cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Skyline media

پست‌های تبلیغاتی
47 518
مشترکین
-3124 ساعت
-1857 روز
-92230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

👍 2
ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አደረገ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል፡፡ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ፥ ለማዕቀፉ ተግባራዊነት የሚረዱ እርምጃዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ ዛሬ ይፋ የተደረገው ለውጥ የብሔራዊ ባንክን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘመንና አሠራሩን ከዓለም ማዕከላዊ ባንኮች መልካም ተሞክሮዎች ጋር በማጣጣም ረገድ ፋይዳ ያለው ታሪካዊ እርምጃ መሆኑም ተገልጿል፡፡ በዚህም የባንኩን ፖሊሲ- ነክ የወለድ መጣኔ መወሰን፣ ከባንኮች ጋር የግብይት ጨረታ መጀመር፣ የአንድ ቀን የብድርና የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት ተግባራዊ ማድረግና የባንክ ለባንክ የገበያ ሥርዓት ማዘጋጀት ብሔራዊ ባንኩ በስትራቴጂአዊ ዕቅዱና በባንኩ ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የተሰጡትን ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት እጅግ አስፈላጊ እርምጃዎች መሆናቸውም ተብራርቷል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ስለጉዳዩ የሰጠው ዝርዝር መግለጫ እንደሚከተለው ይቀርባል፡-...                                                                                                                                                          https://www.fanabc.com/archives/252969
نمایش همه...
ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል፡፡ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ፥ ለማዕቀፉ ተግባራዊነት የሚረዱ እርምጃዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ ዛሬ ይፋ የተደረገው ለውጥ የብሔራዊ ባንክን የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘመንና አሠራሩን ከዓለም ማዕከላዊ ባንኮች መልካም ተሞክሮዎች ጋር በማጣጣም ረገድ ፋይዳ ያለው ታሪካዊ […]

Photo unavailableShow in Telegram
👍 4 1
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሆኑት ቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀርና ማሊ ተዋሃዱ ይህ ለመላው አፍሪካ በተለይ ለኛ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ምሳሌ ይሆናል የተባለው ውህደት የተፈፀመው በትላንትናው እለት በኒያሚ ሲሆን የሶሱቱ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች በይፋ ተፈራርመዋል። የቀኝ ገዢ ሀገራት የሆኑትን እነ ፈረንሳይን ከሀገራቸው ሙልጭ አርጎ በማባረር የጀመረው ይህ የውህደት ጉዞ እነኚህን የሳህል ቀጠና ሀገራት በመጨረሻም በኮንፌዴሬሽን አዋህዷል። እነኚህ ሀገራት በተለምዶ ኢክዋስ የሚባለውን ምዕራባዊያን ለጥቅማቸው የመሰረቱትን ማህበር በይፋ የተፋቱ መሆኑንም በትላንትናው እለት ይፋ አርገዋል። በዚህም መሰረት ውህደቱ " Confederation of Sahal State / AES" የሚል የጋራ ስያሜ የተሰጠው ሲሆን የጋራ መገበያያ ገንዘብ፣ የጋራ ህገ መንግስት ፣ የጋራ የመከላከያ ጦር ፣ የጋራ ኤምባሲ፣ የጋራ ፓስፖርት ወዘተ የመሳሰሉትን የሚኖራቸው ሲሆን የ72 ሚሊየን የህዝብ ብዛት በማቀፍ ገዝፈው ተመስርተዋል። ሀገራቱ በተፈጥሮ ሀብት እጅግ የበለፀጉና በነ ፈንሳይ ሲበዘበዙ የኖሩ ሲሆን በተለይም ለኒውክሌር ሀይል ሚውለው የዩራኒየም ክምችትና ወርቅን የመሳሰሉ ማዕድናት በከፍተኛ ሁኔታ በመሬታቸው ይዘው ይገኛሉ። ኢትዮጵያን ከባህር ለማራቅ ሲሉ ድህነትና መከራን የመረጡት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ከዚህ ምን ይማሩ ይሆን ? ኢትዮጵያስ እንዲህ ያለውን መንገድ ለመከተል ምን ይጠበቅባታል ? መልሱን ለናንተ ትተናል ! ኢትዮጵያዊነት Ethiopiawinet
نمایش همه...
👍 21
ሶማሊላንድ፣ ለኢትዮጵያ እሰጠዋለሁ ያለችው የባህርበር ስፍራ፣ ከኢትዮጵያ ድንበር 100 ኪ/ሜ እርቀት ላይ ይገኛል የሚል መረጃ አለ። ባይረጋገጥም፣ ሶማሊያ፣ ከኢትዮጵያ ድንበር 200ኪ/ሜ ርቀት ላይ ወደፊት ሊለማ የሚችል የባህር በር ቦታ ለመስጠት ( ሆብዮ) ፈቃደኛ ነች የሚል መረጃ እየወጣ ነው። ሥፍራውም፣ለወደብነት በሚውል መልኩ፣ በቱርክ እና በቃታር እንዲለማ ታስቧል ይባላልም። ሥራው፣ የተወሰነ ጊዜ መጠየቁ አይቀርም። የባህር በሩ፣ ለኢትዮጵያ የባህር ሀይል አገልግሎት የመስጠቱ ነገር ግን፣ ከእስካሁኑ የሶማሊያ አቋም አንጻር አጠራጣሪ መሆኑን መገመት አይከብድም። ሶማሊያ፣ለንግግር ልቀመጥ ማለቷ ግን፣ በተወሰነ ደረጃ፣ የዲፕሎማሲ ጠቀሜታ ሊያስገኝላት ይችላል። ይህ መረጃ እርግጠኛ ከሆነ ደግሞ፣የታሰበው የባህር በር፣ የኢትዮጵያን ሙሉ ፍላጎት ስለማያሟላ( የባህር ሀይል ጦርሰፈር የማቋቋም ጉዳይ እና የባህር በሩ አስተማማኝ ደህንነት) ይሁንታ የምትሰጠው አይመስልም። በመሆኑም፣ ከበርካታ ምክንያቶች አንጻር፣ኢትዮጵያ፣ ከሶማሊላንድ የምታገኘው የባህር በር፣ ሳይበልጥባት አይቀርም። ብርሃኑ አሰፋ
نمایش همه...
👍 15
Photo unavailableShow in Telegram
👍 12 1
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባብያ ስምምነት ተከትሎ በኢትዮጵያ እና ሶማልያ መሀል የተከሰተውን ውጥረት ለማርገብ ያለመ ውይይት በሁለቱ ሀገራት መሀል በቱርክ፣ አንካራ ነገ ንግግር እንደሚጀመር መረጃዎች እየወጡ ነው። በዛሬው እለት የሶማልያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ልኡካቸው ወደ ቱርክ ያቀኑ ሲሆን የኢትዮጵያ ልኡክም ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ይጠበቃል። ውይይቱ የሚደረገው ከሳምንታት በፊት የኢትዮጵያው የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ መንግስትን "እንነጋገር" ጥያቄ ይዘው ለአሸማጋይነት ለቱርኩ መሪ ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን መልዕክት ካደረሱ በኋላ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ውይይት ውጤት ካፈራ በመሪዎች ደረጃ ንግግር ወዲያው እንደሚጀመር የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።
نمایش همه...
👍 11 3
የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ባለፉት 11 ወራት ውስጥ በከተማው 12 ሴቶች ተገድለው በድምሩ ከ4 ሺህ በላይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል አለ። ከሰሞኑን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲሰራጭ የነበረው መረጃ የ11 ወራት ሪፖርት መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በ2016 ባለፉት 11 ወራት 4 ሺህ 340 ወንጀሎች የተመዘገቡ ሲሆን ወንጀሎቹ 7 ዓይነት ናቸው። ✔12 ሴቶች ሲገደሉ፣ ✔80 የአስገድዶ መደፈር፣ ✔1 ሺህ 953 የስርቆት፣ ✔583 የድብደባ፣ ✔178 የግድያ ሙከራ እንዲሁም ✔10 የጠለፋ ወንጀሎች መሆናቸውን የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ገልጿል። ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ170 በላይ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ሃይሎችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ በእጅጉ ያስፈልጋል ተብሏል። በቅርቡ በክልሉ ዋና ከተማ እና ሌሎችም አካባቢዎች በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እና አፈና ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፎች እንደተካሄዱ መዘገባችን አይዘነጋም።
نمایش همه...
👍 10 4
37ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
نمایش همه...
👍 16
Photo unavailableShow in Telegram
የትናንቱን የባህርዳር የሰላም ኮንፈረንስ ተከትሎ የተደረገውን የመንግሥት የሰላም የውይይት የድርድር ጥሪን ተከትሎ በጎንደር በኩል ጫካ ወጥተው የነበሩት ምላሽ መሰጠት ጀምረዋል። ከ39 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ማህበረሰባቸውን ተቀላቅለዋል። ማህበረሰባቸውን የተቀላቀሉ ታጣቂዎችም ለተደረገላቸው የሰላም ጥሪ መንግሥትን አመሥግነው በቀጣይ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው መደበኛ ሥራቸውን እንደሚጀምሩ እና ሌሎች አካላትም መንግሥት ያመቻቸውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች የጀግንነትን መንገድ የመረጡ ለማህበረሰባቸው እረፍት ማግኘት የፈለጉ ናቸውና ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። የሽፍታ ትግል ለራስም ሆነ ለወጡበት ማህበረሰብ እረፍት የማይሰጥ ልማትን የሚያርቅ የጥፋት መንገድ ነው!!
نمایش همه...
👍 18 2
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.