cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሃይማኖታችንስ✞?

✞የኦርቶዶክስ ቻናል✞ > የየዕለቱ ስንክሳር >ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች ከነመልሱ > በቅርብ የጀመረው አስተማሪ ታሪኮች > መንፈሳዊ ዝማሬዎች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ > መንፈሳዊ ፊልሞች > መንፈሳዊ ትምህርቶችና የተለያዩ ፁፎች #ሁሉም_በየእለቱ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
955
مشترکین
-324 ساعت
-97 روز
-630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🕊 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ [ † ግንቦት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት † ] †   🕊 ቅዱስ አርሳኒ   🕊 †    ቅድስት ሃይማኖት እዚህ ዛሬ እኛ ጋር የደረሰችው በበርካታ ሰማዕታትና ጻድቃን ደም ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ግድግዳዎቿ እንጨትና ድንጋይ እንዳይመስሏችሁ:: አጽመ ቅዱሳን ነው እንጂ:: ቅዱሳን ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስን እንደ እኔ እና እንደ ዘመኑ ትውልድ በከንፈራቸው የሚሸነግሉ አልነበሩም:: እነርሱ በፍጹም ልባቸው ስለ ፍቅሩ ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ እንጂ:: በቅድስናቸው ከተመሰከረላቸው ቀደምት ቅዱሳን አንዱ ደግም ቅዱስ አርሳንዮስ ነው:: ቅዱሱ የተወለደው በ፫፻፵፭ [ 345 ] ዓ/ም ሮም ውስጥ ነው:: በወጣትነቱ ይሕ ቀረህ የማይሉት የጥበብና የፍልስፍና ሰው ነበር:: በተለይ በትልቁ የሮም ቄሳር ቴዎዶስዮስ ዘመን በቤተ መንግስት አካባቢ የተከበረና የንጉሡ ልጆች መምሕር ነበር:: አኖሬዎስና አርቃዴዎስን ቀጥቶ ያሳደጋቸውም እርሱ ነበር:: በድንግልና እስከ ፵ [ 40 ] ዓመቱ ድረስ ሮም ውስጥ ቆየ:: ከዚህ በኋላ ግን ስለ ሰማያዊ ነገሮች ሲያስብ መልዐኩ በሕልም ወደ ግብፅ ሒድ አለው:: በመጀመሪያ ወደ እስክንድርያ ቀጥሎ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ መነኮሰ:: በቆይታ ግን ብሕትውና ምርጫው ሆነ:: ቅዱስ አርሳኒ በእነዚሕ ነገሮቹ ይታወቃል :- ፩. በምንም ምክንያት ከማንም ጋር አያወራም:: [ለ፷ [60] ዓመታት በአርምሞ ኑሯል] ፪. በቤተ መቅደሱ ግድግዳ ተጠግቶ እንባውን ሲያፈስ የርሱን አካል አርሶ በመሬት ላይ ሲፈስ ይታይ ነበር:: ከእንባው ብዛት ቅንድቦቹ ተላልጠው አልቀው ነበር:: ፫. በርካታ ድርሳናትን ደርሷል:: ብዙዎቹ ዛሬም ግብጽ ውስጥ አሉ:: ፬. ሸንጎበቱን ወደ ደረቱ አዘንብሎ ስለሚቆም ማንንም ቀና ብሎ አያይም ነበር:: ፭. ለጸሎት አመሻሽ ፲፩ ሰዓት [11:00] አካባቢ ላይ ይቆምና ጸሎቱን የሚጨርስ ፀሐይ ግንባሩን ስትመታው ነው:: ፮. ሁል ጊዜ ራሱን "አንተ ሰነፍ [ሐካይ] እያለ ይገስጽ ነበር:: ፯. በገዳማውያን ታሪክ የርሱን ያሕል በቁመቱ ረዥም አልተገኘም ይባላል:: የራሱ ጸጉር በጀርባው የወረደ ሲሆን ጽሕሙን በስዕሉ ላይ እንደምታዩት ነጭና እስከ መታጠቂያው የወረደ ነበር:: እነዚህ ግን በጣም ጥቂቶቹ ናቸው:: ቅዱስ አርሳንዮስ አካሉ በተጋድሎ ደቆ: ለ፷ [60] ዓመታት በግሩም መንፈሳዊነት ኑሮ በ፻ [100] ዓመቱ በዚሕች ዕለት ዐርፏል:: አምላካችን እግዚአብሔር ከታላቁ የቅድስና ሰው አርሳኒ በረከት አይለየን:: 🕊 [ †  ግንቦት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ አርሳንዮስ - አርሳኒ [ጠቢብ ገዳማዊ] [ †  ወርኀዊ በዓላት ] ፩. እግዚአብሔር አብ ፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት ፫. ፺፱ "99ኙ" ነገደ መላዕክት ፬. ቅዱስ አስከናፍር ፭. ፲፫ " 13ቱ " ግኁሳን አባቶች ፮. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ " የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል:: ደግሞ ተገርቷል:: ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም:: የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው:: በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን:: በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን:: ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ:: ወንድሞቼ ሆይ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም:: " [ያዕ.፫፥፯-፲፩] (3:7-11) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
                        †                         🕊  💖                     💖  🕊 [  መንፈሳዊ ብርታት እንዴት እናግኝ !  ] 🕊                         †                         [ ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል ! ] ❝ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው ፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል ፤ እግዚአብሔርም ይመስገን። ❞ [ መዝ . ፷፰ ፥ ፴፭ ] [  💖  መ ን ፈ ሳ ዊ ብ ር ታ ት 💖  ]                    ]      [      🕊    ምክረ ቅዱሳን   🕊 🕊 [ በብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ] †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
ሁሌ አስባለው ዘወትር ስነቃ ማልጄ ስነሳ የቀን ውሎዬን እቅዴን ሳነሳ አምላክ አንተነትክን እንዴት እኔ ልርሳ እናማ አምላኬ እንዳትቆጥርብኝ እኔ እኮ ልጅህ ነኝ ከትላንት ማንነት ምንም ያልተረፈኝ ነገን የተራብኩኝ በነበር ታጅዬ በዓለም የተቋጠርኩ ለካ የሄድኩ ሲመስለኝ ነበር ላይ ነው የቆምኩ በትላንትናዬ ዛሬን ተመፃደኩ እውነት ባይገባኝ ነው እንጂ ባልረዳ ውሉን ማንስ ፈቀደልኝ አድሬ መዋሉን ማንስ ዘመንን አደለኝ ማንስ ዛሬን ሰጠኝ ማንስ የልቤን መሻት ሞላልኝ ጎደሎዬንስ ማነው ያየልኝ ታድዬ ፈጣሪዬ ማልጄ ስነሳ የቀን ውሎዬንም እቅዴን ሳወሳ አምላክ ቸርነትክን እንዴት እኔ ልርሳ ባይሆን አንተ እውነት አለህ ጠፍቼብሀለው ከቤትህ እርቄብሀለው እውነት ከእቅፍህ ወጥቼብሀለው ዝማሜው ዝማሬው ጠፍቶኝ ፈልጋለው ዜማህን በዳንኪራ ቀይሬብሀለው ከለምለሙ መስክም ኮብልዬብሀለው አቤት በደሌ አቤት አጢያቴ ይህም ሳያንሰኝ የፍቅርህን ወሰን የለሽነት ዘንግቼብሀለው እግዚኦ እግዚኦ እግዚኦ አምላክ ይቅር በለኝ ንስሀ አድርግልኝ አዎ በእርግጥ አንተ ይቅር ባይ አባት ነህ ምንም ብበድልህ ፊትህን ማታዞር ዘወትር በእቅፍህ እየቀጣህ ምታስተምር አረ አንተ ደግ አባት ነህ አረ እሩሩነህ ቆይ ታድያ ማልጄ ስነሳ እቅዴን ሳወሳ ያንተን ቸርነትክን ይቅር ባይነትህን እዴት እኔ ልርሳ ይልቅ ተለመነኝ አንድ ፈቃድ ልጠይቅህ ተለመነኝ አንተም አባቴ አደለህ አምላኬ አለም አጅላ እንዳታበሰብሰኝ በትላንትና ጎርፍ እንዳታሶስደኝ እባክህ አምላኬ በይቅርታ ዳብሰኝ ከጉሮኖዬ ከመንጋው መልሰኝ የቀድም ቤቴ በጣም ነው የናፈቀኝ አሜን አሜን አሜን አሁን ተለመነኝ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
🕊 [ እንኳን ለታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ለፈለሰበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። ] በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ፶፮ [56] ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል:: [ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሥላሴን በማመን ተተከለ [ ተገኘ ]። በማስተዋል ስሙት ፣ በጸጥታ እና በርጋታም ሆናችሁ አድምጡት። በጌታው የሠርግ ቀን [ በዕለተ ምጽዓት ] በመከራው ከሚገኘው ደስታ ትሳተፉ ዘንድ ፣ የነፍስ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ብላችሁ መጥራት ይቻላችሁ ዘንድ በመገዛት ፣ በማኅሌት እና ኅሊናን በመሰብሰብ በዐሉን አክብሩ። ] [ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ] ሰዳዴ ጽልመት አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት ❝ አንተ የደከምክበት ያ መልካም አዝመራ እንክርዳድ ሞላበት ተክለ አብ ቶሎ ና አውሬው ሰልጥኖብን ተፍገምግመናል ኪዳን የሚጠብቅ አባት ያስፈልጋል፡፡ ❞ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram