330
مشترکین
-224 ساعت
-87 روز
-1730 روز
آرشیو پست ها
330
DDos Attack
@simatechnology
🔺Denial Distributed Of Service
🔺በቀላሉ Ddos Attack ማለት አንድን ዌብሳይት ወይንም Server በ1 ጊዜ ከሚያስተናግደው በላይ Request በመጠየቅ ስራውን ማቆም ወይንም ማዘግየት ወይንም እስከመጨረሻው እንዳይሰራ ማድረግ መቻል ማለት ነው...
📌ምሳሌ : 1
አንድ ነጋዴ የተለያዩ እቃዎችን ይሸጣል እንበል ያንን ነጋዴ ደግሞ የሚፎካከረው (የሚጠላው ሰው) አለ እንበል የዛን ሰውዬ ገበያ ለመዝጋት በጣም ብዙ ሰዎችን ይልክና የተላኩት ሰዎች ደግሞ ልክ እንደ ትክክለኛ ገዢ በመከራከር የሰውየውን ገበያ ይዘጉታል ሰውየውም በጣም Busy ስለሚሆን ትክክለኛ ገዢ ቢመጣ እንኳን ማስተናገድ አይችልም!
📌ምሳሌ : 2
የቴሌ Server በ 1 ጊዜ 2 Million ጥሪዎችን ያስተናግዳል እንበል...እና DDOS ማለት በ1 ጊዜ ከ2 Million በላይ 3million 4million Or ከዛ በላይ ጥሪ በTele Server ላይ ስንፈጥር ሰርቨሩ ከአቅሙ በላይ ስለሚሆን ከሌሎች የሚመጣለትን ጥሪ Network Busy እያለ ያዘገያል ማለት ነው...የዚህን ጊዜ ቴሌ አልተጎዳም? ይጎዳል! DDOS በቀላሉ ይህ ነው!
📌የDDOS Attack አላማ
ለመጉዳት
ለመዝናናት
እራስህን ለማሳወቅ
📌የDDOS Attack ጉዳት
ለጊዜያዊውም ቢሆን አገልግሎት ያቋርጣል
ትልቅ ውድመትና ኪሳራ እንዲያጋጥም ያደርጋል።
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።
**************
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
👨💻 @simatechnology
330
#ሊያውቋቸው_የሚገቡ_ጠቃሚ_መረጃዎች
@simatechnology
@simatechnology
💎 የ PDF ፋይሎችን ዳውንሎድ ሲያደረጉ የፋይሉ ስም ምጨረሻ ላይ .exe የሚል ካዩ ቫይረስ ነውና ወዲያውኑ ያጥፉት፡፡
💎 ማንኛዉንም የ ዩቲዩብ video ዳውንሎድ ለማድረግ ከፈለጉ በ www. እና youtube በካከል ss ይጨምሩና ኢንተርን ይጫኑ።
💎 የወርድ ፋይልን save ሳያደርጉ በድንገት ከዘጋብዎ አይጨነቁ ወደ file explorer ወይም this pc ይሂዱና የሰርች ቦታ ላይ .asd ብለው ይፈልጉት።
💎 ሁሉንም ወይም የመረጡትን የወርድ ፊደሎች ወደ ካፒታል ወይም አስሞል ሌተር ለመቀየር ከፈለጉ የሚፈልጉትን ወርድ መርጠው shift+F3 ይጫኑ፡፡
💎 የ poworepoint presentation በቀጥታ እንዲከፍትልዎ ከፈለጉ save ሲያደርጉ .ppsx ብለው save ያድርጉት፡፡
💎 ማንኛዉንም የጎግል ምስሎችን በቀጥታ ዳወንሎድ ለማደረግ ከፈለጉ alt ተጭነው የሚፈልጉት ምስል ላይ ከሊክ ያድርጉ፡፡
👥 ለወዳጅዎ ያጋሩ
@simatechnology
@simatechnology
330
ዛሬ 5 ዋና ዋና የኮምፒውተር ክፍሎች | 5 basic computer components| እናያለን።
@simatechnology
ከኛ ጋር መሆናቹን በ 👍 ንገሩን።
① Motherboard
〰〰〰〰〰
❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡
❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
②Central Processing Unit (CPU)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡
❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡
❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
③ Random Access Memory (RAM)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡
❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል
④Hard Drive
〰〰〰〰〰
❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡
❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
⑤Power Supply Unit
〰〰〰〰〰〰〰〰
❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡
@simatechnology
@simatechnology
@simatechnology
@simatechnology
330
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ገንዘብ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ ማድረግ የሚያስችል ኤቲኤም (ATM) ማሽን ስራ ላይ አዋለ
====================================
@simatechnology
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የኤቲኤም (ATM) ማሽን በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ።
ይህ አዲስ የATM ማሽን ቀደም ሲል አገልግሎት ላይ ከዋለው የገንዘብ መክፈያ የATM ማሽን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል በመሆኑ ደንበኞች ገንዘብ ወደ ሂሳባቸው ገቢ ማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚችሉበት ነው።
ይህ አገልግሎት ለመጀመርያ ጊዜ ስራ ላይ ያዋለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዲሱ ATM ማሽን በአሁኑ ሰዐት በሙከራ ደረጃ በባንኩ ፍንፍኔ ቅርንጫፍ ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ይህ ማሽን ባንኩ አገልግሎት የመስጠት ሥራውን ከማቃለሉ በተጨማሪ በተለይ ባንኮች ክፍት በማይሆኑበት ዕለታት ደንበኞች የእለተ እለት ስራቸውን ለማቀላጠፍ እንዲችሉ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።
በአሁኑ ወቅት ባንኩ ካሉት ከ22 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች፣ 30 በመቶ የሚሆኑት የዲጅታል የክፍያ አማራጮችን የሚጠቀሙ ሲሆን፣ ይህ አዲስ ATM ማሽን የዲጅታል የክፍያ አማራጭ ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥርን እደሚያሳድግ ይታመናል፡፡
በሙከራ ደረጃ አገልግት መስጠት የጀመረው አዲሱ ATM ማሽን በዋናነት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፤ደንበኞች ካርዱን ወደ ማሽኑ በማስገባትና የሚስጥር ቁጥሩን በመጠቀም፤
ገንዘብ ማስገባት
ገንዘብ ማውጣት
ቼክ ወደ ሂሳብ አካውንት ማስገባት
ማሽኑ የኢትዮጵያ ባለ 5፣ 10፣ 50፣ እና የ100 ብር ኖቶችን በቀላሉ ለይቶ ይቀበላል፤
ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለይቶ ማስወገድ ይችላል።
© CBA
@simatechnology
330
#PHYTON 🔍(part - #one)🔍
@simatechnology
ሠላም ሠላም ውድ የ simatechnology ቤተሠቦች ዛሬ ይዘንላቹ የመጣነው ከ Programming language ሥለ ፓይተንን (phyton) በተመለከተ የመጀመርያውን ክፍል ይዘንለቹ መተናል ተከታተሉን እውቀት እንደምታገኙበት ተሥፋ አናደርጋለን ። 🧲ፓይተን(phyton) ፓይተን ብዙ ግልጋሎት ያለው ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ሢሆን ልክ እንደ ጃቫሥክሪፕት ተፋላጊ እና በጣም በማደግ 📈ላይ ካሉ ፕሮግራሚን ላንጉጅኦች አንዱ ነው።
ፓይተን የተፈጠረው በ ጊዶ ቫን ሮሠም በ 1991 ነው ።
ፓይተንን በአሁኑ ሠአት⏱ በአለማችን🌐 ላይ ብዙ ሠዎች ይጠቀሙታል ።ሦፍት ዌር ኢንጂንየርኦች፣ሣይንቲሥትዎች ፤
አካውንታትኦች እንዲሁም ታዳጊህፃናት እነዚህ ሁሉ ፓይተንን ይጠቀማሉ። ምክንያቱም ፓይተን ጀማሪዎች እንኳን በቀለሉ ሊረዱት የሚችሉት በመሆኑ ነው። ሥለዚህ የተለያዩ ሠዎች ማለትም የተለያየ ሥራ ላይ የሚገኙ ሠዎች ለሥራቸው ፓይተንን ይጠቀማሉ።
ተከታታይ (ተደጋጋሞሽ) ያላቸው ነገሮች መሥራት like ፦ 📍ፋይል ኮፒ ማድረግ 📍 ማህደር (ፎልደር ) ክሬት ማድረግ
📍 ሥሙን መቀየር
📍 ወደ ሠርቨር መጫን just የሚያሠለች ነገር ነው ። ነገር ግን ፓይተን ሥክሪፕት በመፃፍ ሁሉንም ነገር በቀለሉ መሥራት እና ጊዜአችንን መቆጠብ ይሥችለናል።
ፓይተንን በመጠቀም 🔌፦ዌብ አፕሊኬሽን 🔎
🔌፦ሞባይል አፕሊኬሽን📱
🔌፦ ዴሥክቶፕ አፕሊኬሽን🖥
🔌፦ ለሦፍትዌር ሙከራ
🔌፦ለሃኪንግ ወዘተ...ሥለዚህ ፓይትን ብዙግልጋሎት ያለው ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ነው።ነገር ግን ከላይ የተጠቀሡትን ነገሮች ሌላ ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ በመጠቀም መሥራት አንችልም እንዴ?🤔 ብላቹ ልትጠይቁ ትችላላቹ ። መልሡ እንችላለን ነው። ሆኖም ግን ፓይተንን ሥንጠቀም
1 📌ውሥብሥብ ( complex) ነገሮች በአጭር ጊዜ እና በጥቂት መሥመር ኮድ መፃፍ ያሥችለናል።
🖍ለምሣሌ 'hello world' ከሚለው ቃል ውሥጥ ሦስቱን(hel) ብቻ ፕሪንት ለማድረግ
🔹C# str.substring(0, 3)
🔹JS str.substr(0, 3)
🔹phyton(py) str[ 0,3 ]
ከዚህም ፓይተን(phyton) ምን ይህል እጭር እና ግልፅ እንደሆነ መረዳት እንችላለን።
2📌 አፃፃፋ (syntax)ቀላል በመሆኑ
ፓይተን ለመማርም ሆነ በራሣችን አንብቦ ለመረዳት ቀላል ነው።ፓይተንን ከሌሎች ጋር ብናነፃፅር like ከC++,C#,Php,java etc... ከሁሉም በላይ ግልፅ እና እጭር ኮድ መጠቀም ያሥችለናል። 🖍ለምሣሌ
🔹በጃቫ(java)
public class EthioTech{
public static void main(String [ ]args){
sysstem.out.println("hello World")
}
} hello world 💻
🔹በፓይተን (phyton)
print ('hello members')
hello members 💻
በምሣሌው እንደተጠቀሠው በጃቫ 3 መሥመር ሢሆን በፓይተን ደግሞ አንድ መሥመር ብቻ በቂ ነው።በመጨረሻም ፓይተንን ለመማር ሶፍት ዌር ዴቨሎፐር መሆን አይጠበቅብንም።ፓይተንን ለመማር ጊዜው አሁን ነው።
ለዛሬ በእዚህ እናበቃለን በቀጣይ በሚኖረን ቆይታ ቀጣዩን ክፍል ይዘንላቹ እንመጣለን እሥከዛው ግን መልካም ጊዜ።
© @simatechnology
330
የእንጦጦ የሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታ ተጠናቀቀ!
በእንጦጦ ኦብዘረቫቶሪና ምርምር ማዕከል የሚካሄደው የሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡ በማዕከሉ የተገነባው የመረጃ መቀበያ አንቴና ኢትዮጵያ በቅርቡ የምታመጥቃትን ሳተላይት ጨምሮ ለሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ አገልግሎት የሚውል መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
(የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት)
@simatechnology @simatechnology
330
How to increase Virtual RAM to Make Your System
Faster⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
1. Press and Hold down the 'Windows' Key and Press the 'Pause/Break' button at the top right of your keyboard. Or simply Right-Clicking 'My Computer' and then Select 'Properties'.
2. Click on the 'Advanced' tab.
3. Under 'Performance', click 'Settings'.
4. Then click the 'Advanced' tab on the button that pops up.
5. Under 'Virtual Memory' at the bottom, click 'Change'.
6. Click the 'Custom Size' button.
7. For the initial size (depending on your HD space), type in anywhere from 1000-1500 (although I use 4000), and for the Maximum size type in anywhere from 2000-2500 (although I use 6000).
8. Click 'Set', and then exit out of all of the windows.
9. Finally, Restart your computer.
10. You now have a faster computer and 1-2GB of Virtual RAM.
Sʜᴀʀᴇ ᴀɴᴅ sᴜᴘᴘᴏʀᴛ ᴜs👇
🆔 @simatechnology
330
ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች
@simatechnology
1. የሀርድዌር መቃረን
ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ
Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡
እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር
IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት
ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት
ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር
ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡
2. የተበላሸ ራም
ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue
screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር
( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር
አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም
የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት
ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና
የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns
ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል
በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡
3. ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)
እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡
እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ
ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ
ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡
ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ
ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር
ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡
ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡
4. ቫይረስ
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች
ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን
በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን
ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን
ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡
5. መጋል
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ
በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው
ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ
ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር
ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ
በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር
ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት
እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል
ወይም ክራሽ ያደርጋል፡፡
@simatechnology
330
#ቴሌግራምን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ❓
✔️መፍትሄውን እነሆ👇👇👇
@simatechnology
👉ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatts app,viber, imo,tango.....etc
👉ቴሌግራም እንደ whatsapp,viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል✅
✴️ሌሎችም hack ማድረጊያ አፕሊኬሽኖች አሉ
ማለትም 👉desktop app
👉android app አሉ።
እናም በነዚህ👆 የሀኪንግ አይነቶች አካውንታቹ ሌላ ስልክ ላይ ወይም ሌላ #pc ላይ ሊኖር ይችላል✅
1⃣.በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉኝ
💢Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session 👉 ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።
⚠️Note: እራስዎ በሌላ #አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል መርጠው መርጠው ነው።
✴️ ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት፤ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ 📱 የእናንተን #አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።
2⃣.Security ደግሞ ለማጠናከር👇
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password *..
⚠️ግን የ #gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።
✴️ ይህ👆 ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።
✔️የሚጠቅመው #እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ📲 ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
✔️ ሌላ ሰው #በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
✴️ ማንም ሰው ለመግባት #በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ❌ መግባት አይችልም፥፥
⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት::
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ
******************
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
@simatechnology
330
✳️ #ቪፒኤን ለምን እንጠቀማለን? ጥቅሙስ ምንድን ነው?
#ቪፒኤን (VPN) የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና የምንለዋወጣቸዉ መረጃዎች ከመረጃ #በርባሪዎች ጥቃት የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚረዳ #ሶፍትዌር ነው፡፡
#ተጠቃሚዎች የቪፒኤን ግንኙነት ሲፈጥሩ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ መተላለፊያ መንገድ ይፈጥራሉ፡፡
#ቪፒኤን በተለየ ማስተላለፊያ መንገድ የሚተላለፉ ዳታዎችን ሚስጥራዊ የሚያደርግ በመሆኑ #ማንኛዉም የመረጃ በርባሪ የመረጃዉን ይዘት ማዎቅ እንዳይችል ከማድረጉ ባሻገር የመረጃ ግንኙነቱ የሚሆነዉ #በሁለቱ ባለመብት(ባለፍቃድ) አካላት ብቻ ነዉ፡፡
#ሶፍትዌሩ የቀጥታ የበይነ-መረብ ግንኙነት 'የኦንላይን' እንቅስቃሴ በመደበቅ እንዲሁም እንዳይታይ በማድረግ(የትኛዉን ድረ-ገጽ እንደጎበኘን እና ምን አይነት ዳታዎችን እያስተላለፍን መሆኑን) ባለማሳዎቅ ያግዘናል፡፡
#ይህን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ማግኘት የምንችለው ደግሞ የቪፒኤን ሶፍትዌር ደንበኛ በመሆን አገልግሎቱን መጠቀም ስንጀምር ነዉ፡፡
#ደንበኛ በመሆናችን የምናስተላልፋቸዉ ዳታዎች ከመዳረሻዉ ኔትወርክ ከመድረሳቸዉ በፊት #ይመሰጠራሉ፡፡
ቪፒኤንን ለምን መጠቀም አስፈለገ?
ማንኛዉንም የዌብ ተግባራት #ኢንክሪፕትድ(የተመሰጠሩ) እንዲሆኑ ያደርጋል።
የቀጥታ የበይነመረብ ግንኙነት (online) ተግባራችንን #በመደበቅ ከሚከታተሉን የመረጃ መንታፊዎች ያድነናል፡፡
መዳረሻችንን በግልፅ እንዳይታይ እንዲሁም በቦታ የተገደቡ ዌቦችና ይዘቶችን አገልግሎት ማግኘት እንድንችል ይረዳናል።
በዌብ(በይነ-መረብ) ተግባር ላይ የማንነት መታዎቅ አጋጣሚን በእጅጉ ያጠባል።
የህዝብ ዋይፋይ ሆትስፖቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ግንኙነቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርግልናል፡፡
በአጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ መረጃና የመረጃ ልዉዉጥ መንገድ ይፈጠርልናል ማለት ይቻላል፡፡
😎 መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@simatechnology @simatechnology
@simatechnology @simatechnology
330
"ሳይበር" ምንድን ነው
@simatechnology
ሳይበር የሰው ልጅ የእርስ በርስ ግንኙነቱ ማደግ የፈጠረው ረቂቅ የቴክኖሎጂ ውጤት እና መሰረተ-ልማት፣ የመረጃ እንዲሁም የሰዎች መስተጋበር የሚገለጽበት ፈጠራ ነው፡፡
የሳይበር ምህዳር የምንለው የተለያዩ የኢንፎርሜሽን መሰረተ-ልማቶች ማለትም ኮምፒውተሮች ፣ራውተሮች፣የኮምፒውተር ኔትዎርኮች፣ወ.ዘ.ተ. ተሳስረው የፈጠሩት ምናባዊ ዓለም ሲሆን በዚህ ምህዳር ውስጥ ኢንፎርሜሽን ይቀመጣል፣ይሰራጫል፣እንዲሁም ይተነተናል፡፡
የሳይበር ምህዳሩን አንዳንዶች በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሰው ልጅ የተቆጣጠረው አምስተኛው ግዛት በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህም ከየብስ ፣ ውሃ ፣ የአየር እንዲሁም የውጫዊው የህዋ ግዛት መካከከል በመመደብ፡፡
የሳይበር ምህዳር፡ የብዙዎቻችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አካል ከሆነም ውሎ አድሯል፡፡ ይህ ሲባል ለስራ ፣ለትምህርት ፣ ለመዝናኛ ከመጥቀምም አልፎ ለተለያዩ የእርስ በርስ ግንኙነቶች ማሳለጫ አድርገን የምንጠቀምበት ዋነኛ መሳሪያ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አልፎ የምህዳሩ እውን መሆን የኢንፎርሜሽን ዋጋ ከምንጊዜውም በላይ እንዲጨምር ምክንያት እየሆነ ይገኛል፡፡
የሳይበር ምህዳር አካላት
የሳይበር ምህዳር የምንለው ኮምፒውተሮች ብቻ የሚፈጥሩት ሳይሆን የተለያዩ አካላት ተሳስረው እውን ያደረጉት ምህዳር ነው፡፡ እነዚህ የሳይበር ምህዳር አካላት ከላይኛው የምህዳሩ ክፍል እስከ ታችኛው ድረስ በ4 ዋና ዋና ክፍለች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡
የውስጠኛው የምህዳሩ ክፍል፡ የሳይበር ምህዳር እውን እንዲሆን መሰረት የጣለው አካላዊ ወይም ፊዚካል ደረጃ የምንለው ነው፡፡ ይህም የተለያዩ ማሽኖች፣ኮምፒውተሮች፣ኬብሎችና የመሳሰሉ አካላት ጥምረት ነው፡፡
ሁለተኛው የሳይበር ምህዳር ውስጥ የሚቀመጠው፣ የሚተነተነው እና የሚሰራጨው ኢንፎርሜሽን ነው፡፡
ሶስተኛው የሳይበር ምህዳር ክፍል ለኢንፎርሜሽን መፈጠር፣ መተንተንና መሰራጨት መሰረት የሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የኢንተርኔት አገልግሎት ፕላትፎርሞች ናቸው፡፡
እንዲሁም የመጨረሻው እና ውጫዊ ክፍሉ፡ የሳይበር ምህዳሩን የሚጠቀመው፣ ኢንፎርሜሽን እና ቴክኖሎጂውን የሚያንቀሳቅሰው የሰው ልጅ የሳይበር ምህዳር ውጨኛው ክፍል ነው፡፡
⚜የሳይበር ምህዳሩ ልዩ ባህሪያት
🔻ያልተማከለ ወይም ልዩ የተማከለ አስተዳደር የሌለው ሲሆን ይህም ለቁጥጥር አዳጋች እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
🔻ለግለሰቦች እና ለቡድኖች ከፍተኛ ሃይል የሚሰጥ ሲሆን የግለሰቦች እና ቡድኖች አስተሳሰብ፣እምነት እና እሴቶችን ማንጸባረቅ የሚያስችላቸው ነው፡፡
🔻የጎንዮሽ እና ትስስራዊ ሃይል የሚያበረታታ ነው፡፡
🔻ዓለም አቀፋዊ እና ድንበር የለሽ ነው፡፡
🔻እውቀት መረጃና ምናባዊነት ላይ ያተኩራል
🔻ለደካሞች ልዩ ተጠቃሚነትን የሚሰጥ ነው
🔻ሁሉም ጋር የደራሽነት አቅም ያለው፡፡
🔻በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ የሆነ ፍልስፍናዊ ባህሪ ያለው ነው፡፡
በእነዚህ ልዩ ባህሪያት ምክንያት ምህዳሩ ለተጠቃሚዎች መልካም እድሎችን ይዞ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለየ መልክ እየያዘች ከመምጣቷ ባሻገር የእውቀት እና የኢንፎርሜሽን ማህበረሰብ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ መልካም እድሎች ካመጧቸው ቱሩፋቶች ጎን ለጎን ምህዳሩ የተለያዩ የደህንነት ስጋቶችን ይዞ መጥቷል፡፡ እነዚህን ስጋቶች ለመቋቋምና ምህዳሩ ያለውን መልካም ጎኖች አሟጦ ለመጠቀም ሃገራት የደህንነት ስትራቴጂዎች ከቴክኖሎጂ፣ ከሰው ልጆች እንዲሁም ከኢንፈርሜሽን ደህንነት አስተዳደር እና አሰራር ስርዓቶች አንጻር ቀርጸው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከስትራቴጂዎች መካከልም የኢንፎርሜሽን ደህንነት ገዥ ሰነዶች በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡
🙏Join & share 🙏
👉 @simatechnology👈
330
⭕️ዳርክ ዌብ ምንድነው❓
https://www.csoonline.com/article/3249765/
what-is-the-dark-web-how-to-access-it-and-what-youll-find.html
ዲፕ ዌብ/ዳርክ ዌብ ድብቁ የኢንተርኔት ክፍል ሲሆን ማንኛውም ሰው በቀላሉ Google,Yahoo,Bing ላይ መጠቀም ወይንም ማግኘት አይችልም!
🔴አሁን እየተጠቀምነው ያለው ኢንተርኔት Surface web ይባላል!
🔴ዲፕ ዌብ የራሱ የሆነ Domain አለው . com.net.edu.org ግን .Onion በሚባል በራሱ Domain name ይሸፈናል!
⭕️ከሊንኩ በፊት https ሳይሆን http ብቻ ብሎ ነው የሚጀምረው ምክነያቱም s የሚያመለክተው Secured የሆኑ ዌብሳይቶችን ሲሆን s የሌለው ደግሞ unsecured መሆኑን ነው!
🔴.onion ከዚህ በፊት surface web ላይ አይታችሁት አታውቁም!
🔴.onion ራሱ የ internet DNS root አይደለም! ወይንም በቀላሉ ከእነ .com .net .org .edu...ጋር አብሮ አይመደብም!
⭕️ዲፕ ዌብ/ዳርክ ዌብ ላይ ምን ልዩ ነገር አለ?
🔴እንግዲህ እጅግ አስገራሚና ሰምታችኋቸው የማታውቋቸው ነገሮች ይከናወኑበታል
🔘የጦር መሳሪያዎች ይሸጡበታል
🔘የተለያዩ አደንዛዥ እፆችና መድሀኒቶች
ኬሚካሎች
🔘Fake ዲግሪ ፣ Fake ዲፕሎማ
Fake passport ፣ fake መንጃ ፍቃድ
የሰው ልጅ አካል(ኩላሊት...)
🔘የመመረቂያ እና Research ፅሁፍ
🔘የክሬዲት ካርድ ቁጥሮች
🔘የወሲብ ፊልሞች
🔘አደገኛ የሀኪንግ ሶፍትዌሮችና ሃርድዌሮች
🔘የክሬዲት ካርድ ሽያጭ(Visa, MasterCard, Amex..)
🔘ህገወጥ ሶፍትዌሮች
🔘የተሰረቁ ፊልሞች
🔘የሀከሮች ኪራይ(በገንዘብ ተስማምታችሁ የሆነ ነገር ሀክ እንዲያረጉላችሁ)
🔘የተለያዩ ድርጅቶችን ፓስዎርድ
🔘የኮንትሮባንድ እቃዎች(ኤሌክትሮኒክስ እና ልብሶችን በጣም በርካሽ ዋጋ)
🔘አደገኛ የሀኪንግ እና የተለያዩ ትምህርቶችን...
🔘ዘግናኝ ነገሮችም ይገኙበታል (Red ROOM, ISIS..)
🚩ምን አለፋን ብዛት ህገ ወጥ የሚባል ነገር ያለው እዚህ ነው.....
🚩በነገራችን ላይ ወደ 75% የሚሆኑ ዳርክ ዌብን የሚጠቀሙት ሀከሮች ናቸው!
🚩ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ የሚጠቀሙበት Bitcoin ነው! ምክንያቱም ግዢ ሲፈፅሙ በባንክ እና በሌላ ዘዴ ከሆነ ሀከሮቹ የመያዝ እድላቸው የሰፋ ነው በBitcoin ከሆነ በምንም አይነት አይያዙም!
#share🙏
@simatechnology
330
💢#ሞባይል #ባትሪና #ቻርጀር ስንገዛ ኦርጅናልና ፌክ ኮፒ
መሆኑን እንዴት ማወቅ (መለየት) እንደምንችል እነሆ...⬇️⬇️⬇️
✔️ከሌሎች በይበልጥ ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ #ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችም📱 በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡
🔆ሳምሰንግ የጉግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይጠቃማል፣ የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል
ፍቃድ ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች #ከኦርጂናሉ ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡
⚠️ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን እነዚህን 👇 መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ
ስልኮችን መለየት ይችላሉ...
✅ የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም 👇
💢#ፌክ ሳምሰንግ ስልክ፡
1⃣. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም‼️
2⃣. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል‼️
3⃣. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል‼️
4⃣. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል‼️
5⃣. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ❌ መሆናቸዉን ይመለከታሉ‼️
✅የስልኩን ፍጥነት እና የትእዞች አፈጻፀም በመገምገም *
1⃣. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል 😡
2⃣. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች 🎮 እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡ 😡😡
3⃣. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም😡😡😡
✅የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም *
1⃣. ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps) የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ...
2⃣. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ #Settings የሚለዉን ይጫኑ...
3⃣. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ #ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
4⃣. እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም #ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡
✅የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም *
💢ወደ ስልክ📱 መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል ✔️
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን 😭 ፌክ ስልክ ነዉ፡፡
1⃣. *#0*# 👉 አጠቃላይ መገምገሚያ
2⃣. *#1234# or *#9999# 👉 ስልኩ የሚጠቀመዉን
ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ
3⃣. *#12580*369# 👉 ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ
4⃣. *#06# 👉 የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር
ማወቂያ
5⃣. *#9998*246# 👉 የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ
✅ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም *
💢ከላይ 👆 በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡
1⃣. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት💻 ላይ
ይጫኑት...
2⃣. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት
3⃣. ሶፍትዌሩ ስልኩን 📱ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል✅፤
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡😭😭
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
⚠️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ቻናላችንን #Mute ያደረጋችሁት #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን🙏🙏🙏"
⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።
************************
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻
@simatechnology @simatechnology
330
🌐ድህረ ገፅ ስራ ላይ ኖት??
ለፕሮፈሽናል ዌብሳይት ገጽ (Front end) ለማስዋብ የምጠቅሙ ምርጥ አምስት ፍሬምወርኮች(Framework) ከነ ማብራሪያቸው !
https://codeaddis.github.io/news/best-html5-frameworks
#እጅግ የኮዲንግ ስራዎችን የሚያቀሉ እንዲሁም ዘመናዊ ድህረገጽ ለመስራት በአሁን ሰዓት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ ጥቅማቸውም በተለያዩ ስክሪን ስፋት ባላቸው መሳርያዎች ተጠቃሚዎች ሲመለከቱት የተስተካከለ እይታ እንዲኖረው ያደርጋሉ።
ከነዚህም በጥቂቱ
#Bootstrap
#w3css
#foundation
#skeleton
Read more
https://codeaddis.github.io/news/
Stay connected
🤵 @simatechnology
©2019
330
💻የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ መፍትሄ አለው ። ከብዙ መፍትሔዎች ሀለቱን መንገዶች እንመልከት።
✅የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso” ወይም "isee password Windows password Recovery pro"
ሲሆኑ ሁለትም ከ internet ላይ ማውረድ ትችላላችሁ
🔒በ "Spotmou Bootsuit.iso ሶፍትዌር ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ:-
🔘ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡
👉1 መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ እንጭናላን
👉2 ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡
👉3 ፍላሹን /ሲዲውን/ ኮመፒዩተሩን ጋር አገናኝተን Turn ON ማድረግ፣ ከዛF12 (Boot key) (ለHp ላፕቶፕ F9) መንካት፡፡
👉4 “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB” የሚለውን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን መከተል፡፡
👉5 ኮምፒዩተሩ ከተከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite 2012 Application” ይከፈትልናል፡፡
👉6 ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder” የሚለውን “Menu” እንመርጣለን፡፡
👉7 “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡
👉8 “Please select the target widows” ከሚለው ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User Account” መርጠዉ “Reset” የሚለውን መጫን፣ ከዛ “OK” ከዛ “YES” የሚለውን እንጫናለን፡፡
👉9 መጨረሻ ላይ “Password is reset successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡
👉10 ኮምፒዩተሩን ዘግተው ይክፈቱት (Reboot). በትክክል 100% ይሰራል።
⚠️🔒በ "iSee password windows password recovery Pro" ፓስዎርዳችሁን መክፈት ለምትፈልጉ የሚከተለውን step ይከተሉ።
1⃣ ሶፍትዌሩን Download ያድርጉ ።
2⃣ ሌላ Computer ላይ install ያደርጉት
3⃣ ሶፍትዌሩን ስከፍቱት ምስል ያመጣላችኋል።
4⃣ ባዶ Flash or CD ትከቱና
🔘ፍላሽ ከሆነ የከተታችሁት Create password Reset Usb Flash drive ከሚለው ስር የፍላሹን ስም መርጣችሁ "Burn Usb" የሚለውን ስነኩት Burn አድጎ ሲጨርስ flashun ትነቅላላችሁ።
5⃣ከዛ በፓስዎርድ የተዘጋብንን ኮምፒዩትራችንን Turn OFF ማድረግ
6⃣ፍላሹን/ሲዲውን/ ከኮምፒዩተራችን ጋር አገናኝተን Turn On ማድረግ ከዛም (F12 ለቶሽባ/ዴል) F9 ለHp Computer (Boot key) መንካት
7⃣ " Boot sequence" የሚል ሲመጣልን " USB" የሚለውን መርጠን "Enter"ን በመንካት ትዕዛዙን መከተል።
8⃣ ኮምፒዩተራችን ከተከፈተ ብኋላ "isee password Windows recover pro" ይከፍትልናል ከአፕልኬሽኑ ላይ ካሉት አማራጭች(Option) ውስጥ "Admin Password Resetter" የሚለውን መንካት ከዛም "yes" የሚለውን እንጫናለን።
Via:-@simatechnology
330
ፍላሽ ዲስክ ኮምፒዩተርዎ ላይ ሲሰካ ሾርት ከት እየሆነ ተቸግረዋል?
ፍላሽ ዲስካችን ወይም ኮምፒዩተራችን በቫይረስ ሲጠቃ በውስጡ ያሉት ፋይሎች በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሾርትከት ይቀየራሉ። ይህም ማለት ዋናው የኛ file(ፋይል) ይደበቅና ለመጠቀም
አንችልም ማለት ነው። የዚህ ቫይረስ ሌላው አስቀያሚ ገጽታ ከኮምፒዩተር ወደ ሌላ ኮምፒዩተር በቀላሉ በፋላሽ አማካኝነት ሊተላለፍ መቻሉ ነው።
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ዛሬ ይህን ሾርትከት ቫይረስ የምናጠፋበትን Tricks. እናካፍላችኋለን ተከታተሉን። By using CMD
cmd (command prompt) በመጠቀም
ይህ ዘዴ ከሁሉም የተሻለ ውጤታማ ሲሆን ለሀርድ ዲስኮች ለፍላሾች እንዲሁም ለሞባይል ስልኮች ያገለግለናል።
1. በመጀመሪያ cmd እንከፍታለን።
Win + R then we write Cmd ( run፦cmd፦enter)
2. cmd ከከፈትን በኋላ ለማጽዳት የምንፈልገው ፋላሽ ዳይሬክተሪ እንሄዳለን። ( ለምሳሌ ፍላሹ removable disk G ከሆነ G:\ ብለን እንጽፋለን።)
3. በመቀጠል ይህን ኮማንድ እንጽፋለን። G፡*.* /d /s -h -r -s (G ለምሳሌ ሲሆን እናንተ በራሳችሁ ፋላሽ ሆሄ
4. አሁን ኢንተርን ስትጫኑ ከሾርትከት ቫይረስ ተገላገላችሁ ማለት ነው።
መረጃዎቹን ጠቃሚ ሆነው እንዳገኛችኋቸው ተስፋ እናደርጋለን።።
═════════════════
Please Share & Join Us
💥💥💥💥💥
@simatechnology
@simatechnology
330
ትንሽ ምክር ለጀማሪ ፕሮግራመሮች!
ከጥዋት እስከ ማታ ያለው ጊዜ ለተማሪዎች ትምሮቤት ምትውሉት አሳይመንት ምትሰሩበት, ምትዝናኑበት የተለያዩ ማትፈልጉት ነገር ምታረጉበት ሊሆን ይችላል:: እንዲሁም ሰራተኞች ደግሞ ስራ ቦታ ምትውሉበት ለእለት ተእለት ኑሮዋችሁ ገንዘብ ምታገኙበት ይሆናል:: ዋናው ነገር ከስራው ከትምህርቱ በተጨማሪ እስከለሊት ያለውን ጊዜ ደግሞ በራሳችሁ ላይ ለመስራት መጣር እጅግ ጠቃሚ ነው:: ከትምህርቱ ይልቅ በራሳችሁ ለመማር ምታደርጉት ጥረት የወደፊት ህይወታችሁን ላቅ ያለ ቦታ እንድታደርሱ ትልቅ ሚና ይጫወታል:: ይህን ለሊት ማትጠቀሙ ከሆነ እለት ተእለት አይምሮዋችሁ እየሰፋ እየመሰላችሁ ጊዜያችሁ ያልቃል::
እርግጥ በቀናት ውስጥ ምናሳልፈው ነገሮች ለራሳችን ጠቃሚ እና አይምሮዋችንን የሚያሰፋ ይሆናል ነገር ግን የምናገኘው ትምህርት እውቀታችንን በፈለግነው ፍጥነት ላያሳድግ ይችላል:: ነገር ግን ያለማንም አዛዥነት, ያለማንም ጊዜ ተቆጣጣሪነት, ያለማንም ውጤት ሰጪ("ሰነፍ ጎበዝ ባይ") በራሳችን ፍላጎት ለራሳችን የምንሰጠው ነገር በፍጥነት ስኬታማ እንድንሆን ይረዳናል:: ስለዚህ በፕሮግራሚንግ ህይወት ውስጥ ብዙ ለሊቶችን በብቸኝነት አንዳንዴም ያለ እረፍት እንቅልፍን በማጣት ራሳችንን ለማሻሻል ዋጋ መክፈል ግድ ይለናል:: ግዴታ ነው እያልኩ አይደለም ነገር ግን, ሊያጋጥመን ይችላል እና በርቱ!
"ራሳችሁን ከሰዎች ጋር አታወዳድሩ! ይልቁስ ራሳችሁን ትላንትና ከነበራችሁበት ራሳችሁ ጋር አወዳድሩ::"
ይህ የእኔ አስተያየት ነው ትችት ወይም ሙግት እቀበላለሁ::
ቻናልን ተቀላቀሉ:: @simatechnology
330
⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨
ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች እና ጥቅማቸው (ለጀማሪዎች)
የአብዛኛዎቹ ጥያቄ የሆነው ከየትኛው ልጀምር🤔 ጥቅሙ ምንድነው🤔 የሚል ሲሆን አጠር አድርጌ ለማቅረብ እሞክራለሁ
-----------
📱ፓይተን ( #Python)
ይህ open-source programming language በብዛት በሶፍትዌር ኢንጂነሮች ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የ #back-end Web developers በአሁኑ ግዜ ዕይታቸውን ወደ ፖይተን አዙረዋል። Python ለሳይንቲፊክ ካልኩለሽን እንድሁም ሰው ሰራሽ ክህሎት artificial intelligent ዋነኛ ነው ። ከሌሎች አንፃር ለመልመድ ቀላል ነው ።
ከዚህም ውጭ እጅግ ብዙ ጥቅሞች ነው ያሉት ፓይተን። ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ አስገራሚ ኮዶች መፃፍ እስክትችሉ ድረስ ተጠቃሎ በስልኮች ላይ መቷል።
📲ጃቫ ( #Java)
አብዛኛዎቻችን ስለ ፕሮግራሚንግ ሲነሳ ቶሎ አምሯችን ወስጥ የሚመጣው ጃቫ ነው።
በ1995 የተፈጠረ ሲሆን ለ Web-based development አንድሮይድ አፕ ጨምሮ ብዙ ስራ ይሰራበታል።
ብዙ የጤና, የት/ት የፋይናንስ እና እንዱስትሪ ድርጅቶች Java ይጠቀማሉ። እንድሁም ለbrowser አፖች ከተለያዩ ድህ ገፆች ፋይል ዳወንሎድ እንዲያደርጉ ያስችላል።
🍎ሩብይ ( #Ruby)
ይህ open-source scripting language ፕሮግራመሮች በምቾት የሚጠቀሙት ሲሆን ለapple ስልኮች አፕ ከመስራት ባለፈ ብዙ ስራዎች ይሰሩበታል።
ግዙፉ የህዋ ምርምር ተቋም NASA ለsimulation ክፍል ስራ ወስጥ Ruby ይጠቀማል።
🌐 #HTML
ለድህረ ገፅ ስራ ያገለግላል።
የweb page ስትራክቸሩን እንሰራበታለን አጠቃላይ በድህረገፁ ላይ የሚታዩ ፁሁፎች ፓስዎርድ ማስገብያ ሳጥኖች.......ሁሉም በዚህ ስር ይካተታሉ።
🌐#CSS, #JavaScript
ቡዙሃን ፕሮግራመሮች የሚጠቀሙት ይበልጥ ድህረገጽ ለማስዋብ አና በbrowser ሲታይ በደንብ የተቀላጠፈ ለማረግ እንዲሁም አንዳንድ ስራዎችን ለመስራት ያገለግላል።
#SQL
enables programmers to create, read, update, and delete information in a database. Companies use SQL to gather data.
ለበለጠ መረጃ ተጨማር ያንብቡ 👇
http://www.maggiore.net/programming.asp
👨💻 @simatechnology
@simatechnology
@simatechnology
@simatechnology
330
ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን በኢትዮጵያ ማስጀመር የሚያስችል መርሃ ግብር ይፋ ሆነ
፨፨@simatechnology ፨፨
ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን በኢትዮጵያ ማስጀመር የሚያስችል መርሃ ግብር በዛሬው እለት ይፋ ሆነ።
ግብይቱን በኢትዮጵያ ማስጀመር የሚያስችለው ስምምነት ከአሊባባ ኩባንያ ጋር በዛሬው እለት ተፈርሟል።
በስምምነቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፥ የዲጂታል ቴክኖሎጂ በበርካታ ዘርፎች እየተስፋፋ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ቴክኖሎጂው ከሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጋር እየተያያዘ መምጣቱን ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂው አዳዲስ አሰራሮችንበማሳደግ በመተግበር ለሀገራትና ህዝቦች ተጠቃሚነት ከፍ ያለ ድርሻ እንዳለውም ነው የተናገሩት።
ግብይቱ በታዳጊ ሀገራት የግሉን ዘርፍ ተሳታፊነት በተለይም ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፥ ዓለም አቀፍ የገበያ መረጃዎችን በማድረስ በኩል ተጠቃሚነታቸውን ያሳድጋልም ነው ያሉት።
የአሊባባ መስራችና ባለቤት ጃክ ማ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ለዲጂታል ቴክኖሎጂው የሰጠችው ትኩረት ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን በኢትዮጵያ ለማስጀመር እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል።
ዓለም አቀፉ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ኢትዮጵያ የምታመርታቸውን ምርቶች በአሊባባ አማካኝነት በዓለም ገበያ ግብይት እንድትፈፅም የሚያስችል ነው ተብሏል። ምንጭ፡ኤፍቢሲ
©INSA
@simatechnology
