✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
رفتن به کانال در Telegram
የጥበብ አፍቃሪ ኖት እንግዲያውስ ትክክለኛውን ቻናል አግኝተዋል። በቻናላችን 👉 በኔና በሌሎች የተፃፉ 👉ግጥሞች🌸 🌹ወጎች 🌸 🌹ልቦለዶች 🌸 አዝናኝ አስተማሪ ታሪኮችና ሌሎች ፅሁፎችን ያገኛሉ... ━━━━━━━━ ✦ ለማንኛውም አስተያየት @itsmetsita Paid Promotion @Tsiyon_awit ይጠቀሙ። Join us @Tsion_liboled
نمایش بیشتر7 773
مشترکین
-624 ساعت
-197 روز
-5030 روز
آرشیو پست ها
በቃ ህይወትን እንዲህ ነው መቋጨት የምትፈልጉት?
የማናቀውን ነገን ፈርተን ዛሬን ከመኖር መጉደል አለብን?....more
ሠላሜን ለማግኘት በጣርኩባቸው አመታት ነበር ለካ ሠላሜን ያጣሁት! ለማረፍ፦ ሠላም ማግኘት አይጠበቅብንም ነበርኮ... ህይወት ሁከታምና ሠላመቢስ መሆኗን መቀበል ብቻውን ማረፍ ነበርኮ!አጋጣሚ... ምዕራፍ ፬ ከአንዲት እራሷን ከማታውቅ ምሀይም ሴት እና ከአንድ ቅሌታም ሽማግሌ ወንድ.. እወለድ ዘንድ የህይወት እስትንፋስን በችግር ማህፀን ውስጥ እፍ አለብኝ! ምናል እጄን በቆረጠው!... ምናምን እንድል እንጂ አሁን በጥፊ ተመታሁ ብሎ ሰው እራሱን ይሰቅላል? የሚል የልጅነትም የጅልነትም ጥያቄ ነበረኝ... አሁን አሁን ሲገባኝ... ልጅነትም ጅልነትም እየቀረ ሲመጣ... ያቺ ጥፊ ጥፊ ብቻ አልነበረችም! የዘመናት ብሶትም ጭምር ነበረች....ያን የታመቀ... የተብላላ..ከአያቷ በእናቷ የወረሰችው የዘመናት ብሶቷ... ትንሽዬ የክብሪት ጥፊ ተለኮሰች ተብላ ሊፈነዳ መሆኑ ነው እንጂ... እኔም አልገባኝም!... ደግሞኮ ከየት እንደለመድኩት አላውቅም.... እናቴን ለመምታት አስቤውም አላውቅም... ከመታኋት ብኋላ እራሱ እኔ መሆኔን አላመንኩም... እጄ ሙሉ በሙሉ ከአእምሮዬ ቁጥጥር ውጪ ነበር... እንዴት እጄን እንደሰነዘርኩ አላውቅም... እጄ የእናቴ ፊት ደርሶ እስኪመለስ ያለውን ሁኔታ ፈፅሞ አላስታውሰውም... ከሕይወቴ እቺ ቅፅበት ተቆርጣ የተሰረቀችብኝ ይመስለኛል... ምንም የማቀው ነገር የለኝም እራሴን የማስታውሰው ከመምታቴ በፊት እና ከመታኋት ብኋላ ነው እየመታኋት የማቀው እኔ የለሁም.... በዛች ቅፅበት ከነጭራሹኑ አልተፈጠርኩም... እሷ ግን ይህንን አታውቅልኝም... እሷ የምታውቀው የእራሷን ሕመም ነው! እኔ ጥፊ ብቻ መስሎኝ እንደነበረው... እሷም ጥላቻ ብቻ መስሏች ነበር! እናቴ ማንበብና መፃፍ ብትችልም... ሒሳብና ሳይንስ ግን አታውቅም... አያቴ መንንበብም መፃፍርም አታውቅም!! እንደእኔ ያለ የገዛ ሠውነቱን አለማወቅ ያለ አለማወቅን አይቼ አላውቅም! የእኔ ቤተሰብ ባለማወቅ የተካነ ነው... የእኔው ግን ከፋ... የማስበው እኔ እና የሚከውነው ደመነፍሴ ሁለት የተለያዩ ሰዎች እስኪመስሉኝ ድረስ ግራ እጋባለሁ! ሳስብኮ ምርጥ ነኝ ስራዬ ግን የመጨረሻ ጅል ያደርገኛል... ይህም የደመነፍሴ ጅልነት ነው። እኔ የአእምሮዬ አለመብሰል መስሎኝ በፀፀት ብዙ አነበብኩ.. ብዙ አሰብኩ... ሲገባኝ ግን ጉዳዩ የIQ አልነበረም! ሕይወት እናቴን ትመስለኛለች... ምክንያቱም ሕይወት ሒሳብ አይደለችም በስሌት አትገፋም... ሕይወት ሳይንስ አይደለችም አንዱን ከአንዱ ቀላቅለን ነገን ማወቅ አንችልም... እጄን የሚያዘው አእምሮዬ ይመስለኝ ነበር.. ለካ አካሎቻችን ከአእምሯችን ውጪ እራሳቸውን ያዛሉ... ይህም የደመነፍስ ሀይል ነው! የአብዛኛው ሕዝብ ችግር ቤቱ ውስጥ ነው ያለው... ለምን? ምክንያቱም ያሀ ትክክል ስለሚመስለው! ጉድ የሚደበቀው ጓዳ የሚመስለን ምስኪን ሕዝቦች ስለሆንን ነው... ውጪ በጣም ደህና እንደሆንን ለማሳየት ጭንብሎቻችንን ለማሳመር ብዙ እናስብና እቤታችን ስንመጣ ግን ለጭንብላችን ስፍራ እናጣለታለን... ይህ ደግሞ ከማናቀው እኛ ጋር ያጋጨናል... ምናለበት እናቴ.. አባቴ.. አያቴ.. እኔ የገባኝ ቢገባቸው እላለሁ... አያቴ ደብዳቤዋን ታቅፋ ለዘመናት ኖረች... እናቴ ስሜቶቿን አምቃ ወደ አእላፍ ተነነች... የሚያሳዝነኝ ግን አባቴ ነው.. አላውቅም ምናልባት ማንም እንዳያይበት በጓደው የደበቀው ጉዱን ስላየሁበት መሠለኝ... ሁሌም ከተኛን ብኋላ ወደ ላይብረሪው ይገባና እንደሚያነብ ሁሉ አንዱን መፅሐፍ ያወጣና ጠረጴዛው ላይ ዘርግቶት ዘፈን ይከፍታል... ውብ ዓለሜ ነይ ነይ ዓለሜ.. ብሷል ድካሜ አወይ ልቤ ደጓ ትራሴ.. አስተውይ ነፍሴ ባከነልሽ ፍቅር ቢያምሰው.. አንቺ እንደው አትዘልቂ.. አትረጊም ካአንድ ሰው በዳዊት ዝማሬ በማርያም ውዳሴ.. ጧት ማታ በፀሎት ስትተጋ ለነፍሴ ዓለም በውበቷ ስባ እያጓጓችኝ.. ልቤን አሸፍታው(×3) ቆቤን አስጣለችኝ ጌታ አትማረር ደርሰህ አትገስፀኝ.. ቤት የለኝ በሠማይ በምድር እሷን ካሰኝ.. ኮብልዬ ከገዳም ቆቤን ቀዳድጄ.. አንድ ዓለሜን መረጥኩ(×3) አርባራቱን ክጄ ለፍቅር ምናኔ ቢመነኩስ ገላ.. ይቀመስ የለም ወይ ጠግቦስ ባይበላ ፍቅርን ዘክረሽው ጠበል ከጠራሽኝ.. ለኔም ላንቺም ብለሽ ፀዲቁን አቅምሺኝ ላፍ አመል ካልሆነ የምላት ወዳጄ.. ተመኘኋት እንጂ አልገባችም ከጄ! ከዘፋኙ እኩል እያንጎራጎረ ያለቅሳል... እያለቀሰ ይዘፍናል! በአያቴ መቃብር ላይ የተፃፈውን ታሪክ ሳነብና... በአባቴ መቃብር ላይ የተፃፈውን የዚህን ዘፈን ግጥም ሳነብ ግር ይለኛል... ቆይ አባቴ ነው እንዴ ለዘፋኙ ግጥሙን ፅፎ የሰጠው? እላለሁ.. ከ ሀ እስከ ፐ ለአያቴ እና ለአባቴ የተዘፈነ ዘፈን ነበር.. በዚህ መሀል የጦዘችና የጦዘባት እናቴ ደግሞ አለች... ይህን ሁሉ ጉድ ሳትሰማ እራሷን ሰቅሌ ለባለታሪኮቹ መንገድ የከፈተች... ስለመቃብሯ እንኳ ግድ ያልሰጣት.. አውቃለሁ ያ ጥፊ ጥፊ ብቻ አልነበረም ግን ደግሞ አመናቅሮ የሚያሰቅልም አልነበረም... አሁን የምታመመው የእናቴን ህመም ነው። እሷ በሕይወት ኑራ ይህንን የእናቷንና የባሏንና ያባቷም ውስብስብ ሰምታ መታመም መፀፀት የነበረባትን ጭምር ነው እኔ የተሸከምኩላት... ይሄ ሁሉ ጦርነት ውስጤን ርዋንዳ አድርገውት... "ውይ እሱኮ አያወራም! ፀጥ ያለ ነገር ነው የሚወደው" ይሉኛል ይቀጥላል....
✍ሌዊ
@Lewi_derest
ሠላሜን ለማግኘት በጣርኩባቸው አመታት ነበር ለካ ሠላሜን ያጣሁት!
ለማረፍ፦ ሠላም ማግኘት አይጠበቅብንም ነበርኮ... ህይወት ሁከታምና ሠላመቢስ መሆኗን መቀበል ብቻውን ማረፍ ነበርኮ!...more
ሌዊ ጓደኛዬ፣ የላክልኝን የ"አቶ" እኔ... ሙሉ መጽሐፍ ፒዲኤፍ (PDF) በትልቅ ትኩረትና በንቃት አነበብኩት። መጽሐፉን አንብቤ እንደጨረስኩ የተሰማኝን ስሜትና ያገኘሁትን ስነ-ልቦናዊና ፍልስፍናዊ ጥልቀት ለእኔ ብቻ አፍኜ መያዝ አልቻልኩም። ይህ ሥራ ተራ ልብ-ወለድ ሳይሆን በአማርኛ ስነ-ጽሑፍ ውስጥ እምብዛም የማይታይ፣ የሰውን ልጅ አእምሮ ራቁቱን የሚያሳይ ታላቅ "ስነ-ልቦናዊ እና ፍልስፍናዊ ድራማ" (Psychological & Existential Fiction) ነው ጓደኛዬ።
በመጽሐፍህ ውስጥ ገጸ-ባህሪው በህይወቱ የደረሱበትን 6 ታላላቅ ክህደቶች ተከትሎ፣ አእምሯችን ራሱን ከውድቀት ለመጠበቅ የሚፈጥራቸውን የውሸት ማህበራዊ ጭንብሎች (Persona) እና ወደ እውነተኛ ንቃት (Awakening) የሚደረገውን የውስጥ ፍልሚያ እያንዳንዱን ምዕራፍ ከሳይኮሎጂ፣ ከፍልስፍና እና ከንቃተ-ህሊና አቅጣጫ መስመር በመስመር ስመለከተው እንዲህ አይነት ጥልቀት አገኘሁበት፦
ምዕራፍ ፩፦ "አቶ" እኔ (የማንነት መከፈል)
ገጸ-ባህሪህ ከደረሰበት ከባድ ትራውማ (Trauma) የተነሳ ራሱን ከሰው መንጋ አግልሎ ጎዳና ላይ፣ ከድንጋይ ስር መውደቁን ስመለከት በጣም አዘንኩ።
ነገር ግን አእምሮው ራሱን ከእውነተኛ እብደት ለመጠበቅ የፈጠረውን የመከላከያ ግንብ (Ego Defense Mechanism) ያሳያል።
በዚህ ጨለማ ውስጥ "አቶ እኔ" የተባለው ረቂቅ የውስጥ ድምፅ መገለጡ፣ ካርል ዩንግ "The Higher Self" (የበሰለውና ንቁው የውስጥ ማንነት) ከሚለው ፅንሰ-ሀሳብ ጋር ይገናኛል። የሰው ልጅ ውድቀቱን ተቀብሎ ከራሱ ነፍስ ጋር የሚነጋገርበት ታላቅ መክፈቻ ነው የሰራኸው።
ምዕራፍ ፪፦ የጠንቋዩ ትንቢት (ያልተፈቱ ጥያቄዎች)
የገጸ-ባህሪህ የልጅነት የኋላ ታሪክ፣ የእህቱ መከራ እና የአስራ አምስት አመት ልጅ እያለ የእህቱን ልጅ የማሳደግ ከባድ ኃላፊነት በትከሻው ላይ መውደቁ ያለ እድሜ የአዋቂዎችን ሸክም መሸከም (Parentification) በልጁ ላይ የፈጠረውን የታፈነ ጥላ (Shadow) ያሳያል። "አቶ እኔ" የነገረው የመንታ ወንድማማቾች እና የሐይቁ ታሪክ የመላው መጽሐፍ የንቃት ቁልፍ (Self-reflection) ነው። ውጫዊውን ዓለም ከማዳን በፊት ቆም ብሎ የራስን የውስጥ ነጸብራቅ መርምሮ "መስተዋት" መሥራት መቻልን ያስተምራል።
ምዕራፍ ፫፦ ዱንያ (የምድራዊ ህይወት መረብ)
3ኛዋ ትልቅ ክህደት፣ የታማሚው ሕፃን (የእስማኤል) ሸክም እና ገጸ-ባህሪህ ከመገናኛ እስከ ላምበረት ድረስ ያለጥፋቱ ባደባባይ መወቀሱን ስታስነብበኝ ልቤ ተነካ።
ገጸ-ባህሪህ ያለጥፋቱ ባደባባይ ሲሰደብ "መስቀሌን እስማኤልን ተሸክሜ ተወቀስኩ" ማለቱ፣ የክርስቶስን ስቅለት ስነ-ልቦናዊ ስቃይ (Crucifixion Archetype) በገዛ ህይወቱ መኖሩን ያሳያል።
ከዚህ ስብራት በኋላ ራሱን ለመጠበቅ የገነባው "የውሸት ሳቅ ጭንብል" የሰውን ልጅ ማህበራዊ እስራት በጥልቅ ፍልስፍና ይሞግታል።
ምዕራፍ ፬፦ እግዜሩ (የህልውና ሙግት)
ገጸ-ባህሪህ በአባትነት መልክ በመጡለት ሽማግሌ (ጋሼ) የደረሰበት አስከፊ ወሲባዊ ጥቃት፣ የዱርዬዎች ዝርፊያ እና የፖሊሱ ክህደት በሀገራችን ያለውን ውጫዊ እና ሀሰተኛ መንፈሳዊ ጭንብል ፍጹም ራቁቱን ያወጣል።
ገጸ-ባህሪህ መከራውን እያየ ከፈጣሪ (ከእግዜሩ) ጋር የሚያደርገው ፍጥጫ ፍጹም "Existential Protest" (የእምነት እና የፍትሃዊነት ፍለጋ ቀውስ) ነው።
"አቶ እኔ" ፍርድ ቤት ስላለው ሚዛን የሰጠው ትንታኔ (ሚዛን ለእውነት ሳይሆን ለከበደው ይፈርዳል ማለቱ) የዓለምን ሥርዓት ድክመት ያጋለጠበት የሊቅ ፍልስፍና ነው።
ምዕራፍ ፭፦ ሰካራሙ መልዐክ (የልማድ እስራት)
ከሰካራሙ "ቸቡዴ" ጋር የሚደረግ ስብሰባ፣ የዶፓሚን (Dopamine) ሳይንስ እና የአስተሳሰብ መበተን (Deconstruction) መጽሐፉ ወደ ከፍተኛ ንቃት ከመሸጋገሩ በፊት አእምሮን ከማንኛውም ሱስ ነጻ ማድረግ የመጀመሪያው መስፈርት መሆኑን በሳይንሳዊ መንገድ ያስረዳል።
"አቶ እኔ" ለገጸ-ባህሪህ የሰጠው የ"ታዛቢ አእምሮ" (The Witness Mind) መመሪያ፣ አንድ ሰው ካለፈው ቁስሉ ጋር ማውራቱን ትቶ ለአላማው የሚመጥን ቃል መናገር ሲጀምር የሚገኘውን ፍጹም ነጻነት ያሳያል።
ምዕራፍ ፮፦ ሳምራዊቲቱ ሴት (የመጨረሻው ውህደት)
የሳምራዊት ታሪክ፣ የስድስተኛው ክህደት ፍጻሜ፣ የዝንጀሮዎቹ እና የሙዙ ታሪክ ታሪኩን ፍጹም በሆነ ክብ (Full Circle) የሚዘጋ ታላቅ ማጠቃለያ ነው ሌዊ።
ገጸ-ባህሪህ ያንን የውሸት ሳቅ እና የውሸት ለቅሶ ጭንብል ሰብሮ፣ ነፍሱ፣ መንፈሱና ሥጋው ተዋሕደው፣ ዳግም ወደ ውድቀት እንደማይወርድ ቃል የሚገባበት ክፍል ነው። የይድነቃቸው ብርሃኑን ጥቅስ ("እገነባለሁ እንጂ ድካሙ ቢያመኝም... ለፈረሰው ቤቴ ሳለቅስ አልገኝም!") በመጠቀም መጽሐፉን በተስፋና በብርሃን አጠናቀቀኸዋል።
የመጨረሻ ወዳጅነቱ አስተያየቴ፦
ሌዊ ጓደኛዬ፣ መጽሐፍህ በአሁኑ ሰዓት አሮጌውንና የተለመደውን አጻጻፍ ለሰለቸው፣ ወደ ራሱ የውስጥ ጥልቀት መጓዝ ለሚፈልግ አንባቢ የሚሆን ድንቅ የጥበብ ማዕድ ነው። ይህ መጽሐፍ የብዙዎችን አእምሮ የሚከፍት ታላቅ የማንቂያ ደወል ነው። በጥበብህና በንቃትህ እጅግ ኮርቼብሃለሁ!......
@lewi_derest
የልቤ ታዬ ሔዋንህ ዓለምህ በስተመጨረሻ ፍቅርህን ተረዳች... ከረፈደ ሁሉም ነገር ተገለጠላት... ከእንግዲህ መኖሬ...." ይላል...
ካልተማረችው በላይ የተማርኩት የእኔ መሀይምነት ጎዳኝ... ለምለም ሸወደችኝ... ለእራሷ ተጠቀመችብኝ....
ፀፀት አሰከረኝ... ስወላገድ ተራምጄ ስኮላተፍ ዝቼ ለምለምን በስተርጅናዋ የአንገቷን ጅማት በጣጥሼ ገደልኳት...
ልጄን አግብቼ ከልጄ ልጅ ወለድኩ! ደደብ ነኝ ደደብ! ታዲያ ለእኔ ሞት ይበዛብኛል?
ሔዋኔንና ልጄን የወሰደ ገመድ እነሆ የእኔም አንገት..
ከልጄ ብወልደውም ልጄ ነውና ልጄን አደራ የምለው ለእናንተ ነው.. እኔማ የቆምኩበትን ወንበር ገፍቼ አንገቴን ለገመድ ሰጠሁ...
ምዕራፍ ፬ ይቀጥላል...
✍ሌዊ
@lewi_derest
ለአቅመ እርጅና የደረሰችን ሴትዮ ለምን አንቺ እንደምላት የሚገባችሁ ከዚህ ብኋላ ነው።
እሺ ብዬ ስቀመጥ ስልኳን አንስታ እንቅልፍ የሚያመጡ የፈረንጅ ዘፈኖችን ከፈተች...
ሻማዎችን ለኳኮሰች... መብራቱን አጠፋች... ከገጠር አይደል የመጣሁት ይህን ለምን እንደምታደርግ አልገባኝም ነበር በላን ተጎራረስን... የሚጠጣ አለችኝ ጠጣን... እስከዚህች ስአት ድረስ የእናትነት ፍቅር ነበር የመሠለኝ... ከጠጣን ወይም ከጠጣሁ ብኋላ ግን ከእሷ ጋር ስደንስ አስታውሳለሁ... እራሴን ግን አላውቅም...
ስነቃ አልጋዋ ላይ ነኝ ምን እንደተፈጠረ ግን አላውቅም...
"ገና ከእናትህ ሆድ ሳትፈጠር ከአጥንትህ ወስዶ የሰራኝ ይመስል ሔዋኔ ሔዋኔ ስትልብኝ አደርክ አይደል? ሂሂሂሂሂ"
አቦ የአሮጊት ሳቅ እንዴት ያስጠላል...
ማን እንደወረወረው አላውቅም ሱሪዬ እዛ ማዶ ተሽቀንጥሯል...
"አባቴ ይሙት አንበሳ ነህ ግን እንድገምና ቀኔን አሳምረው... ጨዋ ከሆንክ ይሄ ሁሉ ንብረት ያንተ ነው... ልጆቼ እኝደሆኑ የተረፋቸው ናቸው ይሄንን አይፈልጉም" አትለኝም!
መርከሱንማ ዛፍ ስር እረከስን ብዬ...ከሆኑ ቀናት ወይም ወራት ብኋላ በመኪናዬ ተሽቀርቅሬ ሀገሬ ሂጄ ሔዋኔን ሳመጣት እያሰብኩ ከአሮጊት ጋር የአልጋ ትግሉን ተያያዝኩት...
የድስትሮ ስራዬን ትቼ የአሮጊቷን ሱቆችና ንብረቶች ማስተዳደር ጀመርኩ... አሁን ብር እንደፈለኩ ነው...
የሆነ ቀን ግን ፍቅር አስተከዘኝ... ሔዋኔ ናፈቀችኝ... ፍቅር አውሬ አደረኝ መጥፎ ምክርም ሹክ አለኝ...
አሮጊቷ የምታደርገውን ሁሉ እኔ ዛሬ ቀድሜ አደረኩት... ሻማውን ዘፈኑን እራቱን.. ንሄ ይገርማችኋል? የአስራ ስምንት አመት ኮረዳ የምታሸበርቅበትን ቆንጆ የእራት ቀሚስ ገዝቼ አለበስኳት ከመጠጡ ቀድማ በደስታ ሰከረች...
ትንሽ አጠጥቼ አስፈረምኳት ሙሉ ንብረቷን በስሜ እንዳዞረችልኝ የሚያረጋግጥ ወረቀት ላይ....
ያን ምሽት የመጨረሻዋ ነው ብዬ አስደሰትኳት... መድሀኒት ውጬ ነው ሁላ የወሲብ ጥጉ ላይ ያደረስኳት...
በነጋታው ከስአት ለእኔ የምስራች ለእሷ መርዶዋን አበሰርኳት...
"አንተ ባላገር" አለች...ትበል እኔ ምን ገዶኝ...
"ከተሜነት በመቁረቢያ መባለግ ከሆነ እንኳንም ቀረብኝ..." አልኳት
"እኔ አንቺን ብሆን እንደዚህ ጉድ ተሰርቼ ከነቅሌቴ ለመኖር አልወስንም በዚህ ገመድ እራሴን ነበር የምሰቅለው" ብዬ ጠረጴዛው ላይ ገመድ አስቀመጥኩና ለመውጣት ወደበሩ ተራመድኩና በሩን ከፍቼ ልወጣ አንድ እግሬን አስቀድሜ ቆምኩና ወደእሷ ዞርኩ...
"በዛ ላይ ልጆቼ ቅሌቴን እንደሚሰሙ ካወኩ ሁሌቴ አላስብም ነበር" ብያት ወጣሁ...
ልክ ነበርኩ... ማታ ስመጣ አጅሪት ወይዘሪት ወይም ወይዘሮ እራሷን አጥፍታ ነበር...
አይገርምም ገመዱን ከጎኗ አድርጋ እራሷን በቢላዋ ነበር ወግታ የገደለችው...
ከሔዋኔ የለየኝ እግዜር ሲያተርፈኝ ቲቪስታንዱ ላይ የተቀመጠ የሳሎን ካሜራ ነበር... እንደነገረችኝ ከዚህ በፊት ሰራተኛዋ ዘርፋቸው ሌባ ገባ ብላ አታልላቸው ነበር... ለካ ነው የሳሎን ካሜራ የነበረው...
ይሄንን ስለማውቅ ነበር ገመዱን የምግብ ጠረጴዛው ላይ ያደረኩት ካሜራው እዛ አይደርስማ...
የካሜራውን ማስረጃ አሳይቼ እራሴን ነፃ አደረኩ... ሀብቴ ጀመረ... ሀብቴ በጀመረበት የመጀመሪያው ወር በአሮጊቷ የተከማቸ ሀብት መኪና ገዛሁ... በመኪናዬም ወደሀገሬ ሄድኩ... እነሆ ሄዋኔ መጣሁልሽ... አይነት አነዳድ ነበር የነዳሁት...
ግን ምን ያደርጋል... ሔዋኔ የለችም!
መጣሁ መጣሁ ሰከንፍ
አጣኋት የእኔን ወፍ!
መጥቼላት ነበር ይዤ ሠረገላ
አረገዘች አሉኝ እሷ ግን ከሌላ!
ለምለምን ጠየኳት.. እሷ ግን ደብዳቤውን እንዳልሰጠቻት ነገረችኝ... ጭራሽ ከጓደኛዬ ፍቅር ጀምራ እንደነበርና ሚስጠረኛዋም እንደነበረች ነገረችኝ...
ጓደኛዬን ልጣላው... በዛች መናጢ አሮጊት በተማርኩት አውሬነት ልገድለው ቢላ ገዝቼ ስሄድ እንደሞተ ተነገረኝ...
መልሼ ለምለም ጋር መጣሁ... ስጠይቃት.. ከእሱ እንዳረገዘችና እሱ ከዛፍ ላይ ወድቅ ሲሞት አፍራ ወደአዲስ አበባ እንደጠፋች ነገረችኝ...
የቀረብኳት እሷ ስለነበረች የምታፅናናኝም ወዳጄም እሷ ስለነበረች ተቀራረብን...
በሔዋኔ ተስፋ ቆርጬ ለምለምን እንደሔዋኔ ተቀብዬ ወደአዲስ አበባ ይዣት መጥቼ አገባኋት...
ለልጅ የተለየ ፍቅር ነበረኝ.. ሌላ ነገር እኮ አይደለም ልጅ አስተዳደግን ለሀገሬው ሰው በእልህ ላሳያቸው ነበር... ልጄ በእኔ ሳይሆን በእሱ ፍላጎት እንዲያድግ ላደርገው... እኔ በወላጆቼ ያጣሁትን ለልጄ ልሰጠው ፈልጌ ነበር መውለድ የምፈልገው...
አሁንም እግዜሩ አረመኔ ሆነብኝ... ልጅ ከለከለኝ.. ለምለም መሀን ሆነችብኝ... ከወጣትነቴ እስከርጅናዬ በመማገጥ አለሜን ጨረስኩ...
በስተመጨረሻ ግን የተባረከ ማህፀን በቆንጭዬ ወጣት ታደልኩ...
ልጅ እንዳረገዘችልኝ ሳውቅ ለምለምን ፈትቼ ያቺን ወጣት ቆንጆ ለማግባት ተስገበገብኩ... አገባኋት...
እናቷ ግን ትረብሸኝ ነበር... ለምን እንደሆነ አላውቅም... የሆነ ቀን መጠጥ እየጠጣሁ አሰብኩ አሰብኩ.. በመጠጥ ሀይል ስካር ሹክ አለኝ...
መልሶ ስካሬ በኖ ጠፋ... አዎ እሷ ሔዋኔ ነበረች የልቧታ የሆንኩ!
ልጠይቃት እፈልጋለሁ... ለምን አልጠበቅሽኝም? ለምን ደብዳቤውን ለለምለም እንድታነብልሽ አልሰጠሻትም? ልላት እፈልጋለሁ ግን ልጄን ሳስብ ደስታዬን ማጣጣም ይበልጥብኝና ዝም እላለሁ...
የልጄን እናት ያቺን ቆንጅዬ ወጣት እወዳት ነበር.. እንደንግስት በአእላፍት ሰራተኛ አጅቤያት ነበር... እናቷ ሔዋኔ እንደሆነች ሳውቅ ግን ጠላኋት...
ለምን እንደሆነ አላውቅም.. ከጓደኛዬ ስለወለደቻት ቀንቼ ይሁን ወይም ፀፀት ብቻ ጠላኋት... ከልጄ ሁላ ላርቃት እሞክር ነበር.. ሆን ብዬ አስቤው ምናምን አይደለም እኮ እንዲሁ በደመነፍስ ነው እንዲህ የማደርገው...
ከእለታት በአንዱ ቀን ልጄ በጥፊ መታኝ ብላ እራሷን ሰቀለች... አውሬ ሁኜ አይደል ከቋንጣም አልቆጠርኳት... ከልጄ እንጂ ከእሷ ምን አለኝ...
ስትኖር ስትኖር ከእለታት በአንዱ ቀን እናቷም ተከትላት እራሷን ከቋንጣ ባልተናነሰ ሰቀለች...
ይህን አልክድም ሔዋኔ ነበረችና ሀዘን ገብቶኝ ነበር...
ፖሊሶች ደብዳቤ ሰጡኝ... አነበብኩት...
ሔዋኔ የእኔ ዓለም.. ዓለምዬዋ! ደብዳቤዬን እንደ እኔ ታቅፋው ለዘመናት ኑራ ነበር!
የፃፍኩትን ደግሜ አነበብኩት... ከፃፍኩት በታች የተፃፈ አየሁ...
"የልቤታዬ አሁንም ቀለም አልችልም! መንገደኛ አስቸግሬኮነው አልገርምህም...
አሁን የፃፍከውን ሳስነብብ እንደዛን ጊዜው ፀፀት የተሞላበት ለቅሶ ውስጥ ገባሁልህ... ደብዳቤው ስለለምለም መስሎኝ በቅንሀት መሸሸጌ ይሄም አለመማሬ እኮ ነው... ይቅር በለኝ የልቤታዬ...
ደግሞ እኮ የምፅናናባት ልጅ ወልጄልሀለሁ...
ቄስ መሸሻ ቆሌህን ቢገፉትም ዘርህን ግን ከማህፀኔ ሊገፉት አልቻሉም.. ደስ አይልም የልቤታዬ ያኔ እዛች ዛፍ ስር የዘራሀት ዘር በግላ አሁን ትልቅ ሁናልሀለች..
አለመማሬ ለልጄም ተርፎ ያላቅሟ ቅሌታም ሽማግሌ አግብታ ወለደችብኝ እንጂ ልጅስ ወልጄልህ ነበር...
የልቤታዬ አትዘንብኝ... ቢያንስ በመቃብሬ የሚያልፍ ሰው ሁሉ በአግራሞት ጀግንነትህን ያነቡልሀል የእኔ መሀይምነት ምን ያክል እንደበደለህ እያዩ በሰዎች ሁሉ ፊት ልወቀስልህ በእራሴ ወስኛለሁ...
ደራሲው...∞:
ተራ ቤተሰብነት ሳይሆን የሃይልዬ ቤተሰቦች ተብለው የሚጠሩበትን ኩሩ ቤተሰብን ነው መመስረት የምፈልገው...አጋጣሚ ምዕራፍ ፫ እነሆ አዳም በሠላም ገነት ውስጥ ሲኖር ሳለ ከእለታት ባንዱ ቀን... ይመስለኛል የሆነ ሰፊ ጥላ ያለው ዛፍ ስር ነው አረፍ ልበል ያለው ሰውዬ... ዘላለም የመሰለ እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አይልም! እናላችሁ ከዘላለሙ.. ከዛፉ ስር ሄዋኑ ከአጥንቱ ተረግዛ... ዘጠኝ ወር ይሁን ዘጠኝ ደቂቃ... አዳም ስላንቀላፋ ምን ያክል እንደሆነ አናውቅም ብቻ ተወለደችለት... እነሆላችሁ አዳምና እግዜሩ አባሮሽ የጀመሩት ከዚህ ብኋላ ነው! ወንድ ለሴት ብሎ ከወንድ ጋር ይጣላ! Normal አይደለም ቢሆንም እሺ... ግን እንዴት ወንድ ለሴት ብሎ ከእግዜሩ ጋር ይጣላል? አጅሬ አዳም ግን አደረገው... እኔስ የማን ዘር ሆንኩና ይቅርብኝ.... አባቴን እንጂ እኔን ባለመኖሬ... ቄሶቼን እንጂ እኔን ባለመከተሌ በጥልቁ አንቀላፍቼ የነበርኩት እኔ... ልክ እንደ አዳም ያለ ትልቅ ጥላ ያለው ዛፍ ስር ነቃሁ... የቀሰቀሰችኝ ደግሞ ሄዋኔ ነበረች! ደፋር ነህ ትሉኝ ይሆናል ግን እስካሁን መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄዬ... አዳም ግን እግዜርን እንዴት አሸንፎት ኘው ከሄዋኑ ጋር አብሮ የኖረው? እኔ ለምን በእግዜሩ ተሸነፍኩ? ለምን ሄዋኔን ነጠቀኝ... ይህ ጥያቄዬ ዘወትር ከእግዜሩም ከእኔውም ጋር ያጣላኛል። ሁሉን ውብ አድርጎ የሰራ አምላክ አይደል? ከውቦቹስ ምሀል ሄዋኔ አንዷ አልነበረች? ታዲያ ውበት እንዲህ ነው እንዴ? በዛፍ ጥላ ጥለት ፍቅራችንን ሸምኖ ሲያበቃ.... እበሳጫለሁ አላውቅም ማን ነበር ስህተት የሰራው? ሄዋኔ ለምን ደብዳቤውን ለለምለም አልሰጠቻትም? ሰታት የፃፍኩላትን ሁሉ ካስነበበች ብኋላ ከእኔ ጋር መሄድ ስላልፈለገች ይሆን? ነው ወይስ ለምለም የውሸት ሌላ ነገር አንብባላት ነው? በዛ ብርድ በዛ ሌሊት በፉጨቶቼ መሀል ሳስብ የነበረው ይሄንንኑ ነበር... አዲስ አበባ ገብቼ የስንቱን እከካም ጫማ ስጠርግ... ባልገቡኝና ባልተመለሱልኝ ጥያቄዎቼ ናውዤ ጫማውን ስፈትግ... ታታሪ ነው አሉኝ... ናውዤ መሆኑን ማን በነገራቸው! አንዳንዴ ደጉ ጊዜዬን አስብና በእራሴ እገረማለሁ.... ያ ቄሶች ሁሉ የሚያሞግሱት እኔ ምን እንደነካው ግር ንለኛል... በቅዳሴው መሀል በቤተመቅደሱ ውስጥ እጣኑ እንደጉድ ሲንቦለቦል በካህናቱና በመእመኑ ላይ ጎልቶ የሚታየው ነጭ ቀለም ከቅዳሴው ዜማ ጋር ተዳምሮ የመላዕክት ዝማሬን የታደምኩ እስኪመስለኝ ፍስስ የምለው እኔ... በማላውቀው ስሜት ታውጄ ዓይኖቼ ተነክተው ሲያለቅሱ የነበርኩት እኔ... መንፈሳዊነቴ ክንፍ የሚያስበቅለኝ የሚመስለኝ እኔ የት ጠፋሁ? እላለሁ... የሔዋኔን ከናፍርት መቅመሴ አበላሸኝ? አይ አይ እንደዛማ አይደለም! ስንቴ ነው ከእሷ ወደቤተክርስቲያን.. ከቤተክርስቲያን ወደእሷ የተዛመድኩት... ሁሌም ግን ለሁለቱም የሚጋጭ ስሜትና ፍላጎት ውስጥ ገብቼ አላውቅም ነበርኮ... ምክንያቱም እሷ ሔዋኔ ናታ! ከእሱ የተሰጠችኝ! ሔዋኔን ፍሬዬን ቀመስኩና እርቃን መሆንን መፍራት ተዘነጋኝ... ቀበቶዬን ስፈታ መንገድ መኖሩ ተዘነጋኝ... ኡኡታቸው ዓይኔን ገልጦት እርቃኔን ልሸፍን ተወላከፍኩ.... እርቃኔ አይደለም በበለስ ቅጠል በእግዜሩ ቁርበት እንኳን የማይጋረድ መሆኑ የገባኝ ያዩን ቄስ መሸሻ መሆናቸውን ሳውቅ ነው። በየት ይደርስብኛል ብለው እንደሰጉ አላውቅም.. ቆብም ስልጣን ሁና ይነጥቀኛል ብለው መሠለኝ ደርሰው ይቀኑብኛል... በእግዜሩና በሰይጣን መካከል ቄስ መሸሻን የመሰለ ቆንጆ አቃጣሪ መልዐክማ አለ!... አሯሯጣቸውኮ ሸለፈት ያንጠለጠልኩ እኔን ያዩ ሳይሆን እራሱ እግዜርን ሲባልግ ያዩት ነበር የሚመስሉት... አባቴ የክብር ሰው ነው... አይደለም ልጁ በዕለተ አርብ ያስቀደቀበትን ነጠላውን ከላዩ ሳያወርድ ያውም ሜዳ ላይ ያውም ቀለም ከማታውቅ ሴት ጋር ሲባልግ ታየ ተብሎ አይደለም አይጥ እንኳን በቤታችን ውል ካለች... "እንዴት ተደፈርኩ!" ብሎ የሚደነፋ ነው! ቄስ መሸሻ መሰሎቹን ሰብስቦ አባቴ ጋር ለስሞታ ከመምጣቱና ከቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በአባቴ ከመኖርም ከመወገዜ በፊት ብዬ ባገኘሁት ወረቀትና እስክሪብቶ ሌሊት ሳፏጭላት እንድትወጣ ፅፌ ለሔዋኔ ሰጥቼያት... ከኋላዬ እየጮኸ ከሚከተለኝ አባቴ መሸሼን ተያያዝኩት... "ቤት አለኝ ብለህ ብትመጣ! ዋ ብቻ እኔን አያርገኝ! እንዳዋረድከኝማ አትቀርም....." እያለኝ ድምፁ እየራቀኝ እየራቀኝመጣ... ብርድ ነበርኮ ግን ሔዋኔ መታልኝ አብረን አዲስ አበባ ስንሄድ እያሰብኩኝ ልቤ ስትሞቅብኝ... ጡቶቿን ያልጠገቡ መዳፎቼ... ከናፍሯን ያጣጣሙ ከንፈሮቼ ያሰረጉትን ሙቀት ሲተፉ... ብርዱ እንደጠራራ ፀሐይ ያልበኝ ጀመር... መስሎኝም ይሆና... በጣም ቅዝቃዜ ቦታ ላይ ለረጅም ጊዜ የቆየ እቃ ሲያልበው አይቻለኋ! በዚህ ሙግቴ መሀል ነው ሔዋኔ የቀረችብኝ... ያላበኝ በሙቀት ወይስ በቅዝቃዜ? አሁን አሁን ስፈታው በምናቤ ሙቀት በእውነታው ቅዠት ነው ያላበኝ... ሸገር ለመግባትም ሔዋኔን አንጠልጥሎ አውቶቢስ ተራ መሄድ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ የገባኝ... እረዳቶቹ ብር ሲሰበስቡ ሳይ ነበር... አፈርኩ በእራሴ አፈርኩ... አሁን ሔዋኔ መታ ቢሆንስ አልኩ! አቅም አጠረኝ... ተሸነፍኩ... ያኔ ሔዋኔ በመጨረሻ አቅሟ ስታለቅስ እንዳየኋት ያለ ለቅሶ አለቀስኩ... ማንበብ ተስኗት ያለመቻል ጣራዋን እኔ ብር የማጣት ጣራው ላይ ደርሼ ስሜቷ ተሰማኝ... በቆምኩበት ፊቴ ሳይኮሳተር ሳይስቅ... አፌ እንደተገጠመ ዕይኖቼ ብቻቸውን አለቀሱ... "ሸበላው ምን ሁነህ ነው የምታለቅሰው? አለችኝ... አንዲት ለአቅመ እርጅና የደረሰች ሴትዮ... "እህ.. እህ.. መ.. መሳፈሪያ አጥቼ.." አልኳት በስቅታ ታጅቤ "የት ልትሄድ?" "አዲስ አበባ" "ውልጄን አታልቅስ እኔ እከፍልልሀለሁ እኔም ወደአዲስ አበባ ነኝ ና ልጄ" ብላ ይዛኝ ገባች። ሌቱን እንዳልተኛሁ የገባኝ ለምሳ ሴትዮዋ ስትቀሰቅሰኝ ነው... ምግብ ሁላ አላሻኝም መተኛቴን መቀጠል እንደምፈልግ ነግሪያት መኪና ውስጥ ብቻዬን ተኝቼ ቀረሁ... በድጋሚ ስትቀሰቅሰኝ መኪናው ከቆመበት ከተማ ወቶ በረሀማ ቦታ ላይ ለሽንት በቆመበት ነው... "ሽንት ካለብህ ሽናና ምግብ አምጥቼልሀለሁ ብላ" አለችኝ ወርጄ ሸንቼ መጥቼ ምግቤን በላሁ... ከዛ ብኋላ ነቃ አልኩኝ መተኛትም እንቢ ሲለኝ ከሴትዮዋ ጋር ወሬ ጀመርን... አዲስ አበባ የማቀው ሰው እንደሌለና ለስራ እንደምሄድ.. ቤተሰቦቼ በእሳት አደጋ እንደሞቱብኝ ዋሽቼ ነገርኳት። "ውይ ልጄ እኔን በቃ እኔ ጋር ታርፋለህ እኔ በስተርጅና ብቻዬን ነው የምኖረው.. ልጆቼ ሁሉ ከሀገር ወተው ብር ብቻ ይልካሉ ብር ሰው ይሆን ይመስል" አለችኝ... ሸገርን በእማማ ቤት እገፋው ጀመር... ለድስትሮ የሚሆኑ እቃዎችን ገዛችልኝ ጫማ መጥረግ ጀመርኩ... እስከሆነች ሌሊት ብቻ.... የሆነኛው ቀን ማታ ከስራ ወደቤት ስገባ ከማድርባት ጠባብና ትንሽዬ ቤት ጠራችኝና.. "ናስኪ ሻወር ውሰድና እቺን ልብስ ሞክራት ገዝቼልህ ነው" አሉኝ ታጠብኩ ለበስኩ... እራሴን በመስታወት ከእግር እስከ ፀጉሬ ሳየው ሀብት በእኔ እንደሚያምር ገባኝ... "ነገ ደግሞ ፀጉርህን ትስተካከላለህ" አለችኝ ከእኔ በላይ በእኔ እየሻፈደች... እሺ ብዬ ልወጣ ስል... "ቆይ ቆይ እንጂ ዛሬማ እራት አብረን ነው የምንበላው አለችኝ...
ምዕራፍ ፫
ተራ ቤተሰብነት ሳይሆን የሃይልዬ ቤተሰቦች ተብለው የሚጠሩበትን ኩሩ ቤተሰብን ነው መመስረት የምፈልገው...more
ለ 2 ሳምንት ብቻ የሚቆይ ከ 15% - 18% ልዩ ቅናሽ በዋና ሼልፎች ላይ!
የሱቅ ኪራይ እና ግብር አስጨንቆዎታል?
መገናኛ Zefmesh Mall በሚገኘው የሴቶች material ሱቃችን ኦሪጅናል ዕቃዎን ብቻ በማምጣት መሸጥ ይጀምሩ!
ለኦንላይን ነጋዴዎች ትልቅ ዕድል
እኛ የምናሟላቸው አገልግሎቶች፦
✅ ንግድ ፈቃድ አያስፈልግዎትም
✅ የሽያጭ ባለሙያ (Salesperson) ከእኛ
✅ ነፃ ፕሮሞሽን
የቦታ ኪራይ በወር (ከቅናሹ በፊት ያሉ ዋጋዎች):
* 40x40 ሼልፍ:** 3,000 ብር
* 40x60 ሼልፍ:** 3,500 ብር
* የዕቃ መረከቢያ (Pick-up): 1,500 - 2,000 ብር (ከ Shein/Amazon ለሚያመጡ የተዘጋጀ)
ቦታችን ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ!
📞 0904405974
💬 Telegram: @meronterefe
"ልጄ የእኔን ኑሮ አይታ እንደእኔ ኖረች... እኔ ደግሞ አሁን የልጄን ሞት አይቼ እንደልጄ እሞታለሁ..."
ወደተንጠለጠለችበት ቦታ ሄድኩ አይገርምም እሷን እንጂ ገመዱን አላወረዱትም ነበር...
ለብቻ ይህን ወረቀት መቃብሬ ላይ እንደፎቶ እንዲለጥፉት የሚጠይቅ ፅሁፍ ያፃፍኩትን እንዲያዩት አስቀምጬ ወንበሩን አመጣሁና የልጄን መንገድ ተከተልኩ...
ልትሞት አንድ ሐሙስ የቀራት አሮጊት ምን ልሁን ብላ ነው እራሷን የምታጠፋው? እንደሚሉኝ አውቃለሁ ግን አሁንም እነሱ፦ መኖርን እንጂ ሕይወትን አላዩም።
ከዚህ በላይ ላወራችሁ አልችልም... ምክንያቱም እግሮቼ የረገጡትን ወንበር ለቀው በመፍጨርጨር ላይ ናቸው!
✍ሌዊ
@lewi_derest
አሁንም ሲገባኝ ለውሸትም እውቀት ያሻዋል ለካ... ኸተማሪ ቤት ፅሁፍ ብቻ ሳይሆን ነገሮችንም ማንበብ ያስተምሩ ኑሯል ለካ?
ልጄን ሳይ ግን ይህ የግል ችሎታ እንጂ ኸተማሪ ቤት የሚሰጥ እውቀት አልነበረም።
ከልቤታ ጋር ሦስተኛ ወራችን ላይ ደረስን ግን አንድ ወር እንኳን በቅጡ ቀለም አልተማርኩም... ስነካካው ሲነካካኝ ስሜታችን ከኮከባችን ገጥሞ ከንፈር ተቃመስን...
አሳሳሙ ጥበብ ነበረው... ከዚህም አለመማሬ ያጎደለኝ መስሎ ይሰማኝ ነበር...
ቀጠሯችን ከቀለም ትምህርት ወደ ፍቅር አርነት አደረሰን...
ከቀናችን በአንዱ ቀን... የልቤታ እንዳለኝ ክርስቶስን የሰቀሉት በእለተ አርብ ነው... ፍቅሬንም ይሰቅሉት ዘንድ...ከስስት ተራክቧችን በዓይኖቻቸው አሰናከሉን።
ቄስ መሸሻ አውሬ እንዳዩ ሁላ ኡኡ አሉ...
"በለተ አርቡ?! አቤቱ መሐረነ!..." የማይገባኝን ግዕዝ እየተረቱ ወደመጡበት ተመልሰው ሮጡ...
የኔታ የልቤታ
ሆነበት ቀኑ ማታ
ሰማይ ከምድሩ
ሊጥሉት አበሩ
ፍቅሬ ተሰቅሎ
ሄደ እኔን ጥሎ
ወዴት እንደሆነ አላውቅም... ሲሮጡ የታጠቁትን ተረት በልቤታ አየሁት... እየሮጠ ቢታገለው አልታሰር ብሎት በብስጭት ቀበቶውን መዞ ወዲያ ወርውሮት ሱሪውን በእጁ ጨብጦ እሮጠ...
አነሳሁት ቀበቶውን በልብሴ ሸሽጌ ከልብሶቼ መሀል ዶልኩት።
ደንግጬ ቤቴ ተሰብስቤ በተቀመጥኩበት ስሜን እየጮኸ ሲጣራ ሰማሁት... ባዶ እግሬን እየሮጥኩ ስወጣ... እየተጣደፈ
"እንቺ... እንቺ" እያለ ወረቀት ያውለበልባል
እሱጋር ስደርስ... "ይሄንን ደብዳቤ ለምለም ጋር ይዘሽላት ሂጂና...."
አውርቶ ሳይጨርስ አባቱ ከማዶ ሽመላቸውን እያወናጨፉ "ና ብዬሀለሁ ዛሬ!" እያሉ ይሮጣሉ... እሱም ሳይጨርስልኝ ትቶኝ እሮጠ...
እስካሁን ግን ምን ግራ እንደሚገባኝ ታውቃላችሁ... ቄስ መሸሻ እሱን እንጂ እኔን አለማየቱ... አባቱ ልጁን ማባረሩ እንጂ እኔ ጋር መቆሙን አለማየቱ...
ማን ትሆን እያሉ ሲዘብቱ ሰምቻቸው አውቃለሁ! ለነገሩ የሚጥሉትን እንጂ የወደቀውንማ ለምን ብለው ያስተውሉታል... አለመማሬ የጣለኝ እኔ ከዓይናቸው አልገባ ብያቸው!
ከለመድናት ዛፍ ልሄድ ልቤ ይሻፍድብኛል... እዛ ቢያገኙኝ ደግሞ ያውቁብኛል ብዬ እየፈራሁ እቀራለሁ።
የሰጠኝን ወረቀት አገላብጣታለሁ... ያኔ የተሰማኝ የመሰበር ስሜት ተሰማኝ አሁንም አላነበብኳቸውማ!
ለምን ደብዳቤውን ለለምለም ውሰጂላት አለኝ... እኔን ቸው እንኳን ሳይለኝ ለእሷ ደብዳቤ ፃፈላት? ለነገሩ በድንቁርና ካለች ሴት ምን አለው... እወድሻለሁ ብሎ ፅፎላት ይሆን? በእኔ አለመማር እየቀለደላት ይሆን? እንዴት ሲያደርገኝ እንደነበር በጉራ እየነገራት አንቺ ብትኮሪብኝም.. እያላት ይሆን? ለምን ከእኔ ይልቅ ለእሷ ደብዳቤ እስከመፃፍ ቅድሚያ ሰጣት?.... ይህን ሁሉ የሚያስቀባጥረኝ አለመማሬ ነው።
ከወራት ብኋላ መታመም ጀመርኩ... ሆዴም ጤነኛ አልመስልሽ አለኝ... እየጠላኋትም ቢሆን ለምለምን አወራኋት...
"አንቺ ነበርሽ?" አለችኝ ደንግጣ
"ምኑ?"አልኳት ግራ እየተጋባሁ እኔ እኮ እንዴት እንደሚያደርገኝ ነው የነገርኳት
"ማነው ይሄ ከዲያቆኑ ጋር ባለገች ምናምን ተብላ እየፈለጓት የነበረችው ሴት" አለችኝ
ደነገጥኩ እቺማ ቀለም ብቻ ሳይሆን ጥንቁልናም ተምራለች.... ከእኔ ይልቅ ቅንሀቴና ጥላቻዬ በልጦብኝ "ስሙን አታቂውምና ነው?" አልኳት
"ኧረ አቀዋለሁ ቢልልኝ አይደል ድቁናው ከክወናው ጋር አልገጥም ቢለኝ ነው እንጂ" አለችኝ
ቅናት ተንገበገብኩ... የሆነ ነገር ባይኖራቸውማ እንዲህ አትናደድበትም ነበር እሷ ቄስ አይደለች እንዴት ዝም ብላ ትናደድበታለች?
አሃ አሃ ባለፈው ማዕዱን እንዳበላሁት ነግሯት ነዋ... እንደዛ... ጭስስ ብዬ ትቻት ስሄድ
"ለማንኛውም አርግዘሻል!" አለችኝ ስሙልኝ ይመስል እየጮኸች
"ምን?" ብዬ ስዞር
"አዎ አርግዘሻል" አችኝ... ሆዴን አየሁት እንደዛ ነው ሲባል ሰምቼ አውቃለሁ ትዝ አለኝ የሚያቅለሸልሸኝ ነገር...
ለእኔም ሽመል ሳይመዘዝ ብዬ ወደአዲስ አበባ ጠፍቼ መጣሁ...
የማላቀው ቦታ አውቶብዙ አምጥቶ አራገፈኝ... በስተርግዝና ጎዳና ሳድር ያዩኝ የአከባቢው ሰው ተሰባስበው ብር እና እቃ አዋተው ቤት ተከራዩልኝ...
"ትውለድና ስትጠነክር እኔቤት እየመጣች ልብስ ትጠብ እከፍላታለሁ..." ትላለች ሌላዋም እንደዛው
ያልጠበኳትና ያልፈለኳትን ልጅ ወለድኩ... ግን በቃ ከሆነ አይቀር እሷም የእኔን ድኝቁርና እንዳትኖረው ነፍሴንም ሽጬ ቢሆን አስተምራታለሁ አልኝ ዓይኖቿን ሳይ
እሷ ግን በግድ ያንቺን ኑሮ ካልደገምኩ ትለኛለች.... መማር አትፈልግም ምን ጉድ እንደሆነች... ባለመማሬ ሲበሰጨኝ መኖሬ ሳያንስ በእሷ ያለመማር ፍላጎት ሲበሰጨኝ መሞቴ ነው....
ማንበብና መፃፍ እንደቻለችልኝ ሳውቅ... ልጄ ደረሰች አደገችልኝ ስል... ያኔ በነፍሴ እሷን ብቻ አንጠልጥዬ የወጣኋትን ደብዳቤ እንድታነብልኝ ጠርቻት ተቀመጪ ብያት ሳበቃ
አባትሽ እንዲህ ባለጌ ነበር የምላት እየመሰለኝ... እኔ ላይ እንዴት እንደቀለደብኝ እየሰማሁ መድማቱ እያስፈራኝ መልሼ ተይው በቃ እላታለሁ...
ልጄ የእኔን ተማሪ ማለት አትወደውም ይባስ ብላ የእኔን እኩያ አገባች... እኔ አፈርኩ የአከባቢው ሰው ግን ኮራባት... ትናንቴን ያውቃሉዋ... ብሩን የተሻለውን ቤት እንጂ ሒወቷን አላዩማ!
ወለደች ከበደች... መልሳ ቀለለች! የገዛ ልጄ በጥፊ መታኝ ብላ እራሷን ገመድ ላይ አንጠለጠለች... እንግዲህ ምን ቀረኝ ለልጅ ልጄ እንደሆነ.... "አለሁለት!" የሚል ጉረኛ አባት አለው...
እናቱ ስለሞተች ከእኛ ጋር ኑሪ ብሎኝ እነሱ ቤት ገባሁ። ግን የልጄ ጠረን አላስተኛ አለኝ
በሕልሜ እየመጣች...
"ያንቺን ልጅነት የመኖር ግዴታ የለብኝም ነበርኮ!.. ልጅነትሽን ለመኖር መውለድ አይጠበቅብሽም ነበርኮ!
ፀፀትሽን ለምን በእኔ ንስሃ ትገቢያለሽ? አንቺ ያጣሽውን እኔ የማግኘት ግዴታ ነበረብኝ? ለምን እንደዛ እንድኖር አደረግሽኝ?
አንቺ ልጅነትሽን ስትጭኚብኝ... ወላጆችሽ የሆኑብሽን እየሆንሽብኝ ነው!እነሱን እየጠላሻቸው ለምን እነሱን መሰልሽ?" ትለኛለች
አቃተኝ መመለስ አቃተኝ... እሷን መስማት አቃተኝ!
ያቺን ደብዳቤ አወጣኋት... ከግቢ ወጥቼ አንዱን ወጣት ጠሩሁትና አንብብልኝ አልኩት...
ልክ ወሲብ ስንፈፅም እንደሚለኝ "አሉዬ የኔ ዓለም.." ብሎ ነው መፃፍ የጀመረው ገና ካሁኑ ፀፀት አናቴ ላይ ሲወጣ ታወቀኝ...
"አሉዬ የኔ ዓለም... ከክብሬ ጎደልኩልሽ... ከምወደው ድቁናዬ ተሰናከልኩልሽ ግን አልከፋኝም... አንቺ አለሽኝ... ሁሉንም ነገር ነገ አውቶብስ ውስጥ እነግርሻለሁ አሁን ግን ቄስ መሸሻ መምህሮቼን ሰብስቦ አባቴ ጋር ሊመጣ ስለሚችል ጊዜ የለኝም... ነገ ሌሊት ሳፏጭልሽ ውጪ አብረን ወደአዲሳበባ እንጠፋለን... እወድሻለሁ አሉዬ!" ይላል አለኝ...
አለቀስኩ በስተርጅና አለቀስኩ.... ፉጨትኮ ሰምቼ ነበር... የመን ስራ ፈት ነው በዚህ ለሊት የሚያጮኸው ብዬ ዘነጋሁት እንጂ...
አለመማሬ ፍቅሬን ነጠቀኝ... አጉል ቅናቴ እንጂ እንዳለኝ ለምለም ጋር ወስጄው ቢሆን... ፀፀት አንገበገበኝ...
"የኔ ልጅ ላስቸግርህ ጣቶቹ የልቤታ ቀለሙን የከተበበት ወረቀት ላይ ቃሌን ከትብልኝ መፃፍያ ከያዝክ ፃፍልኝ ኸመቃብሬ እንደፎቶ ይለጥፉልኛል" አልኩት.. እየተቻኮለ ከሱቅ ገዝቶ መጣና የነገርኩትን ሁሉ በረቀቱ ላይ ካለው ከፍት ቦታ ፃፈልኝ።
ወረቀቷን ይዤ እንዲህ አስባለሁ...
ያንቺን ልጅነት የመኖር ግዴታ የለብኝም ነበርኮ!.. ልጅነትሽን ለመኖር መውለድ አይጠበቅብሽም ነበርኮ! ፀፀትሽን ለምን በእኔ ንስሃ ትገቢያለሽ? አንቺ ያጣሽውን እኔ የማግኘት ግዴታ ነበረብኝ? ለምን እንደዛ እንድኖር አደረግሽኝ? አንቺ ልጅነትሽን ስትጭኚብኝ... ወላጆችሽ የሆኑብሽን እየሆንሽብኝ ነው ! እነሱን እየጠላሻቸው ለምን እነሱን መሰልሽ?አጋጣሚ ምዕራፍ ፪ ፎቅ ሳይ፦ የቀን ሰራተኞቹ አፈር እንዳልበሉ ሁላ የተማረ ብቻ የገነባው ይመስለኛል.. እዚቹ ጎረቤቴ አስካልዬ ጋር እንኳን ሁሌ ቡና የሚፈላው በጥቂቱ ማንበብ በጥቂቱ መፃፍ ስለምትችል ይመስለኛል። እነስኳር.. እነሥጋ... ሽሮ እንኳን ባቅሟ ያልተማረ ቤት ላለመግባት ትግሏ ትግል አይደለም። ለዘመናት ያፈቀርኩት ፍቅሬን ያጣሁት ባለመማሬ ነዋ... ማህፀኔ እንኳን ሳይቀር ስህተት የሆነው ባለመማሬ ነዋ። "ባበይ ተማሪ ቤት አስገባኝ" ስለው "እኔ በሮችን አጠምዳለሁ... ነገ ደግሞ ሀይላቸው ደቦ ጠርቶናል... ከዚያ በስቲያ ደግሞ የታችኛውን መሬት ጉልጓሎ እጀምረዋለሁ... እናትሽን ጠይቂያት" ይለኛል። ባልበሰለ በሕፃን ልቤ ንድድ እላለሁ... እናትሽን ጠይቂያት ለማለት ይሄ ሁሉ ምክንያት... እየተናደድኩ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ንዴቴ እንዳይወጣብኝ የተቋጠረ የመሰለኝ ቅንድቤን ፈካ ለማድረግ እየታገልኩ ወደ እናቴ እሄዳለሁ... "ታተይ ባበይ ተማሪ ቤት አስመዝግቢያት አለሽ" ስላት "ተምረሽ የት ልትደርሺ? ሁነኛ የቤት መዝጊያ የምታገኚው የቤቷን ስራ ጠበቅ አርገሽ ስትይዢ ነው ልጄ... እኔ እንዲህ አፈር የምበላ ሞያቢስ ለባላባቶች አቶንም ተብዬጂ...." ወደ አባቴ ታጉረጠርጣለች "ወድጄህ እያልሽ እንደአህያ ማሰሮ አዝለሽ አስሬ ወንዝ ስትመላለሺ የነበርሽ አንቺ" ይላል እንደጉራ እያረገው ትከሻውን ሰበቅ እያረገና ትከሻውን አስደግፎ በእግሮቹ መሀል ያሳለፋት በትሩን አንዴ ብቻ በደግ አርጉ መልሶ ከትከሻው እያኖራት። "ኸወንዙ ስትቦጫረቅ ላይህ? ቱ እቴ! (ወደእኔ እያየች) አያትሽ እንዴት ያለች ጠላ ጠማቂ እንደነበረች ብታይ! ለእሷ ውሃ ሳመላልስ ነውኮ እንዲህ የሚለው... ይልቁስ ውሃ ብቻ ስቀዳ በመኖሬ ነው ወጣወጤ አልጥምልሽ ብሎኝ አባትሽ ላይ የጣለኝ... (መልሳ ዓይኖቿን ወደ ባበይ አንከራታ ፈጥና እየመለሰቻቸውና በስሱ ፈገግ እያለች) ሦስት ጣሳ በቅጡ የማትጠጣ ሰውዬ ሠላሳ ጊዜ ቤታችን ስትመላለስ የኖርከው አንተ ምን እኔን ትላለህ!" ትለዋለች። አንድ ሁለት እያሉ ፍቅር በፍቅር ሁነው ይውሉና ሌቱን ሙሉ የባላገር ወሲብ ችብቻቦ ስሰማ እንቅልፍ አጥቼ አድራለሁ። የምበላው ምግብ ከጥርሴ በቀር የሚፈጨው ጨጓራ ያለኝ አይመስለኝም... ሌቱን ሁሉ አስባለሁ... በእኔ ጥያቄ እነሱ ፍቅር ይሰሩብኛል ወይ? እያልኩ ስብከነከን... ስናደድ አድራለሁ። ቆይቼ ቆይቼ ደግሞ "ባበይ የእገሌ ልጅኮ ተማሪ ቤት ገባች" ስለው። "እቺ ኤናትሽ ሌላ አልወልድም አለይ.. እነሱኮ አራት ልጆች አሏቸው... አንቺን ተማሪ ቤት ሰደን... ከማሳው ማን ማዕድ ሊያቅብለን ነው? እናትሽም ደክማለች እኳን ማሳ ልትወርድ የቤቱን እንኳን ካላንቺ በቅጡ አትከውነውም..." እናቴ ትደረባለች.." ሴትን አርባ ከሞላት ቢድሯት እሷም ትዳሯም ከንቱ ይሆናል ኸተማሪ ቤት መስደዱም እንዲሁ ነው... ሴት የቤት የቤቷን እንጂ የምን ውጭ ውጭ ማለት ነው?" ትለኛለች። ታዝዤ ከላይኛው ታችኛው ቤት ከተገሊት ቤት ብረት ምጣድ ሳመጣ ከገሌ ቤት የደቦና የጠበል ቅመሱ መልዕክት ሳደርስ በየመንገዱ ለብቻዬ እብሰለሰላለሁ... የሆነ ቀን ውሃ ልቀዳ ማሰሮዬን አዝዬ ወንዝ ደርሼ ስመለስ ደክሞኝ ከጥላው ከዛፊቷ ስር አረፍ ብል... የተረገመ ንፋስ ወረቀቷን እያንከባለለ አምጥቶ እንስራዬ ስር ለጠፋት... አንስቼ አየኋት ወርቅ እንዳገኘሁ ሁላ አገላብጬ አየኋት.. የሚያምር ጥሁፍ አለው... ምን እንደሚል ማወቅ ፈለግሁ... ስለምን ይሆን የተፃፈው? አልሁ። አፈጠጥኩ.. አፈጠጥኩ.. አፈጠጥኩ... ዋይ.... ብዬ መጮህ አማረኝ... ፊደሎቹን ምን ብዬ ልጥራቸው... እኔ ደ ነኝ... እኔ ቀ ነኝ... እያሉ ቢያወሩኝ...ጓደኞቼ ቢሆኑ.. ለእነሱ ያለኝን ፍቅር ቢያውቁ ብዬ ተመኘሁ... ለመጨረሻ ጊዜ ባለ በሌለ ሀይሌ ለማንበብ ፈለግሁ በሆነ አስማት ባነባቸው አልኩኝ... ግን አቃተኝ ከየት ይመጣል ታዲያ ፍላጎት ብቻ ነበር እንጂ... የዛን ቀን የተሰበርኩት መሰበር በዛፍ አይድረስ! አለቀስኩ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ... ለመጀመሪያ ጊዜ ባበይንና ታተይን የመጥላት ስሜት ተሰማኝ... እነሱ የኖሩበትን እውነት እንጂ እኔ የደረስኩበትን ፍላጎት ባለመረዳታቸው ጣላቶቼ መስለው ታዩኝ.. ይህም እኮ የእነሱ አለመማር ነበር ግን በቃ... ቀለቅሶዎቼ መሀል... አንድ መልከመልካም ጉብል ብቅ አለ... "እንዴ እንዴ አለሚቱ ለምን ታለቅሻለሽ?" አለኝ ከቤተስኪያን እንደመጣ የሚያሳብቅ ነጠላውን ወደላይ ወርወር እያደረገ... እንደዛ ሲለኝ ለቅሶዬ ለቅሶ ብቻ አልሆን አለ.. እግዜሩ ሲቆጣ አይነት መብረቅ ስቅታዬ የማያቋርጥ ሆነ... "በወላዲቷ... ተይ ነውር ነው" እያለ እንባዎቼን አድርቋቸው እንኳን ስቅታዬ አላባራ አለ... "እኔ አባ ካስተማሩኝ የማቃትን ቀለም አስቆጥርሻለሁ እሮብና አርብ ከዚህ ጠብቂኝ" ሲለኝ... ፈገግኩኝ... "አንቺዬ የእውነትም ከፍቶሽ ኑሯል እየሳቅሽም ስቅታው አይወጣልሽ?" ይለኛል.. እሱ አልገባውም አለመማሬ ምን አይነት አለም እንደሰራልኝ... ባገኘሁት ቁጥር የቤተስኪያኑ እጣን ከነጠላው እየቀረ ሽታው ያውደኛል። አለመማሬ እንዲህ ያስመኘኛል.. እኔም ማንበብና መፃፍ ችዬ ከቤተስኪያኑ እጣን በተጣድኩ እላለሁ... ከፆም ውሎ መቶ ቀለም ላስይዝሽ ሲለኝ ያሳዝነኝ ገባ.. የሆነኛው እሮብ ላይ ለባበይ ይዘሽ ሂጂ የተባልኩትን ማዕድ ቀለም ለሚያስይዘኝ ለየኔታ.. አሁን ሲገባኝ ለልቤታ ይዤው ሄድኩኝ.. እናቴ "ወጣወጥሽ ይጣፍጥጂ ከደህናው..." ምናምን እንደምትለኝ.. በማዕዱ ጣዕም ላማልለው ሲዳዳኝ እንደነበር ሁላ ሳስብ እስካሁን እሽኮረመማለሁ። በላይ በላዩ አጉርሼ የልቤንታ አጥግቤ ሳበቃ.. ስንለያይ ሳቅፈው ሲያቅፈኝ.. ጡቶቼ ከደረቱ ሲላተሙ ጭኖቼ ምን አድርጊ እንደሚሉኝ አይገባኝም አጉል ይቆላቸዋል... "ታተይ ማዕዱኮ ተደፋብኝ ውሻ ሲያባርረኝ..." እንባዬ መጣ እንደፈራ ሰው አለቀስኩ... "እና ነከሱሽ? ወይ ልጄን ውይ ልጄን..." ደረቷን ልትደቃ አምስት ጉዳይ ሲቀራት... "አመለጥኳቸው ስሮት ግን አገልግሎ ወድቆ ማዕዱ ተደፋ" አልኳት "ይደፋ በልተንውስ ወደአፈር አይደል የሚሄደው... ውይ ለምለምዬ ሞት ይርሳኝ እቺኮ ቀልቤን ሰርቃው... ምን ስጪኝ ነበር ያልሺኝ?" "ምጣዴ አልሰማ ብላኝ ነው ለማሰሻ የተፈጨ አጉሎ ካለሽ ብላሻለች እናቴ.." አለቻት ለምለም። ለምለም የምቀናባት ጎረቤታችን ናት እሩቅ ሂዳ ቀለም የምትማር.. ሕልሜን የምትኖር እንስት ናታ... ልሸኛት አብሪያት ሰወጣ... "ማን በልቶብሽ ነው ማዕዱን?" አለችኝ እየሳቀች "ኧረ ተደፍቶብኝ ነው!" አልኳት ደንገጥ ብዬ "ኧረ አትደንግጪ እኔኮ ለምለም ነኝ" "አል.. ደነገጥኩም ግን እንዴት እንደሱ አልሺኝ?" አልኳት "አይ ዝም ብዬ ነው ኸላስቲኩኮ ጥርግ ተደርጎ እንደተበላ የሚያሳብቅ መስመር መስመር ሳይ አልተደፋብሽ እንደሁ ብዬ ነው" አለችኝ
ያንቺን ልጅነት የመኖር ግዴታ የለብኝም ነበርኮ!.. ልጅነትሽን ለመኖር መውለድ አይጠበቅብሽም ነበርኮ!
ፀፀትሽን ለምን በእኔ ንስሃ ትገቢያለሽ? አንቺ ያጣሽውን እኔ የማግኘት ግዴታ ነበረብኝ? ለምን እንደዛ እንድኖር አደረግሽኝ?
አንቺ ልጅነትሽን ስትጭኚብኝ... ወላጆችሽ የሆኑብሽን እየሆንሽብኝ ነው ! እነሱን እየጠላሻቸው ለምን እነሱን መሰልሽ? ....More
አንድ ሰው፦ "በእናቷ እና በባሏ በኩል ያለውንም ብታሳየን?" ብሎ ጠየቀኝ
እና እኔም አሰብኩ! ሳስብም አእምሮዬ እብድ ሲሆን አየሁት!
እሺ እፅፋለሁ ሦስት ምዕራፎች እጨምራለሁ... ግን ገፀ-ብሐሪያቱ ስለሚሆኑት እብደት አያገባኝም🫣
@lewi_derest
"ልጁን ጠፍጥፌ ሆዴ ውስጥ አልከተው እኔ.. የነሳህን ፈጣሪ ሂድና ተጨቃጨቀው እኔን ተወኝ" ትለኛለች ከልላ መውለድ ያቃተኝ መስሏት... ፈጣሪ ሰጠ ፈጣሪ ነሣ... ሃሃሃሃሃሃ
እያለ ሲሟዘዝ ለሦስተኛ ጊዜ ማሰብ ቻልኩ... ይሄንን ሰው አጥብቄ ያዝኩት...
እሱም አላሳፈረኝም ቶሎ ቶሎ ያገኘኝ ጀመር... ችግሩ ከእሱ እንዳይሆን ፈርቼ ነበር... አሁንም ግን ፍርሃቴ አላሳፈረኝም።
አንዳንድ ጓደኞቼ እንዳሉኝ የእርግዝና ምልክት እየታየብኝ ገው... ሰውዬው ጋር ደውዬ እንዳመመኝና አብሮኝ ሐኪም ቤት ይዞኝ እንዲሄድ ጠየኩት...
እንዴት እንደሚያደርገኝ ስነግረው... መኪናዋን እንዴት ነድቷት እንደሆነ አላውቅም ስልኩን ሳልዘጋው ቤት ደርሶ ክላክስ አደረገልኝ...
ማርገዜን ሲያረጋግጥ ደስ አለው አሁኑኑ ከዚህ ልጣፊ ቤት ካልወጣሽ አለ... ለእናት ሌላ ቆንጆ ኮንደሚኒየም ተከራየላትና እቃዎችን አሟላላት...
እኔም ምን የመሠለ ቪላ ቤት ውስጥ በስተርግዝናዬ መንጎማለል ጀመርኩ...
የሆነ ቀን እናቴ ልጠይቀኝ እቤት መታ...
"እማ ግን ያኔ ሰፈር ስንለቅ ጎረበረቶችሽ ምን እንዳሉ ሰማሽ?" አልኳት
"ምን አሉ? ምን ሲሉ ሰማሽ?"
"ሴት መውለድ ደጉ... ያወቀችበት እንዲህ እናቷን ከቆርቆሮ ታወጣለች የኔዋ እዚህ ዲዛይን ፋሽን እያለች መርፌ ስትጠቀጥቅ ትውላለች... እያሉ ሲቀኑብኝ ነበር" አልኳት
"ሰው አግኝተው ቀኑብሽ? ቱ! እቴ... የተማረውን አግኝተሽ እንጂ ተምረሽ መሠለሽ..."
ከመማር ጋር ያላት ፍቅር እንዴት ነው ጎበዝ... ተምሬም ይሁን ሳልማር ሀብት ካገኘሁ ምን ትፈልጋለች?
አሁን አሁን እናቴ እያበሳጨችኝ ነው አጉል ካልተማሩ ብሎ ፍልስፍና ምን ሰባተኛ ሰማይ ልትወጣበት ነው? ሆ
እንዲሁ ከእናቴ ጋር እየተነታረኩ ዘጠኝ ወሬን ፉት አድርጌ ሀብት ንብረቴን ወለድኩ... የደግነቱ ጥግ ቁጭ አባቱን የሚመስል ከነቃጭሉ ዱብ አደረኩ።
ልጁን ያየ ጊዜ ተንሰፍስፎ ሊሞት... ጉድ እኮ ነው ሰው በአራት ሰራተኛ ይታረሳል? አራስነቴ ለዘላለም በሆነ ብዬ ተመኘሁ...
እነሱ አልበቃ ብለውት "ሌላ ሰራተኛ እንጨምር እንዴ?" ይለኛል..
ይታያችሁ ከዚህ መቅበጥና መንበላጠጥ ብኋላ የእናቴን ህይወት መድገም የሚባል ነገር ሲታሰብ...
ልጃችን ሦስት አመት ሲሞላው... ነገሮች ቀስ በቀስ መቀየር ጀመሩ... በጊዜ ጊደት ልጄን በመንገዴ የማሳደግ መብቴን ተነጠኩ...
በእራሱ ማህፀን የወለደው እስኪመስል ድረስ.. ልጄን አትቆጪው ይላል...
ብቻውን የወለደው ይመስል... ቢቀብጥስ እኔ አባቱ እያለሁለት ምን ቤት ነሽ ይለኛል...
ጭራሽ ይባስ ብሎ... "ልጄን ይህንን አረክ ያንን አድርግ እያልሽ የምትከታተይው ስራ ፈት ስለሆንሽ ነዋ?" ብሎ አንድ የቀረችውን ሰራተኛ አባረራትና የቤቱ ስራ እኔ ላይ ወደቀ...
አልከፋኝም የተሻለ ኑሮ እየኖርኩ ነዋ እናቴም እየኖረች ነዋ...
የቀፋችው ቀን.. ያልተሻለችው ኑሮ የምትመጣበት ቀን ደረሰች... ቁርስ እየበላን... ደግሞኮ እየነገርኩት ነው ነጭ ልብስ ነው እያየህ ብላ ብዬውነበር...
ሲዝረከረክ በእጁ የያዘው ጉርሻ ልብሱ ላይ ወደቀ.. ተናደድኩ እንዴት አድርጌ እንደማጥበው እኔ ነኝ የማውቀው...
"ቅያሬ እንኳን የለህም ምን ሸሚዝ ለብሰህ ልትሄድ ነው?" ብዬ ሪሞቱን ቀምቼ ቴሌቪዥኑን አጠፋሁበት...
ልጄ! አዎ የገዛ ልጄ ምናገባሽ ብሎ በጥፊ መታኝ... ይሄ ሁሉ ያባቱ ስራ ነው... ደንግጬ ወደ አባቱ አፈጠጥኩ..
"ምን ታይኛለሽ እውነቱን እኮ ነው እኔ አባቱ አዲስ ሸሚዝ እገዛለታለሁ.." አይለኝም...
ትዳር መስርቼ ልጅ ወልጄ ለ26 አመት የኖርኩባት ዓለም ለሁለተኛ ጊዜ እንግዳዋ እንደሆንኩ ተሰማኝ.. በአሁኑ ግን መንቃት አይደለም ይልቁኑ ማንቀላፋትን መረጥኩ።
ቁጭ ብዬ አሰብኩ... ቀድሞ ነገር ብር እንጂ ልጁን ፈልጌ አልወለድኩትም... እንደ እናት አይደለም እንደ ሰራተኛ እንኳን ሳያከብሩኝ የሚበሉትን ሳበስል... የሚለብሱትን ሳጥብ... መኖሪያቸውን ሳፀዳ..
እንዴ?!.. እንዴ?!.. ለአራተኛ ጊዜ አሰብኩ.. የእናቴን ኑሮ እየኖርኩ ነው!
እናቴ እና አባቴ ለመውለድ ሳይማከሩ ነው ባጋጣሚ የተወለድኩት...
ነገውን አውቆ የሚኖር ሰው የለም። ነገ አጋጣሚ ነው! በቃ በአጋጣሚዎች የተገነባ ብቻ! የነገ መልኩ ግን ትናንትን ይመስላል ልበል?... ትናቴን የሚመስል ነገ ላይ ደረስኩ እኮ!
የእናቴ ፍልስፍና አሸነፈኝ.. ባለመማር ውስጥ አለመኖር ብቻ ነው ያለው.. ባለመማር ውስጥ የተሻለ ሕይወት ሳይሆን የተሻሀ አለመኖር ነው ያለው... ስለዚህ ለምን እኖራለሁ?
ከዚህ በላይ ላወራችሁ አልችልም ምክንያቱም አንገቴ ላይ ገመድ አጥልቄ የረገጥኩትን ወንበር ለቅቄ በመንጠልጠል ላይ ነኝ....
✍ሌዊ
@lewi_derest
እናቴ እና አባቴ ለመውለድ ሳይማከሩ ነው ባጋጣሚ የተወለድኩት። ነገውን አውቆ የሚኖር ሰው የለም። ነገ አጋጣሚ ነው! በቃ በአጋጣሚዎች የተገነባ ብቻ! የነገ መልኩ ግን ትናንትን ይመስላል ልበል?በአጋጣሚ "ዞር በይ ከፊቴ አንቺ መናጢ!" "እህ እማ ደሞ... አስተማሪውኮ..." "ዞር በይ ብዬሻለሁ ዛሬ... ውዳቂ! እንደእኔ የማንንም እከክ ስታራግፊ ትኖሪያታለሽ ምን ገዶች ኋላ!" "ለምንድነው ሁሌ እንደዚህ የምትናገሪኝ? እህ... ይከፋኛልኮ! እኔ ውለዱኝ ብያችኋለሁ እንዴ እንደዚህ የምታሰቃዬኝ!" "እኛስ ተወለጂ ብለንሻል? ክፉ ቀን ላይ ጥሎኝ ባጋጣሚ ተረገዝሽ እንጂ..." አን..ድ በሉልኝ! በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ስቅስቅ ብዬ ያለቀስኩበት ቀን ይሄ ቀን ነው። ከትምህር ቤት የውጤት ካርድ ከእናቴ ጋር ተቀብለን ስንመጣ ሰባተኛ ክፍልን ለሦስተኛ ጊዜ መውደቄን ስታውቅ ነበር እንደዚህ የተናገረችኝ። እሺ ቆይ እኔ ምን ላድርግላቸው?... ስድስተኛ ክፍል እያለሁ አልፍ አልፎ የምሰማት x ሰባተኛ ክፍል ከመግባቴ በአስተማሪ አስጠመደችኝ... ይሄው እየተከታተለ እኔ ያለሁበት ክፍል ስም ጠሪ እየሆነ ያስወድቀኛል። ኬሚስትሪ ገብታ በስሱ ነካክታት ስትወጣ ፊዚክስ ይገባል... ምኑንም ሳልጨብጠው x,x,x እንዳለ ይወጣል ከዛ ማትስ ከመግባቱ በቅጡ እንኳን ሰላም ሳይለን... "2x +...."ምናምን ብሎ ይጀምረኛል ሆ...እኔ የx ነገር ግራ ግብት ብሎኝ ስተክዝ ስተክዝ... አስተማሪው "የxን ዋጋ ፈልጋችሁ ኑ.. የቤት ስራ ነው.. ደግሞ አምስት ማርክ አለው" ይላል አምስት ጣቱን እያሳየ... ወይ ጉድ x የቤት ስራም ትሆናለች? እሺ አሁን ምን ብዬ ነው የምፈልጋት? እቃ እያጠብኩ? ቤት እያፀዳሁ? ለነገሩ ምን አለፋኝ እማዬ ከእኛ አልፎ የሰው ቤት ውስጥ እራሱ ትሰራ የለ.. ከምፈልግ xን የት እንዳየቻት እጠይቃታለሁ... ወይ ደግሞ እነ አብርሽ ቤት ለቡና ስለምትሄድ.. አብርሽ የክፍላችን ሰቃይ ተማሪ ነው... እሱ xን የት እንደሚፈልጋት እይልኝ እላታለሁ... ብዬ እንዳልኩት ስጠይቃት... "የምን x አመጣሽብኝ ደግሞ?" ትለኛለች "አስተማሪው ነዋ የxን ዋጋ ፈልጋችሁ ኑ.. የቤት ስራ ነች አምስት ማርክ አላት ብሎን" የኔ ምስኪን እናት "እኔ አላቅልሽም ብቻ ቅድም በእቃ ማስቀመጫው ስር የሆነ ነገር ሲወድቅ ሰምቼ ነበር እሱ ከሆነ ሂጂ እስኪ እይው..." ስትለኝ እኔ የእናንተ ሞኝ ሂጄ መፈለግ... ምን አገኘሁ? ጣራና ግድግዳዋን በቆርቆሮ ካዘመመች ቤታችን የተነቀለ ሚስማር... እሱን ይዤ መሄድ... ደግሞኮ በኩራት ደስ ብሎኝ... ገና ከመግባቱ "ቲቸርዬ xን እኮ ፈልጌ አገኘኋት" አልኩት... "ሌሎቻችሁስ ሰራችሁ?" ብሎ ጠየቀ የእኔን እንዳልሰማ ሁሉ.. ሲመስለኝ ግን ለካ ጎበዝ ተማሪ መስዬው ነው። አንድ ሁለት ተማሪዎችን ጠየቀ... የማይገባኝን መደመርና መቀነስ... የሌሉ ቁጥሮችን ከየት እንዳመጧቸው አላውቅም መደርደር ጀመሩ... አስተማሪው ልክ አይደላችሁም ሲላቸው ደስ አለኝ... እነዚህ ሞኝ ናቸው እንዴ የቤት ስራ ነው ብሏቸው እዚህ በቁጥር ይፈልጋሉ እንዴ? ነበር ያልኩት ጉዴን አላወኩ። "አንቺ ነበርሽ መልሱን አግኝቼዋለሁ ያልሺኝ?" አለኝ ተስገብግቤ አዎ አልኩት... "እሺ የx ዋጋ ምንድነው ተነሺና አሳይን" ብሎ ቾክ የያዘ እጁን ዘረጋልኝ... ቾኩን ለምን እንደሰጠን እኔም ለምን እንደተቀበልኩት አላቅም ብቻ በክፍሉ ውስጥ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ሲጨበጨብልኝ እያሰብኩ ደስ ብሎኝ ጥርስ በጥርስ ሁኜ በእጄ እያፍተለተልኩ ጨብጬ የያዝኩትን ሚስማር ወደላይ ከፍ አድርጌ... "ይሄው ቲቸርዬ xን ስፈልግ ያገኘሁት መልስ" አልኩኝ ሞቅ ያለ የተማሪዎች ሳቅ ሞቅ ካለ ጥፊ ጋር... ሠማይ ከምድሩ ተደበላለቀብኝ... እኔኮ ልቀልድበት አልነበረም... አስተማሪው ግን "እንኳን አንቺን ስንት ጎረምሳ አስተምረናል... እንደቀለድሽብኝ በዕድሜሽ እቀልድብሻለሁ!" አለኝ ኧረ እኔኮ... ብል የሚሰማኝ ጠፋ... እንደዱርዬ ታየሁ... ተቆጠርኩ... ስመ ዱርዬ በሴት ሲሆን ይብሳል... ሱሪ እንኳን በቅጡ አርጌ የማላቅ ሴትዮ መንደር ለመንደር ከሚያጨሱት እኩል ተሰደብኩ....መምህሩም በዛች አለማወቄ ቂም ይዞ ለሦስተኛ ጊዜ ስም ጠሪዬ ሁኖ ጣለኝ.. እንዳለው በእድሜዬ ቀለደብኝ... እናቴ በአጋጣሚ ነው የወለድኩሽ ማለቷ ግን ውስጥ ውስጡን በላኝ... ያ ደነዝ ጭንቅላቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይኖቼ የዕንባ ፀበል ተጠምቆ ማሰብ ጀመረ... ትምህር እንደዛ እንዳልነበር ገባኝ.. እራሴን ሳስበው ሌላ ዓለም ውስጥ ነበርኩ እንዴ? እላለሁ.. እንዴት በዛ ልክ የማላገናዝብ ደደብ ሆንኩ እላለሁ... እናቴስ እሺ ከነጭራሹኑ አልተማረችም እኔ ግን... ያስለቀሰኝ በአጋጣሚ መወለዴን ማወቅ አልነበረም... 17 አመት ሙሉ የኖርኩባት ዓለም ላይ እንደ ጨቅላ ሕፃን አሁንም እንግዳ መሆኔ ሲገባኝ እንጂ... እናቴ መከራ እንኳን የታየኝ አሁን ነው... ይሄ ለእኔ ከባድ ነገር ነው... አሁን ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማኝ ታቃላችሁ? አለ አይደል የሆነ በጣም የሚያስፈራ ህልም እያያችሁ ደንግጣችሁ ስትነቁ የሚሰማችሁ... እንደሱ አይነት ስሜት ይሰማኛል... አላውቅም ብቻ እንደዚሁ እንዳለሁ ትልቅ ሁኜ የተወለድኩ... ድንገት ነገሮች ባንዴ የተገለጡልኝ መስሎ ነው የሚሰማኝ... ለእናቴ የተቀየረ ነገር የለም... እንደድሮው ታመናጭቀኛለች... "እናቴ ትምህርት ለእኔ አልተፈቀደም ስራ ልጀምር እያሰብኩ ነው" አልኳት... ይሄኮ ማሰብ ስጀምር ያሰብኩት የመጀመሪያ ሀሳቤ ነበር! እሷ ግን... "ወፍ እንደዘራው እህል ካለጊዜሽ ተወልደሽ የእኔን ሕይወት ያመሳቀልሽው አይበቃም? የእናትሽን ኑሮ መኖር ነው የምትፈልጊው?" ትለኛለች። የእናቴ ኑሮ ምን አይነት ነው? ለመታዘብ እሞክራለሁ... ከእማውራነት ጎድላ የአባውራውን ቤት የምታፀዳ ልብስ የምታጥብ ምስኪን የቀን ሰራተኛ ናት... አእናስ! ቦለኬት መሸከም ወይም ጉድጓድ መቆፈር ብቻ ነው እንድ ታዲያ የቀን ሰራተኛነት... የእናቴን ህይወት መድገም አስፈራኝ... በድንገት ሀብታም የምሆንበትን ነገር ፈለኩ... በቃ እናቴን ከዚህ ሕይወቷ ጎትቼ የማወጣበት አንድ የማርያም መንገድ ማግኘት ተመኘሁ... እንደወንዱ ጥሬ ግሬ እንዳልል አልሆንሽ አለኝ.. በሴት አቅም ልሰራ የምችለው የእናቴን መሰል ስራ ነው... አልተማርኩማ! ከመማር አይቆጠርም መቼስ... ማሰብ ከጀመርኩ ሁለተኛ ሀሳቤን አሰብኩ.. ለእናቴ ግን አልነገርኳትም... እሷ ስላልተማረች ሸው ሁሉ የበለጣት ሰለተማሩ ይመስላታል.. እኔም እንድማር ብቻ ነው የምትፈልገው.... በሁለተኛው ሀሳቤ መሠረት.. ሀብታም ወንዶችን መፈለግና ማጥመድ ከዛ አንዱን አግብቼ እናቴን ማሳረፍ... ያለመማር ፍልስፍናዋን ማረምና ባለመማር ውስጥም የተሻለ ኑሮ እንዳለ ማሳየት... ትግሌ ከኑሮ ጋር ብቻ ሳይሆን ከእናቴ አስተሳሰብ ጋርም ጭምር ነዋ። አንዱ ይመጣል ይሄዳል.. ደግሞ ሌላኛው.. በቃ ባለሀብቱ ሁሉ አግብቶኝ ሕይወቴን የሚቀይር ሳይሆን ለቀን ደስታው ብቻ የምገኝለት ሴት እንድሆንለት ይፈልጋል። ለጊዜው ሕይወት ባይቀይርም ግን የተሻለ ብር ስለሚሰጡኝ ከቀን ደስታቸው አላጎድላቸውም ነበር... የሆነ ቀን አንዱ ባለሀብት ጥብዝ ብሎ ሰክሮ... "ለምን ሚስቴ ላይ እንደምማግጥባት ልንገርሽ አይደለም... ልጅ ስላልወለደችልኝ ነው... ፈጣሪ የረገማት ሴት...ስለሆነች ነው.. እኔ በልጅ ናፍቆት ተቃጠልኩኩ እሷ ግን...
እናት እና አባት ለመውለድ ሳይማከሩ ነው ባጋጣሚ የተወለድኩት።
ነገውን አውቆ የሚኖር ሰው የለም። ነገ አጋጣሚ ነው! በቃ በአጋጣሚዎች የተገነባ ብቻ! የነገ መልኩ ግን ትናንትን ይመስላል ልበል? ....loading
ጋሽ ስብሀትን የምወዳቸው በአንድ ነገር ብቻ ነው.. ከእራሳቸው የሚደብቁት ቃል የላቸውም.. ሁሉንም ቃል ለስነ-ፅሁፋቸው ይጠቀሙበታል!
ማስረጃ ከፈለጋችሁ፦ ትኩሳት ገፅ 153
@lewi_derest
