cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Fikir Eske Mekabir

ke teleyayu channaloch lay yetewesedu @fikireskemekabirtireka

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
815
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬ 👩‍💼 ናርዲ 👩‍💼 ክፍል ▭▭▭▭▭ 2⃣ 📜...የቀኑ ሙቀት እንዳይገባ ዘጋግቼው የሄድኩት ቤት ቀዝቀዝ ብሎ ነው የጠበቀኝ::መስኮቶቹን ከፋፍቼ ከሶፋው ላይ ዘፍ አልኩ:: አሁንም ሀሳቤ ከቁራጩዋ ወረቀት ላይ ነው::እንደገና ከቦርሳዬ አውጥቼ አተኮርኩባት:: በችኮላና ያለማስደገፊያ ለመጻፉ አልፎ አልፎ የተነባበሩት ቃላቶች ይመሰክራሉ::የእጅ አጣጣሉ ብዙም እንግዳ አልመሰለኝም...... "የማን ሊሆን ይችላል?...." የምሽቱን እድምተኞች አሰብኳቸው ሳሙኤል ከባለቤቱ ከልያ ጋር ሰለሞንና ገርል ፍሬንዱ ሳባ ሰብለና ጓደኛዋ መቅደስ አንተነህና እህቱ ሚሚ እንዲሁም የባለቤቴ የቅርብ ጓደኛ ስምኦን ሳሙኤል በጭራሽ ሊሆን አይችልም:: በእርግጥ ከልያ ጋር አሁን አሁን ከሚስማሙበት የሚጣሉበት ጊዜ ቢበልጥም በእንደዚህ አይነት ቅሌት የሚጠረጠር ግን አይደለም.....በዚህ ላይ ከኛ ቀድመው ጋብቻን የመሰረቱት እነሱ ናቸው::....... ᐸᐸግን ምን ይታወቃል>> ጥርጣሬ በዚህ በኩል ብቅ አለብኝ ᐸᐸኸረ በፍጹም>> ሰለሞንስ........እሱ መሆን አለበት:: በንዴት ጆሮዬ ሲግል ተሰማኝ:: ከድሮም ቀልቤ አልወደደውም ቀልቃላነቱ...ለወሬ መቸኮሉ ሁሉ ነገሩ አይመቸኝም::ግን ባለቤቴ ዮሀንስ ጥሎበት ይወደዋል ᐸᐸአይ ናርዲ ወሬ ስለሚወድ እኮ ነው እንጂ ልቡ እንዴት ንጹህ መሰለሽ >> ወገቡን ይዞ ይከራከርለታል እኔግን በፍጹም ፊት ሰጥቼው አላውቅም:: በእኔ ፊት እንደ ደመራ የሚደምረውን ሲጋራ እንኳን ለማጨስ ይታሻል:: ᐸᐸበፍጹም ሰለሞንማ ሊደፍረኝ አይችልም>> ለነገሩ ሳባ ጥሎባት ትወደዋለች እንጂ እሱ ለሷ እንብዛም ነው::ከብቸኝነት ይሻላል ብዬ ነው እያለ ይሳለቅባታል:: ሀሳቤ ደግሞ ወደ ባለቤቴ ውድ ጓደኛ ወደ ስምኦን ተንደረደረ...... ከእራት በኍላ ቀዝቀዝ እንዲል ፍሪጅ ያስገባሁትን የኪያንቲ ዋይን ለመክፈት ስታገል ᐸᐸጥሩ እራት ነበር>> አለኝ ኩሽናው በር ላይ ቆሞ ነበር ᐸᐸሞያዬን ዛሬ ነው የምታውቀው>> ᐸᐸኸረ በፍጹም>> ፈገግ አለ ᐸᐸመቼም የሆድህ ነገር አይሆንልህም:: የእኔ ቢጤዋን እንድታጋጥምህ ጸልይ.......>> አሽሟጠጠኝ ᐸᐸእርግጠኛ ነኝ የሁልጊዜ የመጀመሪያ ጸሎትህ......የናርዲን ያህል ሞያ ያላት ሴት ባትገኝም ባይሆን ግማሹን እንኳን ......>> አላስጨረሰኝም ᐸᐸግዴለም ሌላው ነገሯ ሁሉ ከተስማማኝ የሆዴን ነገር ባንቺ ነው የምተወው.....መቼም በእኔ አትጨክኚም>> ዋይኑን ከፍቶልኝ እየተሳሳቅን ወደ ሳሎን ሄድን ᐸᐸምን ለማለት ፈልጎ ነው.......>> ከተለዋወጥናቸው ቃላቶች ውስጥ ጠቋሚ ነገር መፈለግ ያዝኩ......ምንም ᐸᐸአንተነህስ ቢሆን?>> አልተዋጠልኝም.......ለራሱ በቅርብ ጓደኛዬ በሰብሊ ፍቅር ከናወዘ አመታትን አስቆጥሯል..እሷም ወይ ቀርባ አትቀርበው ወይ ርቃ አትርቀው ሄድ መጣ እያለች ኑሮውን ሲኦል አድርጋበታለች:: .....አይ የሰብሊ ግፍ ይህ ሰው ምሽቱን በአይኑ ሲከተለኝ ካመሸ እኔ እንዴት ልብ አላልኩትም .... ምሽቱ ላይ ከአንዳቸው ለየት ያለ አመለካከትን አይቼ እንደሆነ ለማስታወስ እንደገና አውጠነጠንኩ.....ስምኦን ኩፍስ እንዳለ ነው ያመሸው.....አንድ ጥግ ደገፍ ብሎ ለሰከንድ የማትቆይ ፈገግታውን እየሸለመ ከመሳተፍ መታዘብ ያዘወትራል ። ᐸᐸእኔኮ የዚህ ሰውዬ በእኛ መሀል መገኘት ትርጉሙ አይገባኝም......እኔማ አስተያየቱን እንዴት እንደምፈራው>> የሰብሊ የዘወትር እሮሮ ነው..... ከእኔና ሞቅ ብሎ ከነበረው ጨዋታ ይልቅ ትኩረቱ በየ አምስት ደቂቃው ከሚያስተካክላት ከረባቱ ላይ እንደነበር እርግጠኛ ነኝ ሳሙኤል እንደወትሮው የምሽቱ ጆከር ነበር...ቁጭ ብድግ ጎርደድ እያለ ያን ምሽት ያልዳሰሰው ርዕስ አልነበረውም..... ድንገት ፍንጥዝጥዝ ያልኩት የምትለዋ ሀረግ አቃጨለችብኝ ይቀጥላል ..... 👮 የLike (👍) ምልክቷን አንድ ጊዜ ብቻ ይጫኑ ቁጥሩ በራሱ ጊዜ ይጨምራል ። 💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬
نمایش همه...
attach 📎

‍ ናርዲ..(አጭር ልቦለድ)➰▬▭▬▭ አዘጋጅ :- ሳምሶን(Channel Admin) ደራሲ :- ያሚ የደራሲው መልዕክት:- ይህንን አጭር ልቦለድ ለመጀመር ብዙ አመንትቻለሁ.... ለብዙ አመታት በውስጤ ያዳፈንኩትን የስነጽሁፍ ፍቅር ቀስቅሶ ከብእርና ወረቀት ያገናኘኝን ይዚህን የኢትዮፊክሽን ቻናል ውለታ በትንሹ ቢከፍልልኝ........ ክፍል ▭▭▭▭▭ 1⃣ ✍...ዛሬ የኔ ቀን አልነበረም የስራ📝 ባልደረቦቼንም ሳመነጫጭቅ ነው የዋልኩት:: የተለመደ ተረባቸውን ቀርቶ ቀልዳቸውንም በኤጭና በኡፍ ነው የሸኝሁት::አለ አይደል አንዳንድ ቀን ሰማይን በትከሻዬ የተሸከምኩ ያህል ክብድ ብሎኝ ነው የዋለው ፊቴን እንዳጨፈገግኩ ገብቼ ፊቴን እንዳጨፈገግኩ ከስራ ወጣሁ......... ከልብስ መቀየሪያው ክፍል ስወጣ አንዳቸውንም ቻዎ አለማለቴ የታሰበኝ በከተማው መሀል የሚያቋርጠውን የወንዝ ዳርቻ ተከትዬ ወደ መኪናዬ ማዝገም ከጀመርኩ በኋላ ነበር:: ያለምክንያት የስሜቴ መዘበራረቅ ...... የሀሳቤ መበታተን ግራ ቢያጋባኝም እንደለመድኩት ቁራጭ ፒዛ ፍለጋ ከተለመደው ፒዛ ቤት ዘው አልኩ ሽማግሌው ወዳጄ ዛሬ የለም በቅርቡ የተቀጠሩት ሁለት ወጣቶች ባንኮኒውን ደገፍ ብለው ያወጋሉ::ወደ መስታወቱ ጠጋ ብዬ ተቆራርጠው የተደረደሩትን ፒዛዎች ቃኘኋቸው........ያ ሽማግሌው ወዳጄ ቢኖር ኖሮ ᐸᐸሲኞሪና ዛሬ ምን የመሰለ በዘይት የደረቀ ፒሳ አለ መሰለሽ >> ወይንም አይኖቼ ወደዛ ወደእዚህ ሲያማትሩ አርቴፊሻል ጥርሶቹን በምላሱ ወደ ላይ እየገፋ ᐸᐸእነዚህ እንኳን ይቅሩብሽ ለአንቺ ለውድ ደንበኛዬ የሚሆኑ አይደሉም......>> ይለኝ ነበር። አመናትቼ የማዘወትረውን በዘይት የደረቀ ፒዛ ድምጼን ከፍ አድርጌ አዘዝኩ የሞቀ ወሬያቸውን ለማቋረጥ ሆን ብዬ ማድረጌ የገባት ወጣት ፈገግ አለች ወጣቱ ፒዛውን መዝኖ በስስ ወረቀት መጠቅለል ሲጀምር የገንዘብ ቦርሳዬን ለማውጣት እጄን ወደ ቦርሳዬ ሰደደኩ.....የሚንኮሻኮሽ ነገር ተሰማኝና አይኖቼን ወደ ቦርሳዬ ወርወር አደረኩት...........የተጣጠፈ ወረቀት ነው አጠር ያለ መልዕክት ሰፍሮበታል.... ማንበብ ጀመርኩ ᐸᐸአይኖቼ አይኖችሽን ፍለጋ ሲራወጡ አመሹ.....>> ᐸᐸሲኞሪና>> ቀና አልኩ ወጣቱ በወረቀት የጠቀለለውን ፒዛ ዘርግቶ ይጠብቀኛል ᐸᐸይቅርታ..........>> ከፍዬ ውልቅ አልኩ ᐸᐸሲኞሪና.......>>የሽማግሌው ድምጽ ነው እንዳልሰማ ዞርም ሳልል ወደ መኪናዬ ገሰገስኩ.......የቁራጩን ወረቀት መልዕክት ጨርሳ እስክታነብ የተጣደፈች ነፍሴን ይዤ.......... የመኪናዬን ወንበር ተደግፌ እንደገና የተጣጠፈችውን ወረቀት ዘረጋኋት ᐸᐸአይኖቼ አይኖችሽን ፍለጋ ሲራወጡ አመሹ::ሁሉም የአዲሶቹን የወደፊት ሙሽሮች ደስታ ደስታችን ብለው ሲደሰቱ እኔ ግን እንደገና አንቺን ለማየት ስላበቃኝ ነበር ፍንጥዝጥዝ ያልኩት......ይህንንም የምጽፍልሽ አንድ አፍታ መጸዳጃ ቤት ገብቼ ነው::........ደውይልኝ።>> ᐸየፍቅር ደብዳቤማ ሊሆን አይችልም!> ᐸᐸ😂..😂..😂..>> ከልቤ አሳቀኝ በግርምት ደግሜ ደጋግሜ አነበብኩት ትላንት ማታ የውድ ጓደኞቻችን የሰመረና የመሰረት የቃልኪዳን ቀን በማስመልከት እኔና ባለቤቴ ዮሀንስ አዲሶቹን ሙሽሮች ከሌሎች የቅርብ ጓደኞቻችን ጋር እራት ጠርተን ነበር ደብዳቤው በምሽቱ ላይ ከነበሩት በአንዳቸው ለመጻፉ ጥርጥር አልነበረኝም:: ᐸᐸወይ ድፍረት በትዳር አለም አመታትን ላስቆጠረች ሴት እቤቷ ተጋብዞ ከመጣ ጓደኛ እንደዚህ አይነት ድፍረት ይጠበቃል....... ደፋር ከሆነ ለምን ስሙን አይተውም ነበር>>..ተሳለቅኩበት። ወረቀቷን አጣጥፌ ቦርሳዬ ውስጥ ሻጥ አድርጌ ወደቤቴ ለመሄድ መኪናዬን አስጓራሁ.. ከ 50 like 👍 በኋላ ይቀጥላል ..... 💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬
نمایش همه...

💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬ 👩‍💼 ናርዲ 👩‍💼 ክፍል ▭▭▭▭▭ 4⃣ ᐸᐸየትላንቱ ምሽት ላይ ምን ለየት ያለ ነገር አስተውለሻል>> መቼም ከእኔ ቢያመልጥ ከሷ አያመልጥም ብዬ ᐸᐸእንዴ ምን አይነት ጥያቄ ነው?>> ዙሪያ ጥምጥም ከመዞር ብዬ ወረቀቷን ከቦርሳዬ አውጥቼ ሰጠኋት:: አነበበችው ᐸᐸጸሀፊው ማነው የተጻፈውስ ለማን ነው?>> ወረቀቷን የት እንዳገኘሁ.... ከዚያም በኋላ ያከናወንኩትን ዘረዘርኩላት:: ᐸᐸእኔ አላምንም.....ወይኔ ናርዲ....እኔ ያላገባሁት እዚህ ቁጭ ብዬ አንቺ ሌላ አጠመድሽ 😂😁😁>> ተፍነከነከች ᐸᐸቀልዱን ተይና ምን ታስቢያለሽ>> ᐸᐸውይ በናትሽ አምስት ደቂቃ ስጪኝ በደንብ ልሳቅ....😂😂😂>> ᐸᐸጀመረሽ ደግሞ>> ᐸᐸእ..........ሺ ይህንን ወረቀት ትላንት ምሽት ከነበሩት አንዱ ቦርሳዬ ወስጥ ተወልኝ ነው የምትይው>> አይኖቿ ሁሉ ይስቃሉ:: ᐸᐸየስ>> አረጋገጥኩላት ᐸᐸከስምኦንም ሆነ ከሳሙኤል ጋር ተነጋግረሽ ያነሳብሽ የለም?>> በአወንታ አንገቴን አወዛወዝኩ ᐸᐸያ ማለት ደግሞ ጥርጣሬው ወደ ሰለሞንና አንተነህ......ኖ ኖ ኖ>> በተራዬ መሳቅ ጀመርኩ:: ᐸᐸእሱ ይሁንና ይህንን ቤቱን ነው እሳት የምለቅበት>> ተያይዘን በሳቅ አውካካን:: ᐸᐸናርዲዬ እኔ ግን አንቺን ብሆን ምን አደርግ እንደነበር ታውቂያለሽ በቀጥታ ለዮሀንስ ወስጄ ነበር የምሰጠው>> አልተጠራጠርኳትም:: ᐸᐸእኔ የምልሽ የእጅ ጽሁፉ የምታውቂው አይነት አይደለም? >> ጠየቀችኝ ᐸᐸአዲስ አልሆነብኝም ..ግን......እስቲ አስቢው ለመጨረሻ ጊዜ በአማርኛ መልእክት የተውሽበትን ወይም የተቀበልሽበትን ጊዜ .....እኔ በግምት አምስት አመት ይሆነኛል::>> ᐸᐸቦርሳሽ ለመሆኑ የት ነበር>> ᐸᐸበሩ አጠገብ ካለው የልብስ ማንጠልጠያ ላይ አንጠልጥዬው ነበር::የሚገርምሽ ከሁለት ቀን በፊት ከአንቺ ጋር የገዛሁት ቦርሳ እኮ ነው:የእኔ ቦርሳ ለመሆኑ እንዴት እርግጠኛ እንደሆነ.........>> ድንገት ወሬዬን አቋርጬ ᐸᐸሚሚ ምን አይነት ቦርሳ ይዛ ነበር።>> አልኳት ᐸ>ኦ...ኬ........>> ቤቱን በጩኸት አቀለጥነው::ሁሉም ነገር ግልጽልጽ አለልን:: ከእራት ግብዣው አንድ ቀን በፊት ሰብሊንና ሚሚን ከስራ ሰአት ውጪ ቀጥሬያቸው ነበር:: ለግብዣው የሚሆን ሽንኩርት ሊያላልጡኝ ነበር ቀጠሮው::ሰብሊ ከምትሰራበት ሱቅ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ ስፈልግ ሚሚ ቀድማ የሱቁን በር ተደግፋ ቆማ ነበር:: ᐸᐸየት ለመሄድ ነው እንዲህ የተለበሰው........አንቺ እኮ ስራውን እረስተሽው ይሆናል እንደዚህ ዝንጥ ብለሽ የመጣሽው>> አልኳት ወንድሟን አንተነህን ብላ ሁለት አመት የኖረችበትን ከተማ ጥላ ከመጣች ሶስት ወር ሊሆናት ነው....ባህሪዋን ወድጄላታለሁ.... ለክፉም ለደጉም እይታን ላለመልቀቅ በሚፈታተኑት ውብ ጥርሶቿ የታጀበ ፈገግታ ነው መልሷ:: ዛሬም ቅናት አይሉት ፍርሀት ላዘለው አስተያየቴ ፈገግታዋን ችራኝ ተያይዘን ከሱቅ ገባን::የሱቁ በሰዎች በሰዎች መሞላት አስገርሞኝ ሰብሊን በአይኔ መፈለግ ያዝኩ:: "እዚህ " እጇን አውለበለበችልን....... ተሽሎኩልከን አጠገቧ ደረስን:: በመሞከሪያ ክፍል ውስጥ ተሞክረው የሚተውትን ልብሶች በመስቀያ እያስተካከለች ነበር:: ᐸᐸምንድነው ጉዱ>> አልኳት ᐸᐸዛሬ እኮ ስምንት ነው>> ᐸᐸእና>> ᐸᐸእናማ ታላቅ ቅናሽ ከጀመረ ሁለት ቀን ሆነው>> ᐸᐸኦ....ምነው አልነገርሽንም ታድያ>^ ሚሚ ነበረች ከፈገግታዋ ጋር ᐸᐸኦ..ኦ....እናንተ እንድሆናችሁ ለሁሉም ነገር አስታዋሽ ትፈልጋላችሁ..... ለማንኛውም ያ የወደድሽው ቦርሳ ከግማሽ ሰአት በፊት ሰባ አምስት በመቶ ቅናሽ ሆኗል ሳያልቅ በፊት ውሰጂ>> አለችኝ ወደኔ ዞራ:: ᐸᐸየትኛውን>> አልኳት ግራ ገብቶኝ ᐸᐸባለፈው አክስቴ ይዛው የነበረውን ነዋ>> አክስቴ በሚል ቅጽል ስም የሚጠሯት በሀምሳ አመቷ የሀያ አመት ወጣት ለመምሰል ትንቅንቅ የያዘችውን የሱቁን ባለቤት ነው::በደቂቃ ውስጥ ከግርግሩ መሀል ገብታ ቦርሳውን ይዛ ተመለሰች:: ᐸᐸይኸው ሰላሳ አምስት ኢውሮ" አለችኝ እጇን ዘርግታ...ሚሚ ቦርሳውን ከእጇ ላይ አፈፍ አድርጋ ᐸᐸእውነትሽን ነው...........በዚህ ዋጋማ እኔም አልተወውም።>> አለች:: ሰብሊ ከጓደኞቼ ጋር ተመሳሳይ እቃ መግዛት አለመውደዴን ስለምታውቅ በአይኗ ምን ላድርግ አይነት አስተያየት አየችኝ::ሁኔታችንን ሚሚ እንድታስተውል ስላልፈለግሁ አይኖቼን ወደሚተራመሰው ገብያተኛ ወረወርኩ:: "ሌላ ከለር ካለው ቼክ አደርግልሻለሁ" ሰብሊ ግራ ተጋብታለች:: ᐸᐸኖ...ኖ....እኔም እንደዚህ ነጭ ነው የምፈልገው....ጥቁር ቦርሳ በብዛት ነው ያለኝ።>> አለቻት ቦርሳውን እያገላበጠች:: ሰብሊ አሁንም አንድ በዪኝ አይነት አይኖቼን በአይኖቿ ትፈልጋለች:: ᐸᐸወይ ጣጣ>> በሆዴ አጉተመተምኩ ከግማሽ ሰአት በኍላ ሰብሊ የስራ ልብሷን ቀይራ ከሱቁ ስንወጣ እኔና ሚሚ ተመሳሳዮቹን ነጫጭ ቦርሳዎች በፌስታል አንጠልጥለን ነበር:: ቶሎ ብለን እንጨርሰው like አድርጉና ይቀጥላል ..... 👮 የLike (👍) ምልክቷን አንድ ጊዜ ብቻ ይጫኑ ቁጥሩ በራሱ ጊዜ ይጨምራል ። 💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬
نمایش همه...
attach 📎

የቀጠለ.... ᐸᐸሰብሊ...ዛሬም ምን ይሰማኛል ብለሽ መጠየቅ የለብሽም......ይህ እኮ አመታት ያለፈው ታሪክ ነው።>> ᐸᐸሆነም ቀረ ደስታው ደስታዬ ነው>> ቡና የጠጣንበትን ስኒዎች አንስታ ብድግ አለች መደፍረስ የጀመሩትን አይኖቿን እንዳላይ ሽሽት መግባቷ ነበር:: እንዳለፉት አመታት ይሄንን አታድርጊ ይህንን አድርጊ ብዬ ልሞግታት አላሻኝም ምክሬ የተመሰቃቀለ ህይወቷን የበለጠ ከማመሰቃቀል ውጪ ምን ፈየደላት::በሷ የደረሰው ያልደረሰብን ወግ አጥባቂዎች ሁሉ ᐸᐸእርሺው ወንድ እሱ ብቻ ነው እንዴ>> እያልን ከመዘባበት ሌላ የተሻለ መንገድ ጠቁመናት አናውቅም...... ስለዚህ አንገቴን አቀርቅሬ ከንፈሬን ከመምጠጥ ሌላ ትንፍሽ አላልኩም:: አጉል የሆነ ዜና ይዤ በመምጣቴ አፈርኩ::ለነገሩ እኔስ መላ ፍለጋ መምጣቴ አልነበር መላው መለመላውን ይዞብኝ መጣ እንጂ:: ለብቻዋ ብተዋት የተሻለ እንደሚሆን ስላሰብኩ ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ለመሄድ ተነሳሁ:: ተንቀርዝዞ የነበረው እንባዋን ወደ መጣበት ብትመልሰውም የደፈረሱት አይኖቿ የስሜቷን ግብግብ አልደበቁላትም:: ᐸᐸትንፍሽ>> ራሴን አስጠነቀኩ:: ᐸᐸበይ ሰብሊዬ ነገ ስራ ገቢ ነሽ አይደል>> አልኳት ሁኔታዋን ልብ ያላልኩ መስዬ በአዎንታ ቅንድቧን ሰቀለች:: ᐸᐸነገ እደውልልሻለሁ>> ለስንብት ጉንጮቿን ከጉንጮቼ ሳላትም የሰውነትዋ ግለት ተሰማኝ:: ᐸᐸእሺ>> አለች ዝቅ ባለ ድምጽ.......ብቸኝነቱን እሷም ስለፈለገችው እንደወትሮዋ ᐸᐸአምስት ደቂቃ ብቻ.....>> የሚለው ልመናዋም አልነበረም:: በሩን ከጀርባዬ ዘግቼ የመኪናዬን ቁልፍ እያቅጨለጨልኩ አዘገምኩ:: ከስራቸው የመውጫ ሰአት ስላለፈ መንገዱ ከትራፊክ ትንቅንቅ ጋብ ብሏል::ቴፑ ቢያቀነቅንም ልቤ ግን ያለው ሰብሊ ጋር ነው::የስምኦንና የሚሚ መፋቀር በአንድ በኩል እንደሚጎዳት ሁሉ በአንድ በኩል ተስፋ ቆርጣ ህይወቷን እንድታደላድል ያደርጋት ይሆናል የሚል ተስፋ አድሮብኛል:: ምናልባት የሚስጥር ደብዳቤ ቅብብሉ ምክንያትም የሷን ስሜት ላለመጉዳት ይሆን ይሆናል::ዛሬም ቢሆን ስምኦን በአካባቢው ካለ ሰርሳሪ አይኖቹን ስትሸሽ ለአይኖቿ ማሳረፊያ ስትፈልግ ሁላችንም ታዝበናል:: የቤቴን በር ከፍቼ ስገባ የተከፈተ ውሀ ከባኞ ቤት ተሰማኝ::ዮሀንስ ቀደሞኝ ገብቷል::የሰአቱን መክነፍ ልብ አላልኩም ነበር:: ᐸᐸናርዲ አንቺ ነሽ>> አለኝ በሀይል የዘጋሁትን የበር ድምጽ ሲሰማ ᐸᐸማን ይሆናል ታድያ>> ᐸᐸምነው አመሸሽ ዛሬ>> ስለ ዛሬው ምሽት ምንም ላልነግረው ስለወሰንኩ በደፈናው ᐸᐸሰብሊ ጋር ነበርኩ>> አልኩትና ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ:: የራስጌው ሰአት ከምሽቱ ሰባት ሰአት ከሀያ ይላል:: እራት ከማዘጋጀቴ በፊት አንድ አፍታ ገላዬን ለመታጠብ ስለፈለግሁ ዮሀንስ ባኞውን እስኪለቅልኝ ድረስ በቁሜ ሙሉ አልጋው ላይ ተዘረጋሁ:: ከራስጌው ኮመዲኖ ላይ በስሜ ከባንክ የተላከ ፖስታ አግኝቼ ቀድጄ ማንበብ ስጀምር ዮሀንስ መለስ ያደረኩትን የመኝታ ቤቱን በር ከፍቶ ገባ:: ᐸᐸእኔኮ ሳጣሽ ሱፐር ማርኬት የሄድሽ መስሎኝ ነበር>> አለኝ ከተጋደምኩበት መጥቶ ጉንጮቼን እየሳመ:: ሰውነቱን የታጠበበት ሳሙና ሽታ መኝታ ቤቱን አላወደውም:: ᐸᐸከስራስ በሰአቴ ነው የወጣሁት በዚያው ሰብሊ ጋር ሄጄ ነው።>> አልኩት አይኖቼን ከወረቀቱ ላይ ሳልነቅል በዝምታ ምን ያህል ደቂቃዎች እንዳለፉ አላውቅም......በድንገት ᐸᐸሚሚ መጥታ ነበር እንዴ?>> አለና ጠየቀኝ:: ᐸᐸኸረ አልመጣችም ......ምነው>> አልኩት እንዳቀረቀርኩ ለጥያቄዬ መልስ ሳጣና ሚሚ የሚለው ስም ለዘጠና ዘጠነኛ ጊዜ ሲጠራ መስማቴ አስገርሞኝ ቀና ብዬ አየሁት..... አይኖቹ በድንጋጤ ፈጠው አልጋው ላይ ካስቀመጥኩት ቦርሳዬ ላይ ተተክለዋል:: 💕💞....ተፈጸመ....💕💕 💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬
نمایش همه...
attach 📎

💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬ 👩‍💼 ናርዲ 👩‍💼 ክፍል ▭▭▭▭▭ 3⃣ 📜...ተነስቼ ቡና ጣድኩ.....ቢያነቃቃኝ ብዬ ቡናዬን ፉት እያልኩ ሀሳቤም ከአንዱ ወደ አንዱ እንደዘለለ ደቂቃዎች ከነፉ:: ᐸᐸየፍቅርን ደብዳቤ ማንነቱን ከማያውቁት ሰው መቀበል ምን ትርጉም አለው:: ይህንን ሚስጥር ዛሬውኑ መፍታት አለብኝ::>> ዮሀንስ ከስራ እስከሚመጣ ሻወር ወስጄ አረፍ ለማለት የነበረኝን ሀሳብ ሰርዤ ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ወጣሁ:: ᐸᐸእርግጠኛ ነኝ ከሳሙኤል ወይም ከስምኦን አያልፍም:: በመጀመሪያ ሳሙኤልን አነጋግራለሁ.... .. ከዚያ............እግረ መንገዴን በስምኦን የስራ ቦታ አልፋለሁ....>> እያሰላሰልኩ ወደ ሳሙኤል ባር ለመሄድ በትራፊክ ብዛት ከተደረደሩት መኪኖች ስር ተወተፍኩ:: እንደ ዘወትር ቤቱ ሞቅ ብሏል::ቴዲ አፍሮ ሼመንደፈርን ያቀነቅናል::ስራ ላይ የሚያዘወትራትን ቀይ ኮፍያውን ሳይ በሩቁ ለየሁት....ሳሙኤልን ልቤ ድንግጥ አለብኝ:: ᐸᐸምንድነው የምለው......ቆይ እሱ ባይሆንስ....>> ᐸᐸአይ ናርዲ>> ቆምም ሳይል በሰሀን የተደረደሩትን ብርጭቆዎች ይዞ ወደ ውስጥ ተፈተለከ::ከአጠገቤ ያገኘሁት ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ:: እንግዶቹን ከዚያ ከዚህ እያለ ሲያስተናግድ በአይኔ ተከተልኩት:: በአጠገቤ ደጋግሞ እያለፈ መኖሬንም ከቁብ የቆጠረው አይመስልም:: አምስት ደቂቃዎች አለፉ:: ጠረጴዛውን ደገፍ ብዬ ለአፍታ አይኔን ጨፈንኩ:: "ናርዲ ምነው ደህና አይደለሽም እንዴ?>> አጠገቤ ደረሰ:: ᐸᐸእ..እ..ደህና ነኝ......ሊያን ፈልጌያት ነበር>> አልኩት አፌ እንዳመጣልኝ:: ᐸᐸፖስታ ቤት አሁን ሄደች ምናልባት አስር ደቂቃ ብትቆይ ነው::ከስራ ነው?>> ᐸᐸአዎ>> አይኖቼን አይኖቹ ላይ ተከልኩ ሚስጥር ያቀብሉኝ ይመስል:: ᐸᐸያቺ ከፈሷ የተጣላች ጓደኛሽ ማታ በሰላም ገባች>> አለኝ ፈገግ ብሎ ᐸᐸእንዴት ከናንተ ጋር አይደል እንዴ የወጣችው>> ᐸᐸእቤትሽ እናድርስሽ ብንላት እንቢ ብላ ታክሲ ጠርታ ሄደች>> ᐸᐸሞቅታዋን ወደ ስካር ልትለውጥ ነው....ወይ አለመጠጣት ወይ መስከር የሚለውን አላማዋን አልሰማህም እንዴ>> ᐸᐸቆይ ደበበ>> ሰብሊ ሼሂ እያለች የምትጠራው ባለ ሪዛሙ አበሻ እጁን አውለብልቦለት ሊወጣ ሲል መጣሁም ሳይለኝ ፊቱን አዙሮ ጥርግ አለ:: ግምቴ እንዳልሰራ ገባኝ::ሳሙኤል ያው የማውቀው ሳሙኤል ነው:: ᐸᐸእንኳን የወደዳትን ሴት ከፊቱ ያስቀመጠ ቀርቶ>> እያጉተመተምኩ ወደ መውጫው አዘገምኩ:: ᐸᐸቻዎ ሳሙ..ሌላ ጊዜ ብቅ እላለሁ>> ከሼኪ ጋር የያዘውን ወሬ እንዳላቋርጠው በጆሮው ሹክ ብዬው ወጣሁ:: የመኪናዬን ወንበር ተደግፌ ማሰላሰል ያዝኩ::ᐸᐸሳሙኤል ካልሆነ ስምኦን ነው ማለት ነው>> ወረቀቷን ለዘጠና ዘጠንኛ ጊዜ አነበብኳት::ድንገት ᐸᐸደውይልኝ>>የምትለው መልእክትን ሳይ .የእጅ ስልኬን አውጥቼ ስምኦን ጋር ደወልኩ.... ᐸᐸኦ ሂሩት>> ᐸᐸታድያስ ስምኦን>> ᐸᐸእንዴት ነሽ>> ᐸᐸአለሁ>>...የምለው ጠፋብኝ ᐸᐸእሺ.......>> ጠበኩ.....ሰከንዶች አለፉ:: ᐸᐸእ....ትላንት በሰላም ገባህ>> ተኮለታተፍኩ ᐸᐸአዎ በሰላም ገባሁ>> ᐸᐸቼክ ላድርግህ ብዬ ነው የደወልኩልህ>> ᐸᐸያን ያህል እኮ አልመሸም ነበር::>> የመደወሌ ምክንያት እንዳልተዋጠለት ጠቆም አደረገኝ::>> ᐸᐸእሱስ አዎ....>> የምለው አልነበረኝም:: ተሰናብቼው ስልኩን ዘጋሁ.:: ᐸᐸስምኦንም አይደለም ማለት ነው:: እና ማን ሊሆን ነው>> ለምን አልተወውም ጊዜ ይፈታው የለ::የአንድን ነገር መጨረሻ ካላወቀች የማታርፈው ልቤ ተሟገተችኝ:: ለመጨረሻ ጊዜ ሰለሞን ጋር ደውዬ ለማጣራት አሰብኩ::ግን ድፍረቱን አላገኘሁም::አንድ ቀን እንኳን በአካል ቀና ተነጋግረን የማናውቅ ሰዎች ጭራሽ በስልክ ምን ልንባባል እንደምንችል አሰብኩና ወዲያውኑ ሰረዝኩት:: ᐸᐸኤጭ.....>> አደባባዩን ዞሬ የቤቴን አቋራጭ መስመር እንደያዝኩ የእጅ ስልኬ ተንጫረረ:: ᐸᐸሄ-ሎ>> ᐸᐸቻ......ዎ>> ሰብሊ ነበረች እያዛጋች ᐸᐸገና መነሳቴ ነው እንዳትይኝ>> አልኳት በመገረም ᐸᐸከነጋ እኮ ነው የገባሁት>> ᐸᐸየት ነው ያለሽው?>> ᐸᐸውይ ናርዲ ደግሞ የሚጠየቅና የማይጠየቅ ነገር አታውቂም >> ᐸᐸእንዴ ፈልጌሽ ነው.....እንዴት አይነት ስራ አግኝቼልሻለሁ መሰለሽ>> አልኳት ᐸᐸመች ፈልጊልኝ አልኩሽ እንደውም ያለኝንም ውሰጂልኝ>> አለችኝ እየሳቀች ᐸᐸየት እንዳለሽ ነገሪኝ......ይልቅ>> ᐸᐸአ-ን-ተ-ነ-ህ ቤት ነኝ >>ቃላቶቹን ጉትት አደረገቻቸው ᐸᐸአ..ሀ.......>>ዛሬም እንደወትሮዬ አንተነህን ደግፌ ለመከራከር ጊዜ አልነበረኝምና ከአስር ደቂቃ በኍላ እንደምደርስ ነግርሪያት ስልኩን ዘጋሁ:: ᐸᐸቡና >> አለችኝ እቤት እንደገባሁ:: በአዎንታ አንገቴን ነቀነቅኩ:: ጸጉሯ ተንጨፍሯል.:: ያለቀቀ ማስካራዋ የአይኗን ዙሪያ አጥቁሮታል::ከዳሌዋ የቀረች ሳሳ ያለች ቲሸርት ለብሳለች:: የአንተነህ ለመሆኑ አልተጠራጠርኩም:: ᐸᐸወይኔ ሰብሊ ከእንቅልፍሽ ስትነሺስ አንቺን አለማየት ነው ሞረቴ እኮ ነው የምትመስይው>> ገላመጠችኝ ᐸᐸስሚ እንጂ >>አልኳት ቡናችንን ይዘን የምግብ ጠረጼዛው ላይ ቁጭ እንዳልን:: ይቀጥላል ..... 👮 የLike (👍) ምልክቷን አንድ ጊዜ ብቻ ይጫኑ ቁጥሩ በራሱ ጊዜ ይጨምራል ። 💞 @ethio_fiction ➰▭▬▭▬
نمایش همه...

ዘመም ይላል እንጂ (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፤ እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ ፤ ታምር ነው መኖሬ:: የበጎ ሰው ሀሳብ ፤ ሲካድ እለት በለት ጉድጏድ ተምሶለት ሰብእና ሲቀበር፤ በዚህ ምድር መኖር ፤ አያስመኝም ነበር:: ምድሩ ሳር ቅጠሉ፤ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፤ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር ፤አያስመኝም ነበር:: አዎ ለጊዜውም ቢሆን፤ ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፤ ወደ ፊት ይጏዛል በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ፤ ሚስቱን ያስረግዛል:: ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው ፤ ቢሆን የሞት ሽረት ዳገት ይወጣሉ ፤ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ ፤ ተገርስሶ አይወድቅም::
نمایش همه...
አንዳንዴ ህይወት በሲሲፈሳዊ ንውዘቷ ስታታክተን -ተግ ብለን በናርሲሳዊ ስሜት ድልን እንቀዳጃለን። ለራስ ባለን ፍቅር ወዝ እንጨልፋለን። ያማርን የቆነጀን መሆናችንን ለራሳችን እንዘክራለን። ይኽ የሚያነቃቃን ራስን የመውደድ ስሜት የህይወት ሌላኛው ወጥመዷ ቢሆንም አፍታ ከዚያ ከድግግሞሻዊ አድካሚ እሽክርክሪት አርፍ እንላለን። በውዴታችን ባህር ጠልቀን እስክንቀር ፈገግ እንላለን። ደግሞ ወዛችን ተመጦ እስክንገረጣ ደመ ግቡ እንሆናለን። ህይወት ሁለት ገጽ አላት። አንዱ በውጫዊው አለም ቀኖና የሚያቆረቁዝ ሲሆን ሌላኛው በራሳችን ውስጣዊ ኃይል የሚቀይደን ነው። ሆኖም ሰው መሆን ሌላ ዕድል ፈጣሪ ያደርጋልና በሁለቱ አጣብቂኝ አማራጮች መሀል በሚያገናዝብ አእምሮ ሶስተኛ አማራጭ ይፈጠራል። ለውጩም (ለሲሲፈሳዊው) ሆነ ለውስጣዊው (ለናርሲስቱ) ጠፍናጊ ኃይሎች ሚዛናዊ ተገዥ የመሆን እሳቤ ያመነጫል። ይኽቺ ንቃት ላይ የደረሰ ሁሉን እንዳመጣጡ በአማን ያስተናግዳል። በይሁንታ ይቀበላል። ለፍቺና ለትርጓሜ ሳይሆን ለነፃነቱ ይታዘዛል። ያኔ ሲሲፈሳዊነትና ናርሲሳዊ እስራቶች ይበጣጠሳሉ። መሰልቸትና ሽንፈት ይወድማሉ። ሠላም ታብባለች። ደስታ ለብ ለስለስ እንዳለ ንፋስ ትሆናለች። ቁርና ሐሩራዊነት ይጠይማሉ። @ዘቢደር!
نمایش همه...
የማይረግፍ አበባ ከልቤ ተቀምጦ የሚያቁነጠንጠኝ፣ ከውቦቹ መሀል ተመርጦ የተሰጠኝ፤ አባባዬ ሳለህ በልቤ የበቀልክ፣ ረጋፊ አበባ ለምን ታመጣለህ??? አንተ ብቻ ለኔ እኔም ላንተ ብቻ፣ ሲያጣምራት ነፍስህ አርጓት የነፍሴ አቻ፤ ቃል-ኪዳን ተጽፎ ከቀይ አባባ ላይ፣ ጸሀይ ሲበረታ ጠውልጎ እንደሚታይ፤ ሲያድሉ እየኖሩ ቀጥፈው ለሚጥሉት፣ አትሁን ምሳሌ. . . .!!! ቃል-ኪዳን ተናዘው ቃል-ኪዳን ‘ሚበሉት፡፡ እናማ የኔ ውድ፡- በፍቅር ለተረታው በድን አካላቴ፣ ገና እንዳየሁህ ለዛለው ጉልበቴ፤ ከጎኔ ስትቆም አብረህ ስትራመድ፣ አለሁልሽ ስትል ከጎኔ ስትሄድ፤ ነውና ደስታዬ በአበባ አትደልለኝ፤ እንደምታፈቅረኝ ቀድሞ የነገረኝ፤ ዓይነ-ውሀህ ብቻ ከአይኔ አይለየኝ፤ እኔ እንደማፈቅርህ -ከልብህ አፍቅረኝ፡፡
نمایش همه...
ሁሉም ሀዘኖቻችን ምንጫቸው የገዛ ራሳችን የራስ ወዳድነት ስሜት ነው። ለራስ የምንሰጠው ግምት በምን ልክ እንደተሰፈረ ካወቅን ደስተኞች መሆን አይሳነንም። ስንራመድ ጠልፎ የሚጥለን ሆነ አበርትቶ ከመሻታችን የሚያደርሰን ሚዛናዊነት ያለው የራስ ወዳድነት ስሜት በውስጣችን የዳበረ ለት ነው። ስናፈቅር ጉዳያችን ፍቅር ውስጥ መሆን ብቻ ከሆነ ሚዛናችን አልተዛባም። ልካችን መልኩ አምሯል። ማፍቀር ያፈቀሩትን አካል የራስ ማድረግ ላይ ካነጣጠረ ይኽ የራስ ወዳድነት ስሜታችን የፈጠረብን ድንቁርና መሆኑን ልብ ልንል ይገባል። በራሳችን ላይ የፈጠርነው ሽባነት በሉት። ራስ ወዳድነት ጥቅም ላይ ሲያነጣጥር በፍቅር አብሮን የነበረ ሰው ሲለየን የልብ ስብራት፣ ሀዘንተኝነትና ቁጣ በውስጣችን ይፈጠራል። ይኽ ግንዝነት መሰረቱ ግብዝ የራስ ወዳድነት ስሜት ነው። ትላንት ልብ ለልብ የተጣመርነው ሰው ዛሬ ከእኛ ሲለየን በልባዊ ውዴታ ስቀን እንሸኘው። አፍቅሮታችንም እንዲቀጥል በልቦቻችን ፍቃደኛ እንሁን። ይህ ነው የእውነተኛው ፍቅር መገለጫ። ሲወሃዱን በእልልታ መፈንጠዝ፣ ሲለዩን እዮዮ ማላዘን ከጥቅመኝነት የመነጨ የስብእና መዛነቅ ነው። ያ ዶስቶቭስኪ <<በምድር ላይ ታላቁ እድለ ቢስነት ማፍቀር አለመቻል ነው።>> ይለናል። ጉዳያችን ፍቅር ሲሆን ማፍቀር አለመቻላችን ብቻ ነው የተስፋ እጦትና የህይወት ትርጉም የሚያሳጣን። ማፍቀር ከተካን ግን አለቀ ህይወት ከነቡግሯ ውብ ነች። በበኩሌ በፍቅር ውስጥ ሁኘ ያፈቀርኩትን ለራሱ ልባዊ ፍቃድ ነፃ አደርገዋለሁ። በፍቅር ካቀፍኩት አበባ በላይ የፍቅር ስሜት ውስጥ መሆኔ ነው የሚያስደስተኝ። ማግኘትና ማጣት ሌላ ተራ የወረተኝነት ስሜቶች ናቸው። መሰረትህ ያፈቀርከውን ማግኘት የሚል መርህ ሲሆን መዳረሻህ ራስን መናቅና የተፈላጊነት ስሜት ማጣት ይሆናል። ይኽን ቀንበር ራሳቸው ላይ የሚጭኑ እነሱ ካለሌላ ሰው ድጋፍ መቆምና መራመድ የማይችሉ ደካሞች ናቸው። ቀና ማለት የሚያምረው በውብ ስብዕና፣ ራስን ከጥቅመኝነት በማላቀቅ ሲሆን ነው!! አፍቅሩ ነገር ግን ያፈቀራችሁ የእኔ ብቻ ይኹን አትበሉ!! ደስታችሁም መሠረቱ በፍቅር ላይ እንጂ በተፈቃሪው ትካሻ ላይ አይሁን!! @ዘቢደር! ሸግዬ አመሻሽ ይኹንልን!
نمایش همه...
Repost from ቀሰም Academy
ተማሪዋን እንርዳት...አድሚሽን ካርዷን ባስ ውስጥ ጥላ ወረደች.. 😔 የ ጀነራል ዋቆ ጉቱ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነቺው እና የፊታችን ሰኞ ሀገር አቀፍ ፈተና የምትወስድ RADIA EDIRIS BUNKA የተሰኘች ተማሪ አድሚሽን ካርዷን ባስ ውስጥ ጥላ ወርዳለች... ያለ አድሚሽን ካርዱ ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ መቀመጥ አትችልም ለዚህም ሲባል የ ጀነራል ዋቆ ጉቱ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምታውቁ ሰዎች ለትምህርት ቤቷ እንድታሳውቁላት በትህትና እንጥይቃቹዋለን 🙏🙏 አድሚሽን ካርዱን 0910222366 ጋር ይገኛል 👉 #Share ያድርጉ 🙏    
نمایش همه...