cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

አንባቢያንን እናበረታታለን። ደራሲያንን እንገነባለን!! የተሻለች ሀገር ለመፍጠር እንተጋለን! እኛ ጋር ነዎት!? 👉የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ 👇👇👇👇 https://youtube.com/@Ethel608?si=s0sl3_kQ8qTGZr3B አስተያይት አለዎ 👇👇👇 https://t.me/ethelmezgebu

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
808
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-1530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

አንድ የስነ-ሰብ /Anthropology/ ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።  ጨዋታውም፣  በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው ፦ "እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ  የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል።" ጨዋታው ተጀመረ። ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ። ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ። የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው። ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ /Ubuntu/ !" በማለት መለሱለት። በመቀጠል አንዱ ህፃን  እንዲህ አለው ፦ "እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም።" "ኡቡንቱ/Ubuntu/" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪካው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም ፦ "ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!" የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው። 👉 https://t.me/yinuca
نمایش همه...
ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

አንባቢያንን እናበረታታለን። ደራሲያንን እንገነባለን!! የተሻለች ሀገር ለመፍጠር እንተጋለን! እኛ ጋር ነዎት!? 👉የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ 👇👇👇👇

https://youtube.com/@Ethel608?si=s0sl3_kQ8qTGZr3B

አስተያይት አለዎ 👇👇👇

https://t.me/ethelmezgebu

👍 2
አንቂ መልዕክት! ከትላንትህ ጋር ተወዳደር ! በህይወት ሩጫ ውስጥ የሚያሸንፈው ቀድሞ የደረሰ ብቻ አይደለም ውድድሩን የጨረሰም ነው። የግድ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ቀድመን ወይም እኩል መድረስ አለብኝ ብለን ራሳችንን ማስጨነቅ የለብንም። ራሳችንን ካወዳደርን አይቀር ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከትላንቱ ማንነታችን ጋር መሆን አለበት። ስኬት የሚለካው በራስ መነፅር እንጂ ከሌሎች ጋር ባለን ንፅፅር አይደለም።[Inspire ethiopia] ደስታ የሞላበት ከሰዓት ተመኘን🙏 https://t.me/yinuca
نمایش همه...
ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

አንባቢያንን እናበረታታለን። ደራሲያንን እንገነባለን!! የተሻለች ሀገር ለመፍጠር እንተጋለን! እኛ ጋር ነዎት!? 👉የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ 👇👇👇👇

https://youtube.com/@Ethel608?si=s0sl3_kQ8qTGZr3B

አስተያይት አለዎ 👇👇👇

https://t.me/ethelmezgebu

''ነፍስ ሳትን'' Dîž Âb ''ይነበብ በፅሞና!!! ከተማ እየወደመ ፈገግ ይላሉ ደስተኞች ናቸው ይቦርቃሉ ይወራጫሉ። የውጪኛው አለም ቢፈረካከስ ቢሰባበርና ምድር ወደ ሲኦልነት ብትቀየር እንኳ ምንም አይጎረብጣቸውም ... ልጆች በጦርነት ውስጥ እንኳን የፍቅር ጨዋታን ያውቃሉ ከተማ እየወደመ ፈገግ ይላሉ ፍፁም ሙላተኞች ናቸው ደስተኞች ናቸው ያለድካም ይቦርቃሉ በሀሴት ይወራጫሉ። ውጪው አልገዛቸውም በራሳቸው ግዛት ብቻ ናቸው። በድርቅ በተመታ ስፍራ ውስጥ እንኳን የልጆች ፈገግታ ፈፅሞ አይታጣም ሁሌም እፁብ ናቸው። ልጆች በራሳቸው አለም ይኖራሉ! አንተ ግን ከውስጥህ ወደ ውጪ እንደ ልጆች መኖር ስላልቻልክ የውጪኛው Atmosphere አንተን እያሽከረከረህ እያቃዠ ይኖርሀል። ከነፍስህ ተለያይተሀል #ነፍስ_አወቅ ተብለህ ነፍስህን #ስተሀል... ውጪውን እየኖርክ ውስጥህን ገለሀል:: ክርስቶስ ''እንደ ልጆች ካልሆናቹ በስተቀር መንግስተ ሰማያትን አትወርሷትም'' ያለው ለምን ይመስልሀል!?... መንግስተ ሰማይ ማለት Physical State አይደለም መንፈሳዊ አለም እንጂ ። መንግስተ ሰማይ በሆነ በሀይማኖት ጓራ ውስጥ በመንጋ እሳቤ ያሆሆሆሆሆ በል ያሆሆሆ እያልክ የምትገባበት አይደለም። መንግስተ ሰማይ ''የነፍስ ንቃት'' ''የልብ ንፅህና'' ''የእግዜር መቅደስ'' መሆን የመቻል ልእልና ነው። Higher Vibration ውስጥ የመገኘት ምልአት ነው! ልክ እንደ ህፃናቶች! ''መንግስተ ሰማይ'' መንፈሳዊ ቤት ማለት ነው! ይሄን ቤት አሁን መፍጠር ትችላለህ.... በምድር እያለህ ገነትህን መስራት ትችላለህ.. መንፈሳዊውን አለም ብቻ ተከተል ይሄን ለመከተል ምን ያስፈልግህ ይሆን? ምንም ባለህባት ቅፅፈት ብቻ ተገኝ ሀሳብህን ሰብስበው ራስህን አድምጠው! Meditation አድርግ! አእምሮህን ከተለያዩ የሀሳብ ብክለቶች ጠብቀው የራስህን አለም ከአሁን ጀምረህ መገንባት ትችላለህ ራስህን መርምረው አጥናው ስማውም! በአለምህ መ'መላለስ ትችል ዘንድ ትኩረትህንም አትበታትነው ራስህን በፅሞና ውስጥ አድምጠው!!! ''ብዙ ትሰማለህ ብዙ ትማራለህ የንቃት ጉዞ ይጀመራል የእግዜር ክብር በሁለንታህ ያርፋል... ያኔ ክርስቶስ እንደሚለው #ዳግመ_ውልደት ይሆናል... ልጅነትህን ትወርሳለህ እንደገና ትወለዳለህ ስነ ፍጥረታዊም ትሆናለህ #ነፍስ_አወቅ ትሆናለህ...! አሁን ባለህበት ቅፅፈት ሀሳብህ ሳይበታተን ንቁ'" በነፍስህ ንቃት ብቁ! የአሁኗን ብርሀን ብቻ የምትመለከት ትሆናለህ ገነትን በልብህ ትፈጥራለህ.. በመንፈስህም ትጠራለህ... #ነፍስ_አውቅ ትሆናለህ:: ዳግመኛ ተወልደሀልና
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ሶሻል ሚዲያ ገዝተው ይጠቀሙ! በአጭር ቀን ውስጥ ስራውንና እራስዎን ያሳድጉ!! ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው! ስለዚህ ሁላችሁም ብትሆኑ ሶሻል ሚዲያችሁን ወደ ገንዘብ ቀይሩት!! እኛ ጋ አለ መላ!! የሚሸጥ ሶሻል ሚዲያ አለን!! ሲገዙ ✅ድካሞን ይቀንሳል! ✅ጊዜዎን ይቆጥባል! ✅በቀላሉ ሰው ጋር ያደርሰዎታል! የሚሸጥ የቲክቶክ የቴሌግራም የዩቲዩብ ቻናል አለን ያናግሩን!! የምትሸጡም ብትሆኑ አናግሩን! በዚህ ሊንክ በመግባት @ethelmezgebu
نمایش همه...
"አዎ ! እሱ ጋ ያመኛል " መጽሐፍ አንዳንድ ሀሳቦች ፦ ___ ➫ ሁልጊዜ እሮሮ የሚዘበዝቡ፣ ሁልጊዜ ሰው ማጣጣል ላይ የተመሰጡ ሰዎች፣ ሁልጊዜም አልተሳካልን ዓይነት ደረት የሚመቱ፤ ለውድቀታቸው ሰው የሚወቅሱ ሰዎች፣ ለመውደቃቸው ኃላፊነት ከማይወስዱ ጋ አትወዳጅ ” ( ገጽ 17 ) ➫ ደካማነት ምቹ ስፍራ ሲያገኝ እና ጊዜ ሲደላደልለት የሚያብብ ደዌ ነው። ( ገጽ 25 ) ➫ መልካም አድራጎት የሚገዝፈው መልካም አድራጊው በየሰበቡ ካልፎከረበት ነው። ( ገጽ 28 ) ➫ ወደ በጎ መለወጥ ብዙ ጠመዝማዛ መንገድ አለው። እንደ መበላሸት ቀላል አይደለም። ( 31 ) ➫ አንዳንድ ትናንት ትናንት ላይ ብቻ አይቆምም። ዛሬያችንን የፈለገ ከትናንት አርቀን ሰቅለነዋል ብንል ፣ ጥለነው ብዙ መጥተናል ያልነው ትንናት ነጋችን ላይ በሁለት እግሩ ቆሞ እናገኘዋለን። ( ገጽ 49 ) ➫ ፍቅር ማለት ለሚያፈቅሩት ሲሉ ከማይችሉት ጋ መታገል እንጂ የሚያሸንፉትን ማሸማቀቅ አይደለም። ( ገጽ 59 ) ➫ ከአማኝ ጥቅማጥቅማችን አንደኛው ከአቅማችን በላይ የሆነ ሁነት ሲጋረጥብን እግዜር ላይ ሙጥኝ ማለት አይደል ?” ( ገጽ 65 ) ➫ ለራስ ሰው አለመድረስን ያህል አርፋጅነት የለም። ( ገጽ 70 ) ➫ ሴት ልጅ ትታለልልሃለች እንጂ አታታልላትም። ( 72 ) ➫ የወንዶች መስገብገብ ይመስለኛል ወሲብን ወንድ ብቻውን የተለየ ደስታ የሚያገኝበት ያስመሰለው። ( ገጽ 91 ) ➫ ፍቅራችን ለምናፈቅራቸው እንድንጠነቀቅ ካላደረገን ፍቅራችን የእውነት ላለመሆኑ ምስክር ነው። ( 95 ) ➫ ሰው በዕድሜ ብዛት ማስተዋል ከቻለ የሚማረው ነገር አለመፍረድን ነው። ( 96 ) ➫ የበዳይን ምክንያት ሳንጠይቅ በደልን ከምንጩ ማድረቅ እንዴት ይቻላል ?” ( 99 ) ➫ ችግራችንን የምናይበት መንገድ የገዘፈ ስለሆነ ነው ከችግራችን በታች የምንሆነው። ( 104 ) ➫ በአለም ላይ ስሜቱን እንደሚከተል ሰነፍ የለም፤ ስሜቱን ብቻ መከተል የሰው ባሕሪ አይደለም፡፡ ከስሜት እውነት ይበልጣል ፣ እውነት ነው በጊዜ ብዛት የማይደበዝዘው ፣ ስሜት ዘለቄታዊ ደስታን አይፈጥርም። ማደግ ማለት ደግሞ እውነትን እየመረረንም ቢሆን የመዋጥ ክህሎትን የማዳበር ሂደት ነው። ( 118 ) ➫ አሸናፊነት የሚመጣው ተጋጣሚ የሚፈልገውን ባለመስጠት ነው። የምንፈልገውን የምናገኘው እራሳችንን ከምንፈልገው ነገር ባለማሳነስ ነው። ( ገጽ 130 ) ➫ ራስን የመሆን እና ራስን የማወቅ ጥግ ራስን መቀበል ነው። በዙሪያችን ያሉ ሰዎች እንዲቀበሉን እኛ ቀድመን ራሳችን መቀበል አለብን። ደካማ ሰው ነው ድክመት ላይ የሚመሰጠው ፣ በራሱ የማይተማመን ፣ እንከኑ የሚያሳቅቀው ነው ጉድለት የሚያስሰው። የማይለወጥ ነገርን መቀበል ከራስ ጋ ያዋሕዳል። ያየነውን ጥሩ ነገር በትክክለኛው ሰዓት ማንፀባረቅ በራስ መተማመን ይባላል። በራሳቸው የማይተማመኑ ሰው ማሳነስ ላይ ሲረማመዱ የሚውሉ ናቸው። ( ገጽ 130 ) ➫ ማደጋችን የሚለካው የምንፈልገውን ሁሉ ባለማድረግ ነው። ( ገጽ 155 ) ➫ ሕመማችን የሚባባሰው የበሽታችን ምክንያቶች እናክምህ ሲሉን አይደል ?” ወዳጃችን ሲያቆስለን ሕመማችን የሚበረታው እንደሚያስብልን ማስመሰሉ ስለማይቀር ነው። ( 155 ) ➫ ባልተሳተፍንበት ነገር መስዋዕት የመሆን ያህል ከንቱነት የለም !! ( ገጽ 157 ) ➫ ተገማች አለመሆን ዓላማን ለማሳካት ምቹ ነው። ( 162 ) ➫ ከተበደለ የበለጠ ፣ መበደሉ የገባው በዳይ ኑሮው ሲኦል ነው !! ( 165 ) (Rama Gutema) https://t.me/yinuca
نمایش همه...
ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

አንባቢያንን እናበረታታለን። ደራሲያንን እንገነባለን!! የተሻለች ሀገር ለመፍጠር እንተጋለን! እኛ ጋር ነዎት!? 👉የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ 👇👇👇👇

https://youtube.com/@Ethel608?si=s0sl3_kQ8qTGZr3B

አስተያይት አለዎ 👇👇👇

https://t.me/ethelmezgebu

Photo unavailableShow in Telegram
ከሂሳብ እናወራርዳለን ፣ እስከ ሂሳቡን ስሩ ! . ትንሽ ለማመን ቢከብድም ተከታዩን ፅሁፍ የለጠፈው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ነው ። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት !! ፅሁፉ እንዲህ ይለናል ... <<ሂሳቡን ስሩ! ከፋኖ ጋር ያለውን ውጊያ መከላከያ በራሱ መንገድ ይጨርሰዋል>> ይልና ...ይህ መንገድ ደግሞ ምን አይነት እንደሆነ ቀጥሎ ያብራራልናል። 1..ጦርነቱ ሲያልቅ ቤተ/ክ እና መስጊድ መዋጮ ይደረግላቸዋል (ስለሚያፈርሷቸው?) 2, ወረዳና ዞኖቻችሁ ወደ ኋላ ይቀራሉ (በትግራዩ ጦርነት መቀሌን በሻሻ እናደርጋታለን ሲሉ ጠቅላዩ ተናግረው ነበር) 3, ብሔራዊ ፈተና እንዳለፋቸው ሰምተው ብዙ ተማሪዎች ይደነግጣሉ። .ፅሁፉ እንዲህ እያለ የሚቀጥል ነው። እንግዲህ የጠቅላዩ አማካሪ እንዲህ የሚሉን ...የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢ/ያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል የፈፀማቸውን የአስገድዶ መድፈርና የግድያ ወንጀሎች ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። የፅሁፉ መልዕክትም "ገና መቼ ተነካና ..ተማሪዎቻችሁ ብሄራዊ ፈተና እንዳይፈተኑ ፣ ገበሬዎቻችሁ እንዳያርሱ ፣ ሴቶቻችሁንም እንዲደፈሩ ይደረጋል" የሚል ነው። . . ዳንኤል ክብረት እንደዛሬ ቅልል ብሎ ...ትክክለኛ አውሬያዊ አላማውን ነግሮን አያውቅም ነበር። ለማንኛውም የዳንኤል ፅሁፎች ለአማራው ትግል ጉልበት የሚሰጡ ናቸው።አማራ ራሱን መከላከል እንዳለበት የሚመሰክሩ ናቸው። . . የአማራ ህዝብ ትግል "ከአማራ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን የሚለውን ሀይል እንደደረመሰው ሁሉ ፣ ሂሳቡን ስሩ ያስባለውንም ስርአት አሽቀንጥሮ ይጥላል" . ድል ለተገፋውና ፣ ሀቀኛ ምክንያት ላለው ሐበሻ!! . Zadhir !! https://t.me/ethelmeaia
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
📕 ቢነበብ የማይጠገብ መፅሐፍ ነው" የኛ ሰው በደማስቆ"። እውነተኛ ታሪክ ሲሆን የታላቁን እስራኤላዊው ሰላይ የኤሊ ኮሄንን ማንነትና ፍፁም ለአላማው መሰጠትን የሚገልጽ እና የእራኤልን ሞሳድ እንዲሁም ስለላውን በሶሪያ ውስጥ እስከ ስቅላት ሞት ሂወቱን ስለሰጠው ድንቅ ሰላይ(ስለላ) ይተርካል። 🙏 ይህ መፅሐፍ ለህይወታችን ለማንነታችን እጅግ የሚጠቅም የዓላማ ፅናትን ታማኝነትን ሐገር መውደድን የሚያስተምርና ራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርግ የማሞ ውድነህ ከምርጥ ስራዎቹ አንዱና ተወዳጅ መፅሐፍ ነው #አንብቡት እውነት ሁሌም የፀናች መሆኗን በማስረጃ የሚያሳይ ምርጥ መፅሐፍ ነው።
نمایش همه...
👍 1
📕 ቢነበብ የማይጠገብ መፅሐፍ ነው" የኛ ሰው በደማስቆ"። እውነተኛ ታሪክ ሲሆን የታላቁን እስራኤላዊው ሰላይ የኤሊ ኮሄንን ማንነትና ፍፁም ለአላማው መሰጠትን የሚገልጽ እና የእራኤልን ሞሳድ እንዲሁም ስለላውን በሶሪያ ውስጥ እስከ ስቅላት ሞት ሂወቱን ስለሰጠው ድንቅ ሰላይ(ስለላ) ይተርካል። 🙏 ይህ መፅሐፍ ለህይወታችን ለማንነታችን እጅግ የሚጠቅም የዓላማ ፅናትን ታማኝነትን ሐገር መውደድን የሚያስተምርና ራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርግ የማሞ ውድነህ ከምርጥ ስራዎቹ አንዱና ተወዳጅ መፅሐፍ ነው #አንብቡት እውነት ሁሌም የፀናች መሆኗን በማስረጃ የሚያሳይ ምርጥ መፅሐፍ ነው።
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.