰው እይታ ሲል ሶላቱን ያጌጠዋል‼️» 👉 ወንድሜ "ሪያ" ቀላል ወንጀል እንዳይመስለን... በጣም አደገኛ ነው‼️ ለዚህም ነበር ሰለፎች "ታይታን" እጅግ በጣም ከመፍራታቸው የተነሳ ይሰሩት የነበረውን መልካም ስራ በመደበቃቸው ማን እንደሰራው ይታወቅ የነበረው ከሞቱ በኋላ የነበረው። ለምን ??? ስራቸውን ሰዎች ማወቃቸው ኢኽላሳቸውን ያበላሽብናል በማለት ስለሚፈሩ ነው‼️ 👉 ከእውነተኛ ዒማን የሚመነጭ ድርጊት ከሆነ በትክክልም መልካም ስራን መደበቅ ነው !!! 👉 እኛ ግን እንደምንታየው የሰራናትን እያንዳንዷን መልካም ስራ ሰው እንዲያይልን እንፈልጋለን !!! 👉 በዚህም የተነሳ በምንሰራው ዒባዳ ልክ የልብ ጥፍጥና አጥተን ግራ ተጋብተናል !!! ምፅዋት እንሰጣለን እርካታ አይሰማንም‼️ ሶላት እንሰግዳለን እርካታ አይሰማንም‼️ "ሐጅ" እና "ዑምራ" እናረጋለን እርካታ አይሰማንም‼️... 👉 ግን ለምን ??? ሲባል። አብዛኞቻችን ሰርተን አላህን ከማስደሰት ይልቅ ለሰው ልጆች አሳይተን ጊዜያዊ ደስታን መጎንጨት ነው የምንፈልገው‼️ ለዚህም ነው ረሱል እንደነገሩን ዕለተ-ትንሳዔ በሚያሳቅቅ ሁኔታ የሰዎችን አድናቆትና ሙገሳ ፈልገክ ሰርተክ የምትፈልገውን አግኝተካልና ከኔ ዞር በል ተብሎ በኪሳራ ይመለሳል ያሉት ‼️ 👉 ታዲያ አላህ ፊቱን ያዞረበት ሰው ምን መሄጃ ይኖረው ይሆን ?‼️ 👉 መቼስ ውድ ወንድሜ እንዲሁም እህቴ እኔንም አንተንም አንቺንም ጨምሮ በምንሰራው ስራ "ሙኽሊስ" ነን ? ወይንስ አይደለንም ? ብለን ለራሳችን (ለነፍሳችን) ማለትና መጠየቅ (መገምገም) የሚችል ስነ-ልቦና እንኳን የለንም !!! 👉 ከቀደምት ሰለፎች ውስጥ የአንዳንዳቸውን ታሪካቸውን ስትሰማ " እኔ ለአላህ ብዬ ጥርት አርጌ ሶላትን አስተካክዬ ለመስገድ 20...ዓመትና ከዚያ በላይ ፈጀብኝ" ሲሉ ትሰማለክ !!! እኛስ አንድ ወር አከታትለን ከሰገድን... ነገሩ አበቃ !!! 👉 ይልቁንስ አንዳንድ የ"ዐቂዳ"ን ጥፍጥና በስሱም ቢሆን ያልቀማመሱ ሞኝ ወገኞች እንደሚሞግቱት " ኢማን በልብ ነው ! " እያልን የልብ ኢማን በውጫዊ ማንነት እንደማይገለፅ ነገር ከራሳችን አልፈን ለሰው ልጆች አመፅ ጠበቃ እንቆማለን !!! ጥሩም አይደል !!! ሞኝነት ይቅር !!! ተውሒድን እንማር !!! 👉 በአብዛኛው የ"ሐጅ" ስርዓትን የሚፈፅሙ ሰዎችን ስናይ በ"ዐረፋ" ተራራ ላይ ፥ በካዕባ ዙሪያ ... ፎቶ ሲነሱ የፈለጉበት ምንድነው ??? ፎቶውን በፍሬም አሰርተው ማስለቀሻ ማድረግ ፣ ወይም ልክ በአምልኮታቸው ግራ ተጋብተው እርካታ እንዳጡት ካፊሮች ቤታቸው ለመጣው ወዳጅ ዘመድ አልበም አሰርተውለት እንግድነቱን በፎቶ መቀበልና አድናቆትን ማግኘት ነው !!! 👉 ካልሆነ ፎቶ መነሳትና እዩልኝ እያሉ በሞባይል ላይ " ፕሮፋይል" ማድረግ በ"ሐጅ " ስነ-ስርዓት ላይ እንደሚፈፀሙት "ጠዋፍ" ማድረግ ፥ "ሰዒይ" ማድረግና ጠጠር የመወርወር ዓይነት የሚተገበር አንዱ ተግባር ሆኖ አይደለም‼️ ለዚህም ነው ጠቢቡ አምላክ እዩኝ የማለትን አደገኝነት ሲያወሳ መናፍቃኖች "ዒባዳ" ሲሰሩ የሚያሳዩትን ባህሪ በመግለፅ የመሰለው... (( " إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا " )) ((መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ (ይቀጣቸዋል)፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም፡፡ " ))
نمایش همه...
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-3 ♻️ ክፍል ሦስት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
نمایش همه...
الدرس_الثالث_فتح_رب_الأنام_بتوضيح_لامية_شيخ_الإسلام_بعد_صلاة_الظهر.mp39.09 MB
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-4 ♻️ ክፍል አራት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
نمایش همه...
الدرس_الرابع_فتح_رب_الأنام_بتوضيح_لامية_شيخ_الإسلام.mp313.64 MB
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚فتح رب الأنام بتوضيح لامية شيخ الإسلا لشيخ الإسلام  أحمد بن عبد الحليم بن تيمية رحمه الله تعالى-متوفى:٧٢٨هـ                                 جمع وترتيب:-أبي سلمان فارس بن عبد الله الحبشي حفظه الله تعالى 🎙 በኡስታዝ:-አቡ ሰልማን ፋሪስ ቢን አብደሏህ አላህ ይጠብቀው። -ቁ-² ♻️ ክፍል ሁለት 🕋በመስጂደ ሱና {{ወራቤ}> حرسها الله تعالى ذو الحجة ١٤٤٥/١هـ 📅 በቀን ══≪ °📓🖇📓° ≫══ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf ↓↓↓ 📍ትምህርቱን ለመከታተል 👇👇👇 https://t.me/mesjidalsunnabewerabe https://t.me/abuselmanfaris
نمایش همه...
الدرس_الثاني_فتح_رب_الأنام_2_ذي_الحجة_بعد_الفجر.mp314.68 MB