cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
766
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-57 روز
-830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

. 🔥 አባ ጳኩሚስ ❤ ግንቦት 14 የአንድነት ማኅበርን የመሠረተ፣ በአባ መቃርስ እጅ ከመነኮሰ በኋላ እነ አረጋዊን ያመነኮሰውና ገዳማዊ ኑሮንና ምንኩስናን ያስፋፋው ወንድና ሴት መነኮሳትም ፊት ለፊት እንዳይተያዩ ብሎ ሕግ የሠራ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዐረፈ፡፡ እርሱም በአዳም መቃብር ላይ 60 ዓመት ቆሞ የጸለየ ሲሆን በአንዲት ሴት ላይ አድረው የነበሩትን 100 አጋንንት በጸሎት ወደ እርሱ እንዲገለበጡና በእርሱ ላይ እንዲያድሩ አድርጎ በጾም ጸሎት ስግደት ያቃጠላቸው ነው፡፡ አባ ጳኩሚስ ግብፅ ውስጥ ኤስና በምትባል መንደር ከአረማውያን ቤተሰቦች በ290 ዓ.ም ተወለደ፡፡ በቆስጠንጢኖስ ዘመነ መንግሥት ለውትድርናም ተመልምሎ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በውትድርናው ዘመን የክርስቲያኖችን ቆራጥነት፣ ደግነትና ርኀራኄ በማየቱ ልቡ ስለተነካ ግዳጁን ፈጽሞ ሲመለስ በ313 ዓ.ም የክርስትናን እምነት ጠንቅቆ በመማር አምኖ ተጠመቀ፡፡ የአባ ጳኩሚስ ልቡና የቅዱስ እንጦንስ ደቀ መዝሙር በነበረው በአባ ጴላጦንስ ኑሮ ስለተማረከ ወደ በረሃ ወርዶ የብሕትውናን ኑሮና ሥርዓት ሲማር ከቆየ በኋላ በ320 ዓ.ም በዓባይ ወንዝ አጠገብ ታቤኒስ ከተባለው ቦታ የራሱን ገዳም መሠረተ፡፡ ይኽም ታላቅ አባት ከአባ ጰላሞን ዘንድ መንኩሶ ሲያገለግለው ኖረ፡፡ የምንኩስናንም ሥራ እየሠራ ብዙ ዘመናት ኖረ፡፡ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጦለት እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት የአንድነትን ማኅበር ለመሥራት መነኮሳትን እንዲሰበስብ አዘዘው፡፡ በታዘዘውም መሠረት ብዙዎች መነኮሳትን ሰብስቦ በየቦታው ብዙ ገዳማትን ገደመላቸው፡፡ ርዕሰ መነኮሳት የሆኑት አቡነ እንጦንስ በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ምንኩስናን ከሊቀ መልአኩ ከቅዱስ ሚካኤል እጅ ተቀበሉ፡፡ እንጦንስም ታላቁ መቃርስን አመነኮሷቸው፤ ታላቁ መቃርስም ጳኩሚስን አመነኮሷቸው፤ አባ ጳኩሚስም አባ ቴዎድሮስ አመነኮሷቸው፤ አባ ቴዎድሮስም አቡነ አረጋዊን አመነኮሷቸው፡፡ አቡነ አረጋዊ ክርስቶስ ቤዛነን፣ ክርስቶስ ቤዛነ መስቀል ሞዐን፣ መስቀል ሞዐ ዮሐኒን፣ ዮሐኒ ኢየሱስ ሞዐንና ተክለ ሃይማኖትን (በቆብና በአስኬማ)፣ ኢየሱስ ሞዐ ተክለ ሃይማኖትን (በቅናትና በቀሚስ)፣ ተክለ ሃይማኖት ኢየሱስ ሞዐን (በቆብና በአስኬማ) ወልደዋል፡፡ አባ ጳኩሚስ መጀመሪያ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣው በታላቁ አባ ጰላሞን አማካኝነት ነው፡፡ ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሄድ ከአባ ጰላሞን ተለይቶ ማሕበር መሥርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል፡፡ ቅዱስ አባ ጳኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር፡፡ አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ በጾም በጸሎት ይጋደል ነበር፡፡ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል፡፡ እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር፡፡ ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ ጳኩሚስ እንደወትሮው ሲሰግድ ወዙ ወርዶ መሬቱን ጭቃ አደረገው፣ ወዲያው ጌታችን ተገለጸለትና ጳኩሚስ ‹‹አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹እኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሆኜ ተሰቅያለሁ›› ብሎ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ ሆኖ ጐኑን እንደተወጋ ደሙ እንደፈሰሰ ሆኖ ታይቶታል፡፡ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባ ጳኩሚስ በበረሃ ሳለ መልአክ መጥቶ በነሐስ የተጻፈ ሕግ ሰጠው፤ እርሱም በዚህ የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳትን አዘጋጅቷዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር፡፡ አባታችን ቅዱስ ጳኩሚስ ከርሕራሔው የተነሣ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያደርግ ነበር፡፡ ከዚያም በጾም በጸሎትና በስግደት መድረሻ ያሳጣቸዋል፡፡ ያንጊዜ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ አባ ጳኩሚስ ‹‹ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ›› እያለ ይቀጣጠብባቸዋል፡፡ አንድ ዕለት ቅዱስ አባ ጳኩሚስ አንዲት ሴት ብዙ አጋንንት ሰፍረውባት ስትሠቃይ አየና ‹‹አቤቱ ጌታዬ ሆይ! ይህን ሁሉ እንዴት ትችለዋለች?›› ብሎ በእርሷ ላይ ያለውን የአጋንንት መንጋ ወደ እርሱ እንዲገለበጥ ፈጣሪውን በጸሎት ጠየቀ፡፡ በዚያም ጊዜ በአንድ ቀፎ ውስጥ ያሉ ንቦች ወደ ሌላ ቀፎ እንደሚገለበጡ እነዚያ በሴትዮዋ ላይ አድረው የነበሩ አጋንንት በሙሉ ከዚያች ሴትዮ ወጥተው በአባ ጳጉሚስ ላይ ሰፈሩ፡፡ እርሱም ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ በሥግደት በጾምና በጸሎት አሠቃያቸው፡፡ አጋንንቱም የአባ ጳኩሚስን ትሩፋትና ተጋድሎ መቋቋም ስላልቻሉ አጋንንቱ ‹‹እንሂድ እንጂ እንግዲህማ ከዚህ ምን እናደርጋለን›› ሲሉ ሰማቸው፡፡ ቅዱስ ጳኩሚስም ‹‹ለምን አትቆዩም ሰው እንዲህ ካለ ኃጥእ ወዳጁ ቤትኮ ጥቂት ጊዜ ያርፋል›› ቢላቸው ‹‹እኛስ ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ያለ ሰው አላየንም፣ ትሩፋቱ አቃጠለን ሊያስቀምጠን አልቻለም›› ብለው መስክረውለት ወጥተው ሄዱ፡፡ አባ ጳኩሚስን ስለ ክብሩ መልአክ ነጥቆ ወስዶ ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ በኋላ ወደ ምድር መልሶታል፡፡ ከዚህም በኋላ ጻድቁ በዙሪያው ለተሰበሰቡት መነኰሳት የአንድነት ኑሮ ሕግ አወጣላቸው፡፡ ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ጳኩሚስን ያህል የደከመና የተሳካለት ግን የለም፡፡ በአባ እንጦንስ የተጀመረውን የመነኰሳትን የማኅበር ኑሮ አባ ጳኩሚስ በተጠናከረ መልኩ ሥርዓት አውጥቶ የበለጠ ከማስፋፋቱም በተጨማሪ ዘጠኝ የወንዶችና ሁለት የሴቶች ገዳማት መሥርቷል፡፡ አባ ጳኩሚስ ያወጣው የመነኰሳት የአኗኗር ሕግ ዋናው ቅጂ ሲጠፋ ወደ ላቲን የተተረጐመው ግን እስከዛሬ ድረስ ይገኛል፡፡ ከሕግጋቱ መካከል፡- መነኮሳት ጠዋትና ማታ በማኅበር እንዲጸልዩ፣ በኅብረት በአንድነት እንዲሠሩ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትረው እንዲመለከቱ፣ መነኮሳት ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል፣ መነኮሳት የቁም ጽሕፈት እንዲማሩ፣ ገቢና ወጫቸው አንድ ላይ እንዲሆን፣ በአንድነት እንዲመገቡ፣ አንድ ዓይነት ልብስ እንዲኖራቸው፣ ንጽሕናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ፣ ከገዳማቸው በፍጹም እንዳይወጡ ከልክሏል፣ የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል፣ መነኮሳት ደግነት፣ ፍቅርና ታዛዥነት እንዲኖራቸው የሚሉትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ ወደ ላዕላይ ግብጽ በወጣ ጊዜ ይህን አባት ጳኩሚስን ቅስና ሊሾመው ወደደ፡፡ ከእርሱም ሸሸ፡፡ እጅግ የከበረ አትናቴዎስም ልጆቹን ‹‹‹የማይናወጽ ቤትን የሠራህ ቅዱስ ሆይ! ከከንቱ ውዳሴ የራቅህ አንተ ብፁዕ ነህ፣ ልጆችህም ብፁዓን ናቸው› ብሎሃል በሉት አባታችሁን›› አላቸው፡፡ ይኽም ቅዱስ አባት አንድ ጊዜ ሲኦልን ያዩ ዘንድ ወደዱ፡፡ እነሆም የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወስዶ በገነት የጻድቃንን ማደሪያ እንዲሁም በሲኦል የሥቃይን ቦታዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡
نمایش همه...
ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

አባ ጳኩሚስ ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን አስፋፍቷል፣ ብዙ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ ቅዱስ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ አንድ ሰው ወደ ገዳማቱ ሲመጣ የሦስት ዓመት አመክሮ ይሰጠውና ጠባዩና ፍላጐቱ ይገመገማል፡፡ ከዚያ በኋላም ብርታቱና ጽናቱ ታይቶ ወደ ማኅበረ መነኰሳቱ ይቀላቀላል፡፡ አባ ጳኩሚስ በዚሁ ዓይነት መንገድ ሥርዓት ሠርተው ሕግ አጽንተው ገዳማትን ካስፋፉና አበምኔት ሁነው 40 ዓመት ካገለገሉ በኋላ ከጌታችን ቃልኪዳን ተቀብለው ለደቀ መዛሙርቶቻቸው ቅዱስ ቴዎድሮስ ሹመውላቸው በተወለዱ በ56 ዓመታቸው በ346 ዓ.ም በሰላም ዐርፈው ቅድስት ነፍሳቸውን ጌታችን በክብር ተቀብሏታል፡፡ የአባ ጳኩሚስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 1️⃣4️⃣ ቀን ስንክሳር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ Tᴇʟᴇɢʀᴀᴍ - https://t.me/Synaxarium
نمایش همه...
ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

አቡነ ያሳይ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ተጉለት ነው፡፡ አባታቸው ንጉሡ ዓምደ ጽዮን ቀዳማዊ ነው፡፡ ይኸውም ከ1296-1326 ዓ.ም የነበረው ነው፡፡ አቡነ ያሳይ በልጅነታቸው በንጉሡ አባታቸው ቤት ሲኖሩ የገዳማ መነኮሳት ለመንፈሳዊ ሥራ ወደ ንጉሡ ዘንድ እየመጡ ደጅ ሲጠኑ ያዩአቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ገና በልጅነታቸው የመነኮሳቱን እግር ያጥቡ ስለነበር በዚሁ አጋጣሚ መነኮሳቱን ስለምንኩስና ሕይወት ይጠይቋቸው ነበር፡፡ መነኮሳቱም ሕይወታቸውን ያስረዷቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም ብሉያትንና ሐዲሳትን ከልጅነታቸው ጀምሮ የተማሩ ስለነበር የአባቶችን ትምህርትና የወንጌልን ቃል በማገናዘብ የፈጣሪያቸው ፍቅር በልቡናቸው እንደ እሳት ነደደ፡፡ ይልቁንም ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› የሚለውን የጌታችንን ቃል አሰቡ፡፡ ማቴ 16፡26፡፡ ከዚህም በኋላ የንጉሡ አባታቸውን የአልጋ ወራሽነት ማለትም የንጉሥነትን ክብር ፈጽመው በመናቅ ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› (ማቴ 16፡27) ያለውን የጌታችንን ቃል አስበው ንጉሣውያን ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ለምነና ወጡ፡፡ ለምነና እንደወጡም ከሸዋ ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር በአክሱም አቅራቢያ ከሚገኘው ገዳም ደብረ በንኮል ከሚባለው ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደረሱ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም አቡነ ያሳይ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረባቸው ሰው መሆናቸውንና ወደ እርሳቸውም እየመጡ መሆኑን በመንፈስ ዐውቀውት ስለነበር በደስታ ተቀበሏቸውና በረድእነት ከወንድሞቻቸው ጋር ጨመሯቸው፡፡ አቡነ ያሳይም የገዳም መነኮሳትን በማገልገል በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብዙ ደከሙ፡፡ በደብረ በንኮል ገዳምም ብዙ እገራሚ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ወደ መካነ ገድላቸው በጣና አካባቢ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ቀደም ብለን የጠራናቸውን ‹‹ሰባቱን ከዋክብት›› ምግባር ሃይማኖታቸውን፣ ተጋድሎ ትሩፋታቸውንና ገቢረ ተአምራታቸውን አይተው ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው በአንድ ቢያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰባቱ ቅዱሳን ውስጥ ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ሆነው ከደብረ በንኮል ገዳም አባታቸውን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ተሰናብተው ወደ ጣና ደሴት መጥተዋል፡፡ አቡነ ያሳይ በ13ኛው መ/ክ/ዘመን በአባታቸው የዘመነ ንግሥና መጨረሻ ወደ አርባ ምንጭ ሄደው ከዚያው ሱባኤ ገብተው ፈጣሪያቸውንነ ቢማጸኑ እግዚአብሔርም ከዚያው አካባቢ የሚኖር አንድ ባሕታዊን የመድኃነዓለምን ጽላት እንዲወጣቸው አዘዘላቸው፡፡ እርሳቸውም ጽላቱን ተቀብለው በጎጃም በኩል አድርገው ወደ ጣና ተመልሰው በዘጌ አከባቢ ሲደረሱ ከጣና ባሕር ዳር ቆመው በየብስ ያለውን ርቀትና በባሕሩ ያለውን ቅርበት አይተው አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው በጸሎት ተማጸኑ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ አትጨነቅ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ ከጎንህ ያለውን ድንጋይ በባሕሩ ላይ ጫነው፤ ድንጋዩም ለልጅ ልጅ እኔ ዓለምን ለማሳለፍ እስከምመጣበት ሰዓት ድረስ መታሰቢያ ትሁንህ›› አላቸውና ተሰወረ፡፡ አቡነ ያሳይም የመድኃኔዓለምን ጽላት ይዘው በድንጋዩ ላይ እንደተቀመጡ ድንጋዩ እንደታንኳ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ፡፡ ባሕሩም ከማዕበሉ ብዛት የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡ አባታችንም ያለ ምንም ቀዘፋ ልብሳቸውም ውኃ ሳይነካው ቁጭ እንዳሉ ማን እንደአባ ወደ ተባለው ቦታቸው ደረሱ፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ያሳይ ገዳማቸውን ገድመው ወንድሞቻቸውን ሰብስበው በተጋድሎ በመኖር ብዙ ቅዱሳንን አፍርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የጌታችንን እግር ያጠቡት አቡነ አብሳዲ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዝናብንና ነፋስን የከለከሉት አቡነ ያዕቆብ፣ እሬትን እንደ ማር ያጣፈጡት አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተሞሉት አቡነ ዳንኤል፣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ጥበብን የተሞሉት አቡነ ፊቅጦርና ሌሎችም ብዙዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱም ብዙ የበቁ ቅዱሳን በአካባቢው ነበሩ፡፡ በአጽፋቸውና በእግራቸው በባሕሩ ላይ የሚሄዱ ነበሩ፣ በጸጋ ክንፍ ተሰጥቷቸውም የሚበሩ ነበሩ፡፡ የአቡነ ያሳይ ተአምራቶቻቸው ተነግረው አያልቁም፡፡ በወቅቱ የነበሩት ቅዱሳን ልጆቻቸው ‹‹ከቅዱሳን ማን እንደ አባ ያሳይ በከባድ ድንጋይ ላይ ተጭኖ በባሕር ላይ የተጓዘ አለና..›› ብለው ይገረሙባቸው ነበር፡፡ ቦታቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ማን እንደ አባ›› ተባለ፡፡ ይህም የአቡነ ያሳይ ገዳም በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በደንቢያ ወረዳ በጎርጎራ ጣና ሐይቅ አካባቢ ይገኛል፡፡ በጣና ደሴት ላይ ከሚገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ነው፡፡ ይህም ዋሻ ታሪኩ ከአቡነ ያሳይ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፡- አትማረኝ ዋሻ በጣና ሐይቅ ደሴቶች መካከል ከሚገኙ ገዳማት መካከል ከማን እንደ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንድ ተራራ ሥር የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡ ይህ ዋሻ ለብዙ ዘመናት አንድ ታላቅ አባት የጸሎት በዓት አድርገውት ‹‹አትማረኝ›› እያሉ የጸለዩበት ቦታ ነው፡፡ አቡነ ያሳይ ወደ ጣና ደሴት ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጋር በመሆን በጸሎት ይተጉ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ በጣና ሐይቅ ላይ እንደ ጀልባ የሚጓዙበት አንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ፣ አትማረኝ፣ አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው ‹‹አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?›› አሏቸው፡፡ ያም አባት ‹‹አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው ‹አትማረኝ› እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው›› በማለት መለሱላቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ‹‹እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው ‹ማረኝ› እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው ይሄዳሉ፡፡ ‹‹አትማረኝ›› እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም ‹‹ማረኝ›› እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ቀሩና ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ወደ ሐይቁ ሲመለከቱም አቡነ ያሳይ ድንጋዩን እንደጀልባ ተጠቅመው እየሄዱ ነው፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸው ያ አባት በውኃ ላይ በእግራቸው እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡ ከኋላቸውም ሆነው ‹‹አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፤ እባክዎን እንደገና ያስተምሩኝ›› አሏቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ሐይቁን በእግራቸው እረገጡ እስኪሄዱ ድረስ ጽድቃቸው የተገለጠውን የእኚህን አባት መብቃት ተመልከተው ‹‹አባቴ እግዚአብሔር የልብ ነውና የሚመለከተው እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል›› ብለዋቸው ሔዱ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ የአቡነ ያሳይ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 ሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ
نمایش همه...
ይኽም ቅዱስ አባት አንድ ጊዜ ሲኦልን ያዩ ዘንድ ወደዱ፡፡ እነሆም የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወስዶ በገነት የጻድቃንን ማደሪያ እንዲሁም በሲኦል የሥቃይን ቦታዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡ አባ ጳኩሚስ ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን አስፋፍቷል፣ ብዙ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ ቅዱስ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ አንድ ሰው ወደ ገዳማቱ ሲመጣ የሦስት ዓመት አመክሮ ይሰጠውና ጠባዩና ፍላጐቱ ይገመገማል፡፡ ከዚያ በኋላም ብርታቱና ጽናቱ ታይቶ ወደ ማኅበረ መነኰሳቱ ይቀላቀላል፡፡ አባ ጳኩሚስ በዚሁ ዓይነት መንገድ ሥርዓት ሠርተው ሕግ አጽንተው ገዳማትን ካስፋፉና አበምኔት ሁነው 40 ዓመት ካገለገሉ በኋላ ከጌታችን ቃልኪዳን ተቀብለው ለደቀ መዛሙርቶቻቸው ቅዱስ ቴዎድሮስ ሹመውላቸው በተወለዱ በ56 ዓመታቸው በ346 ዓ.ም በሰላም ዐርፈው ቅድስት ነፍሳቸውን ጌታችን በክብር ተቀብሏታል፡፡ የአባ ጳኩሚስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 አባ ሲማኮስ ይኽም ቅዱስ ከሀገረ ፈርማ የተገኘ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡ ወዳጆን ሁሉ በሃይማኖት ጸንቶ ስለመኖር ያስተምራቸው ነበር፡፡ ቡላሚስ የሚባለው ከሃዲ መኮንን ክርስቲያኖችን ሊያሠቃይና ሊገድል እንደመጣ በሰማ ጊዜ አባ ሲማኮስ ሰማዕት ይሆን ዘንድ ወደደና ቤተሰቦቹን ተሰናብቶ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ወጣ፡፡ ወደ ሀገረ ድሜራ ቅርብ ወደሆነ ወደ ሀገረ በክሩዝ ሄዶ ከሃዲውን መኮንን አገኘው፡፡ እርሱም አንዲቷን ሰማዕት ይዞ ሲያሠቃያትና ወደ እሳቱ ምድጃ ሲጨምራት እሳቱም በተአምራት ሲቀዘቅስ ተመለከተ፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ሲማኮስ በፊቱ ቆሞ የጌታችንን ክብር መሰከረ፡፡ መኮንኑም አባ ሲማኮስን ይዞ ብዙ አሠቃየው፡፡ በዚህ ጊዜም አባ ሲማኮስ ዕድሜው 20 ዓመት ነበር፡፡ በመጀመሪያ ሰቀሉት፤ ቀጥለውም ከመንኮራኩር ውስጥ ጨምረው አበራዩት፡፡ ከእርሱም ብዙ ደም ፈሰሰ፡፡ አንዲትም ዐይኗ ሥውር የነበረች ሴት ደሙ ፈሶ ዐይኗን በነካት ጊዜ ዐይኗ ዳነ፡፡ ከዚኽም በኋላ ደግመው በእንጨት ላይ ሰቅለው አሠቃየው፡፡ በሥቃይም ላይ ሆኖ ወደ ጌታችን በለመነ ጊዜ አዳነው፡፡ መኮንኑም የአባ ሲማኮስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ሰያፊውም ይቆርጠው ዘንድ ሰይፉን መዘዘ ነገር ግን ኃይል ተነሥቶት ማነቀሳቀስ አቃተው፡፡ እንዲሁም ሁለተኛው፣ ሦስተኛው … እስከ ዐሥራ አራት ሰይፈኞች ኃይላቸው ደከመ፡፡ እነርሱም በምድር ላይ ወደቁ፡፡ ከዚህም በኋላ በአንገቱ ገመድ አስገብተው እስከ ረጅም ተራራ አናት ድረስ ጎተቱት፡፡ ነፍሱንም በክብር ባለቤት በጌታችን እጅ አሳልፎ ሰጥቶ የምስክርነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ከወታደሮቹም ውስጥ ዲዳና ደንቆሮ የነበረ የቅዱሱን ሥጋ ባየጊዜ ጆሮዎቹ ሰሙ፣ አንደበቱም መናገር ጀመረ፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ብዙ አረማውያንም የቅዱስ አባ ሲማኮስን ተአምራት አይተው በጌታችን አምነው ተጠመቁ፡፡ የጌታችንንም ክብር መስከረው በሰማዕት ዐረፉ፡፡ ቁጥራቸውም አንድ ሺህ ሰባት መቶ ኃምሳ (1750) ሆነ፡፡ የአባ ሲማኮስና የማኅበርተኞቹ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ 🔥 አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ አቡነ ያሳይ ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ከሚባሉት የሀገራችን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ እነዚህም ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› የተባሉት አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ ናቸው፡፡ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ አስተምረውና አመንኩሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኮሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኮሷቸው መነኮሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ‹‹ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን›› በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት፡፡ አቡነ መድኃኒነ እነዚህንም ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ላይ የመነኮሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ባሕሩን በእግራቸውም እየረገጡ ጠቅጥቀው የተሻገሩ አሉ፤ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፤ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ አንዱ ዛሬ በዓላታቸውን የምናከብራለቸው አቡነ ያሳይ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› (መዝ 67፡35) ብሎ እንደተናገረ ጻድቁ አቡነ ያሳይ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ ጣና ሐይቅን የሚያቋርጡት በአንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነበር፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ከአቡነ ሳሙኤል ጋር አብረው ወደዚህ ቦታ መጡ፡፡ ከዚያም የቦታው አቀማመጥ የብስ መሬትና ደሴት መሆኑን አይተው ‹‹እግዚአብሔር ፈቅዶ ይችን ደሴት የጸሎት ቦታችን አድርጎ ቢሰጠን በጸሎት እንጠይቀው›› ተባብለው ሁሉቱም ቅዱሳን ሱባኤ ገቡ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንም ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ተገሃድ ተልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ይህ ቦታ የአንተ አይደለም የወንድምህ የያሳይ ቦታ ነው፡፡ እኔ ወዳዘጋጀሁልህ ቦታ ወደ ዋሊ ሂድ›› ብሎ የዋልድባን ምድር አሳያቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም የጌታችንን ትእዛዝ ተቀብለው ወንድማቸውን አቡነ ያሳይን ተሰናብተው ወደ ዋልድባ ሄደው ገዳማቸውን አቅንተው ተጋድሎቸአውን በዚያ ፈጸሙ፡፡ ጌታችን ዳግመኛም ለአቡነ ያሳይ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ የአባትህን መንግሥትና የዓለሙን ክብር ከምኞቱ ጋር ለእኔ ብለህ ስለተውክ ይህንኑ ቦታ በዚህ ዓለም ሳለህ ለአንተ፣ ወደ ዘላለማዊ መንግሥቴ ከወሰድኩህ በኋላም ለልጆችህ ምንዳህ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፤ ምሕረቴንም በቦታህ አዘንባለሁ ቸርነቴም አይለያትም፣ ብዙ የመንፈስ ልጆችንም ታፈራለህ፤ ቦታህም እኔ ለፍርድ እስክመጣ ድረስ ትኖራለች›› በማለት ቃልኪዳኑን አቆመላቸውና ተሰወራቸው፡፡ ‹‹ምንዳህ›› ማለት ደመወዝ ማለት ነውና በዚህም ‹‹ማንዳባ›› ማለት ‹‹የአቡነ ያሳይ ምንዳ-ደመወዝ›› ማለት ነው ሲሉ አባቶች ገዳሙን ‹‹ማንዳባ-ምን እንደ አባ›› ብለው ሰየሙት፡፡
نمایش همه...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 14 ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ የተሻገሩት የአቡነ ያሳይ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡ ➛ ሙሽራው ቅዱስ ገብረክርስቶስ ከጫጉላ ቤቱ ወጥቶ የመነነበት ዕለት ነው፡፡ ➛ የአንድነት ማኅበርን የመሠረተ፣ በአባ መቃርስ እጅ ከመነኮሰ በኋላ እነ አረጋዊን ያመነኮሰውና ገዳማዊ ኑሮንና ምንኩስናን ያስፋፋው ወንድና ሴት መነኮሳትም ፊት ለፊት እንዳይተያዩ ብሎ ሕግ የሠራ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዐረፈ፡፡ እርሱም በአዳም መቃብር ላይ 60 ዓመት ቆሞ የጸለየ ሲሆን በአንዲት ሴት ላይ አድረው የነበሩትን 100 አጋንንት በጸሎት ወደ እርሱ እንዲገለበጡና በእርሱ ላይ እንዲያድሩ አድርጎ በጾም ጸሎት ስግደት ያቃጠላቸው ነው፡፡ ➛ ከሀገረ ፈርማ የተገኙት አባ ሲማኮስ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ 🔥 አባ ጳኩሚስ አባ ጳኩሚስ ግብፅ ውስጥ ኤስና በምትባል መንደር ከአረማውያን ቤተሰቦች በ290 ዓ.ም ተወለደ፡፡ በቆስጠንጢኖስ ዘመነ መንግሥት ለውትድርናም ተመልምሎ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በውትድርናው ዘመን የክርስቲያኖችን ቆራጥነት፣ ደግነትና ርኀራኄ በማየቱ ልቡ ስለተነካ ግዳጁን ፈጽሞ ሲመለስ በ313 ዓ.ም የክርስትናን እምነት ጠንቅቆ በመማር አምኖ ተጠመቀ፡፡ የአባ ጳኩሚስ ልቡና የቅዱስ እንጦንስ ደቀ መዝሙር በነበረው በአባ ጴላጦንስ ኑሮ ስለተማረከ ወደ በረሃ ወርዶ የብሕትውናን ኑሮና ሥርዓት ሲማር ከቆየ በኋላ በ320 ዓ.ም በዓባይ ወንዝ አጠገብ ታቤኒስ ከተባለው ቦታ የራሱን ገዳም መሠረተ፡፡ ይኽም ታላቅ አባት ከአባ ጰላሞን ዘንድ መንኩሶ ሲያገለግለው ኖረ፡፡ የምንኩስናንም ሥራ እየሠራ ብዙ ዘመናት ኖረ፡፡ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጦለት እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት የአንድነትን ማኅበር ለመሥራት መነኮሳትን እንዲሰበስብ አዘዘው፡፡ በታዘዘውም መሠረት ብዙዎች መነኮሳትን ሰብስቦ በየቦታው ብዙ ገዳማትን ገደመላቸው፡፡ ርዕሰ መነኮሳት የሆኑት አቡነ እንጦንስ በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ምንኩስናን ከሊቀ መልአኩ ከቅዱስ ሚካኤል እጅ ተቀበሉ፡፡ እንጦንስም ታላቁ መቃርስን አመነኮሷቸው፤ ታላቁ መቃርስም ጳኩሚስን አመነኮሷቸው፤ አባ ጳኩሚስም አባ ቴዎድሮስ አመነኮሷቸው፤ አባ ቴዎድሮስም አቡነ አረጋዊን አመለኮሷቸው፡፡ አቡነ አረጋዊ ክርስቶስ ቤዛነን፣ ክርስቶስ ቤዛነ መስቀል ሞዐን፣ መስቀል ሞዐ ዮሐኒን፣ ዮሐኒ ኢየሱስ ሞዐንና ተክለ ሃይማኖትን (በቆብና በአስኬማ)፣ ኢየሱስ ሞዐ ተክለ ሃይማኖትን (በቅናትና በቀሚስ)፣ ተክለ ሃይማኖት ኢየሱስ ሞዐን (በቆብና በአስኬማ) ወልደዋል፡፡ አባ ጳኩሚስ መጀመሪያ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣው በታላቁ አባ ጰላሞን አማካኝነት ነው፡፡ ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሄድ ከአባ ጰላሞን ተለይቶ ማሕበር መሥርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል፡፡ ቅዱስ አባ ጳኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር፡፡ አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ በጾም በጸሎት ይጋደል ነበር፡፡ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል፡፡ እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር፡፡ ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ ጳኩሚስ እንደወትሮው ሲሰግድ ወዙ ወርዶ መሬቱን ጭቃ አደረገው፣ ወዲያው ጌታችን ተገለጸለትና ጳኩሚስ ‹‹አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹እኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሆኜ ተሰቅያለሁ›› ብሎ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ ሆኖ ጐኑን እንደተወጋ ደሙ እንደፈሰሰ ሆኖ ታይቶታል፡፡ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባ ጳኩሚስ በበረሃ ሳለ መልአክ መጥቶ በነሐስ የተጻፈ ሕግ ሰጠው፤ እርሱም በዚህ የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳትን አዘጋጅቷዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር፡፡ አባታችን ቅዱስ ጳኩሚስ ከርሕራሔው የተነሣ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያደርግ ነበር፡፡ ከዚያም በጾም በጸሎትና በስግደት መድረሻ ያሳጣቸዋል፡፡ ያንጊዜ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ አባ ጳኩሚስ ‹‹ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ›› እያለ ይቀጣጠብባቸዋል፡፡ አንድ ዕለት ቅዱስ አባ ጳኩሚስ አንዲት ሴት ብዙ አጋንንት ሰፍረውባት ስትሠቃይ አየና ‹‹አቤቱ ጌታዬ ሆይ! ይህን ሁሉ እንዴት ትችለዋለች?›› ብሎ በእርሷ ላይ ያለውን የአጋንንት መንጋ ወደ እርሱ እንዲገለበጥ ፈጣሪውን በጸሎት ጠየቀ፡፡ በዚያም ጊዜ በአንድ ቀፎ ውስጥ ያሉ ንቦች ወደ ሌላ ቀፎ እንደሚገለበጡ እነዚያ በሴትዮዋ ላይ አድረው የነበሩ አጋንንት በሙሉ ከዚያች ሴትዮ ወጥተው በአባ ጳጉሚስ ላይ ሰፈሩ፡፡ እርሱም ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ በሥግደት በጾምና በጸሎት አሠቃያቸው፡፡ አጋንንቱም የአባ ጳኩሚስን ትሩፋትና ተጋድሎ መቋቋም ስላልቻሉ አጋንንቱ ‹‹እንሂድ እንጂ እንግዲህማ ከዚህ ምን እናደርጋለን›› ሲሉ ሰማቸው፡፡ ቅዱስ ጳኩሚስም ‹‹ለምን አትቆዩም ሰው እንዲህ ካለ ኃጥእ ወዳጁ ቤትኮ ጥቂት ጊዜ ያርፋል›› ቢላቸው ‹‹እኛስ ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ያለ ሰው አላየንም፣ ትሩፋቱ አቃጠለን ሊያስቀምጠን አልቻለም›› ብለው መስክረውለት ወጥተው ሄዱ፡፡ አባ ጳኩሚስን ስለ ክብሩ መልአክ ነጥቆ ወስዶ ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ በኋላ ወደ ምድር መልሶታል፡፡ ከዚህም በኋላ ጻድቁ በዙሪያው ለተሰበሰቡት መነኰሳት የአንድነት ኑሮ ሕግ አወጣላቸው፡፡ ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ጳኩሚስን ያህል የደከመና የተሳካለት ግን የለም፡፡ በአባ እንጦንስ የተጀመረውን የመነኰሳትን የማኅበር ኑሮ አባ ጳኩሚስ በተጠናከረ መልኩ ሥርዓት አውጥቶ የበለጠ ከማስፋፋቱም በተጨማሪ ዘጠኝ የወንዶችና ሁለት የሴቶች ገዳማት መሥርቷል፡፡ አባ ጳኩሚስ ያወጣው የመነኰሳት የአኗኗር ሕግ ዋናው ቅጂ ሲጠፋ ወደ ላቲን የተተረጐመው ግን እስከዛሬ ድረስ ይገኛል፡፡ ከሕግጋቱ መካከል፡- መነኮሳት ጠዋትና ማታ በማኅበር እንዲጸልዩ፣ በኅብረት በአንድነት እንዲሠሩ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትረው እንዲመለከቱ፣ መነኮሳት ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል፣ መነኮሳት የቁም ጽሕፈት እንዲማሩ፣ ገቢና ወጫቸው አንድ ላይ እንዲሆን፣ በአንድነት እንዲመገቡ፣ አንድ ዓይነት ልብስ እንዲኖራቸው፣ ንጽሕናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ፣ ከገዳማቸው በፍጹም እንዳይወጡ ከልክሏል፣ የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል፣ መነኮሳት ደግነት፣ ፍቅርና ታዛዥነት እንዲኖራቸው የሚሉትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ ወደ ላዕላይ ግብጽ በወጣ ጊዜ ይህን አባት ጳኩሚስን ቅስና ሊሾመው ወደደ፡፡ ከእርሱም ሸሸ፡፡ እጅግ የከበረ አትናቴዎስም ልጆቹን ‹‹‹የማይናወጽ ቤትን የሠራህ ቅዱስ ሆይ! ከከንቱ ውዳሴ የራቅህ አንተ ብፁዕ ነህ፣ ልጆችህም ብፁዓን ናቸው› ብሎሃል በሉት አባታችሁን›› አላቸው፡፡
نمایش همه...
ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ወላጅ አባቱ የቍስጥንጥንያው ንጉሥ ቴዎዶስዮስና እናቱ ንግሥት መርኬዛ በስለት ያገኙት ብቸኛ ልጃቸው ስለሆነ ሃይማኖትን እያስተማሩት በምግባር በእጅጉ ተንከባክበው አሳድገውታል፡፡ የአባቱን ንግሥና በመውረስ ቍስጥንጥንያን እንዲገዛላቸው በመፈለግ ወላጆቹ ለአካለ መጠን ሲደርስ የሮሙን ንጉሥ ሴት ልጅ አጋቡት፡፡ እርሱ ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም የተዘጋጀ ነበርና የሠርጉ ዕለት ሌሊት የእርሱንም ሆነ የሙሽይቱን ድንግልና እንደጠበቀ ከጫጉላ ቤት ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ሩቅ ሀገር በመሄድ በቤተክርስቲያን ተቀምጦ ከነዳያን ጋር ተደባልቆ በመለመን ለምኖ ያገኘውንም ለሌሎች እየመጸወተ በጾም በጸሎት ተጠምዶ 15 ዓመት ኖረ፡፡ እመቤታችን ተገልጻ ለአንድ የቤተክርስቲያኑ አገልጋይ የገብረ ክርስቶስን ጽድቅ ብትነግረው ምሥጢሩን ለሀገሩ ሁሉ አዳረሰበት፡፡ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስም ‹‹ግብሬ ታወቀ፣ ከዚህ ውዳሴ ከንቱ ልሽሽ›› በማለት ወደሌላ ሀገር በመርከብ ሲጓዝ ፈቃደ እግዚአብሔር መርከቢቱን ያለ አቅጣጫዋ ወስዶ አባቱ ደጅ አደረሰው፡፡ ማንነቱን እንደደበቀና ዓለምን ምን ያህል እንደናቃት ይረዳ ዘንድ በአባቱና በንጉሡ ደጅ የኔ ቢጤ ለማኝ ሆኖ ለአባቱ ውሾች የሚሰጠውን ፍርፋሪ እየተመገበ አሁንም 15 ዓመት ሙሉ በትዕግስት ተቀመጠ፡፡ የአባቱ አሽከሮች እንኳን እጣቢና ቆሻሻውን ሁሉ እየደፉበት ሲያሠቃዩት የአባቱ ውሾች ግን የእግሩን ቁስል ይልሱለት ነበር፡፡ በአጠቃላይ ገብረ ክርስቶስ እጅግ የተከበረ የታላቅ ንጉሥ ልጅ ሲሆን ነገር ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ ስለ ጽድቅ ተሰዶ እየለመነ ያገኘውን እየመጸወተ በጾም በጸሎት እየተጋደለ 30 ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፡፡ በመጨረሻም ጌታችን እመቤታችንን፣ ቅዱሳን መላእክትን ሁሉ፣ ከገብረ ክርስቶስ በፊት የነበሩ ነቢያትን ሁሉ፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ቃልኪዳን ከገባለት በኋላ ከጌታችን ጋር አብረውት የመጡት ሁሉ በታላቅ ክብርና ምስጋና እያመሰገኑት ጌታችን ክብርት ነፍሱን በእቅፉ ተቀብሎ አሳርጓታል፡፡ የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ በቅዳሴ ላይ ሳሉ ከንጉሡ ቤት ሄደው የገብረ ክርስቶስን ሥጋ እንዲያመጡ የእግዚአብሔር ድምፅ ከሰማይ በትእዛዝ መጣላቸውና ሄደው ቢያዩ የገብረ ክርስቶስን ሥጋ በንጉሥ አባቱ ደጅ ወድቆ አገኙት፡፡ በገብረ ክርስቶስም እጅ ላይ በጥቅል ወረቀት የተጻፈ ደብዳቤ ነበርና ወስደው ሊያነቡት ሲሞክሩ ወረቀቱ አልላቀቅ ብሎ ፈጽሞ እምቢ አላቸው፡፡ ብዙ ምሕላና ጸሎት ከተደረገ በኋላ ወረቀቱ ከእጁ ላይ ተላቀቀና ሲነበብ ገብረ ክርስቶስ ስለ አምላኩ ፍቅር ብሎ ለ30 ዓመታት ያሳለፈውን እጅግ አሠቃቂ መከራ በተለይም በአባቱ ደጅ ማንም ሳያውቀው ያሳለፈውን እጅግ አሳዛኝ መከራና በኀዘን የሚያስለቅሰውን ታሪኩን በራሱ እጅ በዝርዝር ጽፎት ተገኝቷል፡፡ ንጉሡ አባቱና ንግሥት እናቱም ይህንን ልጃቸው የጻፈውን መልእክት ባነበቡ ጊዜ የሚሆኑት ጠፋቸው፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ መጀመሪያ ላይ ወላጆቹ ሚስት አድርገው ያመጡለት የሮሙ ንጉሥ ሴት ልጅ ለባሏ ታማኝ ሆና 30 ዓመት ሙሉ በእናት አባቱ ቤት በትዕግስት ስትጠብቀው መኖሯ ነው፡፡ እርሷም ታሪኩ ሲነበብ ብትሰማ እንደ ዕብድ ሆነች፡፡ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስን ሥጋውን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱ እጅግ አስገራሚ ተአምራት በድውያን ሕመምተኞች ላይ ተፈጽሟል፡፡ ከተአምራቱ የተነሣ መንገዱ በሕዝብ ተጨናንቆ አላሳልፍ ቢላቸው ነገሡ በመንገድ ዳር ወርቅ እየበተነ ሰው ወርቁን ለማንሳት ሲሄድ በፍጥነት ወደ ቤተ ክርስቲያን አድርሰውታል፡፡ የሙሽራው ቅዱስ የገብረ ክርስቶስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 1️⃣4️⃣ ቀን ስንክሳር ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ Tᴇʟᴇɢʀᴀᴍ - https://t.me/Synaxarium ግንቦት 1️⃣3️⃣ ቀን 2011 ዓ.ም
نمایش همه...
ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

Photo unavailableShow in Telegram
አካውንቱ post ያላረግነው ለማይረባ ብር ለምን ብለን አስበን ነው አሁን ግን የግላቸው የሚለጥፉ ስላየን። CBE 1000481007287 KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL CMC Michael Branch
نمایش همه...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ግንቦት 13 የአቴናን ፍልስፍና ጠንቅቆ የተማረ፣ የፀሐይንና የጨረቃን አካሄዳቸውን የተመራመረና የሮሙን ንጉሥ ልጆች ቅዱሳን የሆኑ የከበሩ አኖሬዎስንና አርቃዴዎስን አስተምሮ ያሳደጋቸው በኋላም በዓት አጽንቶ የጌታችንን መከራ እያሰበ ሲያለቅስ ከለቅሶው ብዛት የተነሳ ቅንድቡ የተነቀለ አባ አርሳንዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ 🔥 አባ አርሳንዮስ (አባ አርሳኒ) ይኽም ቅዱስ ከሮሜ አገር ሰዎች ከባለጸጎችና ከታላላቆቿ ወገን ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተምሮ ዲቁና ከተሾመ በኋላ ወደ አቴና ሄዶ ፍልስፍናን ጠንቅቆ ተማረ፡፡ የፀሐይንና የጨረቃን አካሄዳቸውንና የዘመናትንም መለኪያ ተማረ፡፡ በትምህርቱም ከሁሉም በላይ ከፍ ያለ ሆነ፡፡ በመንፈሳዊ ትምህርቱም ፍጹም ሆኖ አምላካዊ ትሩፋትን የሚሠራ ሆነ፡፡ በሮሜ አገር ታላቁ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ ልጆቹን አኖሬዎስንና አርቃዴዎስን የሚያስተምርለት ጥበበኛ ሰው ፈለገ፡፡ በዚኽም ጊዜ ከአባ አርሳንዮስ የበለጠ ደገኛ አዋቂ አልተገኘምና እርሱን ወስደው ከንጉሡ ጋር አገናኙት፡፡ ንጉሡም ልጆቹን እንዲያስተምርት ለመነው፡፡ አባ አርሳንዮስም አኖሬዎስንና አርቃዴዎስን እያስተማረ አሳደጋቸው፡፡ በብዙ ድካምም ስለሚያስተምራቸው ያለርኅራኄ ብዙ እየቀጣና እየደበደበ ነበር ያሳደጋቸው፡፡ ‹‹ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፣ መሞቱንም አትሻ›› (ምሳ 18፡19)፣ ‹‹ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሠጥሃል›› (ምሳ 29፡17) እንዲል መጽሐፍ፡፡ ንጉሡም በሞት ባረፈ ጊዜ ልጆቹ አኖሬዎስ በሮሜ አገር፣ አርቃዴዎስ ደግሞ በቁስጥንጥንያ ነገሡ፡፡ በታናሽነታቸው ጊዜ እየገረፈ ሲያስተምራቸው የነበረው አባ አርሳንዮስ ግን እነርሱ ሲነግሡ በዚህ ጊዜ ከዓለም ይወጣ ዘንድ ወደደ፡፡ ምን እንደሚያደርግም ሲያስብ ከእግዚአብሔር ዘንድ ‹‹አርሳኒ አርሳኒ ከዚህ ዓለም ውጣ›› የሚል ድምጽ መጣለት፡፡ እርሱም ፈጥኖ በመውጣት ልብሱን ለውጦ ወደ እስክንድርያ አገር ሄደ፡፡ ከዚያም የከበረ የአባ መቃርስ ገዳም ወዳለበት ወደ አስቄጥስ በረሃ ደርሶ በጾም በጸሎት በመስገድ በአርምሞና በትሩፋት ሁሉ ፍጹም ተጋድሎን ተጋደለ፡፡ ምንም ምን የማይናገር ሆነ፡፡ ስለዝምታውም በጠየቁት ጊዜ ‹‹እኔ ስለራሴ አዝናለሁ›› ይላቸዋል፡፡ እርሱ ግን በውስጥና በአፍአ ፍጹም ትሑትና ቅን የዋህ ነው፡፡ የእጅ ሥራውንም እየሠራ ከዕለት ምግቡ እያስተረፈ ይመጸውታል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያንም በገባ ጊዜ ሰው እንዳያየው በምሰሶው ኋላ ይሠወራል፡፡ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትንም ያደርጋል ነገር ግን ከውዳሴ ከንቱ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ እግዚአብሔርም የብዙ ቅዱሳንን ገድል ገለጸለትና ገድላቸውን ጻፈ፡፡ አባ አርሳንዮስ የነፍሳቸውን ድኅነት ለሚሹ ሁሉ ጥቅም ያላቸውን ብዙ ድርሳትንና ተግሣጻትን ደረሰ፡፡ መልኩ ያማረ ፊቱም ብሩህ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ቁመቱ ረጅም ነው፡፡ ፂሙም ከወገቡ መታጠቂያ የሚደርስ ረጅም ነው፡፡ ከልቅሶው ብዛት የተነሣ ቅንድቡ ተነቀለ፡፡ በታላቅ ተጋድሎም ከኖረ በኋላ ወደ መልካም ሽምግልና ደረሰ፡፡ በሮሜ አገር 40 ዓመት፣ በአስቄጥስ ገዳም 35 ዓመት፣ በምስር ገዳም 20 ዓመት፣ በእስክንድርያ ሦስት ዓመት ወደ ገዳምም ተመልሶ 2 ዓመት ኖረ፡፡ በአጠቃላይም ዕድሜው መቶ ዓመት ሲሆነው በዚኽች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ የአባ አርሳንዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ የአባ አርሳንዮስ ገርፈውና ገሥጸው ያሳደጓቸው ልጆቻቸው የከበሩ ቅዱሳን ነገሥታት አኖሬዎስና አርቃዴዎስ እንዴት ላለው ጽድቅ እንደበቁ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ ከቅዱስ አኖሬዎስ እንጀምር፡፡ የአኖሬዎስን ቅድስና ለማወቅም የአባ ዳንኤልን ታሪክ ማየቱ ግድ ነው፡፡ ዓለሙ ሁሉ የእግሩን ትቢያ ያህል እንኳን ዋጋ የሌለው እጅግ የከበረው አባ ዳንኤል ከታለቁ ጻድቅ ንጉሥ ከቅዱስ አኖሬዎስ ጋር የተገናኘ ታሪክ አለው፡፡ ይኸውም አባ ዳንኤል 40 ዓመት ሙሉ በአስቄጥስ ገዳም ሲኖር ከቅጠል በቀር ተመግቦ አያውቅም ነበርና ከጽድቁና ከብቃቱ የተነሣ ከብዙ ዘመን በኋላ የመመካት ክፉ ሀሳብ መጣበት፡፡ ‹‹በገዳም ውስጥ እንደእኔ ትርሕምትን ገንዘብ ያደረገ ይኖር ይሆን?›› ብሎም አሰበ፡፡ ሰውን ወዳድ የሆነ ጌታችንም ይህን ክፉ ሀሳቡን ሊያርቅለት ሽቶ ብርሃናዊ መልአኩን ላከለት፡፡ መልአኩም አባ ዳንኤልን ስለ ትምክህቱ ቢቆጣውም አባ ዳንኤል መልአኩን መልሶ ‹‹ጌታዬ ከእኔ የሚሻል ካለ ንገረኝ፣ ወደ እርሱ ሄጄ አየው ዘንድ እወዳለሁ፣ በመመካቴም ወደ ፈጣሪዬ በልመና እመለስ ዘንድ›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የሮሜና የቁስጥንጥንያ ንጉሥ አኖሬዎስ በመንግሥተ ሰማያት ባልንጀራህ ነው›› አለው፡፡ ‹‹ንጉሥ አኖሬዎስም የመነኮሳትን ሥራዎች ሁሉ ስለሚሠራ ከልብሰ መንግሥቱ ሥር በሥጋው ላይ ማቅ ይለብስ ነበር›› ተብሎ በስንክሳሩ ላይ የተጻፈለት ጻድቅ ንጉሥ ሲሆን ሰማያውያን የሆኑ ቅዱሳን መላእክትም ቅድስናውን የመሰከሩለት በንግሥና ያለ ታላቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡ አባ ዳንኤልም ይህ በሰማ ጊዜ መሬት ላይ ወድቆ በራሱም ላይ አመድ ነስንሶ የዚህን የሮም ንጉሥ አኖሬዎስን ግብር ያሳየው ዘንድ ጌታችንን ለመነ፡፡ ደመናም መጥታ ነጥቃ ወሰደችውና ንጉሥ አኖሬዎስ ደጅ አደረሰቸውና ንጉሡን በዙፋኑ ላይ ሆኖ ባየው ጊዜ ከግርማው የተነሣ አይቶት በታላቅ ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ከእግሩም በታች ሰገደለትና አኗኗሩንም ይነግረው ዘንድ በጌታችን ስም አማፀነው፡፡ ንጉሥ አኖሬዎስም ሰሌን በመታታት በእጅ ሥራው ደክሞ ከሚያገኘው በቀር ምንም ሳይበላና ሳይለብስ 40 ዓመት እንደሆነው፣ ሰሌን ታቶ ሸጦ ካገኘውም ውስጥ ከዕለት ምግቡ መግዣ የሚተርፈውን ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች እንደሚመጸውት፣ ምግቡም እንጀራና ጨው፣ ቅጠል መጻጻም እንደሆነ፣ የማንንም ንብረት ፈጽሞ እንዳልንካ፣ ድንግልናውንም ጠብቆ እንደሚኖር፣ ከንግሥና የወርቅ ካባው ውስጥ ወገቡን በሰንሰለት አሥሮ እንደሚኖር ነገረው፡፡ አባ ዳንኤልም ድጋሚ ከእግሩ ሥር ወድቆ ሰግዶለት ስለ ትምክህቱም ፈጽሞ እያዘኑ ወደ በዓታቱ ተመልሷል፡፡ 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 🍃🍃🍃🍃 ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 1️⃣3️⃣ ቀን ስንክሳር ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
نمایش همه...
ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ