fa
Feedback
Elon Academy plc ኤሎን አካዳሚ

Elon Academy plc ኤሎን አካዳሚ

رفتن به کانال در Telegram

EVERY STUDENT,EVERY CHANGE,EVERY DAY AT ELON!!! For more information ✍ጠቃሚ የስልክ ቁጥሮች✍ https://t.me/Elonschool7/4669

نمایش بیشتر
5 837
مشترکین
+1424 ساعت
+867 روز
+8230 روز
آرشیو پست ها
#📚📚የአመቱ_የመጨረሻ_የንባብ_ቀን📚📚📚 https://youtube.com/watch?v=IPJlTmTdLyQ&si=KJdQrAD8XebW5fJ9

ለቅምሻ.....😉😁❤

🍾ታላቅ የምስራች🍾 ትምህርት ቤታችሁ አስደማሚ ግስጋሴዉን በመቀጠል ዊንጌት አካባቢ በተለምዶ ትራፊክ ሰፈር የሚባለዉ ቦታ ላይ በ8,000 ካሬ ላይ ከአፀደ ሕፃናት -12 ክፍል ተጨማሪ ቅርንጫፋን በ
🍾ታላቅ የምስራች🍾 ትምህርት ቤታችሁ አስደማሚ ግስጋሴዉን በመቀጠል ዊንጌት አካባቢ በተለምዶ ትራፊክ ሰፈር የሚባለዉ ቦታ ላይ በ8,000 ካሬ ላይ ከአፀደ ሕፃናት -12 ክፍል ተጨማሪ ቅርንጫፋን በመክፈት የአገልግሎት አድማሱን ለማስፋት በከፍተኛ ዝግጅት ላይ መሆኑን ለእናንተ ዉድ ቤተሰቦቻችን ስናበስር ደስ ይለናል። ተባብረን በመስራት ተጨማሪ እድገቶችን እናስመዘግባለን። የትምህርት አጋርዋ!!!

የኤሎን አመታዊ መልዕክ፦ ገደብ አልባነት ለባርነት ዳርጎናል።
የኤሎን አመታዊ መልዕክገደብ አልባነት ለባርነት ዳርጎናል።

የኤሎን አመታዊ መልዕክት.....ስማ ላልሰማ አሰማ😉🧐😉
የኤሎን አመታዊ መልዕክት.....ስማ ላልሰማ አሰማ😉🧐😉

የኤሎን አመታዊ መልዕክት.....ስማ ላልሰማ አሰማ😉🧐😉
የኤሎን አመታዊ መልዕክት.....ስማ ላልሰማ አሰማ😉🧐😉

🎯 ማስታወሻ 🎯 🏆የአመቱ የመዝጊያ የቤተሰብ ቀን🏆 🏅ቅዳሜ ሰኔ 27 ጠዋት ከ2:30-6:00 የዊንጌትና የራስደስታ አፀደ ሕፃናት ልጆችና ወላጆች የሚገኙበት የቤተሰብ ቀን። 🎖 ቅዳሜ ሰኔ 27
🎯 ማስታወሻ 🎯 🏆የአመቱ የመዝጊያ የቤተሰብ ቀን🏆 🏅ቅዳሜ ሰኔ 27 ጠዋት           ከ2:30-6:00 የዊንጌትና የራስደስታ አፀደ ሕፃናት ልጆችና ወላጆች የሚገኙበት የቤተሰብ ቀን። 🎖 ቅዳሜ ሰኔ 27 ከሰዐት          ከ7:30-10:00 የዲዝኒ አፀደ ሕፃናት ተመራቂና የፓላስ አንደኛ ደረጃ ተሸላሚ ልጆችና ወላጆች የሚገኙበት የቤተሰብ ቀን።      🏅እሁድ ሐምሌ 4፦           ከ2:30-6:00 የ22 አፀደ ሕፃናትና የኢስት ዊንግ አንደኛ ደረጃ ተመራቂና ተሸላሚ ልጆችና ወላጆች የሚገኙበት የቤተሰብ ቀን።። 🎯  ሌሎች ዝርዝር መረጃዋች በSchoolx እና በደብዳቤ ይገለፃል ል።

#አርብ_ቀን_5_ውድ_መምህራኖቻችንን_አመስግነናል https://youtube.com/watch?v=GVrvU1hOdsQ&si=pUhVbxoSOisKljgP

የፈተናዋቹ ቀናትና የትምህርት አይነቶቹ
+1
የፈተናዋቹ ቀናትና የትምህርት አይነቶቹ

🎯 ለዘንድሮ ክልላዊ ፈተና ተፈታኞች ተማሪዋች ና ወላጆች🎯 የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡ ➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ ⓫ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ ⓬ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም። ⓭ በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን። መልካም ፈተና🙏

መልዕክት ከኤሎን የበላይ አላፊዋች ለቤተሰቦቻችን፣ ዉድ ወዳጆች/ቤተሰቦች በድርጅታችን ኤሎን አካዳሚ በጣም ትልቅ ቦታ ከምንሰጣቸዉ ቀናት መካከል ከአዉራዋቹ አንዱ በዚህ ሳምንት ያሳለፍነዉ የምስጋና ሳምንት ቀዳሚዉ ነዉ። ከቀናቱም ደሞ እንዲህ እንደዛሬዉ የምናከብረዉ የመምህራንና የርእሳነ መምህራን የምስጋና ቀን የተለየ ስፍራ እንሰጠዋለን። ባለፋት ቀናት የትምህርት ባለሙያዋችን ከወረዳ እስከ ክፍለከተማ፣ዉድ የልጆቻችንን ወላጆች/አሳዳጊዋችን፣ወዳጆቻችንን እና በት/ቤታችን በልዩ ልዩ የአገልግሎት ዘርፍ ሲያገለግሉን የቆዩትን የኤሎን ቤተሰብ አባሎቻችንን ለምስጋና እጅ ስንነሳ ቆይተናል። ዛሬ ደሞ ምትክ አልባ የሆናችሁትን እናንተ መምህራንንና ርዕሰ መምህራንን "ስለ ቤተሰብነታችሁ እጅ እንነሳለን፣ኮርተንባችኋል " ስንል በምስጋና እጅ ለመንሳት እነሆኝ ደርሰናል። ዉድ ወዳጆች፣ በእርግጥም ኮርተንባችኃል። ብዙም ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ዉስጥ፣ጊዜያዊ የሚያማልሉ ነገሮች በፈታኝነት በበዙበት በዚህ ግዜ፣ነገሮች ከእለት ወደ እለት ፈታኝነታቸዉ እየጨመረ ባለበት በዚህ ሰዐት ለቃላችሁ ታምናችሁ የተረከባችኃቸዉን ልጆቻችሁን ከትርፋችሁ ሳይሆን ከጉድለታችሁ ጭምር እያካፈላችሁ በተቻላችሁ መጠን ምንም ሳይጎድልባቸዉ አመቱን እንዲጨርሱ በማስቻላችሁ በእርግጥም ልትመሰገኑ ይገባል። ኤሎን አሁን ላይ የደረሰበት ከፍታ በምንም መመዘኛ የእናንተ የትጉሀን ቤተሰቦቻችን እገዛ ና መስዋትነት ባይኖር የሚታሰብ አልነበረምና ዉለታችሁን መቼም አንዘነጋዉም።ቤተሰቦቻችን ስለሆናችሁ ፣ስለተወዳጃችሁን ክብር ይሰማናል። ዉድ የኤሎን ቤተሰቦች፣ ት/ቤታችሁ የ16 አመታት አስደማሚ ግስጋሴዉን ቀጥሎ በቅርቡ በአዳዲስ የብስራት ዜናዋች እናንተን ዉድ ቤተሰቦቹን ማኩራቱን ይቀጥላል። ተባብረን በመስራት ያስመዘገብነዉና የምናስመዘግበዉ ዉጤት  የጋራ ድላችን ነዉና ሁላችንም ልኩራበት ይገባል። ደግሞም በዚህ ጉዞ ማንም የድል አጥቢያ አርበኛ የለምና ኤሎን ዉስጥ አንድም ቀን ሆነ አንድ አመት የቆያችሁት ቤተሰብነታችሁ በግዜ አይለካምና ለደረስንበትና ለምንደርስበት ስኬት ሚናችሁ ከፍ ያለ ነዉ ። በመሆኑም ሁላችንም በእኩል መጠን መደሰታችንና የድሉ ተጋሪ መሆናችን የተገባ ነዉ። ወዳጆች፣ በመጨረሻም በድጋሚ እንኳን ለዚህ የምስጋና ቀን አደረሰን አደረሳችሁ እያልን ቀሪዉ የስራ ግዜያችሁ ስኬታችሁን ይበልጥ የምታጣጥሙበት ፣መጭዉም ግዜ ደሞ ለበለጠ ድልና ስኬት የምትዘጋጁበት እንዲሆን ቤተሰባዊ ምኞቻችንን እንገልፃለን። ተባብረን በመስራት ለዉጥ አምጥተናል። ወንድሞቻችሁ የኤሎን የበላይ ሀላፊዋች። ሰኔ 2018.

የመምህራን ምስጋና -ዊንጌት ቅርንጫፍ🙏
+3
የመምህራን ምስጋና -ዊንጌት ቅርንጫፍ🙏