Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 406
مشترکین
+1024 ساعت
+507 روز
+34930 روز
آرشیو پست ها
“ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (ACTION RESEARCH)”
🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢
✍️ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ EASTRIP PROJECT ጋር በመተባበር በጥናትና ምርምር ለሚገኙ እና የኤ ደረጃ አሰልጣኝ መምህራን በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ላይ ያተኮረ ስልጠና በማዘጋጀት አቅም የሚገነቡበትን እድል ፈጥሯል፤ ይህም ስልጠና መሰረታዊ ጥናትና ምርምር ከተግባራዊ ጥናትና ምርምር ያለው ልዩነት፤ የተቋማዊ ችግሮች ልየታ፤ ምልከታ በማድረግ ለተግባራዊ ጥናትና ምርምር ፕሮፖዛል ማዘጋጀት በሚያስችሉ ጽንሰ ሃሳባዊና ተግባራዊ ዝግጅት ማድረግ በሚያስችል ምልኩ ከኢትዮ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን የስልጠናውም ዋና ዓላማ በኮሌጁ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ተግባራዊ ልየታ በማድረግ በጥናትና ምርምር ላይ ተመስርቶ እንዲፈቱ በሚያስችል የአሰልጣኝ መምህራኑን አቅም ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ ነው፤
🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡
✍️ በዚህም ስልጠና ላይ በኢትዮ ጣሊያን እና በድሬዳዋ ፖሌቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሁም በኢትዮ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ካምፓስ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በቀጣይም ልየታ የተደረገባቸውን ችግሮች ለመፍታት እንዲያስችል በተዘጋጁት ፕሮፖዛሎች መሰረት የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩን ተጨባጭ ውጤት የሚያስገኙ ስራዎች የሚሰሩበት ሁኔታ እንደሚመቻች የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ገልጸዋል፡፡
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
ድሬዳዋ
ጥር 28/2014
የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን
“ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ (STEM)”
===================================
🟢 በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቀደም ሲል ከተለያዩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በተደረገው ውይይትና በተደረሰው የጋራ መገባባትና በተዘጋጀው ዕቅድ መሰረት የአዲሱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ የአዲስ ከተማ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የቅድስት ማርያም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ ማለትም(STEM) ግንዛቤ ለማስጨበጥ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከጥር 26-28/2014 ዓ.ም ጉብኝት አድርገዋል፡፡
🟡 በዚህም ተማሪዎቹ የተግባር ስልጠና የሚሰጥባችውን የትምህርት ክፍል(workshop) በመጎብኘት ስለቴክኒክና ሙያና በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ (STEM) ግንዛቤ ማስጨበጥ ተችሏል፡፡ እንዲሁም ተማሪዎቹ የማኑፋክቸሪግ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል፤ የአውቶሞቲቭ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል፤ የፈርኒቸር ትምህርትና ሰልጠና ክፍል እና የኤሌክትሪክና ኢሌክትሮኒክስ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል አሰልጣኝ መምህራን ለጉብኝት ለመጡት ተማሪዎቹ የተግባር ስልጠና የሚስጥበትን ክፍሎች(workshops) በማስጎብኘት ተማሪዎቹን ግንዛቤ እንዲጨብጡ አድርጓል፡፡
🔴 በተጨማሪም ሌሎችም በድሬዳዋ አስተዳደር ስር የሚገኙ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተዘጋጀው ዕቅድና በተዘረጋው መርሃግብር መሰረት በኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት መሰል ጉብኝቶችን የሚያደርጉ ሲሆን በቀጣይም ከጉብኝት ባሻገር ተማሪዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ(STEM) በፈጠራ ስራ ዝንባሌ ያላችውን የተመረጡ ተማሪዎች ክህሎታችውን ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ የተግባር ስልጠና በሚሰጥባችው የትምህርት ክፍል(workshop) ላይ በተግባር የሚደገፉበት ሁኔታ መመቻቸቱን የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ገልጸዋል፡፡
ድሬዳዋ
ጥር 28/2014
የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን አረንጓዴና ጽዱ የማድረግ የአንድ ወር ዘመቻ ተጀመረ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
"Clean and Green TVET" በሚል መሪ ቃል ለአንድ ወር የሚቆየው እና ዛሬ የኮሌጁን የተለያዩ አካባቢዎችን በማፅዳት በተጀመረው ዘመቻ ላይ የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ አሰልጣኝ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም ሰልጣኝ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመሆኑም ለአንድ ወር በሚቆየው ዘመቻ ላይ ኮሌጁን ውብ፣ ፅዱና በአረንጓዴ ልምላሜ የተላበሰ በማድረግ ለትምህርትና ስልጠና ሂደቱ ምቹ አካባቢ የመፍጠር ዓላማ ያለው መሆኑን የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮ ጣሊያን ኮምኒኬሽን
ጥር 06/2014 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ለክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞቹ እንዲሁም ለመላው የእምነቱ ተከታዮች እንኳን ለ2014ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።
#መልካም_በዓል
" TVET DIGITALIZATION & INTERNATIONALIZATION "
======================
▶ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተያዘው የበጀት አመት የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ለውጥ አምጪ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፤
▶ ከነዚህም ተግባራት አዲስ በጸደቀውና ትኩረት በተሰጠው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ የተቀመጠው TVET DIGITALIZATION & INTERNATIONALIZATION እሳቤ መሠረት ኮሌጁን በአስተዳደሩ አልፎም በሀገሪቱ ካሉ ኮሌጆች ሞዴል ለማድረግ የሚያስችል የመጀመሪያ ምዕራፍ ስራዎች ማጠናቀቅ ተችሏል፤
▶ በዚህም መሰረት ይሄ ስራ ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ በኮሌጁ ትምህርትና ስልጠና እየተከታተሉ የሚገኙ የአይ.ሲ.ቲ ዲፓርትመንት ሰልጣኝ ተማሪዎችና አሰልጣኝ መምህራን እንዲሁም በሁሉም ረገድ ለኮሌጁ ድጋፍ ያደረገው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለይም በአይ.ሲ.ቲ ፑል ስር ለሚገኙ ባለሙያዎች የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፤
▶ በዚህ የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ላይ የድሬዳዋ ቴ/ሙ/ት/ስ ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሳሊም የተገኙ ሲሆን የተሰራውን ስራ ባድነቅና የሰሩትንም አካላት በማመስገን በቀጣይ ይሄን ስራ በማስፋት በአስተዳደሩ የሚገኙ ኮሌጆችን በማስተሳሰር ብክነትን በመቀነስ ቀልጣፋ አሰራርን ሊያመጣ የሚችል ስራ ሊሰራ አንደሚገባ አመላክተዋል፤
▶ በመጨረሻም በሁለተኛው ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ የፕሮግራሙንም ማጠቃለያ የተሰሩትን ስራዎች በመጎብኘት ማድረግ ተችሏል።
የኢትዮ ጣሊያን ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 28/2014 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"ድህረ ጦርነት ስትራቴጂ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ውይይት
=====================================
✍️ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር የሰራ ክህሎትና የቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በወቅታዊው የሀገራችን በተለይም ድህረ ጦርነት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፤
✍️ በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የተገኙ ሲሆን ጦርነቱን ቀልብሰን ከጣለብን ጠባሳ ባሻገር ያሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በዋናነት አንድነታችንን በመጠበቅ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ብልጽግናን የማረጋገጥ መንገዳችንን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ በማተኮር ተጨባጭ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ ይህም መድረክ አስፈላጊነቱ ከዚሁ የሚመነጭ ነው ብለዋል።
✍️ በሌላ በኩል በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ የቢሮውና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችም አስተያየትና ሀሳባቸውን፤ ጥያቄ የፈጠሩባቸውን እና ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ብለው ያሰቡትን ሁሉ በፍጹም ነጻነት መድረኩን ለሚመሩ አካላት ያቀረቡ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽ ለሚያስፈልጋቸው ሀሳቦች ምላሽ በመስጠትና እና ከመረጃ ጉድለት የተነሱ ሀሳቦችን በቂ መረጃ እን ዲያገኙ በማድረግ የተሰጡ ገንቢ አስተያያቶችን መቀበላቸውን የገለጹ ሲሆን፤
✍️ በመጨረሻም የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የመድረኩ ተሳታፊ ሰራተኛች በዋናነት አንድነትችንን ሊከፋፍሉ ከሚችሉ እኩይ እና ጊዜ የሚጠብቁ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እንዲመለከትና መተማመንን በመፍጠር ከድል ሽሚያ ወጥተን በጦርነት ያስመዘገብነውን ድል በልማቱ መድገም እንደሚገባ በማሳሰብ መድረኩን አጠቃለዋል።
የኢትዮ ጣሊያን ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 25/2014 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"ድህረ ጦርነት ስትራቴጂ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ውይይት
=====================================
✍️ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር የሰራ ክህሎትና የቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በወቅታዊው የሀገራችን በተለይም ድህረ ጦርነት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፤
✍️ በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የተገኙ ሲሆን ጦርነቱን ቀልብሰን ከጣለብን ጠባሳ ባሻገር ያሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በዋናነት አንድነታችንን በመጠበቅ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ብልጽግናን የማረጋገጥ መንገዳችንን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ በማተኮር ተጨባጭ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ ይህም መድረክ አስፈላጊነቱ ከዚሁ የሚመነጭ ነው ብለዋል።
✍️ በሌላ በኩል በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ የቢሮውና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችም አስተያየትና ሀሳባቸውን፤ ጥያቄ የፈጠሩባቸውን እና ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ብለው ያሰቡትን ሁሉ በፍጹም ነጻነት መድረኩን ለሚመሩ አካላት ያቀረቡ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽ ለሚያስፈልጋቸው ሀሳቦች ምላሽ በመስጠትና እና ከመረጃ ጉድለት የተነሱ ሀሳቦችን በቂ መረጃ እን ዲያገኙ በማድረግ የተሰጡ ገንቢ አስተያያቶችን መቀበላቸውን በመግለጽ የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የመድረኩ ተሳታፊ በዋናነት አንድነትችንን ሊከፋፍሉ ከሚችሉ እኩይ እና ጊዜ የሚጠብቁ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እንዲመለከትና መተማመንን በመፍጠር ከድል ሽሚያ ወጥተን በጦርነት ያስመዘገብነውን ድል በልማቱ መድገም እንደሚገባ በማሳሰብ መድረኩን አጠቃለዋል።
የኢትዮ ጣሊያን ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 25/2014 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"ድህረ ጦርነት ስትራቴጂ" በሚል ርዕስ የተካሄደ ውይይት
=====================================
✍️ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ በድሬዳዋ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በወቅታዊው የሀገራችን በተለይም ድህረ ጦርነት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፤
✍️ በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የተገኙ ሲሆን የጦርነቱን ቀልብሰን ከጣለብን ጠባሳ ባሻገር ያሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በዋናነት አንድነታችንን በመጠበቅ ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ብልጽግናን የማረጋገጥ መንገዳችንን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ በማተኮር ተጨባጭ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ ይህም መድረክ አስፈላጊነቱ ከዚሁ የሚመነጭ ነው ብለዋል።
✍️ በሌላ በኩል በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ የቢሮውና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችም አስተያየትና ሀሳባቸውን፤ ጥያቄ የፈጠሩባቸውን እና ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ብለው ያሰቡትን ሁሉ በፍጹም ነጻነት መድረኩን ለሚመሩ አካላት ያቀረቡ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽ ለሚያስፈልጋቸው ሀሳቦች ምላሽ በመስጠትና እና ከመረጃ ጉድለት የተነሱ ሀሳቦችን በቂ መረጃ እን ዲያገኙ በማድረግ የተሰጡ ገንቢ አስተያያቶችን መቀበላቸውን በመግለጽ የቢሮው ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው የመድረኩ ተሳታፊ በዋናነት አንድነትችንን ሊከፋፍሉ ከሚችሉ እኩይ እና ጊዜ የሚጠብቁ ጉዳዮችን በጥንቃቄ እንዲመለከትና መተማመንን በመፍጠር ከድል ሽሚያ ወጥተን በጦርነት ያስመዘገብነውን ድል በልማቱ መድገም እንደሚገባ በማሳሰብ መድረኩን አጠቃለዋል።
የኢትዮ ጣሊያን ኮምኒኬሽን
ታህሳስ 25/2014 ዓ.ም
ድሬዳዋ
'''''''''''''''''"""""""'''''''''''''''''''''''''""""""'''''''''''''''''"""""""''''''''''''"" በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቴ/ሽ/ኢ/ኤ/አ የስራ ሂደት ቀደም ሲል በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህራን በሳይንስ፣በቴክኖሎጂ፣በምንድህስና እና ሂሳብ(STEM) የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቶ ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በአስተዳደሩ የሚገኙት የብስራተ ገብርኤል እና ጀሩሳሌም ት/ቤቶች የተመረጡ ተማሪዎቻቸውን በተቋማችን ይዘው በገኘት አስጎብኝተዋል።
ተማሪዎቹ በጉብኝታቸው የተለያዩ ዲፓርትመንቶችና ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በዲፓርትመንት ተጠሪዎችና በተቋሙ ሀላፊዎችም ስለ ቴክኒክና ሞያ ዘርፍ ሰፋ ያለ ማብራሪ ተሰቷቸው ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።
