cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ዘውትር አላህን ያስታውሡ

ከወንድ ወይም ከሴት እርሡ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን።ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳነውን እንመነዳቸዋለን።[ ሱረቱ ነህል: 97] For any comments•••• @zewtr_allahn_enastaws_bot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
342
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
+230 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
🌴ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝ተውበት ያደረገ ሁሉ የአላህ ተወዳጅ ባሪያ ነው።❞ 📚جامع الرسائل 116/1 ══════ ❁ ══════
240Loading...
02
🌴አውን ቢን አብደላህ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ፡- ❝የተውበተኛ ልብ እንደ ብርጭቆ ነች  በውስጧ የሚደርሰው ነገር ሁሉ ተፅዕኖ ያሳድርባታል  የአላህ ተግሳፅ ወደ እርሷ በደረሰ ጊዜ    ወደ ተውበት ፈጣን ጥሪ ያደርግላታል  ምክንያቱም ተውበት ለቀልብ መደሃኒቷ ነው ኃያሉ ጌታዋም ተውበትን ተቀባይ ነው  ተውበትም ወደ ጀነት ጥሪ ታደርጋለች ጀነትን እስከምትገባ ደረስ ከሚፀፀቱ ሰዎች ጋር ተቀመጥ የአላህ እዝነት ለእነርሱ በጣም የቀረበ ነውና።❞    📚صفة الصفوة (٧٠/٣) ══════ ❁ ══════
230Loading...
03
ተክቢረቱል-ኢሕራም የጓደኛ መመዘኛ የታላቁ ሰሓቢይ ኢብኑ መስዑድ رضي الله عنه ልዩ ደረሳና ቅርብ ሰው የሆኑት ታላቅ ታቢዒይ ኢብራሂም አን'ነኸዒይ እንዲህ ይላሉ፥ "አንድን ግለሰብ ተክቢረተል- ኢሕራም (የሰላት መክፈቻ የመጀመሪያው ተክቢረህ) ላይ የሚዘናጋ -ቀድሞ ሶፍ ላይ ተዘጋጅቶ ቆሞ አሰጋጅ አላሁ አክበር እንዳለ ወዲያ ተከትሎ ተክቢር የማያደርግ- ሆኖ ካገኘኸው (ጭቃና መስለ ቆሻሻ እጁን የነካው ሰው እጁን ታጥቦ ከጭቃው እንደሚርቀው) ከዚህ ግለሰብ ራቅ!" 📚አል-ሙኽታር ሚን መናቂቢል አኽያር 1/281።   🔅በዚህም መሰረት ሁሌ ኢቃም ሲሰሙ እንጂ ከቤትና ከሱቅ መቀመጫዎቻቸው የማይነሱ ኋላ ቀሮችን በሙሉ እጅህን ታጥበህ ዳግም ላትነካቸውና ላትቀርባቸው ራቃቸው፤ ተስፋ እስካልቆረጥክ ድረስ ለመምከር ካልሆነ በስተቀር መቼም ተመልሰህ አታግኛቸው።   🔅ኢቃም ተብሎ እየተሰገደ ከመስጂድ ዙሪያ ቆመው ስልክና ሰው የሚያወሩትንም እዚሁ ውስጥ አካታቸው። 🔅 መስጂድ በረንዳ ውስጥ፣ ከዛም አልፎ ወደ ውስጥ ገባ ብለው ከኢማምና መእሙሞች ጀርባ ላይ ቆመው ሰጋጆችን እየረበሹ ውጪ የጀመሩትን የእርሰበርስ ወሬ ወይም ስልክ ከተክቢረተል ኢሕራምና ከሰላት የሚያስበልጡትንም መክረህ አስጠንቅቀህ ካልተመለሱ አብዝተህ ራቃቸው። 🔅ዲኑን በሚገባ የማያከብርና ለሰላት ቦታ የሌለው ላንተ ምንም አይጠቅምህምና!   ✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 7/5/1444 ዓሂ  
411Loading...
04
#ያኔ ፀሐይ በስንዝር ልክ በምቶንበት ቀን ሰዎች ላባቸው በወንጀላቸው ልክ በሚደፍቃቸው እለት ከአሏህ አርሽ ጥላ ስር መሆን ከፈለክ "ወጣትነትህን በመልካም ነገር አሳልፍ".
470Loading...
05
@zewtr_allahn_enastaws
510Loading...
06
💥ድንቅ ንግግር❗️ ✍      ወንድምህ ከረሜላ ስጦታ ሲሰጥህ መመልከት ያለብህ የከረሜላውን ዋጋ ሳይሆን ወንድምህ ልብ ውስጥ ያለህን ዋጋ ነው!   /ኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ /     [የሱረቱ አዝ-ዘልዘለህ ተፍሲር ደርስ ላይ የተወሰደ]
561Loading...
07
🤲 ያ አላህ  የውስጡን ሃጃ መግለፅ አቅቷቸው  ኢላሂ ያሉ  ሰዎች  ሁሉ  ሀጃውን አሳካላቸው ኢላሂ!! ከለመኑህ በላይ አብዘተህ የምትሰጥ ተጣሪን የምሰማ ለባሪያወችህ ቅርብ ምህረትህ የሰፋ እዝነትህ የላቀ     ለምነውህ የምትሰማ እዝነትህን ከጅለው ለተማፀኑህ  ቅጣትህን ፈርተው ወዳንተ ያረብ ላሉ ባሪያዎችህ ሁሉ የልባቸውን ጭቀን አቅልልላቸው ያ አሏህ🤲 @zewtr_allahn_enastaws
742Loading...
08
ውዱዑን አሳምረህ አድርግ! ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ “ውዱዑ አድርጎ ውዱዑን ያሳመረው ሰው፤ ኃጢአቶቹ ከጥፍሮቹ ስር እንኳ ሳይቀር ከአካላቱ ይወጣሉ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 245 @zewtr_allahn_enastaws
750Loading...
09
ያስነጠሰ ሰው አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን ለምኑለት! ካላመሰገነ ግን... وعن أَبي موسى رضي الله عنه، قَالَ: سَمِعْتُ رسول الله صلى الله عليه وسلم، يقولُ:  إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَحَمِدَ اللهَ فَشَمِّتُوهُ، فَإنْ لَمْ يَحْمَدِ الله فَلاَ تُشَمِّتُوهُ  [رواه مسلم] የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቺያለው በማለት አቡ ሙሳ(ረዲያላሁ አንሁ) አሰተላልፈዋል፦ ”ከእናንተ አንዳንቹ ሲያስነጥስ አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን በመመኘት መልሱለት። አላህን ካላመሰገነ አትመልሱለት።” [ሙስሊም ዘግቦታል] عن أَبي هريرة رضي الله عنه، عن النبيِّ صلى الله عليه وسلم،   قَالَ:  إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَلْيَقُلْ: الحَمْدُ للهِ، وَلْيَقُلْ لَهُ أخُوهُ أَوْ صَاحِبُهُ: يَرْحَمُكَ الله. فإذَا قَالَ لَهُ: يَرْحَمُكَ اللهُ، فَليَقُلْ: يَهْدِيكُمُ اللهُ وَيُصْلِحُ بَالَكُمْ  [رواه البخاري] አቡ ሁረይራ(ረዲያላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦ "ከናንተ አንዳቹ በሚያነጥስ ጊዜ 'አልሐምዱ ሊላህ' (ለአላህ ምስጋና ይድረሰው) ይበል፡፡ ወንድሙም 'የርሐሙከላህ አላህ ይዘንልህ) ይበለው፡፡ እርሱም መልሶ 'የህዲኩሙላህ ወዩስሊሕ ባለኩም' (አላህ ቅኑን መንገድ ይምራቹ፣ ጉዳያቹንም ያስተካክልላቹ)' ይበል፡፡ [ቡኻሪ ዘግበዉታል]
901Loading...
10
💫 ብቻቹን ትሞታላቹ ብቻቹን ወደ መቃብራቹ ትገባላቹ ብቻቹን ከአላህ ፊት ትቆማላቹ ሞት ያማል መቃብር ጨለማ ነው ጊዜው ከማለፉ በፊት ራሳችንን እናዘጋጅ።
740Loading...
11
🔎ዱኒያ ላይ ስትኖር  መልካሚስትን አልያም መልካም ጓደኛን ያዝ ...! ‏قال لقمان الحكيم لابنه:  يا بني ”أول ما تتخذه في الدنيا امرأةٌ صالحةٌ و صاحبٌ صالحٌ، تستريح إلى المرأة الصالحة إذا دخلت وتستريح إلى الصاحب الصالح إذا خرجت إليه.“ 📕 |[أدب النساء للٱلبيري - ١٣٨].
810Loading...
12
↷እራሷን በሒጃብና በአይናፋርነት የተሸፋፈነች ሴት፦ .       "ለአባቷ ኩራት፤       " ለወንድሟ ልቅና፤      " ለባሏ ያልተነካ ሐብት፤     " ለሴት ልጆቿ እና ለሙስሊም     "ሴት ልጆች መልካም ተምሳሌት ናት። .            •••⊰✿ ✿⊱••• . "እህቴ ሆይ! ከሱና አስተዳደግ ውጪ ተርቢያ "የተደረጉ ሴቶች አይሸውዱሽ.! የሓያእን ካባ የሚያለብስሽን ተክክለኛው ሒጃብ ልበሺ.!! NikabnewWbete
5434Loading...
13
ጃቢር ረዲየላሁ አንሁ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቻለሁ በማለት አስተላልፈዋል፡- "ለሊት ውስጥ አንዲት ወቅት አለች አንድ ሙስሊም ይህችን ወቅት አግኝቶ አላህን ከዚህችም ከመጭውም ዓለም ጉዳዮች አንዳች በጎ ነገር ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል። ይህች ወቅት በሁሉም ሌሊቶች ውስጥ ትገኛለች። ✍ሙስሊም ዘግበውታል @zewtr_allahn_enastaws
710Loading...
14
🌹ስትናደድ ብዙ አታዉራ ቃላቶችህን ቸቆጣጠር,ቃላቶች እንዲቆጣጠሩክ አታድርግ,ብዙዎቹ በተናደድንበት ቅጽበት የምንናገራቸዉ ቃላት በስተመጨረሻም ተናጋሪዋ ይጸጸታል። © @zewtr_allahn_enastaws
850Loading...
15
ከትልልቆቹም በላይ… ከአቢ በክራ (ረ.ዐ) ተይዞ፡ ከአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ዘንድ ሆነን ባለንበት እንዲህ አሉ፦ ﴿أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِأَكْبَرِ الْكَبَائِرِ - ثَلَاثًا - الْإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ قَوْلُ الزُّورِ،﴾ “ከትልልቆቹም ወንጀሎች የበለጡ የሆነውን ወንጀል አልነግራችሁምን? ሶስት ግዜ ደጋጋሙት። በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ መቁረጥና የሐሰት ንግግር ናቸው።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 87
890Loading...
16
አንድ ሰው ሰላት ከጨረሰ በኋላ "አላሁመ አንተ ሰላም ወሚንከ አሰላም ተባረክተ ያ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም" ሲል መልዕክቱ ምንድነው? ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:- "አንድ ሰው ይህንን ዚክር ሲል አላህ ሆይ ሰላቴን ሰላም አድርገህ የወንጀሌ መታበሻ እና ደረጃዬን ከፍ የሚያደርግልኝ እንድታደርግልኝ በዚህ በተከበረው ስምህ(አስ-ሰላም በሚለው) ወዳንተ እቃረባለሁ ማለቱ ነው።" [شرح رياض الصالحين ٤٩١/٥]
721Loading...
17
ለአላህ የምትነግሩት ነገር የላችሁም ¿¿ ብቻችሁን ከእሱ ጋር ብቻ የሚፈታ ሀጃ የለባችሁም እእ ታዲያ ለምን አትነግሩትም አንዴ ጠይቃችሁት አልተቀበለኝም ብላችሁ ነው¿¿ ህፃን ልጅ እኮ የሆነ ነገር ሲፈልግ እርይ ብሎ አልቅሶ የፈለገውን ያስደርጋል አላህ እኮ ሁሌ እኛን ሰሚ ነው አይሸሸንም አይመቸኝም አይለንም በወንጀላችን ብዛት እንኳን አያባረንም ራህመቱ እኮ ሰፊ ነው .... ሁልጊዜ ለኛ በሩ ክፍት እኮ ነው               
1023Loading...
18
አራት ሴቶች ልብን ያረጋጋሉ 🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን abu_fewzan_abdu_shikur
860Loading...
19
ወደኸኝ እንጂ አትውሰደኝ ! ወንጀሌ የበዛ የአላህ ባሪያ መሆኔ ሲታወሰኝ የወዳጅ ውዳሴም ሆነ የጠላት ዘለፋ  ከንቱ መሆኑ የበለጠ ፍንትው ብሎ ይታየኛል ! ፈጣሪየ አላህ ሆይ! የወንጀል ሸክሜ የገዘፈብኝ ደካማ ባሪያህ ነኝና ይቅር በለኝ ! በሰራሁት አትያዘኝ ! ቀልቤንና ስራየን አጽድተህልኝ እንጂ ሞቴን አታምጣው! ወደኸኝ እንጂ አትውሰደኝ ! Muhammed sirage
900Loading...
20
ሕይወታችንም፣ ሞታችንም፣ ደስታችንም፣ ሐዘናችንም፣ ጤናችንም፣ ሰላማችንም፣ ድክመታችንም፣ ጥንካሬያችንም ሁሉ ነገራችን በአላህ እጅ ነው፡፡ በሰው እጅ እንዳይመስላችሁ፡፡ አምላካችን ሆይ ድህነታችን ወዳንተ ነው፡፡ የምንከጅለው የምንመኘው ካንተ ነው፡፡ መልካሙን ሁሉ ዝነብልን፡፡
881Loading...
21
ለህይወትህ ስኬትን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን! ልብህ #ያረፈባትን ሴት አግባ! ምክንያቱም አይን ቀላዋጭ ነውና ብዙ ያምረዋል ልብህን አድምጥ የአንተ ሚስት ለአንተ ብቻ ቆንጆ ውብ  ልዕልት ናትና። @zewtr_allahn_enastaws
891Loading...
22
ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ ፦ " ከኢማን ቀጥሎ ልትደክምለት የሚገባው ትልቁ ነገር መልካም ጓደኛ ይሁን። መልካም ጓደኛ ምኗም እንደማይጣል መልካም ዛፍ ነው። በጥላው ትጠለላለህ። ከግንዱ ቤት ትሠራለህ። ከፍሬው ትመገባለህ።" @zewtr_allahn_enastaws
1001Loading...
23
#የሆነ ነገር ተመኝተህ እንደተመኘኸው የተሠጠህ እንደሆነ ቀደር ይባላል፤ አላህ ነዉና የሠጠህ ዉሰደው። የሆነ ነገር ተመኝተህ አብዝተህ አገኘዋለሁ የጠበቅከው እንደሆነ ሶብር ይባላል በመጠበቅህ ዉስጥ ሁሉ አጅር አለህና ጠብቀው ። የሆነ ነገር ተመኝተህ ከጠበቅከው በታች ሆኖ ከተሠጠህ ሳታጉረመርም ከተቀበልከው ያ ሪዷ ይባላል ፤ አላህ የወደደልህን በመውደድህ እንኳን ደስ ያለህ። @zewtr_allahn_enastaws
7055Loading...
24
የኩዌቱ ፀሐፊ ዐብደላህ አልጃረላህ አላህ ይዘንለት፡፡ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ 🌺🌺🌺🌱🌺🌺🌺🌺 - ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣ - ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡ 1- ልብሴን ያወልቃሉ፣ 2- ያጥቡኛል፣ 3- ይከፍኑኛል፣ 4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣ 5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣ 6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣ 7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡ ከነኚህ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡ 8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል - ቁልፎቼ - መጽሐፎቼ - ጫማዎቼ - ልብሦቼ ….. በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ - በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣ - የዓለም እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣ - የኢኮኖሚው ቀውስም አልተፈጠረም፣ - በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣ - ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣ - ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤ - ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል - ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤ ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! … በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ 1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ 2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣ 3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣ የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!! 1- መልክህ፣ 2- ሀብትህ፣ 4- ጤናህ፣ 5- ልጅህ፣ 6- ቪላህ፣ 7- ዝናህ፣ 8- ሚስትህ/ባልሽ ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡ እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ 1- በግዴታዎች፣ 2- በሱንና ነገሮች፣ 3- በድብቅ መፅውት፣ 4- መልካም ሥራ አብዛ፣ 5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣ ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡ መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡ ምንጭ ፡ ጠሪቁ ተውበህ
1063Loading...
25
እንደማታገባት ጠንቅቀክ እያወቅክ አትቅረባት! ራስህንም እርሷንም አትጉዳ አሏህ እስኪያገራልህ ራስህን አቅብ! የጌታህን ክልከላ አትዳፈር! @zewtr_allahn_enastaws
790Loading...
26
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ 7 ከንቱ ምኞቶች‼ ============================= ①💫🌸 يَا لَيْتَنِي كُنْتُ تُرَابًا النبأ- (40) ①) «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!» [አ-ን'ነበእ: 40] ②💫🌸 يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي الفجر-(24) ②) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ!» [አል-ፈጅር: 24] ③💫🌸فَيَقُول يَا لَيْتَنِي لَـمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ الحاقة(25) ③) «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!» [አል-ሐቀህ: 25] ④💫🌸 يَا وَيْلَتَى لَيْتَنِي لَـمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا الفرقان (28) ④) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!» [አል-ፉርቃን: 28] ⑤💫 يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ يَقُولُونَ يَا لَيْتَنَا أَطَعْنَا اللهَ وَأَطَعْنَا الرَّسُولَا الأحزاب (66) ⑤) « ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!» [አል-አሕዛብ: 66] ⑥ 💫🌸يَقُولُ يَا لَيْتَنِي اتَّخَذْتُ مَعَ الرَّسُولِ سَبِيلًا الفرقان (27) ⑥) «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!» [አል-ፉርቃን: 27] ⑦ 💫🌸 يَا لَيْتَنِي كُنْتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا النساء (73) ⑦) « ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አ-ን'ኒሳእ: 73] ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው። ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል! ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም።  ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን። 📮👌قال رسول الله ﷺ الدال على الخير كا فاعله 📮👌ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው ረሱል ﷺ‼
880Loading...
27
መልካም ሚስት ይፈልጋሉ? "መልካም ሴት በአንተ ጥረት አትመጣም ይልቁንም ጌታውን ለሚፈራ ሰው የተሰጠች ርዝቅ ናት።" ርዝቅህን ከአሏህ ጠይቅ !
751Loading...
28
አንዳንድ ጊዜ ህይወት በትንሽ መከራ አትፋታክም ፤ በትንሽ ፈተና አትጠግብክም ፤ላይ በላይ ትኮረኩምሃለች  ይህ ሰው ከዚህ በፊት ያየው መከራ ይበቃዋል ብላ አትተውህም ሁለት ሶስት ጊዜ ትሰብርሃለች ዘመንህን  በሙሉ አንተ ማየት የማትፈልገውን ደጋግማ ታሳይሃለች ፤ ለመከራ ነው እንዴ የተፈጠርኩት እስክትል ድረስ አፈር ታስልስሃለች....... ዱንያን ጀሊሉ ሲፈጥራት እንዲሁ ነች በድርጊቷ ብዙ አትዘን........ የሚገርመው ነገር አንተ ምንም ሆንክ ምንም ከመሄድ አትቆምም ፤የቱንም ያክል ችግር ቢደርስብክም አታዝንልክም ፤ ለአፍታ እንኳን ዞር ብላ አታይክም መጎዳትክን አታስተውልም፤ለብሶትህ ጆሮ አትሰጥም ፤ ለሀዘንህ አትቆዝምም ፤ለሞትህ የሃዘን ቀን አታውጅም፤ አንተ ተጎዳህ ብላ ላንተ አዝና ፀሐይ ብርሃኗን ከመስጠት አትወገድም፤ጨረቃ ፊቷ አይጠቁርም ፤አንተ በህይወት ብትቀጥልም ባትቀጥልም እነሱ ጉዳያቸው አይደለም........... እናማ በተጎዳክ ጊዜ ሁሉ ራስክን አክም ፤በተሰበርክ ጊዜ ሁሉ ራስክን ጠግን ፤ በወደቅክ ጊዜ ሁሉ ተነስ በምንም መልኩ አትስነፍ ተስፋ አትቁረጥ ፤የዱንያን ባህሪ ጠንቅቀህ እወቅ ፤ከነ ቁስልህ ተራመድ ........
5294Loading...
29
ኢብኑል ቀይም •••••• በአላህ እምላለው አንድ ሰው ሱጁድ ላይ በሚሆን ጊዜ ምን ያህል  የ አላህ እዝነት እንደሚሸፍነው ቢያውቅ ኖሮ ግምባሩን ከመሬት ባላነሳ ነበር
980Loading...
30
ዒልም እና  ፂም ▪️ፂም የወንድ ልጅ ጌጥና መለያ ነው። ▪️መላጨቱም ከከባባድ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው። ▪️ፂምን መላጨት ከሴት ጋር መመሳሰል በመሆኑ የአላህንና የመልእክተኛውን እርግማንም የሚያስከትል ተግባር ነው። ደጋግ ቀደምቶች በተፈጥሮ እንኳ ፂም የሌለውን ሰው የዒልም መድረካቸው ላይ ተቀምጦ እንዲማር አይፈቅዱም ነበር! 🔅አል-ኢማሙ ማሊክ "ሙርድ" የሚባሉ  ፂም አልባ ወጣቶች እሳቸው ሒዲሥ ሲያስተላልፉ እንዲታደሙ አይፈቅዱም ነበር። አንዴ ፂም አልባ በመሆኑ የሚታወቅ ሂሻም የሚባል ሰው በሰዎች መሃል ተደብቆ ገብቶ 16 ሐዲሥ ከሳቸው ከሰማ በኋላ ለኢማሙ ሲነገራቸው 16 ጅራፍ ገርፈው አስወጡት። እሱም ምናለበት ከእርሳቸው 100 ሐዲሥ ሰምቼ 100 ጅራፍ በገረፉኝ! ይል ነበር። ማሊክ "ረሑመሁላህ" (ይህ እኛ ከፂማሞችና ከታላላቆች የተቀበልነው ዒልም ነው፤ ከእኛም ልክ እንደነሱ ያሉ ሰዎች -ፂማሞች እንጂ መውሰድና መቀበል አይችሉም!) ብለዋል። 📚መጅሙዕ አል-ፈታዋ 15/375 ▪️በተፈጥሮ ፂም ለሌላቸው ይህ ከተባለ በየቀኑ በምላጭ አርግፈውት ለመማርም ይሁን ለማስተማር የሚቀመጡ ምን ሊባሉ ነው?! ✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     ሸዕባን 10/8/1445.ዓሂ @ዛዱል መዓድ
1051Loading...
31
🚫 ወንድሜ የሴትን ልጅ ፈተና ተጠንቀቅ❗ ኮፒ የሴት ልጅ ፈተና ልክ እንደዚህ ታሪክ 👇 ከሱና ሊያንሸራትትህ አልፎም ዲንህን ሊያስቀይርህ ይችላልና ተጠንቀቅ። ታሪኩ እንዲህ ነው:- በግብፅ ከተማ ውስጥ አንድ ከመስጂድ የማይጠፋ መስጂድን በአዛን በሷላት አጥብቆ የሚይዝ ሙዓዚን ነበረ። በርሱም ላይ ጥሩ ለዲኑ መታዘዝና የኢባዳህ ብርሃኖች ይታዩበት ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ ሚናራህ ወጣ ታዲያ አዛን ላይ ሳለ ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ አንዲትን እንስት ይመለከታል፡፡ ወዲያውኑ በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቅና፣ በፍጥነት እርሷ ወዳለችበት ቤት ሄዶ ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች። እሱ ፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው የምፈልገው❗️ እሷ ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"ብላ ጠየቀችው እሱ ፡- "ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን መሰባሰቢያ ይዘሺዋል" አላት እሷ ፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ ልልህ አልችም አለቸው እሱ ፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት እሷ ፡- "አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ (ክርስቲያን) ነኝ አባቴ           ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም" አለችው እሱ ፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት እሷ ፡- እንደዛ ያደረግክ እንደሆን እኔም ፍቃደኛ ነኝ አለችው ከዚያም ይሄ ሰው እሷን ለማግባት ሲል ነሳራ (ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት ተቀመጠ፣ ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወድቆ ወዲያውኑ ህይወቱ አለፈች። እሷንም እስልምናውንም አጥቶ በኩፍር ላይ ሞተ ። ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይል ነበር :- "አላህ አንድም ነብይ አልላከም ሸይጧን በሴት ፈተና ሲያጠፋቸው ከነርሱ ላይ ተስፋ ባይቆርጥ እንጂ" 📚 [መውሱዓቱ ሊብኒ አቢ ዱንያ 4/540] አልሀሰን ኢብኑ ሷሊህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ሲል ይናገራል :- ሸይጣን ለሴት ልጅ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ "አንቺ የኔ ግማሽ ጎኔ ነሽ፣ እኔ በአንቺ የምወረውርብሽ ቀስቴ ነሽ፣ ደግሞም ባንቺ ከወረወርኩ አልስተም፣ አንቺ የሚስጥሬ ቦታ ነሽ፣ አንቺ የኔ የጉዳዬ መልዕክተኛ ነሽ" 📚 [መውሱዓቱ ሊብኒ አቢ ዱንያ 4/539] የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል "ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ የሆነ ፈተና ከኋላዬ አልተውኩም" 📚 [ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል ] ወንድሜ ከእንዲህ አይነት ፊቲና አላህ ይጠብቀን 🤲 [አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ ሊብኒ አልቀይም : ገፅ-167]
1081Loading...
32
Media files
900Loading...
33
‍ 🔰 ተስፋ አለኝ የትላንቱ ክፍተት - የዛሬው ቀዳደ ኋሊት የሚኖር - ነገን እያቀደ የመሸ ይመስለኛል - ጎኅ እየቀደደ ብሮጥ ብሮጥ አያልቅ የህይወት ሜዳ ውስጤ ይሀው አለ - እኔን እየጎዳ ዛሬን እሰጣለሁ - ለትላንትናው እዳ ያለፈው ታሪኬ - በትዝታ ተሞልቶ ዛሬም ትላንት ሆነ - ነገን አስረስቶ ትዝታ አርጌው - ትላንት አርፍዶብኝ በተስፋ ስባንን - ዛሬ ቀደመኝ ትላንትን ትዝታ - ዛሬን ምን ልበለው? እኮ አልታየኝም - ከትላንት አንድ ነው። የትላንት ትዝታ - ታሞብኝ በጠና አሁንም ቆሰለ - ዛሬም እንደገና ነገን ደገመ - እዩ ይሀውና አለሁ እስከዛሬ - በቆሰለ ትላንትና። ዘመን ሲለዋወጥ - ጊዜም ሲቀያየር በኛ አልተጀመረ - መከፋት መቸገር እንዲህ ነው ነገሩ - የህይወት ስንክሳር ደምረን ብንቀንስ - ብንቀምር ቀመር አካፍለን ብናባዛ - ማስተዋል ብንጀምር ኮድ ሆነ ከረመ - የኑሮ ሚስጥር። በተስፋ እየኖርኩ ነው - ጠይቆኛል ፓስዋርድ ውስጤ ሆይ ቻለው - እባክህ አትናደድ ኮዱን ካገኘሁት - ላገላብጥ ሰነድ። ብንዘፈቅ በድህነት - ምንም ባይኖረንም ጠንካራ ማንነትን - ዝቅ አያረግብንም ምንም ቢሞላለት - ሀብታምም ቢሆን ከፍ አያረግም - የሰው ወራዳነትን በቃ አዲስ ነገር የለም - ህይወት እንደዚህ ናት ደስታና ሀዘን - የተፈራረቀባት ሳቅና ለቅሶ - በአንድ የኖረባት ክፋቷ ያመዘነ - ያጠፋች ደግነት በአዋጅ ፈቀደች - የክፋትን ጥግነት ታዲያ ምኑነው አዲስ - ሁሌም ይኖራላ ሀዘንና ደስታ - ይቀያየራላ ለአንዱ ሲሞላለት - ለአንዱ እየጎደለ ሳይስቅ ሳያለቅስ - የሚኖር መች አለ!? ለአንዱ ሲሞላለት - ለአንዱ እየጎደለ ሳይቸገር ሳይከፋ - የሚኖር መች አለ!? በቃ ሰው ራቅኩኝ - እንደው በደፈና ውስጤን አሳዘነው - ትዝታ መጣና ማለፍ ቢያቅተኝ - የህይወት ምዘና በቃ ሰው ጠላሁኝ - እኔም ሰው ሆንኩና ግን ስሞታ አበዛሁ - እኔም ሰውነኝና ሽሽት ሽሽት አለኝ - ግን ወዴት ይሸሻል ያው ህይወት ህይወት ነው - ይነጋል ይመሻል ሰውም እንደዘበት - ይቀርባል ይርቃል እኮ ወዴት ልሽሽ - ውስጤ ይጨነቃል አንድ ፈጣሪ ግን - መድረሻዬን ያውቃል የሰው ልጅማ - ውስጥን ያሳምማል ድህነትህን ሲዘክር - አንገት ያስደፋሃል የሰው እርዳታ አልሻም - እባካችሁ ተውኝ መኖር እችላለሁ - ምንም ሳይኖረኝ መክንያቱም ይህ ነው - በአላህ ተስፋ አለኝ መክንያትህ ላለኝ - በአላህ ተስፋ አለኝ!    ✍ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል መስከረም 30/2012[Oct 11/2019] ▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ ማሳሰቢያ: ግጥሙ በመልዕክቱ ሰዎችን ማስተማር እንጂ የኔን የግል ህይወት (ንዴትና ቁጭቴን) ለመግለፅ የተፃፈ አይደለም!
973Loading...
34
ሔር-ባንድ ምንድነው? ሔር-ባንድ ማለት አሁን ባለነበት ግዜ ብዙ ሙስሊም ሴቶች ፀጉራቸው ላይ የሚደርቡት ሒጃባቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው የሚሰቅሉበት ዘመን አመጣሽ ጨርቅ ነው።በርግጥ ሙስሊም ሴቶች ብቻ አይደለም የሚጠቀሙት።አልፎ አልፎ ሌላ እምነት ተከታዮችም ሲጠቀሙት ይታያል።ነገር ግን በሙስሊሞቹ ላይ በቢዛት ይታያል።ምክኒያቱም የሌሎች እምነት ተከታይ ሴቶች ፀጉራቸውን ገልጠው እንደፈጉት ለሰው እይታ ስለሚታይላቸው ወደ ታችም ለቀው ወደ ላይም ሰቅለው በግልፅ ማሳየት ይችላሉ።ስለዚህ ሔር-ባንዱን ለመጠቀም ብዙም አይጨነቁም።የኛ እህቶች ግን ፀጉራቸውን በሒጃባቸው ስለሚሸፍኑትና ጎላ ብሎ ስለማይታይላቸው ግዴታ ጨርቅ እየጠቀለሉ ወይም ሔር-ባንድ በመጠቀም ወደ ላይ ካልቆለሉት ፀጉር ያላቸው አይመስላቸው ስለዚህ በብዛት የሔር-ባንድ ተጠቃሚ ሙስሊም እህቶቻችን ሁነው ተገኙ። ሔር-ባንድ መጠቀም በኢስልምና መነፅር፦ ሔር-ባንድ መጠቀም በኢስልምና በሁለት መንገድ ሐራም(ክልክል)ነው።ለዚህም ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። 1ኛ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ  ወሰለም) በአንድ ወቅት ላይ ወደ ገበያ ሄደው ገበያ ላይ ዞር ዞር ሲሉ አንደ እህል ሻጭ እህሉን በጆኒያ ሰፍሮ ቆሟል ከዛም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ክንዳቸውን ሰበሰቡና እጃቸውን  ወደ ውስጥ አስገቡት።ከዛም እርጥበት የነካውን እህል በጃቸው ዘገኑና "ለምንድነወ በአንድ ጆኒያ ላይ እርጥቡን ከውስጥ አድርገክ ደረቁን ከላይ ያደረግከው?"ማለትም ያው መቼም ሰው ያየውን ስለሆነ አምኖ የሚገዛው ሰዎች ከላይ ደረቁን አይተው ከታች እርጥብ መሆኑን አያውቁምና ሙሉ ጆኒያውን ገዝተው ይሄዳሉ።ስለዚህ እንዴት ሰውን ታታልላለህ? የገዘ ሊገዛ የተወ ሊተው እንዴት እርጥቡን በግልፅ እያሳየክ አትሸጥም?ደረቁን ከላይ አስመስለክ እርጥቡን ከስር ደብቀክ ትሸጣለክን?ማለታቸው ነው።ከዛም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦"መን ገሸና ፈለይሰ ሚንና(ያተለለን ከኛ አይደለም)"ብለው አሉት።ከዚህ ሐዲሥ በግልፅ የምንረዳው ነገር አንድ ሰው ከላይ ሌላ ነገር እያሰየ ከውስጥ ግን በተቃራኒ ከሆነ ገሽ(ማተለል)ነው ማለት ነው።አንድ ሰው አታላይ ከሆነ ደግሞ ከነብ አይደለም።ይሄው ነብዩ በግልፅ ያታለለ ከኛ አይደለም እያሉ ነው።እሺ ይህንን ሐዲሥ ከተረዳን ወደ ሔር-ባንዱን ስለመልበስ በሐዲሡ አንፈትሸው። እህቴ ሆይ? አንቺ አላህ በሰጠሽ ፀጉር ትንሽም ትሁን አመስግነሽ መኖር ያቃተሽ ዊግንና የመሳሰሉትን አርቴፊሻል ፀጉር ለፀጉርሽ መቀጠል አይቻል።ዊግ የተጠቀመችን ሴት ነብዩ ረግሟታል ስትባይ አሁን ደግሞ "አልሸሹም ዞር አሉ" አይነት ነገር ውስጥ ገብተሻል።አንቺ የሌለሽን ፀጉር ያለሽ ለማስመሰል ዊጉን ስትከለከይ የተለያዩ ዘመን አመጣሽ ጨርቃ ጨርቅ እየለጠፍሽ እንቶ ፈንቶ ጎትተሽ መጣሽ?ወላሂ እመኚኝ አታላይ ነሽ!ቅድም በሐዲሡ እንዳየነው የሌለውን ያለ ማስመሰል ከላይ ሌላ ከውስጥ ሌላ መሆን ገሽ (ማታለል) ነው።አንቺ ከውስጥ የሌለሽን ያክል ፀጉር ከላይ ጨርቅ ከምረሽ ፀጉር ያለሽ ለማስመሰል መጣጣር ይቅርብሽ።"አይ አይቀርብኝም"ካልሽ ደግሞ በቃ ከነቢዩ ላለመሆንሽ እርግጠኛ ሁኚ። 2ኛው ሀዲሥ፦ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደፊት ስለሚመጡ ሸረኛ ሴቶች አላህ በራህመት አይኑ የማያያቸው ብለው ባህሪያቸውን ሲያብራሩ ከጠቀሱት አንዱ "ፀጉራቸውን እንደ ግመል ሻኛ ወደ ላይ ከፍ አደርገው ይቆልሉታል"ነበር ያሉት።ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ተመልከቺ ምን ያክል እንደተዛተብሽ።ዛሬ አንቺ ረጅም ፀጉር ይኑርሽም አይኑርሽም ጨርቃ ጨርቅ ላቃቅመሽ ወደላይ መቆለልሽ በቀላሉ ከአላህ ራህመት እራቅሽ መሆኑን አትጠራጠሪ።ከአላህ ራህት ርቀሽ  በማን ራህመት ስር እንደ ምትሆኚ ደግሞ አስቢበት የቤት ስራ ሰጥቼሻለሁ።"ምነው አካበድክሳ አላህ እንዳንተ አይደለም መሃሪ ነው"ምናም ብለሽ ደግሞ የተለመደውን "ማስተኛ መርፌ" እራስሽን አትውጊ።እኔም  ምንም   ያካበድኩብሽ ወይም ከራሴ ያመጣሁብሽ አዲስ ነገር የለም።ሐዲሥ ነው የነገርኩሽ።ልቦለድ አልፃፍኩልሽም። ምናልባት "ሔር-ባንዱን ፀጉር ማሳዥያ ብለን እንጂ ሌላ ፈልገንበትኮ አይደለም" ልትይኝ ትችያለሽ።ለፀጉር ማሳዝ ከተፈለገማ ድሮ እህቶች ሲጠቀሙት የነበረ ትንንሽ በየ ሱቁ የሚሸጥ ፀጉር ማሳዣም አለ።ኧረ ለምን ሌላ በቀላሉ በብር ላስቲክ ስትጠቀሚ አልነበረም?ዛሬስ የሚጠቀም የለም?ምን አዲስ ነገር አለው?ፀጉርሽን ሰብስቦ ሊይዝልሽ ካልሆነ በቀር።"እንዴት በሰለጠ ዘመን የብር ላስቲ ምናምን ትላለክ?"ልትይኝ ትችያለሽ።አዎ እልሻለሁ!ኧረ እንደውም ለምን በቁራጭ ገመድ ፀጉርሽን አትሰበስቢም!ምክኒያቱም ይህ ነው ላንቺ የሰላም ቀጠና።ከአላህ በራህመት አይን ከመራቅ መቶ በመቶ  የብር ላስቲክ ይሻልሻል።የተፈቀደን ነገር ለክብርሽ "አልመጠነኝም" ብለሽ ወደ ሀራም መሄዱ ትልቁን ክብር ማጣት ይህ ነው የሚሆነው።መቼም እርግጠኛ ነኝ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ቢራ ሲጠጡ ብትመለከቺ ይህ ሰው ሁሉ ቢራ እየጠጠ እየተዝናና እኔ ውኃ መጠጣቴ ሼም ነው።ዘመናዊነትንም ማጣት ነው ብለሽ ቢራ አታዢም አይደል?ሺ ግዚ ዘመናዊ አይደለችም ይበሉሽ እንጂ አቅልሽ ካልደነዘዘ በቀር አይንሽ እያየ ቢራ ገዝተሽ አትጠጪም አደል? ልክ እንደዚሁም ብዙ ሴቶች ሔር-ባንድን ስለተጠቀሙ እኔ እንዴት ፋሽኑ ባለፈ ፀጉር ማሳዣ እጠቀማለሁ ወይም እታች ወርጄ በብር ላስቲክ እጠቀማለሁ ብለሽ ሌሎች የተጠቀሙት ጨርቅ ካልጠቀለልኩኝ ካልሽ የአስተሳሰብ ድንዙዝነት አለ ማለት ነው።ከዚህ ድንዛዜ ደግሞ ማገገም አይቻልም  ዲንን በመማር ቢሆን እንጂ።ስለዚህ አደራሽ ያለ መታከት ዲንሽን በቅጡ ተማሪ።ነገ ከነገ ወዲያ ሳትይ አላህን ፈርተሽ በላይሽ ላይ ያለውን ዘመን አመጣሽ ድርሪቶ አውልቀሽ ጣይ። አደራ ለአላህ ብላችሁ ሼር ማድረግን እንዳትረሱ።ወላሂ ብዙ እህቶች እዚህ በሽታ ላይ ናቸው።
1104Loading...
35
~ሪዝቅን የሚያመጡ  አራት ነገሮች!! ➷የለሊት ሶላት ➷እስቲግፋር ➷ ዚክር እና ➷ ሶደቃ ናቸው። @zewtr_allahn_enastaws
902Loading...
36
“አብዛኞቹ ሰዎች ኃጢአት የሚሠሩት የአብዛኞቹ ሰዎች ኃጢአትን በመጥቀስ ነው።” ✍ኢብኑ ሢሪን ኢላሂ! አንደበታችን የሰው ነውር ከመጥቀስ ጠብቅልን። አንተን በመዘከር የምትንቀሳቀስ አድርጋት።🤲
970Loading...
37
ህጻናትን ከቤት ወደ ሌላ ስፍራ ይዘናቸው ስንወጣ በሰውና በጂንኒ አይን (አይነ-ናስ ወል-ጂን) እንዳይለከፉ ቀጥሎ ያለውን ዚክር አናታቸውን በመያዝ እንበል፡-  1. አንድ ህጻን ብቻ ከሆነ፡- ‹‹ኡዒዙከ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ፣ ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ፣ ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ››  2. ሁለት እና ከዛ በላይ ከሆኑ፡- ‹‹ኡዒዙኩማ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ፣ ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ፣ ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ››  (ቡኻሪና አቡ ዳዉድ)፡፡  የዚህ ዚክር ትርጉም፡-  1. ‹‹አዒዙከ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ›› ማለት፡- ሙሉ በሆነው የአላህ ቃላት እጠብቅሀለው ማለት ነው፡፡ ወደ አንድ መንደር ወይም ቤት ሲገባ ‹‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ-ታምማቲ ሚን ሸርሪ ማ-ኸለቅ›› ያለ ሰው፡ ያንን ቤት እና መንደር ለቆ እስኪወጣ ምንም እንደማይደርስበት በሌላ ሐዲሥ ተነግሮአል፡፡  2. ‹‹ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ›› ማለት፡- ከሸይጧናትና ከመርዛማ ገዳይ ነገራት (ሙሉ በሆነው የአላህ ቃል እጠብቅሀለሁ) ማለት ነው፡፡  3. ‹‹ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ›› ማለት፡- ከክፉ አይኖች በጠቅላላ (ሙሉ በሆነው የአላህ ቃል እጠብቃለው) ማለት ነው።
86229Loading...
38
አንዳንድ ድንቅ እና ክቡር ሰዎች በድህነታቸውም፣በጭቁንነታቸውም፣ በርሀባቸውም በምንም ጊዜያቸው የትም ሆነው የትም፣ ምንም ሆኑ ምንም፣ማንም ጥሏቸው ይሂድ ብቸኝነታቸውን የሚያጋሩት ለብቸኛ ፈጣሪያቸው አላህ ብቻ ነው።
862Loading...
39
እምቢ በይ እታለም! (ከካፊር ጋር ትዳር ለሚያስቡ እህቶች) ለአላፊ ደስታ ስትይ ………. ለምትከስመው ጠውልጋ ትዳር ከምትመሰርቺ ………. ኢስቲንጃ ከሌለው ጋ ለዚች ጤዛ ዱንያ ብለሽ ………. ብልጭ ብላ ለምትጠፋ ከለጋሱ ጌታ ዘንዳ ………. ከትንኝ ክንፍ ለማትሰፋ እያለቀስን መጥተን ሳለ ………. እያለቀስን ለምንለቃት አኺራችንን አስበን ………. ምናለ ብንንቃት?!! እቱ ከጌታችን ጋራ ………. ነገ ከባድ ሂሳብ አለ አስፈሪ ጭንቅ የሚያይበት ………. መናጢ ሁሉ ያልታደለ ዛሬን ከመስመር ለቆ ………. ወደ ጥፋት ያጋደለ ከእርኩሳን ጋር ተጣምሮ ………. በክህደት ላይ የዋለለ ነገን በዛሬ የሸመተ ………. የዋህ እራሱን ያታለለ “ያ ለይተኒ” የሚልበት ………. ነገ የቁጭት ቀን አለ፡፡ ይልቅ ስሚኝ እህት አለም፡ ትዳር የጌታ ሲሳይ ነው ………. ከባለ ዐርሹ የሚወሰን ስለቋመጥን ሳይሆን ………. ፈቃዱ ሲኖር የሚደርሰን “ይታደሉታል እንጂ ………. አይታገሉትም” ነው ነገሩ ውሳኔው ከላይ እስከሚወርድ ………. ከዱዓህ ጋር ይሶብሩ፡፡ እንጂ ከእንጨት አምላኪ ጋ እንጂ “አንድም ሶስትም” ከሚል ዜጋ በስሜት ናላው ዞሮ ………. ሊያጠምድሽ መረብ ቢዘረጋ ማር በሚተፋ ምላሱ ………. በስልት ወዳንቺ ቢጠጋ ምናባዊ ሐሴት አይተሽ ………. ጉም ለመጨበጥ መንጠራራት ለተስፋ ዳቦ እየቋመጥሽ ………. አትሁኚ የ’ሳት እራት፡፡ በምታይው ብልጭልጭ ………. እራስሽን አትደልይ ባለ ገዳይ መርዙ እባብም ………. ለስላሳ ነው አስተውይ፡፡ ይልቁንም ረጋ ብለሽ ………. ከአፅናፍ ማዶ ተመልከቺ ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ………. ለተኩላ አትረቺ ለዚች አጭር ህይወት ስትይ ………. በራስሽ ላይ አትሸፍቺ፡፡ ለዚህ ብላሽ ፈራሽ ገላ ለዚህ ከንቱ ገልቱ አተላ ዛሬ እጅሺን አትዘርጊ ነገ እንዳትጠወልጊ፡፡ ሶላት ቁርኣኑ ተትቶ ሒጃብ አደቡ ተዘንግቶ በላኢላሀ ኢለላህ ቦታ ………. “አንድም ሶስትም” ተተክቶ ግንባር ለመስቀል ሲዋረድ ………. የሐያሉ ሱጁድ ቀርቶ ከቤትሽ ግድግዳ ላይ ………. የፈረንጅ ስእል ተለጥፎ ሐያእ ግብረ-ገብነትሽ ………. ከላይሽ ላይ ተገፎ ከግንባርሽ ላይ ነጥፎ ………. ከልብሽ ላይ ተንጠፍጥፎ መስጂድ የለመዱ እግሮችሽ ………. ወደ ከኒሳ ሲያመሩ ጠላ ኮረፌ እየጠመቅሽ ………. ሰካራሞች ሲያጓሩ ይሄ እውን የሆነ እለት ያኔ ሆነሻል የቁም ሙት!! .   ✍(ኢብኑ ሙነወር) ሀፊዘሁሏህህህህ
892Loading...
🌴ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡- ❝ተውበት ያደረገ ሁሉ የአላህ ተወዳጅ ባሪያ ነው።❞ 📚جامع الرسائل 116/1 ══════ ❁ ══════
نمایش همه...
🌴አውን ቢን አብደላህ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ፡- ❝የተውበተኛ ልብ እንደ ብርጭቆ ነች  በውስጧ የሚደርሰው ነገር ሁሉ ተፅዕኖ ያሳድርባታል  የአላህ ተግሳፅ ወደ እርሷ በደረሰ ጊዜ    ወደ ተውበት ፈጣን ጥሪ ያደርግላታል  ምክንያቱም ተውበት ለቀልብ መደሃኒቷ ነው ኃያሉ ጌታዋም ተውበትን ተቀባይ ነው  ተውበትም ወደ ጀነት ጥሪ ታደርጋለች ጀነትን እስከምትገባ ደረስ ከሚፀፀቱ ሰዎች ጋር ተቀመጥ የአላህ እዝነት ለእነርሱ በጣም የቀረበ ነውና።❞    📚صفة الصفوة (٧٠/٣) ══════ ❁ ══════
نمایش همه...
ተክቢረቱል-ኢሕራም የጓደኛ መመዘኛ የታላቁ ሰሓቢይ ኢብኑ መስዑድ رضي الله عنه ልዩ ደረሳና ቅርብ ሰው የሆኑት ታላቅ ታቢዒይ ኢብራሂም አን'ነኸዒይ እንዲህ ይላሉ፥ "አንድን ግለሰብ ተክቢረተል- ኢሕራም (የሰላት መክፈቻ የመጀመሪያው ተክቢረህ) ላይ የሚዘናጋ -ቀድሞ ሶፍ ላይ ተዘጋጅቶ ቆሞ አሰጋጅ አላሁ አክበር እንዳለ ወዲያ ተከትሎ ተክቢር የማያደርግ- ሆኖ ካገኘኸው (ጭቃና መስለ ቆሻሻ እጁን የነካው ሰው እጁን ታጥቦ ከጭቃው እንደሚርቀው) ከዚህ ግለሰብ ራቅ!" 📚አል-ሙኽታር ሚን መናቂቢል አኽያር 1/281።   🔅በዚህም መሰረት ሁሌ ኢቃም ሲሰሙ እንጂ ከቤትና ከሱቅ መቀመጫዎቻቸው የማይነሱ ኋላ ቀሮችን በሙሉ እጅህን ታጥበህ ዳግም ላትነካቸውና ላትቀርባቸው ራቃቸው፤ ተስፋ እስካልቆረጥክ ድረስ ለመምከር ካልሆነ በስተቀር መቼም ተመልሰህ አታግኛቸው።   🔅ኢቃም ተብሎ እየተሰገደ ከመስጂድ ዙሪያ ቆመው ስልክና ሰው የሚያወሩትንም እዚሁ ውስጥ አካታቸው። 🔅 መስጂድ በረንዳ ውስጥ፣ ከዛም አልፎ ወደ ውስጥ ገባ ብለው ከኢማምና መእሙሞች ጀርባ ላይ ቆመው ሰጋጆችን እየረበሹ ውጪ የጀመሩትን የእርሰበርስ ወሬ ወይም ስልክ ከተክቢረተል ኢሕራምና ከሰላት የሚያስበልጡትንም መክረህ አስጠንቅቀህ ካልተመለሱ አብዝተህ ራቃቸው። 🔅ዲኑን በሚገባ የማያከብርና ለሰላት ቦታ የሌለው ላንተ ምንም አይጠቅምህምና!   ✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 7/5/1444 ዓሂ  
نمایش همه...
#ያኔ ፀሐይ በስንዝር ልክ በምቶንበት ቀን ሰዎች ላባቸው በወንጀላቸው ልክ በሚደፍቃቸው እለት ከአሏህ አርሽ ጥላ ስር መሆን ከፈለክ "ወጣትነትህን በመልካም ነገር አሳልፍ".
نمایش همه...
00:30
Video unavailableShow in Telegram
نمایش همه...
💥ድንቅ ንግግር❗️ ✍      ወንድምህ ከረሜላ ስጦታ ሲሰጥህ መመልከት ያለብህ የከረሜላውን ዋጋ ሳይሆን ወንድምህ ልብ ውስጥ ያለህን ዋጋ ነው!   /ኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ /     [የሱረቱ አዝ-ዘልዘለህ ተፍሲር ደርስ ላይ የተወሰደ]
نمایش همه...
🤲 ያ አላህ  የውስጡን ሃጃ መግለፅ አቅቷቸው  ኢላሂ ያሉ  ሰዎች  ሁሉ  ሀጃውን አሳካላቸው ኢላሂ!! ከለመኑህ በላይ አብዘተህ የምትሰጥ ተጣሪን የምሰማ ለባሪያወችህ ቅርብ ምህረትህ የሰፋ እዝነትህ የላቀ     ለምነውህ የምትሰማ እዝነትህን ከጅለው ለተማፀኑህ  ቅጣትህን ፈርተው ወዳንተ ያረብ ላሉ ባሪያዎችህ ሁሉ የልባቸውን ጭቀን አቅልልላቸው ያ አሏህ🤲 @zewtr_allahn_enastaws
نمایش همه...
ውዱዑን አሳምረህ አድርግ! ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦ “ውዱዑ አድርጎ ውዱዑን ያሳመረው ሰው፤ ኃጢአቶቹ ከጥፍሮቹ ስር እንኳ ሳይቀር ከአካላቱ ይወጣሉ።” ሙስሊም ዘግበውታል: 245 @zewtr_allahn_enastaws
نمایش همه...
ያስነጠሰ ሰው አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን ለምኑለት! ካላመሰገነ ግን... وعن أَبي موسى رضي الله عنه، قَالَ: سَمِعْتُ رسول الله صلى الله عليه وسلم، يقولُ:  إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَحَمِدَ اللهَ فَشَمِّتُوهُ، فَإنْ لَمْ يَحْمَدِ الله فَلاَ تُشَمِّتُوهُ  [رواه مسلم] የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቺያለው በማለት አቡ ሙሳ(ረዲያላሁ አንሁ) አሰተላልፈዋል፦ ”ከእናንተ አንዳንቹ ሲያስነጥስ አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን በመመኘት መልሱለት። አላህን ካላመሰገነ አትመልሱለት።” [ሙስሊም ዘግቦታል] عن أَبي هريرة رضي الله عنه، عن النبيِّ صلى الله عليه وسلم،   قَالَ:  إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَلْيَقُلْ: الحَمْدُ للهِ، وَلْيَقُلْ لَهُ أخُوهُ أَوْ صَاحِبُهُ: يَرْحَمُكَ الله. فإذَا قَالَ لَهُ: يَرْحَمُكَ اللهُ، فَليَقُلْ: يَهْدِيكُمُ اللهُ وَيُصْلِحُ بَالَكُمْ  [رواه البخاري] አቡ ሁረይራ(ረዲያላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦ "ከናንተ አንዳቹ በሚያነጥስ ጊዜ 'አልሐምዱ ሊላህ' (ለአላህ ምስጋና ይድረሰው) ይበል፡፡ ወንድሙም 'የርሐሙከላህ አላህ ይዘንልህ) ይበለው፡፡ እርሱም መልሶ 'የህዲኩሙላህ ወዩስሊሕ ባለኩም' (አላህ ቅኑን መንገድ ይምራቹ፣ ጉዳያቹንም ያስተካክልላቹ)' ይበል፡፡ [ቡኻሪ ዘግበዉታል]
نمایش همه...
💫 ብቻቹን ትሞታላቹ ብቻቹን ወደ መቃብራቹ ትገባላቹ ብቻቹን ከአላህ ፊት ትቆማላቹ ሞት ያማል መቃብር ጨለማ ነው ጊዜው ከማለፉ በፊት ራሳችንን እናዘጋጅ።
نمایش همه...