fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Our Side of the Story

Our Side of the Story

رفتن به کانال در Telegram

"To those who hurt and hunger” Since Oct 14, 2019 Here to help @DebbieTesfaye

نمایش بیشتر
1 733
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+127 روز
+1130 روز
آرشیو پست ها
Official Blender3D video for Dead Internet Society featuring Mussie Gebreselassie. On this piece, I cover the constant state of invisibility within the writer's realm over a concept video done by the ever so talented and brilliant Moss. The link to the full video: https://youtu.be/fwcm4SCy1Oo

Repost from Brown Empire
Pretty hurts ብድግ ብዬ እንደነገሩ አስይዤው የምሄደው ፀጉር፣ ቆንጆ የምለው ፊት እስኪመጣልኝ መዘጋጀት ባይኖርብኝ፣ መጥቶልኝም እስካምነው ድረስ መስታወት ፊት ባልሻጥ፣ ስንት እድሜ አተርፍ ነበር? ከተማ መወለድ ለብዙ ነገር ትርፋማ ቢያደርግም፣ ለመልክ ግን ገበያ ነው። ምን አይነ ግቡ ብንሆን የሚያወዳድሩብን በጣም የምታምር ደግሞ ሌላ አለች፣ እንደሷ ማማር ትችያለሽ የሚል ገንዘብ የሚያስበዘብዝ ማስታወቂያ በየስክሮሉ አለ። ቆንጆ መባል ጎበዝ ከመባል እስኪበልጥብን፣ ሳናምር መውጣት ጠልተን መገኘት ከአለብን ቦታዎች እስክንቀር? ገና እግራችን ሲያደከድክ፣ ከወፌ ቆመች ቀጥሎ ስለመልካችን አስተያየት አልሰማንም ወይ? “አፍንጫዋ ነው እንጂ፣ ጆሮዋ ባይተልቅ፣ ፀጉሯስ ሶስት ፍሬ ናት፣ ሴት ስትቀላ ነው እንጂ፣ ተረከዟ ምን ያክላል?” እየተባልን ቅንጥ ቅንጣችንን ተብለን እሳት እንደነካው ላስቲክ ያልተሰበሰብን አምስት እንሞላለን ወይ? አሁን ላይ “ግን እኮ ቆንጆ ነሽ ለምን እንዲህ ይሰማሻል?” የሚልን አስተያየት ለመስማት ጆሯችን እንደሚያመነታ፣ አይናችን መስታወት ላይ ያለ ምስላችንን ለማመን እድሜውን ደርድሮ በቦውሊንግ ኳስ እንደረመረመ ያለሀፍረት እንዴት ማስረዳት እንችላለን? ብንቆምም፣ ከገላችን ልክ አልቆም እያለ እንደ ሰፊ ውስጥ ልብስ ውልቅ ውልቅ የሚል ቅስም እንዳለን እንዴት ማውራት እንችላለን? “ልጅን ሲወዱ...” ብሎ የተረተ ሀገር መች ከነ ወደደን? ፍቅራቸው በአፍንጫችን ቅናት እና ማጎንበስ አልተወሰነም? ሀሳባችንን ለመሸጥ ስንዝር የማይሞላ ወገብ እንደማይጠበቅብን ሁሉ፣ እድሜያችን 14 ሳይሆን ውሀ ቻፒስቲክ የልጅ ከንፈራችን ላይ ስናፈስ “እሱን ትተሽ ትምህርትሽ ላይ አታተኩሪም?” ተብለናል። በተንኳሽ አለም ተተንኳሽ ይጠነቀቃል:) እኔን ትተህ ትምህርቴ ደጃፍ ላይ ተኮልኩለው የልጅነት ባቴን ከልጅነት ባቷ የሚያወዳድሩንን ጎረምሶች፣ ለገና ማርያምን ለመሆን ቅላት እንደሚያሰፈልግ የምታምነዋን አስተማሪ ተዪ፣ ተው አትልልኝም? አትሉልንም? እድሜ ዘመን የሚከተል ድምፅ እንደምትሰጡን አታውቁም? የውስጥ ድምፃችን የትንኮሳ ቃል እና አሽሙር መሆኑ አያሳዝናችሁም? ስራችሁ ፍሬ አፍርቶ በሌላችሁበትም ለስላሳ ድምፃችንን አሸንፎ የሚወጣው ሸካራ ድምፃችሁ ነው። የፀጉራችን ቴክስቸር ስንት ሚዶ በድዱ እንዳላስቀረ፤ በለስላሳ ሉጫ ፀጉር የሚሰራው ማስታወቂያ እኛን እንዳላየ አልፎን በየቲቪው የሰራጫል። በጥቁር ሀገር ቅላት ይሰበካል፣ ልጅ ያወጣው ፓውች ሁለት ሳምንት ከተቀመጠ የአእምሮ ጤናን የሚያናጋ አስተያየት በየመታጠፊያው እንደመንገድ አበባ ይቀጠፋል፣ በፀጉራችን መሆን ነውር እስኪመስል ድረስ የቀጠልን ለት በተውሶ ውበት በተለየ እንደነቃለን። መጀመሪያ ኢንሴኪዩሪቲው ይሸጣል፣ ያን ኢንሴኪዩሪቲ ተጫርተን ቦዲ ዲስሞርፊያ እንገዛለን፣ ከዛ ጊዜያዊ መፍትሄ በተጋነነ ዋጋ ይከተላል፣ ያቺንም እንደያቅማችን እንቃረጣለን። መፍትሄው አልዘልቅ ሲል ማየት ከምንፈራው መልክ፣ ባዶ ኪስ እና ድባቴ ጋ እንቀራለን። “በሰያፍ በኩል ስታይ ምን እመስል ይሆን?” ብላ በሶስት መስታወት ያንን አንግል ለማየት ያልሞከረች እንስት ለትምህርት እና ለሌላ የህይወት ቁምነገር በቂ የአእምሮ ቦታዋን ያልሰዋች እና መሽቶ በነጋ ቁጥር ለሚፈለፈሉ አሸን ኢንሴኪዩሪቲዎች ያልተሸነፈች ሴት ለኔ ጠንካራዋ እሷ ነች። አብዛኞቻችን ግን ለሲስተሙ እና ለማህበረሰቡ አይን ተሸንፈንለታል። ካፒታሊዝም የቀናው በሴቶች ራስ አለመተማመን ላይ ነው። ገበያውም የጦፈው በሚቀጠለው ፀጉር፣ ጥፍር፣ ሽፋሽፍት፣ የተለያዩ ውበት መጠበቂያ(ማፅናኚያ) ሸቀጦች ነው። ለሀበሻ ማስቀየም እንደንቀት ነው፣ how dare you look like this? Whats with the ድንች አፍንጫ? “ኧረ በመቤቴ ማሰብ ይሻላል?” ብንልም “ዱላ በማይመልሰዉ ነገር አንስማም” የሚለው ብዙ ነው። ደግሞ እኮ nose job, boob job, face lifting, tummy tuck? ካልን ኪሳችንም እንደማህበረሰቡ መሳለቁ አይቀሬ ነው። ይሄ ሁሉ ተደማምሮ ጢባጢቤዉን የሚጫወተው በራስ መተማመናችን ላይ ነው። ገና በልጅነታችን በራስ ያለመተማመን ከጉድሞርኒንግ ሻይ ጋር ነው የሚሸጥልን። "መሆን አለመሆን" የሚለው ጥያቄ የሚጀምረው እዛላይ ፒግቴል ያሲያዘችውን ቆንጆ ትንሽ ልጅ ስናይ ነው። እናማ የውበት ኢንደስትሪው በለጋ እድሜያችን ለበረዶ ባስቀመጥነው ሳንቲም ነው ፐርም(የፀጉር ማለስለሻ) የሚያስገዛን። ቀጭን ሆኖ መታየት፣ ሸንቃጣ መሆንን ያላለመች ሴት፣ በሆርሞን፣ በስራ፣ በኑሮ ምክንያት አልመች ብሏት ከገዛ ሰውነቷ ተኮራርፋ የምትኖረዋም፣ በተገኘው ለማስተካከልም ከጂም ጀምሮ የተለያዩ የሚጠጡ፣ የሚዋጡ ነገሮችንም ያልሞከረች ሴት ቤት ይቁጠራት። ብጉር፣ ማዲያት፣ ዲስከለሬሽን የመሳሰሉትን ለማጥፋት አለ በተባለው ፕሮዳክት ገንዘቧን ያልከሰከሰች ሴት መኖሯም አጠራጣሪ ነው። ስንት ብራ የልጅነት ቀናችን፣ ሮጦ መስሪያ ወጣትነታችን በነዚህ መነጫንጮች ያላግባብ አልፈዋል፣ ፊታችን ላይ ሀፍረት ተሸክመን ኖረናል። አንገታችን በውድድር ብዛት አጎንብሷል። አንዳንዶቻችን ድርድር ያላለ ወጣ ገባ ጥርሳችንን ጮክ ብለን “ሲያምር” ለማለት 34 አመት ፈጅቶብናል። Ain't got no doctor or pill that can take the pain away The pain's inside and nobody frees you from your body It's the soul, it's my soul that needs surgery (It's my soul that needs surgery) Plastic smiles and denial can only take you so far Then you break when the fake façade leaves you in the dark You're left with shattered mirrors and the shards of a beautiful past

It took me years of wandering through oceans of friendships and connections to realise that my belief in me being unlovable came from the exposure to people who were not kind, people who projected so much of their insecurities and anger towards me and not because I was cursed. Learning to accept that I’m lovable, people enjoy my company and look forward to our conversations has been the most bittersweet experience I’ve had. I had to unlearn the pattern of always looking for that hint of disgust, jealousy and competitiveness in the eyes of people. I’m grateful to have learned that there are days where I have been the problem but that’s not always the case. For I write this from a place of knowing whatever unkindness, negativity and spite thrown at me has nothing to do with who I am as a human being. And I will not make the mistake of believing it determines how I speak and think about myself again. This statement stays even if you someday find yourself to be the problem too.

ፓስታ በ እንጀራ ብሉ🫶🏾 እንኳን አደረሰን!

come throughhh :)

no answers from me today, just questions for you to ponder on until we meet this Sunday @thesocialaddis to rant about our concepts of love. 📍 Social Addis 🗓 February 15th ⏰ 6PM (12LT) 🎟 400 ETB 🔗 Link in bio.

Just sat in the living room with my mom and listened to old albums like we used to do when I was younger, I’m beefing with time now. I’ll write about it tomorrow.

ሳራ (we were neighbours) had this ቴፕ መሳይ phone, and every time I had no school መዝሙር ክፈቺ እያልኩ እጨቀጭቃት ነበር። Sara, who introduced me to the beauty of Afaan Oromo songs. We were around the same age, she was a little older but if you stared a little bit longer you could see the lines of aging without her will drawn on her face. ልቧ እስኪጠፋ ነበር መዝሙሮቹን የምትዘምራቸው፣ እያለቀሰች ምናምን። እኔ መዝሙሮቹ ስለሚያምሩኝ ነበር ክፈቺ የምላት፣ the raw emotions I can hear in their voices and the melodies magical ስለነበሩ። She barely understood Amharic and I with no knowledge of her language. ረጅም ሰዓት አብረን እንድንቀመጥ የሚያደርጉን መዝሙሮቹ ብቻ ነበሩ። Every time I come across an Afaan Oromo song, she’s all I can remember. ዛሬም ቋንቋው ሳይገባኝ፣ just the beauty making me float እሰማለሁ።

HAA-TURAMU-Solomon-Alemu-2026.m4a7.23 MB

Repost from አማዶን
እንዲሁ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ አድሮ ቃሪያ ፥ ታጥቦ ጭቃ ዝማሬና እንጉርጉሮ ጠዋት ተስፋ ፥ ማታ ሲቃ ፀደይና ምድረ በዳ ሰላምና አምባ ጓሮ አይሰለችም አይሰለችም ትርጉም የለሽ ፥ ቆንጆ ኑሮ። 01|07|17

Rage bait new? Oke🫶🏾

The three people who said ew, when I catch you!

Any fans of ጭኮ? (Yes the chiko)
Anonymous voting

እንኳን አደረሳችሁ🫶🏾

I love love honest writers. When you choose to write, a tad bit of vulnerability if not more is asked of you. ግን ከዛ ውጪ it’s about your vocabulary and how you express what you want to say. ሁሉም ኩልል ያለ እውነት አይደለም እንዲመስለን ይደረጋል እንጂ። Yes I’m very well aware fiction የሚባል ነገር እንዳለ እሱ አይደለም ነጥቤ። አሉላችሁ አንዳንድ…their words storm to your heart and make themselves known of how honest they are. ተፈጥረው ቢመስሉም you can tell they come from the pits of the writer’s deepest corners. እኔ አልችልም እንደዛ መፃፍ or perhaps it’s something I’m learning to do. On my wrist 24/7 on duty የሆኑ ግብረገብ police officers አሉ…ኧረ እፈሪ እንደዚህ አይባልም የሚሉኝ። እያንዳንዷን ፅሁፌን እየሰነጠቁ ከዚህ ምን እንማር የሚሉ ጨቅጫቃ ተማሪዎች ደግሞ ጣቴ ጫፍ ላይ ይቆጠቁጡኛል። እኔ አስተማሪ ነኝ አልኩ? የ ተርም ክፍያ ተቀበልኩ? ልጣፍ ስለሚወዱ እንጂ። አንደኛው ተማሪ TikTok comment section’ኤ ስር “የማይጠቅመንን ነገር ባታሳዪን” ብሎኝ እንዴት እንደሳኩ፣ የሰው ልጅ አንድ label ከተሰጠው ከዚያ ውጪ መኖር አይችልም አይደል? ነውር ነው? ቀልደኞች። ይኸው አሁንም እጅ እጄን እያሉኝ ነው፣ ምን ላስቀርላቸው እያልኩ እየተጨነኩ lmao. Go read a book or something ለዛሬ theme እና ነጥብ የለንም። (a very mediocre attempt to become an honest writer, ድንቄም)

lmao
lmao