fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ደራሲው...∞

ደራሲው...∞

رفتن به کانال در Telegram

በአጫጭርና እረዥም ልብ ወለዶች፦ ሳይኮሎጂንና ፍልስፍናን የሚኮመኩሙበት ቻናል እነሆ!

نمایش بیشتر
2 070
مشترکین
+124 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+8830 روز

در حال بارگذاری داده‌ها

کانال‌های مشابه
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26
اکتبر '26
+147
در 4 کانال‌ها
سپتامبر '26
+567
در 4 کانال‌ها
Get PRO
اوت '26
+171
در 4 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '26
+143
در 6 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '26
+299
در 9 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+65
در 1 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+103
در 4 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+102
در 2 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+89
در 4 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+170
در 22 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+90
در 1 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+130
در 5 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+28
در 1 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '25
+36
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '25
+73
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '25
+45
در 3 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '25
+53
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مه '25
+67
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
مارس '25
+64
در 2 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '25
+93
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '240
در 1 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '24
+23
در 1 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
29 اکتبر+1
28 اکتبر+1
27 اکتبر+2
26 اکتبر+1
25 اکتبر+3
24 اکتبر+3
23 اکتبر+1
22 اکتبر+5
21 اکتبر+5
20 اکتبر+5
19 اکتبر+2
18 اکتبر+3
17 اکتبر+6
16 اکتبر+7
15 اکتبر+7
14 اکتبر+9
13 اکتبر+13
12 اکتبر+3
11 اکتبر+7
10 اکتبر+5
09 اکتبر+7
08 اکتبر+6
07 اکتبر+5
06 اکتبر+11
05 اکتبر+11
04 اکتبر+3
03 اکتبر+5
02 اکتبر+4
01 اکتبر+6
پست‌های کانال
ይብላኝ ወፍ ዘራሽ ነህ ብላ ጥላኝ ለሄደች! እኔስ ወፏ በመልካሙ መሬት ላይ ዘራችኝና መቶም ስድሳም ሠላሳም አፈራሁ! ገና የልጅ ልጆቼ በክብር የሚጠሩበትን የዘር ሀረግ ነው የምገነባላቸው!
✍ሌዊ
ገፀ-ብሐሪያት ያስፈልጉት ይሆን🫣?
@Lewi_derest

2
🖋️ የህላዌ ብዕር ግጥም ለልብ፣ ቁምነገር ለአእምሮ፣ ቀልድ ለፈገግታ! በአንድ ቦታ ስሜትን የሚነኩ ጽሑፎች፣ የሚያስተምሩ ወጎችና የሚያስቁ ታሪኮችን ያግኙ። አንድ ጊዜ ገብተው ይመልከቱ፤ ምናልባት የልብዎን ቋንቋ እዚህ ያገኙ ይሆናል! 🔗 አሁኑኑ ይቀላቀሉ፦ https://t.me/poem_Hiwe የህላዌ ብዕር — ለስሜት፣ ለሐሳብ፣ ለፈገግታ!
597
3
The Night Shadow ሦስተኛ መፅሐፋችንን ጀምረናል ሰዎች! ከበቀለኛው.. ከፖሊሶቹና ከተጠቂዎቹ እኩል ግራ መጋባት ውስጥ የምትታገሉበት ምርጥ Psychological Thriller & Mystery
The Night Shadow ሦስተኛ መፅሐፋችንን ጀምረናል ሰዎች! ከበቀለኛው.. ከፖሊሶቹና ከተጠቂዎቹ እኩል ግራ መጋባት ውስጥ የምትታገሉበት ምርጥ Psychological Thriller & Mystery መፅሀፍ ነው የሚሆነው! በነገራችን ላይ "ሕያው ሞት"ን እያነበባችሁ ያላችሁ ሰዎች እስከሰኞ ቶሎ ጨርሱ... አንዳንድ ሀሳቦችንና ታሪኮችን አስተካክዬለት... የአእምሮ ንብረት ጥበቃ የምስክር ወረቀት ስላወጣሁለት ከሰኞ ብኋላ ከምዕራፍ ፫ ጀምሮ በከፊል ወይ በግማሽ ላጠፋው እችላለሁ ✍ሌዊ @Lewi_derest
714
4
OALE 17 Pro max 128/8 Dual SIM Price 12,000 Contact 0978283982+1
OALE 17 Pro max 128/8 Dual SIM Price 12,000 Contact 0978283982
630
5
Mesay_Tefera_Dehna_Yigtemesh_ደህና_ይግጠምሽ_New_Ethiopian_Music_2024.m4a
1 159
6
አንቺ ልጅ ነግሬሻለሁ ፍቅር ለወጣትነት እንጂ ለኑሮ አይሆንም.. የእኔስ ተበላሽቷል ሳይብስበት እገላገለዋለሁ እንጂ... እዪለች እያጉረመረመች ትሄዳለች... አባቴ እናቴን ይፈራታል ስልህ ገርሞህ ነበራ? ወንድነት ጎድሎትኮ አልነበረም... ግን እሷ እንደምትፈልገው ሀብታም ባለመሆኑ ስታሳቅቀው አቅም አጣ.. የእሷ እንጂ የእሱ ፍቅር ገና አላለቀም ነበር... እና ሊረዳት ስለሚሞክር.. ስለምታሳዝነው ነው የሚሽቆጠቆጥላት... እናቴ ለምን እራሷን እንዳጠፋች እኔም አባቴምእናውቃለን... እነዛ ለእናቴ ባለቀስኳቸው ስድስት ወራት ውስጥ የእናቴን ሕይወት ላለመድገም ስምል ስገዘት ነበር... አንተ ግን በድንገት መሀላዬን ሰበርከው.. እንደ ክርስቶስ ሕጌን በፍቅር ሰበርከው... እኔ ግን ይሁዳ ነኝ ወደሕጌ ተመለስኩ ፍቅርህን ሸጥኩት..." ከተንተራስኳቸው ጭኖቿ መነሳት ባልፈልግም እየተነሳሁ "ተይ እንደሱ አትበይ ያንቺ ጥፋት አይደለም አባትሽ ነው እሱንም ቢሆን ተረድቼዋለሁ እንደሚስቱ እንዳትሆኚ..." "አይደለም! አይደለም! መስ ልትሰማኝ ይገባል እውነቱን መናገር አለብኝ... አባቴ አይደለም ያንን ያሰበው አባቴ ያመጣልኝ ሀብታም የለም እኔው እራሴ ነኝ ላገባው ነው ብዬ ለአባቴ ያስተዋወኩት... በቃ እነሱ ልክ ናቸው! አባቴን አስገድጄው ነው... እሱ እንዳውም ምን እንዳለኝ ታውቃለህ? "እናትሽ ያልኖረችውን ሌላኛውን መጥፎ ምዕራፍ ልትኖሪው ወሰንሽ? እናትሽን ማዳን አልቻልኩም አሁን ደግሞ አንቺን" አለኝ  እኔ ግን እንቢ አልኩት..." "ውሸትሽን ነው!" መልሼ ጭኖቿ ላይ ልንተራስ ዘመም ስል.. በእጆቿ ጭንቅላቴን እየገፋች "መስ እውነቴን ነው... ስለፈራሁ ነው.. እንደእናቴ የምሆን መሠለኝ... እኔም ልጄን በገዛ ፀፀቴ የማሰቃያት መሠለኝ... እራሴን ስገድል ማሰብ ፈራሁ.. በቃ ፍርሃቴ ከፍቅርህ ገዘፈብኝ..." ተነሳሁ ትቻት ሄድኩ... "መስ... መስ... ይቅርታ ልልህ አይደለም ግን ያንተን እሩቅ መልስ ስትደርስበት ግን ለመስማት ዝግጁ ነኝ ሙቼ ቢሆንምኳን.. ሰማኸኝ መስ... መስ..."  ድምጿ እየራቀእ እየራቀኝ መጣ.. ትቻት ሄድኩ... ተናደድኩ በእራሴ ተናደድኩ.. እንደእናት ሲያደርጋት በነበረችው አሮጊት ተናደድኩ... በሯንና መስኮቷን ሰባብሬላት ወጣሁ... ሌላ ቤት ተከራየሁ... እህቴ ያስመዘገበችኝ ውድድር በቴሌቪዥን ስለሚተላለፍና በጣም ጥሩ አካሄድ ላይ ስለነበርኩ ትልልቅ ቤቶች ላይ ስራ አገኘሁ... ጥሩ ቤት ጥሩ ገቢ አለኝ.. ውድድሩም መጨረሻው ላይ ደርሶ አሸናፊው የሚለይበት የመጨረሻው ውድድር ላይ ነኝ በሯን አንኳኳሁ... ልጇ ነበረች የከፈተችልኝ... አይገርምም ልክ ምናቤ ውጥ እንዳለችው ናት.. የሆነ አባት የሆንኩ ልጄ የሆነች ከሠላሜ የወለድኩ መስሎ ተሰማኝ... ግን እንደማይሆን ግልፅ ነው የረዠም ጊዜ የምናቤ ቅዠት ስለነበር ነው... "እናትሽ አለች ሚጣዬ..." "አዎ አለች ማሚ..." እየጠራቻት ትታኝ ገባች... "ጠይቀሽኝ ነበራ እሩቁ መልሴ ጋር ስደርስ እንድነግርሽ.." በጭንቅላቷ አዎንታዋን ገለፀችልኝ ልታለቅስ እየዳዳት... "ነገ የአሸናፊዎች ውድድር አለብኝ መልሱን መስማት ከፈለግሽ መምጣት ትችያለሽ" ብዬ መጥሪ ወረቀት ሰጠኋት። እህቴ ምን ብላው እንደሆነ አላውቅም አባቴም ውድድሩን ለመመልከት መቶ ነበር... ግጥሙም ዜማውም እኔው ስለሆነና ሰምተውት ስለማያውቁ ዳኞቹ እንዳይጥሉኝ ፈርቻለሁ ግን ደግሞ ስሜቴን ነው የምዘፍነው... ተራዬ ደረሰና ማይኩን ጨበጥኩ... "ልሰማ አልጓጓሁም እንዴት እንደመጣ ስህተት.. ሆነ ምን ያደርጋል ቃልሽ ላይቀይረው እውነቱን! ተይው ምን ያደርጋል ይቅር.. ጊዜ ያልፈቀደው ፍቅር! እኔማ ፈራሁት ሁኔታሽን ሁሉ ሲወራ.. የሰው አፍ እንዲህ ነው ጠብቂ እራስሽን አደራ! ምንም ባላቆይሽ ከኔ.. ክፉሽን አልየው ባይኔ! ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ደጁን አያምንምና ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ልቡን አያምንምና... የሄደን ሰው ምን ይሉታ.. ከራስ አልፎ ለማን ይወቅሱታል! እውነቱን አውቄ.. ህመሙን ደብቄ.. ልኑረው ዝምታን ሰንቄ! ልጠይቅሽ ሁሉን ሲቻል.. ኧረ እንዴት ነው መለየት የሚቻል? ልኑር ስንት አመታት.. የሰጠሽኝ ብርታት.. ቢሰጠኝ ፍቅርሽን ለመርሳት! ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ደጁን አያምንምና ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ልቡን አያምንምና... ቀናት አልፎ ቀን ሲተካ.. ልብሽማ ከኔ ርቋል ለካ! አላወኩም ነበር.. ይህ ሁሉ ሲፈጠር.. የፍቅራችን ፅዋው ሲሰበር! በወደደው ሰው ሲገፋ.. የሞት ያህል ሀዘኑ ቢከፋ! ስሜት እየጎዳ.. ቢሰጥም ለስቃይ. አይሆንም ከይቅርታ በላይ! ሌላው ሌላው ነገር ይቅር.. አይነገር ይሁን ያልፋልና ብቻ.. ሁኚ ደህና! በሄድሽበት ክፉ አይንካሽ.. የቀረበሽ ርቆ አይጉዳሽ! ሌላ ሌላው ነገር ይቅር.. አይነገር ምንም ቢኖር ጥፋት.. አልይ ያንቺን ጉዳት.. ልብሽ ወዶ ሰው አይጣ.. ላንቺ አይስጥሽ የኔን እጣ! ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ደጁን አያምንምና ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ልቡን አያምንምና..." ለእሷ ብዬ ነበር አዝማሪ የሆንኩት.. እሷም ይሄ ስለሚገባት ዓይኖቼን እያየች አዝማሪ አላገባም ማለት ከብዷት በአባቷ አንደበት ተናገረችኝ... ያልዘጋነው አንድ ነገር ነበር... እሱም እኔ ፍቅር ሲይዘኝ እንዴት እንደምገልፀው ማሳየት ነበር ደህና ይግጠምሽ ብዬ አሳይቻታለሁ.. ከእንግዲህምን ቀረኝ? ✍ሌዊ @Lewi_derest
1 087
7
ፍቅራችን ለምለም ነበር.. ንፁህ አየር የሚወለድበት ንፁህ የተፈጥሮ ፍቅር... እዛች ቦታ ፍቅር ካልሰራን ተራራና ሜዳው የሚደርቅ እስኪመስለኝ ድረስ በፍቅራችን ተመካሁ... ላፕቶፔንና መፅሀፎቼን ጥዬ ጊታርና ማይክ ሳነሳ  አባቴ ከቤት አባረረኝ... አሁን መዝፈን ብቻ ሳይሆን መስራትም ግድ ሆነብኝ.. የምሽት ቤት ውስጥ መዝፈን ጀመርኩ.. በቂ ባይሆንም የቤት ኪራይና ሠላምዬ እቤት ስትመጣ ለምታፈላው ሻይ ይሆናል... የሆነኛው ቀን ላይ የምላቸው ብዙ ናቸው.. ከእነዚል ብዙ የሆነኛው ቀኖቼ መሀል የሆነኛው ቀን ላይ ሠላሜ ደወለችልኝ "መስ... ቶሎ ና ድረስልኝ አባቴ ለሀብታም ሊድረኝ ነው..." ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ነገረችኝ... ሄድኩኝ ስሮጥ ስበር ሄድኩኝ... አባቷ ምን የሚያክል ዱላ ይዘው... "ልጄን ትነካና ውርድ ከራሴ! ጭራሽ ላዝማሪ ልጁን ዳረ ልታስብለኝ ነው?.. ዞርበል ብዬሀለሁ... በየበረንዳው አፍ ሲከፍቱ ማደር ሞያ መስሎሀል..."አባቷ ውሻ አርገው አባረሩኝ... ተሰማኝ በጣም ተሰማኝ... ሠላምዬ እያየኋት መኪና ውስጥ ገብታ በረረች... አከራዬ በጣም ጥሩ ሴት ናቸው የቤት ኪራይ ከከፈልኩ አመት ሊሆነኝ ነው.. እሳቸው ግን እንኳን የቤት ኪራይ... ከቦታችን ውዬ ስመጣ ምግብ ሁሉ ቤቴ አስቀምጣ ትጠብቀኝ ነበር... በመንገድ ልጆች ሲያዩኝ ፈርተው ይሮጣሉ ፀጉሬና ፂሜ አድገው ጥቁር ጥርስ እንጂ ፀጉር አይመስሉም ነበር... አንዳንዴ በሕፃናቱ ፈንታ ትላልቆቹ ምናለ ፈርተውኝ ቢሸሹ ብዬ እመኛለሁ... እኔን ሲያዩ ከከንፈር መጠጣቸው ቀጥሎ ሠላምዬን ያሙብኛል... "ሠላም በል ብላው እንጂ አቶ መላኩ እንዲህም የሚናገር አይደለም..." ሌላኛዋ ተቀብላ.. "ኧረ ስንቴ ከባለመኪናው ጋር ስትንዘላዘል አይቻታለሁ.. ሁሌ አይደል እንዴ መታጠፊያው ድረስ የሚሸኛት..." እኔ ከልቧ ስታለቅስ አይቻታለሁኮ ይሄ ከእነሱ ሀሜት አይበልጥም? የእኔ ሠላም እንዲህ ታረጋለች?... ሲያወሩ በሰማሁበት ስፍራ ተዘርፍጬ እነፋረቃለሁ... ብያችኋለሁ የሆነኛው ቀኖቼ ብዙ ናቸው.. የሆነኛው ቀኔ ላይ እንዲሁ ሠላምዬን ሲያሙብኝ ሰምቼ ናፍቃኝ በጣም ናፍቃኝ... በየመንገዱ ስነፋረቅ... እህቴ እንደዚህ ትልቅ ሁና አላቃትም... ከየት እንደመጣች እኔጄ በጥፊ ሦስቴ አራቴ አላቅም ብቻ ፊቴ ላይ አጨበጨበችብኝ... "መሣይ ደከመኝ... እኔምኮ የሚጠብቀኝ ሕይወት አለኝ... እስከመቼ ነው ላንተ እያዘንኩ ባንተ እየተሰቃየሁ የምኖረው?" "እነዚህን ሰዎች አየሻቸው? ልክ እኔን ሲያዩ ነው ሀሜት ትዝ የሚላቸው.. አንቺም እንደ እነሱ ነሽ! ዛሬ ባጋጣሚ በመንገድ ብታገኚኝ አታስመስይ.." "ጥሩ ከዚህ ብኋላ የቤት ኪራይ ማን እንደሚከፍልልህ እናያለን.. ምን እንደምትበላም ጭምር... ያንተ ነገር በቅቶኝ ነበር.. ጥሩ በል ደህና ሁን" ያቺ አሮጊት ለካ ደግነት አልነበረም... ለካ ጨለማዬ ጭላንጭልም ብትሆን ብርሃን ነበራት.. ዛሬ ግን እሷም ቀልጣ አለቀች የእህቴ ጥፊዎች ልከኛ ሳይሆኑ አይቀርም እራሴን ታዘብኩት... አውቃለህ ህመሜን ማዳን አልችልም ግን ቢያንስ ከህመሜ ጋር መኖርን መልመድ አለብኝ... እህቴን በመንገድ ጠብቄ እንድታግዘኝ ጠየኳት እራሴን በትንሹም ቢሆን መቀየር እንደምፈልግ ነገርኳት... በነጋታው የተወሰኑ ልብሶችን አመጣችልኝ "የፍቅረኛዬ ነው እሱም እንዳንተ ግርማ ሞገስ ያለው ስለሆነ ልብሶቹ አምረውብሀል" አለችኝ... ከፍቅረኛዋ ጋር ፀጉር ቤት ገባን... ሁሉ ነገሬ የዳነ መሰለ ዓይኖቼ ግን የቀረ የማይሽር ህመም እንዳለ መደበቅ አቃታቸው... "ከነገ ወዲያ አንድ የሚመረቅ ሆቴል አለ.. እና እነሱ የመድረክ ዘፋኝ ስለሚፈልጉ አውርቼልህ ከባንዱ ጋር መቶ ይለማመድ ተብሏል... ከዛ በተጨማሪ እኔ በወንድሜ ስለምኮራ የድምፅ ውድድር ላይ አስመዝግቤሀለሁ.." አለችኝ እህቴ ደስ እያላት... በምርቃቱ ላይ የታደሙት ሰዎች ሁሉ ድምፄንና የዘፈን ምርጫዬን ወደዱት... እኔ ግን አልወደድኩትም.. ግድ ሁኖብኝ እኝጂ ለሠላሜ ለፍቅሬ የሚሆን ዘፈን መዝፈን ነበር ፍላጎቴ... "ዕረጋ ከማለቱ በቀር ድምፅህ እንደድሮው ውብ ነው..." ይሄን ድምፅ ማመን አልቻልኩም... ዓይኖቼ ብቻቸውን ወደኋላ የዞሩ እስኪመስለኝ አንገቴ ፍጥነቱ... አዎ እሷ ናት ሠላሜ ናት! "መስ ባለቤቴና ልጄ እየጠበቁኝ ነው ግን ስላንተ ስሰማ በጣም ተፀፅቼ ነበር.. እንደዚህ ሁነህ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል ግን ልነግርህ የምፈልገው ነገር አለ... ሰፈር ውስጥ የሚወራው ነገር..." "ሹሹ.. ዝም በይ ተያቸው ያውሩ... አንቺም አታስረጂኝ አትንገሪኝ ሂጂ በቃ ኑሮሽን ኑሪ..." ልጅ መውለዷን መስማቴ ሙሉ በሙሉ ስሜቴን ቀይሮት ነበር... ከእሷ የመውለድ ህልም ነበረኝ... ቦታችን ላይ ቁጭ ብዬ ስተክዝ ሠላሜ ያለችኝ ነገር ትዝ አለኝ... "ስሜታችንን ነው የምንዘፍነው!" አዎ ስሜቴን መዝፈን አለብኝ... እስክሪብቶና ወረቀት ከቦርሳዬ አወጣሁ ፃፍኩ ከተወሰኑ ስንኞች ብኋላ ግጥም አልመጣልህ ሲለኝ ላሉት ስኝኞች ዜማ መስራት ጀመርኩ.... "ልሰማ አልጓጓሁም እንዴት እንደመጣ ስህተት.. ሆነ ምን ያደርጋል ቃልሽ ላይቀይረው እውነቱን! ተይው ምን ያደርጋል ይቅር.. ጊዜ ያልፈቀደው ፍቅር! እኔማ ፈራሁት ሁኔታሽን ሁሉ ሲወራ.. የሰው አፍ እንዲህ ነው ጠብቂ እራስሽን አደራ! ምንም ባላቆይሽ ከኔ.. ክፉሽን አልየው ባይኔ! ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ደጁን አያምንምና ደህና ይግጠምሽ.. ደህና(×2) የሸኘ ልቡን አያምንምና..." "መስ ስለእኔ በዚህ ልክ እንድትብሰለሰል አልፈልግም እኔ ንፁህ አይደለሁም ከመንደሩ አፍ ልትጠብቀኝ አትሞክር አይገባኝምኮ!" በድጋሚ የልብ ምቴን በደቂቃ አእላፍት ጊዜ የሚጨምር ድምፅ ሰማሁ... ባሁኑ ግን አንገቴም ዓይኖቼም የሆነ ነገር ከብዷቸው ነበር መዞር አልቻሉም መታ ልክ ድሮ እንደምንቀመጠው ተቀመጠች... ሁሌ ሳደርግ እንደነበረው ጭኖቿን ተንተራስኩ... ልክ እንዳስለመደችኝ... እናቴ ያስለመደቻት ይመስል የእናቴ እጆች እስኪመስሉኝ እጆቿን በቲሸርቴ አሳልፋ ጀርባዬን በስሱ እየደባበሰች... "ታስታውሳለህ የእነዚህ ጥያቄ መልሶች እሩቅ ናቸው የተባባልናቸውን?" እያለቀስኩ ስለነበር ቃል ማውጣት አቅቶኝ በአዎንታ ጭንቅላቴን ነቀነኩ... "የአንተን አላውቅም የእኔ ያ እሩቅ ነው ያልኩህ መልስ ላይ ግን ዛሬ ደርሰናል... እናቴ ታማ ወይም አደጋ ደርሶባት አይደለም የሞተችው... እራሷን አጥፍታ ነው..." ቀና ብዬ አየኋት... እያለቀሰች ነበር እሷም አየችኝ.. እያለቀስኩ ነበር... እንባዬን እየጠረገችልኝ ቀጠለች... "እናቴ የሚፀፅታትና ደጋግማ የምትለኝ ምን እንደነበር ታቃለህ?... "አባቴ ክብር ቢኖረው ኑሮ ልጄን ለቀጥቃጭ አልድርም!" ባለ ነበር እሱ ግን እኔ በፍቅር ስታወር እሱ ምን እንዳወረው አላቅለትም አንስቶ ላባትሽ ዳረኝ... አልክድም በስአቱ በአባትሽ ፍቅር እብድ ብዬ ኘበር... ግን የጋሽ ንጋቱ ልጅ ላግባሽ ብሎ ያን ሁሉ ሀብት ጥሎሽ ሲያመጣ እንቢ ስል አባቴ እሺ ማለት ነበረበት... እሱን አግብቼ ቢሆን አሁን ከአብሮ አደጎቼ ባላነስኩ ነበር... እንደእነሱ ተኳኩዬ ዘንጬ ለመዝናናት በመኪናዬ በተንፈላሰስኩ ነበር... አሁን ግን የት እንዳለሁ እዬ.. አባትሽ እንጨትኛ ቆርቆሮ ቀጥቅጦ የገዛውን የብረት ስሀን እያጠብኩ ነው....
743
8
ደህና ይግጠምሽ! የሄደን ሰው ምን ይሉታል ከራስ አልፍ ለማን ይወቅሱታል? ተፈጥሮ ግን ቅጥአንባሯ የወጣ ናትሳ... አሁን ሜዳና ተራራ እንዴት በአንድ ገፅታ ይሆናሉ? ተቃራኒ ናቸው! እንደሚገባኝ ከሆነ ደግሞ ተቃራኒ ነገሮች ሁሉ በተቃራኒ እንጂ በአንድ ገፅታ አይሆንም..... እዚህ ግን ሜዳና ተራራ በአንድ ሆኑ እያልኳችሁ ነው... እንዴት እንደሆነ አትጠይቁኝ ግን ሜዳው ተራራ ነው ተራራው ሜዳ ነው..አንዱን ብቻ ማለት ይከብዳል... ተፈጥሮአዊ ቦታ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ወደዚህ ይመጣሉ ግን በጣም ትልቅ ስለሆነ ሰው ያለም እስከማይመስል ፀጥ  ያለ ነበር... ሁሌም የምቀመጥባት ቦታ አለችኝ... ፊትለፊቴ ገዘፍ ያለ ዲንጋይ አለ... በቃ ደስ ሲለኝ ከዲንጋዩ ጋር.. ከፈለኩ ወደአንደኛው ዛፍ ዙሬ ከእሱጋር... አብዛኛውን ጊዜ ግን ከእራሴ ጋር ነው የማወራው። ከሆነ ጊዜ ብኋላ ግን እቺ ቦታዬ ሌላ ሰው ሳትለምድ አትቀርም ሂጄ በመጣሁ ቁጥር ሁሌ የሚሸተኝ የሆነ ጠረን አለ... እሺ ውሻ አይደለሁም ጠረን አሸታለሁ ምናምን ብዬ አልሰክሳችሁ ግን የምቀመጥበት ቦታ ላይ ምን የመሰለ ዳሌ ተሸክሞ እንደነበር የሚያሳብቅ ወረቀት አገኛለሁ... ቦታዬ ላይ ሌላም ሰው መቀመጥ ስለጀመረ ቀንቼ ይሁን ወይም ለተፈጥሮ ተቆርቁሬ አላውቅም ብቻ እኝደመበሳጨት እያረገኝ... "ተፈጥሮን ፈልገው ከመጡ ዝም ብለው አይዘረፈጡም? ወረቀት ላይ ምናምን ይቀመጣሉ እንዴ? ቀሽሞች" ምናምን እያልኩ እያጉረመረምኩ ወረቀቱን በእግሬ አብንኜ እቀመጣለሁ.... ዲኔጋዩ ይሁን ዛፎቹ ባላውቅም ለሚመጣው ሰውማ ስለእኔ ያሳብቁለታል... እንጂማ እንደዚህ እኔን ለማናደድ እንደዚህ ቆርጠው አይነሱም ነበር... በሚቀመጡበት ወረቀት ስናደድ ጭራሽ የሶፍት ምአት ቆልለው ይሄዳሉ? ሴት ይሁን ወንድ አላቅም ግን ስድስትና ሰባት ወር ሙሉ ጉንፋን ይይዛል እንዴ? አመቱን ሙሉ በሉት ሶፍቱን ስለቅም ሳቃጥል.... እሰይ... እሰይ.. ዛሬስ ወረቀቱን ከነዳሌው ደረስኩበት... እንዴት እንዴት በስድብ ከፍ ዝቅ እንደማደርጋት በጋለ አእምሮዬ ምስል እየታየኝ ገሰገስኩ... የሆነ ሰልካካ... ምን ልበላችሁ? ለጡት ጉች ጉች... ለከንፈር ኢንጆሪ.. ለጥርስ በረዶ... አቦ ለድምፅ ምን ቁልምጫአለው? ከቁጣ ግስገሳዬ አደናቅፎ ያቆመኝ እንቁርጉሮዋን ሰማሁ... "የልቤን ስብራት ባንተ እንዳልጠግነው.. የኔ ማቶንበት ምክንያቱ ብዙ ነው! የምቶድህ ልቤ የሰው መሆንህን አምና ተቀብላ... ይመስልሀል እንዴ ሰላሟን አግኝታ የምትልህ ችላ!..." "ምን ልታረጊኝ?ልክ ቦታዬን እንደቀማሽኝ ሚስቴንም ልትቀሚኝ?" አልኳት ፈገግ ብዬ "Noo.. ለዘፈኑ ያክል ነው..." "ድምፅሽ ያምራል" "ዘፈኑስ?" "እኔ የሀገራችንን ዘፈኖች አልወዳቸውም" "Ok...ፍቅር ይዞህ አያቅም ማለት ነዋ!" "ቢይዘኝም ፍቅሬን በዛቻማ አልገልፅም..." "እና በምንድነው የምትገልፀው?" "አንዳንድ ጥያቄዎች መልሶቻቸው እሩቅ ናቸው... ለማንኛውም ዛሬ ጎበዝ ሁነሻል ቦታዬን በሶፍት አላዝረከረክሻትም" "አታስብ ከዚህ ብኋላ አላቆሽሽብህም" "በስተመጨረሻ ጉንፋኑ ለቀቃት.. ቢጨንቀኝኮ ትኩስ ነገር ባስቀምጥላት ብዬ ሳስብ ነው የተሻለሽ" "አይደል..!" በትካዜ ተዋጠች... "ኦ sorry ምክንያቱን ሳላውቅ ቀባጠርኩብሽ.. ምን ነበር የሶፍቶቹ ሚስጥር?" "ከሶፍቶቹም በፊት እመጣ ነበር..." "አው አውቅ ነበር..." "ያን ታውቅ ነበር?" "አዎ ጠረንሽ ሁሌም ይሰማኝ ነበር.." "ገባኝ ወረቀቱ.." ብላ ከዳሌዋስር ጎትታ አወጣችውና ጨመዳዳ ወረወረችው... "ሶፍቶቹ እንግዶችሽ የሆንበትን ምክንያት ንገሪኛ?" "የቤቱ አባውራ አባቴ ሳይሆን እናቴ ነበረች... የምገባበትን የምወጣበትን ስአት የምትፈቅድልኝ እሷ ነበረች... አባቴ እናቴን ይፈራት ነበር" "ለምን?" አልኳት ተገርሜ "አንዳንድ ጥያቄዎች መልሶቻቸው ሩቅ ናቸው ያልከው እራስህ አይደለህ!... ባጭሩ አስር ስአት ሲል ከዚህ መሄድ ነበረብኝ ለዛ ነበር ሁሌ የማታገኘኝ.." አባቷ እናቷን ደበደባት... ከዛ ተለያዩ... እያለቀሰች ነበር.... አይ ሄዬ ጭንቅላቴ እስኪ ዝም በል እሷ ልትነግርህ አይደል እንዴ... "እና ምን ተፈጠረ.. ዛሬ እንዴት ዘገየሽ?" "እናቴ ስለሞተች!" "sorry በጣም አዝናለሁ በቃ ወሬ እንቀይር..." "አትዘን ስድስት ወር ሙሉ አዘንኩላት አይበቃትም? አሁን ወደእራሴ አለም እየተመለስኩ ነው... በነገራችን ላይ ሠላም እባላለሁ" አለችኝ "መሣይ..." እጆቿን ጨበጥኳቸው... የድምጿን ያክል ውበት አላቸው... ከዚህ ትውውቃችን ብኋላ ሁሌም እንገናኛለን.. እናወራለን እናወራለን ሠላምዬ ዘፈን ትወዳለች... በእሷ ምክንያት ዘፈን ከመስማት አልፌ ዘፋኝ የመሆን ህልም ሁላ እየጀማመረኝ ነው ነው የምላችሁ... "መስ..." "ወዬ ሠላሜ..." "አንድ ጨዋታ እንጫወት?" "ምን አይነት ጨዋታ?" "እየውልህ አንዳችን መዝፈን እንጀምራለን ልክ የዘፈኑ የመጀመሪያው ስንኞች ሲያልቁ ሌላኛው ሰው ከዛ ዘፈን ጋር የሚስማማ ሌላ ዘፈን ይቀጥላል.. እያልን እያልን መቀጠል ያቃተው ሰው ቸኮሌት ይጋብዛል" "ዝብለሽ ቸኮሌት ግዛልኝ አትይም ጦጣ..." "እኔ እንድንጫወት ነዋ የምፈልገው..."እንጫወታለን አንድም ቀን ቸኮሌት ጋብዛኝ አታውቅም ምክንያቱም አሸንፌያት ስለማላውቅ.... መቼም መሸነፌ አይቀርም ብዬ ቸኮሌት ገዝቼ ቦታችን ላይ ተገናኘን... "መስ.. ዛሬ አዲስ ሕግ ልጨምር ነው.. ግን ከዛሬ ውጪ ስለማይሰራ ተጠቀምበት..."አለችኝ እንደሆነ ነገር እያደረጋት "አንቺ በቃ ሁሌ መረበሽ ብቻ ነዋ የምታውቂው እሺ አዲሱ ህግሽ ደግሞ ምንድነው?" "ዛሬ ዘፈን ብቻ አይደለም የምንዘፍነው... ስሜታችንንም ጭምር ይሆናል!" "ማለት? እንዴት?" "በቃ አሁን በዚህ ስአት እየተሰማህ ያለውን ስሜት ሊገልፅልህ የሚችል ዘፈን መዝፈን..." "አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ?" "እሺ ባክህ..." "ከዚች ቦታ ውጪ ቀሪው ዓለም ላይ የሌለሽ ቢሆንስ? የሆነ አለ አይደል እዚህ ቦታ በተደጋጋሚ ለረዥም ጊዜ በመምጣቴ የሆነ መንፈስ ነገር እኝደሰው ሆኖ እያወራኝ ቢሆንስ ብዬ አስባለሁ... በቃ የሆነ መልዐክ ወይ ሌላ ነገር ብቻ የሆነች ጣኦት ነገር ነው የምትመስይኝ..." "እንግዲህ ቤቴን ታቀዋለህ.. ትምህርት ቤቴ ትመጣለህ.. አየህ ሰው ነኝ በል አሁን አታረሳሳኝ ወደጨዋታችን.. በል ጀምር መቼስ ተሸናፊ እንደሚጀምር የማንሽረው ህጋችን ነው" አለችኝ... አሰብኩ.. አሁን የሚሰማኝ ምንድነው.. ይሄንን ስሜቴንስ ምን ዘፈን ይገልፀዋል?... አሃ ቅድም ስሰማው የነበረው ዘፈን.... "እሺ ልጀምር ነው..." ለመስማት ምንድነው የዚህን ያክል ተስተካክሎ መቀመጥ... በቂጧ ነው እንዴ የምትሰማው? "መራርጬ ቃላቴን ልገልፅላት ስሜቴን በቃ ዛሬስ እነግራታለሁ ብዬ ወስንና እፈራለሁ ብቅ ስትል ዓይኗን ሳየው ገና..." እሷ ቀጠለች፦ "አሄሄ ቆላውን ደጋውን.. ካንተ ጋር ደክሜ.. ደክሜ.. ደክሜ አሄሄ ለፍቅራችን ነበር.. ያለኝን እንዳቅሜ.. ያለኝን.. እንዳቅሜ..." እንዴት ከንፈሮቻችን እንደተጣበቁ አላውቅም.. ይመስለኛል እሷም አታውቅም... እሷን ለማስደሰት ከእሷ እኩል በዘፈን ፍቅር ወደኩ... ምናቤ ሁሉ የተሞላው የሆነ ቀን ለእሷ ስዘፍንላት.. መድረክ ላይ ሳቀብጥ ሳቆላምጣት ነው....
775
9
movie recommendation Silo ያበደ tv series ነው ሕግ ያስፈለገው እኛን ለመጠበቅና ፍትህ ለማስፈን እንደሆነ አብዛኞቻችን እናስባለን... ይሄንን ፊልም ካየሁ ብኋላ ግን ምናልባት ሕ+1
movie recommendation Silo ያበደ tv series ነው ሕግ ያስፈለገው እኛን ለመጠበቅና ፍትህ ለማስፈን እንደሆነ አብዛኞቻችን እናስባለን... ይሄንን ፊልም ካየሁ ብኋላ ግን ምናልባት ሕግጋቶች እኛን ሳይሆን የተዋሸናቸውን ውሸቶች ቢሆንስ የሚጠብቁት? ብዬ ማሰብ ጀምሪያለሁ... ብዙ ነገር ታዩበታላችሁ... ፊልሙን በትርጉምም በእንግሊዝኛም ታገኙታላችሁ ከፈለጋችሁ በውስጥ አዋሩኝ እልክላችኋለሁ... @Mr_Lewi ያያችሁት ካላችሁ ከፊልሙ ብኋላ እንዴት ናችሁ? @lewi_derest
846
10
ነገ ማታ ዘፈኑን የምመርጥ ይሆናል... ዕሮብ ፅሁፉ ይለቀቃል እስከዛ ዘፈኖቹ ላይ ቶሎ ቶሎ react አድርጉ
1 045
11
New update... እዮባ፦ ተርቦ ልብ ይደርባል
1 058
12
11 ዘፈኖች ተመርጠዋል... የወደዳችሁት ዘፈን ላይ react አድርጉና ብዙ react ያለውን ዘፈን ልብ ወለድ እንፅፍለታለን
1
13
11,ብስራት ጋርደው፦ እኔ እንጂ
1 395
14
10, ሚካኤል በላይ ነህ፦ ለካስ ለበጎ ነው
1 404
15
9, ሀይሉ አመርጋ፦ እንግዳ
1 317
16
8, መሳይ ተፈራ፦ ደህና ይግጠምሽ
1 323
17
7,ሚካኤል በላይ ነህ፦ የእኔ ፀይም
1 302
18
6, ማስተዋል እያዩ፦ መራርጬ ቃላትን
1 294
19
5, ዳዊት ፀጋዬ፦ ድሃ አይጣላ ከውሃ
1 279
20
4, ነዋይ ደበበ፦ ድሃ ናት
1 266