cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

⇓ከይር ኢስላሚክ⇓ ቻናል !!

ለአሳብ አስተያየቶ= @faruza_bot ይህ bot የነብያትን ታሪክ እናየሰሐባዎችንታሪክ በቀላሉ እንዲ ያገኙበት ይረዳዎታል ➠ @islamic_1bot @islamic_1bot

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 587
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-347 روز
-22730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ፊቶቻችሁን መመልከት በራሱ ሃሴት ይሰጣል። ይህ ዑማ በእናንተ ቀና ብሏል። መስእዋትነታችሁ አይዘነጋም። በዘመን የማይደበዝዝ ገድል ፈፅማችዃል። አዎ ህያዋን ናችሁ አምላካችን ነፍሶቻችሁን በመላእክት መካከል የኩራት ካባን አለበሳት፣ ሰማይ ቤት በእናንተ ነፍስ መዓዛ የደመቀ ሆነ፣ አዎ መልካም ነፍስ ከፍታ እንጅ ዝቅታ አያውቃትም!! የዚህ ዘመን ጀግኖች♥♥♥♥♥♥ ሁሌም በልባችን ውስጥ ትኖራላችሁ!!!! @Alahu_Mewjudun_Bilamekan
نمایش همه...
👍 20🎉 1
ይህ ነበር የነብያን የዘወትር ዱአ ‼️ ____ ኡሙ ለማ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ አለች ፡ በአብዛኛው የነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ዱአ ይህ ነበር ፡   - አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ ፡፡ ከዚያም ረሱል ይሄን ዱአ ለምን እንደሚያደርጉ ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መለሱ ፡   " የማንም የአደም ልጅ ልብ በአላህ ጣቶች መካከል ነው የፈለገውን ቀጥ ሲያደርገው የፈለገውን ደግሞ ያጠመዋል ፡፡ ምንጭ፡- ሶሒሁል ጃሚዕ (4801) JOIN→ https://t.me/YereSulwedajoch_12 JOIN→https://t.me/YereSulwedajoch_12    
نمایش همه...
8👍 1
‹‹ባለቤት አለዉ፣ ባለቤቱም ሕዝባችን ነው!›› ... .‹‹በሸዋ መኳንንቶች ጥርስ ውስጥ ታስገባኛለህ አይሆንም!.....››➾ፊታውራሪ ሐብተጊዮርጊስ ናቸው በዘውዲቱ ዘመን ለመስገጃ ቦታ ሸይኽ ኢሳ ሲጠይቁዋቸው የሰጡት ምላሽ። ያኔ ሙስሊሞች የሚሰግዱት በየቤታቸው ሲሆን አርብን ግን የባንያ ወንድማማቾች ሲንክ ነጋዴዎቹ ሕንዶች ቤት ነበር። ቤቱን ከሊፋ ሕንፃ ፊት ለፊት ታገኘዋለህ። በንጉሱ ግዜ ምድር ቤቱ ለሊወን መርከንታይል በመሰጠቱ ለሱቅ ሲከፋፈል ዲዛይኑን አጣ እንጂ ..ሙስሊሞቹ በደላቸውን መገፋታቸውን ለማስታመም .. መካ መዲናን እንዲያስታውሱ ቅርፁን የካዕባ አስመስለው በጥቁር ድንጋይ የታነፀ ባለ1ፎቅ ሕንፃ ነው። ➾በአጭሩ ተስፋ ያልቆረጡት ሸይኽ ኢሳ ... ፊታውራሪ ሓብተ ጊዮርጊስ ከውጭ ሲመለሱ በለገሃር ተገኝተው፤ አከባቢውን ሳር አሳጭደው በተሸለሙ በቅሎዎች አቀባበል አደረጉላቸው። ➾ፊታውራሪም ‹‹መስጊዱን አትጠይቀኝ እንጂ ሹመትና ርስት ልስጥሕ›› አሉ:: ሸይኽ ግን ‹‹ከፖስታቤትና አትክልት ተራ አከባቢ ካሉ ቤቶች የሚወጣ ፍሳሽ የሚከማችበት ረግረጋማ ቦታ ይስጡኝ›› አሉ። 👉በተፈቀደላቸው ቦታ ወዳጆቻቸውን በማስተባበር ሰኢድ አብዱላል የሚባል የግንበኞች አስተባባሪ በመቅጠር የበኒን መስጊድ መሰረት ተጣለ። ቆሻሻ ቦታው ፀዳ ፍሳሾቹና ምንጩ ውስጥ ለውስጥ እንዲሔድ ተደረገ (የምንጩን አሻራ ማየት ከፈለክ ከበኒ ፊት ለፊት አስፖልት ተሻግረሕ ታገኘዋለህ። በፎቶ በቀይ ነጠብጣብ አስቀምጨልሓለው -ምስል 2) ወዘተ.. ➾ቦታው ፀድቶ መስጊድ መሰራቱ ያልተመቻቸው ሓይለስላሴ በሰበብ አስባቡ መሬቱን እየቆራረሱ ለተለያዩ ሰዎች ማደል ጀመሩ። ይበልጥ ሚናራው እንዲከለል በ L ቅርፅ ሸዋ ሕንፃ ዙርያው ገነቡ። ➾በአምስት አመቱ ኢጣልያ ቆይታም ኢጣልያ መሬት ቆርሶ በመውሰድ የካቶሊክ ተቋምና ቤ/ክ ገነባች ➾በደርግ ዘመንም የድርሻውን በዙርያ መሬት በመንጠቅ መጋዘኖች የቀበሌ አዳራሾች፣ መዝናኛ፣ ጋራጅ ተሰራ...። ➾በዘመነ ኢሕአዴግ የባሰው ሆነ ለዛውም ብዙ መስጊድ አሰራ ተብሎ በሚወራበት አሊ አብዶ ከንቲባ እያለ ቦታው ለልማት ይፈለጋል ተለዋጭ ቦታ ይሰጣቹዋል ተባለ። ➾አባቴ አፍራሽ ግብረሓይል የመጣ ግዜ 👉ሊጥ እያቦኩ የነበሩ እናቶቻችን እጃቸውን ሳይለቃለቁ፣ የአትክልት ተራ ነጋዴ ሱቅ ሳይዘጋ፣ የጎላ ልጆች ጎርደሜን ዘለው በኒን መስጊድ ተገኙ ። ወዘተ..... ➾ከሕዝብ ጋር መላተም ያልፈለገው ኢሕአዴግ አቅሞ ካላቹ ግዙት አለ። ወዳጄ ያ የራሱን መሬት፣ ያ በላብ የተደላደለን ቦታ አማራጭ ባለመኖሩ የዛን ሁላ የአከባቢ ሕዝብ ካባኮራን እስከ ሊሴ ከፒያሳ እስከአሜሪካን ግቢ ሕዝብ .... ያባቶችን ኪስ የናቶችን መሓረብ ሊያስፈታ ግድ ሆነ። ➾ከመስጊዱ በስተግራ (አሁን ፖርኪንግ የሆነው ) ወደ ቀድሞ ይዞታ ማስገባት ቢቻልም የሸዋ ሕንፃና የፊለፊቱ መንደር በአቅም ማነስ (ፍሉስ መታጣት) አልተቻለም ...... ወዘተ... 👉ምን ልል ፈልጌነው .... #ምናገባሕ #በኛ_ጉዳይ እያላቹኝ ላላቹ ወዳጆች ግልፅ እንዲሆንላቹ ነው። 👉አሁንስ ለምን እንደሚያገባኝ ገባቹ ቤተሰቤ (እናቴ )። አብሯደጎቼ ። ሰፈሬ ዋጋ ከፍለውበታል ለዛውም የደም ዋጋ !!! በኒን መስጊድ (ኑር ) ለናንተ መስጊድ ብቻ ሊሆን ይችላል ለኛ ፒያሳዎች ግን አንዱ የታሪካችን ክፍል ነው ። ባለቤት አለው ➾ባለቤቱ #ሙስሊሙ_ሕዝብ ነው አስተዳዳሪ አለው ➾አስተዳዳሪው በሕግ የፀደቀ በመጅሊስ መዋቅር የተሰራ በሕግና አንቀፅ የታሰረ ( አዋጅ ቁ 1207/2012 ) ነው ። ➾ዱርዬ ዱርዬ መጫወት በተመቸሕ ሜዳ እንጂ በሕዝብ ላብ ና ደም በተገነባ ታሪክ አይደለም !!! ሰላም 👐 / ኤርሚያስ አድዋ /
نمایش همه...
የዙህር ሰላት ደርሶ ቢላል አዛን እያደረገ ነው። ነቢም ሰ ዐ ወ እያደመጡ ነበር። የቢላልን አዛን እየተከተለ እዛን የሚል ሰው ድምፅ ከርቀት ይሰማል። ቢላል አዛኑን ካጠናቀቀ በኋላ ረሱል ሰዐወ፦‹‹ማን ነው አዛን ሚለው ከወደ ውጭ በኩል? ›› ሲሉ ጠየቁ። አባ መሕዙራ የተባለ እረኛ በማላገጥ ስሜት አዛን እያለ ግመሎቹን እንደሚያግድ ነገሯቸው። ረሱልም ሰዐወ በተረጋጋ ስሜት ይህ ሰው ተይዞ እሳቸው ዘንድ እንዲቀርብ ዐሊይን እና ዙበይርን ላኳቸው። ሁለቱም ወደተላኩበት ሂደው አላጋጩን ከነ ግብረ-አበሮቹ ጠፍረው አመጧቸው። ሁሉም አቀርቅረው ረሱል ሰዐወ ፊት ቆሙ። ‹‹ ከናንተ ውስጥ ማን ነበር አዛን ሲል የነበረው?›› ረሱል ስዐወ ጠየቋቸው። ፍርሀት ስላደረባቸው ሁሉም ዝም አሉ። ዝምታቸውን ያስተዋሉት ነቢይም፦‹‹እንግድያ ማን አዛን እንዳለ ለመለየት እያንዳንዳችሁ በየተራ አዛን በሉ›› አሏቸው። ሁሉም አዛን ካሉ በኋላ የአባ መሕዙራ ተራ ደርሶ አዛን ሲል እሱ መሆኑ ታወቀበት። ‹‹ስምህ ማን ነው?›› አሉት ነቢ ወደሱ ጠጋ ብለው። ‹‹አባ መሕዙራ እባላለሁ›› አለ ፈራ ተባ እያለ። ‹‹የመልአክ ድምፅ ይመስል እየተጠበብክ አዛን ትል የነበርከው አንተ ነህ?›› ነቢ ጠየቁት። ቅጣቱን ለመቀበል ሲዘጋጅ የነበረው ሙሽሪክ በቅጠቱ ፈንታ ይህንን ልብ የሚማርክ ንግግር ሲሰማ ውስጡ ተናወጠ። ረሱል ሰዐወ ከአላጋጩ እረኛ ፊት ቁመው በጭንቅላቱ የጠመጠመውን ፎጣ ከጭንቅላቱ ላይ አውልቀው ፀጉሩን እየዳበሱ፦‹‹አላህ በረካ ያድርግህ፣ ወደ እስልምናም ልብህን ይምራልህ›› አሉት። በስብዕናቸው የተማረከው አላጋጩ እረኛም የመልዕክተኛው እጅ ከራስ ቅሉ ሳይወርድ ጓደኞቹ እየተመለከቱ ሸሀዳውን ያዘ። የድምፁን ውበት የመሰከሩለት ይህን እረኛም ረሱል ሰዐወ ወደ መካ ሂዶ አዛን እንዲል ሾሙት።ከዝያች ቀን አንስቶ ወደ መካ የተመመው ይህ እረኛም የመካ ሙአዚን ሁኖ‹‹ነቢ የዳበሱትን ፀጉር መቼም አልላጨውም›› ሲል ስለት ተሳለ። መካ ላይ ቁጭ ብሎም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ የነቢን ሰዐወ ትዕዛዝ እየፈፀመ ከረመ። ከሱ ህልፈት በኋላም ልጆቹ እና የልጅ ልጆቹ ለ300 አመታት ያህል መካ ላይ አዛን ይሉም ነበር። Sefwan Ahmedin ምንጭ፦ سنن النسائي سنن ابو داود مسند أمام احمد
نمایش همه...
ኢማም አል ቡካሪይ ዒልም ፍለጋ ጉዞ ጀምረዋል። እሳቸውን እና ሌላ በርካታ ተጓዦችን ያሳፈረችው መርከብም አድማሱ እማይታየውን ውቅያኖስ እያቆራረጠች ትከንፋለች። ኢማማችን ለጉዞአቸው እና ለቆይታቸው ይጠቅማቸው ዘንድ አንድ ሺህ ዲናር በከረጢታቸው ይዘዋል። በዝያ ዘመን አንድ ሺህ ዲናር እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ ነበር። ይህን የተመለከተ አንድ ተሳፋሪ ኢማማችንን መወዳጀት ፈለገ ና ቀረባቸው። መርከባቸው ጉዞ ላይ ሳለችም ሌት ተቀን ይህ ሰው ኢማሙን የሙጥኝ ብሎ ተጎዳኛቸው። እሳቸውም ቅርበቱን እና ጓደኝነቱን ሲመለከቱ ሚስጥራቸውን ማካፈል ጀመሩ።ኢማሙ ጓደኛ ብለው ለያዙት አዲሱ ጓደኛቸው ስለ ያዙት ዲናሮች ሳይቀር ሹክ አሉት። በባህሩ ላይ መርከቧ እየተንሳፈፈች ቀናት ተፈራረቁ። ከእለታት አንድ ቀንም ንጋት ላይ ተሳፋሪዎች ሀገር ሰላም ብለው በተኙበት ከፍተኛ የሆነ የዋይታ ጩኸት ተሰማ። ሁሉም ተሳፋሪ ጩኸቱ ወደሚሰማበት የመርከቢቱ ስፍራ ሲያቀኑ ይህ የኢማማችን ጓደኛ ብቻውን ቁሞ ልብሱን እየቀዳደደ ጩኸቱን ተያይዞ አገኙት። ሊያረጋጉት ቢሞክሩም አሻፈረኝ ብሎ ጩኸቱን ቀጠለበት። በመጨረሻም ምክንያቱን ሲጠይቁት ፦‹‹በከረጢት የያዝኩት አንድ ሺህ ዲናር ጠፋብኝ ማን እንደወሰደው አላውቅም›› ሲል ያለቅስ ጀመር። የሰውየውን ሁኔታ የተመለከቱት መርከበኞች እና ተሳፋሪዎች ተወያይተው ሁሉንም ተሳፋሪ ለመፈተሽ ተስማሙ። ፍተሻው ተጀመረ። የተሴረው ሴራ የገባቸው ኢማማችንም ፈታሺዎቹ እሳቸው ጋ ከመድረሳቸው በፊት የገዛ ዲናራቸውን ከነ ከረጢቱ እባህሩ ውስጥ ወረወሩት። ፍተሻው ተጠናቀቀ። ግና ገንዘብ ጠፋብኝ ሲል እሪ ያለው ሰውዬ በመርከበኞቹ ፍተሻ ገንዘቡ ስላልተገኘ በውሸታምነቱ ተመናጨቀ፣ ተሰደበ። ከቀናት በኋላ ጉዞዋን ያጠናቀቀችው መርከብ ከባህር ዳርቻ ቁማ መንገደኞቹን ስታራግፍ ሰውዬው ወደ ኢማማችን ጠጋ ብሎ፦‹‹ዲናሮቹን ቆይ የት ደብቀህ ነው?›› አላቸው። እሳቸውም፦‹‹በባህር ወረወርኳቸው።›› አሉት። ተገረመ፦‹‹ቆይ እንዴት ታግሰው ያን ያህል ገንዘብ በባህር ይወረውራሉ?›› ሲል ጠየቃቸው። እሳቸውም፦‹‹አንተ ጅል! እድሜዬን በሙሉ የረሱልን ሰዐወ ሀዲስ ስሰበስብ መክረሜን አታውቅም? በዝያ ላይ ትንሽ ትልቁ የማህበረሰብ ክፍልም ተአማኒነትን ችሮኛል። ታድያ ለዚህ ተራ ዲርሀም ብዬ ለቅጥፈት በር ምከፍት ይመስልሓል?››
نمایش همه...
ጥቆማ፦ እንግሊዘኛ ቋንቋን ለማሻሻል እና ለመማር ካሰቡ ይሄን ግሩፕ ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/ethioengclub
نمایش همه...
በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!! ደስታን በልግስና ውስጥ ያገኙት የአለማችን ቁጥር አንድ በጎ አድራጊ ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ይባላሉ:: ሳዑዲ አረቢያ ካፈራቻቸው ቢሊየነሮች መካከል አንዱ ናቸው:: ከንጉሳውያን ቤተሰብ ሳይሆኑ ቢሊየነር መሆን የቻሉ ሰው ናቸው:: በአለም ግዙፉን አልራጅሂ ኢስላማዊ ባንክ መመስረት ችለዋል:: በህይወታቸው ያጋጠማቸውን አንድ አስተማሪ ክስትተት እንዲህ ሲሉ ያካፍሉናል - "በልጅነቴ እጅግ በድህነት ውስጥ ነው ያደኩት:: ቤተሰቦቼ ድሆች ነበሩ:: በአንድ ወቅት ትምህርት ቤት ተማሪ እያለው ትምህርት ቤቱ የመዝናኛ ጉዞ ስላዘጋጀ በዚህ የሽርሽር ጉዞ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ 1ሪያል ማዋጣት እንደሚጠበቅበት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስታወቀ:: እኔም በዚህ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ እጅግ ስለጓጓው ለወላጆቼ አንድ ሪያል እንዲሰጡኝ እያለቀስኩኝ ጠየኳቸው:: ነገር ግን ወላጆቼ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ህይወት የሚኖሩ ሚስኪኖች ስለነበሩ ይህን አንድ ሪያል ስለሌላቸው ሊሰጡኝ አልቻሉም:: የጉዞ ቀናት መቃረቡን ተከትሎ አንድ ሪያሉን የሚሰጠኝ በማጣቴ እጅግ በጣም አለቀስኩኝ ፤አዘንኩኝ:: ለጉዞ አንድ ቀን ሲቀረው በትምህርት ቤቱ የወሰድነው ፈተና ውጤት ደርሶ ስለነበር የፈተና ውጤታችንን ስንቀበል ከሌሎች ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማምጣቴ ፍልስጤማዊ የሆነው መምህራችን ተደስቶብኝ በተማሪዎች ፊት አስጨብጭቦ ውጤቴን ሰጠኝ:: ለማበረታታም አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ አበረከተልኝ:: ለጉዞ መዋጮ የሚያስፈልገኝን አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ በማግኘቴ እጅግ በጣም ተደሰትኩኝ:: ያንን የተሸለምኩትን ኣንድ ሪያልም ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በፍጥነት ሄጄ በመስጠት ብዙ በጓጓሁለት ጉዞ ላይ መሳተፍ ቻልኩኝ:: ለቀናት ሳነባ የነበረው እንባ በደስታ ተቀየረልኝ:: የቀናት ለቅሶዬ በዛች አንድ ሪያል ሽልማት የተነሳ ለረጅም ጊዜያት ውስጤ በቀረ ደስታ ተለወጠልኝ:: ጊዜያት ነጎዱ:: እኔም ትምህርቴን አጠናቀኩኝ:: ጠንካራ እና ታታሪ ሆኜም በስራ ዘርፍ ላይ ተሰማራው:: የአላህ ፀጋ ብዙ ነውና ስራዬን በረካ አደረገልኝ:: ፀጋውንም በኔ ላይ አንቧቧልኝ:: ከትንሽ ስራ ተነስቼ በሳኡዲ አረቢያ የመጀመሪያው የሸሪዓ መር ባንክ በመመስረት በመላው ሳኡዲ አረቢያ ቅርንጫፎች በዙልኝ:: በአንድ ወቅት በልጅነቴ ተማሪ እያለው አንድ ሪያል የሰጠኝ መምህሬን በማስታወስ በወቅቱ የሰጠኝ አንድ ሪያል ሽልማት ነው ወይስ እርዳታ ? በሚል ከእራሴ ጋር ሙግት ውስጥ ገባው:: እራሴን ደጋግሜ ጠየኩኝ:: ግን ፈፅሞ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም:: መምህሩ ያንን አንድ ሪያል የሰጠኝ ምንም አስቦ ቢሆን ለእኔ ግን በወቅቱ የነበረብኝን ትልቅ ችግሬን ቀርፎ አስደስቶኛል ፤ ያንን የደስታ ስሜት ደግሞ ከእኔ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም ስል ለራሴ ነገርኩት:: ውስጤ ለሚመላለሰው ትዝታ እና ጥያቄ ምላሽ ሊሆነኝ የሚችለው ይህን መምህር ካለበት አፈላልጌ አግኝቼው ስጠይቀው ነው በሚል ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤቴ በመሄድ ፍልስጤማዊ መምህሬን ማፈላለግ ጀመርኩኝ:: በአላህ እገዛ መምህሬ ያለበትን ቦታ አፈላልጌ ማግኘት ቻልኩኝ:: እሱን ለማግኘትም ቀድሜ ተዘጋጀሁና ወዳለበት ስፍራ አቀናው:: ፍልስጤማዊው መምህሬ በጡረታ ላይ ሆኖ፣ እጅግ በድህነት እና በችግር ላይ ሆኖ አገኘውት:: የእርሱ ተማሪ እንደነበርኩኝ በማብራራት እንዲያስታውሰኝ አደረኩት :: የተከበርከው ውዱ መምህሬ ሆይ ፣እኔ እኮ ለረጅም አመታት የቆየ ያንተ ባለእዳ ነኝ አልኩት:: አንድ ደሃ ሰው ምን የሚያበድረው ነገር ኖሮት ነው የማበድርህ ሲል ተገርሞ ጠየቀኝ:: እኔም ተማሪ እያለው በውጤቴ ምክንያት የሰጠኝን አንድ ሪያል አስታወስኩት:: መምህሬም :- ክስተቱን በማስታወስ እየሳቀ ባለእዳ ነኝ ያልከኝ ታዲያ አሁን ያቺን አንድ ሪያል ልትከፍለኝ ነው ? በማለት ተገርሞ እየሳቀ ጠየቀኝ:: እኔም አዎ ውዱ መምህሬ በማለት መለስኩለት:: ወደ መኪናዬ እንዲገባ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ መኪና በግቢው ውስጥ የቆመበት ግዙፍ ዘመናዊ ቪላ ቤት ውስጥ ይዜው ገባው:: መምህሬ ሆይ ተማሪ እያለው ለሰጠኸኝ አንድ ሪያል ምላሽ ባይመጥንም፤ ይሄ ግዙፍ ቪላ እና መኪና ላንተ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀሁት ነው፤ በህይወት ዘመንህም የሚበቃህን ያህል ገንዘብ እኔ ዘንድ ተዘጋጅቶልሀል ብዬ ነገርኩት:: መምህሬ እጅግ በመደንገጥ ይሄ ፈፅሞ ለእኔ አይገባም፣ ይህ በጣም ከልክ ያለፈ ብዙ ነው በማለት አይኑ በእንባ ተሞልቶ መቀበል እንደሚከብደው ነገረኝ::: መምህሬ ሆይ በወቅቱ አንድ ሪያል ስትሰጠኝ የነበረኝ ደስታ ዛሬ አንተ ይህን ቪላ እና መኪና ስታገኝ ከተሰማህ ደስታ በላይ ነው:: የዛኔ የነበረኝ የልጅነት ደስታ እና ሀሴት ዛሬም ድረስ አይረሳኝም በማለት ለመምህሬ ስጦታዬን አበረከትኩለት::ይላሉ በመጨረሻም ሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ ምክር ሲመክሩ "ምን ጊዜም ለሌሎች ደስታን ፍጠር፣ የሌሎችን ጭንቀት አሶግድ ፣ ምንዳህን እጅግ ከሰጪው ፣ከለጋሹ እና ከደጉ ጌታ ጠብቅ ይላሉ' ለመረጃ ያህል ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ያላቸውን ሀብት ግማሹን ለልጆቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ግማሹን ደግሞ ለበጎ አድራጎት አበርክተዋል:: በአለማችን ታሪክ ግዙፉ የተባለለትን እና በአለም ድንቃ ድንቅ መዘገብ ላይ ሊሰፍር የቻለ ለበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚውል በሳኡዲ አረቢያ በቀሲም ግዛት የሚገኘውን 5466 ሄክታር ስፋት ያለው የእርሻ ማሳቸውን፤ ይህም የእርሻ ማሳ በአመት 10ሺህ ቶን የቴምር ፍሬ የሚሰጥ እና በውስጡም 45 አይነት የተለያዩ የተምር ፍሬዎችን የያዘ፣ 200,000 የሚሆን የተምር ዛፍ ለበጎ አድራጎት ይውል ዘንድ ወቅፍ ማድረግ የቻሉ ሰው ናቸው:: ሸይኽ ሱለይማን አራጅሂ ለዳእዋና ለበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ቋሚ ድጋፍ እንዲሆን ወቅፍ ያደረጉት ካፒታል አሁን ላይ 60 ቢሊዮን ሪያል ደርሷል። ይህ በአለማችን እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ወቅፍ ነው:: ሼይኹ ወቅፍ ካደረጉት የተምር እርሻ የሚገኘው የቴምር ምርት ተሽጦም ገቢው ለበጎ አድራጎት ማህበራት የሚከፋፈል ሲሆን ቀሪው ተምርም ለሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች መካ እና መዲና ለሚገኙት ሀረሞች የረመዳን ኢፍጣር ፕሮግራም አገልግሎት ይውል ዘንድ ለምዕመናን በነፃ ይከፋፈላል:: በሳዑዲ አረቢያ ባሉ ከተሞች ላይ በሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ እና ቤተሰባቸው አማካኝነት መስጂድ እና መድረሳ ያልተገነባበት ከተማ ማግኘት ያዳግታል:: በሁሉም ቦታዎች ላይ መስጂዶችን አስገንብተዋል:: በስራቸው ላለው ሰራተኞቻቸውም ደሞዛቸውን ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት በመክፈል ይታወቃሉ:: ሽይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ በአንድ ወቅት ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው ግማሹን ሀብታችሁን ለቤተሰባችሁ፤ ግማሹን ደግሞ ለወቅፍ ለግሰውታል:: ለራስዎት የግል ወጪ የሚሆንስ ምን አስቀምጠዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ውብ በሆነ ፈገግታ ተሞልተው "ባጭሩ ምላሼ ምንም ነው!" የምለብሳቸው ልብሶች ብቻ እኔ ጋር አሉኝ:: እድሜዬ በሰማኒያዎቹ ውስጥ ነኝ! ከዚህ ቡኃላ ምን ልፈልግ እችላለሁ? የወቅፍ ፕሮጀክቴ ወጪዬን ይሸፍናል፣ መጠለያ፣ ምግብ፣ ህክምና እና መጓጓዣ አገኛለው::በትንሹ ለመኖር በደንብ የተብቃቃው ነኝ:: ሲሉ መልሰዋል:: ” ቢሊየነር ሆነው ግን ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው በመሆኖት! "ምን ይሰማዎታል?" ሲባሉም
نمایش همه...
"ፈገግ እያሉ በናፍቆት እይታ ውስጥ ሆነው ውስጤን ብርሃን ይሰማኛል! ነፃነት ይሰማኛል! የበራሪ ወፍ ያህል ነፃነት ይሰማኛል…በህይወት ዘመኔ ሁለት ጊዜ ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው ሆኜ አውቃለው:: በፊት ላይ የድህነትን ስሜት እና ሁኔታ በደንብ በህይወቴ አውቀዋለው:: ያሁኑ ግን በፍላጎቴ እና በምርጫዬ ነው:: ምንም ለራሴ ባይኖረኝም እጅግ መረጋጋት፣ የዐዕምሮ ሰላም እና ደስታ ይሰማኛል::ሀብት ሁሉ የአላህ ነው:: የእሱን ሀብት እንድንጠብቅ ነው የተሰጠን:: አሁን ላይ ጌታዬ አላህ ሲጠራኝ ያለ ምንም እክል ጥሪውን መመለስ እችላለሁ! ይህ ታዲያ እንዴት ያለ እፎይታ እና እረፍት የሚሰጥ ነው!!በማለት አስደናቂ ምላሻቸውን ሰጥተዋል:: በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!! አላህ ከችሮታው አሁንም ይጨምርላቸው ለኛም የመለገስን ልብ ይወፍቀን
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.