fa
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

رفتن به کانال در Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

نمایش بیشتر
4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
#በደላችንን_ይቅር_በለን https://telegram.me/EOTC2921 1. እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን እንደሚወድ አምላካችን ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ባይወድ ኖሮ ይቅርታን እንድንጠይቅ አይነግረንም ነበር፡፡ አዎ እኛ ከተመለስን ምንም ያህል በደለኛ ብንሆን ይቅር ሊለን፤ ምንም ያህል ብንቆሽሸ ሊያድነን ዝግጁ ነው፡፡ እንዲህ እያለ ይጠራናል፤ «እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ»፡፡ ስለዚህ በዚሀ ጸሎትም ላይ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጠይቀው አስተማረን፤ ይቅር ይለን ዘንድ፡፡ 2. ይቅር ለመባል ምን ማድረግ እንዳለብን፤ ይቅር ሊለን ስለወደደም ይቅርታን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በዚሁ ቃል ነግሮናል፤ ማድረግ ያለብን ምንድን ነው? - ኀጢአታችንን ማወቅ፣ ማመን፣ ማስታወስ - የበደሉንን ይቅር ማለት - ይቅርታን መለመን #ኅጢአታችንን_ማወቅ /ማመን/ ጌታ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጸልይ ሲነግረን በመጀመሪያ ደረጃ በደለኛ እንደሆንን እያስታወስን /እንድናስታውስ እያደረገን/ ነው፡፡ ሁልጊዜም በማሰብ፣ በመናገርና በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የሆነውን ልባችንን /ኅሊናችንን/ እና ሰውነታችንን እናቆሽሻለን፤ መድኃኔዓለም ክርስቶሰ የሞተለትን ማንነታችንን እናጎድፋለን፡፡ ይህም የሰው ልጆች በቅድስና እርሱን መስለን እንድንኖር በኋላም የተዘጋጀልንን የዘለዓለም መንግሥት እንድወርስ ብቻ ፈቃዱ የሆነውን እግዚአብሔርን ያሳዝናል፤ በአርአያውና በአምሳሉ ለክብር የፈጠረው ሰውነታችን መጉደፍ ያስቆጣዋል፤ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ እርሱ ኀጢአት አይስማማውምና፡፡ እንግዲህ ይቅር ለመባል በመጀመሪያ እንዲህ ኀጢአት እየሰራን መሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልገናል፡፡ ወደዚህ ዕውቀት ለመድረስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መማር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ስህተት የሚታወቀው ያለውን ሁኔታ /ድርጊታችንን ንግግራችንን፣ ሀሳባችንን.. / መሆን ከነበረበት /ከትክክለኛው/ ጋር በማነጻጸር በሚዛን ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የማነጻጻሪያ ሚዛኖቻችን ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ሕግጋትና ትዕዛዛት ናቸው፡፡ እነዚህን ስናውቅ ጉድለቶቻችን፣ ድካሞቻችን ፍንተው ብሎ ይታዩናል፡፡ አሊያ ግን እየበደለን ያልበደልን ሊመስለን ይችላል፡፡ https://telegram.me/EOTC2921 #የበደሉንን_ይቅር_ማለት ጌታ በዚህ ጸሎት ይቅርታ እንድንጠይቀው በማስተማር ይቅር ሊለን እንደሚወድ ዝግጁም እንደሆነ ቢነግረንም ይቅር ለመባል ግን እኛ የበደሉንን ይቅር ማለታችን የግድ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦልናል፤ «በደላችንን ይቅር በለን» ከማለታችን በፊት «እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል» እንድንል ያዘዘን እኛ ይቅርታ የምናገኘው ሌሎችን ይቅር ስንል ብቻ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ጌታችን ይህንን ጉዳይ በሌሎች የተለያዩ ቦታዎችም በተደጋጋሚ አስተምሮናል፤ በዚሁ በተራራው ስብከት ይኸው ጉዳይ ሁለት ጊዜ በጌታችን ትምህርት ተሰጥቶበታል፡፡ «እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡ » /ማቴ.7-2/ በሌላ ቦታም እንዲህ ሲል ይህንኑ ጉዳይ በምሳሌ አስተምሯል፤ መንግስተ ሰማያት ባሮቹን ለመቆጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች መቆጣጠርም በጀመረ ጊዜ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ባለ እዳው ሰው የሚከፍለው ስላጣ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ንጉሡ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው፡፡ የዚያም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፡፡ ይህ ባርያ ግን ወጥቶ ከባልጀሮቹ /እንደርሱ ባርያ ከሆኑት/ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው፡፡ ባልንጀራው ባርያም ወድቆ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤ ብሎ ለመነው፡፡ እርሱ ግን ሊተወው አልወደደም፡፡ ዕዳውን እስኪከፍልም በወኀኒ አኖረው፡፡ ይህንን ያዩ ሰዎችም አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ሁሉ ለንጉሡ ተናገሩ፡፡ «ከዚህ ወዲያ ንጉሡ ጠርቶ፣ አንተ ክፉ ባርያ ስለለመንከኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን የሆነውን ባርያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን አለው፡፡ ጌታውም ተቆጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚያሰቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡» ጌታ ይህንን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ የምሳሌውን ትርጉም እንዲህ ሲል ገልጦታል፤ ብሏል፤ «ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርገባችኋል»/ማቴ.18. 23- 35/ በአጠቃላይ ይቅር ለመባል ይቅር ማለት የግድ ነው፡፡ በእኛ ላይ የሚፈረድብን ፍርድ በእኛው እጅ ላይ ነው፡፡ ጌታችን በእነዚህ ትምህርቶች እንዲህ እያለን ነው «እኔ እናንተ ላይ የምፈርደው እናንተ በራሳችሁ ላይ በፈረዳችሁበት መንገድ /መልኩ ነው/»፡፡ #ይቅርታ_መጠየቅ ኀጢአታችንን ካወቀንና ካመንን፣ የበደሉንንም ከልብ ይቅር ካልን በኋላ ይቅር እንድንባል መጠየቅ /መለመን/ አለብን ፡፡ «ይቅር በለን» ብላችሁ ጸልዩ ብሎ በማስተማሩ ይህንን እንረዳለን፡፡ ወደ ንስሐ አባት መሄድና ኀጢአትን ተናዞ ቀኖና መቀበለ የሚገባወሙ መጀመሪያ በዚህ መልኩ ስለ ኀጢአት ካለቀሱ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም ቀኖና ተቀብለን ስንፈጽምም ሆነ ከዚያ በኋላ ይኸው ስለ ኀጢአት ይቅርታ መጠየቁ ይቀጥላል፡፡ በእርግጥም ይቅርታ የምንጠይቀው አዳዲስ ስለሰራናቸውና ንስሐ ገና ስላልገባንባቸው ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ስለገባንባቸው ስለ ቀደሙት በደሎቻችንም ጭምር ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ዳዊት «የቀደመ በደላችንን አታስብብን ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን» /መዝ.78-8/ እያልን ሰለ ቀድሙ በደሎቻችንንም እያሰብን በሕይወታችን ዘመን ሁሉ መጠየቅ አለብን፡፡ ይቅርታ የምንጠይቀው ስለምናውቃቸው /ስለምናስተውላቸው/ ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ስለማናስተውላቸውም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ «ይቅር በለን» ስንል እኛ ካስተዋልናቸው መንገዶች ውጪ በብዙ መልኩ እርሱን እንደምንበድል አስበን ተማጽኗችን ስለነዚህም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ለጸሎት ከመቆማችንና የጌታን ጸሎት ከመጸለያችን በፊት የበደሉንን ይቅር እንዳልን እርግጠኛ መሆን አለብን እኛ የበደሉንን ይቅር እንዳልን ልንል ነውና፡፡ «እኛንም በደላችንን ይቅር በለን» ስንልም ከላይ ያየናቸውን ነገሮች ሁሉ እያሰብን፤ ይቅር ሊለን የወደደ አምላካችንንም እያመሰገንን መሆን አለበት፡፡ በእውነት ይህንን ጸሎት የምንጸልየው በዚህ መልኩ ነውን? ካልሆነ ልምምዱን ዛሬውኑ እንጀምረው ፡፡ ይህንን ማድረግ እንችል ዘንደ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን፡፡ https://telegram.me/EOTC2921 ወስብሐት ለእግዚአብሔር

❖ የ 2012 ዓ.ም አጽዋማትና በዓላት ❖ ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ(ፍዳ) = 2012 + 5500 =7512 ❖ ወንጌላዊ፦ በዓመቱ የሚሾም ወንጌላዊ ማለት ነው፡፡ ዓመተ ዓለምን ለአራት አካፍለን የዓመቱን ወንጌላዊ እናገኛለን። = 7512 ÷ 4 = 1878 1878 ፦ መጠነ ራብዒት ይባላል 7512 - 4×1878 = 0 ቀሪው ' 1 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ ቀሪው ' 4 ' ወይም ' 0 ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል። ስለዚህ ቀሪው ' 0 ' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ዮሐንስ ስሆን ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይባላል። ❖ መባቻ= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት ÷7 = 7512 + 1878 ÷ 7 = 9390 ÷ 7 = 1341 ቀሪ 3 ቀሪው ' 0 ' ከሆነ ሰኞ ቀሪው ' 1' ከሆነ ማክሰኞ ቀሪው ' 2 ' ከሆነ ረቡዕ ቀሪው ' 3 ' ከሆነ ሐሙስ ቀሪው ' 4 ' ከሆነ ዓርብ ቀሪው ' 5 ' ከሆነ ቅዳሜ ቀሪው ' 6 ' ከሆነ እሁድ መባቻ ይሆናል። በመሆኑም ቀሪው ' 3 ' ስለሆነ ዘንድሮ መባቻ(ዘመን መለወጫ) ሐሙስ ይሆናል። ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ❖ መደብ = ዓመተ ዓለምን በ19 በመግደፍ እናገኛለን። = 7512 ÷ 19 = 395 ደርሶ 7 ይቀራል። ስለዚህ መደብ 7 ይሆናል ❖ ወንበር = ከመደብ አንድን ለዘመን በመተው ወንበርን እናገኛለን። ስለዚህ ወንበር 6 ይሆናል። ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ❖ አበቅቴ ፦ አበቅቴን ወንበርን በጥንተ አበቅቴ አባዝተን በ30 ገድፈን እናገኛለን። አበቅቴ = 6 ×11= 66 ÷ 30, ' 2' ደርሶ ቀሪው '6' ስሆን ዘንድሮ አበቅቴ ' 6 ' ይሆናል። ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ❖ መጥቅዕ ፦ ወንበርን በጥንተ መጥቅዕ አባዝተን ለ 30 አካፍለን እናገኛለን። መጥቅዕ = 6×19 = 114 ÷ 30 ቀሪው ' 24 ' ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ ' 24 ' ይሆናል። ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ✿መጥቅዕ፦ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ፤ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ይውላል፡፡ ❖ ፆሜ ነኔዌ = ፆሜ ነኔዌን መጥቅዕና የዕለቱን ተውሳክ በመደመር እናገኛለን፡፡ ዘንድሮ መጥቅዕ በመስከረም ሲውል መስከረም 24 በቅዳሜ ይውላል። የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው። ስለሆነም ፆሜ ነኔዌ 8 + 24 = 32 ስሆን በ30 ገድፈን ' 2' ይቀራል። ስለዚህ ዘንድሮ በየካቲት ' 2 ' ሰኞ ፆሜ ነኔዌ ይገባል። ✿ ሌሎችን አጽዋማት ተውሳኩን ከነኔዌ(መባጃ ሐመር) ጋር ደምረን ከ30 ከበለጠ ለ30 እያካፈልን እናገኛለን። ❖ ዓብይ ፆም = ተውሳኩ 14 ነው = 14 + ነኔዌ = 16, ስሆን ዘንድሮ በዘመነ ዮሐንስ ዓብይ ጾም በየካቲት 16 ሰኞ ይገባል፡፡ ❖ ደብረ ዘይት = ተውሳኩ 11 ነው = 11 + ነኔዌ = 13, ይሆናል፡፡ 13 ከ 30 ስለሚያንስና በየካቲት ስላለፍን በመጋቢት 13 እሁድ ደብረዘይት ይሆናል። ❖ ሆሣዕና = ተውሳኩ 2 ነው = 2+ነኔዌ = 4, ስሆን ከ30 ስለሚያንስና በመጋቢት ስላለፍን በሚያዝያ 4 እሁድ በዓለ ሆሣዕና ይውላል። ❖ ስቅለት = ተውሳኩ 7 =7 + ነኔዌ = 9, ስሆን በሚያዝያ 9 ዓርብ ስቅለት ይሆናል፡፡ ❖ ትንሣኤ = ተውሳኩ 9 ነው = 9 + ነኔዌ = 11, ስሆን ሚያዝያ 11 እሁድ በዓለ ትንሣኤ ይውላል። ❖ ርክበ ካህናት = ተውሳኩ 3 ነው = 3 + ነኔዌ = 5 , ስሆን በግንቦት 5 ረቡዕ ርክበ ካህናት ይሆናል። ❖ ዕርገት = ተውሳኩ 18 ነው = 18 + ነኔዌ = 20, ስሆን ግንቦት 20 ሐሙስ በዓለ ዕርገት ይሆናል። ❖ጰራቅሊጦስ = ተውሳኩ 28 ነው = 28 + ነኔዌ = 30 ስለዚህ ግንቦት 30 እሁድ በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል። ❖ ፆመ ሐዋርያት = ተውሳኩ 29 ነው = 29 + ነኔዌ = 31, በ30 ገድፍን ቀሪው 1 ስሆን ሰኔ 1 ሰኞ የሐዋርያት ፆም ይገባል። ❖ ፆመ ድህነት = ተውሳኩ 1 ነው = 1 + ነኔዌ = 3, በመሆኑም ጾመ ድህነት(የረቡዕና ዓርብ ፆም) ሰኔ 3 ረቡዕ ይገባል።

✍✞በመስከረም 11 ባህርዳር ከተማ የተዋህዶ ሰልፍ ሁሉም ከየአጥቢያው ቤተክርስቲያን በመነሳት መስቀል አደባባይ ላይ ከ2:00 ጀምሮ ይሰባሰባል፡፡ ☞ #መስቀል_አደባባይ_ይጀምራል ☞ #ወደ_አዝዋ ☞ #
✍✞በመስከረም 11 ባህርዳር ከተማ የተዋህዶ ሰልፍ ሁሉም ከየአጥቢያው ቤተክርስቲያን በመነሳት መስቀል አደባባይ ላይ ከ2:00 ጀምሮ ይሰባሰባል፡፡ ☞ #መስቀል_አደባባይ_ይጀምራል ☞ #ወደ_አዝዋ ☞ #ፓፒረስ_አደባባይን_በመዞር #ወደ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_እዛው_ቤተክርስቲያን[ፀሎት ይደረጋል] ☞ #ከጊዮርጊስ_በመውጣት ☞ #ወደ_ዲፖ #ከዛም_ወደ_ኖክ_መስመር_ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት_ቤተክርስቲያን_በቦታው[ፀሎት ይደረገጋል] ☞ #ከዛም_ወደ _ኖክ ☞ #ከኖክ_ወደ_መስቀል_አደባባይ [ከፀሎት በኃላ ሰልፉ ያልቃል]፡፡ #በሚካሄደው_ሰላማዊ_ሰልፍ_ላይ_የሚዘመሩ_መዝሙራት_ዝርዝር ፩ የእቲሳ አንበሳ ተክልዬ ተነሳ ፪ ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ ፫ ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን ፬ እመቤታችን ማርያም ፭ ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሄር ፮ ቤተ ክርስቲያን ባህረ ጥበባት ፯ የአባቶቸ ርስት ከሚጠፋ ፰ ኖላዊ ትጉህ ዘኢትነውም ፱ ሀይል የእግዚአብሔር ነው ፲ ትንሳኤሽን ያሳዬን ፲፩ ተዋህዶ ንጽህት ፲፪ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለዬን ምነው ፲፫ ተዋህዶ ሀይማኖት ፲፬ አንችው ነሽ ተስፋው ለአዳም ፲፭ ፍቅር እምነት ተስፋ እነዚህ ሁሉ ጸንተው ይኖራሉ ፲፮ ለዛቲ ቤት ሀነጻ ወልድ ፲፯ የማያልፍ ዬለም ሁሉም ያልፋል ፲፰ አቤቱ የሆነብንን አስብ ፲፱ ኖላዊሀ ለኢትዮጵያ ፳ የጠላታችን ቢመስልም ጊዜው • • • ‼️❕ #ከተለያዩ_መፈክሮች_ውስጥ❕‼️ •✔የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ይከበር❗️ •✔መንግሥት የዜጎችን መብት ያስከብር❗️ •✔አክራሪ ብሔርተኞችና ጽንፈኞች እጃቸውን ከቤተክርስቲያን ላይ ያንሡ❗️ •✔ኢትዮጵያ ሥጋችን ቤተክርስቲያ ነፍሳችን ናት❗️ •✔ቤተክርስቲያንን ያቃጠሉና ካህናትን የገደሉ በሕግ ይጠየቁልን❗️ •✔ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከዘርና ከቋንቋ በላይ ናት❗️ •✔ስለጽዮን ዝም አልልም❗️

#አንቺ_ነሽ_ተስፋው_ለአዳም_ኪዳነምሕረት https://telegram.me/EOTC2921

https://telegram.me/EOTC2921 ኢትዮጵያ ታበጽህ 'እደዊሃ'(2) ኀበ እግዚአብሔር:(2) እንዘ ትብል 'አምላኪዬ'(2) ነጽረኒ ወአድኅነኒ እምኃይለ ጸላኢ ወጸር:(2) መዝሙር ፳፮

#ቤተክርስቲያን_ባሕረ_ጥበባት https://telegram.me/EOTC2921

https://telegram.me/EOTC2921 ሐይል የእግዚአብሔር ነው፣ ማዳን የእግዚአብሔር፣ ጥበብ የእግዚአብሔር፣ አንመካም በጉልበታችን፣ እግዚአብሔር ነው የኛ ሀይላችን።

#ተዋህዶ_ሐይማኖቴ https://telegram.me/EOTC2921