cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

✨𝕪𝕖 ግጥም 𝕛𝕚ረት✨

ጦቢያ የ ግጥም ጅረት ከ ✨ጥበብ✨ማእድ....✍️ @Senaboru 👶ተቀላቀሉን..✍️ https://t.me/yegixemjiret

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 286
مشترکین
+1124 ساؚت
+357 عوز
+18630 عوز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ህልሜን ተረጂ
.........................ሴናዬ✍️ ሀሳቤን ባታውቂ ግን ቢያንስ አትሳቂ የልቤ ባይገባሽ ሰው መሆኔ ይብቃሽ ትረጂያት ከሆነ የነብሴን ዝማሪ ሰው ነው ልመናዋ ግን እንዳትኮሪ እኔ በማስበው የሀሳብ መንገድ ላይ መራመድ ብችይ.. ልቤ ላይ ብትቆይ ዓለሜን ባወቅሻት በአለምሽ በኖርሻት ልቤ ልብሽ ቢሆን በሰጠው እራሴን በፈታውት ህልሜን እሺ በይኝ እና ህልም እንፍጠር ሂጂ ህልሜን ግን ተረጂ.... የሴቷ ልጅ
نمایش همه...
❤ 2🥰 2👍 1
እንደ ግዜ ትልቅ መምህር የለም።
نمایش همه...
👍
👎
🤕ድምፅ አልባ ፊደላት💔 ፀጉሩን #አንጨብርሮ ፂሙን #አጎፍሮ #ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት ሂድና ታዘዘዉ #ስጠዉ አንድ ድራፍት ቅዳለት ደብል ጂን ሀሳቡን #ይርሳበት‼️ በፂሙ #መጎፈር በፀጉሩ #መንጨብረር ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር☹️ ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል #ነገር! . . እዚያምከጨለማዉ #ብቸኝነት ዉጧት💔 ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችዉ ወጣት🤒 ሂድና #ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት! . . ምጋ #በተፋችዉ በጭሶቹ መሀል ሴትነት #ሲበደል ‼️💔 እህትነት #ሲጣል ‼️ አናትነት #ሲጎል 😔 ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል ፊደል.... @fonkabcha1 @fonkabcha1
نمایش همه...
❤ 3👍 1
ቅናት...☺️
نمایش همه...
👍 3
..............................ሴናዬ✍️ ጨረቃም ተቆጣች ፀሀይም ጠቆረች ሰማይም ተነነች ምድርም ውሀ ሞላች ኮከባት በነኑ አእዋፋትም ጠፉ የሰው ዘር በነነ መለአክትም ከፉ አምላኬም ተቆጣ ክንዶቹን አሳየ እኔም እዚ አለው አይቼ እንዳላየ ይሄ ሁሉ ሲሆን ቢገርመኝ መኖሬ ከቶ አለመጥፋቴ ለካስ መሸሸጊያ ዓለሜ ስጠፋ ዓለም ናት ሂወቴ ዓለም ላይ ተገኘው አለሜን አጥቼ ምድርን እረገጥኩ ከራሴ ጠፍቼ ሰው ለካ ሲጠፋ ከማንነቱ ላይ ምድር ይወለዳል እነደገና ከላይ ዓለሜም ዓለምም ጭለማ ነበሩ አሁን ሞት ተመኘው ያው ከተባበሩ እንደገና ደሞ ልሞት ስሰናዳ የሞት ድግስ ይሉ ጨለማ ተነዳ ጨለማው ሲነሳ አለሜ ተገኘች ብቸኛዋ ነብሴ ወደዓለሟ ሄደች        እንደገና ነቃች ህልም ነበር ለካ       አይኗን ስትገልጠው ብረሀኗ ጠፍቶ ጨለማ ተተካ . . .       አልቻልኩም በምድር አሁን የተማጠች የብሶት ልጅ! እነሆ ለእናንተ🙏 የሴቷ ልጅ
نمایش همه...
👍 4👏 2🔥 1
አትመኚው ቃሌን
..............................✍️.ዮሐንስ ከንፈርሽ እንቡጥቡጥ፣ፀጉርሽ ፀሀዳ አይኖችሽ ማራኪ፣መልክሽ ነው እንግዳ አያልኩ ስትሰሚኝ፣ እንዳትደነቂ ባክሽ እንዳታምኚኝ። ጨረቃን ለክቼ በውብ ብርሃኗ፣አንቺን ብመስልሽ የፀሐይን ጀንበር፣ ካንቺ ፈገግታ ጋር፣ባመሳስልልሽ እንዳትደነቂ እንዳታምኚኝ ባክሽ እኔ ገጣሚ ነኝ ፣ ቃሌ የለውም እውነት ፊደላትን ማብሰል፣ማሽሞንሞን በውሸት ለኔ ስራዬነው፣እውነት አልባ ድርሰት ያለም ሞናሊዛ፣ ፍቅርሽ ነው ምግቤ ያልኩ ካሞገስኩሽ ካፌ ቃላት እንጂ፣አይደለም ከልቤ ልክ እነደሰማዪ፣ፍቅርሽ ነው የላቀ ልክ እንደ አልማዝ ወርቅ፣ወዝሽ የደመቀ የዋህንትሽማ ፣ከውቂያኖስ የሰፋ እያልኩኝ በውሸት ፣ ቃላት ባንከራፋ አትመኚኝ ውዴ እንዳታምኚ ቃሌን ገጣሚ ነኘና፣ብዙ ሺ ፊደላት ሞልተውታል አፊን መልክሽ የሚያበራ፣የለሽ የሰው አቻ የጥርሶችሽ ውበት ፣ልክ እንደ ሀይቅ ዳርቻ እያልኩሽ ብመሰጥ ቃላትን አርቅቄ እንዳታምኚኝ ውዴ ቃላቶችን ማጉረፍ፣ለኔ አይደለም ብርቄ          #ነፃ_ስሜቶች       @Scat_Johny 𝖏𝖔
نمایش همه...
👍 4🔥 3✍ 2🥰 2
ተስፋ
نمایش همه...
👍 1
.....ትዝብት🫢
.......................................ሴናዬ✍️ አዬ የሰው ልጅ ቅሌት አዬ የመኖር ውጤት መታዘብ አይታክት የምድርን አቀበት የሰው ልጅ ክፋቱ እጅጉን ይልቃል የጎደለው በዝቶ ደምቆ ያሸበርቃል እኔን ምስኪን ደሀ ፈጥሮኛል ፈጣሪ አርጎት ማንነቴን የኮከብ ቆጣሪ ጓዴንም ፈጥሮታል አድርጎ ገጣሚ ወንድሜም ተችሯል ሀብት ባጋጣሚ በሴቲቷ እይታ እኔ አስቀያሚ የሆንኩኝ እርካሽ ላይኗ የማልሞላ ሆኛለውኝ ፍራሽ በሴቲቷ እይታ ጓዴም ተገፍትሯል ባይኗ ቦታ አቷል ጭንቅላት ነው እንጂ ገንዘብ ኪሱ ጠፍቷል በሴቲቷ እይታ ሀብታሙ ወንድሜ ዘንድሮም ቀንቶታል ፍቅርን...ገንዘብን... ውበትን ሰቶታል!!🤗 እኔ ሟች ለሴቷ ፍቅርን የማልሰስት እሷ ለኔ ጠላት እኔ ለሡ ህይወት ሾር ሾሯ እያልኩኝ እስክኮነን ድረስ መታከት አቃተኝ ልቤ በሷ ቢፈርስ     እርሷ ስትገፋኝ ጀርባዋን አዙራ      እኔ አፍቃሪ ሞኙ ሆኜ አረፍኩት ጭራ ቅንጣት ሳያስፈራት ፍቅርን መርገጧ እረጋግጣኝ ሔደች ገንብ በመምረጧ     ውበት ምንስ ቢፈርስ ገንዘብስ ቢጠፋ      ፍቅር አይበልጥም ወይ  ምን እንኳ ቢከፋ እንዴት ፍቅር ይረገጥ መታዘብ ነው ጎበዝ ሂወት ላይ ተራምዶ ለገንዘብ መደንዘዝ አወይ የሰው ባህሪ እጅግ አሳፋሪ...!!😱 የተገላቢጦሽ ለካስ ሆኖ ኖሯል ፍቅርን ስትሰጠው ጥላቻ ይመልሳል ይቅርታ ስትጠይቅ ከመቀበል ይልቅ ያየ ይመስል ድንቅ በብዙ የሚደነቅ እረዳሁኝ ብለህ እጅህን ስትሰጠው ጎትቶ ሚጥልህ ከሾ ጉርጓድ ቀጋው እምነት የሚበላ ለገንዘብ የሚባላ በሒወት ለመኖር ሒወት የሚያጠፋ ደስተኛ ለመሆን ሀዘን የሚሠፋ አዬዬዬ!! የሰው ልጅ ክፉ ነው ትላለህ ይህን ሁሉ ስታይ ትዝብት ትጭራለህ!! መታዘብ ነው! 2015.ዓ.ም✍️ የሴቷ ልጅ
نمایش همه...
👍 3🥰 1