cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
998
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

'ቤቲንግ' ~ ቁማር በኢስላም የተከለከለ ነው። በሐራም ስራ ላይ መሰመራትም መተባበርም አይፈቀድም። ስለዚህ የቁማር (betting) ቤት መክፈት፣ ቁማሩ ላይ መሳተፍ፣ ለአቋማሪዎች ቤትን ማከራየት፣ ከነሱ ዘንድ ተቀጥሮ መስራት፣ በየትኛውም መልኩ ለቁማሩ ስራ /ቤት ድጋፍ መስጠት አይፈቀድም። {وَتَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلۡبِرِّ وَٱلتَّقۡوَىٰۖ وَلَا تَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَ ٰ⁠نِۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِیدُ ٱلۡعِقَابِ } "በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ። ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ። አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።" [አልማኢዳህ፡ 2] Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ጀነት ውስጥ ትልቁ ፀጋ ምንድነው? (አላህ ይህን ከሚጎናፀፉት ያድርገን) ኢብኑል ቀዪም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል። "አብዛኛው ሰው ለጀነት ያለው አመለካከት የተሳሳተ ነው፣ ጀነት ማለት ዛፎች ያሉባት፣የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ምግብ፣መጠጥ፣ሑረልዒን፣ወንዞችና ህንፃዎች ለነዚህ ለዛዎች ብቻ የዋለ ስም አይደለም። ጀነት ማለት ሙሉና ልቅ የሆነች የመጠቃቀሚያ አገር ናት፣ ከመጠቃቀሚያዎች በሙሉ በላጩ ፀጋ፦ የቸሩ አላህን ፊት መመልከት ፣ንግግሩን መስማት፣የጀነት ሰዎች የአይን ማረፊያቸው ከርሱ መቅረብና ውዴታው መሆኑ። የዚህ ፀጋ (ለዛ)ከመብላት ከመጠጣት ከመልበስ ለዛ ጋር ፈፅሞ ሊነፃፀር አይገባም።" 【መዳሪጁ ሳሊኪን፤2/80】 አላህ ሆይ በራህመትህ ጀነትን ከሚገቡና ፊትህን ከሚያዩ ሰዎች አድርገን!።
نمایش همه...
ለዱዓህ ምላሽ ቶሎ ባታገኝ ራሱ ዱዓእ ትልቅ ዒባዳ መሆኑን እወቅ ለዒባዳኮ አላህ ወፍቆሃል ማለት ነውኮ ☺
نمایش همه...
╭「• አለ ቃል ኪዳንሽ •」 │ ❏ በልቤ ተከትቦ │ 🏝🔎 ደስ የሚል ግጥም ├─────────── ├📲 📝 ኡሙ ፈውዛን ╰—————————— ⏸↘️⤵️↙️ #ሰለፍያ____!!! ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ አለ ቃል ኪዳንሽ በልቤ ተከትቦ በመከራ መሀል ደምቆና ተውቦ ሙሀባሽ እንደ ነርቭ አካሌን ተብትቦ ብዙውን አለፍኩት ፍቅርሽ ተደራርቦ አሻግሬ አይቼ የእውነትሽን ልቀት ከጨለማ ወጣሁ ገዝቶኝ ያንች ድምቀት ☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅ #ሰለፍያ___!!! ሁሌ በእየለቱ ፍቅርሽ ይጨምራል ተውሒድና ሱናሽ እጂግ በጣም ያምራል ሙሉ ማንነትሽ እውነት ይናገራል ብርሀንሽ በርቀት ጨለማን ያበራል ሰው ጂን እንስሳትን ህግሽ ያስከብራል ይሔ ሚስጥርሽ ነው የኔነቴ ሞራል #ሰለፍያ___!!! ✅⭕️☑️✅⭕️☑️ የኔ መታወቂያ ንፁህ የደም ስሬ የመንፈሴ እርካታ የእውነት መምህሬ የጀነት ትኬቴ የሰውነት ክብሬ ሀዘን ማስወገጃ የደስታ ጂምሬ ሀቅን ያየሁብሽ ማጉያ መነፀሬ የالله ስጦታ አንችኮ ነሽ ፍቅሬ ☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️ #ሰለፍያ___!!! ፍቅሬ ከልቤ ነው ማስመሰል አይደለም ካንች ተለይቼ ከምኖር ዘላለም ያንች ሆኘ ልሙት ይድረቅብኝ ቀለም አስተማማኝ መርከብ በሁለቱም አለም ሰለፍያ አንች ነሽ ካንች ሌላ የለም ✍️⭕️✅📱☑️↪️📝↩️ #ሰለፍያ__!!! ሰንት ነገር ገጥሞኝ ባንች ተፅናንቼ አንች አለሽኝ ብዬ ወደ አንች ገብቼ ያንች አገልጋይ መሆን ልቤን አስመኝቼ ምርኮኛሽ ሆኛለሁ እጅ እግሬን ሰጥቼ ከሽርክ ከቢዲዐ ወደ አንች ቶብቼ ምንም ብዘገይም እንቅልፌን ተኝቼ ባለ ማወቅ አለም ብቆይም ዘግይቼ ሳውቅሽ ገሰገስኩኝ እጂግ ተፀፅቼ አሁን ግን ያንች ነኝ ፅናት ተመኝቼ ➘➴➘➷➴ #ሰለፍያ___!!! አካሌ ከርፍቶኝ በወንጀል ጨቅይቼ የአመፅን ቁልቁለት ዳገቱን ወጥቼ ጭንቅንቅ ብዬ ሰውነቴን ስቼ ከሀሳብ ስመለስ ራሴን አንፅቼ ሀዘኔ ይጠፋል አንችን ተመልክቼ ☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅ #ሰለፍያ___!!! መጥፎ ነሽ እያሉ ሰወች ሲፀየፉኝ በጎን እየገፉ በማስመሰል ሲያቅፉኝ ሀቅን እንዳልሰማ እያደናቀፉኝ እውነትን ደብቀው ውሸትን ሲያቀብሉኝ አብሽር በርቺ ጠንክሪ ግፊበት እያሉኝ በሆነ ባጋጣሚ በሆነ ክስተት እውነትን ፍለጋ ሁሌም ስንከራተት ድንገት ቀና ብዬ ሀቅን ስመለከት አንችን አገኘሁሽ በالله በረከት ✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅ #ሰለፍያ___!!! በወንጀል ጨቅይቼ ምን ብሸማቀቅም አንችን በመምረጤ እኔ አልሳቀቅም ከቶ ይስጠኝ እንጂ የእውነት ያድለኝ ፍቅርሽን ዘምሬ ማንም ምንም ቢለኝ ህዝብ ፊት መንገድ ዳር ቀጥቅጦ ቢገድለኝ በالله ይሁንብኝ ምንምኮ አይመስለኝ ♻️☑️✅⭕️♻️☑️✅⭕️ #ሰለፍያ__!!! እውነተኛ ሚዛን የሌለሽ አምሳያ የስኬትን ሚስጥር አብራርቶ ማሳያ ጥፍጥናሽ የሚገዝፍ ከማር ከቡቃያ መታወቂያዬ ነሽ ጥምጣምም ኮፍያ ከህይወት በላይ ነሽ ደዕዋ ሰለፍያ!!! 📝 በኡሙ ፈውዛን https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy
نمایش همه...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

ያ የቁጭት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬን እንጠቀምበት ~ ሶደቃ የብዙ በላእ መመከቻ ሰበብ ነው። ለዱንያም፣ ለአኺራም፣ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ... የሚሻገር ብዙ ፋይዳዎች አሉት። መታከሚያ ያጡ ህመምተኞች፣ ዱንያ ጨልማባቸው ጎዳና ላይ የወደቁ ጎስቋሎች፣ የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሞት ሸሽተው ሜዳ ላይ የፈሰሱ ተፈናቃዮች፣ ተዘርፈው አገራቸው መግቢያ ያጡ መንገደኞች፣ ገቢ የሚያስገኝ ስራ አጥተው ሃሳብና ጭንቀት የወረሳቸው ምስኪኖች፣ ለያዙት ጨቅላ ጡት የሚሆን ነገር ያጡ አራሶች፣... በየጥጋጥጉ አሉ። በመሰል ቦታዎች ላይ ትንሽም ብትሆን የሶደቃ ድርሻ ይኑረን። * ይህ ሲሆን ለወገን የመቆርቆር ስሜት እናዳብራለን። ይህንን ስሜትኮ ብዙዎቻችን አጥተነዋል። * የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። ይህንን አላህ ያደለው ብቻ ነው የሚያውቀው። * የመስጠትን ባህሪ እያዳበርን እንሄዳለን። ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጎለብተው ልብም ኸይር ስራን በማዘወተር ይጎለብታል። መስጠትን ስናዘወትር መስጠት ባህሪያችን ይሆናል። ስንርቅ ከልባችን ይርቃል። ልባችንም ይደርቃል። ስለዚህ በሶደቃ ልባችንን እናክም። * ከነገ ፀፀት ለመትረፍ ሶደቃ እናብዛ። ሰዎች በፀፀት እሳት ከሚቃጠሉባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ "ምነው ጥቂት እድሜ አግኝቼ ሶደቃ ባደረግኩ?!" የሚል ነው። ሁሉን አዋቂው ጌታ እንዲህ ይላል፦ { وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقۡنَـٰكُم مِّن قَبۡلِ أَن یَأۡتِیَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ فَیَقُولَ رَبِّ لَوۡلَاۤ أَخَّرۡتَنِیۤ إِلَىٰۤ أَجَلࣲ قَرِیبࣲ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِینَ } "አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና 'ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድሆን ዘንድ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ' ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።" [አልሙናፊቁን፡ 10] Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ሡፍያን አስ–ሰውሪይ እንዲህ ይላሉ፦ “ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህን በመፍራት ላይ አደራህን! ከሰዎች መገለልን አጥበቀህ ያዝ፣ በራስህ ላይ ተጠመድ፣ የአላህን መፅሐፍ (ቁርኣን) መጽናኛ አድርግ።” 📚አልጀርህ ወት–ተዕዲል (1/87)
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.