fa
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

رفتن به کانال در Telegram

EEP Communication

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام EEP Communication

کانال EEP Communication (@eepcommuication) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 567 مشترک است و جایگاه 8 356 را در دسته فناوری و برنامه‌ها و رتبه 2 162 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 567 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 24 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 24 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 19 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.91% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 15.83% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 035 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 465 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 8 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
EEP Communication

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 25 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته فناوری و برنامه‌ها تبدیل کرده‌اند.

15 567
مشترکین
+1924 ساعت
+197 روز
+2430 روز
آرشیو پست ها
በሀረር እና ጅግጅጋ ከተሞችና አካባቢያቸው የተቋረጠውን ኃይል ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው .......///....... ከድሬዳዋ 3 ወደ ሀረር የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በገጠመ ችግር ኃይል መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ። በዘርፉ የምስራቅ አንድ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ እንደገለፀው ከድሬደዋ ቁጥር ሦስት ወጥቶ ወደ ሀረር እና ጅግጅጋ ከተሞች በሚሄደው መስመር የታወር መገናኛ (Jumper) ቦታ ላይ ችግር አጋጥሟል። በዚህ የተነሳ ከማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኙት የሀረር እና ጅግጅጋ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ከጣቢያዎቹ ኃይል የሚያገኙ የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል መቋረጡን መምሪያው አስታውቋል። የተቋረጠውን መስመር ለመጠገን የጥገና ባለሙያዎች ርብርብ እያደረጉ በመሆኑ በተጠቀሱት አካባቢዎች ያሉ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ መምሪያው ጠይቋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 06 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

ቋሚ ኮሚቴው የይርጋለም ቁጥር አንድና ሁለት የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ጎበኘ ……..///……… በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የይርጋለም ቁጥር አንድ እና ሁለት የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያዎችን ጎብኝቷል። ቋሚ ኮሚቴው ያደረገው ጉብኝት በጣቢያው የታዩ የኦዲት ግኝቶችን መሠረት ያደረገ የእርምት እርምጃ ስለመውስዱ እንዲሁም በኦዲት ግኝቱ ወቅት የተቀመጡ አቅጣጫዎች ተግባራዊ ስለመደረጋቸው በመስክ ተገኝቶ ለመገምገም ያለመ ነው። የቋሚ ኮሚቴው አባላት ስለማከፋፈያ ጣቢያዎቹ አሰራር እና ተቋሙ የኃይል ፍሰቱን የሚቆጣጠርበትን ሥርዓት በተመለከተ በጣቢያው ኃላፊዎች ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን ጣቢያዎቹን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ እና የቡድኑ አስተባባሪ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ ከኦዲት ግኝቱ ጋር ተያይዞ የንብረት አያያዝ፣ የካሳ ክፍያ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስለመኖሩ እና የማስተካከያ እርምጃዎች ስለመወሰዳቸው በመስክ ምልከታው ወቅት አንስተዋል። ተቋሙ በፕሮጀክቶች ላይ የሚታየውን የፋይናንስና የግብዓት እጥረት በመቅረፍ የሀገር ሀብትን ከብክነት ለመጠበቅ በግኝቶቹ ላይ ማስተካከያና የእርምት እርምጃ መውሰድ እና ሊያሰሩ የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶችን መዘርጋት እንደሚያስፈልገው ምክትል ሰብሳቢዋ አሳስበዋል። ተቋሙ የፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራን በሚመለከት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በመስራት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የጀመረውን ቅንጅታዊ አሠራርን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው አመልክተዋል። ቋሚ ኮሚቴው የሀዋሳ ቁጥር አንድ እና ሁለት ማከፋፈያ ጣቢያዎችንም ጎብኝቷል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 06 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 05  ቀን 2017 ዓ.ም

በማከፋፈያ ጣቢያው መቆጣጠሪያ ላይ የጥገና ሥራ እየተከናወነ ነው …….///……… በአዲስ አበባ ጎፋ ማከፋፈያ ጣቢያ የትራንስፎርመር መቆጣጠሪያ ላይ የገጠመውን ችግር ለማስተካከል የጥገና ሥራ መጀመሩን
በማከፋፈያ ጣቢያው መቆጣጠሪያ ላይ የጥገና ሥራ እየተከናወነ ነው …….///……… በአዲስ አበባ ጎፋ ማከፋፈያ ጣቢያ የትራንስፎርመር መቆጣጠሪያ ላይ የገጠመውን ችግር ለማስተካከል የጥገና ሥራ መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 3 ሪጅን የማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ አስታወቀ፡፡ መምሪያ እንደገለፀው እየተከናወነ ያለው የጥገና ሥራ ከማከፋፈያ ጣቢያው የሚወጡ መስመሮችን በማቀያየር የሚከናወን በመሆኑ ለኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም ከማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል በሚያገኙት በጎፋ ኮንዶሚኒየም፣ ላፍቶ፣ ቫቲካንና ቄራ አካባቢ ኃይል በጊዜያዊነት ሊቋረጥ ስለሚችል ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ መምሪያው ጠይቋል፡፡ በዚህ ሰዓት ከባድ ተሽከርካሪዎች ለመንቀሳቀስ የማይፈቀድላቸው ቢሆንም የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት 12 ነጥብ 5 ቶን የመሸከም አቅም ያለው ክሬን እንዲንቀሳቀስ ፍቃድ ስለሰጠ ተቋሙ አመስግኗል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በመካኒሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ላይ የጥገና ሥራ ይከናወናል፡፡ ስለሆነም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9
ለጥገና ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በመካኒሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ላይ የጥገና ሥራ ይከናወናል፡፡ ስለሆነም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በጎፋ ካምፕ አካባቢ፣ በባቱ ኮንዶሚኒየም አካባቢ፣ በመካኒሳ ቆሬ፣ አረቄ ፋብሪካ እና አቦ ቤተክርስቲያን አካባቢ፣ በቫቲካን ጀርባ፣ በመከላከያ ሚኒስቴር መኖሪያ፣ በላፍቶ እና አካባቢው፣ በለቡ ሙዚቃ ሰፈር እንዲሁም በኃይሌ ጋርመንት እና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ ይቆያል፡፡ በተመሳሳይ ቀን እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመሮች ላይ የጥገና ሥራ ይከናወናል፡፡ ስለሆነም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በቄራ፣ በገነት ሆቴል፣ በኦሎምፒያ፣ በመስቀል ፍላወር፣ በወሎ ሰፈር፣ በቦሌ መድኃኔዓለም፣ በዮሴፍ እና አደይ አበባ አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ የሚቆይ ስለሆነ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

ትምህርት ቤቱ በተሻሉ መምህራን ጥራት ያለው ትምህርት እየሰጠ ነው ……….///……… በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመልካ ዋከና ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሻሉ መምህራን ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠቱ በአካባቢው ማህበረሰብ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን የት/ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ገለፁ። ምክትል ርዕሰ መምህሩ ጫላ ደሜ እንደገለፁት ትምህርት ቤቱ የጣቢያው ሠራተኛ ልጆች እንዲማሩ ታስቦ ቢከፈትም በሂደት የአካባቢውን ማህበረሰብ ልጆችን ተጠቃሚ ማድረግ ጀምሯል፡፡ የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ለትምህርት ቤቱ የግብዓት ድጋፍ የሚያደርግ ከመሆኑ ባሻገር ለመምህራን የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት፣ መብራትና ውሃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል። የጣቢያው የአስተዳደር፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ተሻገር በበኩላቸው እንደተናገሩት ጣቢያው ኃይል ከማመንጨት ባሻገር ትውልድ ቀረጻ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የሚተዳደረው በክልሉ ትምህርት ቢሮ በኩል ቢሆንም ጣቢያው ክትትልና የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በትምህርት ቤቱ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ሙዘሚር ሙሐመድ እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ተማሪ ፈትያ ጀማል እና ተማሪ ሮቤ አለሙ ቱሉ እንደገለጹት የትምህርት ቤቱ መከፈት ከቤተሰብ ሳትርቅ የመማር እድል ፈጥሮላቸዋል። ጣቢያው የከፈተው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአካባቢው ልጆች የመማር ተስፋ መፈንጠቁን ገልጿል። ጣቢያው ትምህርት ቤቱን ከመክፈት በተጨማሪ ተማሪዎች ሲታመሙ በጣቢያው ክሊኒክ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ወቅት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል 876 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን ተናግረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+8

በቅየሳ ሥራ ለረጅም ዓመታት ላገለገሉ ሴት ሠራተኞች ዕውቅና ተሠጠ ………///…….. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ ዘርፍ ለ36 ዓመታት በቅየሳ ሥራ ላይ ላገለገሉ ሦስት ሴት ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ዕውቅና ሰጥቷል። የዘርፉ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ውድነህ የማነ በዕውቅና መርሀግብሩ ላይ እንደተናገሩት የቅየሳ ሥራ ተቋሙ ለሚያከናውናቸው የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል። ሠራተኞቹ አሁን የደረስንበት ቴክኖሎጂ ላይ ሳንደርስና ሴትነታቸው ሳይበግራቸው ለተቋሙ ላበረከቱት አስቸዋጽዖ አመስግነው በቀጣይ ጊዜ  ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል ለተቋሙ የሚያደርጉትን አስተዋፅዖ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። ሠራተኞቹ ለረጅም ዓመታት በአንድ መደብ መስራታቸው ከራሳቸው ይልቅ ለተቋሙ ቅድሚያ መስጠታቸውን የሚያሳይ በመሆኑ ሌሎች ሠራተኞችም ይህን አርዓያ ተከትለው ለተቋሙ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። በዘርፉ የቴክኒካል ድጋፍ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አብዱልአሊም አህመድ በበኩላቸው ዕውቅናው ሠራተኞቹ ለሥራ አመቺ ያልሆኑ አስቸጋሪ የሥራ ሁኔታዎችን ተቋቁመው ያገለገሉበትን ዘመን ታሳቢ ያደረገ ነው። በዛሬው ዕለት የተሰጠው ዕውቅና ሌሎች ሠራተኞች የፈጠራ ችሎታቸውን አዳብረው ለተቋሙ ስኬት በርትተው እንዲሰሩ ተነሳሽነትን እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። በቀጣይ ዘርፉን ለማሳደግ ጥረት ለሚያደርጉ ሠራተኞች የሚሠጠው  እውቅና ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት በተቋሙ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ ዕውቅና የተሠጣቸው ሠራተኞች ሴቶች በማንኛውም ዘርፍ እንደሚችሉና ውጤታማ እንደሚሆኑ በተግባር አሳይተውናል በማለት ገልፀዋል። ዘርፉ ለሴት ሠራተኞች ለሠጠው ዕውቅና አመስግነው ሌሎች የሥራ ክፍሎች ይህን አርዓያ እንዲከተሉ እና ለሴቶች ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳሰበዋል። በዕለቱ ዕውቅና ከተሰጣቸው ሠራተኞች መካከል ተቋሙን ከ1981 ዓ.ም ጀምር በቅየሳ ሥራ ያገለገሉት ወ/ሮ አባይነሽ ፅጌ እንደተናገሩት በአንድ መደብ ላይ ለረጅም ዓመታት ማገልገል የራስን ልምድ ከማዳበሩም ባለፈ ለተቋሙ ውጤታማነት ከፍተኛ ፉይዳ ይኖረዋል። የቅየሳ ሥራ ተቋሙ ለሚያከናውናቸው ሥራዎች "የጀርባ አጥንት" ነው የሚሉት ወ/ሮ አባይነሽ ተቋሙም ሥራው ለዘርፉ የሚኖረውን ፋይዳ በመገንዘብ ለሠጣቸው እውቅና አመስግነው ዕውቅናው በቀሪ ጊዜያቸው ለሚያከናውኑት ሥራ  ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሹፌር 4ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ጥቅ
+6
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሹፌር 4ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ በመንገድ ትራንስፖርት በሚፈቅደው ህግ እና ደንብ መሰረት 74 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 14 ለተግባር ፈተና ያለፋችሁ በመሆኑ ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 የታደሰ መንጃ ፈቃድ በመያዝ ኮተቤ ብረታብረት ፊትለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ተሽከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተግባር ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና አንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም

ፕሮጀክቱ ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጥሯል .......//........ የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የሳይት ሥራ አስኪያጁ ተናገሩ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ቴዎድሮስ ጋሻው እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ 190 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል። የአካባቢው ወጣቶች በፕሮጀክቱ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ ቴዎድሮስ ይህም ወጣቶቹ በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቅመው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲያስተዳድሩ ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ በሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተመርቆ ሥራ አጥ ሆኖ መቆየቱን የጠቀሰው ወጣት ጌታቸው ገብሬ አሁን ላይ በፕሮጀክቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ሠራተኛ ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል። በፕሮጀክቱ በተፈጠረለት የሥራ ዕድል ከሥራ አጥነት ወጥቶ ራሱንና ቤተሰቡን እያስተዳደረ መሆኑንም ጠቁሟል። ከዕቃ ግምጃ ቤት ሥራው ጎን ለጎን ከሰለጠነበት ሙያ ጋር ተያያዥ በሆኑ ስራዎች ላይ እንዲሳተፍ ዕድል እንደፈጠረለት የተናገረው ወጣት ጌታቸው በቀጣይ በሙያው ተቀጥሮ በመሰል ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ሀገሩን እንደሚያገለግል እምነት እንዳለው ገልጿል። ሌላኛዋ የሥራ ዕድሉ ተጠቃሚ ወጣት ትህትና ብርሃኑ በበኩሏ በፕሮጀክቱ የሥራ ሰዓት ተቆጣጣሪ በመሆን እየሰራች መሆኑን ገልጻለች። የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቱ በአካባቢው መጀመር በፈጠረላት የሥራ ዕድል የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንደረዳት እና ሌሎች የአካባቢው ወጣቶችም የዚሁ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግራለች፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

የውጤት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም በሎየር 1ኛ የስራ መደብ በቋሚነት ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁት
+1
የውጤት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም በሎየር 1ኛ የስራ መደብ በቋሚነት ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች መካከል ከተ.ቁ 1 እስከ 11 ያላችሁ በተሰጠው የጽሁፍ እና የቃል ፈተና አብላጫ ውጤት ያመጣችሁ በመሆኑ ከህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ኮተቤ ብረታብረት በሚገኘው ዋና መ/ቤት የሰራተኛ ምደባ ቢሮ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ እየቀረባችሁ የቅጥር ፎርም እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሹፌር 3ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ጥቅ
+3
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሹፌር 3ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ በመንገድ ትራንስፖርት በሚፈቅደው ህግ እና ደንብ መሰረት 74 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጣችሁ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 17 ለተግባር ፈተና ያለፋችሁ በመሆኑ ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 የታደሰ መንጃ ፈቃድ በመያዝ ኮተቤ ብረታብረት ፊትለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ተሽከርካሪ ጥገና አስተዳደር ቢሮ የተግባር ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 03 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ………///……... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአይሻ 3 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ገለጹ፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለጹት የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ 120 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዲኖረው ታስቦ እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ አፈጻጸሙ 83 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል፡፡ ግንባታው ደረጃ በደረጃ እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሞገስ ፕሮጀክቱ 80 ሜጋ ዋት ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት እያስገባ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቀሪውን 40 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችን የመትከል ሥራ ለማከናወን የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተርባይኖችን የመትከል ሥራው በፋይናንስ አቅርቦት ምክንያት መዘግየቱን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አበዳሪዎችን ሳይጠብቅ በራሱ ፋይናንስ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ወስኖ ወደ ሥራ መግባቱን አብራርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ታሪክ የአዳማ አንድ እና ሁለት እንዲሁም የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫን ጨምሮ የአይሻ ሦስት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አራተኛው ነው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 03 ቀን 2017 ዓ.ም

ጣቢያው ለረጅም ዓመት አስተማማኝ ኃይል እያመረተ እንዲቆይ የጥገና ክፍሉ ሚና ከፍተኛ ነው ……//….. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለረጅም ዓመት አስተማማኝ ኃይል እያመረተ እንዲቆይ የጥገና ክፍሉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጣቢያው የጥገና ክፍል ኃላፊ ገለፁ፡፡ ኃላፊው አቶ መንበሩ ደምሴ እንደገለጹት የጥገና ክፍሉ በራስ አቅም ወቅቱን የጠበቀ ትልልቅ የጥገና ሥራዎችን በማከናወኑ ጣቢያው ላለፉት 37 ዓመታት አስተማማኝ ኃይል በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ በጣቢያው ላይ የመልሶ ግንባታ ሥራ ካለመሰራቱ ጋር ተያይዞ በኦፕሬሽንና በጥገና ክፍሉ ላይ ጫና መፍጠሩን የተናገሩት አቶ መንበሩ በማመንጫ ጣቢያው በየቀኑ፣ በየሳምንቱና በየወሩ የቅድመ መከላከል፣ የትንበያ እና የፍተሻ ጥገና ሥራዎች በማከናወን ጣቢያው ዛሬም ድረስ ኃይል ማምረቱ ሳይቋረጥ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡ የጥገና ሥራዎችን በአግባቡ ለማከናወንም ለባለሙያዎቹ አጫጭር የሥራ ላይ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጡና እርስ በእርስ የሚማማሩበት ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቁመዋል፡፡ በጣቢያው ከ3 ዓመት በላይ የሠራችው የጥገና ባለሙያ ስናፍቅሽ ጴጥሮስ ተርባይኖች እንዳይቆሙ ዕቃዎች ላይ ማሻሽያ በመስራት ጭምር በራስ አቅም በርካታ የጥገና ሥራዎችን እየሰሩ መሆኑን ተናግራለች፡፡ የጥገናና የኦፕሬሽን ክፍሉ ጥንካሪ ጣቢያው ለረጅም ዓመት ኃይል በአስተማማኝነት እንዲያመርት ማስቻሉንም ጠቁማለች፡፡ በጣቢያው የጥገና ባለሙያ ጥላሁን አጥሌ በበኩሉ የጥገናና የኦፕሬሽን ሥራዎች የጣቢያውን የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነት ለመጨመር በሚያስችል መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጿል፡፡ በጣቢያው ከ30 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው የጥገና ሠራተኞች ልምዳቸውን እያካፈሉ ከኦፕሬሽን ክፍሉ ጋር በመናበብ ጣቢያው ችግር ሳይገጥመውና ሳይቆም በርካታ የቅድመ መከላከል የጥገና ሥራዎች እንደሚሰሩ ተናግሯል፡፡ በመልካ ዋከና የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የኦፕሬሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ተክሉ ጎንፋ ክፍሉ በኃይል ማመንጫ ጣቢያው የማዘመን ሥራ ባለመሰራቱና ማንዋል በመሆኑ የኦፕሬሽን ሥራውን ከማዕከል ሆኖ ለመቆጣጠር ፈታኝ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 03 ቀን 2017 ዓ.ም