Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 382
مشترکین
+624 ساعت
+787 روز
+36130 روز
آرشیو پست ها
የኢትዮ-ጣልያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ::
ኮሌጁ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አክለውም የዘንድሮ አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ኮሌጁ መጠነ ሰፊ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀው ወጣቶች እንደ ሀገር የትኩረት ዘርፍ የሆነውና ለወጣቱ ብዙ እድሎችና አማራጮችን ወደያዘው የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በመቀላቀል ራሳቸውንም ሆነ ሀገርንም መጥቀም ሚችሉበት መልካም አጋጣሚ የተፈጠረ በመሆኑ በተለይ የ2015 ዓ.ም የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ወጣቶች ይህን መልካም እድል በአግባቡ እንዲጠቀሙም መልዕክት አስተላልፈዋል::
የኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ኤልያስ መሀመድ በበኩላቸው ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም የስልጠና ዘመን በዘጠኝ የሙያ ዘርፎች(ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፣ አውቶሞቲቭ፣ ማኑፉክቸሪንግ፣ ውድ ዎርክ፣ አይ.ሲ.ቲ፣ኮንስትራክሽን፣ ሆቴልና ቱሪዝም፣ ድራፍቲንግና ሰርቬይንግ፣ አካውንቲግ) ስልጠን ለመስጠት እንደተዘጋጁ ጠቅሰው በተጨማሪም ኮሌጁ ዘንድሮ እስከ 2000 አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማሰልጠን አቅም እንዳለውና ለዚህም ወጣቶችን በሰፊው እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ገልፀዋል::
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙን የዝግጁነት ምዕራፍ ሪፖርት እና የ2016 ዓ.ም መሪ እቅድ ላይ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ተወያየ።
በእለቱ በነበረው መድረክ በጠዋት ውሎ በ2015 ዓ.ም በኮሌጁ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለተቋሙ ሰራተኞች ማቅረቡ የተቻለ ሲሆን በመቀጠልም በዝግጁነት ምእራፍ ወቅት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ሰፋ ባለ ሁኔታ ለሰራተኛው ቀርበዋል።
መድረኩ በከሰአት ውሎው ሲቀጥልም የ2016 ዓ.ም የኮሌጁ መሪ እቅድ ለሰራተኛው በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በቀረቡት ሪፖርቶችና መሪ እቅዶች ላይ ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ ሀሳብና አስተያየት ተሰቶባቸው ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገባቸው በኅላ በመጨረሻም በኮሌጁ ዲኖች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰቶባቸውና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ፍፃሜውን እጊኝቷል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥቅምት 09/2016 ዓ.ም
"የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው" በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ፡፡
በዓሉንም የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና በስሩ የሚገኙ የድሬዳዋ እንዲሁም የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡
ከመድረኩም ማጠናቀቂያ በአንድነት ለሰንደቅ ዓላማ ክብር በሰጠና የህብረ-ብሄራዊነታችን መገለጫ እንዲሁም የብሔር ብሔረሰቦች የብሩህ ተስፋ ምልክት መሆኑን በሚያሳይ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የታጀበ የባንዲራ መስቀል ስነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 5/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
