fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ | Unity Gebi Gubae

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ | Unity Gebi Gubae

رفتن به کانال در Telegram

በኢ.ኦ.ተ.ቤ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። በግቢ ጉባኤያችን የሚከናወኑ ተግባራት፣ መረጃዎችንና መልእክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል። Instagram: https://www.instagram.com/unitygebigubae TikTok: https://www.tiktok.com/@unitygebigubae

نمایش بیشتر
2 325
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+207 روز
+11730 روز
آرشیو پست ها
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ" ማቴ 26፥41 ወርኃዊ የመሐረነ አብ ጸሎት የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በግቢ ጉባኤያችን በወሩ የመጨረሻ አርብ
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ" ማቴ 26፥41 ወርኃዊ የመሐረነ አብ ጸሎት የእግዚአብሔር  ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በግቢ ጉባኤያችን በወሩ የመጨረሻ አርብ የመሐረነ አብ ጸሎት እንደምናደርስ ይታወቃል። ስለሆነም የፊታችን አርብ መሰከረም 29/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 - 12፡00 በመገኘት ስለ ሀገራችን ፣ ስለ ሃይማኖታችን ፣ ስለ ማኅበራችን ፣ የትምህርት ዓመታችንንም በሰላም አስጀምሮ ያስፈጽመን ዘንድ በኅብረት ወደ ፈጣሪያችን እንጸልይ ስትል ግቢ ጉባዔያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ለበለጠ መረጃ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እምዓጽሙ፤ ለዘአምኀኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ፤ ለተአምርኪ አኀሊ እሙ፤ ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፡፡ — አበባ ከአጽሙ ወጥቶ
ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እምዓጽሙ፤ ለዘአምኀኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ፤ ለተአምርኪ አኀሊ እሙ፤ ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፡፡ — አበባ ከአጽሙ ወጥቶ ታየ። ስለዚህም ማርያም የተአምርሽ የጣዕሙ መዓዛ ባማረኝ ጊዜ ስሙ ማኅሌተ ጽጌ በሚባል ምስጋና እዘምርልሻለሁ (አመሰግንሻለሁ)። ማኅሌተ ጽጌ
✨እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ዘመን (ወርኀ ጽጌ) እንዲሁም ለግቢ ጉባኤያችን የመስከረም ወር የጽዋ መርሐግብር  በሰላም አደረሳችሁ! ✨ እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የዓመቱ መጀመሪያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የጽዋ መርኃግብር ይኖረናል። በዕለቱም ጸሎት፣  ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ፣ የኅብረት ዝማሬ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርኃግብራት  ስለሚኖሩ ሁላችንም ተጠራርተን በመምጣት በዓሉን አብረን እንድናከብር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች 🙏 ሁላችንም ወንድም እና እኅቶቻችን በመጥራት በዓሉን አብረን እናከብር ዘንድ የእርሱ የአምላካችን ልኡል እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንልን! አይቀርም!!! 📆 ቅዳሜ መስከረም 30 ፤ 2019 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 06:00 ጀምሮ አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

🌹 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹            🌹 #መስከረም ፳፮ (26) ቀን። 🌹 እንኳን  ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ ለፈቃድ ጾም ለጽጌ ጾም (ለዘመነ ጽጌ) እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                                                      ✝ ✝ ✝ 🌹 የዘመነ ስደት መታሰቢያ ለምን በዚህ ጊዜ ሆነ? ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5። 🌹  እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ስደትን የጀመረችው ጥር 3 ነው፥ አገረ ግብጽ የገባችው ግንቦት 24 ነው፥ በግብፅ እና በኢትዮጵያ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ከቆዩ በኋላ ስደቱ አብቅቶ ተመለሱ ብሎ መልአኩ ሲነግራቸው ካሉበት ተነስተው ቁስቋም ከተባለች ቦታ ኅዳር 6 ደርሰዋል ። 🌹የስደት መታሰቢያ ለምን በመነሻው ጥር 3 አልሆነም? ይህ ወቅት ዘመነ አስተርእዮ የደስታ ጊዜ ነው ታኅሣሥ 29 ልደቱን ጥር 11 ጥምቀቱን የምናከብርበትና በልደቱ እና በጥምቀቱ የተደረገልንን እያሰብን ደስ የምንሰኝበት ጊዜ በመሆኑ ለስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም። 🌹 ግንቦት 24 አገረ ግብፅ የገባችበትን ይዘን ለምን ስደትን አናስብም? 🌹 ግንቦት 24 በዓለ ሃምሳን የምናከብርበት እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ጌታችን በትንሳኤው የሰጠንን ነጻነት የምናስብብት ደስ የምንሰኝበት ጊዜ ስለሆነ መስገድ መጾም ስለማይፈቀድ የስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም። 🌹 ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ዕፅዋት አበባን ፍሬን የሚያሳዩበት ወቅት ነው። 🌹 ወቅቱ ለምሳሌ የተመቸ ነውና። "ትወጽእ በትረ እምሥርወ እሤይ ወየዓርግ ጽጌ እምኔሃ"  ኢሳ 11፥1 እንዲል የዕሤይ የዘር ግንድ ከተባለች ከእመቤታች ጽጌ ጸኣዳ ወቀይህ የተባለ የፍጥረት ሁሉ ጌጥ ጌታችን የተገኘ ነውና በዚህ መስሎ ለማስተማር የሚያመች ወቅት ነውና። በተጨማሪም ጽጌ በእመቤታች ፍሬ በጌታችን ይመሰላል። 🌹 #አንድም፦ ተመለሰ ከማለት በፊት ተሰደደ ማለት ይቀድማል። 🌹 በዓመት ውስጥ ያሉት የወራት ቅድመ ተከተል ኅዳር 6 ከጥር 3 እና ከግንቦት 24 ይቀድማል። ኅዳር ላይ ከስደት ተመለሰ ብለን ካከበርን በኋላ ጥር ተሰደደ ግንቦት ግብፅ ገባ ብንል አመቺ አይደለም። ስለዚህ ከጥር 3 ወይም ከግንቦት 24 ይልቅ ኅዳር 6 መታሰቢያ ለማድረግ አመቺ በመሆኑ ቤተክርስቲያን በዚህ ወቅት የስደቱን መታሰቢያ ታደርጋለች። 🌹 በቅዱስ ያሬድ አባባል ስደት ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 20 ሲነገር፤ ከጥቅምት 21 እስከ ኅዳር 6 ድረስ ሚጠት (መመለሳቸው) ይነገራል። ይኼውም ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት የሚለው ሰላም እንዲቀርብ በማኅሌት ስለተወሰነ ነው። ምንጭ፦ አምኃ ሥላሴ መኩሪያ ተስፋዬ። 🌹 ጾሙ ከአገራችን ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያጠፋ እና ሰላም፣ ፍቅርን አንድነትንና መተሳሰብ የሚያመጣ ያድርግልን። መልካም ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።                    የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

ሰላም እንዴት ናችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ እንደምንስ እስከዚህች ሰአት ደረሳችሁ? አሜን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ገናና ስም የከበረና የተመሰገነ ይሁን🙏 እንኳ
ሰላም እንዴት ናችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ እንደምንስ እስከዚህች ሰአት ደረሳችሁ? አሜን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ገናና ስም የከበረና የተመሰገነ ይሁን🙏 እንኳን ለ፳፻፲፱(2019) ዓመተ ምኅረት የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ መርኃግብር መክፈቻ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ🥰 ክረምቱን ባማረና እና በእግዚአብሔር መግቦት እንዳሳለፋችሁት ተስፋ እያደረግን ፤ እንደሚታወቀዉ የ 2019 የትምህርት ዘመን እንደተጀመረ ይታወቃል ፤ ስለሆነም የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ መርኃግብሩን ነገ ሰኞ 25/01/2019 ዓ.ም ለመጀመር አስቧል። ስለዚህ ሁላችሁም ከላይ በተቀመጠዉ መርኃግብር መሠረት እየተጠራራን እንሳተፍ ዘንድ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።   ሰላመ እግዚአብሔር  ከሁላችንም ጋ ይሁን አሜን !! ለበለጠ መረጃ 0912947576 0978419497 የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

#መስከረም_21 #ብዙኃን_ማርያም በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም 21 ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤ #ጉባዔ_ኒቅያ በ325 ዓ.ም አርዮስ የሚባል መ*ና**ፍ*ቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአር*ዮስ ክህ*ደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡ በዚህም መሠረት ከሚያዝያ 21 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ 2348 ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡ ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር 9 ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ2348ቱ መካከል 318 ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ 318ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት 318ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው (ዘፍ.14፥14)፡፡ 318ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር 9 ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም 21 ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡ #ዕፀ_መስቀል በሌላ በኩል መስከረም 21 ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤ ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡ ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡ መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ1446 ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም 21 ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

➕➕➕ በዓለ ቅዱስ መስቀል ➕➕➕ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ “መስቀል” የሚለው ቃል ሦስት መሠረታዊ ቁም ነገሮችን ያመለክታል፡፡ ፩. የመጀመሪያው ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሞተ ነፍስ ለማዳን ሲል የተቀበለው መከራና የከፈለው መሥዋዕትነት (የክርስቶስ መከራ መስቀል) ነው፡፡ ፪. ሁለተኛው  ደግሞ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥም ልዩ ልዩ ዓይነት መከራም (መከራ መስቀለ ክርስቲያን) ነው፡፡ ፫. ሦስተኛው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው፡፡ በሦስቱም ቁም ነገሮች ነገረ መስቀል (የመስቀሉ ነገር) ከክርስትና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡  መስቀል የሰላማችንና የድኅነታችን የመቀደሳችን ዓርማ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን፥ የዘላለም ሕይወትን ለመስጠት መስዋዕትነት የከፈለበት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት መንበር፥ ሲሆን አምላካችንን የምንመለከትበት መስታወታችን ነው (ገላ.፫:፩ ፣ ፩.ቆሮ.፩:፲፰ ፣ ገላ.፮:፲፬) ። መስቀል በዘመነ አበው 👇 በዘመነ አበው መስቀል የመባረኪያ ምልክት እንደነበረ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሷል፤ ዘፍጥረት ላይ ፤ ‹‹ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ የዮሴፍን ልጆች በእምነት ባረካቸው›› ‹‹እጆቹን በኤፍሬምና በምናሴ ላይ በመስቀል ምልክት አድርጎ ጭኖ ባረካቸው›› ይላል፡፡ (ዘፍ. ፵፰፥፲፩ ፤ ዕብ. ፲፩፥፳፪) ዛሬም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህኑ ቀድሶ በሚወጣበት ጊዜ በእጆቹ ይባርካል፤ ይህም የሚያሳየው ቤተ ክርስቲያኗ መሠረቷ ከላይ በዓለመ መላእክት ከታች ደግሞ በዘመነ አበው ያየነው መስቀል መሆኑን ነው፡፡ መስቀል በብሉይ ኪዳን 👇 መስቀል በብሉይ ኪዳን እንደየሀገሩ ሁኔታ ልዩ ልዩ ተግባራት ሲፈጸምበት ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ፡- ፩. ለወንጀለኞች መቅጫነት አገልግሏል (መ.አስ. ፯፥፱ ፣ ዘዳ. ፳፩፥፳፩-፳፫) ፪. ለአርማ ይጠቀሙበት ነበር (ዘጸ. ፲፬፥፲፮ ፣ መዝ.፶፱:፫-፬) መስቀል በሐዲስ ኪዳን 👇 መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ፣ ሰው ሆኖ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በመስቀል ተሰቅሎ፣ ድኅነትን ለሰው ልጆች ሰጥቶ፣ በመስቀሉ ተጣልተው የነበሩ ሰባቱን መስተጻርራን (ሰውና እግዚአብሔርን መላእክትና ሰውን፣ ነፍስና ሥጋን፣ ሕዝብና አሕዛብን) አስታርቋል፡፡ መስቀል በሐዲስ ኪዳን የመዳን ምልክት መሆኑ የተረጋገጠበት በክርስቶስ ደም የተቀደሰ፣ የጠብ ግድግዳን ያፈረሰ፣ ቅድስናና ክብር ያለው የአበው ተስፋ የተፈጸመበት፣ ሰው ከውድቀቱ የተነሳበት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማእከለ ምድር … እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፤ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ›› (መዝ. ፸፫፥፲፪) መድኃኒት መስቀል መድኃኒት ክርስቶስን ተሸክሞ ታየ (ዮሐ. ፲፱፥፲፯ ፣ ኤፌ. ፪፥፲፮ ፣ ቆላ. ፩፥፳)፡፡ ደመራ 👇 ደመራ ማለት መጨመር፣መሰብሰብ፣መከመር ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ደመራ የሚለውን ቃል ደመረ ከሚለው የግእዝ ቃል አውጥተው ደመራ ግእዝና አማርኛን ያስተባበረ መሆኑን ገልጸው የበዓለ መስቀል ዋዜማ እንጨቶች የሚደመሩበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ ከቁስጥንጥንያ ተነሥታ ከጌታችን መድኃኒችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡ ኢየሩሳሌም በደረሰች ጊዜ የጌታችን መስቀል ተአምራትን እንዳያደርግ አይሁድ በምቀኝነት ቀብረውት ነበርና የተቀበረበትን ቦታ የሚያሳያት አጥታ በመፈለግ ብዙ ጊዜ አሳለፈች፡፡ በኋላ ግን አንድ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊ አካባቢውን ነግሯት መስከረም ፲፮ ቀን ደመራ አስደምራ ዕጣን አጢሳ ወደ ፈጣሪዋ ብትማፀን የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ መንበረ ጸባዖት ደርሶ ተመልሶ መስቀሉ የተቀበረበትን ስፍራ አመለከታት፡፡ እርሷም በምልክቱ መሠረት ብታስቆፍር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኘች፤ ከእርሱ መስቀል ጋር ሁለት ወንበዴዎች የተሰቀሉበትን መስቀል አብራ አግኝታው ስለነበር የጌታችን መስቀል ለይታ ያወቀችበት መንገድ ግን ድውያንን በመፈወሱ፣ አንካሳ በማበርታቱ፣ ጎባጣን በማቅናቱ የዕውራንንም ዐይን በማብራቱ ነው፡፡ ስለዚህም በየዓመቱ የመስቀልን በዓል ስናከብር ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒን አብነት በማድረግ ነው፡፡ እርስዋም መስከረም ፲፯ ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲ ቀን መስቀሉን አግኝታ አስወጥታ የቤተ ክርስቲያኑም መሠረት ወዲያው እንዲጣል አደረገች። ከዓመታት በኋላም መስከረም ፲፮ ቀን ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል። የቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ በዓላት 👇 1. መስከረም ፲ (ተቀጸል ጽጌ/አፄ ዳዊት መስቀሉን ወደ ሀገራችን ያስገቡበት ዕለት) 2. መስከረም ፲፮ (ቅዳሴ ቤቱ) 3. መስከረም ፲፯ (አይሁድ ከቀበሩበት ስፍራ ይገኝ ዘንድ ቁፋሮ የተጀመረበት። አንድም የመጋቢት ፲ በዓሉ በዐቢይ ጾም ምክንያት ተውላጥ ስለሆነ) 4. መስከረም ፳፩ (መስቀሉ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ግሸን ደብረ ከርቤ የገባበት ዕለት) 5. መጋቢት ፲ (ተቆፍሮ የተገኘበት) 6. መጋቢት ፳፯ (ጌታችን ተሰቅሎ መስቀሉን የቀደሰበት ዕለት) 7. ነሐሴ ፲፪ (ለቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የተገለጠበት) 8. ነሐሴ ፲፬ (በተአምሩ አይሁዳዊውን የገደለበት) ለመላው የግቢ ጉባኤ አባላት እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል። ➕➕➕ ስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ዕፀ ሣህል ➕➕➕

እንቁጣጣሽ❤ እንኳን❤ ከዘመነ 🌹ማርቆስ 🌹ወደ ዘመነ 🌹ሉቃስ❤ ለዘመን መለወጫ🌹 በዓል በሠላም አደረሰን🌹 አደረሳችሁ 🌹 በዓሉን ያለ ፀብ ~በፍቅር🌹 ያለ ህመም ~በጤና❤ ያለ ቂም ~በይቅርታ
እንቁጣጣሽ❤ እንኳን❤ ከዘመነ  🌹ማርቆስ 🌹ወደ ዘመነ 🌹ሉቃስ❤ ለዘመን መለወጫ🌹 በዓል በሠላም አደረሰን🌹 አደረሳችሁ 🌹 በዓሉን ያለ ፀብ ~በፍቅር🌹 ያለ ህመም ~በጤና❤ ያለ ቂም ~በይቅርታ🌹 ያለ  ሀሜት ~ በፀሎት ❤ ያለ  ስስት ~በምፅዋት🌹 ያለ ክፋት -በቅንነት ♥️ ያለ ሀጢአት~በቅድስና🌹 ለማክበር የእናቱና የልጇበረከት ከሁላች ጋር ይሁን። ወስብሐት ለእግዚአብሄር።❤ መልካም🌹🌹🌹አዲስ ዓመት🌹🌹🌹!!!

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ መንፈስቅዱስ ስም ጳጉሜን 3 በዚህች ቀን የረድኤት የፈውስ መልአክ የተባለ፣ በመናብርት ላይ ለተሾመ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የሲመቱና የቅዳሴ ቤቱ በአል ሆነ። ይህቺ ቀን የፍጡር ሁሉ ጸሎት የሚሰማባት፣ መተትና ስራይ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት የሚደመሰስባት፣ የአጋንንት ስራ የሚፈርስባት፣ የረድኤት፣ የበረከት፣ የጸጋ ሁሉ ቀን ነችና፣ ሁላችንም በአቅማችን ጸሎት እናደርግ ዘንድ፣ አንዳችንም ሌላዎችን እናስብ ዘንድ ይገባናል። ዳግመኛም በዚህች ቀን ለዘመኑ ጥንትና ፍጻሜ የለውም ተብሎ የተነገረለት በእግዚአብሔር እጅ  ካህን እና ነቢይ ሆኖ ሊሾም፣ የክርስቶስም ምሳሌ ሊሆን የተገባው ታላቁ ቅዱስ መልኬጼዴቅ በሰላም አረፈ። እግዚአብሔር አምላካችን በቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ይማረን፣ በረከታቸውም ከኛ ጋር ይሁን አሜን። እንኳን ፈታሔ ማህጸን፣ ዐቃቤ ሥራይ ለተባለ ለታላቁ መልአክ  ለሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በአል አደረሳችሁ።

"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ" ማቴ 26፥41 ወርኃዊ የመሐረነ አብ ጸሎት 🤲 የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በግቢ ጉባኤያችን በወሩ የመጨረሻ
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ" ማቴ 26፥41
ወርኃዊ የመሐረነ አብ ጸሎት 🤲 የእግዚአብሔር  ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በግቢ ጉባኤያችን በወሩ የመጨረሻ አርብ የመሐረነ አብ ጸሎት እንደምናደርስ ይታወቃል። ስለሆነም የፊታችን አርብ ነሐሴ 29/11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 - 11፡00 የአመቱ የመጨረሻው የመሐረነ አብ ጸሎት ስላለ ሁላችሁም በመገኘት ስለ ሀገራችን ፣ ስለ ሃይማኖታችን ፣ ስለ ማኅበራችን በኅብረት እንጸልይ ስትል ግቢ ጉባዔያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ለበለጠ መረጃ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

✨እንኳን ለአቡነ ተክለሃይማኖት አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✨ የአቡነ ተክለሃይማኖት ታሪክ   ከአባታቸው ከጸጋ ዘአብ (ዘርአ ዮሐንስ) እና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኅረያ (ሣራ) በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት በመጋቢት 24 1196 ዓ.ም ተጸንሰው በዕለተ ሰኞ ታህሳስ 24 1197 ዓ.ም በቡልጋ፣ ሸዋ በዘመነ ዛግዌ ሥርወ መንግሥት በቅዱስ አፄ ነአኩቶ ለአብ ዘመን ተወለዱ ። እንደተወለዱም ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመሰገኑ። በ3ተኛውም ቀን ደግሞ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግናዋል። ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍስሐ ጽዮን አሏቸው።ይህም የጽዮን ደስታ ማለት ነው በእመቤታችን አማላጅነት ተወልደዋልና:: ከአባታቸው ጸጋ ዘአብ ሥርዓተ ቤ/ክ እየተማሩ በ15 እና በ22 ዓመታቸው በዘመኑ ከነበሩት ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ዘእስክንድሪያ ዲቁና እንዲሁም ቅስና ተቀበሉ። ከጓደኞቻቸው ጋር ለአደን ወደ ጫካ በወጡ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላችው፤ "እኔ እናትና አባትህን ስለአንተ ከውሃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኩኝ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ" አላቸው በታላቅ ብርሃን ተገልጦላቸው ባዩት ጊዜ አላወቁትም ነበርና። ደግሞም እንዲህ አላቸው "ከእንግዲህ ሙታንን ታስነሳለህ፣ ደውያንንም ትፈውሳለህ፣ አጋንንትም ከአንተ ይሸሻሉ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ፍስሐ ጽዮን አይሁን ተክለሃይማኖት እንጂ" ብሏቸው ከአጠገባቸው ተሰወረ (ተክለሃይማኖት ማለት ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ወይንም የሥላሴ ተክል ማለት ነው) ። ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሐዋርያቱ ጋር ተገልጦላቸው "ባንተ ብዙ ተአምራትን ያደረግሁብህ በእናት በአባትህም ቤት ረሃብ በነበረበት ጊዜ ምግብ እንዲመላ በእጅህ ሀብተ በረከትን ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ" ብሎ ንሣእ(ውሰድ) መንፈስ ቅዱስ ብሏቸው የሹመት ሀብትን ሰጣቸው። እንደ ሐዋርያቱም "በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው በሰማይም የተፈታ ይሆናል፤ አንተን እምቢ ያለ እኔን እምቢ አለ ወንጌል በሌለበትም ቦታዎች ሕዝብን አስተምረህ ታጠምቃለህና ስምህን ተክለሃይማኖት ብየዋለሁ። ቅዱስ ሚካኤልም በምትሰብከው ነገር ሁሉ ረዳትህ ይሆንሃል እኔም ከአንተ አልለይም" ብሎ የክህነትን ስልጣን ሰጥቷቸው ከአጠገባቸው ተሰወረ።   አገልግሎት እና ተአምራቸው ጻድቁ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአገልግሎት የወጡት በከተታ ነበር። ከ1219-1222 ዓ.ም  ለተከታታይ 3 ዓመት ወንጌልን ሰበኩ። ለ9 ወራት ያህልም ደግሞ 'በቡሂፋት' እንዲሁ ወንጌልን አስተማሩ። ከ1222-1234 ዓ.ም በወላይታ ለተከታታይ 12 ዓመት በማስተማር ህዝቡን ከጣዖት አምላኪነት አውጥተው አጥምቀዋል። ይህም በዚያ ስፍራ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች ሰይጣን በዛፍ ተመስሎ እኔ አምላካችሁ ነኝ እያለ ከእውነተኛው መንገድ አስወጥቶ እርሱን እንዲያመልኩት ያደርግ ነበርና። በዚያም ስፍራ ጻድቁ ቤተክርስቲያንን አንጸዋል። ከ1234-1244 ዓ.ም ወደ አማራ ጋይንት ወሎ ተጉዘው ከአባ ጸሎተ ሚካኤል ሥርዓተ ምንኩስናን እየተማሩ ተአምራትንም እያደረጉ ቆዩ። ከ1244-1254 ዓ.ም አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ወደ ሚገኙበት ሀይቅ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም በመጓዝ ሳሉም ሀይቁን እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግራቸው ሄዱ። በገዳሙም መንፈሳዊ ተጋድሎንና ትሩፋትን ሲሠሩ ቆይተዋል። የአባ ኢየሱስ ሞዓ የንጽሕና ምልክት የሆነውን ቀሚሳቸውንም ተቀብለዋል። ከ1254-1266 ዓ.ም ወደ ትግራይ አቅንተው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ገብተው ከአባ ዮሃኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው ለ12 ዓመታት በተጋድሎ፣ በትሩፋት እና በተአምራት መንፈሳዊ ትግላቸውን ቀጠሉ። ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሌላ ገዳም እንዲሄዱ ባዘዛቸውም ጊዜ  አባ ዮሃኒ እና መነኮሳቱ አብረው ሊሸኟቸው በወጡ ጊዜ ጻድቁ በገመድ ከገዳሙ እየወረዱ ሳለ ሰይጣን መጥቶ ገመዱን ቢቆርጠውም እግዚአብሔር የመረጣቸው ታላቅ አባት ናቸውና 6 የብርሃን ክንፍን ሰጥቷቸው እየበረሩ እንዲሄዱ አደረገ። ከዚያም ተመልሰው ከአባ ዮሃኒ የተቀበለቱን ቆብና አስኬማ ለአባ ኢየሱስ ሞአ ሰጧቸው። ወደ ዋሊ ገዳምም ገብተው እንደገና በትሩፋት፣ በመጋደል እና በተአምራት ቆይተዋል። ከ1266-1267 ዓ.ም ወደ ግብጽና ኢየሩሳሌም ሄደው ካሉት ከቅዱሳን አባቶች ጋር ተገናኙ። በዚያን ጊዜም ዳዳ የተባለውንም 75 ክንድ የሚረዝመውን ጣዖት በጸሎትና በተአምራት ገድለዋል። በቦታውም ቤተክርስቲያን አንጸው በውስጧ ታቦትን አስገብተዋል። በቤተክርስቲያኒቱም  3000 ህዝብንም አጥምቀው አቁርበዋል። ከ1267-1289 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ አሰቦት ዋሻ ገብተው 2 ጦር ከፊታቸው፣ 2 ጦር ከኋላቸው፣ 2 ጦር ከቀኝ እንዲሁም 2 ጦር ከግራ አድርገው እጃቸውንም በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የጌታችንን የመስቀል ህማምና ሞት በማሰብ በጾምና በጸሎት ሌትና ቀን በአርምሞ ተወስነው ለ22 ተከታታይ አመታት በሁለት እግራቸው ቀጥ ብለው በጽናት ቆመው ጸለዩ። ከጸሎት ብዛትም የተነሳ ጥር 4 1289 ዓ.ም በቀኝ በኩል ያለችው የእግራቸው አገዳ ተሰበረች። ከ1289-1296 ዓ.ም እግራቸው ከተሰበረ ቡሃላ ሳይበሉ ሳይጠጡ ቆመው ስለ ሰው ልጆች ድኅነትን ለመኑ። በአራተኛውም አመት ነበር ጥቂት ውሃ ቀምሰው የነበረው። ጌታችን ተገልጦም ታላቅ የመንግሥት አዳራሽን ሰጥቷቸው የመለኮትን ነገር የሚያሳይ የእሳት አንደበት ያላቸውን ልብስ አለበሳቸው። በመስቀል ያጌጡ 7 የመስቀል አክሊሎችንም አቀዳጀቸው። "ዝክርህን የዘከረ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ፣ ባንተ ስም በታነጸው ቤተክርስቲያን ሄዶ ለተሳለመና ለጸለየ ሁሉ እስከ 10 ትውልድ እምርሃለሁ እባርክልሃለሁም" የሚል ታላቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው። "በዚህም ዋሻ ለ57 አመት ከተቀበርክ ቡሃላ ይህ ገዳም ፈርሶ ልጆችህ ሥጋህን በዚያ አፍልሰው ያኖሩታል" ብሎ ነገራቸው። በመጨረሻም በተስህቦም ቢሉ በቸነፈር ህመም ለ10 ቀን ከቆዩ ቡሃላ ጌታቸው የገባላቸውን ቃልኪዳን ለመነኮሳት መንፈሳዊ ልጆቻቸው ካስተማሩ ቡሃላ በዕለተ ሰኞ ነሐሴ 24 1296 ዓ.ም በ99 ዓመታቸው በታላቅ ክብር አረፉ። ከማረፋቸውም ጥቂት አስቀድሞ ልጆቻቸውን እየባረኳቸው ሲሰናበቷቸው ሳለ አንዲት ሴት መጥታ "በእርሶ ቃል የታሰሩ ስላሉ ይፍቱ" ስትላቸው ከሰው እስከ እንስሳ የታሰሩ የዱር አራዊት ሁሉ የተፈቱ ይሁኑ አሉ። በቃለ ግዝታቸው መሰረት ለ18 አመታት ታስረው ነበርና። ይህም ደቀመዛሙርቱ የሚተክሉትን እያበላሹና እየነቀሉ ስላስቸገሯቸው ነበር። የአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ በዓላት: - ፩. ህዳር 24: -  ከካህናተ ሰማይ(ሱራፌል) ጋር 25ተኛ ካህን ሆነው መንበረ ሥላሴን ያጠኑበት ፪. ታኅሣሥ 24: - ልደታቸው ፫. ጥር 4( ጥር 24 ሚሉም አሉ): - የቀኝ እግራቸው አገዳ በጸሎት ብዛት የተሰበረችበት ፬. መጋቢት 24: - ጽንሰታቸው ፭. ሚያዝያ 22: - የኢየሩሳሌም መካናትን የተሳለሙበት ፮. ግንቦት 12: - አጽመ ፍልሰታቸው ፯. ነሐሴ 24(ዋናው በዓላቸው): - ዕረፍታቸው ይታሰባል።   አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን በእኛ ላይ ያሳድርብን 🙏🙏🙏 !!!

✨እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗 እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የጽዋ መርኃግብር ይኖረናል። በ
✨እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗
እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የጽዋ መርኃግብር ይኖረናል። በዕለቱም ጸሎት፣  ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ፣ የኅብረት ዝማሬ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርኃግብራት  ስለሚኖሩ ሁላችንም ተጠራርተን በመምጣት በዓሉን አብረን እንድናከብር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች! 📆 ቅዳሜ ነሐሴ 23 ፤ 2018 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 06:00 ጀምሮ አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ለበለጠ መረጃ ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

እንኳን አደረሳቹሁ በዓለ ፍልሰታ ወዕርገታ ለማርያም   ወፍልሰተ አጽሙ ለሊቀ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤  ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለ መኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ  እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ  ከሀገረ ስብከቱ  (ሕንድ) ወደ   ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።     ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው።        ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

የታቦር ብርሃን ቀድሞ  የሚያበራ  የትንሣኤ ብርሃን ነው::   በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሶቹም እንደ ብርሃን ነጭ ሆኑ። ሙሴና ኤልያስም በግራና በቀኙ ቆመው ነበር። "ብሩህ ደመናም ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ እንዲህ የሚል ድምፅ መጣ፦ 'የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ በእርሱ ደስ ይለኛል'" (ማቴዎስ 17፥1 -8)።   ክርስቶስ ለሐዋርያው እንደተገለጠው "በእግዚአብሔር መልክ" (ፊል 2፥6-7) ነበር—እርሱም ከሥላሴ አካላት አንዱ ሆኖ ነው። ይህ መገለጥ ስለዚህ የሥላሴ መገለጥ (theophany) ነበር፤ የአብ ድምፅና መንፈስ ቅዱስ በብርሃናዊው ደመና ውስጥ ተገኝተዋል።   "የታቦር ብርሃን የተፈጠረ ብርሃን አይደለም፤ እርሱ የመለኮት ያልተፈጠረ ክብር በሥጋ ልብስ በኩል ሲያበራ ነው::እንደ ፀሐይ ያበራው ፊት የቃል ፊት ነበር፤ ውበቱንም ዓለም ሊይዝ አልቻለም::” ፟ _ ቅ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ      ብርሃኑ ሥጋን አላጠፋም፤ ሥጋን አበራው እንጂ። ይህም የተዋሕዶን ምሥጢር ያሳያል—መለኮትና ትስብእት ሳይደባለቁ፣ ሳይለያዩ፣ ሳይለወጡ በአንድነት ተዋሕደው መኖራቸውን ያስረዳል።   ደቀ መዛሙርቱም ከገደል አፋፍ ላይ ወድቀዋል፤ በእሳታማው  ራእይ ተጨናንቀዋል፣ ተደንግጠዋልም። ብዙ ጊዜ ጴጥሮስ በቀኝ በኩል ተንበርክኮ እጁን ዘርግቶ ራሱን ከብርሃኑ ለመጠበቅ ሲሞክር ይታያል። ዮሐንስ በመሃል ላይ ሆኖ ጀርባውን ከብርሃኑ አዙሮ ይወድቃል። ያዕቆብ ደግሞ በግራ በኩል ሆኖ ወደ ኋላው ይወድቃል።ለምን?   "ብሩህ ደመና  ጋረዳቸው፤ የሥላሴ ምሥጢር ያለ ፍርሃት አይቀረብምና።” ቅ. ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ   በታቦር ተራራ ላይ ደቀ መዛሙርቱን የጋረደው ደመና ተራ የአየር ሁኔታ አልነበረም። እርሱ የመንፈስ ቅዱስ መገለጫ፣ የእግዚአብሔር ግርማ መኖሪያ፣ የመለኮት ጥላ ነው። በብሉይ ኪዳንም እግዚአብሔር በደመና ውስጥ ተገልጦ ነበር—በሲና ተራራ፣ በምድረ በዳ ድንኳን ላይ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ። ይህ ደመና የእግዚአብሔር ልዩ መገኘት ምልክት ነው። "ፍርሃት" ማለት እዚህ ላይ የሚያስደነግጥ ሽብር ሳይሆን፣ ቅዱስ የሆነ አክብሮት ነው። የእግዚአብሔር ግርማ ሲገለጥ ፍጡር የራሱን አነስተኛነት በጥልቅ ይገነዘባል። ይህም የጥበብ መጀመሪያ የሆነው "የእግዚአብሔር ፍርሃት" ነው (መዝ. 111:10)። ነቢዩ ኢሳይያስ የእግዚአብሔርን ክብር ሲመለከት "ወዮልኝ! ጠፋሁ" ማለቱ ይህንኑ ያሳያል (ኢሳ. 6፥5)።     “ሐዋርያት ያዩትን እኛም እናየዋለን፤ ወደ ጸሎትና ወደ ንጽሕና ተራራ የምንወጣ ከሆነ።መለወጡ የእርሱ ክብር ብቻ አይደለምና፤  በእርሱ ውስጥ የሚሆነው የእኛ የራሳችን መለወጥ ተስፋ ነው።" -ቅ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ   ተስፋውም  የጸና ነው። በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ሰው ሁሉ በዚያው መለኮታዊ ብርሃን እንዲያበራ ተጠርቷል። ይህ መለወጥ የሚጀምረው አሁን ነው—በጸሎት፣ በንስሐ፣ በቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት ምሥጢራት ውስጥ—ፍጻሜውንም የሚያገኘው በሚመጣው ዘመን ነው፤ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ።   ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ወለወላዲቱ ድንግል፤ ወለመስቀሉ ክቡር፤ይቆየን።

✅ የስራ ማስታወቂያ የስራ መደቡ መጠሪያ: Architect የስራ ልምድ : 0 - 2 ዓመት የስራ ሰዓት: ከ ጠዋቱ 2 :00 - 11:00 አድራሻ : Gerji Unity University ከፍ ብሎ ደሞዝ: በስምምነት Portfolio በ 0916832471 ይላኩ

✨እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗 እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የበዓለ ደብረታቦር ልዩ መርኃግብር ይኖረናል። በዕለቱም ጸሎት፣ ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች
✨እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗
እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የበዓለ ደብረታቦር ልዩ መርኃግብር ይኖረናል። በዕለቱም ጸሎት፣  ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ፣ የኅብረት ዝማሬ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርኃግብራት  ስለሚኖሩ ሁላችንም ተጠራርተን በመምጣት በዓሉን አብረን በድምቀት እንድናከብር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች! 📆 ቅዳሜ ነሐሴ 9 ፤ 2018 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 06:00 ጀምሮ አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ለበለጠ መረጃ ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አስቀድሞ ከቅዱስ ምሥጢር የሚቀበሉ ሁሉ እንዲህ ይበሉ፤ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ርኵስት ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም። እኔ አሳዝኜሃለሁና  በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና ሥራም ምንም ምን የለኝምና። ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፣ ስለ ክቡር መስቀልህም፣ ማሕየዊት ስለ ምትሆን ስለ ሞትህ፣ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ፣ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ እማልድሃለሁም። የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልኩ ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ።   የዓለም ሕይወት ሆይ! በእርሱ የኃጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ። በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን    በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም፣ በመጥምቁ በዮሐንስም አማላጅነት፣ ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም፣ በሰማዕታትና፣ ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።

በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ቀን እነሆ ደረሰ 🤗 በነገው ዕለት በግቢ ጉባዔያችን የሕይወት ቀን (በሕብረት ቅዱስ ቁርባን የመቀበል ቀን) እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም ከቅዳሴ ሥርዓት ጀምሮ ሁላችንም በዕለቱ የሚቀበሉ ወንድም እና እህቶቻችንን በማጀብ አብረን በማስቀደስና ከቅዳሴ በኋላ ደግሞ አጋፔ (የጋራ ማዕድ) በመሳተፍ ይህንን ልዩ ቀን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን🤗 🕰 ከቀኑ 05:00 - 11:00 አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ለበለጠ መረጃ ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

✨ የሕይወት ቀን - '1 ቀን' ብቻ ቀረው ✨ 📆 ነገ አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
✨ የሕይወት ቀን - '1 ቀን' ብቻ ቀረው ✨ 📆 ነገ አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

ከመቁረባችን በፊት ማድረግ ያለብን ነገሮች። 1,ንስሃ መግባት እና ቀኖናን መጨረስ። 2, ለመቁረብ ንስሃ አባትን ማማከር እና ማሳወቅ። እነዚን ከጨረስን በዋላ 3, 18 ሰዓት መጾም። 4, ንፁህ ልብስ ማዘጋጀት። ⚠️ማሳሰቢያ ገላ መታጠብ፣ ጥፍር መቁረጥ፣ ጥርስ መቦረሽም ሆነ ጠዋት ተነስቶ መጉመጥመጥ፣ ፀጉር መቆረጥ (ለወንዶች) ወዘተ የሚደረጉት ከ18 ሰዓት በፊት ብቻ ነው። ለመቁረብ 18 ሰዓት መጾም ከጀመርን በዋላ እነዚን ነገሮች ማድረግ አይፈቀድም። ከቆረብን በዋላ ማድረግ ያለብን ነገሮች 1, የቆረብንበትን ልብስ አለማውለቅ። 2, ምራቅ ከአፋችን ሊነጥም ስለሚችል ብዙ አለማውራት ማውራት ካለብንም በስርዓት። 3, ከሰውነታችን ላብ እዲወጣ ከሚያደርጉ ነገሮች መራቅ ለምሳሌ እረጅም መንገድ መሄድ የመሳሰሉትን አለማድረግ። 4, እጅ አለመታጠብ ።           ⚠️ ከቆረብን በዋላ ገላን መታጠብ የሚቻለው ከ24 ሰዓት በዋላ ነው። 5, ከሶሻል ሚዲያ መራቅ በተለይ ከTikTok እና Instagram አዕምሯችን ማረፍ አለበትና። እግዚአብሔር አምላክ ፈቅዶ ለዚህ ልዩ ምሥጢር ያዘጋጀን🙏

✨ የሕይወት ቀን - '2 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ
✨ የሕይወት ቀን - '2 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ