cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ደሸት777.... (፯፯፯)

ደሸት777(፯፯፯) ድርጅታችን ቢመረመር ውጤቱ ታላቋን ኢትዮጵያን ለመገንባት እና ኃያል ሥልጡን ለማድረግ የተቋቋመ ብሎም ብዙ ሊቃውንቶችን በይፋ ጥበባቸውን የሚያስቀጥል ኃያል ድርጅት ነው። https://www.facebook.com/ደሸት-፯፯፯-103696061536486/ ይሄ ደሞ የFacebook ፔጃችን ነው በዚህ ቻናል ላይ ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት በዚህ @Dessht777bot መላክ ትችላላችሁ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 371
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ሶሻል ሚዲያ ገዝተው ይጠቀሙ! በአጭር ቀን ውስጥ ስራውንና እራስዎን ያሳድጉ!! ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው! ስለዚህ ሁላችሁም ብትሆኑ ሶሻል ሚዲያችሁን ወደ ገንዘብ ቀይሩት!! እኛ ጋ አለ መላ!! የሚሸጥ ሶሻል ሚዲያ አለን!! ሲገዙ ✅ድካሞን ይቀንሳል! ✅ጊዜዎን ይቆጥባል! ✅በቀላሉ ሰው ጋር ያደርሰዎታል! የሚሸጥ የቲክቶክ የቴሌግራም የዩቲዩብ ቻናል አለን ያናግሩን!! የምትሸጡም ብትሆኑ አናግሩን! ስልክ ቁጥር #0994452644 ይደውሉ!! @ethelmezgebu
نمایش همه...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
📕 ቢነበብ የማይጠገብ መፅሐፍ ነው" የኛ ሰው በደማስቆ"። እውነተኛ ታሪክ ሲሆን የታላቁን እስራኤላዊው ሰላይ የኤሊ ኮሄንን ማንነትና ፍፁም ለአላማው መሰጠትን የሚገልጽ እና የእራኤልን ሞሳድ እንዲሁም ስለላውን በሶሪያ ውስጥ እስከ ስቅላት ሞት ሂወቱን ስለሰጠው ድንቅ ሰላይ(ስለላ) ይተርካል። 🙏 ይህ መፅሐፍ ለህይወታችን ለማንነታችን እጅግ የሚጠቅም የዓላማ ፅናትን ታማኝነትን ሐገር መውደድን የሚያስተምርና ራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርግ የማሞ ውድነህ ከምርጥ ስራዎቹ አንዱና ተወዳጅ መፅሐፍ ነው #አንብቡት እውነት ሁሌም የፀናች መሆኗን በማስረጃ የሚያሳይ ምርጥ መፅሐፍ ነው። https://t.me/yinuca
نمایش همه...
👍 2
#ድህነትን_ተማርኩት አንድ በጣም ሃብታም የሆነ አባት ለልጁ ከሚያቀስመው የህይወት ልምድ ትምህርት አንዱ ድህነት ምን እንደሁ እንዲያውቅ ማስቻል ነበር። እንደ ዲታው ሃሳብ ከሆነ ልጁ ስለድህነት ካወቀ፤ ድሃ እንዳይሆን በመስጋት ለገንዘቡ ጥንቃቄ ያደርጋል የሚል ግንዛቤ አለው። ሃብታም አባት ልጁን ከደሃ ገበሬዎች ጋር ቆይታ እንዲያደርግ ላከው። ልጁ 3ቀንና ሶስት ሌሊቶችን ከገበሬዎች ጋር ቆይቶ ወደ ከተማው የሃብታምነት የቅንጦት ህይወቱ ሲመለስ.... አባቱ "ጥሩ ልምድ ቀሰምክ?" ሲል ጠየቀ። ልጁ:- " አዎ አባ!" አባት:- "እናም ምን ተማርክ?" ልጁም እንዲህ ሲል መለሰ.... "በቆይታየ ያየሁት...." 1 –  እኛ አንድ ውሻ አለን እነሱ አራት አላቸው። 2 –እኛ የጓሮ አትክልታችን ጋር የሚደርስ የመዋኛ ገንዳና የታከመ ውሃ አለን... እነሱ ደግሞ ኩልል ያለ ውሃ ያለው ወንዝ በውስጡ አሳዎችንንና ሌሎች ውብ ነገሮችን አቅፎ አላቸው። 3- እኛ ግቢያችን ላይ የኤሌክትሪክ ማብራት አለን እነሱ ደግሞ ደማቅና ያማሩ ከዋክብትና ጨረቃ አላቸው። 4 – የኛ የአትክልት ቦታ እስከግቢያችን አጥር ድረስ ብቸ ሲወሰን የነሱ ግን እስከ አድማስ ተንጣሏል። 5 – እኛ ምግባችንን እንሸምታለን እነሱ ያመርቱታል። 6 – እኛ ከስፒከር የሚወጣ የሙዚቃ ዜማን ስንሰማ... እነሱ ግን ተፈጥሮኣዊ የሆነ የዛፎችን ሽውሽውታ፣ የአዕዋፍትን ጥዑመ ዜማ፣ የፏፏቴዎችን ጭርጭርታና የእንስሳቱን ህብረዜማ ያጣጥማሉ። ምናልባትም ይሄ ሁሉ በስራ ላይ ባለ አንድ ጎረቤት ገበሬ እንጉርጉሮ አለያም በእረኛ የዋሽንት ስርቅርቅታ ይታጀብና ነፍስን ሰማየ ሰማያት ወስዶ በቀስተ ዳመና ያንሳፍፋል። 7 –  እኛ በማይክሮ ዌቭ ስናበስል የእነሱ በእንጨት ዝግ ብሎ የሚበስል ምግብ ግን እንኳን ጣዕሙ መኣዛው አካባቢውን ያውዳል። 8 – እኛ ራሳችንን ከአደጋ ለመከላከል በአደገኛ አጥር ተከልለን ስንኖር እነሱ ግን አጥር አልባ ህይወታቸውን በወገኖቻቸውና ጎረቤቶቻቸው ፍቅር ተጠብቆ ይኖራሉ። 9 –የኛ ህይወት ከስማርት ስልኮች፣ከኮምፒውተሮችና ከቴሌቪዥኖች ጋር ሲቆራኝ የነሱ ደግሞ ከኑሮ፣ ከሰማይ፣ከፀሃይ፣ ከከዋክብት...አጠቃላይ ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አላቸው። አባት በልጁ ስሜት ተደነቀ። ልጁም ሃሳቡን እንዲህ ሲል ቋጨ "አባዬ ምንያህል ደሃዎች እንደሆንን እንድገነዘብ ስለረዳሃኝ አመሰግናለሁ...በየእለቱ የበለጠ እየደኸዬን እንደምንሄድም ተረድቻለሁ....ምክንያቱም የፈጣሪ ዕፁብ ድንቅ ስጦታ ከሆነው ተፈጥሮ እየራቅን ስለመጣን!" __ አበቃሁ.....መልካም የናቶች ቀን🙏🙏🙏 ሁሌም ምንጊዜም ሠላም ሁኑልኝ🙏🙏🙏🙏 ቴሌግራም 👇👇👇 https://t.me/yinuca
نمایش همه...
ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

አንባቢያንን እናበረታታለን። ደራሲያንን እንገነባለን!! የተሻለች ሀገር ለመፍጠር እንተጋለን! እኛ ጋር ነዎት!? 👉የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ 👇👇👇👇

https://youtube.com/@Ethel608?si=s0sl3_kQ8qTGZr3B

አስተያይት አለዎ 👇👇👇

https://t.me/ethelmezgebu

2
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ የግሪክ አፈታሪክ አለ። ፕሮሜቴየስ የተባለው የእሳት አምላክ የሆነው እሳቱን ለሰው ልጆች ከሰጠ በኋላ ዜኡስ(የመብረቅና የሰማይ አምላክ) የሆነው ለሄፋስተስ(የጥበባት አምላክ) የመጀመሪያዋን ሴት ከአፈርና ከውሃ እንዲፈጥር አዘዘው። ሴቲቱም ከፈጠራት በኋላ ሁሉም አማልክት ለሴቲቱ በስጦታ ያበሸብሿት ጀመር። አቴና - ጥበብን፣ አፍሮዳይት - ውበትን፣ ሄርሜስ - ተንኮልን የመሳሰሉትን እንደ ስጦታ ሰጧት። የዚህች ውብ ሴት ስም ፓንዶራ ነበር። በግሪክ ፓንዶራ ማለት 'ሁሉንም ስጦታ የተሰጣት' ማለት ነው። ዜኡስ ለፓንዶራ አንድ ማሰሮ ሰጣት፤ ቀጠለና "ይህ ማሰሮ በየትኛውም አጋጣሚ እንዳትከፍቺው!" ብሎ ከጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር ሰጣት። ኤፒሜቲየስ የተባለው 'ለሰው ዘር እንደተወካይ' የነበረው ለፓንዶራ ከዜኡስ ምንም ስጦታ እንዳትቀበል ብሎ መንታ ወንድሙ የሆነው የጥበባትና የእሳት ባለቤት የሆነው ፕሮሚትየስ አስጠንቅቆት ነበርና፤ ማሰሮውን ተቀብሏት ዜኡስ እንዳትከፍቺው ያላትን ትዕዛዛ በማፍረስ ማሰሮውን ይከፍተዋል። ልክ ማሰሮውን እንደከፈተው በአለም ላይ ሁሉንም ጥፋቶችና መቅሰፍቶች ተለቀቁ። በሽታ፣ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ ረሀብ፣ ሞት፣ ህመም፣ አደጋዎች ........የመሳሰሉትን ! ያቺ ፓንዶራ በስጦታዎች የተንበሸበሸችሁ ባመጣችው ጦስ፣ ያ ዜኡስ በሰጠው ትዕዛዝ፣ ያ 'ለሰው ልጅ ተወካይ ነኝ' በሚለው ኤፒሜቲየስ አስተዳደራዊ ስህተት አለም በጥፋትና በመቅሰፍት እንድትቀጣ ሆነ። ዛሬም ፓንዶራዎች አሉ ለጥፋት ሰበብ የሆኑ! ዛሬም ኤፒሜቲየሶች አሉ በእነርሱ እንዝላልነት ትውልዱ የሚቀጣ! ምን ለማለት ነው..... ፓንዶራዎችና ኤፒሜቲየሶች ስጦታዎቻችሁና ፀጋዎቻችሁ በስርዓቱ ተጠቀሙ። የሌላን ንፁህ ነፍስ ስቀቀን አትሁኑ! https://t.me/yinuca
نمایش همه...
👍 2
نمایش همه...
የድል ዜና - ፋኖ የድል ዜና አበሰረ | ማዕከላዊ ጎንደር የብልፅግና ባለስልጣን ተወገዱ | አብይን ያስጨነቀው ጦር | የባህርዳሩ ውጊያ |Anchor media

#ethiopia #ethiopianews #subscribe #abiyahmed #mereja_today #zehabeshanews #ethiopianewstodayinamharic #ኢትኤል_ሚዲያ #ethiopian_news #ሰበር_ዜና @Ethal_Media

👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቀይ ሸንኩርት ሲቀንስ ለቀይ ባህር እዘምታለን😜 ሕዝቤ ነቆራውን ቀጥሎበታል!! https://t.me/ethelmeaia https://t.me/ethelmeaia https://t.me/ethelmeaia 💚💛❤️ 💚💛❤️ https://t.me/ethelmeaia https://t.me/ethelmeaia https://t.me/ethelmeaia
نمایش همه...
🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
የትግራይ ኢሊቶችና ፖለቲከኞች አሁንም ድረስ የገደላቸው አማራ እንደሆነ ነው የሚያስቡት። ይገርማል ትላንት ደብረሲና ድረስ መጥተው እህቶቻችንን ደፍረው፣ ማይካድራ ላይ ህዝባችንን በገፍ አርደው፣ እንዳንማር መማሪያ ትምህርት ቤቶችን አውድመው፣ ታመን እንዳንታከም ሆስፓታሎቻችንን አውድመውብን፣ "ሞኝ አማራ " አህያ አማራ " እያሉ በሙዚቃ ጭምር  ህዝባችንን ከሰብአዊነት ደረጃ ዝቅ አድርገው ሲገልፁ እንዳልነበር ዛሬም ፀፀት ሳያድርባቸው እየዛቱ ይገኛሉ። እየታዘብን! https://t.me/ethelmeaia
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፍኖተ ሰላም ላይ ሰሞኑን በነበረው ስብሰባ  "መንግስትን ካልደገፋችሁ ትወድማላችሁ፣ ትሰረቃላችሁ፣  የታጠቀውን ሁሉ እናጠፋዋለን። በቋሪት፣ በደጋ ዳሞት፣ በሰከላ ከፍተኛ ጭፍጨፋ አድርገን እናጠፋዋለን" ሲል በተሰብሳቢው ፊት እንደዛተ ታውቋል። የዘር ማጥፋቱ በአብይ ቅጥረኛ ሰራዊትም በብአዴን ሰዎችም ተደግፎ አለም የማያውቀው silent genocide እየተፈፀመ ነው። ሰሞኑን አብይ አህመድ ለመከላከያ አመሮች አቅጣጫ በሰጠበት ሰነድ ላይ ገድላችሁ አሳዩኝ ማለቱ አይዘነጋም። https://t.me/ethelmeaia
نمایش همه...
#ዞር_ዞር_ስል_ያገኘውት_ነው_አንብቡትማ የእስራኤልና የፍልስጤም ጦርነት ከየት ወዴት ? አሁን አሁን አለማችን የህግ ድጋፍ የሌለው ነገር ግን በደማቁ የተፃፈ ህግ አላት፡፡ አለም የጉልበተኞች ናት፡፡ በአለም የትኛውም ጫፍ ብንጓዝ ጉልበተኞች እንጂ ህግን የተማመኑ ክንዳቸው ያልፈረጠመ መንግስታት ከዛሬ ተሻግረው ነገን ሲደርሱ መመልከት እንብዛም ነው፡፡ እንደውም አሁን አሁንማ ግራ በሚያጋባ መልኩ የጡንቸኛ መንግስታት ጉዳይ አሰፈፃሚ ያልሆኑ መንግስታትን ማግኘት የክት እየሆነ ይመስላል፡፡ በወፍ በረር እንግዲህ ከሰሞኑ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የፍልስጤም ታጣቂዎች(ቢያንስ የእስራኤል መንግስት እንዲህ ብሎ ነው የሚጠራቸው፡፡ የቤት ስማቸው ደግሞ ሃማስ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡) በእስራኤል ላይ ጥቃት ከከፈቱ በኋላ በሁለቱ መካከል የጦፈ ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ አይነኬዋ እስራኤል በአለም አቀፍ መድረክ ያላትን ግዝፈት የሚኮስስ ለካ እንዲህም ማድረግ ይቻላል የሚያስብል ጥቃት ደርሶባታል፡፡የሁለቱ አገራት ጦርነት አጀማመር ወደኋላ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ሚሊዮኖችን ለስደት፣ ለመፈናቀልና ለሞት ያደረገ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ከ100 አመት በፊት ምን ሆነ መሰላችሁ? ጥቅምት 2 1917 የባልፎር መግለጫ (Balfour Declaration) እ.አ.አ ከ1917 እስከ 1947 ብሪታኒያ ፍልስጤምን በቅኝ ግዛትነት ይዛ ነበር፡፡ ታዲያ የወቅቱ የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ፀሀፊ የነበረው አርተር ባልፎር የብሪታኒያ አይሁዳዊ ማህበረሰቦች እንደራሴ ለነበረው ሊዮኔል ዋለትር ሮዝስቻየልድ አንድ ደብዳቤ ጽፎ ነበር፡፡ 67 ቃላት ብቻ የያዘ ደብዳቤ፡፡ ነገር ግን ዛሬ ላይ ፍልስጤም ለሆነችው ነገር ሁሉ ተጽዕኖ ማሳደር የቻሉ 67 ቃላት፡፡ የደብዳቤው ሙሉ ቃል ይህ ነበር “በብሪታኒያ ለሚኖሩ አይሁዳዊ ማህበረሰቦች የሚሆን አከባቢ በፍልስጤም የሚዘጋጅ ሲሆን ይህን ለማሳካትም የብሪታኒያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል” እንቀጥል የብሪታኒያ መንግስት እ.አ.አ እስከ 1948 ድረስ በቆየው ማንዴቱ አማካኝነት 90 በመቶ የሚሆነው ህዝብ አረብ በሆነባት ፍልስጤም አይሁዳዊያንን አሰፈረ፡፡ ታዲያ እነዚህ በአውሮፓ ተሰደው ይኖሩ የነበሩ አይሁዳዊያን የጀርመን ናዚን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፍራቻ የሸሹ ነበሩና በፍልስጤም ሆነው ሳለ ቀስ በቀስ ተቃውሞዎችን ማሰማት ጀመሩ፡፡ ይሄኔ ፍልስጤማዊያን አይናቸውን ገለጡ፡፡ የአገራቸው ዲሞግራፊ (በገደምዳሜው ወደ አማርኛ ስንመልሰው የህዝብ አሰፋፈር እንለዋለን) መቀየሩንና በጠራራ ፀሀይ መሬታቸውን መነጠቃቸውን አስተዋሉ፡፡ እዚህ ላይ የአለማችን ረዥሙ ግጭት መጣሁ መጣሁ ማለት ጀመረ፡፡ እ.አ.አ በ1936 እያደገ የመጣው ውጥረት የአረብ አብዮትን ቀሰቀሰ፡፡ ይህ አብዮትም እ.አ.አ እስከ 1939 ቆየ፡፡ እንግዲህ ፍልስጤም በወቅቱ የብሪታኒያ ቅኝ ግዛት ነበረች ብለናችሁ አይደል፣ በወቅቱ የተቋቋመው አዲሱ የአረብ ብሄራዊ ኮሚቴ ፍልስጤማዊያንን ለተቃውሞ ጠራ፡፡ ፍልስጤማዊያንም ግብር አንከፍልም አሉ፣ የአይሁዳዊያንን ምርት ያለመግዛት አድማ መቱ፣ ሰፈራቸውን ተቃውመው አደገኛ የተባለ ንቅናቄ አካሄዱ፡፡ ይህን ስድስት ወራትን ተቃውሞ ለመቆጣጠር ብሪታኒያ አሰቃቂ የሆኑ እርምጃዎችን ወሰደች፡፡ በርካቶች ከእስር ቤት ፍርግርግ ጀርባ ተወረወሩ፣ መኖሪያ ቤቶች በገፍ እንዲፈርሱ ተደረገ፡፡ በነገራችን ላይ ይህ የቤት ማፍረስ እርምጃ እስራኤል ዛሬም ድረስ በሁለቱ መካከል የሚፈጠረውን ትኩሳት ለማብረድ የምትጠቀምበት እርምጃ ነው ይባላል፡፡  አ.አ በ1937 ደግሞ ሁለተኛው የተቃውሞ ንቅናቄ ተጀመረ፡፡ የፍልስጤም ገበሬዎች ተቃውሞ እንቅስቃሴ ተቀጣጠለ፡፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ግን የተቃውሞ እንቅስቃሴው ኢላማ ያደረገው አይሁዳዊያንን ሳይሆን የብሪታኒያ ሀይሎችንና ቅኝ ግዛትን ነበር፡፡ ይህ ንቅናቄ በተጀመረ በሁለተኛ አመቱ ግን ብሪታኒያ 30ሺ የሚሆኑ ወታደሮቿን ወደ ፍልስጤም በማስገባት መንደሮቻቸውን በአውሮፕላን ደበደበች፣ የሰአት እላፊ አወጀች፣ ቤቶቻቸውን አፈራረሰች፣ አስተዳደራዊ ጥርነፋ እዚህም እዛም ሆነ፣ የጅምላ ግድያዎች የፍልስጤም መገለጫዎች ሆኑ፡፡ ኋላ ደግሞ በብሪታኒያ ቅኝ ገዥዎች የሚመራ Special Night Squads የሚል መጠሪያ ያለው የአይሁዳዊ ሰፋሪዎች ሀይልና እና የብሪታኒያ ቅኝ ገዥ ሀይሎች ጥምረት የሆነ የፀረ-ሽምቅ ኃይል ተቋቋመ፡፡ ይህ ጥምር ሀይል በድብቅ የጦር መሳሪያዎች ማስገባት እንዲሁም የጦር መሳሪያ መስሪያ ፋብሪካ እስከማቋቋም ደረሰ፡፡ የኋላ የኋላ ይህ ጥምር ሀይል የእስራኤል ሀገር መከላከያ ልቡ ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ እዚህ ላይ ፍልስጤማዊያን “ምናለ በእንቁላሉ ሳለሽ በቀጣሁሽ ኖሮ” ሳይሉ አይቀሩም ባይ ነን፡፡ እንግዲህ በእነዚህ ሶስት የአረብ አብዮት ወቅቶች 5000 ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፣ ከ15ሺ እስከ 20ሺ የሚሆኑት ደግሞ ለቀላልና ለከባድ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ያው 5600 የሚሆኑት መታሰራቸውንም ሳንዘነጋ፡፡ እ.አ.አ በ1947 አይሁዳዊያን በፍልስጤም ውስጥ ከሚኖሩ ህዝቦች 33 በመቶ ያህሎችን መሆን የቻሉ ሲሆን የያዙት መሬት ግን 6 በመቶ የሚሆነውን ብቻ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ እንግዲህ የሁለቱ ህዝቦች እሰጥ አገባ ከድጡ ወደማጡ ሆኖ በርካታ አስርት አመታትን ካስቆጠረ በኋላ እ.አ.አ በ1981 ደግሞ ምን ሆነ መሰላችሁ፣ የተባበሩት መንግስታት ለምን አገሪቱ የፍልስጤም ህዝቦችና የአይሁዳዊያን በሚል ለሁለት ተከፍላ አትሰጣችሁም የሚል Resolution 181 የሚባል መግባቢያ ሰነድ አቀረበ፡፡ ይሄኔ ፍልስጤማዊያን አገር ይያዝልን አሉ፡፡ ይህ ስምምነት 59 በመቶ የሚሆነውን ያውም ለም የሆነውን የድንበር አካባቢ መሬታችንን ለአይሁዳዊያን ይሰጥብናል ብለው ነበር አገር ይያዝልኝ ማለታቸው፡፡ በነገራችን ላይ በወቅቱ ፍልስጤማውያን 94 በመቶ ታሪካዊ የፍልስጤም ባለቤት ሲሆኑ 67 በመቶ የሚሆነውን ህዝብም ያቀፉ ነበሩ፡፡ ግጭቱ ቀጠለ፡፡ ፍልስጤማዊያን እየተሸነፉ አይሁዳዊያን እያሸነፉ ቀጠሉ፡፡ ዛዮናዊያን 78 በመቶ የሚሆነውን የፍልስጤማዊያንን ታሪካዊ ቦታ በቁጥጥራቸው ውስጥ አስገቡ፡፡ ቀሪው 22 በመቶ የሚሆነው ቦታ በአሁኑ ጊዜ ጋዛ እና ዌስትባንክ እያልነው የምንጠራው ቦታ መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡ እዚህም እዛም የሰዎች ህይወት እንደቅጠል ረገፈ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ለስደት ተዳረጉ፣ ጦርነት የእለት ተእለት ህይወታቸው አንደኛው አካል ሆነ፡፡ እዚህና እዛ ከዛ እስከዚህ ድረስ ጎራ ለይተው ተፋለሙ፡፡ በመጨረሻም እ.አ.አ በግንቦት 15 1948 እስራኤል እንደአገር ተቋቁሜአለሁ ብላ አወጀች፡፡ በበነጋው የመጀመሪያው የእስራኤልና የአረብ አገራት ጦርነት ተጀመረ፡፡ ጦርነቱ በሚቀጥለው አመት በፈረንጆቹ ዘመን መለወጫ አበቃ፡፡ እንግዲህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሁለቱ አገራት ጦርነት ሌሎችንም ባለድርሻ አካላትን እንደአሜሪካ እና ሩሲያ ኢራንና እንግሊዝ የመሳሰሉ አገራትን ጨምሮ ጠፋ ሲሉት ብቅ እያለ ከሰመ ሲባል እየተቀጣጠለ ዛሬን ደርሶ በሽዎች የሚቆጠሩትን እየገደለ እያፈነቀለ ይገኛል፡፡ ከጦርነት የፀዳች አለምንን እንናፍቃለን!! https://t.me/yinuca
نمایش همه...
ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

አንባቢያንን እናበረታታለን። ደራሲያንን እንገነባለን!! የተሻለች ሀገር ለመፍጠር እንተጋለን! እኛ ጋር ነዎት!? 👉የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ 👇👇👇👇

https://youtube.com/@ethal730

አስተያይት አለዎ 👇👇👇

https://t.me/ethelmezgebu