fa
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

رفتن به کانال در Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

نمایش بیشتر
4 374
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
✞ #መቶ_ሃያው_የክርስቶስ_ቤተሰቦች ✞ https://telegram.me/EOTC2921 #ሐዋርያት (፲፪/12 ናቸው) •••★★★♥✞♥★★★•••• *ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ (ስምዖን) *ቅዱስ እንድርያስ (የጴጥሮስ ወንድም) *ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ *ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ *ቅዱስ ፊሊጶስ *ቅዱስ በርተሎሜዎስ *ቅዱስ ቶማስ ዘህንደኬ (ዲዲሞስ) *ቅዱስ ማቴዎስ (ቀራጭ) *ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እማትያስ *ቅዱስ ታዴዎስ (ልብድዮስ) *ቅዱስ ናትናኤል (ስምዖን ቀነናዊ) *ቅዱስ ማትያስ #ቅዱሳን_አርድእት (፸፪/72 ናቸው) •••★★★♥✞♥★★★•••• +ወንጌላዊው ማርቆስ +ሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ +ሐዋርያው ጳውሎስ +ቅዱስ ጢሞቴዎስ (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ) +ቅዱስ ሲላስ +ቅዱስ በርናባስ +ቅዱስ ቲቶ (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ) +ቅዱስ ፊሊሞና (የጳውሎስ የመንፈስ ልጅ) +ቅዱስ ቀሌምንጦስ +ቅዱስ ዘኬዎስ +ቅዱስ ቆርኔሌዎስ +ቅዱስ ቴዎፍሎስ +ቅዱስ ኤውዴዎስ +ቅዱስ አግናቴዎስ +ቅዱስ አናንያኖስ (ይሁዳ) +ቅዱስ ማልኮስ (አድሊጦስ) +ቅዱስ ኤሌናስ (ኢተኮስ) +ቅዱስ አርሳጢስ (አርጣቦሉ) +ቅዱስ አስተራቲዮስ (ሐናንያ) +ቅዱስ አርስጦበሌስ +ቅዱስ ጋይዮስ +ቅዱስ አድማጥስ +ቅዱስ ሉኪዮስ +ቅዱስ ድዮናስዮስ +ቅዱስ መርአንዮስ +ቅዱስ አርክቦንዮስ +ቅዱስ አናሲሞስ +ቅዱስ ከርላዲስ +ቅዱስ አኪላስ +ቅዱስ ንኪትስ (ኢያሶን) +ቅዱስ ቀርጶስ (ጢባርዮስ) +ቅዱስ ክርስቶፎሮስ +ቅዱስ ፊሊጶስ ካልዕ +ቅዱስ ጰርኮሮስ +ቅዱስ ኒቃሮና +ቅዱስ ጢሞና +ቅዱስ ጰርሚና +ቅዱስ ኒቆላዎስ +ወንጌላዊው ሉቃስ +ቅዱስ ዮሴፍ +ቅዱስ ኒቆዲሞስ +ቅዱስ ያዕቆብ እሁሁ ለእግዚእነ +ቅዱስ አብሮኮሮስ +ቅዱስ ሮፎስ +ቅዱስ እስክንድሮስ +ቅዱስ ስልዋኖስ +ቅዱስ ሳንቲኖስ +ቅዱስ ኢዮስጦስ +ቅዱስ አክዩቁ (አጋቦስ) +ቅዱስ አፍሮዲጡ +ቅዱስ አንሞስ +ቅዱስ ገማልኤል +ቅዱስ አንዲራኒቆስ +ቅዱስ አናንያ +ቅዱስ ድርሶቅላ +ቅዱስ አቄላ +ቅዱስ አጴንጤስ +ቅዱስ አንደራኒቆስ +ቅዱስ ዮልያል +ቅዱስ ጰልያጦስ +ቅዱስ መርማርያን +ቅዱስ ኬፋ +ቅዱስ ኡርባኖስ +ቅዱስ ስጠክን +ቅዱስ አጤሌን +ቅዱስ አክሌምንጦስ +ቅዱስ ሄሮድያኖስ +ቅዱስ ጥርፌናስ +ቅዱስ ጠርፌስ +ቅዱስ አስከሪጦስ +ቅዱስ ሉቅዮስ +ቅዱስ ሱሲ #ቅዱሳት_አንስት (፴፮/36 ናቸው) •••★★★♥✞♥★★★•••• *ቅድስት ኤልሳቤጥ *ቅድስት ሐና *ቅድስት ቤርዜዳን (ቤርስት) *ቅድስት ማርና (መልቲዳን) *ቅድስት ሰሎሜ *ቅድስት ማርያም መግደላዊት *ቅድስት ማርያም እንተ እፍረት (እህተ አልዓዛር) *ቅድስት ሐና ነቢይት *ቅድስት ማርያም እሞሙ ለደቂቀ ዘብዴዎስ *ቅድስት ሲፍያ (በርበራ) *ቅድስት ዮልያና (ዮና) *ቅድስት ሶፍያ (መርኬዛ) *ቅድስት አውጋንያ *ቅድስት አርሴማ *ቅድስት ዮስቲና *ቅድስት ጤግላ *ቅድስት አርኒ *ቅድስት እሌኒ *ቅድስት ኢዮጰራቅሊያ *ቅድስት ቴዎክላ (አሞና) *ቅድስት ቅድስት ጲስ *ቅድስት አላጲስ *ቅድስት አጋጲስ *ቅድስት እርሶንያ *ቅድስት ጲላግያ *ቅድስት አንጦልያ *ቅድስት አሞን (ማርያም *ቅድስት ኢየሉጣ *ቅድስት መሪና *ማርታ እህተ አልዓዛር *የማርቆስ እናት ማርያም *ቅድስት ሣራ (ሶፍያ) *ቅድስት ዮሐና (ዮላና) *ቅድስት ሶስና ናቸው። https://telegram.me/EOTC2921

#ሥርዓተ #ቤተክርስቲያን 💠 #ንዋየ #ቅድሣት #ታቦት 🔹ታቦት ማለት እግዚአብሔር አስርቱ ትዕዛዛትን በእጁ ፅፎ ያስቀመጠበትና ለሙሴ የሰጠው ቅዱስ ንዋይ ነው፡፡ 🔸በቤተክርስቲያንም ፃህሉን እና ፅዋውን በዚህ ላይ በማስቀመጥ መስዋዕቱን እናከብርበታለን፡፡ 🔹ይህም ማለት ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ የሚዘጋጀው በዚህ ላይ ነው፡፡ 📖ዘጸ 31፥18 📖ዘዳ 20፥ #መስቀል 🔸ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ በቀራንዩ የተሰቀለበት ሰይጣን ድል የተነሳበት የመዳናችን አርማ ነው፡፡ 🔹መስቀል ምዕመናንን እና ንዋየ ቅዱሣትን ለመባረክ ያገለግላል፤ የተለያዩ የመስቀል አይነቶች አሉ። ከእነዚህም መካከል #የእጅ #መስቀል 🔹ይህ የክህነት ማዕረግ ያላቸው አባቶች ብቻ የሚይዙት ሲሆን ምዕመናንን ለመባረክ ይጠቀሙበታል፡፡ #የመፆር #መስቀል 🔸ይህ ዲያቆናት በቅዳሴ ጊዜ የሚሠብኩበት ሲሆን በመጠኑም ከፍ ያለ ነው፡፡ #መብራት 🔹መቅረዝ የሻማ ማብሪያ ነው፤ ቀንዲል ደግሞ ሻማ ወይም የዘይት መብራት ነው፡፡ 🔸የመቅረዙ አገልግሎት ለሻማ ማብሪያነት ሲሆን ቀንዲሉ ደግሞ ቅዱሣት መፃህፍት፣ መልዕክታት፣ ወንጌል ሲነበቡ ይበራሉ። #አልባሳት 🔹በቤተክርስቲያን የአገልግሎት ልብስ እንደ ግለሠቡ የስልጣን ሁኔታ ይለያያል፤ የመነኮሣት ልብስ፣ ከካህናት ልብስ የካህናትና ዲያቆናት ይለያል። 👉የጳጳሳት ልብስ፣ 👉የመነኮሳት ልብስ፣ 👉የካህናት ልብስ፣ 👉የዲያቆናት ልብስ 🔺ቀሚስ 🔺ቀሚስ 🔺ካባ ላንቃ 🔺ለምድ 🔺ሞጣህት 🔺ድግድጋት 🔺ቆብ 🔺ስአክሊል #ማኅፈድ 🔹የጨርቅ መሸፈኛ ነው፤ ታቦቱን እና ጻህሉን ለመሸፈን ያገለግላል፡፡ 🔸ከምስራቅ ወደ ምዕራብ፤ ከሰሜን ወደ ደቡብ፤ ከመስዕ/ ከሰሜን ምሥራቅ /ወደ አዜብ /ደቡብ ምዕራብ/ ሆኖ ይለበሳል፡፡ #መንጦላዕት 🔹በሶስቱም የመቅደስ በር የሚጋረዱ መጋረጃዎች ናቸው፤ ቀለማቸውም ቀይ ነው፡፡ #መጎናፀፊያ 🔸ይህ በቅዳሴ ጊዜ መንበሩ (መሠዊያው) የሚለብሰው ሲሆን፤ ታቦት በሚወጣበት ጊዜ የሚጎናፀፈው ነው፡፡ #መንበር 🔹የጽላቱ (የታቦቱ) መቀመጫ ዙፋን ነው፤ ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙ የሚዘጋጀውም በዚህ ላይ ሆኖ ነው፡፡ 🔸ካህን ያልሆነ ሠው መንበሩን መንካት የማይችል ሲሆን መንበሩ እና ታቦቱ ወዳለበት ክፍል (መቅደስ) መግባት የሚችሉት ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ኤጲስ ቆጳሳት ጳጳሳት ናቸው፡፡ #ጻህል 🔹የቅዱስ ሥጋው ማስቀመጫና ማክበሪያ ነው፤ ከወርቅና ከብር፣ ከነሀስና ከብረት የሚሠራ ሲሆን የተለየ ቅርፅና የተለየም ምልክት ያለው ነው፡፡ #ፅዋ 🔸የክርስቶስ ክቡር ደም የሚቀርብበት ነው፤ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከነሀስ፣ ከብረት የሚሠራ ነው፡፡ #ዕርፈ #መስቀል 🔹ማንኪያ ዓይነት ሆኖ ጫፉ ላይ መስቀል ያለው ነው፡፡ 🔸ፅዋው ከተሠራበት ቁስ የሚሠራ ሲሆን አገልግሎቱም የክርስቶስን አማናዊ ደም ለመቀበል የሚያገለግል ነው፡፡ #ዐውድ 🔸በድርገት ጊዜ ጻህል የሚቀመጥበት ሰፋ ያለ ጻህል ነው፤ ሥጋው እንዳይነጥብ መጠበቂያ ነው፤ የሚሠራው ከብረት፣ ከነሀስ፣ ከእንጨት ነው፡፡ #አጎበር 🔹በዐውድ ላይ የሚደፋ አራት ማዕዘን ሦስት እግር ያለው እንጨት ወይም ብረት ሊሆን ይችላል፤ ይህም ቅዱስ ሥጋውን ልብሱ እንዳይነካው ከፍ አድርጎ የሚይዝ ነው፡፡ #ጽንሃ 🔸የዕጣን ማሣረጊያ ነው፡፡ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከብረት፣ ይሠራል፤ ይህን ንዋይ ምዕመናን መጠቀም (መንካት) አይገባቸውም፡፡ 🔹ዲያቆናት ይይዙታል ይነኩታል ነገር ግን ካህናት የሚይዙበት ቦታ ላይ መያዝ አይችሉም (አያጥኑም)። #መሶበ #ወርቅ 🔹የአነስተኛ መሶብ ቅርፅ አለው፤ አገልግሎቱም ቅዱስ ቁርባኑን ከቤተልሄም ወደ ቤተ-መቅደስ ለማምጣት ነው፤ በሚመጣበት ጊዜም በመጎናፀፊያ ተሸፍኖ ነው፡፡ #ሙዳይ 🔸ለማዕጠንት አገልግሎት የሚያስፈልግ ዕጣን የሚቀመጥበት ነው፡፡ #ቃጭል 🔹በቅዳሴ ጊዜ የሚቃጨልና ድምፅ የሚሠጥ ነው፤ በቅዳሴ ጊዜ አራት ጊዜ ቃጭል ይደወላል፡፡ 👉ቅዳሴ ሲገባ 👉ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን ሲባል 👉በእግዚኦታ ጊዜ 👉ድርገት በሚወርድበት ጊዜ #ጥላ 🔸ይህ ከተለመደው ጥላ የሚለየው የተለያየ አንፀባራቂ ቀለም ባላቸው ጨርቆች መሠራቱ ነው፡፡ 🔹አገልግሎቱ በቅዳሴ ጊዜ ምስባክ ሲሰበክ እና ወንጌል ሲነበብ ይዘረጋል፡፡ 🔹ንግስ በሚሆንበት እለትም ከፊት እና ከኋላ በታቦቱ ዙሪያ ይዘረጋል፡፡ #ድባብ 🔹በመጠኑ ከጥላ ሠፋ ያለ ሲሆን በንግስ በዓላት ቀን በታቦቱ ላይ ይዘረጋል፤ ይዞ በታቦቱ አጠገብ መቆም የሚችለው ካህን ብቻ ነው፡፡ #ከበሮ 🔸ከበሮ ከእንጨት እና ከበሬ ቆዳ ተሠርቶ በጨርቅ የሚሸፈን ከፍተኛ ድምፅ የሚሠጥ መሣሪያ ነው፤ ይሁንና ከነሃስ እና ከብርም ተሠርቶ ቆዳው ሊወጠር ይችላል፡፡ 🔹ሁለት ጎኖች ሲኖሩት በእነዚህ ሁለት ጎኖች የሚወጣው ድምፅ የተለያየ ነው፤ አገልግሎቱም በማህሌት ጊዜ ለመዝሙር ማጀቢያነት ነው፡፡ #ፅናፅል 🔸ከነሃስ ወይም ከብር ሊሠራ ይችላል፤ ድምፅ የሚሠጡት በውስጡ ያሉት 5 ወይም 7 የሚሆኑ የነሀስ ወይም የብር ቁርጥራጮች ናቸው፡፡ 🔹አገልግሎቱም በእጅ ተይዞ ወደ ላይ እና ወደታች በማወዛወዝ መዝሙሩን ማጀብ ነው፡፡ #መቋሚያ 🔹ከእንጨት ከነሀስ ከብር ይሰራል። 🔸አገልግሎቱም በመዝሙር ጊዜ በትከሻ በመሸከም ወይም በእጅ በማወዛወዝ መዝሙሩን ይጅባል፤ ለመደገፊያነትም ያገለግላል፡፡ ©dnzema

https://telegram.me/EOTC2921 #መንፈሳዊ_ፊልም እባካችሁ የማትችሉ በwifi አውርዱት

https://telegram.me/EOTC2921 #መንፈሳዊ_ፊልም እባካችሁ የማትችሉ በwifi አውርዱት

#አትንኩን ‼️ አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/፪/፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን/፪/፣ ጥቂቶች ሆነን ተነስተን ነው፣ እንዲሁ ምድርን የመላነው፣ ይበልጣል ከውሃ ከእሳት፣ ጽኑ ነው የያዝነው እምነት፡፡ •••✞••• @EOTC2921 •••✞••• አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/፪/፣ የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን/፪/፣ ድሆች ስንባል ባለጸጋ፣ ሁሉን የያዘ ነው ከእኛ ጋር፣ ብርቱውን ጎልያድ የጣለ፣ በወንጭፋችን ጠጠር አለ፡፡ •••✞••• @EOTC2921 •••✞••• አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/፪/፣ የክርስቶስ ሰምራ የአርሴማ ልጆች ነን/፪/፣ በህይወት በቃል ያስተማረን፣ አምላካችን ነው የነገረን፣ የዚህ ዓለም ጨው ተብለናል፣ አልጫውንም አጣፍጠናል፡፡ •••✞••• @EOTC2921 •••✞••• አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/፪/፣ የቅዱስ መርቆርዮስ የማርቆስ ልጆች ነን/፪/፣ እንደደመና የከበቡን፣ የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩን፣ ስላሉን ብዙ ምስክሮች፣ ደካሞች ሲሉን ነን ኃይለኞች፡፡ •••✞••• @EOTC2921 •••✞••• አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል/፪/፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን፣ የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን፣ ቤተ ክርስቲያን እማማ ዝናሽ በዓለም ይሰማ/፪/፡፡

#ማንም_እንዳያስታችሁ_ተጠንቀቁ⁉️ ውድ የተዋህዶ ልጆች ቀድሞ በትንቢት ብዙ የተባለለት ቃል እየተፈፀመ እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነገር ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የዋሆችም እንደማንጠፋ የታወቀ ነው፤ እናም እባካችሁ ሁሉንም በጥልቀት እንመርምር፤ ምን እንደምላችሁ ቃላት ያጥረኛል፡ ስለሁሉም ነገር ግን እርሱ የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክፋ ነገር ሁሉ ይሰውረን፡፡ ይህ ሜዲያ ጥሩ ጎን እንዳለው መጥፎ ጎኑም እጅግ ገዝፎ የመጣበት ሰዓት ነው፡፡ ተሃድሶ ፕሮቴስታንት፣ ሙስሊም ሌሎችም••• ለምን በእነሱ ላይ ፈተና አይደርስም? ማንም ተነስቶ ከዚች አንድዬ የመጀመሪያይቱ ቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ እጁን ይቀስራል፡፡ ✔ቤተክርስቲያን ቢቃጠል የኦርቶዶክስ፡ ✔የሰው ልጅ ሰው መሆኑ ተረስቶ ቢሰቃይ፣ ቢቃጠል፣ አንገቱን በሰይፍ ቢታረድ ቢገደል የኦርቶዶክስ ልጅ፡ #ይህ_ሁሉ_ለምን_ሆነ⁉️ አሁንም በጥልቀት እናስብ ይህ ሁሉ የደረሰብን አምላክ ስለሌለን አይደለም፡፡ ወይ እምነት ስለሌለን አይደለም፡፡ ይህ ሁሉ ይሆን ይፈፀም ዘንድ የመጽሐፍ ቃል ነው፡፡ ነገር ግን ሁሉም የስራውን ያገኛል፡፡ ማንም ሰውን በመግደል ፅድቅ አለ ቢል ውሸት ነው፤ ማንም ጾም፣ ጸሎትና ስግደት ሳያውቅ እምነት አለኝ ቢል ውሸት ነው፤ መግደል፣ ጥፋትና ተንኮል እንዲሁም ውሸት የአባታቸው የዲያብሎስ ነው፤ እርሱ እንደሁ ጥንት የመላዕክት አለቃ ሳለ አምላክ ነኝ ብሎ በውሸቱ ሲያስታቸው አምላክ እረግሞ ወደ ጥልቁ የተጣው፡ ቆይቶም ለመጀመሪያው የሰው ነፍስ መጥፋት በቃየል አድሮ ወንድሙ አቤልን ያስገደለ፤ የጥንት ጠላታችን አውሬው ዲያብሎስ ዛሬም ብዙዎችን ተቆጣጥሮ በእምነታቸው በስራ በምግባራቸው ተመሳስሎ ትክክለኛይቱን ሀይማኖት ለማጥፋት እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ እናም እባካችሁ በፌስቡክ ቴሌግራም አብረውን ተመሳስለው ታላቅ አላማ ያላቸው እንዳሉ ደርሰንባቸዋል፤ ስለዚህ ሁላችንም በጥልቀት ልንመረምር ይገባል፡፡ ላዩን እየቀቡ ውስጣቸው ሌላ፤ "ጥርሱን እየሰጠ መርዙን የሚተፋ" ትውልድ በዝቷል፡፡ እናም እባካችሁ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ #የማርቆስ_ወንጌል_ምዕራፍ፡13 1 እርሱም ከመቅደስ ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ መምህር ሆይ፥ እንዴት ያሉ ድንጋይዎችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎች እንደ ሆኑ እይ አለው። 2 ኢየሱስም መልሶ፦ እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አለው። 3 በመቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም፦ 4 ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ለብቻቸው ጠየቁት። 5 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ #ማንም_እንዳያስታችሁ_ተጠንቀቁ። 6 ብዙዎች፦ እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። 7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። 8 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። 9 እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። 10 አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። 11 ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። 12 ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ 13 በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። 14 ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፥ 15 በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፥ 16 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ። 17 በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። 18 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤ 19 በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና። 20 ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ። 21 በዚያን ጊዜም ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም፦ እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ 22 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ። 23 እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ። 24 በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ 25 ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። 26 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። 27 በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል። 28 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ 29 እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ። 30 እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። 31 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም። 32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም። 33 ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም። 34 ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፥ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ። 35 እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና 36 ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። 37 ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ #ትጉ። 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር✞🙏

ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ___ኸረ_እንዴት_ነው_አባቴ___.3gp6.05 MB

ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ___እንግዳወርቅ_በቀለ___Geb.3gp5.62 MB

ገብረ መንፈስ ቅዱስ @EOTC2921.3gp4.40 MB

ያን ወረራ በግልጽ አርበኞችን ደግፈዋል፣ ወደ በረሐ ወርደውም ታግለዋል፡፡ በዚህ ምክያትም ሦስቱም አብያተ ክርስቲያናት በጣልያን ዝርፊያና አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ የሦስቱም ካህናት ወደ በረሐ ሲገቡ የገጠሙት ግጥምም በሥነ ቃላችን ተላልፎ እኛ ዘመን ደርሷል፡፡ አንኮበር፡- አቡዬን ብዬ እንጂ ይህን ሁሉ ማይ አገሬ አይደለም ወይ ዠማና አዳባይ ጎንደር ፊት አቦ ጎንደር፡- እንኳን እኔ ጀግናው የፊት አቦ ልጅ ጎንደሬ ለጣልያን አይሰጠውም እጅ ቀበና አቦ፣ አዲስ አበባ፡- ወግጅልኝ ድጓ ወግጅልኝ ቅኔ ወንዶች ከዋሉበት እውላለሁ እኔ ፬. ስምና አቦ እስከ አሁን ድረስ ባለው ባሕል ከእግዚአብሔርና ከቅድስት ድንግል ማርያም ስሞች ውጭ ስማቸው ስም የሚሆነው አቦ ናቸው፡፡ ‹አቦ ነሽ፣ አቦ ነህ› የሚል ስም አለን፡፡ በሌሎቹ ቅዱሳን ግን የለም፡፡ ዘርፍ ይጨመርበታል፡፡ ወለተ፣ ገብረ እንደሚለው ያለ፡፡ ፭. አቦና ጠበል የገጠር ሰው ትዳር ሲይዝ መጀመሪያ የሚጠጣው አቦን ነው፡፡ አቦን ቀድሞ የጠጣ ትዳሩ ይሠምራል፣ ከሰውም ጋር በሰላም ይኖራል ተብሎ ይታመናል፡፡ ፮. አቦ የቅኔ መማሪያ ‹አቦ ቅኔ› ለቅኔ ተማሪ የመማሪያ ሁለት ቤት ቅኔ ነው ‹አቦ ውርዝው እምነ ኩሉ በለጡ አንድ እንጀራ በጨው እስመ በማለዳ ለምጠጡ #ማጠቃለያ ከላይ ያየናቸውን ሥነ ቃላውያን መረጃዎች መሠረት ስናደርግ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከሌሎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን በላይ በሕዝቡ ውስጥ ባሕላዊ ቦታ እንዳላቸው ያሳየናል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ምናልባት ‹ሽምግልናቸው› ሽምግልናን ከሚያከብረው ባሕላችን ጋር ተስማምቶ ወይም አብዛኛው ታሪካቸው ከቤተ መንግሥት የራቀ መሆኑ ሕዝባዊ ቅቡልነትን ስላስገኘላቸው ሊሆን ይችል እንደሆነ እንጃ፡፡ በዚህ ረገድ ከእርሳቸው የላቀ ባሕላዊ ቦታ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያላት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት(የማርያም መቀነት፣ የማርያም አራስ፣ የማርያም ፈረስ፣ የማርያም ግርዝ፣ ማርያም በሽልም ታውጣሽ፣ ማርያም ትቅረብሽ፣ ወዘተ)፡፡ ይህ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ባሕላዊ ቦታ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በእምነት ውስጥ ካላቸው ቦታ በተጨማሪ በሕዝቡ ውስጥ ያላቸውን ሀገራዊ ሥፍራ የሚያሳይ፣ እነርሱን በተመለከተ የምንሠራቸው ሥራዎች የት ድረስ የሕዝቡን ታሪካዊና ባሕላዊ መሠረት ጭምር ሊያንጹ ወይም ሊንዱ እንደሚችሉ ደግመን እንድናስብ የሚያመለክተን ማሳያ ነው፡፡ 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞🙏

#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ማን_ናቸው? ©ዲ/ን ዳንኤል ክብረት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በ13ኛው መክዘ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ግብጻዊ ቅዱስ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መረጃዎች መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ የሚባለው በዐፄ ላሊበላ ዘመን ነው፡፡ የትውልድ ቦታቸው በላዕላይ ግብጽ ንሒሳ (የአሁኑ ባሕቢት አል ሐጋራ) ነው፡፡ [በርግጥ አንዳንድ ሊቃውንት አቡነ ገብረ= መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው፤ ነገር ግን የወላጆቻቸው ስም በሚገባ ለመታወቅ ባለመቻሉ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እናታቸው አቅሌስያ (ቤተ ክርስቲያን)፣ አባታቸውም ስምዖን (ካህን) እንደተባሉና የዚህም ምክንያቱ ከቤተ ክርስቲያን የተገኙ ለማለት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ አንድ መጽሐፈ ታሪክም ‹አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብጹዐን ወቅዱሳን ተወልዱ በኢትዮጵያ› ይላል፡፡ ☞✞አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከ500 ዓመታት በላይ በዚህ ምድር ላይ መኖራቸውንና ከትግራይ እስከ ሸዋ ባለው ክፍል ተዘዋውረው ማስተማራቸውን፡፡ በዚህም ምክንያት ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስንና ምድረ ከብድ ገዳማትን መትከላቸውን ታሪካቸው ያሳያል፡፡ ያረፉት በዐፄ ሕዝብ ናኝ ዘመን (1414-1418ዓም) ነው፡፡ ጻድቁ በትግራይ አቡዬ፣ በአማራው አቡነ፣ በኦሮሞዎች ዘንድ ደግሞ አቦ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ዋናዎቹ ገዳሞቻቸው ሁለት ሲሆኑ ዝቋላ በኦሮምያ ክልል፣ ምድረ ከብድ ደግሞ በደቡብ ክልል ይገኛሉ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ➊ ከውጭ መጥተው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኖሩ ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚታወቁት ቅዱሳን ከአመጣጣቸውና አኗኗራቸው አንጻር በሦስት ይመደባሉ፡፡ ኢትዮጵያ ተወልደውና ኖረው ኢትዮጵያ ያረፉ (አብዛኞቹ ቅዱሳን በዚህ ምድብ ናቸው)፣ ከውጭ መጥተውና ኖረው ኢትዮጵያ ያረፉ(ሰላማ ከሣቴ ብርሃን፣ማኅበረ ጻድቃን፣ ተሰዓቱ ቅዱሳን፣ አባ ሊባኖስ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እጨጌ ዕንባቆም) ኢትዮጵያ ተወልደው ውጭ ኖረው ያረፉ (አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ ሙሴ ጸሊም፣ ሙሴ ሐበሻው(ሙሳ አል ሐበሽ)፣ገብረ ክርስቶስ(አብዱል መሲሕ))፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በውጭ ሀገር ተወልደው ኢትዮጵያ መጥተው ኖረው ካረፉት ቅዱሳን የሚመደቡ ናቸው፡፡ ➋ በቁም ከሚሳሉ ጥንታውያን ሥዕሎች አንዱ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የግድግዳና የብራና ላይ ሥዕሎች መካከል ለብቻቸው በቁም በአብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ከሚሳሉት አራት ቅዱሳን (አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ) አንዱ ናቸው፡፡ የቁም ሥዕላቸው ከወሎ ገነተ ማርያም እስከ አዲስ አበባ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ግድግዳ ላይ ይገኛል፡፡ ➌ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚከበሩ ጻድቅ ናቸው፡፡ በ1990 ዓም በነበረው የሰበካ ጉባኤ የአብያተ ክርስቲያናት ቅጽ መሠረት በመላ ሀገሪቱ ከ2620 በላይ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም የሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡ ➍ የንጉሥ ዐዋጅ ቅድስናቸውን ካወጀላቸው ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡ በዓላቸው በመጋቢትና በጥቅምት 5፣ በጥቅምት 27 እና በታኅሣሥ 29 እንዲሆን ንጉሥ ሕዝብ ናኝ ዐውጇል፡፡ ➎ በ14/15ኛው መክዘ የጸሎት መጻሕፍት የሥርዓተ ጸሎት ቅደም ተከተል መሠረት ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው ለምልጃ የሚጠሩት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ 6 5. በሰዓታትና ኪዳን ጸሎት ጊዜ ገድላቸው ከሚነበቡ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን (አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ አረጋዊ) አንዱ ናቸው፡፡ ➏ የአራዊት አባቶች ከሚባሉት (አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ በርተሎሜዎስ) አንዱ ናቸው፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በሕዝቡ ባሕል ውስጥ፤ ለምን? አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በተለየ በሕዝቡ ባሕል ውስጥ ቦታ አላቸው፡፡ በሕዝቡ ባሕል ውስጥ ቦታ በመያዝ ከቅድስት ድንግል ማርያም ቀጥሎ ያለውን ቦታ ሳይዙ አይቀሩም፡፡ የዚህን ምክንያት በርግጠኛነት መናገር ከባድ ይመስለኛል፡፡ የእኔ ግምት ግን ከሁለት ነገር የመነጨ ነው፡፡ #1. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በሽምግልናቸው የሚታወቁ ጻድቅ በመሆናቸውና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሽማግሌ ካለው የከበሬታ ሥፍራ የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡ #2. ሲመጡ ከቅዱስ ላሊበላ፣ ሲያርፉ ከንጉሥ ሕዝብ ናኝ ጋር ከነበራቸው ግንኙነት ባለፈ ከቤተ መንግሥቱ ርቀው የኖሩ ሕዝባዊ አባት በመሆናቸው የተነሣ የተፈጠረ ሕዝባዊ ቅቡልነት ሊሆን ይችላል፡፡ #ማሳያዎች ፩. በይትበሃሎች ➊ አስታራቂነት፡- ነብርና አንበሳ አይስማሙም፤ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥዕል ሥር ግን ነብርና አንበሳ ተስማምተው ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሣ ለመታረቅ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለማስታረቅ የሚሄዱ ሽማግሌዎች ‹አቦን ሆነን መጥተናል› ይላሉ፡፡ ➋ የአቦ ጠበል፡- አንድ ሰው እየተመገበ ቢያንቀው ‹የአቦ ጠበል› እያልክ ውኃን ሦስት ጊዜ ጠጣው ይባላል፡፡ ➌ የአቦ ብቅል፡- አንድ ሰው ከማያውቀው ቦታ ስሙ ቢጠራና በአካባቢው የሚያውቀውን ሰው ቢያጣ የጠራው ሰይጣን ሊሆን ስለሚችል ‹‹የአቦን ብቅል እፈጫለሁ› በል ይባላል፡፡ ➍ የአቦ መገበሪያ፡- አንድ ሰው አንድን ነገር አጥፍቶ ተሠውሮ እንደማይቀመጥ ለመግለጥ ‹‹የአቦን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይውላል›› ይባላል፡፡ ➎ አቦ ሰጥ፡- አንድ ሰው የማያውቀውን ነገር በግምት ሲናገር ‹አቦ ሰጥ› ይባላል፡፡ ➏ በአቦ ይዤሃለሁ፡- አራዊት የቤት እንስሳትን እንዳይበሉባቸው ገበሬዎች ‹በአቦ ይዤሃለሁ› ብለው ይገዝቷቸዋል፡፡ ➐ የአቦ መንገድ፡- በሰሜን ሸዋ መራኛ አካባቢ ባሉ ሕዝቦች ዘንድ ‹የአቦ መንገድ› የሚባል ብሂል አለ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሚዳ ከሚገኘው የአቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም ጥቂት ጊዜ ቆይተዋል ይባላል፡፡ በኋላ ከዚያ ገዳም ሲወጡ አቡነ መልከ ጼዴቅ ‹‹የት ሊሄዱ ነው›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹እርሱ ወደ መራኝ›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ከተማው ‹‹መራኛ›. የተባለው በዚህ ምክንያት ነው ይባላል፡፡ ታድያ በዚህ ምክንያት አንድ ሰው መድረሻውን በውል ሳያውቀው መንገድ ሲጀምር መንገዱ ‹የአቦ መንገድ› ይባላል፡፡ ➑ የአቦ ቁራ፡- ሰይጣን በቁራ ተመስሎ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዓይናቸውን ሊያወጣ ስለመጣ በጎ ነገር የያዘ መስሎ የሚመጣ ክፉ ሰው ‹የአቦ ቁራ› ይባላል፡፡ ➒ በአቦ በሥላሴ፡- በሕዝቡ ብሂል ውስጥ ከሥላሴ ጋር ተያይዘው ብዙ ጊዜ የሚጠሩት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ‹በአቦ በሥላሴ› ሲባል አጥብቆ መለመን ነው፡፡ በሕዝባዊ መዝሙሮችም ውስጥ ‹በአምስት አቦ ናቸው በሰባት ሥላሴ› የሚል ሐረግ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡ ፪. በባሕላዊ ዘመን ቆጠራ አቦ በገበሬው የወቅት አከፋፈል የዘመን መክፈያ ናቸው፡፡ 1. በገበሬው የዘመን ቆጠራ ክረምት የሚገባው ‹የሐምሌ አቦ› ዕለት ነው፡፡ የሚወጣው ደግሞ ‹የጥቅምት አቦ›፡፡ 2. በልግ ይገባል የሚባለው በየካቲት አቦ ስለሆነ ገበሬው ‹የካቲት አቦን አይተህ ተሰደድ› ይላል፡፡ በየካቲት አቦ ዝናብ ካልጣለ በልግ የለም ማለት ስለሆነ ሀገርህን ልቀቅ ነው፡፤ 3. በገበሬው ዘንድ የወሩ መግቢያ የአቦ ቀን ነው፡፡ ቀጠሮ ሲይዝ ‹አቦ በዋለ በዚህኛው ቀን› ብሎ ነው፡፡ ፫.አቦና ዐርበኛነት የአቦ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በአንኮበር፣ በጎንደርና በአዲስ አበባ ስማቸው ከዐርበኛነት ጋር ይነሣል፡፡ በሦስቱም ቦታ የሚገኙት የአቦ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በአምስት ዓመቱ የጣል

#​​ተነሽ_ኢትዮጵያዬ ተነሽ ኢትዮጵያዬ ከረከሰው ምድር ደም ከፈሰሰበት ከጎደለው ክብር ይሰማ ጩኸትሽ ተነስተው እጆችሽ ይፈጸም ኪዳኑ አምላክ የገባልሽ ሕመምሽ በርትቶ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ማቃሰትሽ በዝቷል - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ሰቀቀንሽ ረዝሞ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ልጆችሽ አዝነዋል - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ከምድር አይንጠፍ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ የረጨነው እንባ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ አምላክ ይራራልሽ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ በአፈሰስነው እንባ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ #አዝ•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ፍርድ ተጓድሎብሽ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ደሃ ተበድሏል - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ቅዱሳን አልቅሰው - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ክፉዎች ስቀዋል - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ከመሶብሽ ረድኤት - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ እርቆሻልና - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ አቅርቢ ለአምላክሽ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ንስሐ ግቢና - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ #አዝ•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ደሃ አደጎች ሆነን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ በገዛ ምድራችን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ በዋጋችን ጠጣን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ገዝተን ውሃችንን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ተሰዷል ልባችን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ከአለንበት አገር - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ እንጀራ ልመና - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ከባእዳን መንደር - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ #አዝ•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• ተበጣጥሰን በዘር - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ አንድነት ስናጣ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ፍሬዋን ነሳችን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ምድር ተለውጣ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ዘራችን ክርስቶስ - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ መሆኑን ዘንግተን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ ምንጮቻችን ነጥፈው - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ አዘንን ተጠምተን - - - ተነሽ ኢትዮጵያዬ #አዝ•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞••• #ኢትዮጵያ_ታበጽሕ_እደዊሃ_ኀበ_እግዚአብሔር✞["ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች"] መዝ ፷፯፥፴፩

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን✞ ✍"ወንድሞች ሆይ፥ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ"ሐዋ፡፲፫÷፲፭ ✍"ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።"1ኛ ጴጥ፡፫፥፲፭ ✞ከቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ ውጪ✞ ☞ፅሁፍ☞ፎቶ☞ድምፅ መልቀቅ በእግዚአብሔር ስም የተከለከለ ነው፡፡ ለቻናሉ @EOTC2921 https://t.me/Ethio_Orthodox1

#ስለኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ያገባኛል ☞✞ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችኹ ተጠንቀቁ••• ዮሐ ስራ፡ 20፥ 28 #ስለቤተክርስቲያን_ዝም_አልልም!!! #ስለቤተክርስቲያን_ዝም_አልልም!!! #ስለቤተክርስቲያን_ዝም_አልልም!!! ✔መስከረም 4/2012 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይካሄዳል፡፡ ✔መስከረም 11/2012 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በባህርዳር መስቀል አደባባይ ይካሄዳል፡፡ #እጃችሁን_ከቤተክርስቲያን_ላይ_አንሱ!! #እጃችሁን_ከቤተክርስቲያን_ላይ_አንሱ!! #እጃችሁን_ከቤተክርስቲያን_ላይ_አንሱ!! ሁሉም ስለኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚያገባው #Share ያድርግ፡፡

ከቤተክርስቲያን_እጃቸውን_ያንሱ!!!_@EOTC2921.mp38.43 MB

#ታላቅ_ሰልፍ_አለ ታላቅ ሰልፍ አለ የማይቀርበት፣ የተዋህዶን ፍቅር የምንገልፅበት፣ በልቡ አምኖ ክሩን በአንገቱ ያሰረ፣ በአደባባይ ይውጣ እየመሰከረ፡፡ #አዝ•••✞✞✞••• @EOTC2921 ኧረ አይቀርም በዚህ ክፋ ቀን አያስችለንም እንዴት ይቀራል፣ ማርያምን ብለን የተዋህዶ ልጆች በትልቅ መሃላ ተማምለናል፣ ወንጌሉ ይዞን ብንታገሰው አርጎ የቆጠረን ደካማ አቅመ ቢስ፣ ይኸው መሆኑን የምናመልከው የጠላት ምሽግ የሚያፈራርስ፡፡ #አዝ•••✞✞✞••• @EOTC2921 ከሁሉም ነገር ተዋህዶ እምነቱን ከፍ ከፍ አርጎ ያላስበለጠ፣ ልበ መንታ ሰው በቃ ይመለስ ፈራሁኝ ብሎ ከደነገጠ፣ የጨከነ ግን ምድርን አጥቶ ከቅዱሳን ጋር ሰማይን ሊወርስ፣ በእውነትም ልጅ ነው የቆራጦቹ የአቡነ ሚካኤል የአቡነ ጴጥሮስ፡፡ #አዝ•••✞✞✞••• @EOTC2921 ለዚህ ቀን ያልሆንህ ታዲያ ለመቼ ለተዋህዶ ልንሆንላት፣ በሉ ተነሱ በአንድነት ሆነን ኤሎሄ ይግባ እናፍስስላት፣ ከአራቱም ማዕዘንበሰልፍ እንውጣ በታላቅ ጩኸት ወደ አደባባይ፣ እስከ መቼ ነው ግፍ እና በደል ሚሆነው ብለን በተዋህዶ ላይ፡፡ #አዝ•••✞✞✞••• @EOTC2921 እድሜ የቋጠሩ ሹመኞች ሁሉ በጠላትነት እየፈረጇት፣ ሲሉ ተሰሙ እንቅልፍ የለንም ተዋህዶን ዛሬ ካላጠፋናት፣ የሌለ ታሪክ እየፈጠሩ ይገነባሉ መጥፎ ገጽታ፣ ሊፈጥሩ ትውልድ ማየት የሚመኝ ሌሎቹ ነግሰው ተዋህዶ ጠፍታ፡፡ #አዝ•••✞✞✞••• @EOTC2921 ቅዱስ ሲኖዶስ ሲፈፀም አይቶ ግፍና በደል በተዋህዶ ላይ፣ ኑ ልጆቼ ሲል በሉ እንፍጠን ለሰልፍ እንውጣ እንዳንዘገይ፣ ያለንን ፍቅር በተግባር ገልጠን በአንድነት ሆነን ለአለም እናሳይ፣ ተዋህዶ ጠፍታ ቅጥሮቿ ፈርሰው የጠላት ደስታ ሆኖ እንዳናይ፡፡ #አዝ•••✞✞✞••• @EOTC2921

#ዕንባን_ማፍሰስ፤ 🌻🌼🌾🌿🕊✞✞✞🕊🌿🌾🌼🌻 ቅዱስ ዳዊትን የጠቀመው ዕንባው ነው። ይኽንንም፦ «ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዓይኖቼ ፈሰሰ። •••ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥበዋለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ። ዓይኔ ከቁጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች። (ሰብአ ትካትን፥ሰብአ ሰዶምን፥ ሰብአ ገሞራን በአጠፋህበት መዓትህ ታጠፋኝ ይሆን ከማለቴ የተነሣ ዓይኔ ባከነች)። አመጻን የምታደርጉ ሁሉ ከእኔ ራቁ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና። •••ዓይኔም ከሐዘን የተነሣ ተፈጀች፤ (ታወከች)፤ ነፍሴም ሆዴም፤ ሕይወቴም በሐዘን አልቃለችና፥ ዓመታቴም በልቅሶ ጩኸት። (ነፍሴም ሥጋዬም ባለመከራ ሆኑ፣ ሰውነቴ በመከራ አልቋልና፣ ዘመኔም በመከራ ተፈጽሟልና)። •••ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረጉህ። (ማቅ ለብሼ አመድ ላይ ላይ ተኛሁ)። •••በደሌንም እናገራለሁ፥ ስለ ኃጢአቴም እተክዛለሁ። •••አቤቱ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴንም አድምጥ፥ልቅሶዬንም ቸል አትበለኝ። •••ዘወትር አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ፥ ይኽንን ሳስብ ነፍሴ (ሰውነቴ) በእኔ ውስጥ ፈሰሰች።» በማለት በመዝሙሩ ገልጦታል። መዝ ፮፥፮፤ ፴፥፱፤፴፬፥፲፬፤ ፴፯፥፲፰፤፴፰፥፲፪፤ ፵፩፥፫፤ ፩፻፲፰፥፴፰። ንጉሥ ሕዝቅያስንም የጠቀመው ዕንባው ነው። በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ በተያዘበት ወራት፥ ነቢዩ ኢሳይያስ ከእግዚአብሔር ተልኮ በመምጣት፦ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርም እና ቤትህን አስተካከል። (ሕይወትህን በንስሐ አስተካክል)።» ብሎት ነበር። በዚህን ጊዜ ንጉሡ ሕዝቅያስ ፊቱን ወደ ግድግዳው በማዞር ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ መኝታው ርሶ ከአልጋው ሥር እስኪንጠባጠብ ድረስ እጅግ ታላቅ ልቅሶን አለቀሰ። እግዚአብሔርም፦ «ጸሎትህን ሰምቻለሁ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ፤ አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ አድናለሁ፥ ለዚችም ከተማ እቆምላታለሁ።» ሲል በነቢዩ በኢሳይያስ በኩል መልስ ሰጥቶታል። ኢሳ ፴፰፥፩-፮። የንጉሥ የሕዝቅያስ ዕንባ የጠቀመው ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቹም ጭምር ነው። እስራኤል ዘሥጋንም ከባርነት ቤት ከግብጽ ያወጣቸው በራሳችው ዕንባ ላይ የራሔል ዕንባ ተጨምሮ ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ፦ «በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፥ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ፥ አድናቸውም ዘንድ ወረድሁ።» በማለት መልስ የሰጠው ለዚህ ነው። ዘዳ ፫፥፯-፰። ስለ ራሔልም፦ «ራሔል ስለ ልጆቿ ስታለቅስ ብዙ ልቅሶና ዋይታ በራማ ተሰማ፥ መጽናናትንም እንቢ አለች፥ ልጆቿ የሉምና።» ተብሏል። ኤር ፴፩፥፲፭፤ ማቴ ፪፥፲፰። በአዲስ ኪዳንም በዝሙት ቆሽሻ፥ ረክሳ ትኖር የነበረችውን ሴት የጠቀማት ከጌታ እግር ሥር ወድቃ ያጎረፈችው ዕንባ ነው።» እነሆ፥ ከዚያች ከተማ ሰዎችም አንዲት ኃጢአተኛ ሴት በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደተቀመጠ አውቃ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ገዝታ መጣች። በስተኋላውም በእግሮቹ አጠገብ ቆማ አለቀሰች፥ እግሮቹንም በዕንባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጉሯም እግሮቹን ታብሰውና ትስመው ፥ ሽቶም ትቀባው ነበር።» ይላል። በዚህም ምክንያት «ኃጢአትሽ ተሰረየልሽ፤» ተብላለች። ሉቃ ፯፥፴፯-፴፰ ፣ ፵፰። ቅዱስ ጴጥሮስም በዕንባ ተጠቅሟል። ጌታ አስቀድሞ እንደተናገረበት «ኢየሱስ የምትሉትን ፈጽሞ አላውቀውም፤» በማለት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስቴ በአፉ በካደው ጊዜ፥ የዶሮውን ጩኸት ሰምቶ ምርር ብሎ አልቅሷል። ማቴ ፳፮፥፷፱-፸፭። ምን እናድርግ? በእግዚአብሔር ቃል ተወቅሰው ስለ ኃጢአታቸው ከልባቸው የተጸጸቱ ሰዎች የመጨረሻ ቃላቸው «ወንድሞቻችን ሆይ ምን እናድርግ?» ነው። የቅዱስ ጴጥሮስ መልስ፦ «ንስሐ ግቡ •••ኃጢአታችሁም ይሰረይላችኋል፥ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ትቀበላላችሁ።» የሚል ነበር። ስለዚህ ከልጅ እስከ አዋቂ፥ ከተገልጋይ እስከ አገልጋይ «ኃጢአት የለብኝም፤» ለማለት ብቃቱ ስለሌለን ሁላችንም ንስሐ እንግባ፥ ምክንያቱም ሁላችንም በደለኞች ነንና። ቅዱስ ዳዊት፦ «በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቆሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራትም የለም፥ አንድም እንኳ የለም። የሚያስተውል፥ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ። ሁሉ ተስተካክሎ በአንድነት ዐመፀ፥ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም፥ አንድም እንኳ የለም።» ብሏል። መዝ ፲፫፥፩-፫። ጠቢቡ ሰሎሞን ደግሞ «በደሉን የሚሰውር ሰው መንገዱ አይቃናም፥ የሚናዘዝና ራሱን የሚዘልፍ ግን ይወደዳል።» ብሏል። ምሳ ፳፯፥፲፫። ይህ ዘመን «እኔ ጻድቅ ነኝ፤» ብለን በሐሰት ተኰፍሰን የምንኖርበት ዘመን አይደለም። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦ የቅዱስ ዳዊትን ቃል ተጠቅሞ «አንድስ እንኳ ጻድቅ የለም። አስተዋይም የለም፥ እግዚአብሔርንም የሚሻው የለም።» በማለት ያንኑ አጽንቶ አስተምሯል። ሮሜ ፫፥፲፩። ይህ ዘመን እንዳለፈው ዘመን ሌላውን እየኮነንን ራሳችንን ብቻ እያጸደቅን የምንኖርበት ዘመን አይደለም። «አንተ ሰው ሆይ፥ እውነት ለሚፈርደው ለእግዚአብሔር ምን ትመልስለታለህ? በወንድምህ ላይ የምትጠላውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠራኸው በራስህ የምትፈርድ አይደለምን? አንተ ራስህ ያንኑ ትሠራዋለህና፥ ይህም እንደዚህ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ቅጣት የሚያመጣ የእግዚአብሔር ፍርዱ እውነት እንደሆነ እናውቃለን።» ይላል። ሮሜ ፪፥፩-፪። እስከ ክፋታችን ዝም ብሎ መመላለሱ ጥቅም የለውም። «ያለፈው ዘመን ይበቃል፤» ማለት መቻል አለብን። ፩ኛ ጴጥ ፬፥፫። አሮጌው ዘመን እንደተወገደ አሮጌው ሰውነታችን መወገድ አለበት። (ሰውነታችንን አሮጌ ካሰኘው ኃጢአትና በደል መላቀቅ አለብን)። አሮጌው መንፈሳችን በጽድቅ መታደስ አለበት። ኤፌ ፬፥፳፫። «እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ። ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና፥ ዘመኑን ዋጁ።» ተብለናልና። ኤፌ ፭፥፲፮። ክፉ ቀን በኃጢአት ይጥላል፥ ወንድምን፥ ወገንን ፥ የትዳር ጓደኛን ያስበድላል። ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። ስለዚህ ሃይማኖት ይዘን፥ ምግባር ሠርተን ዘመኑ የሚጠይቀንን መሥዋዕትነት እንክፈል። ዘመኑ አጭር ነው። እንደ ማቱሳላ ዘጠኝ መቶ ሰድሣ ዘጠኝ ዓመት አንኖርም። ዘፍ ፭፥፳፯። ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረው ቢበዛ ሰባ ወይም ሰማንያ ነው። እርሱንም በተለያየ በሽታ እየተሰቃየን ነው። መዝ ፹፱፥፲። ጻድቁ ኢዮብም፦ «ሕይወቴ (ዘመኔ) እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ቀላል ሆነች፤ (ፈጠነች)፤» ብሏል። ኢዮ ፯፥፮። ስለዚህ ከሸማኔ መወርወሪያ የምትፈጥን ዕድሜያችን ሳትቀድመን እንቅደማት። በንስሐ ታጠበን፥ በሥጋ ወደሙ ተቀድሰን እንኑር። የእግዚአብሔር ቸርነት፥ የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን። Channel @EOTC2921 Group @Ethio_Orthodox1 https://m.facebook.com/EOTC2921 ✞🕊ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር🕊✞

#የምሕረትህን_አክሊል_ትባርካለህ፤ መዝ ፷፬፥፲፩ 🌻🌼🌾🌿🕊✞✞✞🕊🌿🌾🌼🌻 ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ፦ አዲስ ዘመንን ከበረከት ጋር የሚሰጠን እግዚአብሔር መሆኑን በፍጹም ሃይማኖት መስክሯል፡፡ ይኽንንም በገና እየደረደረ በዜማ እግዚአብሔርን በማመስገን ገልጦታል፡፡ «ምድርን ጐበኘሃት፥ አረካሃትም፤ (ይህችን ዓለም በረድኤት ጎበኘሃት፥ የዘሩባትን እንድታበቅል፣ የተከሉባትን እንድታጸድቅ አደረግሃት)፤ ብልጽግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኆችን የተሞላ ነው፤ (እግዚአብሔር የፈጠራቸው አራቱ የገነት ወንዞች፦ ኤፌሶን፣ ግዮን፣ ጤግሮስ፣ ኤፍራጥስ በውኃ የተሞሉ ናቸው፡፡ አንድም፦ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ እንዲመግቡ የፈጠራቸው ወንዞች ውኃን የተሞሉ ናቸው)። ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህ። (አዳም ከመፈጠሩ በፊት ምግቡን እንዳዘጋጀህለት ሁሉ አሁንም አዘጋጀህላቸው)። ትልምዋን አርካው፤ (የታረሰውን መሬት እርሻውን በዝናም ምሕረትህ ጐበኘው)፤ መከሯንም አብጀው፤ (የተዘራው ዘር፥ የተተከለው ተክል፥ ፍሬው፥ ምርቱ በሚሰበሰብበትና በሚለቀምበት ጊዜ እንዲትረፈረፍ አድርገው)። በነጠብጣብህም ደስ ብሏት ትበቅላለች፤ (የተዘራችውን ዘር ጠብ ጠብ እያለ በሚዘንመው ዝናም ቀስ በቀስ ታሳድጋታለህ፤ በነጥብጣብ ባይወርድ ኖሮ የዝናሙ ኃይል ዘሩንም አፈሩንም ጠርጎት ይሄድ ነበር)፤የምሕረትህን ዓመት አክሊል ትባርካለህ፤ (በቸርነትህ ዘመን የተገኘውን እህሉን ታበዛዋለህ፤ አንተ የባረከው ሰው በራሱ አክሊል እንደሚቀዳጅ፥ ዘውድ እንደሚደፋ፥ የተባረከም ዘር በቅሎ አድጐ በራሱ ላይ ፍሬን እንደ አክሊል ይቀዳጃል፥ እንደ ዘውድ ይደፋል)። ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ። (በበረሃ የሚገኙ ተራሮች ልክ እንደ ዝናም ከሰማይ በሚወርድ ጠል ይለመልማሉ። ይኸውም ለዱር እንስሳቱ ነው)። ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። (ኮረብቶች የልምላሜን ዝናር ታጥቀው ለሚያያቸው ደስ ያሰኛሉ)። የበጎች አውራዎችም ስብን ይለብሳሉ)። (የለመለመውን ሣር ነጭተው፥ የጠራውን ውኃ ተጐንጭተው ይወፍራሉ፥ ይሰባሉ)። ሸለቆዎችም ስንዴን ይሞላሉ፤ (የምድር ሸለቆዎች ሳይቀሩ ከእግዚአብሔር በረከት መትረፍረፍ የተነሣ የስንዴ ምርት የሚታፈስባቸው ይሆናሉ)። እየጮኹ ያመሰግናሉ። (አድገው ለፍሬ የበቁ አዝርዕት ነፋስ ሲነካቸው ያፏጫሉ፥ ድምፅ ያሰማሉ። አንድም ይህ ሁሉ በረከት የተሰጣቸው ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ)።» ብሏል። መዝ ፷፬፥፱-፲፫። ምሥጢራዊ መልእክቱ ደግም፦ ከበረከተ ሥጋ አንፃር በረከተ ነፍስን እንደሚሰጠን የሚያመለከት ነው። አጥተነው የነበረውን የእግዚአብሔር ልጅነት፥ ተዘግቶብን የነበረውን ገነት መንግሥተ ሰማያትን፥ ወንጌልን፥ ገቢረ ተአምራትን ፥ ሥጋውንና ደሙን፥ጸጋ መንፈስ ቅዱስን፥ የእመቤታችንን እናትነት፥ የቅዱሳንን አማላጅነት፥ የመላእክትን ተራዳኢነት ሰጥቶን ደስ አሰኝቶናል። ይኸውም ይታወቅ ዘንድ፦ «ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ ሥልጣንን ሰጣቸው። •••ይህ ሥጋዬ ነው፥ እንኩ ብሉ፤ ይህ ደግሞ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፥ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ። •••መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። •••እነኋት እናትህ። ••• በነቢይም ስም ነቢይን የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይቀበላል፥ በጻድቅም ስም ጻድቅን የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ይወስዳል። •••በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና።» ብሎናል። መዝ ፺፥፲፩፣ ፲፥፩፤ ፲፥፵፩፤ ፳፮፥፳፯፤ ማቴ ፲፮፥፲፭፣ ሉቃ ፳፫፥፵፫፣ ዮሐ ፩፥፲፪፤ ፲፱፥፳፯፤ ፳፥፳፪። Channel @EOTC2921 Group @Ethio_Orthodox1 https://m.facebook.com/EOTC2921

#አዲስ_ዘመን_የተሰጠን_ለምንድን_ነው? 🌻🌼🌾🌿🕊✞✞✞🕊🌿🌾🌼🌻 "ዘመን ለፍስሐ፥ ዕድሜ ለንስሐ፤" እንዲል፥ አዲስ ዘመን የተሰጠን፦ ከዘመኑ ጋር በተሰጠን በረከት ፍስሐ (ደስታ) እንድናደርግና በተሰጠን ተጨማሪ ዕድሜ ንስሐ ገብተን ከፍ ብለን እግዚአብሔርን ዝቅ ብለን ነፍሳችንን ደስ እንድናሰኝ ነው። ይኽንን በተመለከተ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፦ «ነገር ግን ስለ እነርሱ ይታገሣል፥ ማንንም ያጠፋ ዘንድ አይሻምና ንስሐ ይገቡ ዘንድ ለሰው ሁሉ ዕድሜን ይሰጣል እንጂ።» ብሏል። ፪ኛ ጴጥ ፫፥፱። ከዚህም የተነሣ ከእግዚአብሔርም ጋር ከእኛም ጋር ቅዱሳንም ደስ ይላቸዋል። ጌታችን በወንጌል፦ «እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ስለሚገባ ስለ አንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት ደስታ ይሆናል።» ያለው ለዚህ ነው። ሉቃ ፲፭፥፲። ስለሆነም በተሰጠን በዚህ አዲስ ዘመን በንስሐ ታጥበን አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ለራሳችን ልናደርግ ይገባል። እግዚአብሔር በነቢዩ በሕዝቅኤል አንደበት፦ «ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአትም እንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ፥ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ለእናንተ አድርጉ፤» ብሎናል። ሕዝ ፲፰፥፴። ጌታችን አምካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንቀጸ ብጹዓን ትምህርቱ (በተራራው ስብከቱ) «ዛሬ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መጽናናትን ያገኛሉና።» በማለት የተናገረው ንስሐን የሚያመለክት ነው ማቴ ፭፥፬። ይኸውም፦ ኃጢአታቸውን እያሰቡ፥ በደላቸውን እየቆጠሩ፥ አላበጀንም እያሉ የሚያለቅሱ ሰዎች ሥርየት ኃጢአትን አግኝተው፥ ለፍጻሜው የማታልፍ ርስት መንግሥተ ሰማያትን ወርሰው ይጽናናሉ፥ ደስ ይሰኛሉ ማለት ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብም፦ «እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፥ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፥ ከእናንተ ይሸሻል። እግዚአብሔርን ቅረቡት፥ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኃጥአን እጆቻችሁን አንጹ፥ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ። እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ፥ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ። በእግዚአብሔርም ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፥ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።" ብሎናል። ያዕ ፬፥፯-፲። Channel @EOTC2921 Group @Ethio_Orthodox1 https://m.facebook.com/EOTC2921