Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
2 366
مشترکین
+1224 ساعت
+977 روز
+37130 روز
آرشیو پست ها
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ቴሬሳ የተመራ የሱፕርቪዥን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ ምልከታ አካሄደ::
በሚኒስትር ድኤታው የተመራው የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በበጀት አመቱ እስከ አሁን የተሰሩ ትግበራዎች ላይ ምልከታ ያደረ ሲሆን ቡድኑ በቅድሚያ በኮሌጁ የተሰሩ ትግበራዎች ሪፖርት በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ቀርቦለት በቀረበው ሪፖርት ላይም ቡድኑ ግብረ መልስ በመስጠት ምክረ ሀሳቦችንም አስቀምጧ።
በተጨማሪም የሱፕርቪዥን ቡድኑ የቀረበለትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በኮሌጁ ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና ከተቋማት ግንባታ አኳያ የተሰሩ ሥራዎች ተዘዋውሮ የተመለከት ሲሆን በዚህም ተቋሙ አሰልጥኖ ወደ ስራ እዲገቡ ያደራጃቸውን ሰልጣኞች ያሉበትን ሁኔታ የተመለከተ ሲሆን እንዲሁም በኮሌጁ የተሟላ ድጋፍ በሰልጣኞች እየተሰሩ ያሉ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል::
በመጨረሻም ሚንስትር ድኤታው በኮሌጁ የተመለከቷቸውን የለውጥ ስራዎች እንዲሁም ሰልጣኞችን አሰልጥኖ ከስራ ጋር በማስተሳሰርና በማደራጀት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ በመሆናቸውና በአስተዳደሩም ሆነ እንደ ሀገር ፍሬያቸው የሚታይ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቢሮው በኩል አስፈላጊውን ትብብር እንዲሁም ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገልፀዋል::
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ህዳር 24/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች በአለም ለ37ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀን በዛሬው ዕለት አክብረዋል::
"ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች.አይ.ቪ አገልግሎት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል በፖናል ውይይት የተከበረ ሲሆን መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንዳሉትም በተቋሙ ያሉ ሰራተኞች በአብዛኛው ወጣት ከመሆናቸው አኳያ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና ተቋሙ ለሚያሰለጥናቸው ሰልጣኞችም ተገቢውን ግንዛቤ በመፍጠር እንደ ሀገር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አፅእኖት ሰተው ተናግረዋል::
በመድረኩ ከጤና ቢሮ በመጣ ባለሙያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ሰነድ ጨምሮ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በዚህም ሰራተኛው የቫይረሱ ስርጭት ላይ ያለውን ግንዛቤ እንዲያሳድግ ረድቶታል::
በተጨማሪም በመድረኩ ሁሉም ማህረሰብ የሚያስፈልጋቸውን የኤች.አይ.ቪ መከላከል እና መቆጣጠር አገልግሎቶች ገደብ ሳይኖር ተደራሽ ማድረግ ተገቢ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይም ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ቅድሚያ መስጠት ተገቢ መሆኑን ተነግሯል፡፡
ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ህዳር 20/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መደበኛ ስልጠና አጠናቃቂ ለሆኑ ሰልጣኝ ተማሪዎች የኢንተርፕሩንርሺፕ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል::
ስልጠና በዋናነት ሰልጣኝ ተማሪዎች መደበኛ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲወጡ ስራ ፈጣሪነትን ተላብሰው እንዲወጡና በሚፈጥሩትም ስራ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከመጥቀም ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ እንዲተርፉ የሚያስችላቸው የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና እንደሆነም ተገልፇል::
የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናውን የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከEntrepreneurship Development Institute(EDI)ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ስልጠናው በቀጣዮቹ ቀናትም ቀጥሎ የሚሰጥም ይሆናል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ህዳር 14/2017 ዓ.ም
በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተከናወነው የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ዙሪያ
ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የADRA ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በፕሮጀክቱ ተወካይ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ስልጠና ላይ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ጭምር በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በዚህም በመጀመርያ ዙር የፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በቀጣይ ለሚሰጠው ስልጠና እንቅፋት እንዳይሆኑ ከወዲሁ ለማስተካከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር የመፍትሄ አቅጣጫዋችን ማስቀመጥ ተችሏል።
መድረኩ ቀጥሎም እንደ አገር አዲስ የሆነው የሶላር ቴክኒሺያን እና ኤክስፐርት የስራ መዘርዝር 'JOB BOX ' ሰነድ ከሲቪል ሰርቪስ በመጣ ባለሙያ የቀረበ ሲሆን ሰነዱንም የሚመለከታቸው ተቋማት ሁኔታውን በደንብ ገምግመው ግብረመልስ ተሰቶበታል።
በቀጣይም የተሰራው የJOB BOX ሰነድ እንዲፀድቅና የሶላር ፒቪ ተጠቃሚ ተቋማት የሶላር ኤክስፐርት/ ቴክኒሺያን በመቅጠር የሶላር ዘርፍ ላይ ያለውን ከፍተኛ ክፍተት መሙላት እንደሚጠበቅባቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም በADRA ፕሮጀክት የሰለጠኑ ባለሞያዋችም ከሚከፈትላቸው የስራ እድልም ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደላድል ይፈጥራልም ተብሏል።
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ህዳር 13/2017 ዓ.ም
በአስተዳደሩ በሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ፖሊቴክኒኮች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራ ሂደቶች አዘጋጅነት ለጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስለሚሰጠው የኢ/ኤ/ቴ/ሽ አገልግሎት ድጋፍ ላይ ያተኮረ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄደ::
የውይይት መድረኩን የሁለቱ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የኢ/ኤ/ቴ/ሽ አገልግሎት ስራ ሂደት ም/ ዲኖች በጋራ የመሩት ሲሆን በመድረኩም የ2016 ዓ.ም የኢ/ኤ/ቴ/ሽ አገልግሎት አፈፃፀም ላይ እንዲሁም የ2017 ዓ.ም በተሰራ የዳሰሳ ጥናት እና በቀጣይ ስለሚደረግላቸው ድጋፍ እንዲሁም የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የሙያ ብቃት ምዘናን በተመለከተ አጠቃላይ ገለጻ በስራ ሂደቱ ባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተችሏል፡፡
በመጨረሻም የ2016 ዓ.ም አፈፃፀምን መነሻ በማድረግና የተለዩ ችግሮችን በመለየት በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንዲቻል ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ በመግለፅ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኮሌጅ ኮምኒኬሽን
ህዳር 10/2017 ዓ.ም
"ሀገራዊ መግባባት
ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት!"
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከበሩ።
በዓሉ በፓናል ውይይት የተከበረ ሲሆን፣ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበር መሆኑን አውስተው፣ ሀገራዊ መግባባትን ለማጽናት ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ ጥያቄዎችን በሰላማዊ አግባብ የሚያስተናግድ ሥርዓት መገንባትና የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ከዳር ደርሶ አንድነታችንን እንዲያጠናክር ቀዳሚ የመንግሥት ትኩረት እንደሆነ ተናግረዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 6/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
የISO 9001:2015 QMS የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተሸላሚ::
