ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر609
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-1130 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ #መጋቢት ፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን #ለከበረ_ተጋዳይ_ለሆነ_ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጦ በጌታችን ማመን ላስተማለው በሐዋርያት እጅ ለተጠመቀ፤ ወላጆቹን በሚያደርገው ተዓምራት ላሳመነ፤ የጣዖት አምልኮን ላጠፋና ሰይጣንን ድል ላደረገ #ለጽኑ_አባት_ለአባ_ኩትን ለዕረፍት በዓል፣ ለከበሩ #ቅዱሳን_ለእድርያኖስና_ለሚስቱ፣
#አውሳብዮስና_አርማ_ሌሎች_አርባ_ሰዎችም ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_ኖብ ጋር በሰማዕትነት ከዐረፉ #ከሁለት_ሺህ_ሰዎች ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ኩትን፦ እርሱም በሶርያ አገር ስሟ በንጣንዮስ ከምትባል ቦታ የሚኖር ነው። አባቶቹም ከዋክብትን ያመልኩ ነበር የአባቱ ስም ንስጣር የእናቱም ስምp iቴዎድራ ይባላል። በአደገ ጊዜም ወላጆቹ ሊያጋቡት ፈለጉ እርሱ ግን አልወደደም ግድ ብለው ያለ ውዴታው ሚስትን አጋቡት ሊገናኛትም አልፈለገም ስለ ሥጋ ድካም ወይም ስለ ጽድቅ ሳይሆን የሥጋ ፍትወትን ስለሚጠላት ነው እንጂ። ደናግልም እንደሆኑ ሁለቱ ሁሉ ከሚስቱ ጋር በአንድነት ኖረ።
❤ "አምላክ ሆይ ወደ ዕውቀትህ ምራኝ" በማለት ጸሎትና ምልጃን ያዘወትር ነበር። ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለቆርኔሌዎስ እንደተገለጠ ተገለጦ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን አስተማረው ከሐዋርያትም ወደ አንዱ ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን እንዲጠመቅ አዘዘው። የሐዋርያት የስብከታቸው ወራት ነበርና ሒዶ ተጠመቀ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሁሉ ሕጉን ሥርዓቱንም ሁሉ ተማረ መለኮታዊ ምስጢርንም ተቀበለ። በየቀኑ ሁሉ የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት ይሰማ ነበር። የጽድቅን ሥራ መሥራትና ንጽሕና፣ ለበጎ ሥራ መጠመድ ትጋት፣ ቅንነት፣ የዋህነት፣ ጾም፣ ጸሎትና ሰጊድ በላዩ ተጨመረ። በእነዚህ ሁሉ የሚተጋ ሆነ እግዚአብሔርም አስደናቂ ተአምራቶችን እንዲያደርግ በርኵሳን አጋንንት ሥልጣንን ሰጠው።
❤ በሚያደርገው ተአምራትም ወላጆቹን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ማመን ስቦ አስገባቸው ደግሞ ሚስቱንና ወላጆቿን አሰገባቸው። ከከሀድያን አንዱ ለሰይጣን ሊሠዋ ወደ ጣዖቱ ቤት በገባ ጊዜ ቅዱስ ኩትን አውቆ በሰይጣን ላይ ጮኸ እርሱ ሰይጣን እንጂ አምላክ እንዳልሆነ በሰው ፊት ያምን ዘንድ አዘዘው። ሰይጣንም እንዳዘዘው ራሱን ገለጠ በዚያ የነበሩ ሁሉም "የቅዱሰ ኩትን አምላክ አንድ እርሱ ብቻ ነው" እያሉ ጮኹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ።
❤ ከዚህ በኋላ ከቀላውዴዎስ ቄሣር የተላከ መኰንን የቅዱስ ኩትንን ዜናውን በሰማ ጊዜ ወታደር ልኮ አስቀረበው ስለ ሥራውም ጠየቀው እርሱም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ መኰንኑም ጽኑ ግርፋት ገርፈው እንዲሥሩት አዘዘ ይህንንም አደረጉበት።
❤ የአገር ሰዎችም ቅዱስ ኩትንን አሠቃይተው እንዳሠሩት በሰሙ ጊዜ ሁሉም ወደርሱ ተራወጡ መኰንኑንም ሊገሉት ወደዱ መኰንኑም ሸሸ። ቅዱስ ኩትንንም ከማሠሪያው ፈትተው ከደሙም አጥበው ተሸክመው ወደቤቱ ወሰዱት ከዚህም በኋላ ብዙ ዘመናት ኑሮ የወደደው እግዚአብሔርን አገልግሎ ደስ አሰኝቶ በፍቅር አንድነት መጋቢት 9 ቀን ዐረፈ።
❤ ከዕረፍቱም በኋላ ቤቱን ቤተ ክርስቲያን አድርገው ሥጋውን በውስጥዋ አኖሩ ጌታችንም ከሥጋው ብዙዎች ታላላቅ ተአምራቶችን አሳየ። አባ ኩትን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትሁን አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የከበሩ_ቅዱሳን_እድርያኖስና_ሚስቱ፣ #አውሳብዮስና_አርማ_ሌሎች_አርባ_ሰዎችም_ሰማዕትነት፦ እሊህንም ምርጦች ለረከሰ ከወርቅና ከብር ለተሠራ ጣዖት ማምለክን እምቢ ስላሉ የክብር ባለቤት ለሆነ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለስሙ ዐላውያን ጽኑ የሆነ ሥቃይን አሠቃዩአቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን መጋቢት 9 ቀን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። በረከታቸው ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦የመጋቢት 9 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለኩትን_በእደ_ሐዋርያት_ዘተጠምቀ። እመልአከ ሰማይ ትምርተ ከመ ተጠየቀ። ሶበ አገበርዎ እንተ ሕሊናሁ ኢጽሕቀ። በፍትወተ ሥጋ ኢተሞዐ ወበሥምረቱ ኢወድቀ። ምስለ ብእሲቱ ሰኪቦ ዘአኮ ርኁቀ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢት_9።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ፈሪሃ እግዚአብሔር እምሀርክሙ። መኑ ውእቱ ብእሲ ዘይፈቅድ ሐይወ። ወያፈቅር ይርአይ መዋዕለ ሠናያት"። መዝ 33፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 1፥1-11፣ ያዕ 2፥1-14 እና የሐዋ ሥራ 4፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ማር 1፥23-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ወራትና በዓል። በሁላችንም ይሁንልን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
👀 Job Vacancy 👀
Job Type: On- Site, Commission Based
Work Location: Addis Ababa
Experience: entry & intermediate level
Job Title:
1, Data Collector(ደንበኞችን መመዝገብ)
2, Sales Person
3, Call Center(የደምበኞች አገልግሎት)(2 person)
4, Accountant(2 person)
5, Finance (2 person)
6, HR
Company-Makiba General Trading PLC
Salary- Attractive
Contact: @slenat_16
+251925253906
መርሐ ግብሩን ይከታተለው ነበር ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የሚሆኑ መጻሕፍትን፣ መዝሙሮችን እና ትምህርቶችን ያዘጋጁ
ነበር፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራንንም ያሠለጥኑ ነበር፡፡ በዚህ የሥራ ብዛት ውስጥ እያሉ እንኳን የሳምንቱን ግማሽ በካይሮ ቀሪውን ደግሞ በገዳማቸው ዋሻ ውስጥ ያሳልፉ ነበር በዚሁ ዓመት ሺኖዳ የመካከለኛው ምሥራቅ የነገረ መለኮት ተቋማት ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሌሎቹ ጋር የማቀራረቡን ሥራ የጀመሩት ገና በጳጳስነታቸው ዘመን ነው፡፡ በእርሳቸው መሪነት ቤተ ክርስቲያኒቱ በአያሌ የነገረ መለኮት ውይይቶች ላይ ተሳትፋለች፡፡
❤ ፓርትያርክ አቡነ ቄርሎስ በመጋቢት 9 ቀን 1971 እኤአ ዐረፉ፡፡ በመጋቢት 22 የተሰበሰበው የግብጽ ሲኖዶስም ተተኪውን ለመምረጥ ዝግጅት ጀመረ፡፡ አምስት እጩዎችንም መረጠ ነገር ግን በመካከሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ አያሌ ፈተናዎች ገጠሟት፡፡ በዚህም ምክንያት ፓትርያርክ ሳይመረጠ ረዥም ጊዜ ቆየ በጥቅምት 29 ቀን የተሰበሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ የእጩዎችን ቁጥር ወደ ሦስት ዝቅ አደረገው ፡፡ የሦስቱም እጩዎች ስም በመንበረ ማርቆስ ካቴድራል መንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ ሕዝቡ እና ገዳማውያኑም ለሦስት ቀን ሱባኤ ያዙ፡፡
❤ ጥቅምት 31 ቀን 1971 እኤአ በሰንበት ዕለት ሕዝቡ፣ ካህናቱ፣ ገዳማውያኑ እና ጳጳሳቱ በተገኙበት ጸሎት ከተደረሰ በኋላ አንድ ዓይኑን በሻሽ ለተሸፈነ አይማን ሙኒር ካሊል የተባለ ሕፃን በመንበሩ ላይ የተጸለየባቸው ስሞች ቀረቡለት፡፡ እጁን ዘርግቶ አንዱን ዕጣ አወጣው በወቅቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በጊዜያዊነት ይመራ የነበረው ኮሚቴ ሊቀ መንበር ለሆኑት ለሜትሮጶሊጣን አንቶኒዮስም ሰጣቸው፡፡ ወረቀቱን ዘረጉት "እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያናችን አባት ይሆኑ ዘንድ አቡነ ሺኖዳን መርጧል" ሲሉ አካባቢው በጭብጨባ እና በእልልታ ተናጋ፡፡
❤ ከሁለት ሳምንት በኋላ የዛሬ ዐርባ ዓመት ኅዳር 14 ቀን 1971 እኤአ በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል፣ ሺኖዳ 3ኛ የግብጽ 117 ኛውፓትርያርክ ተብለው ተሾሙ፡፡በእራሳቸው ዘመን ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደገና ኃይል አገኘች፡፡ አሁንም በነገረ መለኮት ኮሌጅ ያስተምራሉ የኮሌጁ ዲንም ነበሩ፡፡ የኤልኬራዛ መጽሔት አዘጋጅ ናቸው፡፡ ዓርብ ዓርብ ያስተምራሉ፡፡ ገዳማትን እና ትምህርት ቤቶችን አስፋፉ፡፡ ወጣቱን ወደ አገልግሎት ጠሩ፡፡ አሁንም በፓትርያርክነታቸው ዘመን በአባ ቢሾይ ገዳም የሳምንቱን ግማሽ በገዳማዊ ሕይወት ማሳለፋቸውን አልተውም መጻሕፍትን ይፅፋሉ በውጭ እና በሀገር ውስጥ ያለውን ሕዝብ ይጎበኛሉ፡፡ እርሳቸው ሲሾሙ በውጭ ያሉት አጥቢያዎች ሰባት ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን ግን በአሜሪካ እና ካናዳ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት እንኳ ከ80 በላይ አድርሰዋቸዋል ፤በአውስትራልያ 26፣ በአውሮፓ 30 አጥቢያዎች ይገኛሉ፡፡
❤ አቡነ ሺኖዳ ለአቋማቸው እና ለእምነታቸው ሲሉ ስደትን የቀመሱ ፓትርያርክ ነበሩ፡፡ ፕሬዝዳንት አንዋር ሳዳት የግብጽ መሪ በነበሩ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በምእመናኗ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመቃወም አቡነ ሺኖዳ ደጋ ግመው ይናገሩ ነበር በዚህ ያልተደሰተው ሳዳት መስከረም 3 ቀን 1981 እኤአ ባወጣው ዐዋጅ አቡነ ሺኖዳን ከመንበራቸው አሳደዳቸው በግዞትም ወደ አባ ብሶይ ገዳም ተላኩ ሕዝቡ ሌላ አባት አንመርጥም ብሎ ተከትሏቸው አባ ብሶይ ገዳም ገባ እዚያም በሚወዱት ገዳም ተጋድሏቸውን እና ትምህርታቸውን ቀጠሉ፡፡ በገዳሙ በግዞት ለአራት ዓመት ተኩል ከቆዩ በኋላ ሳዳት ሞቶ ሙባረክ ሲተካ በጥር 2 ቀን 1985 እኤአ ወደ መንበራቸው ተመለሱ፡፡
❤ አቡነ ሺኖዳ ቀልድ ዐዋቂ ናቸው በተለይ ሕፃናትን ማስተማር ይችሉበታል ሕዝቡን ሲያስተምሩም ቀልድ እና ታሪክ ጣል ማድረግ ይወዳሉ፡፡ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን የነበራቸውን የአገልግሎት ተሳትፎ በማሳደግም ሺኖዳ ከፍተኛ ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ሺኖዳ ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር ልክ የለውም፡፡ "በልባችን ውስጥ ያለችው ግብጽ ከምናያት ግብጽ ትበልጣለች" የሚለው አባባላቸው በግብጻውያን ልብ ለዘለዓለም ታትሞ ቀርቷል፡፡ ክርስቲያን እና ሙስሊሙ ሕዝብ ተከባብሮ እና ተባብሮ እንዲኖር በብርቱ ጥረዋል፡፡ በዐርባ ዓመት አገልግሎታቸው ከአንድ መቶ በላይ መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡ ንግግር ዐዋቂ፣ ባለ ቅኔ፣ ሰባኪ እና ደራሲ ናቸው ሺኖዳ፡፡ እንደዚህ ያለ ታላቅ ሰው በሀገራችን ሲሞት “አራት ሰው ሞተ” ይባላል።
❤ አባታችን አቡነ ሲኖዳ በሙስሊሞች፣ በፕሮቴስታንቶች እና በካቶሊኮች ዘንድ የሚወደዱ እና የሚከበሩ አባት ሆነዋል፡፡ የታላቁ የአልአዝሐር መስጊድ ኢማም የፖፕ ሺኖዳን ሞት ተከትሎ "ግብጽ እኒህን ጥበበኛ ሰው በምትፈልግበት ወሳኝ ጊዜ እርሳቸውን ማጣታችን የሚያንገበግብ ነው" ነበር ያሉት፡፡ ሞታቸው ለግብጽ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም የጎዳ ነው፡፡ ተወዶ የሚኖርና ተለቅሶለት የሚቀበር የሃይማኖት መሪ በዓለም ላይ እየጠፋ ባለበት በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳ በሕይወታቸውም በሞታቸውም ያስተማሩ አባት ሆነዋል በህክምና ሲረዱ ቆይተውም በመጨረሻ በተወለዱ በ88 ዓመታቸው መጋቢት 8/2004 ዓ.ም March 17/2012 ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። ከአባታችን ከአቡነ ሲኖዳ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ #ዛሬ_መጋቢት_8_የሃያ_አንደኛ_መቶ_ክፍለ ዘመን ሐዋርያ የነበሩ የግብጽ ሊቀ ጳጳስ #ለአቡነ_ሺኖዳ ሦስተኛ የዕረፍታቸ መታሰቢያ ቀን ነው።
✝ ✝ ✝
❤ #ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ፦ ዕለተ አርብ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ድል በነሳበት በመስቀሉ ፍቅር በገዛን ዕለት በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ሐምሌ 27 ቀን 1915 ዓመተ ምህረት በኮፕቲክ አቆጣጠር በዕለተ አርብ አቢብ 27 ቀን 1639 ዓመተ ሰማዕታት እኤአ ኦገስት 3 1923 በላዕላይ ግብጽ አስዩት አብኑብ በተባለ ቦታ የኮፕቲክ ብርሀን የሊቀ ዲያቆናት ሐቢብ ጊዮርጊስ ፍሬ ለቤተሰቦቻቸው የመጨረሻ ልጅ ሆነው የተወለዱት ወላጆቻቸው የሰጧቸው ስም ናዚር ጋዪድ የሚል ነበር፡፡
❤ ገና በተወለዱ በጥቂት ቀናት ውስጥ እናታቸውን በሞት ያጡት ሺኖዳ ከ5 እኅቶቻቸው እና ከ2 ወንድሞቻቸው ጋር ብቻቸውን ቀሩ የመጀመርያውን ትምህርት በዳማንሁር ባንሐ ካይሮ የተከታተሉ ሲሆን ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በታሪክ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ወሰዱ፡፡ ከዚያም ከኮፕቲክ ሴሚናሪ በነገረ መለኮት የመጀመረያ ዲግሪ አግኝተው በዚያው ሴሚናሪ የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን መምህር ሆኑ፡፡
❤ የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ከድካም ያበረታት ሐቢብ ጊዮርጊስ የሰንበት ት/ቤቶችን እንቅስቃሴ ሲጀምር ዋናው የተልዕኮው አንቀሳቃሽ ሺኖዳ ነበሩ፡፡ እርሳቸው በዚያ ወቅት የኮፕቲክ ወጣቶች ኅብረትን መሠረቱ፡፡ ለሰንበት ት/ቤቶች መጽሔቶች የተለያዩ ጽሑፎችን በማበርከት ወጣቱን ያበረቱት ነበር፡፡ በኋላ ዘመን የመንፈስ አርነት ተብሎ የታተመው መጽሐፋቸው የእነዚህ መጣጥፎች ስብስብ ነው በልጅነታቸው በጣም የተረጋጉና አስተዋይ ነበሩ በሐምሌ 18 ቀን 1954 ዓም እኤአ በዋዲ ኤል ናትሩን ወደሚገኘው የሶርያውያን ገዳም ገብተው ምንኩስናን ተቀበሉ፡፡ የገዳሙ አበምኔት እንጦንስ የሚል ስም ሰጧቸው በዚያ ገዳም ሺኖዳ አያሌ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ማንበባቸው ይነገራል፡፡ በመነኮሱ በዓመታቸው ክህነት ተቀብለው ቄስ ሆኑ፡፡
❤ ሺኖዳ ከምንም በላይ ለምንኩስና እና ለምናኔ ሕይወት ልዩ ትኩረት አላቸው፡፡ በእርሳቸው ዘመን በግብጽ የነበሩት እና ለግብጻውያን ገዳማዊ ሕይወት እንደገና ማንሠራራት ታላቅ አስተዋጽዖ ያደረጉት የኢትዮጵያዊው አብዱል መሲሕ (ገብረ ክርስቶስ) ደቀ መዝሙር ነበሩ፡፡ የገብረ ክርስቶስን ፍጹማዊ መንገድም ለመከተል ይጥሩ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ ለብዙ ዓመታት የኖሩትም በተባሕትዎ ነበር በመጀመርያ ከገዳሙ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አንድ ዋሻ ውስጥ ተቀመጡ፤ በመቀጠልም ከገዳሙ 10 ኪሎ ሜትር ወደ ሚርቅ እና በባሕር አል ፋሪግ ወደሚገኝ ዋሻ ገብተው ተጋድሎዋቸውን ቀጠሉ፡፡ ባሕታዊው የተሰኘውንና በኋላ እኤአ በ1954 የታተመውን ቅኔያቸውን የጻፉት በዚህ ጊዜ ነበር፡፡
❤ በ1959 እኤአ አቡነ ቄርሎስ VI ልዩ ጸሐፊያቸው አድርገው ሾሟቸው ሺኖዳ ግን ደስተኛ አልነበሩም ከገዳማቸው መውጣት እና በኣታቸውን መልቀቅ አያስደስታቸውም ነበር ብዙ ጊዜያቸውንም የሚያሳልፉት በዋሻቸው ውስጥ በጸሎት እና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ነበር፡፡ ለብዙ ጊዜያትም ወደ ኤጲስ ቆጶስነት እንዳይጠሩ ሲከላከሉ ኖረዋል በ1962 እኤአ ሺኖዳ በነበሩበት ገዳም ውስጥ አንድ አስተዳደራዊ ችግር ተፈጠረ ጉዳዩም ወደ ፓትርያርክ ቄርሎስ VI ዘንድ ቀረበ በዚያ ጊዜ ሺኖዳ በገዳሙ አስተዳደር ውስጥ ነበሩበት ገዳማውያኑ እንደ ጥንቱ አበው ሆነው እንዲኖሩ፣ ገዳማት የችግር ቦታዎች ሳይሆኑ የጸሎት ቦታዎች እንዲሆኑ፤ የግብጽ ገዳማት አዲሱን ትውልድ ለመቀበል በሚችሉበት መንገድ እንዲደራጁ፤ ገዳማውያኑ ሥራ፣ ጸሎት እና ትምህርትን አጣምረው እንዲይዙ ይታገሉ ነበር ይህ የሺኖዳ ሃሳብ ያልተስማማቸው አንዳንድ ገዳማውያንም ሺኖዳን ከሰው ወደ ቄርሎስ ዘንድ አቀረቧቸው፡፡
❤ አቡነ ቄርሎስ VI ሺኖዳን አስጠሯቸው ሺኖዳ በቄርሎስ እግር ሥር ተደፍተው "አጥፍቻለሁ፣ ድሮም ኃላፊነቱን የተቀበልኩት ያለ አቅሜ ነው፡፡ እባክዎ ከኃላፊነት ያንሱኝና በዋሻዬ ብቻ ተወስኜ ልኑር፡፡ እኔ ደካማ ሰው ነኝ" ሲሉ ለመኗቸው፡፡ አቡነ ቄርሎስም "ዛሬ እንደርና ነገ ውሳኔዬን አሳውቃለሁ" አሉ፡፡ በማግሥቱ መስከረም 30 ቀን 1962 ዓ.ም እኤአ ፓትርያርክ ቄርሎስ እና ሌሎች ጳጳሳት የሺኖዳን ጉዳይ ለማየት በመንበረ ፓትርያርኩ ተሰባሰቡ ሺኖዳ ውሳኔውን በጉጉት ነበር የጠበቁት ኃላፊነት ከሚባለው ነገር ተገላግለው የምናኔ ሕይወታቸውን ብቻ ለመያዝ ፈልገዋል ሺኖዳ ተጠሩ ጳጳሳቱ ቆሙ፡፡ ሁሉም ቄርሎስን ያይ ነበር ሺኖዳ እንዲንበረከኩ ተነገራቸው፡፡ ተንበረከኩ ቄርሎስ እጃቸውን በሺኖዳ ላይ ጫኑ ሌሎች ጳጳሳትም ወደ እርሳቸው መጡ ሳይታሰብ አቡነ ሺኖዳ ተብለው የግብጽ የመንፈሳውያን ኮሌጆች እና የትምህርት ተቋማት ጳጳስ ሆነው ተሾሙ ሺኖዳ ደነገጡ ፤ አለቀሱም፡፡
❤ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥናት በማድረግ የታወቀው የካይሮ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሩ ጀርመናዊው ኦቶአ ሜናድረስ የአቡነ ሺኖዳን መሾም ሲሰማ እንኳን ደስ ያለዎት የሚል ደብዳቤ ላከላቸው ሺኖዳ ግን የመለሱለት የሚከተለውን ነበር "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ካንተ ጋር ይሁን፡፡ እንኳን ደስ ያለዎት ብለህ በቅንነት ስለላክህልኝ መልእክት አመሰግንሃለሁ፡፡ ያንተን ወዳጅነት እና ፍቅር መቼም አልዘነጋውም፡፡ እውነቱን ለመናገር ግን ለእኔ መላክ ያለበት የኀዘን ደብዳቤ እንጂ የደስታ ደብዳቤ አይደለም፡፡ አንድ መነኩሴ ጸጥታ የተሞላበትን የጸሎት በረሃ ለቅቆ ጫጫታ እና ሁካታ በተሞላበት ከተማ እንዲኖር ሲደረግ እንዴት እንኳን ደስ ያለህ ይባላል? ማርያምን ከክርስቶስ እግር ሥር ተነሥታ ማርታን ልታግዝ ወደ ጓዳ ስትገባ ማነው እንኳን ደስ ያለሽ የሚላት? ለእኔ ይህ ደስታ ሳይሆን ሐፍረት ነው፡፡ እኔ ኤጲስ ቆጶስ ሆኜ የተሾምኩበትን ቀን በደስታ ሳይሆን በኀዘን እና በለቅሶ ነው የማስታውሰው፡፡ ብሕትውና እና የተጋድሎ ጸሎት ከምንም በላይ የሚበልጥ ነገር ነው፡፡ ብሕትውና እና ምናኔ ከኤጲስ ቆጶስነት ቀርቶ ከፓትርያርክነት ጋር እንኳን የሚወዳደር አይደለም፡፡ "ወዳጄ ሆይ እውነተኛው ቅድስና ሲመት ሳይሆን ልብን ቤተ መቅደስ አድርጎ ለክርስቶስ መቀደስ ነው፡፡ ክርስቶስ በመጨረሻው ቀን የልባችንን ንጽሕና እንጂ የክህነታችንን መዓርግ አይጠይቀንም ይህንን ደብዳቤ የምጽፍልህ በምወዳት ዋሻዬ፣ በባሕር አል ፋሬግ፣ በዋዲ ኤል ናትሩን ውስጥ ሆኜ ነው፡፡ እዚህም እስከ ጥምቀት ድረስ ለመቆየት አስባለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ካይሮ እመለሳለሁ"፡፡
❤ አቡነ ሺኖዳ እያለቀሱ ያቺን የዋዲ ኤል ናትሩን ዋሻ ትተው ካይሮ ቢመጡም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወደ ዋሻቸው መሄድ ያዘወትሩ እንደ ነበር ታሪካቸውን የጻፈላቸው የቅርብ ወዳጃቸው እና በእምነቱ ፕሮቴስታንት የነበረው ኦቶአ ሜናድረስ ይናገራል፡፡ እስከ 1969 እኤአ ድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱን የትምህርት ተቋማት በዘመናዊ መልኩ አደራጇቸው፡፡ በዚህ የተነሣም በሙሉ ጊዜያቸው የሚሩ ተማሪዎች ቁጥር ከ100 መቶ ወደ 207 አደገ፡፡ ሺኖዳም በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ ሕዝቡን የሚያስተምሩበት እና የሕዝቡን ጥያቄዎች የሚመልሱበት የትምህርት መርሐ ግብር ከፈቱ እስከ 10000 የሚጠጋ ሕዝብም
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ #መጋቢት ፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን ብዙዎች ሰማዕታትን አሠቃይቶ ይገድል ለነበረው ለእንዴናው ገዥ #ለቅዱስ_አርያኖስ በሰማዕታቱ ጸሎት አምኖ እርሱም ራሱ በንጉሡ በዲዮቅልጥያኖስ ፊት የጌታችን አምላክነት መስክሮ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለእስክንድርያ ዐሥራ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ዮልዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #መኰንን_ቅዱስ_አርያኖስ፦ ይህም እንዲህ ነው የከበሩ ፊልሞንና አብላንዮስ በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ከሞቱ በኋላ እርሱም በሥቃይ ውስጥ ሳለ ከአማንያን አንዱ ከቅዱሳን ከደማቸው ወስደህ ዓይንህን ብትቀባ በዳንክ ነበር አለው። ያን ጊዜም ከደማቸው ወስዶ ዐይኑን ቀባ ወዲያው ድኖ ፈጥኖ አየ።
❤ ከዚህም በኋላ በቅዱሳን ላይ በአደረገው ክፉ ሥራ ሁሉ በድንቁርናውም ምሕረት የሌለው ሥቃይ ስለ አሠቃያቸው ታላቅ ጸጸት ተጸጽቶ አዘነ ተነሥቶም ጣዖታትን ሰበረ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምኖ ምእመናንን ማሠቃየቱንም ተወ።
❤ ዲዮቅልጥያኖስም ወሬውን በሰማ ጊዜ ጭፍሮቹን ልኮ ወደርሱ አስመጣው "በምን ምክንያት አማልክትን ማምለክ እንደ ተወ" ጠየቀው። እርሱም "በቅዱሳን ሰማዕታት እጅ እግዚአብሔር የሚሠራቸውን አስደናቂዎች ተአምራት ሊነግረው ጀመረ ሕዋሳታቸውን እንዴት እንደ ሚቆራጡአቸው በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም ሲያሠቃዩዋቸው ያለምንም ጉዳት ጤነኞች ሁነው ተመልሰ እንደሚነሡ" ነገረው። ዲዮቅልጥያኖስም የተአምራትን ነገር ስለ ነገረው ተቆጣ ጽኑ የሆነ ሥቃይንም እንዲያሠቃዩት አዘዘ። ሁለተኛም ከጉድጓድ እንዲጨምሩትና እስኪሞትም የጉድጓዱን አፍ እንዲዘጉ አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልአኩን ልኮ ከጉድጓዱ አውጥቶ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ መኝታ ላይ አቆመው። ንጉሡም በነቃ ጊዜ አይቶ ደነገጠ፣ ፈራ "ማንህ አንተ" አለው።እርሱም "እኔ የእዴናው ገዥ አርያኖስ ነኝ" ብሎ መለሰለት ንጉሡም ደንግጦ እየተንቀጠቀጠ በማቅ ጠቅልለው ከባሕር እንዲያሰጥሙት አዘዘ። በባሕሩም ውስጥ ነፍሱን በጌታችን እጅ መጋቢት8 ሰጠ።
❤ እንዲህም ሆነ ቅዱስ አርያኖስ ዘመዶቹንና አገልጋዮቹን ሲሰናበታቸው እንዲህ ብሎ ነገራቸው "ለሥጋዬ እርሱ እንደሚያስብና ወደአገሬ ወደእንዴናው እንደሚመልሰው በሌሊት ራእይ እግዚአብሔር አስረድቶኛልና እንተም በእስክንድርያ ወደብ ሥጋዬን ጠብቁ" አላቸው። በአሰጠሙትም ጊዜ ጌታችን ዓሣ አንበሪን አዘዘ አንበሬውም ተሸክሞ ወስዶ በእስክንድርያ ወደብ አውጥቶ በየብስ ላይ አኖረው። አሽከሮቹ ከዚያ እየጠበቁት ነበር። ወደ አገሩ ወደ እንዴናው አድርሰው ከቅዱሳን ሰማዕታት ከፊልሞና ከአብላንዮስ ከሥጋቸው ጋር በአንድነት አኖሩት። የቅዱስ አርያኖስ በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዮልዮስ፦ ይህም አባት አስቀድሞ በእስክንድርያ ቄስ ሆኖ ነበር። እርሱም በአለበት ዘመን በግብጽ አገር እንደርሱ ያለ የሌለ አዋቂ ብልህ የሆነ ምሁር ነበር። የክብር ባለቤት በሆነ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ ብዙዎች ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ።
❤ የሹመቱም ዘመን በሰላም የሰፈነበት ነበር በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ሕግና ሥርዓትንም ሁሉ እንዲጠብቁ ሕዝቡን ሁል ጊዜ ይመክራቸውና ያስተምራቸዋል።
❤ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ዐሥር ዓመት ከኖረ በኋላ መጋቢት 8 በሰላም በፍቅር ዐረፈ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 8 ስንክሳር።
❤ "#ሰላም_ለአርያኖስ_አማልክቲሁ_ኀዲጎ። ዘተለወ ፍጹመ ለእግዚአብሔር ሕጎ። ዲዮቅልጥያኖስ ምዑክ ቢጸ አራዊት በዛውጎ። እምድኅረ ደፈኖ አፈ ግብ መሪጎ። መልዕልተ ምስካቡ ንጹፍ ተረክበ ዐሪጎ"። #ሊቁ_አርከ ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢት_8።
አሉ።
❤ የተባረከው ሐዋርያ ቅዱስ ማትያስም የአማልክቱን አዳራሾች ሁሉ ያፈርሱ ዘንድ በውስጥ ከሚደርጉት ክፉ ተግባር የተነሣ ከእርሱ ምንም እንዳይገናኙ ከባሕር ይጥሏቸው ዘንድም ይህን አዘዛቸው። ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ስምም ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው። በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምም አጠመቃቸው። የአገሩን ሰዎችም ወንዶችንም፣ ሴቶችንም፣ ሕፃናቱንም አንድ በሆነ በማይከፈል በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው።
❤ ከጥምቀት በኋላ ቤተ ክርስቲያኒቱን አከበረላቸው (ባረከላቸው)። በይቅርታና በሕይወት ትምህርትም ገሠጻቸው። የወንጌልን ሕግም አስተማራቸው፤ ከእርሱም ተለየ። ሁሉም በሰላም ሸኙት። እርሱ ትክክለኛውን ዕውቀትና ቅን የሆነች መንገድን አስተማሯቸዋልና። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የማመን ዕውቀትን በማስተማርም ከስህተት አድኗቸዋልና።
❤ ካስተማረና የምስራችን ከነገረ በኋላም መልካም እንቅልፍን ተኛ። ከይሁዳ አገሮች ፍዕላዎን በምትባል አገርም በጌታችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ጸጋ መጋቢት ስምንት ቀን ዐረፈ። ምስጋናና ክብር ለእርሱ ይሁን ። ከሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎቱ ይማረን!። አሜን ምንጭ፦ ገድለ ሐዋርያትና የመጋቢት 8 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለማትያስ_ዘተኀረየ_ወተፈቅረ። ህይንተ ይህዳ ይተኌለቊ ምስለ ሐዋርያት ኅቡረ። ከዊኖ #ማትያስ በላእለ እኩያን ኄረ። ሥጋ ወልደ አምላክ ሴሰዮሙ ወደሞ ክብረ። ተውላጠ ሴሰይዎ ሎቱ ከመ ላሕም ሣዕረ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢት_8።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ ያድኅነኒ ምንትኑ ያፈርሀኒ። እግዚአብሔር ምእመና ለሕይወትየ ምንትኑ ያደነግፀኒ። ሶበ ይቀርቡኒ እኩያን ይብልዑኒ ሥጋየ"። መዝ 26፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 18፥35-ፍ.ሜ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 2፥1-17 ይሁዳ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥15-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥1-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ማትያስ የዕረፍት በዓልና የጾም ወራት። በሁላችንም ይሁንልን።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፰ (8) ቀን።
❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ በአስቆርቱ ይሁዳ ፈንታ ለተሾመው #ለቅዱስ_ማትያስ_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ማትያስ፦ ይህ ሐዋርያ የአስቆሮቱ ይሁዳ የሰማይና የምድር ንጉሥ በሚሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም ሰይጣንና ሠራዊቱ ያፍሩ ዘንድ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ ይሁዳ ግን ከፍጥረቱ ሁሉ ተለይቶ ምስኪንና ጐስቋላ ነበር። ጌታውን ክፋ ለሆኑ አይሁድ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ሄደና ራሱን አጠፋ። ክብሩንም አጣ፤ ከሐዋርያት ዙፋንም ተጣለ። ስለእርሱም ማትያስን ሾመው። ቅዱስ ማትያስም ያስተምር ዘንድ ወደ ደማስቆ ወጣ። ዕጣም እንዲያስተምር ደርሶታልና። ቅዱስ ወንጌልንም አስተማራቸው።
❤ ይህም ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ወንጌልን ይሰብክላቸው ዘንድ በሔደ ጊዜ ወዲያውኑ ይዘው ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት ምግባቸው የመጻተኛ ሰው በድን ስለሆነ ልማዳቸውም እንዲህ ነው። መጻተኛ ሰው ሲይዙ ዐይኖቹን አውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል። የያዙበትንም ቀን ይጽፋሉ ሠላሳ ቀንም እስቲፈጸም ሣር ያበሉታል ከዚያ በኋላም አውጥተው አርደው ይበሉታል።
❤ ሐዋርያ ቅዱስ ማትያስም ታሥሮ ሳለ ሠላሳው ቀን ሳይፈጸም በጌታችን ትእዛዝ ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ወደርሱ ደረሰ የአገሩ ሰዎች የሚሠሩትን ክፋ ሥራ አይቶ አደነቀ እጅግም አዘነ እሥረኞችንም ሁሉ አውጥቶ የአገር ሰዎች ወደማያገኙአቸው ቦታ አኖራቸው። እነርሱ ግን ሁለቱ ሐዋርያት ቅዱሳን እንድርያስና ማትያስ ተገለጡላቸው የአገሩም ሰዎች ያዙአቸው በአንገታቸውም ገመድ አስገብተው እስከ ሦስት ቀን በአገሩ ጥጋጥግ ጐተቷቸው ሐዋርያት ስለዚያች አገር ሰዎች ስለድኅነታቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ያንጊዜ ከወህኒ ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃን አፈለቁ ውኃውም ከፍ ከፍ ብሎ በአገር ውስጥ እስከሚአጥለቀልቅና ወደ ሰዎች አንገት እስከ ደረሰ አየበዛ ሔደ። በተጨነቁና የሕይወታቸውን ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ወደ ሐዋርያት መጡ በፊታቸውም ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ አለቀሱ ሐዋርያትም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ እናንተም ትድናላችሁ አሉአቸው እሊያ ሁሉም በክብር ባለቤት በጌታችን አመኑ።
❤ ሐዋርያትም አሰተማሩአቸው ገሠጹአቸውም የአንድነትን የሦስትነትን የመድኃኒታችን ሰው የመሆኑን ምስጢር ገለጡላቸው ደግሞም ይህን የአራዊት ጠባይ ጌታችን ከእነርሱ ያርቅ ዘንድ ጸለዩላቸው ከዚህ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው ያ የአውሬ ጠባይ ከእርሳቸው ርቆ ሰው የሚመገበውን የሚመገቡ የዋሆች ቅኖች ሆኑ። ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትና ዲያቆናትንም ሾሙላቸው በቀናች ሃይማኖትም እያጸኑዋቸውና እያስተማሩዋቸው ሠላሳ ቀኖች ያህል ከእርሳቸው ጋር ኖሩ ከዚህም ወጥተው ሔዱ። የአገር ሰዎች ግን በሌላ ጊዜ ወደ እነርሱ እንዲመለሱላቸው ሐዋርያትን ለመኑዋቸው።
❤ ከዚያም ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ ወደ ደማስቆ አገር በገባ ጊዜም "በኃጢአታቸው የወደቁትን እውነተኛ እግዚአብሔር የማያውቁትን ሰነፍ ሰዎች ሆይ አምላካችሁ ሌላ ሰው ሠራሽ ነው። ሰዎች ሁሉ እንደ እናንተ የወደቁ እንዲሆኑም ትሻላችሁ? በደማስቆ የምትኖሩ ሰዎች ሆይ ትምህርቴን ስሙ አማልክትን ማምለክም ተው። ስህተትን ክፋ መሥራትንም ከእናንተ አስወግዱ። ወደ ፈጣሪያችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። ከእኔ ትምህርት የተነሣም ተመለሱ። እኔም ወደ እግዚአብሔር አቀርባችኋለሁ። እርሱ ለመንግሥቱ የተዘጋጃችሁ ያደርጋችኋል። የመላእክትን ሥርዓት አስተምራችሁ ዘንድም ወደ እኔ ተመለሱ። እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ሕያዋን ትሆኑ ዘንድም የሕይወት ኅብስት እንዲሰጣችሁ ወደ እኔ ተመለሱ። የሰው ሥራ የሆኑ አማልክትንም እንቢ በሏቸው። የእውነተኛው አምላክ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ትሆኑ ዘንድም ከሰይጣናዊ ምክንያት ራቁ። ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይና የምድር ገዢ ነው፤ የወረደው፣ ያለወንድ ዘር በድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረው የእግዚአብሔር ቃል ቀዳማዊ ነው፤ የአዳምን ዘር በክብሩ በገናናነቱ የማይታይ ሰይጣንን ከማምለክ ያድነው ዘንድም መከራን ተቀበለ፤ እንደ ሥጋዊ ልጅም በምድር አባት ያለው አይደለም፤ እርሱም ያለመለየት ከአባቱ ጋር አለ፤ እርሱ ሁሉንም በጥበቡ ያረጋጋል፤ ከመሬት አፈርን የወሰደና አዳምን ከአፈር የፈጠረውም እርሱ ነው፤ የመጀመርያው አባትም እርሱ ነው፤ ይህ አምላክም ፍጥረታት ሁሉ ነፍስ በእጁ ናት፤ እርሱ ይወዳቸዋል፣ መመለሳቸውም በቀናች ሃይማኖት በምታምር ሕሊና ነው፤ እርሱ አባቱና መንፈስ ቅዱስ አንድ ናቸው፤ሦስትም ናቸው፤ አንድ መለኮት አንድ ሥልጣን" አላቸው።
❤ በመጀመሪያ የማዝዛችሁም "ከርኵሰት ሁሉ ትርቁ ዘንድ ነው፤ እግዚአብሔር ንጽሕናችሁን እንዲመለከትና ሰማያዊትና መንፈሳዊት በሆነች በረከት እንዲባርካችሁ፣ በፍርድ ቀንም እንዲምራችሁ ከሴት ጋር አንድ መሆንን (መገናኘትን) አታብዙ" አላቸው።
❤ የአገሩ ሰዎችም ይህን ነገር ከእርሱ በሰሙ ጊዜ በምክንያቱና በክፉ ሥራው ሰይጣን በልባቸው አደረ። እርስ በእርሳቸውም "በእውነትም ይህ ሰው በአገሩ ከሚዞሩ ከዐሥራ ሁለቱ ጠንቋዮች ወገን ነው፤ ሴቶችን ከባሎቻቸው ይለያሉ ምን እንደምታደርጉት አስቡ" ተባባሉ። እነርሱም ተሰበሰቡ። ሐዋርያውንም ያዙትና አሰሩት። በብረት አልጋም አስቀመጡት። ሥጋው እስከ ሚሸት ድረስም በታቹ እሳት አነደዱበት እያንዳንዳቸውም ተመለከቱ። ቁመቱ ከአልጋው ዐሥራ አምስት ክንድ ሆኖ የእሳቱ ነበልባል ከፍ ባለ ጊዜም አደነቁ።
❤ በአደባባይ የቆሙና የተሰበሰቡ ሰዎችም "ይህ ሰው ጠንቋይ ቢሆን ኖሮ እነሆ በጠፋ ነበር" ተባባሉ። ከሦስት ቀን በኋላም ክፉ ተገባራቸው ይገለጣል። ሦስት ቀን ከሆነ በኋላም ቅዱስ ማትያስን ያስቀመጡበት የብረት አልጋ ካለበት ቦታ በደረሱ ጊዜ በእሳት ሳይቃጠል በሕይወትም አገኙት፤ ዓይኖቹም የተገለጡ ነበሩ፤ በጤናም አገኙት፤ ምንም ዓይነት ጥፋት አላገኘውም፤ በእርሱ ላይ ምንም ዓይነት የእሳት ሽታ አልነበረም፤ ልብሱም አልተቃጠለም።
❤ የአገሩየአገሩ ሰዎች ለተባለረከው ሐዋርያ የእግዚአብሔር ይህን ይቅርታ በተመለከቱ ጊዜ ከአገሩ ሰዎች ብዙዎቹ በእግዚአብሔር አመኑ። ይህ አምላካቸው ነውም አሉ። ሰባት ቀንም ስምንት ቀንም አለፈ። ቅዱሱ ግን በአልጋው ተኝቶ ነበር። የአገሩ ሰዎችም ሁሉ ይመለከቱት ነበር። በዚህም ከአገሩ ሰዎች ብዙዎች በትክክለኛዋ ሃይማኖት አመኑ። በተባረከው ሐዋርያ በቅዱስ ማትያስ ትምህርትም አመኑ። በትምህርቱ ያላመኑም ነበሩ። እሳቱም ሃያ አራት ቀን ይንቦገቦግ ነበር።
❤ ሐዋርያው ስሙን የሚጠራው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቀንና በሌሊት ሁሉ ምንም እንዳይነካው ከክፉ ነገር ያድነው ነበር።በእርሱ ስም መከራን ተቀብሏልና። ከዚህ በኋላም ከእሳቱ አወጡት። ሥጋውም ሕያው(ጤነኛ) ነበር። ፊቱም እንደ ሕፃናት ፊት ነበር። ሁሉም ወደ እርሱ ይመለከቱ ነበር። እርሱ በእሳት ውስጥ አልነበረም። "ከራሱ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ ጤነኛ ነውና" አሉ። በዚያችን ሰዓትም የአገሩ ሰዎች ብዙዎች አመኑ። በአገሩ ያሉትም ሁሉ ጮኹ "በቅዱስ ስሙየሚያምኑበትን ሁሉ ከአዳናቸው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከቅዱስ ማትያስ አምላክ ከእግዚአብሔር በስተቀር በሰማይም በምድርም ሌላ አምላክ የለም"
+4
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።
እኔስ፦ አቤቱ፥ ማረኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት አልሁ።
መዝ 41÷3-4
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት በአብይ ጾም ፬ተኛ ሳምንት መጻጉዕ በደብራችን የማለዳው ጉባዬ በዚህ ሁኔታ አሳልፈናል ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።
📷 ከፍኖተ ብርሃን የሚዲያና ዕቅበተ ዕምነት ክፍል የምስል ማህደር በጥቂቱ ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለዐቢይ_ጾም_አራተኛ_ሳምንት_ለመጻጒዕ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የመጻጒዕ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "#አምላኩሰ_ለአዳም_ለዕረፍት_ሰንበተ_ሠርዐ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ #ወይቤሎሙ_ኢየሱስ አነ እገብር አንትሙኒ እመኑ በግብርየ #አነ_ውእቱ_እግዚኣ_ለሰንበት_ወልድ_ዋሕድ ወይቤሎሙ ብውህ ሊተ ኅድግ በዲበ ምድር እስብክ ግዕዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ"። ትርጉም፦ #የአዳም_አምላክ_ሰንበትን_ለዕረፍት ሠራ፤ አይሁድ በምን ሥልጣን ይህን ታደርጋለህ አሉት፤ #ኢየሱስም_በራሴ_ሥልጣን_አደርጋለሁ፤ እናንተ ግን በሥራዬ እመኑ፤ #እኔ_የሰንበት_ጌታ_ነኝ፤ እኔ ወልድ ዋሕድ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር እል ዘንድ፤ ነጻነትን እሰብክ ዘንድ #የዕውራንን_ዐይን_አበራ_ዘንድ የባሕርይ አባቴ ላከኝ አላቸው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ #መጻጒዕ፦ አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት "መጻጒዕ" ይባላል። ፀግ0 ፤መጻጕዕ፦ በቁሙ ጎባጣ በጀርባው ላይ እንደ ሻኛ ያለው ደረቱ ከጉልበቱ የተጠጋ ሕመምተኛ በሽተኛ ማለት ነው።
❤ በዚህ ሣምንተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሳ መዝሙር ይዘመርበታል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጌትነቱ ምልክት በሕዝቡ ያሉ ድውያንን ሁሉ ይፈውስ ነበር። የተአምራቱም ዜና በሶርያ በአራቱ ማዕዘን ደረሰ ተብሎ በተነገረው መሠረት ቅዱስ ማቴዎስ 4፥23-25 አንደጻፈው ቀጥለን እናያለን በማቴ 8 ፥1-4 ከተራራ በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት ለምጻም ቀርቦ ጌታ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና ንፃ አለው ወዲያውም ለምፁ ነፃ።
በማቴ 8፥5-13 የመቶ አለቃውን ልጅ በቃሉ ፈወሰ፣ የጴጥሮስ አማት ከንዳድ ፈወሳት። በማቴ 8 ፥14 አጋንንት አወጣ ማቴ 8፥16ና በማቴ 8፥28 በዚህ ተአምራት የምንረዳው ቁም ነገር በሰዎች ያደሩ አጋንንት ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ ብለው ማመናቸውን ነው። የሐዋ 19÷15፤ ያዕ 2÷19።
❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈወሳቸው ሕሙማን ብዙ ሲሆኑ ለምሳሌ ያህል ከላይ በጠቀስነው በማቴዎስ ምዕራፍ 8 ያሉትን እንዳዳነ ሁሉ በሌሎች ወንጌላውያን ምዕራፍና ቁጥርም በርካታ በሽተኞችን እንደፈወሰ ተገልጿል ከተፈወሱት ሰዎች መካከል የኻያ ሦስቱ ታሪክ ተገልጦአል ከእነርሱ ሌላ ኢየሱስ ሦስት ሙታንን አስነስቶአል አንደኛ የኢያኢሮስን ሴት ልጅ (ማቴ 9፥18-26) ሁለተኛ የመበለቲቱን ልጅ ፈወሳት (ሉቃ 7÷11-17) ሦስተኛውም ደግሞ አልዓዛር (ዮሐ 11፥43-44)፡፡
❤ ክርስቶስ በአምስት አይነት መንገድ ሕሙማን ፈወሰ።
1) በቃሉ (ማቴ8፥16፡፡ ዮሐ 4÷50)
2) በመዳሰስ (ማቴ 8፥} ፣ ሉቃ 5÷13)
3) እጅ በመጫን(ማር 6፥5፣ 8፦22)
4) ጭቃን በመቀባት (ዮሐ 9÷6-7)
5) በልብሱ ጫፍ (ማቴ9፥20፡፡ 14፥36)
❤ እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው (ዘጸ 15፥26) ፈዋሽነቱ ለሁሉ ቢሆንም በሰፊው የሚነገረው ግን በዮሐ 5÷5-15 ያለ በሽተኛ ነው። ይኸውም ኋላ ጌታችን ኢየሱስን በጥፊ የመታው ነው ብለው ሊቃውንት ይተረጉማሉ (ዮሐ 18፥22)። ምንጭ፦ ከመምህረሰ አምኃ ሥላሴ (መኩርያ ተስፍዬ) ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ። ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ። አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ"። መዝ 40፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 5፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 5፥14-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 5፥1-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበት (መጻጕዕ)ና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።
የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መጻጒዕ
እንኳን አደረሳቹ የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መጻጒዕ ለ 38 ዓመት በአልጋ ላይ ተኝቶ የሚኖር አንደ ሰው ነበረ እርሱም መጾጒዕ ይባላል።
((ዮሐ5፥1-11)) ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ ኢየሱስም ወደ አየሩሳሌም ወጣ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ "ቤተ ሳይዳ" የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች አምስትም መመላለሻ ነበረባት፤ በእነዚህ ውስጥ የወኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና፣ ዕዉሮች፣ አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ በዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር አንደንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከወኃውን መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።
በዚያም "ሠላሳ ስምንት" ዓመት ያህል ይታመም የነበረ አንድ ሰው ነበረ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ ልትደን ትወዳላህን? አለው።
ድውዮም፦ አዎ ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ወስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም! ነባር ግን እኔ ስመጣ ሳላሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለስለት፣ ኢየሱስም ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው፣ ወዲያውም ሰውየው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።
ያም ቀን "ሰንበት" ቀን ነበረ ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው "ሰንበት" ነው አልጋውን ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት እርሱ ግን ያዳነኝ ያ ሰው "አልጋውን ተሸክመህ ሂድ" አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
((ማቴ9÷1)) በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ እነሆም በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ ኢየሱስ እምነታቸውን አይቶ ሽባውን አንተ ልጅ አይዞህ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።
((መዝ 40፥3)) እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳላ ይረዳዋል መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል።
አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በየጸበሉ በሆስፒታሉ የታመሙትን ምህረትህን ለሚናፍቁ የምህረት እጅህን ዘርጋላቸው እኛንም የመጣብንን መቅሰፍት በቸርነትህ ያዝልን!
የሐዋሪያት የነብያት የቅዱሳን አበው ጸሎት ልመና የተቀበልክ አምላክ የእኛንም ተቀበል! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
“ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።”
ማቴዎስ 4፥4
በዛሬው ዕለት የሰማዕቷ እናታችን የቅድስት አርሴማ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በጠዋቱ መርሃ ግብር ላይ የእግዚአብሔርን ወንጌል ቃል በሚያስደንቅ አንደበታቸው ለምእመናን ሲመግቡ ቆይተዋል።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እዲሁም በምሽቱ ጉባዬም የተሳካ ጉባዬ አካሄደናል አምላከ ቅድስት አርሴማ ለነገውም በሰላም አሳድሮ ያድርሰን።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
📷 ከሚዲያና ዕቅበተ ዕምነት ክፍል የምስል ማህደር በጥቂቱ በምስልና በድምፅ ይህን ይመስላል።
Repost from የግ/ደ/ቅ/አርሴማ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ቤት መዝሙር ክፍል
+9
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
“ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።”
ማቴዎስ 4፥4
በዛሬው ዕለት የሰማዕቷ እናታችን የቅድስት አርሴማ ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በጠዋቱ መርሃ ግብር ላይ የእግዚአብሔርን ወንጌል ቃል በሚያስደንቅ አንደበታቸው ለምእመናን ሲመግቡ ቆይተዋል።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
እዲሁም በምሽቱ ጉባዬም የተሳካ ጉባዬ አካሄደናል አምላከ ቅድስት አርሴማ ለነገውም በሰላም አሳድሮ ያድርሰን።🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
📷 ከሚዲያና ዕቅበተ ዕምነት ክፍል የምስል ማህደር በጥቂቱ በምስልና በድምፅ ይህን ይመስላል።
ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት ፮
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጋቢት ስድስት በዚች ቀን በእስላሞች ዘመነ መንግሥት ዲዮስቆሮስ በሰማዕትነት አረፈ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ሰማዕት ዲዮስቆሮስ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ ሰዎች ወገን ነው በማግባባት በመገፋፋት ከክርስቲያን አውጥተው ወደ እስልምና አስገቡት በእምነታቸውም ጥቂት ጊዜ ኖረ፤ ፍዮም በሚባል አገር ለአንድ ክርስቲያን ሰው የተዳረች አንዲት እኀት ነበረችው ወንድሟ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት እንደ ተወ በሰማች ጊዜ ታላቅ ኀዘንን አዘነች።
❖ ከዚህም በኋላ እንዲህ ብላ ወደርሱ መልእክትን ላከች የክብር ባለቤት ክርስቶስን አንተ እንደ ካድከው ከምሰማ በክርስትናህ ሳለህ የሞትህ መርዶ ቢመጣልኝ እወድ ነበር፤ ከዚያም ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሳ ጻፈችለት በደብዳቤዋ ፍጻሜም እንዲህ ብላ ጻፈች ።
✍️"ከዛሬ ጀምሮ ወደክርስትናህ ካልተመለስክ ይህቺ ደብዳቤ በእኔና በአንተ መካከል የፍቅር ፍጻሜ እንደሆነች ዕወቅ ከቶ ፊትህንም እንዳታሳየኝ መልእክትም ቢሆን አትላክልኝ"
❖ የእኅቱንም የመልእክት ደብዳቤ በአነበበ ጊዜ መሪር ዕንባን አለቀሰ ተጸጸተ ፊቱን ጸፋ ጽሕሙንም ነጨ ተነሥቶም ወገቡን ታጠቀ ረጅም ጸሎትንም በመጸለይ ማለደ ፊቱንም አዳኝ በሆነ መስቀል ምልክት አማተበ ከቤቱም ወጥቶ በእስክንድርያ ከተማ ውስጥ ተመላለሰ።
እስላሞችም በአዩት ጊዜ ይዘው ወደ መኰንኑ አቀረቡት መኰንኑም ከእርሱ ስለሆነው ነገር ጠየቀው እርሱም ክርስቲያን ነኝ ሌላ ምንም ምን አላውቅም ብሎ መለሰ፤ መኰንኑም ደግሞ የክርስቲያንን ሃይማኖት ትተህ ወደእኛ እምነት ገብተህ አልነበረምን ብሎ መለሰለት።
❖ ቅዱስ ዲዮስቆሮስም መልሶ እንዲህ አለ በወልድ የማያምን ሕይውትን አያያትም የእግዚአብሔር የቁጣው መቅሠፍት በላዩ ይወርዳል እንጂ የሚል በከበረ ወንጌል ተጽፏል፤ ስለዚህ እኔ በክብር ባለቤት በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ እኔም ትውልዴ ከክርስቲያን ነው አሁንም በክርስትናዬ እሞታለሁ፤ መኰንኑም እጅግ ተቆጥቶ ከዚህ ምክርህ ካልተመለስክ እኔ የጸና ቅጣት እቀጣሃለሁ አለው። ቅጣቱንም ፈርቶ ከመልካም ምክሩ አልተመለሰም።
❖ ከዚያም በኋላ ታላቅ ግርፋት ገርፎ አሠረው በእሥር ጥቂት ቀናት ቆየ ከእሥር ቤትም አውጥቶ ከምክሩ ከሐሳቡ ቢመለስ ብዙ ገንዘብ ሊሰጠው ቃል ገባለት፤ ይህ ካልሆነ ግን በእሳት እንደሚአቃጥለው ነገረው፤ ቅዱሱም ሕያው በምታደርግ ከክርስቲያን ሃይማኖት በቀር በሌላ አልሞትም ብሎ መለሰለት።
❖ መኰንኑም በእሳት እንዲአቃጥሉት አዘዘ ከከተማም ውጪ ታላቅ ጉድጓድ ቆፈሩለት፤ ዕንጨትም መልተው አነደዱት ነበልባሉም እጅግ ከፍ ከፍ አለ ያን ጊዜም ብዙ ገርፈው ሥጋውን በሰይፍ ሰነጣጠቁ፤ ወደ እሳትም ጨመሩት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጥቶ በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ።
ጸሎቱና በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም መዲዮስቆሮስ መንገለ አሚን ዘተስሕበ። መልእክተ እኅቱ ብዕዕት በጊዜ አንበበ። ንትፈተ ሥጋሁ በኀፂን ኢያስተዓፀበ። ወአስታቃለለ አመ ይወድይዎ ካዕበ። ዘአዘቅተ እሳት ዕሙቀ ወዘነድ ላህበ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ቅዱስ ቴዎዶስዮስ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ዕለት ታማኝ የሆነ ኤጲስቆጶስ የቅዱስ ቴዎዶስዮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፤ የዚህንም ቅዱስ ዜና ከዲዮቅልጥያኖስ የተሾመ የቆጵሮስ ገዥ ዮልዮስ ሰማ፤ ወደርሱም አስቀርቦ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ ለረከሱ ጣዖቶች ዕጣን እንዲአጥን መሥዋዕትም እንዲአቀርብ ፈለገ።
❖ ቅዱስ ቴዎዶስዮስም እኔስ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ ለእርሱም ዕሠዋለሁ በሎ መለሰ፤ ትእዛዙንም ባልሰማ ጊዜ ጽኑዕ ግርፋትን ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ገረፈው፤ ከዚያም ሰቅሎ ሥጋውን ሁሉ ሰነጠቀ አውርዶም በእሳት በአጋሉት በብረት አልጋ ላይ አስተኛው ጌታችንም ከዚህ ሥቃይ ጠብቆ አዳነው።
❖ ከዚህ በኋላ እጆቹንና እግሮቹን በረጃጅም ችንካሮች ቸንክረው እስከ ወህኒ ቤት ጐትተው በዚያ ጣሉት፤ እግዚአብሔርም ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስን አጥፍቶ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ እስከ ነገሠ ድረስ በወህኒ ቤት ኖረ፤ ቈስጠንጢኖስም የመንግሥት ሥልጣን በያዘ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የታሠሩትን ሁሉ እንዲፈቷቸው አዘዘ፤ ከዚያም በኋላ ወደ አገሩ ተመልሶ በጵጵስናው ሹመት ላይ ሁኖ ምእመናንን በበጎ አመራር እየመራ ኖረ፤ ዕድሜውንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ።
የፈጣሪው በረከትም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለቴዎዶስዮስ በእንት ስምዐ ጽድቅ ዘተዘብጠ። ብዙኀ ዓመታተተ ተሞቂሖ ወአኮ ኅዳጠ። ዲዮቅልጥያኖስ ዕልው ድኀረ እመንግሥቱ ተፈልጠ።ኀበ ዘትካት መንበሩ በትእዛዘ አምላክ ተመይጠ። እሰከ መዋዕሊሁ በኀድዓት ወበዛኀን ተሠልጠ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
አቡነ አርከሌድስ
❖በዚችም ቀን በበረሀ የሚኖሩ እንጦንስና አርከሌድስ ጻድቁ ዘሩፋኤልም አረፉ፤ ሀገራቸው ግብፅ ሲሆን ከተሰዓቱ ቅዱሳ ቀጥሎ ነው ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጡት፤ የነበሩበትም ጊዜ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በነበሩበት ጊዜ ነበር፡፡
❖ ወደ ሀገራችን ከመጡ በኋላ ወሎ ውስጥ ያለችውን እጅግ ጥንታዊቷን ቸር ተከል ማርያምን ቆረቆሯት፡፡
❖ ጻዲቁ የሚታወቁበት ትልቁ ገድላቸውም ሳይንት ውስጥ በቸር ተከል ማርያም ገዳም ውስጥ ለ21 ዓመታት ሳያርፉ ሳይቀመጡ በመቆም ጸሎት ያደረጉ ታላቅ አባት መሆናቸው ናቸው፡፡
❖ አቡነ አርከሌድስ እጃቸውን ሲያጨበጭቡ 500 ርግቦች በአንድ ጊዜ ይሰበሰቡላቸው ነበር፤ እነርሱንም ወደፈለጉት ቅዱሳን መልእክት ይልኳቸው ነበር፡፡
❖ በዚህ አስደናቂ ሥራቸውም በቅዱሳን ዘንድ ትልቅ ክብር ነበራቸው፤ ለቅዱሳን የተለያየ ታሪክ አላቸው፣ ለአንዱ አንበሳ፣ ለአንዱ ጅብና አጋዘን፣ ለአንዱ ንብ፣ ለአንዱ ነብር፣ ለአንዱ አጋንንት ይታዘዙላቸው ነበር፡፡
❖ ጻዲቁ በመጨረሻ ወደ ምረድ ግብፅ ተመልሰው ከሌሎች ሰማዕታት ጋር መጋቢት 6 ቀን ተሰይፈው በሰማዕትነት ያረፉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡
አቡነ አርከሌድስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን
አርኬ
✍️ሰላም ዕብል ሕሊናከ ጽሩየ። ዘኢረሰሐ ምንተኒ ወዘኢጸብለየ። ዘሩፋኤል ኀቤከ እሰመ ትጸርሕ ነፍስየ። መንኖ ዘበቊዓከ አቡየ። በሰማይሰ ኢትኅድግ ኪያየ።
❤ እነዚህም ሦስቱ ቅዱሳን በአባታችን ላይ አድሮ ድንቅ ነገርን የሚሠራ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዋልድባው አቡነ ሳሙኤልም አባታችንን "አባት ሆይ በዚህች ቀን ድንቅ ሥራን አየን፣ አርአያህ የእግዚአብሔርን መልአክ አርአያ ይመስላል፣ ቅድስናህ ፍጹም ነው፣ የጸሎትህ ኃይል ሙታንን ያስነሣል፣ የተበሉ አንበሶችን ከአንበሶች ሆድ አወጣህ" አሏቸው፡፡ቅዱሳኑም ሥራቸውን እያደነቁ በልተው ጠጥተው ጠገቡ፡፡ በማግሥቱም አባታችን ቅዱሳኑን "በሰላም ሂዱ" ብለው መርቀው ሸኟቸውና የእግዚአብሔር ሥራ እያደነቁ
ወደየበዓታቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
❤ በመጨረሻም ከዚህ ዓለም የሚለዩበት በቀረበ ጊዜ እንሆ የክበር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተገለጠላቸው። ስማቸውን ለሚጠራና መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ዐሥራ ሁለት አክሊል ሰጣቸው። ቅዱስ ሚካኤል ሦስት አክሊሎች፣ ቅዱስ ገብርኤል ሦስት አክሊሎች፣ ቅዱስ ሱራፊ ሦስት አክሊሎችና ቅዱስ ኪሩብ ሦስት አክሊሎችን አቀዳጇቸው። የዕድሜያቸውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን መጋቢት5 በሰላም በፍቅር ዐረፉ። ጌታችንም ነፍሳቸውን ተቀቡሎ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት። ከአባትችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ የመጋቢት 5 ስንክሳርና ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወትከይድ አንበሳ ወከይሴ። እስመ ብየ ተወከለ አድኅኖ። ወእከድኖ እስመ አእመረ ስምየ"። መዝ 90፥12-14። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥33-ፍ.ም።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር። እግዚኦ አነ ገብረከ። ገብረከ ወልደ ዓመትከ"። መዝ 115፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 14፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥1-12 እና የሐዋ ሥራ 17፥19-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዠ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍት በዓልና ወራት ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
እንደሚያይ የኃጥአንም ሥራቸው በአባታችን ፊት እንዲሁ የተገለጠ ነውና፡፡
❤ አባታችንም የኢትዮጵያን ሰዎች ኃጢአታቸውን በግልጽ በተመለከቱ ጊዜ ተወርውረው ወደ ባሕሩ በመግባት ተዘቅዝቀው መጸለይ ጀመሩ፡፡ "ከባሕር እንዳልወጣ፣ በእግሬም እንዳልቆም በሕያው ስምህ ምያለሁ" ብለው አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ቆዩ፡፡በ40ኛ ቀናቸው የታዘዘ መልአክ መጥቶ "ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ ብሎሃ" አላቸው፡፡ አባታችንም መልአኩን "መላ ኢትዮጵያን ካልማረ ከዚህ ባሕር አልወጣም" አሉት፡፡ መልአኩም ከእሳቸው ተለይቶ ከሄደ በኋላ አባታችን በዚያ ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖሩ፡፡
❤ አባታችንም በባሕሩ ውስጥ ተዘቅዝቀው መቶ ዓመት ሲጸልዩ ከኖሩ በኋላ ደማቸው ፈሶ አለቀና ውኃው ደም መሰለ፡፡ ሥጋቸውም አልቆ አጥንቶቻው እንደበረዶ ሆኑ፡፡ ሰባት ሺህ እልፍ ሦስት መቶ የሚሆኑ አጋንንትም ከአራቱም አቅጣጫ እየመጡ ሰውነታቸውን በፍላፃዎቻቸው ይወጓቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደ አባታችን መጥቶ ከባሕሩ ዳር በመቆም "ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መላ ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ተነሥ ከባሕሩ ውጣ" አላቸው፡፡ አባታችንም አጥንታቸው እንደመርፌ ቀዳዳ ተበሳስቶ ፈጽመው ደክመው ነበርና ጌታችን በክቡራን እጆቹ ሁለንተናቸውን ቢዳስሳቸው እንደቀድሞው ደህና ሆኑ፡፡ጌታችንም ከባረካቸው በኋላ ወደ ምድረ ከብድ እንዲሄዱ ነገራቸው፡፡
❤ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምድረ ከብድ እንደደረሱ እንደ ዓምድ ተተክለው ሰባት ዓመት ቆመው ጸለዩ፡፡በዚህም ጊዜ ሰይጣን በቁራ ተመስሎ መጥቶ ሁለት ዐይኖቻቸውን አንቁሮ አጠፋቸው ነገር ግን አባታችን ጸሎታቸውን ሳያቋርጡ ሁለት ሳምንት በጸሎት ቆዩ፡፡ ከ2 ሳምንት በኋላ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው በዐይኖቻቸው ላይ እፍ ብለው ብርሃናቸውን ከመለሱላቸው በኋላ አባታችንን "ከሰማይ ፍጹም ኃይል ይሰጥሃልና ጠላቶችህን ትበቀል ዘንድ ወደ ዝቋላ ሂድ" ብለዋቸው ዐረጉ፡፡
❤ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም እንደታዘዙት ወደ ዝቋላ እየሄዱ ሳለ በመንገድ ላይ ከዛፍ ሥር ያረፉ ሦስት ሽማግሌዎችን አገኙ፡፡ አባታችንም ባዩአቸው ጊዜ ለመሰወር ቢያስቡም ሽማግሌዎቹ ግን ይመጡ ዘንድ ጠሯቸውና "በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነናል ሦስታችንንም በጀርባህ አዝለህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን" አሏቸው፡፡ አባታችንም ሽማግሌዎቹን በቀረቧቸው ሰዓት ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሌዎች ሆነው አገኟቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን አንደኛውን ሽማግሌ አዝለው ከአንድ ምዕራፍ አደረሷቸው፡፡ ያም ሽማግሌ "ከዚህ አሳርፈኝ፣ አንተ ደክመሃል የማትበላ የማትጠጣ ነህና" አሏቸው፡፡አባታችንም "አባ የት ያውቁኛል?" አሏቸው፡፡ሽማግሌውም "አሁን ደግሞ ሄደህ ጓደኞቼን አምጣልኝ" አሏቸው፡፡ አባታችንም የቀሩት ሁለቱ ሽማግሌዎች ካሉበት ደርሰው ሁለቱንም በየተራ እያዘሉ የመጀመሪያውን ካደረሱበት ቦታ አደረሷቸው፡፡ከዚህም በኋላ እነዚያን ሽማግሌዎች "አባቶቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" አሏቸው፡፡ ሦስቱም ሰዎች ተነሥተው ቆሙና ለአባታችን በአንድነት በሦስትነት ተገለጡላቸው፡፡ አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ሆኑ፡፡ ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም በመምሬ አድባር ሥር በአንድነት በሦስትነት እንደተገለጡለት ሁሉ አሁንም ለአባታችን ለገብረ መንፈስ ቅዱስ በአንድነት በሦስትነት ተገለጡላቸው፡፡ በጀርባቸውም አዘሏቸው፡፡ የእግዚአብሔርንም ክብር ስላዩ አባታችን ፊታቸው እንደፀሐይ አበራ፡፡ ቅዱሳን መላእክት ወርደው እንደሻሽ ተነጥፈው ሲያመሰግኑ ሰማይና ምድር ተነዋውጠው ተራሮች ኮረብቶች ዓለቶች ተሰነጣጠቁ፡፡ በዚያችም ሰዓት ታላቅ ፍርሃት ሆነ፡፡ አባታችንም ዙሪያቸውን በከበባቸው በምሥጢራት ጎርፍ ተውጠው ተንቀጥቅጠው በግንባራቸው ወደቁና እንደ በድን ሆኑ፡፡በራእይ ውስጥም ሆነው እነዚያ ሽማግሌዎች አባታችንን እስከ ሰባተኛው ሰማይ እንዳደረሷቸው ተመለከቱ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደቀሰቀሳቸው አባታችንንም ቀሰቀሳቸውና "ወደ ዝቋላ ውረድ መቶ ዓመት ሙሉ አጥንትህን ሥጋህን እየነደፉ የተዋጉህን አጋንንት ታጠፋቸው ዘንድ፡፡ እነሆ እኔ እንደወሰድኩህ ባለማወቃቸው በትዕቢት ላይ ናቸውና "በባሕር ውስጥ አለ" ይሉሃል፡፡ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ይረዱሃል፤ መባርቅትም በፊት በኋላ ይከተሉሃል" አላቸው፡፡
ያንጊዜም አባታችን በመብረቅ ላይ ሆነው እነዚያ አጋንንት ወዳሉበት ወረዱ፡፡ አጋንንቱንም ደመናት ከበቡአቸው፣ መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው፣ በመብረቅ አጨዷቸው፤ አመድ ሆነው በነፋስ በተኗቸው፡፡ የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባ ሺህ እልፍ ከአንድ ሺህ ነበር፡፡ ሁሉም በአንድ ጊዜ አልቀዋልና ከእነርሱ ሸሽቶ ያመለጠም አልነበረም፡፡ ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ወደ ሰማይ ዐረጉ፡፡ አባታችንም አንበሶችና ነብሮች፣ ድብና ዘንዶ ወዳሉበት ምድረ ከብድ ተመለሱ፡፡
❤ አባታችንም ወደ ምድረ ከብድ ከተመለሱ በኋላ መንፈስ ቅዱስ የጠራቸው ሦስት ቅዱሳን ሁሉም በየአንበሶቻቸው ላይ ተቀምጠው ወደ ምድረ ከብድ መጡ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል፣ የአዘሎው አቡነ አንበስ እና ከላዕላይ ግብፅ ተነሥቶ የመጣው አቡነ ብንያም ናቸው፡፡ ነገር ግን አባታችን እነዚህን ቅዱሳን ስለተሰወሯቸው ቅዱሳኑ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በምህላ ሰነበቱ፡፡ የአባታችን የሚያስፈሩ አንበሶች ወጥተው የቅዱሳኑን አንበሶቻቸውን ገድለው ደማቸውን አፍስሰው ሥጋቸውን በሉ፡፡ ሦስቱም ቅዱሳን በዚህ ፈጽመው ደንግጠው ሳለ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ 60 ነብሮችንና 60 አንበሶችን አስከትለው ተገለጡላቸውና "ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቅዱሳኑ አትፍሩ" አሏቸው፡፡ ቅዱሳኑም "አባታችን ሆይ! ጸሎትህ ቅድስት እንደሆነች ባወቅን ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንባረክ ዘንድ ወደ አንተ መጣን፡፡ ነገር ግን ባላገኘንህ ጊዜ እስከ ሰባት ቀን አለቀስን" አሏቸው፡፡ ዳግመኛም "የእርስዎም አንበሶች መጥተው አንበሶቻችንን በሉብን" አሏቸው፡፡ አባታችንም አንበሶቻውን "እስከ ዕለተ ሞቴ ድረስ በእግሬ ከረገጥኩት ምድር በቀር እግዚአብሔር ያላዘዛችሁን ለምን በላችሁ? አሁንም የበላችሁትን ትፉ" አሏቸው፡፡ እነዚያም አንበሶች አፋቸውን ከፈቱና የበሉትን የአንበሶቹን ሥጋቸውን አጥንታቸውን ከደም ጋር ተፉ፤ በሆዳቸውም የቀረ የለም፡፡ አባታችንም ወዲያው ወደ ምሥራቅ ዞረው እግዚአብሔር ካመሰገኑ በኋላ "አቤቱ አልዓዛርን ከሞት ያስነሣኸው አንተ ነህና አሁንም እነዚህን አናብስት ከሞት አስነሣቸው፤ ለባሮችህም የድካማቸውን ማረፊያ ይሆኑላቸው ዘንድ የሰጠሃቸውን አትከልክላቸው… " እያሉ ጸለዩ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ብለው ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ የአንበሶቹን ሥጋቸውን በመስቀል ምልክት ባርከ "በጌታዬ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሡ"አሏቸው፡፡ አንበሶቹም እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነው ተነሡና እንደቀድሞው ሆኑ፡፡ ለአባታችንም እጅ ነሥተውና ሰግደው የእግሩን ትቢያ ላሱ፡፡ አባታችንም ወደ ጌቶቻቸው መለሳቸው፡፡
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta):
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ❤
❤ #መጋቢት ፭ (5) ቀን።
❤ እንኳን #ተአምራታቸውና_ትሩፋታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት ለበዛ የእግዚአብሔር ማደርያ ተጋዳይ ለሆኑ #በዝቋላ_ተራራ_ባለው_ባሕር_ውስጥ_100 ዓመታት ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ሰዎች ምሕረትን ለለመኑት #ለታላቁ_አባት_ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ፦ ትውልድ አገራቸው ደቡባዊ ግብፅ ከቆላው ልዩ ስሙ ከንሒሳ አካባቢ ነው፡፡አባታቸው ስም ቅዱስ ስምዖን እናታቸው ስም ቅድስት አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡
❤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ እናታቸው ቅድስት አቅሌስያ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያንጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ "ክቡሩ ከሰማይ ከምድር ከፍ ከፍ የሚል፣ ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር በክብር የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ ንጽሕናው እንደ እንደ ነቢይ ኤልያስ፣ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ የሆነ በክብር ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር የሚተካከል ልጅ ትወልጃለሽ" አሏት። ይኸውም ለአንቺ ብቻ አይደለም ለዓለሙ ሁሉ ነው እንጂ። ያን ጊዜ ከሦስቱ አንዱ ተነሥቶ በእጁ ባርኮ በሰላም ወደ ቤትሽ ግቢ አሏት"። እርሷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ገባች፡፡
❤ ቅድስት አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ "የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን" አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ዳግመኛም "ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን" አለ፡፡
❤ ከ3 ዓመት በኋላም እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንዲህ ብሎ አዘዘው፡- "ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ተቀበል፣ ብዙ ገዳማውያን ወዳሉበት ገዳም ውሰድና ከበራቸው አስቀምጠው፣ አበ ምኔቱንም ዘመደ ብርሃንን ከበር አንሥተህ ካንተ ዘንድ አኑረው ስለ ልብሱ ስለ ምግቡ አታስብ ሕፃኑ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነውና ምግቡም መንፈሳዊ ነው ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚወጣ ቃል ነው፣ ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ዕወቅ በለው" በማለት አዘዘው፡፡ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም እንደታዘዘው ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ በክንፎቹ አቅፎ ስሞ እስከ ሰባቱ ሰማይ አውጥቶ በሥሉቅ ቅዱስ ፊት አቅርቦት አስባረከው፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩን "ወደ እናቴ ወደ ማርያም ውሰደውና ትባርከው" አለውና ወስዶት እመቤታችንም ባረከችው፡፡ ዳግመኛም ከአዳም ጀምሮ ኄሮድስ በግፍ እስካስፈጃቸው ሕፃናት ያሉት ሁሉም ቅዱሳን ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግልና መነኰሳት ሁሉም እንዲባርኩት አደረገው መልሶ ከእግዚአብሔር ፊት አቆመው፡፡ መድኅን ጌታም ሕፃን ገብረ መንፈስ ቅዱስን "በመንግሥቴ ከእኔ ጋር ትነግሣለህና ደስ ይበልህ፣ በርታ የሚደርስብህን ሁሉ ታገሥ ብዙ ነፍሳት በአንተ ምክንያት ይድናሉ፣ ሰላሜ ከአንተ ጋር ይሆናል" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደውና ሕፃኑን ከበር ላይ አስቀምጦ እርሱ ወደ ውስጥ ገብቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉን ነገረው፡፡
❤ አባ ዘመደ ብርሃንም ሕፃኑን አስገብቶ በእንክብካቤ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማረ አሳደገው፡፡ ሕፃኑም ትምህርቱን በጨረሰ ጊዜ ዲቁና ተቀብሎ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ፡፡ ፍጹም የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታልና ሥራው ሁሉ በዕውቀት የተመላና የተቃና ሆነ፡፡ አባ ዘመድ ብርሃንም በሕፃኑ ላይ ያደረበትን ጸጋ እያየ እጅግ ደስ ይለው ስለነበር እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጠው፡፡ ከዚህም በኋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀበሉና በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡
❤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዳግመኛ ተገልጦላቸው ወደ ሰማይ አሳረጋቸውና ከእግዚአብሔር ፊት አቆማቸው፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን ክቡራን የሆኑ እጆቹን ዘርግቶ ከባረካቸው በኋላ "በጸሎትህ ከሲኦል የምታወጣቸው ብዙ ነፍሳት አሉ፤ ድውያንንም ትፈውሳለህ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ገብተህ ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር ኑር" አላቸው ቁጥራቸውም ስልሳ ነብርና ስልሳ አንበሶች፡፡አባታችንም ጌታችንን "የሰጠኸኝ እነዚህ አንበሶችና ነብሮች ምን ይመገባሉ?" አሉት፡፡ ጌታችንም "የረገጥከውን መሬት ይልሳሉ በዚያም ይጠግባሉ፡፡ ወደ እኔም እስክትመጣ ድረስ ይኸው ምግብ ይሆናቸዋል" አላቸው፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ይህንን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፡፡ ጌታችንም መልአኩን ወደ ቀደመ ቦታቸው ይመልሳቸው ዘንድ አዘዘው፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከራሳቸው እስከ እግራቸው ድረስ ጠጉር በቀለላቸው፡፡ የጠጉራቸውም ርዝመቱ አንድ ክንድ ከስንዝር ነው፡፡ አባታችንም በታላቅ ተጋድሎ ሲኖሩ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨመረላቸው፡፡ከዕለታት በአንድ ቀን የፈወሳቸው ሕሙማን ብዛታቸው እልፍ ሆነ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ሥራቸውን ስላወቁባቸው አዘኑ፡፡ "ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንብኝ ተነሥቼ ሰው ወደማያውቀኝ አገር እሄዳለሁ" ብለው ተነሥተው ሄዱ፡፡ሕዝቡም አባታችን እንደተሰወሩ ባወቁ ጊዜ በሀዘን አለቀሱ፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ጫካ ገብተው ብቻቸውን የበጋውን ሐሩር የክረምቱን ቁር ታግሰው ምንም ልብስ ሳይለብሱ ራቁታቸውን ሆነው በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ከጽኑው ተጋድሎአቸውና ከጫካው ቅዝቃዜ የተነሣ ሰውነታቸው አልቆ ከአጥንታቸው ጋር ተጣበቀ፡፡ ፍራፍሬም ሆነ ምንም ነገር አይመገቡም ውኃም ፈጽሞ አይጠጡም ነበር፡፡ አባታችን በምድረ በዳ እንደሰው ሳይሆን እንደመላእክት ኖሩ፡፡ ቅዱሳን መልእክትም ዘወትር ይጎበኟቸው ነበር፤ ስለምግባቸውም ሰማያዊ ኅብስት አምጥተው ይሰጧቸዋል ነገር ግን አባታችን ያንን ኅብስት አይመገቡትም ይልቁንም ጽዋውን ባሸቱት ጊዜ እንዲሁ ይጠግባሉ ይረካሉ፡፡
❤ ዕድአቸው 300 ዓመት በሆነ ጊዜ ጌታችን "ወደ ኢትዮጵያ ሂድ በዚያም ከደይን የምታወጣቸው ነፍሳት አሉ" አላቸው፡፡ አባታችንም "አምላኬ ሆይ ወደዚያች አገር ማን ያደርሰኛል?" አሉት፡፡ እግዚአብሔርም "እኔ በሥልጣኔ አደርስሃለሁ" ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ተሰወረ፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ስድሳ አንበሶችና ስድሳ ነብሮች እየተከተሏቸው ወደ አገራችን ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚሁ ተከታዮቻቸው ጋር በነፋስ ሠረገላ ጭኖ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ዳግመኛም "ደብር ቅዱስ" ወደሚባለው ወደ ዝቋላ ወሰዳቸው፡፡ አባታችንም በውኃው ዳር ቆመው ምሥራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን በመለከቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአታቸው በፊታቸው የተገለጠ ሆነ፡፡ ሰው የገዛ ፊቱን በመሥታወት
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #መጋቢት ፬ (4) ቀን።
❤ እንኳን #ስለ_ፋሲካ_በዓል የአይሁድ ተሳታፊዎች ስለ ሚባሉ ክፉዎች ሰዎች #በአምር_ደሴት_የዐሥራ_ስምንት_ኤጲስቆጶሳት አንድነት ስብሰባ ለተደረገበትና ለከበረና ለተመሰገነ ከጵንፍልያ አውራጃ ብርግያ በትምባል ከተማ ለሆነ ለመኰንን #ለቅዱስ_ሐኑልዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የአሞር_ደሴት_የአንድነት_ስብሰባ፦ እነሱ የከበረ የፋሲካን በዓል በኔሳን ወር ማለት በሚያዝያ ዐሥራ አራት ቀን ከአይሁድ ጋር ያከብሩ ነበርና። ሰኞ ቢሆን ማክሰኞም ቢሆን ወይም ረቡዕ ወይም ሐሙስ ወይም በዓርብ ቀን ወይም በቅዳሜ ሰንበት ከአይሁድ ጋር ያከብሩ ነበርና የደሴታቸውም ኤጲስቆጶስ አወገዛቸው ግን አልተመለሱም።
❤ ስለዚህም ወደ ሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ድምትራጥዮስ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ ሰራባሞን ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ ድሜጥሮስ ወደ ኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ ወደ ሲማኮስ መልእክትን ላከ። የእነዚህንም ሰዎች ስሕተታቸውን ነገራቸው። አራቱም ሊቃነ ጳጳሳት ከእርሱ እየአንዳንዳቸው የከበረ የፋሲካ በዓልን በእሑድ ቀን ካልሆነ በቀር ከአይሁድ በዓልም በኋላ ካልሆነ በቀር አታድርጉ የሚል መልእክትን ላኩ። ይህንም ትእዛዝ የሚተላለፈውን ከምዕመናን እንዲለይ አወገዘ።
❤ በዚህም ጉባኤ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳት ተሰበሰቡ። እነዚያንም ሕግ ለዋጮች አቅርበው የሊቀነ ጳጳሳቱን መልእክቶቻቸውን በፊታቸው አነበቡ ከእነርሱም በከፋች ምክራቸው የተመለሱ አሉ። በስሕተቻቸውም ጸንተው የቀሩ አሉ። ረግመውና አውግዘውም ከምዕመናን ለዩአቸው።
❤ አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያትም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣባት ዕለት ፋሲካን ያለ እሑድ ቀን የሚያከብር እርሱ በበዓላቸው ከአይሁድ ጋር ተሳታፊ ነውና ከምዕመናን ይለይ ብለው እንዳዘዙ እንዲሁ የፋሲካ በዓል በዕለተ እሑድ እንዲከበርና ሕጉም ጸንቶና ተወስኖ እንዲኖር ተሠራ። እግዚአብሔር ከሰይጣን ስሕተት ይጠብቀን። በተጋድሎአቸውና በትሩፋታቸው ደስ ባሰኙት በቅዱሳን ጸሎትም ከወጥመዶቹና ከሽንገላውም ያድነን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ሐኑልዮስ፦ ይህንንም ቅዱስ ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ መውደዱና እርሱንም ስለ ማምለኩ ከዲዮቅልጥያኖስ ተልኮ የመጣ ብርይንኮስ መኰንን ያዘው። በመኰንኑም ፊት በቆመ ጊዜ ምስጋና ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት ከፍ ከፍ ባለ ቃላት አብራርቶ ገለጠ። ብዙ ምስጋናዎችንም ለእግዚአብሔር አቀረበ የረከሱ ጣዖታትንም ረገማቸው።
❤ መኰንኑም በዕንጨት መስቀል ላይ ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ ስለ ከበረ ስሙም ምስክር ይሆን ዘንድ ስለ አደለው ምስጋና ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገነው። ከዚያም ምስጋና ይግባውና በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን መጋቢት4 ሰጠ። የቅዱስ ሐኑልዮስ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋር ለዘላለም ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 4 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለክሙ_አሐተኔ_ጉቡአን። ኤጲስቆጶሳት ዐሥር ዘተውሳክክሙ ሳምን። አመ ፲ ወ ፬ ለወርኃ ኔሳን። በፋሲካ ኦሪት ኢይግበሩ ፋሲካ ወንጌል ብርሃን። ከመ ትምትርዎሙ ለዕልዋን በበሊሕ ልሳን። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመጋቢት_4።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ጸላእኩ ማኅበረ እኩያን። ወኢይነብር ምስለ ጽልሕዋን። ወአሐፅብ በንጹሕ እደውየ"። መዝ 25፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት ፊሊ 3፥1-ፍ.ም፣ 2ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥1-7። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 22፥1-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
