cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሃይማኖታችንስ✞?

✞የኦርቶዶክስ ቻናል✞ > የየዕለቱ ስንክሳር >ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች ከነመልሱ > በቅርብ የጀመረው አስተማሪ ታሪኮች > መንፈሳዊ ዝማሬዎች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ > መንፈሳዊ ፊልሞች > መንፈሳዊ ትምህርቶችና የተለያዩ ፁፎች #ሁሉም_በየእለቱ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
940
مشترکین
+124 ساعت
-37 روز
-2430 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
                       †                           [    🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊    ] [  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] †                       †                       † [ ጽናትና በፈተናዎች መደራረብ አለመታወክ ] 🕊 [ ጠባቧና ቀጥተኛዋ መንገድ ምንድን ናት ? ] ........ አንድ ወንድም አንድን ትልቅ አረጋዊ " አባ ፣ እንደምፈልገው የሆነ አባት ባገኘሁና አብሬው በሞትኩ" አለው፡፡ አረጋዊውም ፦ "ፈጣሪዬ ! የምትፈልገው ነገር ብዙ ይጠቅምህ ይሆናል።" አለው:: ያ ወንድም ግን እያሰበው ያለው ነገር ጥሩ ነው ብሎ ራሱን ስላሳመነ የአረጋዊውን አባባል አላስተዋለም፡፡ በእውነትም ጥሩ የሆነ ነገር እየፈለግሁ ነው ብሎ ከልቡ እያሰበ መሆኑን ያ አረጋዊ ስለ ተረዳ "እንደ ሃሳብህ የሆነ ሽማግሌ ብታገኝ ከእርሱ ጋር ትሆናለህ?" አለው፡፡ ያም "አዎ ፣ እንደ ልቤ የሆነ ከሆነ" አለው። አረጋዊውም "እንዲህ ከሆነ የአረጋዊውን ፈቃድ የምትከተለው አንተ ሳትሆን ምናልባት እርሱ የአንተን ፈቃድ መከተል ይኖርበት ይሆናል ፣ ታዲያ ይህ መልካም ይመስልሃል?" አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ያ ወንድም ተነሣና የተናገረውን ነገር ተገንዝቦ በፊቱ ወድቆ "ይቅር በለኝ ፣ ለካ ምንም ያልሆነ ነገር እያሰብሁ ሳለ እኔ ግን መልካም የሆነ ነገር እያሰብሁ እንደ ሆነ አድርጌ ራሴን እያታለልሁ ኖሯል" አለው:: 🕊 አንድ አረጋዊ ፦ " ጠባቧና ቀጥተኛዋ መንገድ ምንድን ናት ? " ተብሎ ተጠየቀ፡፡ እርሱም "ቀጥተኛዋና ጠባቧ መንገድ ይህቺ ናት ፦ ለራስ ሃሳብ አለ መታዘዝና የራስን ፍላጎት ማሸነፍ፡፡ እነሆ ሁሉንም ትተን ተከተልንህ' ማለት ይህ ነው፡፡" [ ማር.፲፥፳፰ ] የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
11Loading...
02
Media files
11Loading...
03
Media files
431Loading...
04
Media files
452Loading...
05
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊 [ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬    [     ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ !      ] 🕊 ❝ አምላካችን ክርስቶስ የነቢያት የመላእክት ፈጣሪ ሲሆን በሥጋ ተገለጠ ፤ በሰማይ በምድር ፤ ከምድር በታችም ያሉ ፍጥረታት ሁሉ ለእርሱ ይገዛሉ ፥ በሰማይ ያሉ ሊቃነ መላእክት ሥልጣናት ኃይላት ይገዙለታል ፤ የሚገዙ ለሰው አይደለም ፤ ለአምላክ ነው እንጂ። በሰማይ በምድር ከምድር በታች ያለ ፍጥረት ጉልበት ሁሉ ይሰግድለታል፡፡ እንደ እግዚአብሔር አብ ጌትነት የባሕርይ ገዥ እንደሆነ የፍጥረት አንደበት ሁሉ ያምናል፡፡ [ኢሳ.፵፭፥፳፫  ፣ ፊል.፪፥፱-፲፪ ፣ ፩ጴጥ.፫፥፳፪] እንኪያስ ፈጽሞ አይታይ የነበረ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ አምላክ እንደሆነ ተናገረ፡፡ አምላክ እንደ መሆኑ የአምላክነትን ሥራ ሁሉ ሠራ ፤ እርሱም በእውነት የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነው። አንሰ እብለክመው እያለ ለሰው ሕግን ሠራ ፥ ነፋሳትን ባሕርን ርኵሳን መናፍስትን አዘዘ፡፡ [ማቴ.፭፥፳፩–፵፯  ፣ ማር.፩፥፳–፳፰ ፤ ፬፥፴፭–፴፩] ❞ [     አቡሊዲስ     ] ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን። †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
441Loading...
06
Media files
1041Loading...
07
Media files
901Loading...
08
🕊 [ † እንኳን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊  † ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ †  🕊 † በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በደራሲነታቸው : በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው:: ሊቁ የተወለደው መጋቢት ፳፯ [27] ቀን በ፬፻፴፫ [433] ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር:: አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት : ገና በ ፫ [3] ዓመቱ : እናቱ አቅፋ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "አንሰ እፈርሕ ሠለስተ ግብራተ - እኔስ ፫ [3] ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ:: † ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም :- ፩. ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ:: ፪. ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ:: ፫. ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው:: ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "እግዚአብሔር በዚሕ ሕጻን አድሮ ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ ፯ [7] ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ፭ [5] ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ፲፪ [12] ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን:: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው:: "እንግዲያውስ ትንቢተ ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል:: ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በኋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን : ዕጸበ ገዳምን : ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ [በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት] ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል:: † በዘመኑም :- ፩. የ፬፻፶፩ [451] ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል:: ፪. ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል:: ፫. በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል:: 4፬. ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል:: በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በኋላ በተወለደ በ፸፪ [72] ዓመቱ በ፭፻፭ [505] ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ ፳፯ [27] ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች:: † አምላከ ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን:: 🕊 [ † ሰኔ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ፪. ቅዱስ : ቡሩክና አሸናፊ አባ አበስኪሮን [ታላቅ ሰማዕትና ባለ ብዙ ተአምራት ነው] ፫. ፲፮ ሺህ "16,000" ሰማዕታት [በአንድ ቀን የተገደሉ] ፬. የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን የተከፈተበት በዓል (ከ1ሺ ዓመታት በፊት ምስር [CAIRO] ውስጥ] [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ሥሉስ ቅዱስ [ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ] ፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፫. አባ ሲኖዳ [ የባሕታውያን አለቃ ] ፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት ፭. አባ ባውላ ገዳማዊ ፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፯. ቅዱስ አግናጥዮስ [ ለአንበሳ የተሰጠ ] † " ይሕንን እዘዝና አስተምር :: በቃልና በኑሮ : በፍቅርም : በእምነትም : በንጽህናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው:: እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር : ለማስተማርም ተጠንቀቅ:: " † [፩ጢሞ.፬፥፲፩] (4:11) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
951Loading...
09
አንቀፀ ብፁአን ቁጥ.22 የቀጠለ
500Loading...
10
Hello, ĢetÃbe! Thank you for visiting our Channel
40Loading...
11
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊    ም ክ ረ ቅ ዱ ሳ ን   🕊 ▷   "  የ ም ድ ር ጨ ው ና ች ሁ !  " [   " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! "  ] [                        🕊                        ] ----------------------------------------------- ❝ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል ? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። ❞ [ ማቴ . ፭ ፥ ፲፫ ] 🕊                       💖                    🕊
950Loading...
12
Media files
980Loading...
13
Media files
960Loading...
14
                       †                           [    🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊    ] [  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] †                       †                       † [ ጽናትና በፈተናዎች መደራረብ አለመታወክ ] 🕊 [    እናንተን ግን አልሰማችሁም !    ] ........ ከአባቶች አንዱ ይህን አለ ፦ " አንድ ቀን ቅዳሜ ማታ የተወሰኑ ድሆች ምጽዋት ሊቀበሉ መጡ፡፡ ሌሊት ተኝተን ሳለ ከእነርሱ መካከል ትንሽ ብጣሽ ጨርቅ ብቻ ያለችውና እርሷኑ ጣል አድርጎ የተኛ ሰው ነበር፡፡ ሌሊት ስወጣ ከባድ ከሆነው ብርድ የተነሣ ጥርሶቹ ሲንቀጠቀጡ ሰማሁት፡፡ እርሱ ግን እንዲህ እያለ ራሱን ያበረታታ ነበር ፦ " ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ ፣ በዚህ ሰዓት ስንት ባለ ጸጋዎች ብረት ለብሰው በእስር ቤት ታስረዋል ፤ ስንቶችስ ተፈጥሯዊ የሰውነት ፍላጎታቸውን እንኳ ለመፈጸም በማይችሉበት ሁኔታ እግራቸው በሰንሰለትና ከእንጨት ጋር ታስሯል ፤ እኔ ግን እግሮቼን እንደ ፈለግሁ መዘርጋት የምችል እንደ ንጉሥ ነኝ፡፡" ይህን ስሰማ ለወንድሞች አወራሁላቸው ፣ እነርሱም በቁዔት አገኙበት።" 🕊 አንድ ወንድም በጽሞና ጸሎት ይኖር ነበር፡፡ ከመንገዱ ሊያወጡት ፈለጉና አጋንንት መላእክት መስለው ተገለጡለትና ለጸሎት ቀሰቀሱት ፣ መብራትም አሳዩት፡፡ ስለሆነም አንድን አረጋዊ ለማየት ሄደና "አባ መላእክት ብርሃን ይዘው መጡና ለጸሎት ቀሰቀሱኝ" አለው። አረጋዊውም ፦ " የኔ ልጅ ፣ አትስማቸው ፣ አጋንንት ናቸውና ፣ ነገር ግን ሊቀሰቅሱህ ሲመጡ መነሣት ስፈልግ እኔው ራሴ እነሣለሁ ፣ እናንተን ግን አልሰማችሁም በላቸው" አለው፡፡ የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
931Loading...
15
Media files
731Loading...
16
Media files
961Loading...
17
Media files
941Loading...
18
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊 [      ከዚህ የተነሣ አደንቃለሁ !      ]   ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ በአባቱ ጌትነት ተነሣ ፣ በሲኦል ተግዘው የነበሩ የቅዱሳንን ነፍሳት አዳነ ፣ ንጉሥ ፣ ድል የማይነሣ [ " ነ " ጠብቆ ይነበብ ] ገዢም ነውና ፤ በፍጹም ክብር ጌትነት ወደ ሰማይ ዐረገ ፣ በማይመረመር በማይታወቅ ምሥጢር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በከበረው ሥጋው ከአብ ጋር በዕሪና ተቀመጠ ፤ .... ለማይደፈር ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል ፣ ከእግዚአብሔር ጋር በመተካከል የሚኖር [ ግእዙ ዘይነብር በየማነ እግዚአብሔር ይላል ] መላእክትና የመላእክት አለቆች ፣ ሱራፌልና ኪሩቤል የሚሰግዱለት ሥጋ ከእኛ ባሕርይ ይገኝ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ አድናቆት አለን ? ይህን መላልሼ ባሰብሁት ጊዜ ፣ ሰው ያገኘውን [ ለሰው የተሰጠውን ] ልክ መጠን የሌለውን ፍጹም ክብር ፣ ከእግዚአብሔር የተደረገውን ባሕርያችን ያገኘውን ታላቅ ፍቅር አይቼ ከዚህ የተነሣ አደንቃለሁ። ❞ [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ] †                       †                       † 💖                    🕊                    💖
1001Loading...
19
                         †                         🕊 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን 🕊 ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ ❝ የልጅሽ ስም በተነገረ ጊዜ ሁሉ ፣ በዛ ስምሽ ይነሣል ፣ የልጅሽ መለኮት በሚገዛበትም በዛ ገናንነትሽ ይሠለጥናል ፣ አንድ ልጅሽ ከፍ ከፍ ባለና በወለደው ቀኝ በተቀመጠበትም በዛ ካንቺ የነሣው ፍጹም [ እውነተኛ ] ሥጋ ከመለኮቱ ጋር አንድ ሆኖ ይኖራል። ❞ [ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ] 🕊 አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን። ክፍልኒ ድንግል እቁም በየማን።                     [ ወልድ [ ክርስቶስ ] በደብረ ጽዮን በነገሠ ጊዜ ድንግል ሆይ በቀኝ እቆም ዘንድ አድይኝ [ አማልጅኝ ] ] ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን። †                       †                       † 💖                    🕊                    💖
881Loading...
20
Media files
771Loading...
21
Media files
721Loading...
22
                        †                          🕊  [    አረገ በእልልታ   ] 🕊 ❝ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ አረገ። በእልልታ እና በመለከት ድምጽ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ፣ ... በክብር ወደ ሰማያት ዐረገ ፣ በክብር ወደ ሰማያት ዐረገ ፣ ... መላእክት ፣ ኃይል ሁሉ ፣ ፍጥረታት ሁሉ ለእርሱ ተገዙለት [ተገዝተውለታል] ፣ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ፣ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ። በአባቱ ጌትነት ተነሣ ፣ በሲኦል ተግዘው የነበሩ የቅዱሳንን ነፍሳት አዳነ ፤ ንጉሥ ፣ ድልም የማይነ'ሣ ገዥም ነውና ፤ በፍጹም ክብር ጌትነት ወደ ሰማይ ዐረገ ፣ በማይመረመር በማይታወቅ ምሥጢር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በከበረው ሥጋው ከአብ ጋር በዕሪና ተቀመጠ፡፡ ለማይደፈር ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል ፣ መላእክትና የመላእክት አለቆች ፣ ሱራፌልና ኪሩቤል የሚሰግዱለት ሥጋ ከእኛ ባሕርይ ይገኝ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ አድናቆት አለን ? ይህን መላልሼ ባሰብሁት ጊዜ ፣ ሰው ያገኘውን [ለሰው የተሰጠውን] ልክ መጠን የሌለውን ፍጹም ክብር ፣ ከእግዚአብሔር የተደረገውን ባሕርያችን ያገኘውን ታላቅ ፍቅር አይቼ ከዚህ አደንቃለሁ። ❞ [ ድጓ ዘፋሲካ ] †                       †                       † ❝ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ ❞ [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]        🕊  ድንቅ ትምህርት  🕊 †                       †                       † 💖                    🕊                    💖
970Loading...
23
Media files
830Loading...
24
Media files
830Loading...
25
Media files
830Loading...
26
                         †                       🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊 ❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሠሮ ለሰጣን ▸ አግዐዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም ❞ 🕊 ❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞ ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖 🕊 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን 🕊 "ወሶበ ተንሥአ ዐርገ ውስተ ሰማያት ወዘኒ ወረደ ዘእንበለ ሥጋ ውእቱ ዘዐርገ ሥግወ ወአሐዱ ውእቱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ወኢወሰከ ኍልቆ ራብዐየ ወኢካልዐ ገጸ ወነበረ በየማነ አብ ፤ [ ከተነሣም በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። ሥጋ ሳይይዝ የመጣ እርሱ ሰው ሆኖ ዐረገ። ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እርሱ ነው። ለሥላሴ አራተኛ ለቃል ሁለተኛ አልሆነም። በአብ ዕሪና ኖረ፤ ] [ ቅዱስ ባስልዮስ ] ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን። †                       †                       † 💖                    🕊                    💖
970Loading...
27
Media files
810Loading...
28
                         †                       " እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ ! " --------------------------------------------- 💖 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን ! 💖 " አምላክ በእልልታ ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። ዘምሩ ፥ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ። እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ፤ በማስተዋል ዘምሩ። እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል። [መዝ.፵፯፥፭፥፰] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ † [  ዕርገት  ] = ሰኔ ፮ [ 6 ] ይሆናል። † [  ጰራቅሊጦስ  ] = ሰኔ ፲፮ [ 16 ] በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል ። † [  ፆመ ሐዋርያት  ] = ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ይገባል ። † [  የጾመ ድህነት  ] = ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ይገባል። †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
760Loading...
29
Media files
812Loading...
30
🕊 ✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ✞ 🕊  ዕርገተ እግዚእ   🕊 ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን ፪ [2] ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል:: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ [በሕማሙ: በሞቱ] ዓለምን አድኖ: ፵ [40] ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል:: በ፵ [40] ኛው ቀን ፻፳ [120] ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል:: ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ፵ [40] ኛው ቀን ዐረገ:: አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል:: " ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ::" [መዝ.፵፮፥፮] (46:6) ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን:: "እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::" [ሉቃ.፳፬፥፶] (24:50-53) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
832Loading...
31
Hello Dejen, there! We’re happy to see you.
10Loading...
32
🕊 [  † እንኳን ለጻድቅና ሰማዕት አባ ቴዎድሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †  ] †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊   †  አባ ቴዎድሮስ  †    🕊 †  አባ ቴዎድሮስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ግብፃዊ አባት ነው:: ተወልዶ ባደገባት የእስክንድርያ ከተማ ብሉያትንና ሐዲሳት በወቅቱ ከነበሩ አበው ሊቃውንት ተምሯል:: ጊዜው ምንም መናፍቃን የበዙበት ቢሆን በዛው ልክ እነ ቅዱስ እለ እስክንድሮስና ቅዱስ አትናቴዎስን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና ከነሱ የሚገባውን ወስዷል:: አባ ቴዎድሮስ "አባ" ያሰኘው ሥራው:- ሲጀመር ገና በወጣትነቱ ድንግልናንና ምንኩስናን በመምረጡ ነበር:: ምንም እንኳ ሐብት ከእውቀት ጋር ቢስማማለትም ይሕ እርሱን ከምናኔ ሊያስቀረው አልቻለም:: ከከተማ ወጥቶ: በዓት ወስኖ በጾምና በጸሎት ተወሰነ:: በ፫፻፵ [340] ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ግን በምዕመናን ላይ ከባድ ችግር ደረሰ:: የወቅቱ ነገሥታት በስመ ክርስቲያን አርዮሳውያን ነበሩና ሕዝቡን ማስገደድ: አንዳንዴም የአርዮስን እምነት ያልተቀበለውን ማስገደል ጀመሩ:: በዚህ ምክንያትም ታላቁ የኦርቶዶክስ ጠበቃ ቅዱስ አትናቴዎስን ከመንበሩ አሳደዱት:: በምትኩም አርዮሳዊ ሰው ዻዻስ ተብሎ ተሾመ:: ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ እውነተኛ እረኛ ያስፈለገው:: በበዓቱ የነበረው አባ ቴዎድሮስ አላቅማማም:: ቤተ ክርስቲያን ትፈልገዋለችና መጻሕፍትን ገልጾ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ምዕመናንን ያጸናቸው ጀመር:: መናፍቃኑን ተከራክሮ ምላሽ በማሳጣት ሕዝቡን ከኑፋቄ በመጠበቅ የሠራው ሥራ ሐዋርያዊ ቢያሰኘውም ለአርዮሳዊው ዻዻስ [ጊዮርጊስ ይባላል] ሊዋጥለት አልቻለም:: በቁጣ ወታደሮችን ልኮ አባ ቴዎድሮስን ተቆጣው:: እንዳያስተምርም ገሰጸው:: አባ ቴዎድሮስ ግን እሺ ባለማለቱ ግርፋት ታዘዘበት:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲገርፉት ረድኤተ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከዛ ሁሉ ግርፋት አንዲቷም አካሉ ላይ አላረፈችም:: በዚህ የተበሳጨው አርዮሳዊ ዻዻስ የአባ ቴዎድሮስን እጅና እግር ከፈረስ ጋሪ በኋላ አስረው በኮረኮንች መንገድ ላይ በፍጥነት እንዲያሮጧቸው አዘዘ:: ፈረሶቹ መሮጥ ሲጀምሩ የአባ ቴዎድሮስ አካሉ ይላላጥ ጀመር:: ትንሽ ቆይቶ ግን እጆቹ ተቆረጡ:: በኋላም ራሱ ከአንገቱ ተለይታ መንገድ ላይ ወደቀች:: አካሉ በሙሉ መሬት ላይ ተበታተነ:: እግዚአብሔር ቅድስት ነፍሱን ተቀብሎ አሳረጋት:: † ለቅዱሱም ፫ [ 3 ] አክሊል ከሰማይ ወርዶለታል :- ፩. ስለ ፍጹም ምናኔውና ድንግልናው ፪. ስለ ሐዋርያዊ የወንጌል አገልግሎቱ ፫. ስለ ሃይማኖቱ ደሙን አፍስሷልና "እምአባልከ ተመቲራ ለእንተ ሠረረት ርዕስ: እግዚአብሔር አስተቄጸላ በአክሊል ሠላስ" እንዳለ መጽሐፍ:: ምዕመናን ሥጋውን ሰብስበው በዝማሬና በማኅሌት በክብር ቀብረውታል:: † አምላካችን ከቅዱሱ በረከት ይክፈለን:: 🕊 [  † ሰኔ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ አባ ቴዎድሮስ ሰማዕት ፪. አባ ገብረ ክርስቶስ ፫. ፵ "40" ሰማዕታት [   † ወርሐዊ በዓላት    ] ፩. ቅድስት ደብረ ቁስቋም ፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል ፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ ፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ፯. ቅድስት ሰሎሜ ፰. አባ አርከ ሥሉስ ፱. አባ ጽጌ ድንግል ፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል † " መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ:: ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ:: ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል:: ይህንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያሰረክባል:: ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም:: " † [፪ጢሞ.፬፥፯]  (4:7) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
1111Loading...
33
Media files
821Loading...
34
Media files
850Loading...
35
አንቀፀ ብፁአን ቁጥ.21 በእግዚአብሔር ላይ ስለሚደረገ ጭካኔ
610Loading...
36
Media files
1191Loading...
37
Media files
1231Loading...
                       †                           [    🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊    ] [  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] †                       †                       † [ ጽናትና በፈተናዎች መደራረብ አለመታወክ ] 🕊 [ ጠባቧና ቀጥተኛዋ መንገድ ምንድን ናት ? ] ........ አንድ ወንድም አንድን ትልቅ አረጋዊ " አባ ፣ እንደምፈልገው የሆነ አባት ባገኘሁና አብሬው በሞትኩ" አለው፡፡ አረጋዊውም ፦ "ፈጣሪዬ ! የምትፈልገው ነገር ብዙ ይጠቅምህ ይሆናል።" አለው:: ያ ወንድም ግን እያሰበው ያለው ነገር ጥሩ ነው ብሎ ራሱን ስላሳመነ የአረጋዊውን አባባል አላስተዋለም፡፡ በእውነትም ጥሩ የሆነ ነገር እየፈለግሁ ነው ብሎ ከልቡ እያሰበ መሆኑን ያ አረጋዊ ስለ ተረዳ "እንደ ሃሳብህ የሆነ ሽማግሌ ብታገኝ ከእርሱ ጋር ትሆናለህ?" አለው፡፡ ያም "አዎ ፣ እንደ ልቤ የሆነ ከሆነ" አለው። አረጋዊውም "እንዲህ ከሆነ የአረጋዊውን ፈቃድ የምትከተለው አንተ ሳትሆን ምናልባት እርሱ የአንተን ፈቃድ መከተል ይኖርበት ይሆናል ፣ ታዲያ ይህ መልካም ይመስልሃል?" አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ያ ወንድም ተነሣና የተናገረውን ነገር ተገንዝቦ በፊቱ ወድቆ "ይቅር በለኝ ፣ ለካ ምንም ያልሆነ ነገር እያሰብሁ ሳለ እኔ ግን መልካም የሆነ ነገር እያሰብሁ እንደ ሆነ አድርጌ ራሴን እያታለልሁ ኖሯል" አለው:: 🕊 አንድ አረጋዊ ፦ " ጠባቧና ቀጥተኛዋ መንገድ ምንድን ናት ? " ተብሎ ተጠየቀ፡፡ እርሱም "ቀጥተኛዋና ጠባቧ መንገድ ይህቺ ናት ፦ ለራስ ሃሳብ አለ መታዘዝና የራስን ፍላጎት ማሸነፍ፡፡ እነሆ ሁሉንም ትተን ተከተልንህ' ማለት ይህ ነው፡፡" [ ማር.፲፥፳፰ ] የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
P mane tekel fares.mp35.54 MB
A Ye DINIGIL tihtina.mp35.96 MB
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊 [ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬    [     ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ !      ] 🕊 ❝ አምላካችን ክርስቶስ የነቢያት የመላእክት ፈጣሪ ሲሆን በሥጋ ተገለጠ ፤ በሰማይ በምድር ፤ ከምድር በታችም ያሉ ፍጥረታት ሁሉ ለእርሱ ይገዛሉ ፥ በሰማይ ያሉ ሊቃነ መላእክት ሥልጣናት ኃይላት ይገዙለታል ፤ የሚገዙ ለሰው አይደለም ፤ ለአምላክ ነው እንጂ። በሰማይ በምድር ከምድር በታች ያለ ፍጥረት ጉልበት ሁሉ ይሰግድለታል፡፡ እንደ እግዚአብሔር አብ ጌትነት የባሕርይ ገዥ እንደሆነ የፍጥረት አንደበት ሁሉ ያምናል፡፡ [ኢሳ.፵፭፥፳፫  ፣ ፊል.፪፥፱-፲፪ ፣ ፩ጴጥ.፫፥፳፪] እንኪያስ ፈጽሞ አይታይ የነበረ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ አምላክ እንደሆነ ተናገረ፡፡ አምላክ እንደ መሆኑ የአምላክነትን ሥራ ሁሉ ሠራ ፤ እርሱም በእውነት የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነው። አንሰ እብለክመው እያለ ለሰው ሕግን ሠራ ፥ ነፋሳትን ባሕርን ርኵሳን መናፍስትን አዘዘ፡፡ [ማቴ.፭፥፳፩–፵፯  ፣ ማር.፩፥፳–፳፰ ፤ ፬፥፴፭–፴፩] ❞ [     አቡሊዲስ     ] ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን። †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
2
[ ስንክሳር ሰኔ - ፯ - ] .mp38.57 MB

1
አንቀፀ ብፁአን ቁጥ.22 የቀጠለ
نمایش همه...
13.87 MB
Hello, ĢetÃbe! Thank you for visiting our Channel
نمایش همه...