cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬

Advertising posts
8 017مشترکین
+1924 ساعت
+2477 روز
+1 09630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል። በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል። የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል:: ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 📌 t.me/Fastsinfo99     🌴  🌴  🌴
نمایش همه...
ግራኝ አህመድ ብርጌድ ተመሰረተ...⁉️ ሰው ላመነበት አላማ ስለሚከፍለው ዋጋ ሀሳብ መስጠት አልፈልግም። ምክንያቱም ያልገባኝ ነገር ስላለ አያገባኝም። እኔ ግን የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ። ሰው አንድ አይነት ቋንቋ እያወራ ለአንድ አላማ እየታገለ ትልቅ ጠላት አለኝ ብሎ በርሃ ገብቶ እንዴት ትልቁ ጠላቱን እረስቶ እዛው እርስ በ እራሱ ይጋጫል? .* አሜሪካን ሀገር ቁጭ ብለው እኛ የዘመነ ካሴ ነን! እነ እከሌ የእስክንድር ነጋ ናቸው።የጎጃም ፋኖ ተጠሪነቱ ለእከሌ ነው። የምስራቅ ፋኖ መግለጫ እኛ አይመለከተንም። የጎንደር ወጣት በማንም አይመራም ። የሚንሊክ ብርጌድ ተጠሪነቱ በሟች አሳምነው ፅጌ ነው። የወሎ ፋኖ ማንም ተነስቶ አያዘውም። ግራኝ አህመድ ብርጌድ በወሎ እዝ ነው። .* ብቻ ምን አለፋችሁ የማይሰማ ጉድ የለም።ባለፈው ሶስት ሳምንት ናሁሰናይ ብርጊድ ተመሰረተ በአዲስ አበባ ፋኖ እንቅስቃሴ ተጀመረ ተብሎ ጠዋት ተመስርቶ በዛኑ ቀን ጠዋት ፈርሶ በዛኑ ቀን ጠዋት ጥይት ጠጥቶ ሞተ የሚል ዜና በተሰማ በዛው ጠዋት ደግሞ ሌላው የፋኖ ብርጌድ ይህ እኛን አይመለከትም ብሎ መግለጫ ያወጣ ነበር። .* ወንድሜ ሆይ በቁምህ እያለህ አሜሪካ ያለው ዲያስፖራ በስምህ ጎፈንድሚ ከፍቶ ይሰበስባል። ስትሞትም በመሞትህ ያዘነ መስሉ አሁንም ሞትህን ምክንያት አድርጎ ገፈንድሚ ይሰበስባል። በዚህ ብቻ የሚያበቃ እንዳይመስልህ በቤተሰብህ ስም እንደገና ብር ይሰበስባል። ተቸግረዋል ብሎ አደባባይ አውጥቶ መለመኛ ያድርጋቸዋል። ዲያስፖራው በዚህ መጠን ክፉ ነው ንቃ! .* ደግሜ ደጋግሜ አሁንም እኔ ግን እንዲህ እላለሁኝ። ወጣት ሆይ ውድ ነፍስህን በጎፈንድ ሚ እራሱን እና የቤተሰቡን ኑሮ ለሚለውጥ ብለህ አትሙት። አሜሪካ እና አውሮፓ ቁጭ ብሎ ገፋ በለው እያለህ ወደ ነበልባል እሳት የሚከትህን አትስማው። ተበድለናል ብለህ ካመንክ ቀድመህ ውስጥህን አጥራው። ገዳይህ አብሮ የቆመው መንድምህ ነው።😂😭 የተፃፈው በ #TST_APP ____ 📌 t.me/Knowledge055         🥦    🥦    🥦
نمایش همه...
👍 3 1🤯 1
«ለኢትዮጵያ አየርመንገድ አመራሮች እንዲደርስ ሼር አድርጉልኝ» በ©ረከት አደራ! ለካ እንደዚም አለ ወገን ትላንትና ማታ ነው Apr 28 2024 በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከፍሽቱ 2:20  ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የደረስኩት business class  ካውንተር ላይ አንድ ሴት እና አንድ ወንድ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ነበሩ። በስተቀኝ ቼክኢን ሲያደርግ ለነበረ  ቀጭን  የቀይ ዳማ ወጣት የኢትዮጵያ ፓስፖርቴን ሰጠሁት የት ነው የምትሄጂው አለኝ ደብሊን አልኩት በየት በኩል አለኝ በአርላንዳ  ኤርፖርት በስቶኮም በኩል አልኩት ሲስተም ቼክ አላረገ ፓስፖርቴን አላየ መሄድ አትችይም  ትራንዚት አይፈቀድም አለኝ። ሁሌ የምመላለስበት መንገድ ነው እኮ ወንድሜ አውሮፖ ውስጥ ስፔሻል ቪዛ የሚያስፈልገው ለለንደን ብቻ ነው አልኩት  በቃ ዞር በይ ሌላ ከስተመር ላስተናግድበት አለኝ እኔስ አልኩት  የማውቀው ነገር የለም ሴኩሪቲ ከመጥራቴ በፊት  አትረብሺኝ ዞር በይልኝ አለኝ እሺ ጥራ በቃ  ዞር አልልም አልኩት። አንድ ኢሚግሬሽን የሚሰራ ወጣት በአጋጣሚ እያለፈ አይቶ እባክህን እየረበሸችኝ ነው ዞር አድርግልኝ አለው ወጣቱም  ምንም ሳይናገር ጥሎ ሄደ እኔም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ሄጄ  ሱፐርቫይዘር ካለ አናግሩኝ ተቸግሬአለው አልኳቸው  አንድ የአየር መንገዱ ሰራተኛም ምን ልርዳዎት አረፍ ይበሉ አለኝ። የሆነውን ነገርኩት ነይ እንሂድ ብሎ ወደ ካውንተሩ ሄድን ምንድ ነው ይችላሉ እኮ መብረር ለምን አስቆምካቸው ብሎ ጠየቀው  እራሱ ሲስተሙ ውስጥ ገብቶ  ካየ በኃላ እንቢ ያለው ወጣት እንዲሰራ አዘዘው ወጣቱም ቼክኢን አደረገኝ  ቆም ብዬ ብዙ አሰብኩ  የኢትዮጵያ ፓስፖርት በመያዜ ብቻ ሲስተም ቼክ ሳያደርግ  አትበሪም በማለቱ መርህ አልባ  ድርጊት በመፈፀሙ በጣም አዝኛለው አፍሬአለም እኔ አንድ ቀንም ዜግነት ባለመለወጤ ፀፅቶኝ አያውቅም፣ ሀገሬን ወዳታለው  እንደዚ ያሉ ብራንዳችንን ክብራችንን መጠሪያችን የሆነውን  ብቸኛው አየር መንገዳችን  ስሙ እንዲጎድፍ ሰዎች እንዲማረሩበት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚሰሩ ግለሰቦች መኖራቸውን አውቄአለው። እኔ በሌላ አየር መንገድ business class ከምጏዝ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ  ቢሆን ብጏዝ እመርጣለው  ብዙ ጥሩ ሰዎች ያሉበት ቤት ነው ግን ጥቂቶቹ ስርአት አልበኞች  የአየር መንገዱን መልካም ስም እያስጎደፉ ስለሆነ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል  እላለው። ሼር አድርጉ ለሚመለከተው አካል ይድረስ ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 📌 t.me/Fastsinfo99     🌴  🌴  🌴
نمایش همه...
👍 5
የ1 ሺህ 800 ዓመት እስር የተፈረደባት አህላም አልባሽር። አህላም አልባሽር የተሰኘችው ይህች ሶሪያዊት ፈጽማዋለች በተባለ የሽብር ጥቃት 6 ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ እንደቆሰሉ ተገልጿል የሽብርተኝት ወንጀል ፈጽማለች። እንደ ቱርክ ብዙሃን መገናኛዎች ዘገባ ከሆነ ተከሳሿ ከሁለት ዓመት በፊት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ማዕከል በሆነችው ኢስታምቡል ልዩ ቦታው ኢስቲክላል በተሰኘ ስፍራ የተፈጸመውን የሽብር ትቃት አቀነባብራለች ተብሏል፡፡ በዚህ የሽብር ጥቃት ምክንያት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ የአካል ማጉደል አደጋ እንዳጋጠማቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ አህላም አልባሽር የተባለችው ይህች ተከሳሽ በዜግነት ሶሪያዊት ስትሆን በቱርክ ህግ አውጪ ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ፒኬኬ ቡድን አባል ነችም ተብሏል፡፡ ታዋቂው የቱርክ ተዋናይ ትምህርት ቤቱን ወደፍርስራሽነት ለውጦታል ተከሳሿ ከዚህ የሽብር ቡድን ተልዕኮ በመቀበል በኢስታምቡል ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት ዋነኛ ተዋናይ ነች በሚል በሰባት ወንጀሎች የእድሜ ዘመን እስር ተላልፎባታል፡፡ ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 📌 t.me/Fastsinfo99     🌴  🌴  🌴
نمایش همه...
ታሪካዊው የ24 ሰዓት የአፋን ኦሮሞ ኪነ ጥበብ  ነፃነት ቀን ቀኑ ጥር 6 እና 7 ,1969 ዓ/ም ቅዳሜና እሁድ ቦታው ፊንፊኔ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር ግቢ በኦሮሞ ህዝብ የዘመናዊ ታሪክ ምዕራፍ ውስጥ አንድ የታሪክ ክስተት ሲሆን የኦሮሞ ህዝብ ከአፄው መንግሥት መውደቅ በኃላ ለ24 ሠዓታት ቢሆንም ነፃነቱን አውጆ ታሪክ የሰራበትና የኦሮሞ ህዝብ አንድነት የተቀነቀነበት ፣ የኦሮሞ ታሪክ ባህል እሴትና ማንነት በአደባባይ ለመጀመሪያ ጊዜ በቲያትር ቤት በነፃነት ቀርቦ በራሱ በኦሮሞ ህዝብ ልጆች ኦሮሙማ የተሰበከበት ታሪካዊ እለት ነበር ። ከሐረር፣ ከወለጋ፣ ከኢሉአባቦራ ፣ ከባሌ ፣ ከአርሲ ፣ ከሸዋ ቱለማ ፣ ከጅማ : ከቦረና እና ከረዩ ፣ ከወሎ የተውጣጡ የኦሮሞ ህዝብ ልጆች ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ መድረክ የተሰባሰቡባት ታሪካዊው የጥር 6 እና 7 ,1969 ዓ/ም እለተ ቅዳሜና እሁድ በኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ውስጥ የ24 ሰዓቷ ነፃነት በመባል በታሪክ ተመዝግቧል። ይህንን የጥር 6 እና 7 ,1969 ዓ/ም ቅዳሜና እሁድ ታሪካዊ እለት በአንድ የታሪክ መድብል መጽሃፍ በወቅቱ የተሳተፋችሁ አባቶችና እናቶች ይህ  ታሪካዊው የ24 ሰዓት የነፃነት እለት እንዲፃፍ ብታደርጉ በታሪክ ውስጥ የነበረው ይህንን ያልተፃፈ ታሪካዊ ቀን ለትውልድ ስለአፋን ኦሮሞ ኪነጥበብ እድገት አመጣጥና ትግል ምንነት ለትውልድ አስተማሪ ነው እላለሁ። የፎቶግራፍ ምንጨ ይህንን ታሪካዊ እለት የተሳተፊ አባቶችና እናቶች ለኡርጅ መጽሄት የመጋቢት 14 , 1989 ዓ/ም ነው እትም ያበረከቱት ነው ። በነገራች ላይ ይህ ታሪካዊው እለት ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ልጅ ከየአቅጣጫው ወደ ፊንፊኔ መጥቶ እንዲታደም ጥሪ የተደረገው በበሪሳ ጋዜጣ ሲሆን በወቅቱ ይህንን ትልቅ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጀሮ ዳባልበስ ብሎ ፕሮግራሙን በምስል አልቀረጸውም  አንድ ሁለት የመድረክ ስራ ሙዚቃዎች ብቻ በቲያትር ቤቱ በአርካይቭና ዶክመንቴሽን ለመቀረጽ ችለዋል። በነገራችን ላይ በወቅቱ የመግቢያ ትኬት ሁሉ አልቆ በርካታ የፊንፊኔ ነዋሪዎች ፕሮግራሙን ገብተው ባይታደሙም በቲያትር ቤቱ ዙሪያ በመቀመጥ እስከ ፕሮግራሙ ማብቂያ ድረስ በመቆየት ተሳትፈዋል። በዚህ ፕሮግራም የተሳተፊ ታዋቂ አርቲስቶች መካከል የመድረክ መሪ ኩማ ኢዳኤ ፣ ዶ/ር አሊ ቢራ ( Qajimaan daraaree, bilisummaa tantoo sumatu namararee..) ብሎ በመጫዎት ፣ ዛሬ በህይወት የሌለችው አሻ አመዴ ( bilisummaa deyimaa nyaadhuu mee ilaali , waliigalteen makii jaalalan  bul -  bulii) ብላ በመጫዎት ፣  የዳንኤል ነመራ ግጥም በህብረት የተዘፈነ " kottaa aramaa aramnaa midhaan keenya keessa , tuufoo bubuqqifna  copha isaatu balle - essaa የድምፃዊ ዘሪሁን ወዳጆ ዘፈን " .... nurratti kufee turee  ba'aan inni gudaan isaa " ብሎ የተጫዎተው ፣ ድምፃዊት እልፍነሽ ቀኖ " Qawwee male maaltu gabrummaa nu baasaa? ብላ የተጫዎተችውና ድምፃዊ ጋዲሳ አብዱላሂ " Qeerroo Mataa Tuutaa hin jarjartuu suuta" የሚለው ተወዳጅ ሙዚቅ ሲሆን ይህን የድምፃዊ ጋዲሳ አብዱላሂ Qeerroo Mataa Tuutaa hin jarjartuu suuta በወቅቱ በብሄራዊ ቲያትር ቤቱ የተቀረጸው አንድ ኦዲዩ  ሙዚቃ ይገኛል። በዚህ ታሪካዊው የ24 ሰዓት ነፃነት ቀን ታሪካዊ የጀግንነት የትግል ግጥሞች መነባንቦች ፣ የፍቅር ማህበራዊ ግጥሞች ፣ አጫጭር ድራማዎች ቀርበው ነበር። በዚህ ታሪካዊ የ24 ሰዓት የአፋን ኦሮሞ የኪነጥበብ ነፃነት ቀን በኪነጥበብ ሙያተኝነት በታዳሚነት ለተሳተፋችሁ በሙሉ ክብር ይገባችኃል። ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ🙏 የተፃፈ በ #Negash_Qemant ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 📌 t.me/Fastsinfo99     🌴  🌴  🌴
نمایش همه...
🥰 4
... #ሻቢያ ‼️ በፊንፍኔ ከተማ ውስጥ ከ28 ሀገራት የተውጣጡ ከ 77 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኛ ዜጎች ሲኖሩ ከእነዚህ 77,653 መካከል UNHCR እንዳመላከተው በመዲናዋ ከሚገኙ ስደተኞች 92 በመቶ የሚሆኑት  የኤርትራ ዜጎች ሲሆኑ ቁጥራቸውም 71,588 መሆኑን ጠቅሷል።
نمایش همه...
👍 2
'ቅርጣሱ የሚለበጥበት ቆዳ ከአውራ ጣትህ ላይ በሚወሰድ ደም ከተለቀለቀ ቦሀላ ተሰፍቶ አንገትህ ላይ ይንጠለጠላል" በዚህ በ21ኛው ክ/ዘ ፋኖ በትብታብ የሚያምን ታጋይ 😂😎
نمایش همه...
👍 2😁 1