fa
Feedback
Ambara - አምባራ

Ambara - አምባራ

رفتن به کانال در Telegram

Ambara = “The High Place of Greatness” “የከፍታና የታላቅነት ስፍራ” ☞ ታሪኮች ☞ ግጥሞች ☞ ሀሳቦች ☞ የጉዞ ማስታዎሻዎች ☞ ተስፋዎች @Adwa1888 [አምባዬ ጌታነህ] ለስራ ከፈለጋችሁ ደግሞ ታችኛውን ተጠቀሙ @Rich_poet

نمایش بیشتر
3 546
مشترکین
-124 ساعت
-227 روز
-6730 روز

در حال بارگیری داده...

ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژوئن '26
ژوئن '26
+3
در 0 کانال‌ها
مه '26
+9
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+2
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '24
+11
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '24
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '24
+18
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '24
+16
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '24
+21
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '24
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '24
+4
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '24
+12
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '24
+11
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '24
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '24
+5
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '24
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '23
+12
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '23
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '23
+14
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '23
+11
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '23
+38
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '23
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '23
+14
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '23
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '23
+15
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '23
+12
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '23
+11
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '23
+17
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '22
+25
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '22
+29
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '22
+32
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '22
+37
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '22
+39
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '22
+45
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '22
+50
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '22
+66
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '22
+58
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '22
+60
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '22
+54
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '22
+57
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '21
+106
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '21
+60
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '21
+203
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '21
+163
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '21
+136
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '21
+81
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '21
+104
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '21
+22
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '21
+75
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '21
+137
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '21
+28
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '21
+41
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '20
+13 230
در 0 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
14 ژوئن0
13 ژوئن0
12 ژوئن0
11 ژوئن0
10 ژوئن0
09 ژوئن+1
08 ژوئن0
07 ژوئن0
06 ژوئن0
05 ژوئن+1
04 ژوئن0
03 ژوئن0
02 ژوئن0
01 ژوئن+1
پست‌های کانال
ውድ የ @Ambara1 ቤተሰቦቼ 🙏 ቻናላችን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ ድጋፋችሁ ያስፈልገናል። በዚህ ሊንክ ቻናሉን Boost በማድረግ ቻናላችንን ከፍ እናድርግ፦ https://t.me/Ambara1?boost እያንዳንዱ ድጋፍ ቻናላችንን ወደ አዲስ ደረጃ ያደርሰዋል፣ እና ተጨማሪ አስደናቂ ባህሪያትን ይከፍታል። ከልብ እናመሰግናለን ❤️ @Ambara1

2
የቬትናም 🇻🇳 ጉዞ ማስታዎሻ📝 ክፍል -2- (አምባዬ ጌታነህ) አዲስ አበባ በሚያማምሩ የመንገድ ዳር የመብራት ባውዛዎቿ የምሽቱን ማራኪ ውበት ገልጣ አለስስት እያሳየች መንገደኛንም አሽከርካሪንም+1
የቬትናም 🇻🇳 ጉዞ ማስታዎሻ📝 ክፍል -2- (አምባዬ ጌታነህ) አዲስ አበባ በሚያማምሩ የመንገድ ዳር የመብራት ባውዛዎቿ የምሽቱን ማራኪ ውበት ገልጣ አለስስት እያሳየች መንገደኛንም አሽከርካሪንም የምታማልል ኮረዳ መስላለች። ይህንን የአዲስ አበባን አዲስ መልክ ጠግበን ሳንጨርስ የተሳፈርንበት ራይድ በፍጥነት ቦሌ አለምአቀፍ የመንገደኞች መግቢያ በር አደረሰን። እንደደረስን የተጓዡን ሰው ብዛት ሳይ ሁሉም ህዝብ ከሀገር የሚወጣ ያህል ስለተሰማኝ ደነገጥኩ። "ኢትዮጵያ ማን ቀረ ታዲያ?" በማለትም ለብቻዬ አጉተመተምኩ። የሻንጣ ጋሪውን እየገፋ ወደ ኢንተርናሽናል ተርሚናሉ የሚጋፋው ሰው ብዛት ቀላል አይደለም። የእኔ የጉዞ ጓደኞቼ አብረውን ሊሸኙን ከመጡ ወዳጆቻችንና የንግድ አጋሮቻችን ጋር አጥሩ ላይ ፎቶ ለማስታዎሻም ለሽያጭም በመነሳት ተጠምደው ሳለ። እኔ በተጓዡና በሸኚው ሰው መካከል ያለን ጥልቅ ስሜት በአርምሞ እያነበብኩና እያደመጥኩ መሀል ላይ ሻንጣዬን አስቀምጬ ቆሜያለሁ ። አንዳንዶቹ ድጋሚ የማይገናኙ እስኪመስሉ ድረስ ለረጅም ደቂቃ ተቃቅፈው ይላቀሳሉ። ከእንደገና ቸው ተባብለው ሲያበቁ ሁለቱም ከእንደገና ዘወር ብለው ይተያዩና እንደ ህንድ ፊልም ፍቅረኛሞች ከያሉበት ይመለሱና ድጋሚ ይተቃቀፋሉ። ነገሩን ዝም ብሎ ለሚመለከት የእውነተኛ ስሜት ሳይሆን ራቅ ብሎ የሚቀርፃቸው ካሜራ ያለ ነው የሚመስለው። እነሱን አይቼ ተገርሜ ሳልጨርስ አለፍ ስል ደግሞ ትልልቅ ሄድ ሴት በጆሯቸው አድርገው ረጅም ሻንጣቸውን እየጎተቱ በሰላም የሚሄዱ መንገደኞችንም አያለሁ። ከእንደገና አይኔን በሌላኛው አቅጣጫ ሳደርግ ደግሞ በፈገግታ ታጅበው ቦታ እየቀያየሩ ፎቶ የሚነሱ ወጣቶችን እመለከታለሁ። በአጭሩ ወደ ውጪ ሀገር መግቢያ ተርሚናሉ አካባቢ አያሌ ተፅፎ የማያልቅ ትዕይንት በምሽቱ እየተከናወነ ነበር። እኔ ከሀገር ወጥቼ ስለማላቅና የመጀመሪያ የኢንተርናሽናል ጉዞዬ ስለሆነ በንቃትም በግርምትም በፍጥነትም በመደነቅም ነው ሁሉንም የምመለከተው። እኔ እስከዛች እለት ድረስ ሰው የዛን ያህል ብዛት ወደ ውጪ የሚወጣ ሰው ያለ አይመስለኝም ነበር። ለካ እኔ አልወጣም ማለት የሚወጣ ሰው የለም ማለት አይደለም። ይገርማል! ጉዟችንን በሚመሩን መሪዎች አማካኝነት አነስተኛና ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮረ ኦረንቴሽን ከተሰጠንና መጠፋፋት እንዳይኖር ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ከተቀበልን በኋላ ሻንጣችንን ይዘን መንገደኞች ወደ ሚገቡበት በር ዘለቅን። በተሰጠን መመሪያ መሠረትም አለ አይደል ልጅ ሆነን ገበያ ስንሄድ እንዳንጠፋ የእናታችንን ቀሚስ ይዘን እንደምንከተለው እኔም የቡድናችንን ታላላቅ መሪዎች የእግር ዱካ በመከተል ረጅሙን ተርሚናል ቀበቷችንና ጫማችንን እያወለቅን አንዱን ስናልፍ ሌላኛው እየተቀበለን ከብዙ ፍተሻና አድካሚ ቆይታ በኋላ አለፍን ስል ሌላ ፍተሻ ደግሞ ጠበቀን። ከቁመታችን የሚልቁ ረጃጅም ዘመናዊ የ X-Ray መፈተሻዎችን ካለፍን በኋላ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ደረስን። ሁላችንም በሰልፋችን ፖስፖርታችንንና ትኬታችንን በእጃችንን ይዘን የማለፊያ ፈቃድ ከሚሰጡን የመስኮት ደንበኛ መኮንኖች ፊት ቆሜ ተራዬን እየጠበኩ ነው። ተራዬ ደርሶ ወደ መስኮቱ ጠጋ ብዬ ለአንዱ ተቆጣጣሪ ፓስፖርቴን ሰጠሁት። እሱም ፓስፖርቴን አገላብጦ ከተመለከተ በኋላ ፊቴን ደጋግሞ ተመለከተኝ። አስተያየቱ ያስፈራል። "ለመሆኑ Travel history አለህ?" ብሎ ጠየቀኝ ብዙም ስላልገባኝ ዝም ስለው የእንግሊዘኛ ዲዳ ስለመስልኩትና የተናገረውን እንዳልሰማሁት በመገመት በአማርኛ (የጉዞ ታርክ አለህ?) ብሎ ጠየቀኝ ይህን ጊዜ ፈጠን ብዬ ኮራ ጀነን ብዬ በኩራት "አዎ" አልኩት። እሱም ኮስተር ብሎ የት የት? አለኝ "አርባምንጭ ፣ ላሊበላ! ሰውዬው አላቆመም ቀጠላና ሌላስ ሲለኝ "ኮምቦልቻም ሄጃለሁ "ስለው። አጠገቡ የነበረው ሌላኛው ተቆጣጣሪ "ትቀልዳለህ"ብሎ ኮስተር አለ። "ኧረ ማርያምን የምሬን ነው አልኩት" አጠገቤ የነበሩት ጓደኞቼ መቆም አቅቷቸው በድካም እስኪቀመጡ ድረስ ነው የሳቁት! እኔ እኮ ብዙ ጊዜ አርባምንጭ ስመላለስ በጣም ነበር የተጎረርኩት። የጊቢ ጓደኞቼ ላይ እንዴት መልክ እንደሰራሁ እኔ ነኝ የማቀው።አሁን ግን አልገባኝም። በዚህ መሀል አንዱ ከመካከላችን ያለ ይህን ጥያቄ ቀድሞ የተጠየቀው ጓደኛዬ በግራ መጋባት የመለስኩት እንደሆነ ስለገባው "አይ ይህ የመጀመሪያ ጉዞው ነው ከዚህ በፊት ከሀገር ወጥቶ አያቅም ዋልያ ነው" ብሎ በቀልድም መልክ እውነቴን ተናገረ። በዚህ ጊዜ ነው የጉዞ ታሪክ ከሀገር ውጪ የሆነ በረራ እንደሆነ የገባኝ እንጂ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሁሉ ትራቭል ሂስትሪ አለው ማለት እንዳልሆነ ተረዳሁ። ከዛም እሱን በጉዞ አዘጋጆቻችን አማካኝነት ጨራርሰን የምንበርበትን ሰአት መጠባበቅ ጀመርን። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስሙ ለምን በ ባለም አቀፍ ዝነኛ እንደሆነ የገባኝ በዚህ ጊዜ ነበር። እጅግ ዘመናዊ የሆነ የአቬሽን ስርአት ያለው አየር መንገዱም ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን እያስተዋልኩም ነበር። በ ውስጡ ሌላ ከተማ ያለ እስኪመስል እጅግ በርካታ እንቅስቃሴዎች ያሉበት ሱቅና ካፌዎች ተከፍተው በሞቀ ገበያ ውስጥ መሆናቸውን ለሚያይ የአየር መንገድ ውስጥ ያለን ሳይሆን መርካቶ ላይ ያለን ነው የመሰለኝ። እጅግ ፅዱና ማራኪ እይታዎች የተሞሉበት፣ የመንገደኛ መተላለፊያ የደረጃ አሳንሱሮቹ ፅዳት፣ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጡበት የአየር መንገዱ ሰራተኞች ለቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጡት ስብዕና ጎንበስ ቀና በማለት በትህትና የሚያናግሩበት ስርአት ሰዎች ከወዲያና ከወዲህ የሚንሸራሸሩበት አያሌ እንቅስቃሴዎች የተሞሉበት ነው። እኛ እንድንጠብቅ በተነገረን የመጠበቂያ ቦታ ተቀምጠን እስክንጠራ ዙሪያ ገባውን በጥሞና እየተመለከትኩ ነው ። በመጨረሸ መዳረሻችን ሲጠራ ትኬታችንን እያሳየን የመጨረሻውን የማለፊያ በር በድል አልፈን ወደ አውሮፕላኑ የሚወስደን ባስ ውስጥ ገባን። ከተወሰኑ ደቂቃ ጉዞዎች በኋላ መነሻውን ቦሌ አዲስ አበባ መዳረሻውን ደግሞ ቬትናም ሀኖይ ወዳደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት ወደ ሆነው ET 637 የአውሮፕላን ቁጥር ደረስን። ይቀጥላል..... ክፍል 2 ን እንዴት አገኛችሁት ሀሳባችሁን አስቀምጡልኝ እንዲሁም በጉዞ ወቅት የተመለከታችሁት ነገርስ ምንድነው ?! የመጀመሪያ ከሀገር ውጪ በረራችሁ መዳረሻውስ የት ነበር?! @Rich_poet ይህ የጉዞ ማስታዎሻ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሼር እንድታደርጉልኝ በትህትና እጠይቃለሁ። @malefia @malefia
0
3
የቬትናም 🇻🇳 ጉዞ ማስታዎሻ📝 ክፍል -1- (አምባዬ ጌታነህ) ፀሐይ በምዕራብ ሰማይ ስር እየወረደች የሰማይን ቀለም በቀይ ፣ በብርቱካናማና በወርቃማ ቀለሞች የተቀባ ውብ ስዕል ስታስመስል ፤ ባህ+1
የቬትናም 🇻🇳 ጉዞ ማስታዎሻ📝 ክፍል -1- (አምባዬ ጌታነህ) ፀሐይ በምዕራብ ሰማይ ስር እየወረደች የሰማይን ቀለም በቀይ ፣ በብርቱካናማና በወርቃማ ቀለሞች የተቀባ ውብ ስዕል ስታስመስል ፤ ባህሩ ደግሞ እነዚህን ውብ ቀለሞች ተቀብሎ ሲያንፀባረቅ የመርከቡ አናት ወንበር ላይ ተቀምጬ ስመለከት ልቤ ወደ ሌላ ዓለም ተጓዘ። የምሽቱ ጨለማ በእርጋታ እየተሸፈነ፣ አየሩ እየቀዘቀዘ ፣ የባህሩ ሽታ ከነፋሱ ጋር ተቀላቅሎ የሚሰጠውን የተፈጥሮ ሽታ በአፍንጫህ እየማግህ፤ በመርከቡ ቀላል እንቅስቃሴ እንደልብህ እያሰብህ ቀስ በቀስ ወደ መንፈስ መነጠቅ መግባት። በዚያ ከሀሳብ ጫና ርቀህ ከእንደገና ወደዋናው የተፈጥሮ ማንነትህ የምትመለስበትና የምትገናኝበትን መስመር ተፈጥሮ ራሷ ትሰጣለች። ይህ እየሆነ ደግሞ ለሊቱ የውበቱን መጋረጃ ይከፍትና በከዋክብት የተሞላውን ሰማይ እያንዳንዱ ኮከብ የሚያወጡትን የእሳት ራት መሳይ ትንሽ ብርሃን ከታች ያለው ባህር ተቀብሎ በባህሩ እያንፀባረቀ ሰማይና ውሃ አንድ ሆነው የሚፈጥሩት የማይሰማ የማይወራ በዝምታና በማየት ብቻ የሚደመጥ ውብ ጥበብን እነሆ ሲሉ ይታያሉ። የውሃው ለስላሳ ምት ፣ የለሊቱ ዝምታ ፣ አንድ ላይ ተቀላቅለው ደግሞ በጆሮ ተንቆርቁሮ ነፍስ ላይ እንደሚዘልቅ ሙዚቃ ይሰማሉ። የሰው ልጅ ሆኖ ከዚህ በላይ ስጋውን የሚያሳርፍበት፣ ከድካም ገለል የሚልበት ፣ ልቡን የሚያረጋጋበት ፣ የአእምሮውን የፈጠራ አቅም የሚፈትሽበት ፣ አስተሳሰቡን የሚያበራበት ፣ ሕይዎቱን ከእንደገና ለማስተዋል የሚመርጠው የተሻለ ቦታ ሌላ የት ይኖራል?! ጨረቃ በባህሩ ላይ ተፈጥሯዊ ነፃነቷን ተጠቅማ በብርሃኗ ለመርከቡ መንገድ ሰርታ ኮምፓስ ስትሆን ፣ እንደ ተፈጥሮ የተዘጋጀ መንገድ ስትመስል ፣ መርከቡ በዚያ መንገድ ላይ እየተጓዘ መመልከት መቻል ና በእንዲህ አይነት ምሽት ውስጥ ራስን ማግኘት በህልም ውስጥ ያለ የህይዎት ቅኝት ውስጥ ያስመስላል። የተከፈተው ዐይን የሚያየውን ውብ ዓለምም ለመቀበል የውስጥን ዕምነት ይፈትሻል። ምክንያቱም እዚህ ስዓት ይቆማል ሐሳብም በተፈጥሮ እየፀዳ አእምሮም እንደሚያየው አረንጓድ የተራራ ላይ ኩታ መለምለም እያማረው ከተፈጥሮ ጋር በጥልቅ እየተገናኘ ወደፊቱን ከትላንት በተላቀቀ ንፁህ ማንነት እየፈጠረ አምላኩን ከልብ በመነጨ ንፁህ ፍቅር እያመሰገነ ስለሚያኖር። አምባዬ ጌታነህ ✍️ መስከረም 6/2018 ዓ.ም Vietnam🇻🇳 Halongbay ለዚህ ፔጅ አዲስ የሆናችሁ ፔጄን Subscribe አድርጉና ድርሰቶቼ ይድረሳችሁ። ከላይ ያለውን የጉዞ ማስታዎሻስ ከ 10 ስንት ነጥብ ትሰጡታላችሁ? እንኳን ✍በአምባዬ ጌታነህ @malefia @malefia @malefia Join🔗 & Share➡️📇 ስለጉዞው ማስታዎሻ ያላችሁን ከ 10 ነጥብ 📨 @Rich_poet በዚህ ዩዘርኔም አስቀምጡልኝ
0