✨ሊላህ ኢስላማዊ ዳዕዋ✨
رفتن به کانال در Telegram
{የተመረጡ ኢስላማዊ እና አለማዊ የሆኑ ትምህርቶችን በመልቀቅ ኡማውን እናሳውቃለን ፣ እናስታውሳለን!!!}
نمایش بیشتر1 622
مشترکین
-124 ساعت
+47 روز
+630 روز
آرشیو پست ها
1 622
ዊርድ የለንም... አዝካር የለንም...ቁርዓን አንቀራም... አንዘክርም...ለይል አንሰግድም ...ሱና ሰላትም ፆምም በህይወታችን ላይ የለም ። እንዲህም ሆኖ ሀያታችን በሙላ በአመፅ የተሞላ ነው ግን ምርጡ የአላህ ባርያ እንደሆንን ይሰማናል... ጀነት መግባታችንን አንጠራጠርም ።
ተቅዋ የለንም.... ሀያዕና አደብ የለንም....በየትኛውም ዘርፍ የጠለቀ እውቀት አልገበየንም ግን አሁንም የሆነ ጥሩ ሀል ላይ እንዳለን ይሰማናል።
©️ባለዕዳው
1 622
"እንደው 60 አመት ብትኖር በቀን 8 ሰዓት ብትተኛ 20 አመት ተኝተህ ታሳልፋለህ...20 አመት ካባከንክ አይበቃህም ወይ ?" ይላሉ ኢማመል ጘዛሊ
እኔ እንቅልፍ ከሚወድ ሰው እንደመሆኔ ስለ እንቅልፍ የፃፉትን አይቼ ብርግግ አልኩኝ ። አሁን ባለው ተጨባጭ ብዙዎቻችን 20 አመትን በሌሎች እቅድ ውስጥ ነው የምናሳልፈው ከዛ ኋላ ሁሉም የምርጫውን ህይወት ሀ ብሎ ይጀምራል ።
በዚህ ስሌት ያለን 40 አመት ሲሆን ከዚህ ውስጥም በመተኛት ወደ 14 አመት ገደማ እንጨርሳለን ...ቀሪ 26 አመት ብቻ ! ከዚህ ውስጥም በቀን 4 ሰዓትን በስልክ ላይ ተጥደን ብናሳልፍ ከ 4 አመት በላይ እናባክናለን ።
ሲጨመቅ 22 አመት ገደማ ብቻ ይቀረናል ...ከዚህ ውስጥስ ምን ያህሉን በቁም ነገር እንጠቀማለን ? አስቡት አንድ ሰው 60 አመት ቢኖር እንኳ በቅጡ 20 አመት አይኖርም ...ይህን አመትም በአግባቡ ይጠቀም አይጠቀም ራሱና አላህ ብቻ ያውቃሉ ።
እናስብበት በቃ 🙌 copied from ባለዕዳው
1 622
የዱሃ ሶላት...
ነቢዩ (ﷺ) እንዳስተማሩን በሰውነታችን ውስጥ 360 መገጣጠሚያዎች ያሉ ሲሆን፣ በየቀኑ በሰላም ለተንቀሳቀሰበት ለእያንዳንዱ
መገጣጠሚያችን ምስጋናና ሰደቃ ማቅረብ ይጠበቅብናል።
ይሁን እንጂ የአላህ እዝነት ሰፊ ነውና—በረፋድ ሰዓት የምንሰግዳት ሁለት ረከዓ የዱሃ ሶላት ብቻዋን ለእነዚህ ሁሉ 360
መገጣጠሚያዎች እንደ ሙሉ ሰደቃና ምስጋና ሆና በቂ ሆና ትተካለች።
የመስገጃ ወቅቱም ፀሐይ ወጥታ ከፍ ካለችበት (ረፋድ) ጀምሮ እስከ ዙህር ጥቂት ደቂቃዎች እስኪቀረው ድረስ ነው። በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥተን ይህችን ውድ ሶላት በማዘውተር የሰውነታችንን ጤና ጸጋ እናመስግን!
@yasin_nuru @yasin_nuru
