ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
نمایش بیشتر611
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-930 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፳፪ (22) ቀን።
❤ እንኳን በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ በድዮማ ከተማ አረምያ ከምትባል አገር ለሆኑ #ለቅዱሳን_ለቆዝሞስና_ለድምያኖስ ለወንድሞቻቸው #ለአላድዮስ_ለአቢሞስ_ለአብራንዮስና ለእናታቸው #ለቅድስት_ቴውዳዳ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቆዝሞስ ማኅበር #ሰማዕታት_ከሁለት_መቶ_ስልሳ_ሁለት ወንዶችን፣ #ከአርባ_ዘጠኝ_ሴቶችና_ከቀሌምንጦስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ቆዝሞስና_ድምያኖስ ወንድሞቻቸው #አንቲቆስ_ዮንዲኖስና_አብራንዮስ እናታቸው #ቅድስት_ቴዌዳዳ፦ እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው። እናታቸውም ቴዌዳዳ እግዚአብሔርን የምትፈራና የምትራራ መጻተኞችንና ድኆችን የምትወዳቸው የምትረዳቸው ናት አባታቸውም ከሞተ በኋላ ልጆቿን እያስተማረች አሳደገቻቸው። እሊህም ሁለቱ ቆዝሞስና ድምያኖስ የሕክምና ጥበብን ተምረው በሽተኞችን ያለ ዋጋ የሚፈውሱአቸው ይልቁንም ድኆችን አብዝተው የሚረዷቸው ሆኑ። ወንድሞቻቸው ሦስቱ ግን ወደ ገዳም ሒደው መነኰሱ በጾምና በጸሎትም ተጠመዱ።
❤ ከአባ አጋግዮስ አደራ በአስጠበቀው በንጉሠ ቊዝ ልጅ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ የረከሱ ጣዖታትን በአመለከ ጊዜ በምዕመናን ላይ መከራ ሆነ ገንዘብ ወዳጅ አጋግዮስ ብዙ ወርቅን ተቀብሎ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ወደ አባቱ ልኮታልና ከዚህም በኋላ የንጉሠ ቊዝን ልጅ ዲዮቅልጥያኖስ ዳግመኛ ከጦር ሜዳ አግኝቶ ማረከው እርሱንም ንጉሡን ልጅ ሠውሮ አባ አጋግዮስን ጠራው ያንንም አደራ የሰጠውን የንጉሠ ቊዝን ልጅ እንዲአመጣ አዘዘው አጋግዮስም ሙቶ ተቀብሮአል ብሎ በሐሰት ተናገረ በዚያንም ጊዜ በመሠዊያው ፊት አማለው እሳትም ከሰማይ ወርዳ እንደምታቃጥለው ጠበቀ የእሳትም መውረድዋ በዘገየ ጊዜ ወርቅን በእሳት አቅልጦ አጠጣውና አቃጠለው ስለዚህም ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጣዖታትን አመለከ።
❤ ቆዝሞስና ድምያኖስ በአገሩ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እነርሱ እንደሚያስተምሩ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘ በደረሱም ጊዜ ለአገረ ገዢው ለሉልዮስ እንዲአሠቃያቸው ሰጠው። እነርሱም በብዙ ሥቃዮች ማሠቃየትን ጀመረ በእሳት የሚያቃጥልበት ጊዜ አለ በግርፋት የሚገርፍበት ጊዜ አለ ሦስት ወንድሞችም እንዳሏቸው ሰምቶ እነርሱንም ወደርሱ አስመጣቸውና አምስቱንም በመንኰራኵር ውስጥ እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ። ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጨምሩዋቸው በውስጡም ሦስት ቀኖችና ሌሊቶች ኖሩ ያለ ጥፋትም በጤንነት ወጡ ዳግመኛም ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቻቸው እሳቱን አነደዱ እግዚአብሔርም ያለ ጥፋት ጠበቃቸው።
❤ መኰንኑም እነርሱን ማሰቃየት በሰለቸው ጊዜ ወደ ንጉሥ መለሳቸው ንጉሡም ዳግመኛ ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው ቴዎዳዳ እናታቸውም የምታስታግሣቸው ንጉሡንና የረከሱ ጣዖቶቹን የምትረግም ሆነች። በዚያንም ጊዜ አንገቷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለች ሥጋዋ ግን በምድር ላይ ወድቆ ነበር ቆዝሞስም እንዲህ ብለሸ ጮኸ "የዚች አገር ሰዎች ሆይ ይችን አሮጊት መበለት ሥጋዋን አፈር አልብሶ ይሠውራት ዘንድ ከውስጣችሁ ርኅራኄ በልቡ ያደረበት የለምን?" የህርማኖስ ልጅ ቅዱስ ፊቅጦርም በሰማ ጊዜ ተደፋፍሮ ሥጋዋን ገንዞ ቀበራት።
❤ ንጉሡም እነርሱን ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከመከራውም ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 7፥1-5፣ ያዕ 1፥2-17 እና የሐዋ ሥራ 17፥2-13 የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥9-18። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል።ለሁላችን ይሁንልን።
በአጫብር ስም በሰንበት ት/ቤቶች የሚሰጥ ስልጠናን እግድ እንዳልተነሳ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት አስታወቀ።
በ16 /3 /2018ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 1/545/2018ዓ.ም ከመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የወጣውን ደብዳቤ መሠረት በማድረግ በአጫብር ስም በሰንበት ት/ቤቶች የሚደረግ ጥናቶችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ እንደተሻረ አድርገው አንድ አንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ የሐሰት መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል።
የአንድነቱን ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ተከትሎ መጋቤ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ ነሐሴ 26/2017ዓ.ም ለጠቅላይ ቤተክህነት ባሰገቡት ማመልከቻ መነሻነት በትምህርት እና ስልጠና ማሰልጠኛ መምሪያ በኩል የማጣራት ስራ ተከናውኗል ። በሂደቱም የትምህርት እና ማስልጠኛ መምሪያ ኃላፊዎች መጋቤ ሃይማኖት ዲበ ኩሉ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ፣ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት ተወካዮች እና ሌሎች በርዕሰ ጉዳዩን ለመከታተል የመጡ አባቶች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ የተነሱ ጭብጦች በቅድስት ቤተክርስትያን አጫብርን እንዲያስተምሩ የተፈቀደላቸው መጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ በአዲስ አበባ አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ሰንበት ት/ቤቶች ጥናት እንዲያቆሙ የተላለፈው ውሳኔ እሳቸውን ይመለከታል ወይስ አይመለከትም የሚል ሲሆን በውይይቱም አሁን ያለው በአጫብር ስም የሚደረገው ጥናት እና ትእይንት በከፍተኛ መልኩ ቤተክርስትያንን እያስተቸ የሚገኝ መሆኑ እና እግዱ ተገቢ መሆኑንን በውይይቱ ላይ የተሳተፋ አካላት በሙሉ የተስማሙበት ሲሆን በተለይም መጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኅየሰ እኔም በማየው ነገር አዝናለሁ አጫብር እንዳስጠና ቅዱስ ሲኖዶስ የፈቀደው ለእኔ ብቻ ነው ። ከዛ ውጪ የሚደረገውን ጥናት እኔም እቃወማለሁ የኔ ጥያቄ ለምን መስመር የሳተው ነገር ታገደ አይደለም እኔ የተፈቀደልኝ ሆኖ እያለ ለማስጠናት ስላልቻልኩ እሱ እንዲስተካከልልኝ ነው በሚል በሰንበት ት/ቤቶችም ሆነ በሌሎች ባልተፈቀደላቸው አስጠኝዎች የሚደረገውን እቃወማለሁ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋርም በጋራ እሰራለሁ በሚል ሀሳባቸውን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተወካዮች በኩል የጉዳዩ መስመር መልቀቅ እና ተጠያቂነት በሌለው መልኩ በየቦታው ምንም አይነት ፈቃድ ከቅዱስ ሲኖዶስ ሳይሰጣቸው በአጫብር ስም የሚደረጉ ጥናቶች የሚቀርቡ ወረቦች ቤተክርስትያንን በከፍተኛ መልኩ እያስተቹ መሆኑን አጽኖት ሰጥቶ ያቀረቡ ሲሆን በወቅቱም ሁሉም ተወያይ አካላት በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ የተስማማ ሲሆን ለቀጣይ መፍትሔ ጥናት እንደሚያስፈልግ ከስምምነት ላይ የተደርሷል።
መጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉኀየሰ የሚሰጡትን ጥናት በተመለከተ አንድነቱ በአጫብር ስም የሚደረግ እንጂ ቤተክርስትያን የፈቀደችላቸውን አባት አይመለከትም ፣ ነገር ግን አካሄድላይ በተመለከተ ሰንበት ት/ቤት ለማስጠናት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በማያውቀው መልኩ ሁለተኛ አደረጃጀት መፍጠር ስህተት መሆኑን እና የትኛውንም ትክክለኛ ጥናት ከማደራጃው እና ከአንድነቱ ጋር ብቻ በመናበብ እንዲቀጥል በወቅቱ በነበረው ውይይት ከስምምነት ተደርሷል።
በዚህም መሰረት ከላይ በተጠቀሰው ደብዳቤ ለመጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ ማስጠናት የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ እና ይህንንም ሲፈጽሙ ከማደራጃ መምሪያው እና ከአዲስ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጋር ተናበው መሆን እንዳለበት የሚገልጽ እንጂ በአጫብር ስም በሰንበት ት/ቤቶች የሚሰጥ ስልጠናን የሚመለከት አለመሆኑንን የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት አሳውቋል።
አሁንም በጠቅላላጉባኤው ውሳኔ መሠረት ማንም ሰንበት ት/ቤት በአጫብር ስም የሚደረግ ስልጠና የተከለከለ ሲሆን በመጋቢ ሃይማኖት ዲበኩሉ ኀየሰ በኩል የሚሰጠው ስልጠና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የአዲስ አበባ ሰንበት ትቤቶች አንድነት ጋር በመመካከር ሲፈቀድ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን ሲል የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት አስታውቋል።
❤ ከዚህም በኋላ አገሪቱን ማጥፋትን ስለ አባ ዮሐንስ ይተው ዘንድ መልሱን ለመኰንኑ ንጉሡ ጽፎ ደብዳቤዋን ወደ ደመናው ወረወራት የተሰበሰቡትም እያዩ እጅ ተቀበለችውና ወደ ደመናው ገባች ወዲያውኑ አባ ዮሐንስ በዚያች ደመና ወደበዓቱ ተመለሰና በማግሥቱ ያቺን ደብዳቤ ለመኰንኑ ሰጠው በላይዋም የንጉሡ ፊርማውና ማኅተሙ አለ በአያትና በአነበባት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ስለ አገሪቱ ድኅነትም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ አገሩ ተመለሰ። የንጉግሥ ዘመድ የሆነች የከበረች ሴት ዜናውን በሰማች ጊዜ ከደዌዋ ይፈውሳት ዘንድ ወደርሱ መጣች በጸሎቱም ተፈወሰች።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በሞተ ጊዜ መናፍቁ መርቅያን ነገሠ። ቅዱስ አባ ዲዮስቆሮስንም አሠቃየው። የቀናች ሃይማኖትን ስለመለወጡ አባ ዮሐንስ እየዘለፈና እየረገመው ወደ ርሱ ደብዳቤ ላከ ከጥቂት ወራትም በኋላ እግዚአብሔር ቀሠፈው። ለእርሱም ዕድሜው መቶ ሃያ አምስት ዓመት ሲሆነው ዕረፍቱ እንደደረሰ አወቀ እየጸለየም ግምባሩን በምድር አስነክቶ ሰገደ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ከመቃብሩም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች የሆነ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 21 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለኪ_ማርያም_እምነ። ዘሰመናይናኪ ጸወነ። ሶበ እምርኁቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ። ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየሐይድ ዐይነ። ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር _21።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ። ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ። ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ"። መዝ 47፥12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 23፥1-ፍ.ም።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛት ይዕቲ ምዕራፍየ ለዓለም"። መዝ 131፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥5-11 እና የሐዋ ሥራ 7፥44-59። የሚነበበው ወንጌል # ማቴ 21፥42-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጽዮን ማርያም በዓልና የጾም ጊዜ ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን #ለእናታች_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_ታቦተ_ጽዮን የፊልስጥኤማውያን ጣዖት ዳጎንን ለሰባበረችበት (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ # 1ኛሳሙ 5)፣ #ወደ_ኢትዮጵያ_ገብታ_አክሱም ለመጀመርያ ጊዜ ለከበረችበትና ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት #በተአምራት_አብርሃና_አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ለተገኘች ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጽያዊው ጻድቅ #ለአቡነ_ተወልደ_መድኅን ለበዓላቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ አገር ከሆነ ተአምራት ከሚያደርግ (ከገባሬ መንክራት) #ከቅዱስ_ጎርጎርዮስ ዕረፍት፣ ከእስክድርያ ሃምሳ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ቆዝሞስ ዕረፍት ከእስሙናይ አገር ሰማዕታት #ከእልፍዮስ_ከዘኬዎስ_ከሮማኖስ፣_ከዮሐንስ፣ #ከፊቅጦርና_ይስሐቅ ከመታሰቢያቸው፣ ከብርሌና ከብርጭቆ ሠሪዎች ልጅ ከሆነ ከአስዩጥ ሀገር #ከቅዱስ_አባት_ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍትና፣ ጫብሬ ከምትባል ከአገር ድልበት #ከቅድስት_ዲቦራ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም_የበዓልዋ_መታሰቢ ነው። በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የሮሜ_አገር_የሆነ_ገባሬ_መንክራት #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የቀናች ሃይማኖትንም ተምሮ እውነተኛ ክርስቲያን ሆነ። ከዚህም በኋላ የዚህን ዓለም ኃላፊነት የማታልፍ የመንግሥተ ሰማያትንም ኑሮ አሰበ ኀሳቡንም ሁሉ ስለ ነፍሱ ድኅነት አደረገ።
❤ የዚያችም አገር ኤጲስቆጶስ በኤጲስቆጶስነት ሥራ ይረዳው ዘንድ ለመነው እርሱ ግን አልፈቀደም ከውዳሴ ከንቱ የሚሸሽ ሁኗልና ወደ ገዳምም ገብቶ ጽኑዕ የሆነ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ። የዚችም አገር ኤጲስቆጶስ በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶስ የሚያደርጉት ፈልገው አጡ ስለዚህም ተሰብስበው ሳሉ የመለኮትንም ነገር የሚናገር ጎርጎርዮስ ከእርሳቸው ጋር ሳለ ገዳማዊ ጎርጎርዮስን ፈልጋችሁ በእናንተ ላይ ሹሙት የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ። በበረሀም ውስጥ በፈለጉት ጊዜ አላገኙትም እየፈለጉትም ብዙ ቀን ኖሩ እርሱ ግን በአቅራቢያቸው ይኖር ነበር። ባላገኙትም ጊዜ በአንድ ምክር ተስማምተው በሌለበት ወንጌል ይዘው በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሾሙት ስሙንም የመለኮትን ነገር በሚናገር በጎርጎርዮስ ስም ጎርጎርዮስ ብለው ሰየሙት።
❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ተገልጦ "ተነሥተህ ወደ እነርሱ ሒድ እነሆ በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሹመውልሃልና ይህም ከእግዚአብሔር የሆነ ነው" አለው። ያን ጊዜም ወደ እነርሱ ወረደ የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ፈርቷልና በአዩትም ጊዜ ወጥተው በታላቅ ክብር ተቀበሉት የሹመቱንም ሥርዓት ፈጸሙ። እግዚአብሔርም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ተአምራትን በእጆቹ ገለጠ ስለዚህ ገባሬ መንክራት ጎርጎርዮስ ተብሎ ተጠራ።
❤ ከብዙዎች ተአምራቱም አንዲቱ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ ከእርሷም ብዙ ዓሣዎችን የሚያጠምዱባት ታናሽ ባሕር ነበረቻቸው አንዱም አንዱ የኔ ናት በማለት እርስ በርሳቸው ተጣሉ ስለዚችም ባሕር በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ወደ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመሔድ ተስማሙ እርሱም ከሁለት ተካፈሉ ብሎ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ስለዚች ባሕር እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ባሕሪቱ ደርቃ የምትታረስ ምድር ሆነች ስለሚደረጉ ድንቆች ተአምራቴ ዜናው በሁሉ አገር ተሰማ በጎ አገልግሎቱንም ከፈጸመ በኋላ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ አባት በገባሬ መክራት ጎርጎርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የብርሌና_የብልጭቆ_ሠሪዎች_ልጅ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በበጎ ተግሣጽ አሳደገውታል የጥርብ ሥራንም አስተማሩት ከጥቂት ዘመናትም በኋላ አባቱና እናቱ ዐረፉ። ያን ጊዜ ወደ ቅዱስ ኢስድሮስና ወደ አባ ባይሞን ዘንድ ሒዶ መነኰሰ በጾምና በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምዶ ተጋደለ ዜናውም በራቀ ገዳማት ሁሉ ተሰማ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠለት ወደ አገሩ ሒዶ ወገኖቹን የጽድቅን ጎዳና ይመራቸው ዘንድ አዘዘው። ቅዱስ ቊርባንንም ሳይቀበል ከበዓቱ የማይወጣ ሆነ። በአንዲት ዕለትም ሁለት ቅዱሳን አረጋውያን አባ አብዢልና አባ ብሶይ ወደርሱ መጡ ገና ወደርሱ ሳይቀርቡ ከሩቅ ሳለ ስማቸውን በመጥራት ሳያውቃቸው አባቶቼ ለመምጣታችሁ ሰላምታ ይገባል ብሎ ተናገረ እጅግም አደነቁት አባ ሲኖዳም ከግብጽ አገር እየመጣ ብዙ ጊዜ ይጎበኘው ነበር።
❤ የከዳተኞችም ጠብ በግብጽ አገር ላይ በተነሳ ጊዜ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የላከው የጦር መኰንን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጣ። በጸሎቱም ይረዳው ዘንድ ለመነው ቅዱስ ዮሐንስም መስቀሉን አንሥቶ መኰንኑን "አይዞህ አትዘን አንተ ጠላቶችህን ድል ታደርጋለህና"፧ አለው እንደ ቃሉም ሆነ። ዳግመኛም በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላይ ጠላት በተነሣበት ጊዜ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ላከ እርሱም "አትዘን ጠላትህን ታሸንፋለህ" አለው ያን ጊዜም ጠላቶቹን አሸነፈ።
❤ ከዚህም በኋላ በእነዚያ ወራት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የርኵሰትን ሥራ ስለ ሠሩ የአስዩጥን ሰዎች እንዲገድላቸው ሀገራቸውንም እንዲአጠፉ አዘዘ። ንጉሡም የላከው መኰንን ሳይደርስ የእግዚአብሔር መልአክ ይህን ነገር ለአባ ዮሐንስ አሳወቀው የአገርም ሰዎች የንጉሡን ትእዛዝ በሰሙ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ገዳም ወጥተው ስለ መጥፋታቸው በፊቱ አለቀሱ አባ ዮሐንስም "አትጨነቁ አይዟችሁ እግዚአብሔር ያድናችኋላና" አላቸው። መኰንኑም በመጣ ጊዜ ከእርሱ በረከትን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሰ አባ ዮሐንስም ንጉሡ ያዘወውን ሁሉ ነገረው መኰንኑም ሰምቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዢ ሆነ ለመኰንኑም ርኵስ መንፈስ ያደረበት የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረው ያድንለት ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስን ለመነው በዚያንም ጊዜ ዘይትን ቀብቶ አዳነው።
❤ ከዚህም በኋላ የአስዩጥ ሰዎችን መገደላቸውን እንዲተው ወደ ንጉሥ ይጽፍለት ዘንድ መኰንኑን አባ ዮሐንስ ለመነው መኰንኑም ጽፎ ለአባ ዮሐንስ ሰጠው አባ ዮሐንስም ተቀብሎ ወደ ዋሻው ገባ ወደ ጌታችንም ጸለየ ብርህት ደመናም መጣች ተሸክማም ወደ ንጉሡ አደሰገችው ያን ጊዜም ንጉሥ ከማዕድ ላይ ነበረ ያንንም ደብዳቤ ከወደላይ ጣለለት ንጉሡም አንሥቶ በአነበበው ጊዜ ከመኰንኑ የተጻፈ እንደሆነ በመካከላቸው በአለ ምልክት ተሸፎ አገኘው የተጻፈውም ቃሉ ስለ አባ ዮሐንስ ልመና ሀገሪቱን ማጥፋትን እንዲተው የሚል ነበር ቀና ባለ ጊዜም ደመና አየ ንጉሡም አደነቀ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለዘመነ_አስተምሕሮ_ሦስተኛ_ሳምንት ለዕለተ ምኵራብ መታሰቢያ እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "#አምላክ_ፍጹም_በህላዌሁ ዘሀሎ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ዘበመንግሥቱ ይኴንን ዓለም ሰማየ ገብረ ለስብሐቲሁ ዓለም ፈጠረ ወምድረ ሣረረ ወገሠፀ ባሕረ ወገሠፃሙ ለኵሉ ፍጥረት እለ ውስተ ደይን ያዕርፉ ባቲ አብ ቀደሳ ለሰንበት ቅረቡ ኀቤሁ ለአምላከ ጽድቅ ማኅደር ለንጹሐን ከመ ትንሥኡ አክሊለ ስብሐት ዘአስተዳለወ ለእለ ያፈቅርዎ ፀንዑ በጸጋ በስን ወበሃይማኖት ወረሱ አክሊለ ስምዕ በእምነቶሙ እለ እምዓለም አሥመርዎ ለእግዚኦሙ መምህረ ቅዱሳን አክላለ ሰማዕት ሠያሜ ካህናት"። ትርጉም፦ ቅድመ ዓለም በመንግሥቱ የነበረ፣ #በአናናሩ_ፍጹም_አምላክ የሆነ ዓለምን ይገዛል፣ ለክብሩ ሰማይን አደረገ፣ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፣ ባሕርን ገሠፀ ፍጥረትን ሁሉ ገሠፃቸው በመከራ ውስጥ ያሉ ያርፉበት ዘንድ አብ ሰንበትን ቀደሳት ለሚወዱት ያዘጋጀውን በንጹሐን ማደሪያ ያከብር አክሊልን ትቀዳጁ ዘንድ ወደ እውነት አምላክ ቅረቡ በዓለም ላሉ የቅዱሳን መምህራቸው፣ የሰማዕታት አክሊላቸው፣ የካህናት ክብራቸው የሆነው ጌታቸውን ደስ ያሰኙት ዘንድ በሃይማኖት፣ በጸጋና በልጅነት ጽኑ፣ በእምነታቸውም የምስክርነትን አክሊል ወረሱ። #ሊቅ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
፫ #ምኵራብ
❤ ሦስተኛው የዘመነ አስተምሕሮ ሳምንት "ምኵራብ" የሚባል ሲኾን ይህም ከኅዳር ፳–፳፮ ያሉትን ሰባት ቀናት የሚያካትት ሳምንት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ጌታችን፣ አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራበ አይሁድ ሕዝቡን እየሰበሰበ ማስተማሩ፤ ባሕርና ነፋሳትን መገሠፁ፤ አጋንንትን ከሰዎች ማውጣቱ ይነገራል፡፡
በዕለቱ (እሑድ) የሚቀርበው መዝሙር፡- "አምላክ ፍጹም በህላዌሁ ዘሀሎ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ….፤ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበረው አምላክ (እግዚአብሔር) በህልውናው (አነዋወሩ) ፍጹም ነው …." የሚለው ሲኾን፣ ምስባኩም፡- "ቅረቡ ኀቤሁ ወያበርህ ለክሙ ወኢይትኀፈር ገጽክሙ ዝንቱ ነዳይ ጸርሐ ወእግዚአብሔር ሰምዖ፤ ወደ እርሱ ቅረቡ፤ ያበራላችሁማል፡፡ ፊታችሁም አያፍርም፡፡ ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤" የሚል ነው (መዝ ፴፫፥፭-፮)፡፡ ወንጌሉም ከማቴዎስ ፰፥፳፫ እስከ መጨረሻው ድረስ ነው፡፡ ቅዳሴውም ቅዳሴ እግዚእ ነው፡፡
❤ የዕለቱ ወንጌል ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመርከብ ውስጥ ሳለ መርከቢቱ እስክትናወጥ ድረስ ታላቅ ማዕበል መነሣቱን፤ ቅዱሳን ሐዋርያት "ጌታ ሆይ እንዳንጠፋ አድነን?" እያሉ በመተማጸኑት ጊዜ ጌታችን ነፋሱንና ባሕሩን በመገሠፅ ጸጥታን፣ ሰላምን፣ መረጋጋትን ማስፈኑን የሚናገረው ክፍል ነው፡፡ በባሕሩ ዓለም ውስጥ የምትገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰዎች በፈቃደ ሥጋቸው ተሸንፈው ባመጡት ጥላቻ፣ ኑፋቄ፣ ክህደት፣ ፍቅረ ንዋይ፣ በአጠቃላይ በልዩ ልዩ የኀጢአት ማዕበልና ሞገድ እየተናወጠች ናት፡፡ ይህን ማዕበልና ሞገድ ጸጥ በማድረግ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ሰላምንና ጽድቅን ማስፈን የሚቻለውን መድኀኒታችን ክርስቶስን እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት በአንድነት ኾነን "ጌታ ሆይ እንዳንጠፋ አድነን?›› እያልን እንማጸነው፡፡ የሰላሙ ዳኛ፣ የሰላሙ መሪ፣ የሰላሙ ጌታ፣ የሰላሙ ንጉሥ፣ የሰላሙ ባለቤት እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን፣ መረጋጋትን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን ካወጀ በቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር፣ አንድነት ሰላም ይሰፍናልና፡፡
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ቅረብ ኀቤሁ ወያበርህ ለክሙ። ወኢይትኀፈር ገጽክሙ። ዝንቱ ነዳይ ጸርሐ ወእግዚአብሔር ስምዖ"። መዝ 33፥5-6 የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥25-ፍ.ም፣ ያዕ 3፥4-13 እና የሐዋ ሥራ 21፥27-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 8፥22-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበትና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን #በወንጌላዊ_ቅዱስ__ማርቆስ እጅ ጵጵስና ለተሾመው ለእስክንድርያ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_አንያኖስ_ለዕረፍት በዓልና ለሠራዊት አለቃ ለከበረ #ለሰማዕት_ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሊቀ_ጳጳስ_ቅዱስ_አንያኖስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸዉ እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ወደ እስክንድርያ አገር መጀመርያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ "አቴኦስ" አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገነው።
❤ ከዚህም በኋላ አፈር አንሥቶ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በአንያኖስ ጣት ላይ አደረገውና በዚያን ጊዜ አዳነው አንያኖስም ከዚህ ድንቅ ምልክት የተነሣ አደነቀ ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወሰደው ስለ ሥራው ስለ አምልኮቱም የመጣውም ከወዴየት ቦታ እንደሆነ ጠየቀው። ቅዱስ ማርቆስም ከብሉያትና ከሐዲሳት መጻሕፍት የአንድ እግዚአብሔርን ህልውና ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት የወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን መከራ መስቀልንም ተቀብሎ ስለመሞቱ ስለ ትንሣኤውና ስለዕርገቱ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ ይነግረው ጀመረ። የአንያኖስ ልቡ ብሩህ ሁኖለት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰብ ሁሉ ጋር ተጠምቀ። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላያቸ ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ።
❤ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ለማስተማር በፈለገ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ በግብጽ አገር ለወገኖቹ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምራብ ከእስክድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት።
❤ ይህ የተመሰገነ አባት አንያኖስም በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት አገልግሎ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ አንያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 20 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥5-12፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 20፥20-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አንያኖስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት አንዱ ለሆነው #ለሐዋርያው_ቅዱስ_በርቴሎሜዎስ እልዋህ በሚባል አገር አስተምሮ ብዙዎችን እግዚአብሔር ወደማወቅ ለመለሰበት ለመታሰቢያ በዓሉና #ለቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ከሚስቱ_ቅድስት_ጰጥሪቃ ከአምስት ወር ልጁም #ከቅዱስ_ደማሊስ ጋር #ሰማዕትነት_ለተቀበሉበት_ለዕረፍታቸው በዓልና ሩጻፋ በሚባል አገር #ለሰማዕት_ቅዱስ_ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለከበረችበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ሚስቱ_ቅድስት_ጰጥሪቃ የአምስት ወር ልጁ #ቅዱስ_ደማሊስ፦ ይህ ቅዱስ እግዚአብሔርን በመፍራትና በአማረ አምልኮ ያደገ ነው ሰዎች ሒደው ቅዱስ ቴዎፍሎስ ክርስቲያን መሆኑን ለመኰንኑ ለአንቲጳጦስ ነገሩሩት መኰንኑም በዜውስ ጣዖት ቤት ሳለ ወደርሱ ያመጡት ዘንድ አዘዘ። ቅዱሱንም በአቀረቡት ጊዜ "አንተ ከወዴት ነህ? ሃይማኖትህስ ምንድን ነው?" አለው። እርሱም "የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስን ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ" አለ መኰንኑም "በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ለአማልክተሰ ሠዋ" አለው ቅዱሱም "ክብር ይግባውና ከጌታዬ ከኢየሱስ በቀር ለረከሱ አማልክት አልሠዋም" አለው።
❤ መኰንኑም የሆድ ዕቃው እስቲታይ ሰቅለው ይሠነጥቁት ዘንድ አዘዘ እርሱ ግን በጌታችን ኃይል ስለጠበቀ ምንም ምን አልደረሰበትም ሁለተኛም እሳትን አንድደው ከውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ ቅዱሱም በእሳት መካከል በጸለየ ጊዜ እሳቱ ተበተነ ምንም ምን ሳይነካው ከእሳት ውስጥ ወጣ። መኰንኑም ይህን አይቶ በረኃብ እንዲሞት አሥረው አጽንተው ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ ከስምንት ቀንም በኋላ ሚስቱ ጰጥሪቃ ሕፃኗን ተሸክማ መጣች ምስክርም ሁኖ በክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አጽናቸው።
❤ መኰንኑም ለቅዱስ ቴዎፍሎስ ምግብ የሰጠው እንዳለ ብሎ ሊመረምር ሔደ የእሥር ቤቱንም ደጅ በከፈተ ጊዜ ጣፋጭ የዕጣን መዓዛ ተቀበለው ቅዱስ ቴዎፍሎስንም በተነጠፈ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ሦስት መላእክት ማርና ወተት ሲመግቡት አገኘው በአየውም ጊዜ ደንግጦ ወደኋላው ተመለሰ። በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎፍሎስን ወደ አደባባይ እንዲአመጡት አዘዘ እርሱም ሚስቱ ተከታትለው መጣ መኰንኑም "ዲዮስ ለሚባል አምላክ ሠዋ" አለው። ቅዱሱም "እኔ ዓለምን ሁሉ ለያዘ ለእውነተኛው አምላክ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለሌላ አልሠዋም" አለ።
❤ በዚያንም ጊዜ ለአንበሳ እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ አንበሳውም ሩጦ እግሮቹን ሳመ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ አቈሰለው ተጋድሎውን በዚህ ፈጽሞ ነፍሱን ሰጠ ቅድስት ሚስቱ ጰጥሪቃም ሥጋውን አንሥታ ከሣጥን ጨመረች መኰንኑም እርሷንም ወደ አደባባይ አምጥተው ለአንበሳ እንዲሰጧት አዘዘ ሕፃኑም አንበሳውን በአየው ጊዜ ሣቀ የአምስት ወርም ልጅ ሲሆን "አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምናለሁ" ብሎ በአንበሳ አፍ ከእናቱ ጋር ተበላ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #የሰማዕቱ_ቅዱስ_ሰርጊስ_ቤተ_ክርስቲያን_የከበረችበት፦ ይህም ቅዱስ ሰርጊስ በሩጻፋ አገር በሰማዕትነት በአረፈ ጊዜ ምእመናን ሥጋውን ወስደው ገንዘው በእርሱ ዘንድ አኖሩት በፊቱም መብራቶችን አኖሩ የመከራውም ዘመን እስቲያልፍ በእነርሱ ዘንድ ተሠውሮ ኖረ። ከዚያም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን አነፁለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትንም ሰብስበው አከበሩዋት በዚች ቀን ኅዳር 19 ቀን ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቅ ተአምር ተገለጠ በእምነት ከእርሱ ለሚወስዱ ሁሉ በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሽታው እጅግ ጣፋች የሆነ የሽቱ ቅባት ከሥጋው የሚፈስ ሆኗልና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_እብል_ሐዋርያ_መስተጋድለ። በተወርዎ ባሕር ዕሙቅ እንዘ ሠቀ ጸጒር ጥብሉለ። #በርተሎሜዎስ ገዳመ አመ ምስሌሆሙ ዔለ። በማየ ጸሎቱ ጽምዐ ነጋድያን አጥለለ። ወአንሥአ ዓዲ ዘሞቱ አግማለ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 19።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ጽልአ በአመፃ ይጸልዑኒ። ዕቀባ ለነፍስየ ወአድኅና። ወኢትኀፈር እስመ ኪያከ ተወከልኩ"። መዝ 24፥19-20። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 15፥17-26።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ሕጉ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ። ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ። ኵነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ"። መዝ 18፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 12፥28-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 4፥29-36። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥1-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም በዓልና ጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ለዓለም_ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው #ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ጋር_የሥላሴን_መንበር ላጠኑት #ለአቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት_ለልደታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት፦ አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ዳግም ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ትውልድ ሀገራቸው ወሎ መቄት እንጂፋ ነው፡፡ አባታችን አባ ዮሴፍ ኅዳር 19 ቀን ሲወለዱ በርካታ ሙታን ተነሥተዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲያደንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት።
❤ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና "ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወድዋለህን አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለ ሁሉ" አለው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ እግዚአብሔር እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ።
❤ ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኵስና ልብስ አለበሰው። ወደትግራይ ምድርም ወስደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኵስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ። በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ አባ ናትናኤልም የጋለ ምንቸት በመሐል እጁ ይዞ በመነኰሳቱ ፊት ዞረ። አባ ዮሴፍም የሚያበስሉበት ማሰሮ በተሰበረ ጊዜ ወጡ ሳይፈስ አገናኝቶ እንደ ቀድሞው አደረገው። ገብረ ኄርም ሕዝባዊ ሲሆን በሞተ ጊዜ ሊአጠምቁት ሲሉ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኤጲስቆጶስነት ሹሞኛልና እኔ በእጄ አጠምቃችኋለሁ" አላቸው። እሊህም ቅዱሳን የትሩፋታቸውንና የጽድቃቸውን የአማረ ሥራቸውን አሳዩ።
❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ወደ ጳጳስ ወሰዱትና ቅስና ተሾመ። አባ ዘካርያስም በዐረፈ ጊዜ አባ ዮሴፍ ወደ ሌላ ገዳም ሒዶ ሳይቀመጥ ቁሞ አርባ መዓልትም አርባ ሌሊት ጾመ። ከድካም ጽናትም በወደቀ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል አነሣው። ሁለተኛም ከገደል አፋፍ እጁን ዘርግቶ ሳይሰበስብ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ቆመ። ሰይጣንም መጥቶ ወደ ቆላ ወረወረው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተቀብሎ ወደ መቆሚያው መለሰው። ደግሞም ከደንጊያ ወሻ ውስጥ ገብቶ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ኖረ። ሰይጣናትም ወደርሱ እየመጡ በየራሳቸው ምትሐት በማሳየት ያስፈራሩት ነበር መላእክትም ያበረቱትና ያጸኑታል። ናላው በአፍንጫው እስቲፈስ ድረስ በየእልፍ እልፍ እየሰገደ ኖረ።
❤ ከዚያም የትራይን አውራጃዎች ሁሉ ዞረ። ወደ ሰሜንም ምድር ተሻግሮ ከቅዱስ ያሬድ መቃብር ገባ በደጃፉም ላይ ተቀርጾ አግኝቶ አንቀጸ ብርሃን ተማረ። ሲመለስም ሽፍቶች አግኝተውት በደንጊያ ወገሩት በበትርም ደበደቡት በጦርም ወግተው ጥለውት ሔዱ። አምላክን የወለደች እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ወደርሱ መጥታ አዳነችው። አንዲት ቀንም የሴት በድን አግኝቶ በላይዋ ባማተበ ጊዜ ተነሣች።
❤ ወደ ኢየሩሳሌምም ሦስት ጊዜ ሒዶ ከከበሩ ቦታዎች ተባርኳል ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት መቃብም እስከ አገረ ባርቶስና ሕንደኬ ደረሰ። ውኃው ከመላበት ወንዝም በሚደርስ ጊዜ በላዩ አማትቦ እንደ የብስ በእግሩ እየረገጠ ይሻገረዋል። አንበሶችና ነብሮች ይከተሉታል ምግብ በአጡ ጊዜ ድንጊያውን ባርኮ ሥጋ አድርጎ ይሰጣቸዋል።
❤ ከዚህ በኋላም ወደ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ደብረ ሊባኖስ ሔደ። ከአባ ተወልደ መድኅንም እጅ አሰሰኬማ ተቀበለ። አባ ተወልደ መድኅንም ሊፈትነው ወዶ ሰባት የጽድ ቅርንጫፍ ሰብሮ ትከለው ብሎ ሰጠው በተከላቸውም ጊዜ ወዲያውኑ በቅለው አደጉ እስከ ዛሬም አሉ። ብዙዎችም ወደርሱ መጥተው በእርሱ እጅ መነኰሱ እግዚአብሔር አብና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ድንግል ማርያም ስም በአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በአንድነት ኖሩ።
❤ በአንዲት ዕለትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕጣንን ሰጠችውና ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋራ የአሸናፊ የእግዚአብሔርን መንበር አጠነ። ብዙ ጊዜም ወደርሱ ሐዋርያት እየመጡ ይባርኩታል። በአንዲት ዕለትም ነብር ከእናቱ እጅ ሕፃንን ነጥቆ ወሰደ በአባ ዮሴፍም ስም በአማጸነችው ጊዜ በሦስተኛው ቀን መለሰላት።
❤ ለልጆቹም ገንዘብም ሆነ የእንስሳ ጥሪት እንዳያደርጉ ሥጋ እንዳይበሉ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ትሕትናን ቅንነትን እንዲማሩ ከንቱ ነገር ቧልትን እንዳይናገሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይስቁ ይህ ሁሉና የመሳሰለውን ሥርዓትን ሠራላቸው።
❤ ከዚህም በኋላም ሩጫውን በፈጸመ ጊዜ ግንቦት19 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ ደብረ ታቦር ብሎ በሰየማት ቤተ ክርስቲያንም ተቀበረ ከእርሱም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑረሰ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 19 ስንክሳር።
ነቢያት እንደሰበኩ ነገረቻት።
❤ ሁለተኛም ስለ ከበረ ስሙ መከራ በመቀበል ለሚደክሙ ሰማያዊ ሀብት የዘላለም መንግሥትን እግዚአብሔር ስለ ሚሰጣቸው አስረዳቻት። አጥራስስም የዮናን ትምርቷን ሰምታ እጅግ ደስ አላት በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመነች።
❤ እሊህ ደናግልም ሌሊትና ቀን በተጋድሎ ተጠምደው በአንድነት ተቀመጡ የአጥራስስም አባቷ ይህን አያውቅም ከሌሊቶችም በአንዲቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዩት እናቱን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም አዩአት። እመቤታችንም ወደ ልጅዋ እግዚአብሔር እንደ ቁርባን አቀረበቻቸውና እርሱም ባረካቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ወደ ጦርነት ሒዶ በተመለሰ ጊዜ ወደ ልጁ አጥራስስ ገብቶ "ልጄ ሆይ ወደ መሞሸሪያሽ ከመግባትሽ በፊት ለአምላክ አጵሎን ዕጣን ታሳርጊ ዘንድ ነዪ" አላት። አጥራስስ ድንግልም "አባቴ ሆይ ነፍስህና ሥጋህ በእጁ ውስጥ የሆነ የፈጠረህን በሰማይ ያለ አምላክን ትተህ ነፍስ የሌላቸው የረከሱ ጣዖታትን ለምን ታመልካለህ" ብላ መለሰችለት። ንጉሥም እንዲህ ያለ ነገር ከቶ ያልሰማውን ከልጁ አፍ በሰማ ጊዜ አደነቀ በልጁ ላይ ምን እንደደረሰ ልቧንም ማን እንደለወጠው ጠየቀ የፍላጽፍሮን ልጅ ድንግል ዮና የልጁን ልብ እንደ ለወጠች ነገሩት።
❤ ንጉሡም በእሳት ያቃጥሏቸው ዘንድ አዘዘ በወርቅና በብር በተጌጠ የግምጃ ልብሶችን እንደ ተሸለሙ አወጧቸው እነርሱ የነገሥታት ልጆች ስለሆኑ አላራቆቿቸውም ታላላቆችና ታናናሾች ሁሉም ሰዎች ስለ እሳቸው እያዘኑና እያለቀሱ ወጡ ነፍሳቸውንም እንዳያጠፉ ለንገሥ ይታዘዙ ዘንድ ለመኗቸው እነርሱ ግን ከበጎ ምክራቸው አልተመለሱም።
❤ በዚያንም ጊዜ ጉድጓድ ቆፈሩላቸውና በውስጡ እሳትን አነደዱ ነበልባሉም እጅግ ከፍ ከፍ አለ ያን ጊዜ አንዷ ከሁለተኛዋ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ እሳት ውስጥ ተወረወሩ ፊታቸውንም ወደ ምሥራቅ መልሰው በመቆም ረጅም ጸሎትን ጸለዩ ከዚህም በኋላ ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ እሳቱም እንደውኃ የቀዘቀዘ ሆነ ምእመናንም ሥጋቸውን አነሡ ተጠጋግተውም ልብሳቸውንም ቢሆን ወይም የራሳቸውን ጠጉር እሳት ምንም ምን ሳይነካቸው አገኟቸው ። የመከራውም ወራት እስቲፈጸም በታላቅ ክብር በአማረ ቦታ አኖርዋቸው ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸው ሥጋቸውን በውስጥዋ አኖሩ ከእርሳቸውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ደናግላን ሰማዕታት አጥራስስና ዮና ጸሎት ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 18 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4 ወይም መዝ 145፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-11።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን። እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን። ወይትዌክፎሙ ለዕቤራት ወለእጓለ ማውታ"። መዝ 145፥8-8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ፊል 1፥12-19፣ 1ኛ ጴጥ 3፥10-18 እና የሐዋ ሥራ 16፥14-25። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥16-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ፊሊጶስ የዕረፍትና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) Saints Of The Orthodox Tewahedo Church.:
❤ "በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፲፰ (18) ቀን።
❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት አንዱ ለሆነው #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ፊልጶስ_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ #ከሮሜ_አገር በንጉሥ እንድርያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ለቅዱስ_ኤላውትሮስና_ለእናቱ_ቅድስት_እንትያ ለዕረፍትና #ለቅዱሳን_ደናግል_አጥራስስና_ዮና ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከየዋህ #ከቅዱስ_አትናቴዎስ ከዕረፍቱ መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሐዋርያ_ቅዱስ_ፊሊጶስ፦ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት ውስጥ ነው በማቴ 10፥3 ላይ እንደተጠቀሰው ከ12ቱ ሐዋርያት ውስጥ በ5ኛ ደረጃ ተጠቅሷል፡፡ ከገሊላ የተገኘ የቤተ ሳይዳ ሰው ሲሆን የግሪክ ሰዎችን ወደ ጌታችን ያቀረባቸው እርሱ ነው፡፡ ዮሐ12፥20-22፡፡ቅዱስ ፊሊጶስ ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤልን "የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል መጥተህ እይ…" በማለት ወስዶ ከጌታችን ጋር አገናኝቶታል፡፡ ዮሐ 1፡44-52፡፡ በኋላም ጌታችንን "አብን አሳየንና ይበቃናል" ብሎ የጠየቀውም ይኸው ሐዋርያ ፊሊጶስ ነው፡፡ ይህም ጥያቄው ለእኛ ለሁላችን መሠረታዊውን የክርስትና እውቀት እንድናገኝ ረድቶናል፡፡ ጌታችንም"እኔን ያየ አብን አይቷል፣ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ" በማለት ነው መልስ የሰጠው፡፡ ዮሐ14፥8-14፡፡
❤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ወንጌልን ዞሮ በማስተማር ብዙዎች ጣዖት ማምለካቸውን ትተው በክርስቶስ እንዲያምኑ አድርጓል፡፡ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ሐዋርያው ፍርግያ፣ ሰማርያና ጋዛ በሚባሉ አገሮች ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቆአል፡፡ ሐዋርያው በመጨረሻ ወደ ታናሽዋ እስያ ሄዶ በሄራፖሊስ ከተማ ሲያስተምር ብዙዎችን በማሳመኑ ክፉዎች ይዘው አሠቃዩት፡፡ ከብዙ ሥቃይም በኋላ ጣዖት አምላኪዎች ኅዳር 18 ቊልቁል ሰቅለውት ሰማዕትነቱን ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀዳጅቷል፡፡ ክፉዎችም በግፍ ከገደሉት በኋላ ሥጋውን በእሳት ሊያቃጥሉት በወደዱ ጊዜ የታዘዘ መልአክ የሐዋርያውን ቅዱስ ሥጋ ከእጃቸው ነጥቆ ወሰደባቸውና ሰወረው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር በተመለከቱ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ "ከቅዱስ ፊልጶስ አምላክ በቀር ሌላ አምላክ የለም"ብለው፡ጮኹ፡፡
❤ አሠቀይተው ስለገደሉትም ተጸጽተው እጅግ አዘኑ፡፡ ክብር ይግባውና በጌታችን ካመኑ በኋላ የሐዋርያው የቅዱስ ፊሊጶስን ቅዱስ ሥጋውን ይሰጣቸው ዘንድ በጸሎት ለመኑ፡፡ ሰውን የሚወድ ቸር ይቅር ባይ ጌታችንም የቅዱስ ፊሊጶስን ቅዱስ ሥጋውን መልሶ ሰጣቸውና እጅግ ተደሰቱ፡፡ ከሐዋርያውም ቅዱስ ሥጋ ብዙ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ተፈጸሙላቸው፡፡ የሐዋርያውም መካነ መቃብሩ እስካሁንም ድረስ በዚህች ከተማ ይገኛል፡፡ ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስና ስንክሳር የኅዳር 18።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ኤላውትሮስና_እናቱ_ቅድስት_እንትያ፦
ይህም ቅዱስ እግዚአብሔርን ከሚፈራ አንቂጦስ ከሚባል ኤጲስቆጶስ ዘንድ አደገ ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ዲቁና ተሾመ ደግሞ በዐሥራ ስምንት ዐመቱ ቅስና ተሾመ ከዚህም በኋላ በሃያ ዓመቱ አላሪቆስ ለሚባል አገር ጵጵስና ተሾመ።
❤ በዚያንም ወራት ንጉሥ እንድርያኖስ ወደ ሮሜ አገር መጣ ስለ ኤላውትሮስም ሰምቶ ወደርሱ ያመጣው ዘንድ ፊልቅስን አዘዘው ፊልቅስም በሔደ ጊዜ ቅዱሱን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምር አገኘው። ፊልቅስም ትምርቱን በሰማ ጊዜ አመነና በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቀ።
❤ ቅዱስ ኤላውትሮስንም ወደ ንጉሥ እንድርያኖስ በአደረሱት ጊዜ "ለአማልክት ሠዋ አንተ ነጻነት ያለህ ስትሆን ለተሰቀለ ሰው ለምን ትገዛለህ" አለው ። ኤላውትሮስም "ነጻነትማ ሰማይና ምድርን በፈጠረ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ነው" ንጉሡም መንኰራኩር ካለው የእሳት ማንደጃ ውስጥ ጨምረው እንዲአቃጥሉት አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ እሳቱ ጠፋ መንኩራኩሩም ተቆራረጠ። ንጉሡም አይቶ አደነቀ የሚያደርገውንም አጥቶ ከወህኒ ቤት ጨመረው ርግብም ከገነት መብልን አምጥታለት በልቶ ጠገበ ። ቆሊሪቆስ የሚባለውም መኰንን አይቶ በቅዱስ ኤላውትሮስ አምላክ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ።
❤ ከዚህም በኋላ ፈረሶችን አምጥተው በሠረገላ ላይ እንዲጠምዷቸው ቅዱስ ኤላውትሮስንም ከሠረገላው በታች አሥረው ሕዋሳቱ እስኪሰነጣጠቅ ፈረሶችን እንዲአስሮጡአቸው እንድርያኖስ አዘዘ። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወረደ ከማሠሪያውም ፈትቶ ወደ ከፍተኛ ተራራ ወሰደው በዚያም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ከአራዊት ጋር ተቀመጠ ።
❤ እንድርያኖስም አራዊትን ያድኑ ዘንድ ወታደሮቹን በአዘዘ ጊዜ በዚያ ተራራ ውስጥ ቅዱስ ኤላውትሮስን አግኝተው ከዚያ ወደ ንጉሥ እንድርያኖስ ወሰዱት። ንጉሡም ለአንበሳ እንዲሰጥ አዘዘ አንበሶችም የፊቱን ላብ ጠረጉለትና እግሮቹን ሳሙ ከዚህም በኋላ ተመልሰው ከአረማውያን መቶ ሃምሳ ሰው ገደሉ እንድርያኖስም አይቶ ቁጣን ተመላ ሁለት ወታደሮችን ከእንትያ እናቱ ጋር በጦር እንዲወጉት አዘዘ እርሷንም ብዙ ከአሠቃይዋት በኋላ የልጅዋን አንገት እንዳቀፈች ከእርሱ ጋር ወጓት ነፍሳቸውንም ኅዳር 18 ቀን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በቅዱስ ኤላውትሮስና በእናቱ ቅድስት እንትያ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳት_ደናግል_ሰማዕታት_አጥራስስና_ዮና፦ አጥራስስ ግን ጣዖታትን ለሚያመልክ ንጉሥ እንድርያኖስ ልጁ ናት እርሱም ከሰው ወገን ማንም እንዳያያት አዳራሽ ሠርቶ ለብቻዋ አኖራት እርሷ ግን ስለዚህ ዓለም ኃላፊነት የምታስብ ሆነች አውነተኛውንና የቀናውን መንገድ ይመራት ዘንድ በቀንና በሌሊት እግዚአብሔርን ትለምነው ነበር። "ወደ ፍላጽፍሮን ልጅ ወደ ድንግሊቱ ዮና ላኪ እርሷም የእግዚአብሔርን መንገድ ትመራሻለች" የሚላትን ራእይ አየች ከእንቅልፏም ስትነቃ በልቧ ደስ አላት ወደ ዮና ድንግልም ላከች እርሷም ፈጥና መጣች ለዮናም ሰላምታ ሰጠቻትና ከእግርዋ በታች ሰገደችላት የእግዚአብሔርንም ሃይማኖት ታሰተምራትና ትገልጥላት ዘንድ ለመነቻት።
❤ ድንግል ዮናም የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነበትን ምክንያት እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረበት ጊዜ በመጀመር ልትነግራት ጀመረች አዳም እንደበደለና ከተድላ ገነት እንደ ወጣ በኖኅም ዘመን የጥፋት ውኃ መጥቶ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንደደመሰሰ የእግዚአብሔርን ሕግ የጠበቁ ስምነት ሰዎች ብቻ እንደ ቀሩ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ሰዎች በምድር ላይ በበዙ ጊዜ እንደበደሉና ጣዖትን እንዳመለኩ እግዚአብሔርም ለአብርሃም እንደተገለጠለትና መርጦ ወዳጅ እንዳደረገው ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳንን እንዳጸና እስራኤልንም ከግብጽ አገር እንዳወጣቸው የሰውንም ወገን ጠላት ሰይጣንን ከማምለክ ለእርሱም ከመገዛት ያድነው ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ መምጣቱንና ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው መሆኑን
የአጫብር ዜማ ጥናት እንዲቀጥል የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ውሳኔ አስተላለፈ
ለወራት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እግድ አስተላልፎበት የነበረው የአጫበር ስም የሚደረጉ የተለያዩ ችግሮችን እንጂ በተፈቀደላቸው ባለ ሙያዎች የሚሰጥ ሥልጠናን ስለማይመለከት የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ ከሚመለከታቸውን ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የአጫብር ዜማን ማስጠናት እንዲቀጥል ውሳኔ አስተላልፏል።
የአጫብር ዜማ ጥናቱ ሲቀጥል መጋቤ ሃይማኖት ዲበኵሉ ኅየሰ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍልናከአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጋር ተናበው እንዲሰሩ ተብሏል።
የአጫብር ዜማን በተመለከተ በሊቃውንት ተጠንቶ እስኪተገበር ድረስ ሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤት የአጫበር ዝማሬን እንዲያቆሙ ተወስኖ እንደነበር ይታወሳል ።
❤ መድኃኔዓለም አምላካችን ለአቡነ ባዕለ ማርያም ይህን ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኋላ "እንደ ነቢያት ነቢይ እንደ ሐዋርያት ሐዋርያ እንደ ሰማዕታት ሰማዕት እንደ ጻድቃን ጻድቅ፤ እንደ ካህናት ካህን ነህ፤" አላቸው ክብርና ጸጋን አጐናጸፋቸው አምስት ጊዜ ባረካቸው አምስት ጊዜ እፍ አለባቸው መንፈስ ቅዱስንም አሳደረባቸው እመቤታችን ድንግል ማርያም እና ዘጠኙ ሊቃነ መላእክት አንድ አንድ አክሊል ሰጧቸው ጌታችንም ዐሥር አክሊላትን አቀዳጅቷቸው "በዛሬው ዕለት ወደ እኔ ትመጣለህ" ብሏቸው ወደ ሰማይ ዐረገ።
❤ ጻድቁ አቡነ ባዕለ ማርያምም "ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድ ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፣ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ድንግል ማርያምም ምስጋና ይገባል፣ በክቡር ደሙ ለተቀደሰው ለመስቀለ ክርስቶስም ምስጋና ይገባል"። ብለው ካመሰገኑ በኋላ በዚሁ ዕለት ኅዳር ፲፯ ቀን ዐረፉ ቅድስት እናታችን ወለተ ጴጥሮስም የታሰሩበት ሰንሰለት የማይፈታ ጽኑ ስለ ነበረ እንዳለ ቀብራቸው ወደ ጎንደር ተመልሳ ሄደች። ከአባታችን ከአቡነ ባዕለ ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፤ በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድለ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ መግቢያ ላይ የተወሰደ።
