fa
Feedback
ዉሉደ ብርሃን ሚዲያ

ዉሉደ ብርሃን ሚዲያ

رفتن به کانال در Telegram

ይህ የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ፤ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ገፅ ነው ። በዚህ ገፅ ፦ ● መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ መልዕክቶች ፣ ምክሮች ● መዝሙሮች ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ● ወቅታዊ የቤተክርስቲያን እና የሰ/ት/ቤት ጉዳዮች ● የሰ/ት/ቤት መልዕክቶች ፣ ማስታወቂያዎች ይቀርቡበታል። ዉሉደ ብርሃን ሚዲያ

نمایش بیشتر
1 235
مشترکین
+324 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-230 روز
آرشیو پست ها
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸 ከፎቶ ማህደር የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በደብራችን በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን። መስከረም 16/2019 ዓ.ም
+9
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸 ከፎቶ ማህደር የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በደብራችን በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን። መስከረም 16/2019 ዓ.ም

..:+:.. "የክርስቶስ መስቀል ታላቅ በረከትንና ድኅነትን እንድናገኝ ምክንያት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡ የክርስቶስ መስቀል ስናስበው ሐዘንና ምሬት ነው ነገር ግን እውነታው ደስታና ሐሴትን የሚሞ
+1
..:+:.. "የክርስቶስ መስቀል ታላቅ በረከትንና ድኅነትን እንድናገኝ ምክንያት እንደ ሆነ እናስተውላለን፡፡ የክርስቶስ መስቀል ስናስበው ሐዘንና ምሬት ነው ነገር ግን እውነታው ደስታና ሐሴትን የሚሞላ ነው፡፡ መስቀል ለቤተ-ክርስቲያን ድኅነት ነው መስቀል ተስፋ ለሚያደርጉት መመኪያ ነው መስቀል የእግዚአብሔር ጠላቶች የነበሩት የታረቁበትና ኃጢአን ወደ ክርስቶስ የቀረቡበት ነው፡፡ በመስቀል ከጠላትነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ተሸጋግረናል በመስቀል ከዲያብሎስ ቀንበር ወጥተናል ከሞት ወደ ሕይወት መጥተናል፡፡ ስለ መስቀል የማንሰብክ ከሆነ አሁንም በሞትና በፍዳ እንደ ተያዝን ነው ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 🎤#ዉሉደ_ብርሃን_ሚድያን_ለመቀላቀል➠ YouTube https://www.youtube.com/@WuludeBirhan7 Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl     Telegram https://t.me/weludebirhane Tiktok https://www.tiktok.com/@weludebirhan1?_t=ZM-8t8Bq1Nt0vV&_r=1 ዌብሳይታችንን https://wuludebrihan.org.et Phone +251907777037 🎞 ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe  እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ማድረግ እንዳይረሳ

የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ተኛ ለሐዋርያዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ። በሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ
+7
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ተኛ ለሐዋርያዊ ጉብኝት  አዲስ አበባ ገቡ። በሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ የተመራው ልዑክ ለሐዋርያዊ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን  በመንበረ  ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በአለም ቅርስነት የተመዘገበውን የመስቀል ደመራ በዓልን በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በጋራ  እንደሚባርኩ  እና መስከረም 17 በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው  ሥርአተ ቅዳሴውን እንደሚመሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። 📷 EOTC Broadcasting Service Agency https://t.me/weludebirhane

የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ተኛ ለሐዋርያዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ። በሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ
+7
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ተኛ ለሐዋርያዊ ጉብኝት  አዲስ አበባ ገቡ። በሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ የተመራው ልዑክ ለሐዋርያዊ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን  በመንበረ  ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። ቅዱስነታቸው በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በአለም ቅርስነት የተመዘገበውን የመስቀል ደመራ በዓልን በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በጋራ  እንደሚባርኩ  እና መስከረም 17 በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው  ሥርአተ ቅዳሴውን እንደሚመሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። 📷 EOTC Broadcasting Service Agency

"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ መስከረ
+2
"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በእንጦጦ ሐመረኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ከሰንበት ት/ቤት አገልጋይ  እህታችን ሰናይት አሻግሬ ጋር የጋብቻ ሥነ ሥርዓትክን  የፈጸምከው  መልካሙ ያሬድ እንኳን ደስ ያለህ እንኳን ደስ ያላችሁ ። የአብርሃምንና የሣራን ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ ሥላሴ አንድነታችሁን  ይባርክ ኪዳነምህረት በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ እያለች ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት መልካም የትዳር ሕይወት ትመኝላችኃለች። " ጋብቻ ንጹሕ ነው የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል "                           መጽሐፈ ዲድስቅልያ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ መስከረ
+1
"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ መስከረም 3/2019 ዓ.ም በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከሰንበት ት/ቤት አገልጋይ  እህታችን ሜሮን ሙሉጌታ  ጋር የጋብቻ ሥነ ሥርዓትክን  የፈጸምከው  እዮብ መስፍን እንኳን ደስ ያለህ እንኳን ደስ ያላችሁ ። የአብርሃምንና የሣራን ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ አንድነታችሁን  ይባርክ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ እያለች ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት መልካም የትዳር ሕይወት ትመኝላችኃለች። " ጋብቻ ንጹሕ ነው የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል "                           መጽሐፈ ዲድስቅልያ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

የዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ የዉሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤት ልዩ የአጋፔ የፍቅር መዓድ መርሃ ግብር በዛሬው እለት ተካሄደ ። መስከረም 2, 2019 ዓ.ም ዉሉደ_ብርሃን_ሚድያን_ለመቀላቀል➠ YouT
+7
የዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ የዉሉደ ብርሀን ሰ/ት/ቤት  ልዩ የአጋፔ የፍቅር መዓድ መርሃ ግብር በዛሬው እለት  ተካሄደ ። መስከረም 2, 2019 ዓ.ም ዉሉደ_ብርሃን_ሚድያን_ለመቀላቀል➠ YouTube https://www.youtube.com/@WuludeBirhan7 Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl     Telegram https://t.me/weludebirhane Tiktok https://www.tiktok.com/@weludebirhan1?_t=ZM-8t8Bq1Nt0vV&_r=1 ዌብሳይታችንን https://wuludebrihan.org.et Phone +251907777037 🎞 ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe  እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ማድረግ እንዳይረሳ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፤ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣ በየዓመቱ የይቅርታ እጁን እየዘረጋ የሚመግበን እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ወደ ዘመነ ሉቃስ ሁለት ሺሕ ዓሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወይእዜኒ ነስሑ ወተጠመቁ፤ ወይደመሰስ ለክሙ ኃጢኣትክሙ፤ ወይመጽእ ለክሙ መዋዕለ ሣህል እምቅድመ ገጹ ለእግዚአብሔር፤ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላችሁ፣ ኃጢአታችሁም እንዲደመሰስ አሁንም ንስሐ ግቡ ተመለሱም” (የሐ.ሥራ ፫፡፲፱) የሰው ልጅ በስሑት ስራውና አእምሮው ምክንያት የኃጢአት ማዕበል በሚያናውጠው ባሕረ ዓለም እንደሚኖር ይታወቃል፤ የዓለሙ ባሕር በማዕበሉ በተናጠ ቁጥር በመርከቡ ተሳፍረው የሚጓዙ ሁሉ ጭንቀት ላይ መውደቃቸው የማይቀር ነው፤ በዚህ ጊዜ የሚያጽናና የቊርጥ ቀን ረዳትና ኃይል ያስፈልጋቸዋል፤ ሆኖም ረዳት በፍጥነት እንዲደርስላቸው መጮኽና መጣራት ከነሱ ያስፈልጋል፤ የምንኖርባት ዓለም ወይም ፕላኔት የክፋትና የጭካኔ ማዕበል በእጅጉ እየበረታባት መጥቶአል፤ ዓለማችን በስጋትና በፍርሓት፣ በራስ ወዳድነትና ባለመተማመን ተከባለች፣ በመሆኑም ዓለማችን ከምን ጊዜውም  በላይ የመጽናናት ዘመን እንዲመጣላት ትሻለች፤ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ የሰጠ አምላክ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፤ ይሁንና እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልጋቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ በማያሻማ ሁኔታ አሳውቆአል፤ ከእነሱም መካከል በእውነተኛው መንፈስ ንስሐ መግባት፤ መጸጸትና መመለስ ናቸው፤ የዓለምን ሕዝብ በወሳኝነት ማጽናናት የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እኛ ራሳችንን በራሳችን ለማጽናናት እንኳ በቂና ዘላቂ ዓቅም የሌለን ውሱኖች ነን፤ ይህንን እውነት ዓውቀን የእርሱን ርዳታ እንድንሻ እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ይህንንም ከልብ በመጸጸትና ከቀደመው ስሑት ተግባራችን በመመለስ በፊቱ ተንበርክከን መታዘዛችንን በተጨባጭ እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት! እግዚአብሔር ከታላቅ ቸርነቱ የተነሣ የመታደስ ዘመንን በየዓመቱ ከመስጠት አልተቈጠበም፤ እንደ ሁሉጊዜ አሁንም አዲሱን ዘመን ባርኮ ሰጥቶናል፤ ሆኖም አዲሱ ዘመን የመጽናናት ዓመት እንዲሆንልን የእኛ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው መዘንጋት የለብንም፤ ከሁሉ በፊት ያለፈውን ዓመት እንደ ግልም፣ እንደ ማኅበረ ሰብም፣ እንደ ሃገርም፤ እንደ ሃይማኖትም በኅሊናችን ልናስበውና ልንገመግመው ይገባል፤ ያለፈውን ዓመት በንጹህ ኅሊናችን በጥልቀት ስንገመግመው፤ የመጣንበትና ያለፍንበት ስለሆነ ኮለል ብሎ በፊታችን ይታያል፤ ጥቅሙም ሆነ ጉዳቱ በሙሉ ከኛ የራቀ ስለማይሆን ዳኝነት ለመስጠትና ውሳኔ ለመወሰን አንቸገርም፤ በመሆኑም ለፈጸምነው ስሕተት ይቅርታን ከመጠየቅ ባሻገር ድጋሚ ላንደግመው መወሰንና ለተግባራዊነቱ በጽናት መቆም አለብን፤ እኛ በዚህ ደረጃ ከቀደመው ስሕተታችን ተጸጽተን ንስሐ ከገባን እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገውን አግኝቶአል ማለት ነው፤ በመካከላችንም ትክክለኛ መግባባት ተፈጥሮአል ማለት ነው፤ በዚህ ጊዜ እሱም ዘላቂ የሆነ የመጽናናት ዘመን ለኛ ይሰጣል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት! በዓለሙ እንዳለው ሁሉ እኛም ወዲያና ወዲህ ከሚያወዛውዝ ፈተና አላመለጥንም ያለፈውን ዓመት በንጹሁ አእምሮአችን ስንመዝነው፤ ጥሩ የሚባል አልነበረም፤ በየአካባቢው ግጭቶች የቀጠሉበት፣ የሰው ደም የፈሰሰበት፣ ዕገታዎች የተፈጸሙበት፣ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉበት፣ ምእመናን የተገደሉበትና የተፈናቀሉበት፣ ስጋት ያየለበት፣ ኑሮም የተወደደበት፣ ሌላም ሌላም ለሰው ልጅ የማይበጁ ነገሮች የተከሠቱበት ዓመት አሳልፈናል፤ ታዲያ አዲሱን ዘመን ስንቀበል እነዚህን ሁሉ እንዳሉ ይዘናቸው እንቀጥል ይሆን? ይህስ ከሆነ ‹‹እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሳችሁ›› መባባሉ ትርጉም ይኖረው ይሆን? እንዲህስ ልንሆን ፈጽሞ አይገባም፤ ይልቁንም ባለፈው ዓመት የሆኑትን ሁሉ ላንደግማቸው ሁላችንም እንወስን፤ እነሱንም ማስቀረት እንችላለን፤ ምክንያቱም ችግሮቻችን በሙሉ ሰው ሰራሽ እንጂ የተፈጥሮ አይደሉም፤ ሰው ሰራሽ ችግሮች ደግሞ በሰው እንደመጡ ሁሉ በሰው ሊቀሩ የሚችሉ ናቸውና እናስቀራቸው፤ ጦርነቱን፣ ዕገታውን፣ ጥላቻውን፣ ፉክክሩን፣ እልከኝነቱን፣ ጭካኔውን ራስ ወዳድነቱን ግድያውን፣ አብያተ ሃይማኖት ማቃጠሉንና ማፍረሱን እኛው እንዳመጣነው እኛው ማስቀረት እንችላለን፤ ስንተወው እኮ ይቀራል፡፡ ስለሆነም ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን እንዳለች የጋራ ዕድልና ሃብት አድርጋችሁ ተቀበሉ፤ ሌላውን ረጅም ጊዜ ሰጥታችሁም ቢሆን በውይይትና በመግባባት እየፈታችሁ በአንድነት ቀጥሉ፤ በይቅርታመንፈስ በአንድነት ተቃቅፎ ከመቀጠል ውጭ ሌላ የተሻለ ዕድል እንደሌለ በውል ተገንዘቡ፤ ለዚህ ሁላችሁም የበኩላችሁን ልባዊ ጥረት ከማድረግ አትቈጠቡ ብለን ከልብ እንመክራለን፡፡ በመጨረሻም፤ ለሁሉም መድኃኒቱ ቀና አእምሮ ነውና በአዲሱ ዓመት እግዚአብሔር ቅንና በጎ አሳቢ አእምሮ እንዲሰጠን በሱም ያሉብንን ጉድለቶች አርመንና አስተካክለን ሰላም የሰፈነበትን የመጽናናት ዘመን ማየት እንችል ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችንን እንለምን፤ እኛም በንስሐ እንመለስ እያልን በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ በማለት አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን ፡፡     እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዘመን ያድርግልን፡፡ እግዚአብሔር ኣምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ኣሜን!! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ መስከረም ፩ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

እነሆ ሁለት ቀናት ብቻ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እነሆ ሁለት ቀናት ብቻ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 #መስከረም 1 የዘመን መለወጫ #ዘመን መለወጫ ምንድ ነው.? #እንቁጣጣሽ ምንድነው..? #አዲስ አመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል...? ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡           #ዘመን_መለወጫ ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 366 ቀናት ይሆናል፡፡ “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ /ሄኖክ.26፥44/ “ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ” /ሰ.ኤር.5፥21/ከቆየ እንዲል፡፡ በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት  በኋላ ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ /ኩፋሌ 7፥1/ “በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች” እንዲል፡፡                 #ዕንቁጣጣሽ ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት አንደኛ “ዕንቁ - ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውንአህጉራትን መፈንዳት ያመለክታል፡፡ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ  በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ ሦስተኛው /1ነገ.10፥1-10/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /መንሻ አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ  በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “እንቁ ለጣትሽወርኀ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም  መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡        #ቅዱስ_ዮሐንስ ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ /ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3/ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡ በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኀጥያት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡               መልካም አዲስ አመት ምንጭ :- ከተለያዩ መጽሐፍት 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼      🌻🌻🌻አዲሱ ዓመት 🌻🌻🌻 (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው) 🌼ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ 🌼የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ በትግሃ ሌሊት፣ በቀዊም፣ በጾም በጸሎት እንድንበረታ ስንቅ ይኾነናል፡፡ በስካር፣ በዘፈን፣ በኀዘን የምንጀምረው ከኾነ ግን ዓመቱ ሙሉ እንዲህ የተጐሳቈለ ዓመትን እናሳልፋለን፡፡ ሕይወታችንን በከንቱ እንገፋለን፡፡ ዲያብሎስም ይህን ጥንቅቅ አድረጐ ስለሚያውቅ ዓመቱን በገቢረ ኀጢአት እንድንጀምረው እየቀሰቀሰ ነው፡፡ ፈቃዳችንን አጥፍቶ፣ ዓይነ ልቡናችንን አሳውሮ በዘፈን፣ በስካር፣ በዋይታ እንድንጀምረው በተለያየ መንገድ እየለፈፈ ነው፡፡ 🌼ሰነፍ ሰው “ቀኑ ክፉ ወይም መልካም የሚኾነው በእኔ ምክንያት አይደለም” ብሎ ያምናል፡፡ እንዲህ በማመኑም ክፉ ነው ብሎ በሚያስበው ቀን ገቢረ ጽድቅ መሥራት እንደሚቻል አያስብም፡፡ ቢያደርግም ትርጕም እንደሌለው አድርጐ ይቈጥሯል፡፡ የጽድቅ ሥራ ለመሥራት በተመቻቸለት ቀንም ልል ዘሊል ከመኾኑ የተነሣ ምግባር ትሩፋት ለመሥራት አይሽቀዳደምም፡፡ ስንፍናው ምን ዓይነት ጉዳት እንደሚያመጣበት አይረዳም፡፡ ድኅነቱን ሳይፈጽም ዕድሜውን ኹሉ በከንቱ ይገፋል፡፡ እንዲህ ያለ የሥጋም የነፍስም ጕዳት እንደሚያገኘው ዲያብሎስ ዓይነ ልቡናውን ስለሚያሳውርበት ከአጋንንት ወጥመድ ለመሸሽ ዓቅምን ያጣል፡፡ ዲያብሎስም ዕለት ዕለት ይህን እንዳንገነዘብ በተለያየ ማጥመጃ መንገዶች እኛን ለመጣል ይሯሯጣል፡፡ አንዱ መንገድም ስለ ክርስትና ሕይወታችን ግድ እንዳይኖረን ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ክርስቲያናዊ ተፈጥሮአችንን ያሳጣናል፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ በገቢር እንድንሰድብ ያደርገናል፡፡ ነፍሳችንን በቆሸሸ ስፍራ ተወሽቃ እንድትቀር ያደርጋታል፡፡ 🌼የምወዳችሁ ልጆቼ! እኛ ግን ይህን ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ በዓለም ላይ ከኀጢአት በቀር ክፉ ነገር እንደሌለ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ ከምግባር ከትሩፋት በቀርም መልካም ነገር እንደሌለ ልናውቅ ልንረዳ ይገባናል፡፡ በዚህም ዘወትር እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተን ልንኖር እንዲገባን ማወቅ መረዳት ይገባናል፡፡ 🌼መጠጥ ደስታን አያመጣም፤ ደስታን የሚያመጣው ጸሎት ነው፡፡ ደስታን የምናገነኘው ቃለ እግዚአብሔርን ከመስማት እንጂ ከስካር አይደለም፡፡ ስካር የነፍስ መታወክን ያመጣል፤ ቃሉን መስማት ግን ተመስጦን ያመጣል፡፡ ስካር ሁካታን ያመጣል፤ ቃሉን መስማት ግን ሁካታን ያርቃል፡፡ ስካር ዓይነ ልቡና እንዲጨልም ያደርጋል፤ ቃለ እግዚአብሔር ግን የጨለመው ዓይነ ልቡናችን ብሩህ እንዲኾን ያደርጋል፡፡ ስካር የኀጢአት ጓዝ ይዞ ይመጣል፤ ቃለ እግዚአብሔር ግን አዲስ የሚመጡትን ብቻ ሳይኾን የነበሩትንም ያስወግዳል፡፡ 🌼ልጆቼ! የዚህን ዓለም ደስታ ንቆ ሰማያዊ ደስታን እንደ መሻት ያለ ጥበብ ምንም የለም ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡ ይህን ገንዘብ የምናደርግ ከኾነ፣ ለሰማያዊ ሕይታችን ቅድሚያን የምንሰጥ ከኾነ የዚህ ዓለም ዝባዝንኬ ቢቀርም አይከፋንም፡፡ አንድ ሰው ባለጸጋ ስለኾነ ቅናት አይይዘንም፡፡ ምንም ምድራዊ ሀብት ባይኖረንም ድኾች እንደኾንን አናስብም፡፡ ባለ ጸጋውን ክርስቶስ የያዘ ሰውስ እንዴት ድኻ ይባላል? በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይኾን በየዕለቱ በዓል ማድረግ ማለትም ይኸው ነው፡፡ 🌼እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ሆይ! አንድ ክርስቲያን በዓልን ሲያከብር ሳምንትን ወይም ወርን ወይም ዓመትን ጠብቆ መኾን የለበትም፡፡ ከክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ጋር እንደሚስማማ አድርጐ ዕለት ዕለት በዓል ሊያደርግ ይገቧል እንጂ፡፡ ከክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ጋር የሚስማማ በዓል ማለትስ ምን ማለት ነው? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ምን እንደሚለን አብረን እናድምጠው፡- “በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም” (1ኛ ቆሮ.5፡8)፡፡ ንጽሐ ልቡናን ገንዘብ ያደረገ ሰው ዕለት ዕለት በዓልን ያከብራል፡፡ ተስፋ መንግሥተ ሰማያት የተጠበቀለት ነው፡፡ ከሰማያዊው ማዕድና መጠጥ ተካፍሎ ሐሴት ያደርጋል፡፡ በዚህ ምድር ላይ የሚደረጉ ጊዜያዊ ክንውኖች ስለቀረበት የኾነ ነገር እንደቀረበት አያስብም፤ እርሱ ያገኘው ከዚህ በእጅጉ የሚልቅ ነውና፡፡ ነፍሱን ከሚያቆሽሹ ገቢረ ኀጢአቶች ራሱን ይጠብቃል፡፡ 🌼በገቢረ ኀጢአት ተሰማርተን ሳለ ሺሕ ጊዜ በዓላትን ብናከብር ግን እንዳከበርን ልንቈጥረው አይገባንም፡፡ ያከበርነው የበዓል ቀን (በዓል ማለት ደስታ ማለት ነው) ሳይኾን የኀዘን ቀን ነውና፡፡ ነፍሴ በኀጢአት ቀንበር ተይዛ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሳለች የደስታን ቀን ባከብር ለእኔ ምን ጥቅም ያመጣልኛል? 🌼እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” 🌼ተወዳጆች ሆይ! አዲስ ዓመት ሲመጣ እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ ልናስብባቸው ይገባናል፡፡ ይህን እያደረግንም ስለ ቀጣዩ ዓመት እናስብ፡፡ ይህን የምናደርግ ከኾነ “ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፤ ዓመቶቻቸውም በችኰላ” አይባልብንም (መዝ.78፡3)፡፡ ዕለት ዕለት በዓልን እናድርግ ብዬ የገለጥኩላችሁም ይኸው ነው፡፡ የእኛ በዓል ዘወትር መኾን ይገባዋል፡፡ የክርስቲያኖች በዓል በዓመታትና በቀናት ብቻ መወሰን የለበትም፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በሳምንት፣ በወር፣ በዓመት የሚከበሩ በዓላት እንዲኖሩ ማድረጓ ዘወትር ከዚሁ ልንርቅ እንደማይገባ ማሳሰቧ እንጂ ሌላ አይደለምና፡፡ ይህን በዓል በየዕለቱ ማድረግም ለኹሉም ይቻላል፤ ለድኻውም ለባለጸጋውም ይቻላል፡፡ በዓልን ለማድረግ (የጽድቅ ሥራን ሠርቶ ሐሴት ለማድረግ ያብቃን።) 🌼ወስብሀት ለእግዚአብሔር    ይቆየን🌼

እነሆ ሁለት ቀናት ብቻ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
እነሆ ሁለት ቀናት ብቻ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌼🌼🌼🌼አጋፔ🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🗓እሁድ መስከረም 2, 2019 ዓ.ም ⏰ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ⛪️በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ✅ሁላችንም ተጋብዘናል መቅ
🌼🌼🌼🌼አጋፔ🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🗓እሁድ መስከረም 2, 2019 ዓ.ም ⏰ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ⛪️በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ✅ሁላችንም ተጋብዘናል መቅረት ሳይሆን ማርፈድም ያስቆጫል!!!

#​​ፈታሔ ማሕፀን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ቅዱሳን መላእክት ምእመናን ለመርዳት ለማገልገል ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት አይደሉምን? ( ዕብ ፩÷፲፬) ብሏ
#​​ፈታሔ ማሕፀን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ " የዘለዓለም ሕይወትን እንዲወርሱ ቅዱሳን መላእክት ምእመናን ለመርዳት ለማገልገል ከእግዚአብሔር የሚላኩ ረቂቃን ፍጥረታት አይደሉምን? ( ዕብ ፩÷፲፬) ብሏል። ቅዱስ ዮሐንስም "የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ"( ራእዩ ለዮሐንስ ፰÷፬)  በማለት ተናግሯል። ቅዱሳን መላእክት ያለማያቋረጥ ለፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው።   በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ለተልእኮ ይፋጠናሉ። የሰውን ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፤ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ምሕረት ወደ ሰው አድርሰው በእምነት ያጸናሉ። "በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው" (ራእ. ፰÷፪) የሚለው የሚያስረዳን ለተልእኮ መፋጠናቸውን ነው። ሄኖክም “በሰው ሰውነት ላይ የተሾሙ ከከበሩ ፯ቱ ሊቃነ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አንዱ ነው”  (ሄኖ.፮÷፩-፵፪) ብሏል። የሰዎችን ልመና ወደ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና በረከት ወደ ሰው የሚወርድባት ዕለት"ነው። † ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

photo content
+2

#ጳጕሜን_3 #ሩፋኤል_ሊቀ_መላእክት_ወመልከጼዴቅ_ካህን ‹‹#ርኅወተ_ሰማይ_/ሰማይ የሚከፍትባት እለት››፤:: #እንኳን_ለቅዱስ_ሩፋኤል_በዓለ_ሢመትና_ለቅዳሴ_ቤቱ_በ4ኛው_መቶ_ክ_ዘመን_በቅዱስ_ቴዎፍሎስ_ዘእስክንድርያ_አማካኝነት_በሚደንቅ_ተዓምራት_በአሣ_አንበሪ_ጀርባ_ደሴት_ላይ_ለታነጸው_ቅዳሴ_ቤት #እንዲሁም_ለካህኑ_መልከጼዴቅ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን_፡፡ # ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው። ሣልሳይ ሊቀ መላእክት ነው። (“ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ” እናዳለ /ጦቢ ፲፪፥፲፭/፡፡ ✤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3):: ✤ ለሄኖክ ወልደ ያሬድ 6 ዓመት በእግረ ገነት ወድቆ ሳለ ኅበዓቱን ክሡታቱን አሳይቶታል። መ.ሄኖክ 8፡5 ቅዱስ ሩፋኤል ሰማያውያን መዛግብትን በእጁ የሚጠበቁ በመሆናቸው "ዐቃቤ ኖኅቱ ለአምላክ" ይባላል፡፡ እግዘአብሔር እንዳዘዘው የሚዘጋቸው የሚከፍታችው እርሱ ነው፡፡ ✤✤✤ ቅዱስ ሩፋኤል ሰውን በመርዳት ሲኖር የነበረውን የጦቢትን ዓይን ያበራና፤ ሣራ ወለተ ራጕኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው አስማንድዮስ ጋኔን (ያገባችውን ባል የሚገድል) አላቅቆ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት ያደረገ በመኾኑ “ፈታሔ ማሕፀን (መወልድ/አዋላጅ፥ ምጥን የሚያቀል) ይባላል:: ” ና ‹‹መልአከ ከብካብ›› ተብሏል (ዛሬም ድረስ የእናቶች ሐኪም ነው)፤ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት ቤቱንም በበረከት ሞልቶታል፤ በዚህም ፈዋሴ ቊስል (ድውያን)፥ ዐቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ) ተብሎ ይጠራል፡፡ #ጦቢት ልጁን ወደ ሜዶን ክፍል ወደ ምትሆነውና ራጌስ ወደ ምትባለው ሀገር ወደ ገባኤል ቤት ሲልከው መንገዱን የመራው አዛርያስ /ቅዱስ ሩፋኤል/ ነው፤ በዚህም ቅዱስ ሩፋኤል ‹መራኄ ፍኖት› /መንገድ መሪ/ ይባላል፡፡ #ቅዱስ ሩፋኤል በራማ ሰማይ ሁለተኛ ክፍል ላይ የሰፈሩትንና መናብርት በመባል የሚጠሩትን 10ሩን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ነው፤ በዚህም ‹‹ሊቀ መናብርት›› ተብሎ ይጠራል፤ መናብርት የሚባሉት መላእክት ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ፥ የእሳት ጦር ይዘው፤ ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ፤ ከእነዚኽ 10ር ነገደ መላእክት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡ በኢትዮጵያ በቅዱስ #ሩፋኤል ስም ከተሰየሙት ቤተ ክርስቲያን መካከል፤ 1,ጎንደር ደብረ ሣሕል ቅዱስ ሩፋኤል  ወአቡነ ሐራ ድንግል  ወቅዱስ ያሬድ  ቤተ ክርስቲያን (ጐንደር)፤ በአፄ በካፋ የተመሠረተና ዚቅ እንደተጀመረባቸው  ከሚነገርላቸው ቦታዎች አንዱና ታላቁ ደብር፡፡   2,አዲስ አበባ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል፤ በ1878 ዓ.ም. በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የተመሠረተና ባላ አንድ ጣሪያ   ያለው ቀደምት የአዲስ አበባ ደብር፡፡ 3,ደብረ ዘይት (አየር ኃይል) ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ. 4,ወላይታ ዳሞት ፑላስ ቅዱስ ሩፋኤል ቤ.ክ. † ወስብሐት ለእግዚአብሔር †