cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ዘውትር አላህን ያስታውሡ

ከወንድ ወይም ከሴት እርሡ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን።ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳነውን እንመነዳቸዋለን።[ ሱረቱ ነህል: 97] For any comments•••• @zewtr_allahn_enastaws_bot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
338
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#የሆነ ነገር ተመኝተህ እንደተመኘኸው የተሠጠህ እንደሆነ ቀደር ይባላል፤ አላህ ነዉና የሠጠህ ዉሰደው። የሆነ ነገር ተመኝተህ አብዝተህ አገኘዋለሁ የጠበቅከው እንደሆነ ሶብር ይባላል በመጠበቅህ ዉስጥ ሁሉ አጅር አለህና ጠብቀው ። የሆነ ነገር ተመኝተህ ከጠበቅከው በታች ሆኖ ከተሠጠህ ሳታጉረመርም ከተቀበልከው ያ ሪዷ ይባላል ፤ አላህ የወደደልህን በመውደድህ እንኳን ደስ ያለህ። @zewtr_allahn_enastaws
نمایش همه...
የኩዌቱ ፀሐፊ ዐብደላህ አልጃረላህ አላህ ይዘንለት፡፡ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ 🌺🌺🌺🌱🌺🌺🌺🌺 - ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣ - ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡ 1- ልብሴን ያወልቃሉ፣ 2- ያጥቡኛል፣ 3- ይከፍኑኛል፣ 4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣ 5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣ 6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣ 7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡ ከነኚህ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡ 8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል - ቁልፎቼ - መጽሐፎቼ - ጫማዎቼ - ልብሦቼ ….. በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ - በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣ - የዓለም እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣ - የኢኮኖሚው ቀውስም አልተፈጠረም፣ - በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣ - ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣ - ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤ - ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል - ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤ ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! … በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ 1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ 2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣ 3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣ የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!! 1- መልክህ፣ 2- ሀብትህ፣ 4- ጤናህ፣ 5- ልጅህ፣ 6- ቪላህ፣ 7- ዝናህ፣ 8- ሚስትህ/ባልሽ ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡ እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ 1- በግዴታዎች፣ 2- በሱንና ነገሮች፣ 3- በድብቅ መፅውት፣ 4- መልካም ሥራ አብዛ፣ 5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣ ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡ መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡ ምንጭ ፡ ጠሪቁ ተውበህ
نمایش همه...
እንደማታገባት ጠንቅቀክ እያወቅክ አትቅረባት! ራስህንም እርሷንም አትጉዳ አሏህ እስኪያገራልህ ራስህን አቅብ! የጌታህን ክልከላ አትዳፈር! @zewtr_allahn_enastaws
نمایش همه...
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ 7 ከንቱ ምኞቶች‼ ============================= ①💫🌸 يَا لَيْتَنِي كُنْتُ تُرَابًا النبأ- (40) ①) «ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ!» [አ-ን'ነበእ: 40] ②💫🌸 يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي الفجر-(24) ②) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ!» [አል-ፈጅር: 24] ③💫🌸فَيَقُول يَا لَيْتَنِي لَـمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ الحاقة(25) ③) «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ!» [አል-ሐቀህ: 25] ④💫🌸 يَا وَيْلَتَى لَيْتَنِي لَـمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا الفرقان (28) ④) «ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ!» [አል-ፉርቃን: 28] ⑤💫 يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ يَقُولُونَ يَا لَيْتَنَا أَطَعْنَا اللهَ وَأَطَعْنَا الرَّسُولَا الأحزاب (66) ⑤) « ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፤ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ!» [አል-አሕዛብ: 66] ⑥ 💫🌸يَقُولُ يَا لَيْتَنِي اتَّخَذْتُ مَعَ الرَّسُولِ سَبِيلًا الفرقان (27) ⑥) «ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ!» [አል-ፉርቃን: 27] ⑦ 💫🌸 يَا لَيْتَنِي كُنْتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا النساء (73) ⑦) « ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አ-ን'ኒሳእ: 73] ሁሉም የሟቾች ምኞቶ ናቸው። ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው። ግን ምን ዋጋ አለው! አልፏል ተቀድሟል! ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም።  ብልህ የሆነ ሰው ከመጸጸቱ በፊት ሥራውን ይሥራ አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን። 📮👌قال رسول الله ﷺ الدال على الخير كا فاعله 📮👌ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው ረሱል ﷺ‼
نمایش همه...
መልካም ሚስት ይፈልጋሉ? "መልካም ሴት በአንተ ጥረት አትመጣም ይልቁንም ጌታውን ለሚፈራ ሰው የተሰጠች ርዝቅ ናት።" ርዝቅህን ከአሏህ ጠይቅ !
نمایش همه...
አንዳንድ ጊዜ ህይወት በትንሽ መከራ አትፋታክም ፤ በትንሽ ፈተና አትጠግብክም ፤ላይ በላይ ትኮረኩምሃለች  ይህ ሰው ከዚህ በፊት ያየው መከራ ይበቃዋል ብላ አትተውህም ሁለት ሶስት ጊዜ ትሰብርሃለች ዘመንህን  በሙሉ አንተ ማየት የማትፈልገውን ደጋግማ ታሳይሃለች ፤ ለመከራ ነው እንዴ የተፈጠርኩት እስክትል ድረስ አፈር ታስልስሃለች....... ዱንያን ጀሊሉ ሲፈጥራት እንዲሁ ነች በድርጊቷ ብዙ አትዘን........ የሚገርመው ነገር አንተ ምንም ሆንክ ምንም ከመሄድ አትቆምም ፤የቱንም ያክል ችግር ቢደርስብክም አታዝንልክም ፤ ለአፍታ እንኳን ዞር ብላ አታይክም መጎዳትክን አታስተውልም፤ለብሶትህ ጆሮ አትሰጥም ፤ ለሀዘንህ አትቆዝምም ፤ለሞትህ የሃዘን ቀን አታውጅም፤ አንተ ተጎዳህ ብላ ላንተ አዝና ፀሐይ ብርሃኗን ከመስጠት አትወገድም፤ጨረቃ ፊቷ አይጠቁርም ፤አንተ በህይወት ብትቀጥልም ባትቀጥልም እነሱ ጉዳያቸው አይደለም........... እናማ በተጎዳክ ጊዜ ሁሉ ራስክን አክም ፤በተሰበርክ ጊዜ ሁሉ ራስክን ጠግን ፤ በወደቅክ ጊዜ ሁሉ ተነስ በምንም መልኩ አትስነፍ ተስፋ አትቁረጥ ፤የዱንያን ባህሪ ጠንቅቀህ እወቅ ፤ከነ ቁስልህ ተራመድ ........
نمایش همه...
ኢብኑል ቀይም •••••• በአላህ እምላለው አንድ ሰው ሱጁድ ላይ በሚሆን ጊዜ ምን ያህል  የ አላህ እዝነት እንደሚሸፍነው ቢያውቅ ኖሮ ግምባሩን ከመሬት ባላነሳ ነበር
نمایش همه...
ዒልም እና  ፂም ▪️ፂም የወንድ ልጅ ጌጥና መለያ ነው። ▪️መላጨቱም ከከባባድ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው። ▪️ፂምን መላጨት ከሴት ጋር መመሳሰል በመሆኑ የአላህንና የመልእክተኛውን እርግማንም የሚያስከትል ተግባር ነው። ደጋግ ቀደምቶች በተፈጥሮ እንኳ ፂም የሌለውን ሰው የዒልም መድረካቸው ላይ ተቀምጦ እንዲማር አይፈቅዱም ነበር! 🔅አል-ኢማሙ ማሊክ "ሙርድ" የሚባሉ  ፂም አልባ ወጣቶች እሳቸው ሒዲሥ ሲያስተላልፉ እንዲታደሙ አይፈቅዱም ነበር። አንዴ ፂም አልባ በመሆኑ የሚታወቅ ሂሻም የሚባል ሰው በሰዎች መሃል ተደብቆ ገብቶ 16 ሐዲሥ ከሳቸው ከሰማ በኋላ ለኢማሙ ሲነገራቸው 16 ጅራፍ ገርፈው አስወጡት። እሱም ምናለበት ከእርሳቸው 100 ሐዲሥ ሰምቼ 100 ጅራፍ በገረፉኝ! ይል ነበር። ማሊክ "ረሑመሁላህ" (ይህ እኛ ከፂማሞችና ከታላላቆች የተቀበልነው ዒልም ነው፤ ከእኛም ልክ እንደነሱ ያሉ ሰዎች -ፂማሞች እንጂ መውሰድና መቀበል አይችሉም!) ብለዋል። 📚መጅሙዕ አል-ፈታዋ 15/375 ▪️በተፈጥሮ ፂም ለሌላቸው ይህ ከተባለ በየቀኑ በምላጭ አርግፈውት ለመማርም ይሁን ለማስተማር የሚቀመጡ ምን ሊባሉ ነው?! ✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም     ሸዕባን 10/8/1445.ዓሂ @ዛዱል መዓድ
نمایش همه...
🚫 ወንድሜ የሴትን ልጅ ፈተና ተጠንቀቅ❗ ኮፒ የሴት ልጅ ፈተና ልክ እንደዚህ ታሪክ 👇 ከሱና ሊያንሸራትትህ አልፎም ዲንህን ሊያስቀይርህ ይችላልና ተጠንቀቅ። ታሪኩ እንዲህ ነው:- በግብፅ ከተማ ውስጥ አንድ ከመስጂድ የማይጠፋ መስጂድን በአዛን በሷላት አጥብቆ የሚይዝ ሙዓዚን ነበረ። በርሱም ላይ ጥሩ ለዲኑ መታዘዝና የኢባዳህ ብርሃኖች ይታዩበት ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ ሚናራህ ወጣ ታዲያ አዛን ላይ ሳለ ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ አንዲትን እንስት ይመለከታል፡፡ ወዲያውኑ በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቅና፣ በፍጥነት እርሷ ወዳለችበት ቤት ሄዶ ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች። እሱ ፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው የምፈልገው❗️ እሷ ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"ብላ ጠየቀችው እሱ ፡- "ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን መሰባሰቢያ ይዘሺዋል" አላት እሷ ፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ ልልህ አልችም አለቸው እሱ ፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት እሷ ፡- "አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ (ክርስቲያን) ነኝ አባቴ           ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም" አለችው እሱ ፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት እሷ ፡- እንደዛ ያደረግክ እንደሆን እኔም ፍቃደኛ ነኝ አለችው ከዚያም ይሄ ሰው እሷን ለማግባት ሲል ነሳራ (ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት ተቀመጠ፣ ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወድቆ ወዲያውኑ ህይወቱ አለፈች። እሷንም እስልምናውንም አጥቶ በኩፍር ላይ ሞተ ። ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይል ነበር :- "አላህ አንድም ነብይ አልላከም ሸይጧን በሴት ፈተና ሲያጠፋቸው ከነርሱ ላይ ተስፋ ባይቆርጥ እንጂ" 📚 [መውሱዓቱ ሊብኒ አቢ ዱንያ 4/540] አልሀሰን ኢብኑ ሷሊህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ሲል ይናገራል :- ሸይጣን ለሴት ልጅ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ "አንቺ የኔ ግማሽ ጎኔ ነሽ፣ እኔ በአንቺ የምወረውርብሽ ቀስቴ ነሽ፣ ደግሞም ባንቺ ከወረወርኩ አልስተም፣ አንቺ የሚስጥሬ ቦታ ነሽ፣ አንቺ የኔ የጉዳዬ መልዕክተኛ ነሽ" 📚 [መውሱዓቱ ሊብኒ አቢ ዱንያ 4/539] የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል "ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ የሆነ ፈተና ከኋላዬ አልተውኩም" 📚 [ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል ] ወንድሜ ከእንዲህ አይነት ፊቲና አላህ ይጠብቀን 🤲 [አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ ሊብኒ አልቀይም : ገፅ-167]
نمایش همه...