cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Dr.Afewerk Medium clinic

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
235
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Repost from HAKIM Ethio
የበዓላት ሰሞን ምግቦችን ከጤና አንፃር 🍜በበዓላት ሰሞን የምናዘጋጃቸውና የምንመገባቸው ምግቦች የበዓሉን ድምቀት መጨመር፣ በምግቦቹ ጣዕም (ቃና) የምናገኘውን ደስታና ርካታን ታሳቢ የሚያደርጉ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ስለምንመገባቸው ምግቦች ተገቢነትና ጤናችን ላይ ስለሚያስከትሉት ችግር አብዛኞቻችን ግንዛቤ የለንም (Melese et al., 2020). 🍜ከዚህ ጋር ተያይዞ ብዙ ሰው በበዓላት ሰሞን በሚፈጠር የምግብ ለውጥ ምክንያት አዳዲስ የህመም ስሜት ሲሰማው ወይም ነባር ህመሙ ሲባባስበት ማየት የተለመደ ሆኗል 🍜በበዓላት ሰሞን በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ የተለመዱና ቤት ውስጥ ከማይጠፉ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዶሮ ወጥ ፣ ቁርጥ (ጥሬ ስጋ)፣ ክትፎ ፣ ጥብስ ፣ እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል 🍲ከነዚህ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዶሮ ወጥ (በዶሮ ወጥ መንገድ የሚዘጋጁ) ምግቦችን አንስተን ከጤና አንፃር የሚያስከትሉትን ችግር ለማየት እንሞክር:- 🍅ዶሮ ወጥን ለመስራት ከምንጠቀምባቸው ግብአቶች ውስጥ ሽንኩርት ፣ ቲማቲም ፣ በርበሬ ፣ ዘይት (ቅቤ) እና ሌሎች ቅመማቅመሞችን መጥቀስ ይቻላል 🍜የዶሮ ወጥ ዝግጅት ሂደት ደግሞ በከፍተኛ ሙቀት ዘይትን በማጋል ሽንኩርት እና ሌሎች ግብአቶችን ለረጅም ጊዜ ማቁላላት (ማብሰልን) ይጠይቃል በዚህ ሂደት:- 🍅በሽንኩርትና ሌሎች ግብአቶች ውስጥ የሚገኙ ሙቀት መቋቋም የማይችሉ ለጤና እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ቫይታሚኖችና ውህዶች ሊጠፋ (ሊቀንሱ) ስለሚችሉ ከምግቡ ተገቢውን ጥቅም ላናገኝ እንችላለን 🍟በተጨማሪም የምንጠቀመው ፈሳሽ ዘይት ሙቀትን የመቋቋም አቅሙ ዝቅተኛ ከሆነ ሲስ (cis) ተብሎ የሚጠራው ጤነኛ እና ተፈጥሯዊ የዘይቱ ክፍል ትራንስ (trans fat) ወደሚባል እጅግ መርዛማ ቅባት ይቀየራል (Iqbal et al., 2014). 🍟ከዶሮ ወጥ በተጨማሪ ይህ መርዛማ ቅባት በተጠበሰ ስጋ ወይም አሳ፣ ችፕስ ፣ ሳንቡሳ ፣ ቦንቦሊኖ እና በመሳሰሉት ምግቦች ውስጥ ይገኛል 🥫ሌላኛው እና ዋነኛው የትራንስ ቅባት (trans fat) መገኛ ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ነው 🥫አንዳንድ የዘይት አምራቾች በተለያየ ምክንያት በከፍተኛ ሙቀትና ግፊት hydrogenation የሚባል ሂደትን በመተግበር ፈሳሽ የአትክልት ዘይትን ወደ ጠጣር ሰው ሰራሽ የአትክልት ቅቤ ይቀይራሉ 🥫በዚህ ሂደት ከፍተኛ መጠን ያለው ትራንስ (trans) እና ሳቹሬትድ ቅባት (saturated fat) ይፈጠራል 🥫እነዚህ የቅባት አይነቶች "partially hydrogenated oil" በመባል የሚታወቁ ሲሆን ጤና ላይ በሚፈጥሩት ከፍተኛ ችግር ምክንያት በብዙ ሀገራት እገዳ (ክልከላ) የተደረገባቸው (FDA, 2020) ቢሆንም በእኛ ሀገር ግን በሰፊው እየተመረቱና ለተጠቃሚ እየቀረቡ ይገኛሉ 🥫በብዙ ጥናቶች እንደተረጋገጠው ትራንስ ቅባት (trans fat) LDL ተብሎ የሚጠራውን መጥፎ ኮሌስትሮል (bad cholesterol) እና TAG የሚባለውን የቅባት አይነት በመጨመር፣ HDL ተብሎ የሚጠራውን ጠቃሚ የኮሌስትሮል አይነት በመቀነስና የኢንሱሊን መጠን በመጨመር:- 🥫የደም የኮሌስትሮል መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደርጋል 🥫የደም ግፊት ፣ የልብ ፣ የስትሮክ እና የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራል ወይም ችግሮቹ እንዲባባሱ ያደርጋል (Harvard, 2006, Liska et al., 2016). 🥫ትራንስ ቅባት ለሰውነታችን ምንም አይነት ጥቅም የሌለው እና በአንፃሩ ጤና ላይ እጅግ ከፍተኛ ችግር ስለሚያስከትል ሁሉም የማህበረሰባችን ክፍል እነዚህን ቅባቶች እዳትመገቧቸው እንመክራለን 🍚ሌላኛው ለጤና ጎጂ ናቸው ከሚባሉ የቅባት አይነቶች ውስጥ አንዱ ሳቹሬትድ ቅባት (saturated fat) ነው 🍚እነዚህ የቅባት (የዘይት) አይነቶች በመደበኛ አከባቢያዊ ሙቀት የመርጋት ባህሪ ያላቸውን እንደ ቅቤ፣ ጮማ ስጋ ፣ የሚረጋ ዘይትና የመሳሰሉትን ያጠቃልላሉ 🍚ሳቹሬትድ ቅባት የትራንስ ቅባትን ያክል ባይሆንም በብዛት የሚወሰድ ከሆነ LDL የሚባለውን ኮሌስትሮል በመጨመር የልብ ጤናን ያውካል (Siri-Tarino et al., 2010). 🦴ስለዚህ የኮሌስትሮል መጨመር ፣ የደምግፊት ፣የልብ በሽታ፣ ስትሮክ፣ የስኳር በሽታ እና የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭነት የሚያሰጋችሁ ወይም ችግሩ ያለባችሁ 🌭ከበሬ ስጋ ይልቅ አሳና የዶሮ ስጋን ምርጫችሁ ማድረግና ዘይትን በማጋል ምግባችሁን ከማዘጋጀት ይልቅ በውሀ ወይም በእንፋሎት በማብሰል መመገብ ተመራጭ ይሆናል 🥑በተጨማሪም የተቀነባበሩ ዘይቶችንና ሰው ሰራሽ ቅቤ አለመጠቀምና በምትኩ ተፈጥሯዊና ጤነኛ የሆኑ እንደ ተልባ፣ ሱፍ፣ ሰሊጥ፣ አቮካዶ፣ ኦቾሎኒና የመሳሰሉትን ብትጠቀሙ የተሻለ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ 🍽️ ሌሎችን የምግብ አይነቶች በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን ‘’ ምግብ የጤናችን መሰረት እንጅ መጥፊያችን ሊሆን አይገባም’’ 🍓🍓🍓🍓አዲሱ አመት የሰላምና የጤና ይሁንልን🍇🍇🍇🍇 Muluken Fekadie... Asst prof. of Medical Biochemistry @hakimethio1 @hakimethio2
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የልጆች የቋንቋ እድገት ችግሮችን መለየት 📌ልጅዎ እነዚህን ችግሮች ካሳየዎት ወይም ስለሌሎች የልጅዎ የንግግር እና የቋንቋ እድገት ሌሎች ጉዳዮች የሚያሳስብዎት ከሆነ የንግግር እና የቋንቋ ባለሙያን ያነጋግሩ ፡፡ ልጅዎ ከዚህ በታች 1 ዓመት 🔘ለድምጽ ምንም ምላሽ አለመሥጠት 🔘ምንም ድምፅ አለማውጣት 🔘የመመገብ ችግር 🔘የመድገም እክል 🔘 የተገደቡ የእጅ ምልክቶችን መጠቀም። 2 ዓመት 🔘 በእጅ ምልክቶች ወይም በቃላት ለመግባባት ጥቃቅን ሙከራዎች 🔘የመጀመሪያ ቃላት ከሌለው 🔘ቀላል ትዕዛዞችን የመከተል እክል 🔘ለ“አይ” ትክክለኛ ያልሆነ ምላሽ 3 ዓመት 🔘 ውስን የንግግር አጠቃቀም 🔘ንግግራቸው ለመረዳት ያስቸግራል 🔘ውስን የሆነ ቀላል ጥያቄዎችን መረዳት 🔘ስሞችን የመጥራት ወይም የመሰየም እክል 🔘 ለተግባቦት ፍርሀት መኖር። ልጆች እና በእድሜያቸው መናገር የሚጠበቅባቸው ቃላት የልጆች ቃላት የመጀመሪያ ቃላቸውን ከተናገሩ በኃላ በፍጥነት እያደገ ይሄዳል፡፡ ቃላት በህይወት ልምድ፣ በትምህርት፣ በማንበብና በመሳሰሉት እያደገ እና እየጨመረ ይመጣል፡፡ 👉ልጆች በእድሜያቸው መናገር የሚጠበቅባቸው ቃላት ከታች ተዘርዝረዋል፡- 📌 12ወር - 2 to 6 (ከአባባ እና ከ እማማ ውጪ) 📌15 ወር -10 ቃላት 📌18 ወር -50 ቃላት 📌24 ወር - 200-300 ቃላት 📌30 ወር - 450 ቃላት 📌36 ወር - 1,000(3 አመት) 📌42 ወር -1,200 ቃላት 📌48 ወር - 1,600(4አመት) 📌54 ወር - 1,900 ቃላት 📌60 ወር - 2,200-2,500 ቃላት (5 አመት) 📌6 አመት - 2,600-7,000 ቃላት 📌12 አመት - 50,000 ቃላት
نمایش همه...
Repost from Hakim
"ልጆች እየተጫወቱ የባዕድ ነገር ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን?" - ዶ/ር አቤል ግደይ ፤ የህፃናት ሐኪም . ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦ ሲገባ ትንታን ያስከትላል። ይህ የአየር ወደ ሳንባ መግባትን በመከላከል እና ትንፋሽን በመቁረጥ የአተነፋፈስ ስርዓትን በማቆራረጥ ለአዳጋ ያጋልጣል። . ለየት የሚያደርገው የአየር መግባት በመከልከል በአጭር ጊዜ ለሞት ሊያደርስን ስለሚችል ነው። ለምሳሌ፦ አጥንት ፣ ክኒን ፣ ውሃ ፣ ኦቸሎኒ ፍሬ ፣ ስንዴ… ሌሎችን ጠጣር ነገሮች ወደ አየር ቱቦ ሊገቡ እና ትንታን ሊያስከትሉ የሚችሉ ናቸው። . የትንታ ምልክቶች ልክ ባዕድ ነገሮች ወደ መተንፈሻ አካላት ሲገቡ የሚኖሩ ምልክቶች እነዚህ ናቸው 1. በሃይል ማሳል 2. መናገር አለመቻል 3. ጮክ ያለ ድምፅ 4. መጥቆር 5. ትንፋሽ ማጠር 6. ማላብ 7. ድንጋጤ 8. አንገት ማሳከክ 9. መፍጨርጨር 10. ቀልብን መሳት 11. ማንቀጥቀጥ . ግዜ ከወሰደ •ተደጋጋሚ ሳል •ሽታ ያለው ዓክታ •ክብደት መቀነስ •ትንፋሽ ማጠርና መድከም . የትንታ የመጀመርያ እርዳታ አሰጣጥ 1. ሁኔታውን መታዘብ 2. መጠየቅ 3. ሰዎች እንዲረዱን መጣራት 4. ጀርባ መምታትና ሆድን መጫን አንድ ከእናንተ ጋር እየተመገበ የነበረ ሰው ድንገት ትን ቢለው በእነዚህ ከላይ በተዘረዘሩ መንገዶች ማገዝ ይቻላል። . ልጆች እየተጫወቱ ቆይተው ክኒን ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን? . 1. ሁኔታን መታዘብ • ምን እንደዋጡ መታዘብ • ይህም ህክምና ሂደን ለማስረዳት ይረዳናል • እርዳታ ሰጪ የአደጋ ምስክር እንደሆነ አስቡ። . 2. መጠየቅ • ምን እንደዋጠ መጠየቅ ለምሳሌ ፍሬ ፣ ምግብ ፣ ድንጋይ . 3. ሰዎች ለእርዳታ መጣራት • እሪ ብሎ መጮህ እና ሰዎችን እርዳታ መጠየቅ 4. ጀርባ መምታትና ሆድ መጫን • ሁኔታውን በፍጥነት በመረዳት ወደ እርዳታ መግባት ያስፈልጋል። . ሀ. ጀርባ መምታት ትልልቅ ሰዎች እንዲያጎነብሱ በማድረግ ከታች ከሚታየው ስዕል አድርገን 5 ግዜ ጀርባቸው መምታት ደጋግመን መተን ተስፈንጥሮ ከወጣ ጥሩ ካልሆነ ወደ ሆድ መጫን መቀጠል። . ለ. ሂልማች ማኑቨር / ሆድ መጫን ጀርባ ደጋግመን 5 ግዜ ከመታን በኃላ ቀጥለን ሆድን መጫን ያስፈልጋል። ይህ መቆም በሚችሉ ሰዎች ጀርባ ከመምታት በኃላ የምንፈፅመው ይህ ባዕድ ነገር መውጣት አለመውጣቱን ማየትና ካልወጣ እንዲወጣ እየመላለስክ መሞከር ወሳኝ ነው። . ትንታ በማይቆሙ ህፃናት . ልክ ባዕድ ነገር ሲገባባቸው ቁልቁል ደፍተን ጀርባቸውን 5 ግዜ በመምታት ከዛም ደረታቸውን እየደጋገምን ሌላ ጉዳት በማያስከትል መልኩ መጫንና መጠፍጠፍ ይጠበቅብናል። . 5. ህክምና መሄድ አንድ ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦው የገባበት ሰው ወደ ህክምና መሄድ አለበት። ሳንባ ቁስለት እንዳይፈጥርበት ሃኪም ሊያየው ይገባል። . የመጀመርያ እርዳታ የመጨረሻ አይደለም! @HakimEthio
نمایش همه...
Urgent Job vacancy Organization – Dr.Afewerk Salih medium clinic Location -Arsi robe didea,Oromia region Position 1. Nursing BSC degree/diploma Experience -1-2years and above - preferably work experience in pediatrics department. No requirement - one Sex – Both Salary – Negotiable 2.Labratory technician – Bsc degree /Diploma Experience – 1-2 year Sex – Both Salary -Negotiable No required – one Contact address – call 0967729428/0974955081
نمایش همه...
Urgent Job vacancy Organization – Dr.Afewerk Salih medium clinic Location -Arsi robe didea,Oromia region Position 1. Nursing BSC degree/diploma Experience -1-2years and above - preferably work experience in pediatrics department. No requirement - one Sex – Both Salary – Negotiable 2.Labratory technician – Bsc degree /Diploma Experience – 1-2 year Sex – Both Salary -Negotiable No required – one Contact address – call 0967729428/0974955081
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
FYI
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የጡት ማጥባት 12 ጥቅሞች የጡት ወተት ለህፃናት ከምግብነት ባለፈ የሚሰጠው ጥቅምና አንዲት እናት በማጥባቷ ብቻ የምታገኛቸውን ጥቅሞች እናያለን። ጡት ማጥባት ለልጅሽ 1. ከብዙ ኢንፌክሽኖች ይከላከላል። ለምሳሌ; የሳንባና የጆሮ ኢንፌክሽን፣ የማጅራት ገትር፣ የሆድ ቫይረስ 2. ከአለረጂክ ይከላከላል። 3. ብሩህ አዕምሮ እዲኖራቸው ያደርጋል 4. ከመጠን በላይ ውፍረትን በመከላከል አስተማማኝ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል 5. በህፃናት ላይ የሚከሰትን ካንሰር መጠንን ይቀንሳል 6. ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይቀንሳል ጡት ማጥባት ላንቺ 7. በእርግዝና ወቅት ያደገው ማህጸን ቶሎ ወደቦታው ስለሚመለስ የሚፈሰው የደም መጠን ይቀንሳል 8. ከልጅሽ ጋር የሚኖረው ፍቅር ይጨምራል 9. ከወሊድ በኃላ ቶሎ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል 10. እድሜ ሲገፋ የሚፈጠረውን የስኳር በሽታ ይቀንሳል 11. ከጡት እና ከእንቁላል ማምረቻ ካንሰር ይከላከላል 12. ወጪ ቆጣቢ ነው።
نمایش همه...