cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የምዕመናን መረጃ መለዋወጫና ትምህርት መስጫ አውታር ነው፡፡

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
34 662
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+2707 روز
+81530 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
https://www.wegenfund.com/causes/yagebi-gubaaeeyaatene-agalegelote-bamadagafe-lahag/
3 9254Loading...
02
በማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ንዑስ ማእከል ለገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ። ንዑስ ማዕከሉ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጉባኤውን  በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምስጋናው፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት አከናውኗል።  በዚህ መርሐ ግብር በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አህጉረ ስብከት ለሚገኙ ለአብነት ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች ድጋፍ የሚውል  የገቢ ማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል። ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች የተገበራቸውን ፕሮጀክቶችና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ገለጻ የተደረገ ሲሆን በዚህም ምእመናን እየተተገበሩ ስላሉ ሥራዎች ግንዛቤ አግኝተዋል። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አእማድ የሆኑ ገዳማትና ጉባኤ ቤቶችን እንዲደግፋ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት መሠረት ድጋፍ መሰብሰብ ተችሏል። በተመሳሳይ ሚያዚያ 12ና 13 /2016 ዓ.ም በሩስልስሃይም ደ/ምጥማቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ አብርሃም፣ የደብሩ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት ዐውደ ርዕይ እና ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳይ ጉዳት ለደረሰባቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ገንዘብ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ የተሰበሰቡ ድጋፎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች በማኅበሩ በኩል እንደሚውል ንዑስ ማእከሉ አስታውቋል።
1 3371Loading...
03
https://www.youtube.com/live/W5Pcegye1Cs?feature=shared
5 67113Loading...
04
Media files
1 03719Loading...
05
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለ582 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ክህነት ሰጡ። ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የምዕራብ አርሲ ፣ጉጂ፣ምዕራብ ጉጂ  ፣ቦረና  ሊበን  ሃጉረስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለ582 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ክህነት በዛሬው እለት በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰጥተዋል። ለዲቁና ለቅስና እና ለቁምስና ፈተና ሲፈተኑ የቆዩ ተማሪዎች 546 ዲቁና፤34 የቅስና እና 3 የቁምስና ማዕረግ የተሰጣቸው ሲሆን  ከእነዚህ ውስጥ 171 ዲቁና እና 5 የቅስና ማዕረግ በአጠቃላይ 176 የተሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማዕከል እና ሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት  ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ጋር  በመተባበር ሲያስተምራችው የነበሩ ደቀመዛሙርት ናቸው። ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማዕከል ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት  ጋር በመተባበር በዚህ ዓመት ከዚህ ቀደም ማዕረገ ክህነትን የተቀበሉ 61 ካህናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 237 ማዕረገ ክህነት እዲቀበሉ አድርጓል። በዛሬው ዕለት ክህነት የተቀበሉት አገልጋዮች በአካባቢው ያለውን የአካህናት እጥረት ለመፍታት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተጠቋሟል።
5 2661Loading...
06
https://youtu.be/Q0WJSswrkTo?si=ajqfBbrGS6e31m5Y ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/፪/ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በኢየሩሳሌም አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/፪/      አዝ ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት/፪/   አዝ ኪሩቤል መንበሩን  የሚሸከሙት መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት/፪/   አዝ የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/፪/
6 23720Loading...
07
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም፣ ቤተ ፋጌ በቀረበ ጊዜ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሁለቱን ሐዋርያት ወደ ቤተ ፋጌ ልኮ የታሰረች አህያ እንደሚያገኙና ፈትተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን ጥያቄ የሚጠይቅ ሰው ከመጣ ‹‹…ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ…›› አላቸው፤ (ማቴ.፳፩፥፫) ፈትታችሁ አምጡ ማለቱ ሕዝቡን ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈቱበት ጊዜ እንደ ደረሰ ሲያጠይቅ ነው፡፡ ዛሬ ዓለም በሥጋዊ ጥቅም በኃላፊ ደስታ ዓይነ ልቡናችንን ጋርዳ፣ ሥጋዊ ፈቃዳችን ከፈቃደ ነፍሳችን አይሎ በኃጢአት ማዕሰር ታስረናል፡፡ ጌታችን በትምህርቱ ‹‹…ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው፤ ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም…›› በማለት እንደገለጸው በበደላችን በኃጢአት ባርነት ቀንበር ሥር ወድቀን በዲያብሎስ ባርነት ታስረናል ፤ (ዮሐ.፰፥፴፬) ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን››፤ ከታሰርነበት የጥላቻ፣ የቂም፣ የዘረኝነት፣ የጎጠኝነት የኃጢአት ማሰሪያ ይፈታን ዘንድ ‹‹እባክህ አሁን አድነን!›› እንበለው፡፡   ‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- አይሁድ፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን የምስጋና ባለቤት ከሆነው ዘንድ በተሰጣቸው ኃላፊነት ምስጋና የባሕርይው የሆነን ፈጣሬ ዓለማት መድኅን ዓለም ክርስቶስን ማመስገን፣ አመስግነው መመስገን፣ ቅዱስ ስሙን ጠርተው መቀደስ ሲገባቸው በተቃራኒው ልባቸው በጥላቻና በቅናት ተመልቶ የሚያመሰግኑት ዝም ይሉ ዘንድ ጠየቁ፤ አንደበትን ለምስጋና የፈጠረ ጌታ ግን ‹‹እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ›› አላቸው፤ ምንም የሚሳነው የሌለ ጌታም ድንጋዮች ያመሰግኑት ዘንድ አደረገ፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵)   ጌታችን በትምህርቱ ‹‹ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ክፉም ስለሆነ ሥራው እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም›› በማለት እንደገለጸው የክፋት ሥራቸውን የሚገልጥ፣ ጨለማ አስተሳሰባቸውን የሚያበራ የብርሃን ጌታ ሲመጣ የእርሱ መገለጥና መመስገን እነርሱን የሚያሳንስ ስለመሰላቸው ተቃወሙ፡፡ ክህነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነና  የሰጣቸውም እርሱ እንደሆነ ማስተዋል ቢሳናቸው የራሱን ገንዘብ ምስጋናውን ለማስቀረት ፈለጉ፤ (ዮሐ.፫፥፳) ማድረግ የማይቻላቸውን ሊያስቀሩ ደፈሩ፤ ክፉዎች  የቅኖች ደግነት፣ የመልካሞች በጎ ሥራ፣ የትሑታን የተሰበረ መንፈስና  የአመስጋኞች ምስጋናቸው ይረብሻቸዋል፡፡ ልቡናቸውን ለጠላት ዲያብሎስ ማኅደር ስላደረጉ የቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ሲጠራና ምስጋናው ሲደመጥ ሰላም ይነሳቸዋል። ዲያብሎስ  እግዚአብሔር ሲመሰገን፣ ሰው ንስሐ ሲገባ፣ የምሥራቹ ወንጌል ሲነገር፣ ምእመናን በቤተ እግዚአብሔር ሲበዙ፣ ሰላም ሲሰፍን፣ ሰዎች ሲፋቀሩ አንድነት ሲጸና፣ ሕገ እግዚአብሔር ሲከበር፣ ክርስትና ሲሰፋ፣ በዓላት ሲከበሩ ማየትና መስማት አይሻም፤ የግብር ልጆቹን እያሰማራ መንፈሳዊውን ዓለም ያውካል፤ ሁሉም እንደ እርሱ ከፈጣሪው ተጣልቶ በክህደት እንዲኖር ይፈልጋሉ። ዓለም ሳይፈጠር ባሕርይው ባሕርይውን እያመሰገነ ምስጋናው ሳይቋረጥ የኖረውን ጌታችንን በእናታቸው እቅፍ ያሉ ሕፃናት፣ አዕባን (ድንጋዮች) “ለምን አመሰገኑት” ብለው የቅናት ጥያቄ እንደጠየቁት ማለት ነው።   ዛሬም በሥጋ ለባሹ የሰው ልጅ አድሮ “ለምን አመሰገናችሁ? ለምን አምልኮተ እግዚአብሔር ፈጸማችሁ” በማለት ምስጋናውን ሊያስቀር ይጥራል፤ ግን አይቻለውም! እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በስሙ እንዳያስተምሩ፣ ባስፈራሯቸውም ጊዜ  ‹‹… ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል…›› አሉ፡፡ (የሐ. ሥራ ፭፥፳፱) እኛም ልጆቻቸው የአሠረ ፍኖታቸው ተከታይ ነንና! ዛቻና ማስፈራራቱን ሳንፈራ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ  አሁን አድነን››  እንላለን፡፡ አመስግነን እንመሰገን፣ ቀድሰን እንቀደስ ዘንድ ከባለጋራችን ዲያብሎስ የተቃውሞ ዛቻና በትር እንዲታደገን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…መድኃኒት ሁነን›› ብለን እንዘምራለን፡፡   ዲያብሎስ በግብር ልጆቹ ልቡና አድሮ በግፍ በትር ሊሸነቁጠን በተስፋ መቁረጥ ገመድ አስሮናልና  ቅዱሳን በቃል ኪዳናቸው ይፈቱን ዘንድ ይልክልን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን›› እንበለው፤ በነቢዩ ዘካርያስ  አማካኝነት ‹‹…የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በይ፥ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል…›› በማለት በተናገረው ቃል መሠረት መምህረ ትሕትና የዓለም ጌታ መድኅን ክርስቶስ በአህያይቱና በውርንጭላይቱ  ዘባን ( ጀርባ) ተቀምጦ ሲመጣ  በኢየሩሳሌም የነበሩ ልብሳቸውን ከምድር አነጠፉ፤ (ዘካ.፱፥፱) “እንኳን ለአንተ ለተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባል” ሲሉ! ትሕትናን ከእርሱ በተግባር ተምረዋልና በትሕትና የለበሱትን ልብስ አውልቀው ከምድር አነጠፉ፤ በጥቂት የትሕትና ሥራቸው ዝቅ ካሉበት ከሰጠሙበት የበደል አዘቅት ከፍ ያደርጋቸውና ያከብራቸው  ዘንድ  ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…!›› በማለት ተማጸኑት፤ እኛም ከልቡናችን እልፍኝ በጎ ሥነ ምግባር ልብሳችንን አንጥፈን ይገባበት ዘንድ ‹‹በሰማይ ያለ መድኃኒት ናልን›› ብለን እንጋብዘው፡፡   በሆሣዕና በዓል ዕለት በምስጋናው ጊዜ ዘንባባን እንይዛለን፤ ጌታችን በአህያና በውርንጭላይቱ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ከልብሳቸው በተጨማሪ የዘንባባ ዝንጣፊም ይዘው ነበር፤ በብሉይ ኪዳን ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ወጡ፤ ዮዲት ወገኖቿን ሲያስጨንቅ ንጹሐንን በግፍ ሲገድል የነበረውን ሆሎፎርኒስ የተባለን ሰው ገድላ በተመለሰች ጊዜ ዘንባባን ይዘው ደስታቸውን ገልጠዋል፡፡ አንድም ይላሉ መተርጉማነ አበው ‹‹ዘንባባ እሾኻማ ነው፤ ትእምርተ ኃይል (መዊእ) አለህ›› ሲሉት አንድም ዘንባባን እሳት አይበላውም፤ ለብልቦ ይተወዋል፤ ባሕርይ አይመረመርም›› ሲሉ ነው፡፡ የሰላም አለቃ፣ ኃያል፣ ልዑል፣ ባሕርይው የማይመረመር አምላካችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት ይሆነን፣ ያድነን ዘንድ በሕጉ ተጉዘን፣ ትእዛዙን፣ አክብረን፣ በትሩፋት ሥራ አጊጠንና የምግባር ዘንባባን ይዘን ጠላት ዲያብሎስን ድል አድርገን ‹‹ሆሣዕና›› እንበለው፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል አድምታ ትርጓሜ ፳፩፥፰) ዝቅ ካልንበት ከፍ ያደርገን ዘንድ ከእግሩ በታች ራሳችንን እናዋርድ፤ ‹‹… በመጠን ኑሩ፤ ንቁም ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና …›› እንደተባለው፤ (፩ኛጴጥ. ፭፥፰) በአህያ ውርንጭላ ጀርባ ተቀምጦ ስለ እኛ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከፍ አድርጎናል፤ ዳግመኛ በኃጢአት ቀንበር ወድቀን በባርነት እንዳንያዝም በጾምና በጸሎት ልንተጋ ያስፈልጋል፡፡   ‹‹አምላካችን ሆይ! እባክህ አሁን አድነን!›› ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ! አሜን  
12 350156Loading...
08
  ‹‹እባክህ አሁን አድነን!››   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹…ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና…››  በማለት  ትሕትናን በአንደበቱ ትምህርት ከማስተማሩ በተጓዳኝ በተግባር ሕይወቱም ተግብሮ ካሳየባቸው ዕለታት አንዱ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት ነው፤ (ማቴ.፲፩፥፳፱) ይህ ግሩም አምላክ በትሕትና ከተገለጠባቸው ዕለታት አንዱ የሆነው ድንቅ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሆሣዕና›› በመባል ይታወቃል፡፡ ሆሣዕና መተርጉማነ አበው በአንድምታቸው ‹‹ ሆሣዕና በአርያም በሰማይ ያለ መድኃኒት››  ብለው ተርጉመውልናል፤ (ማቴ.፳፩፥፱ ወንጌል አንድምታ)  አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደግሞ በመዝገበ ቃላታቸው ሆሣዕና ማለት ‹‹…እባክህ አሁን አድነን፤…መድኃኒት፣ መድኃኒት መሆን …›› በማለት ገልጸውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፫፻፸፫)   ‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- ይህን የተማጽኖ ቃል የተናገሩት ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ ሕዝብ ናቸው፡፡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ አንድም የወይራ ቅጠል እንዲሁም ልብሳቸውን ከምድር አንጥፈው ከልብ በመነጨ፣ ምስጋናቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ሆሣዕና በአርያም ‹‹…እባክህ አድነን…›› በማለት አመሰገኑት፡፡ የነቢየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት ትንቢት ተፈጽሞ በእናታቸው ጀርባ ያሉ የሚጠቡ ሕፃናት አመሰገኑ፤ ‹‹…ከሕፃናት ከሚጠቡ ልጆች አፍም ምስጋናን አዘጋጀህ…›› እንዲል፡፡ (መዝ.፰፥፪) 
11 428145Loading...
09
ዝክረ ቅድስት እናት ኢሪን እና መንፈሳዊ የትርጉም ፊልም የምረቃት መርሐግብር ተከናወነ። በማኅበረ ቅዱሳን መዝሙር እና ኪነ ጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት የዘመናችን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቅድስት እናት ኢሪንን የሚዘክር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካናውኗል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅድስቷን  የተጋድሎ ሕይወት እና ኦርቶዶክሳውያን ከሕይወቷ መማር የሚገባንን ትምህርት በተመለከተ መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል። በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የማኅበሩ አባላት እና ምእመናም የተገኙ ሲሆን በእናት ኢሪን ዙሪያ የተዘጋጀው መንፈሳዊ ትርጉም ፊልም የምረቃትም ሥነ ሥርዓትም  ተከናውኗል። መንፈሳዊ ፊልሙ  በዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን የዩቲዪብ ቻናል ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። https://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905?si=2jTnKZXGAfEJWRi7
2 2720Loading...
10
ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታዎቹ በመገኘት በተደረገው በዚህ የእጅ በእጅ ድጋፍ ርክክብ ወቅትም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካንና የማኅበረ ቅዱሳን ሽሬ እንደ ሥላሴ ማእከል ተወካዮች እንዲሁም የመንግሥት አካላት ተገኝተው ለተፈናቃዮች ድጋፉን አስረክበዋል። ይህ ድጋፍ በዚህ ዓመት በክልሉ ከተደረጉ ድጋፎች 2ኛ ዙር ድጋፍ ሲሆን በቀጣይ በአካባቢው በድርቅና ማኅበራዊ ቀውስ የተጎዱ ወገኖችን ኦርቶዶክሳዊነትንና ሰብአዊነትን መርሕ ባደረገ አግባብ ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ የሚሠራ ይሆናል። የማኅበረ ቅዱሳን #ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በ2016 ዓ.ም ባለፉት 7 የአገልግሎት ወራት ብቻ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃን አሞራ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሰቆጣና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተጎዱ የቅበት ኦርቶዶክሳዊያን፣ በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ መቐለ ኩሓ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና በትግራይ አጽቢ ወንበርታ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፎችን አድርሷል። በቀጣይ ጊዜያትም በድርቅ ለተጎዱ እንዲሁም በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ #ኑ ቸርነትን እናድርግ” በሚል መሪ ቃል እስከ ሚያዚያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም የወገኖቻችንን ሕይዎት ለመታደግ ብሎም ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶችን ከፍልሰት ለመታደግ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል። ድጋፍ ለማድረግ፡- #በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡- 1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901 2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458 3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648 4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101 5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 6. በጎ ፈንድ ሚ https://www.gofundme.com/f/uerc8... 7. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
5 1685Loading...
11
✝️ማኅበረ ቅዱሳን #በሽሬ እንደ ሥላሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 1.7 ሚሊዮን ብር ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ አደረገ፡፡  ✝️ +++ ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ መጠነ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በምእመናን፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ለማቃለል የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ማኅበራዊና ሰብአዊ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ይታወቃል። ማኅበሩ እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 6 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በዶዶላ፣ በአጋርፋ፣ በጅጅጋ፣ በሲዳማ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በፓዊ፣ በቡለን፣ ፣በሽሬ፣ በአክሱም፣ በቦረና ያቤሎ፣ በጎንደር አዘዞ፣ በአዲግራት፣ በማይ ጨው፣ በሽረ እንደ ሥላሴ ፣በመቐለ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣በሑመራ፣ በላሊበላ ፣በሐይቅ እስጢፋኖስ፣ በወሎ ገራዶ፣ በደባርቅ ፣በጃን አሞራና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ተጎጅዎች ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣ የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ተፈናቅለው #በሽሬ እንደ ሥላሴ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ 1033 አባወራዎች 1.7 ሚሊዮን ብር ወጭ የሆነበት 150 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም በአካባቢው ለሚገኙ አገልጋዮች የአልባሳት ድጋፎች ተደርገዋል። ድጋፉ የተደረገው ማስተባበሪያው ከአሜሪካ ማእከል ጋር በመሆን ባለፉት ጊዜያት በውጭ ዓለም ከሚገኙ ምእመናን ማኅበራዊ ድጋፍ ባሰባሰበበት ወቅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው።
970Loading...
12
የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ ዛሬ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በኤሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተካሄደ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቶች እንዲሁም አስተምህሮዎች ላይ ያተኰረ መዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፔዲያ) ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የሚዘጋጀው መዝገበ አእምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ ጥንታዊና ሐዋርያዊ አስተምህሮ፣ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት እንዲኹም የጳጳሳትን፣ የሊቃውንትን፣ የትልልቅ ገዳማትንና አድባራትን ታሪክ ወዘተ. የሚያካትት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የመዝገበ አእምሮ (ኢንሳይክሎፒዲያ) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ለማዘጋጀት እንዲቻል በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን ዕውቀታቸውንና ልምዳቸውን ማካፈል የሚችሉበት መድረክ ማዘጋጀት አስፈልጓል ተብሏል።
2 6250Loading...
በማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ንዑስ ማእከል ለገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ። ንዑስ ማዕከሉ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጉባኤውን  በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምስጋናው፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት አከናውኗል።  በዚህ መርሐ ግብር በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አህጉረ ስብከት ለሚገኙ ለአብነት ትምህርት ቤት መምህራን እና ተማሪዎች ድጋፍ የሚውል  የገቢ ማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል። ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች የተገበራቸውን ፕሮጀክቶችና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ገለጻ የተደረገ ሲሆን በዚህም ምእመናን እየተተገበሩ ስላሉ ሥራዎች ግንዛቤ አግኝተዋል። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ያሬድ ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አእማድ የሆኑ ገዳማትና ጉባኤ ቤቶችን እንዲደግፋ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት መሠረት ድጋፍ መሰብሰብ ተችሏል። በተመሳሳይ ሚያዚያ 12ና 13 /2016 ዓ.ም በሩስልስሃይም ደ/ምጥማቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ አብርሃም፣ የደብሩ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት ዐውደ ርዕይ እና ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳይ ጉዳት ለደረሰባቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ገንዘብ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ የተሰበሰቡ ድጋፎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች በማኅበሩ በኩል እንደሚውል ንዑስ ማእከሉ አስታውቋል።
نمایش همه...
نمایش همه...
MK TV || ቀጥታ ሥርጭት || ሰሙነ ሕማማት ከመ/ፓ/ቅ/ቅ/ ማርያም ገዳም - ዕለተ ሰኑይ

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

https://www.facebook.com/eotcmkidusan/

29🙏 13👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🙏 23 15👍 8
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለ582 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ክህነት ሰጡ። ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የምዕራብ አርሲ ፣ጉጂ፣ምዕራብ ጉጂ  ፣ቦረና  ሊበን  ሃጉረስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለ582 ደቀመዛሙርት ማዕረገ ክህነት በዛሬው እለት በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አ/ተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰጥተዋል። ለዲቁና ለቅስና እና ለቁምስና ፈተና ሲፈተኑ የቆዩ ተማሪዎች 546 ዲቁና፤34 የቅስና እና 3 የቁምስና ማዕረግ የተሰጣቸው ሲሆን  ከእነዚህ ውስጥ 171 ዲቁና እና 5 የቅስና ማዕረግ በአጠቃላይ 176 የተሰጣቸው በማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማዕከል እና ሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት  ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ጋር  በመተባበር ሲያስተምራችው የነበሩ ደቀመዛሙርት ናቸው። ማኅበረ ቅዱሳን ሻሸመኔ ማዕከል ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት  ጋር በመተባበር በዚህ ዓመት ከዚህ ቀደም ማዕረገ ክህነትን የተቀበሉ 61 ካህናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 237 ማዕረገ ክህነት እዲቀበሉ አድርጓል። በዛሬው ዕለት ክህነት የተቀበሉት አገልጋዮች በአካባቢው ያለውን የአካህናት እጥረት ለመፍታት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተጠቋሟል።
نمایش همه...
👍 6
https://youtu.be/Q0WJSswrkTo?si=ajqfBbrGS6e31m5Y ሰላምሽ ዛሬ ነው ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/፪/ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በኢየሩሳሌም አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/፪/      አዝ ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት/፪/   አዝ ኪሩቤል መንበሩን  የሚሸከሙት መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት/፪/   አዝ የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/፪/
نمایش همه...
"ሰላምሽ ዛሬ ነው"ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video)

"ሰላምሽ ዛሬ ነው"ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video) #MKZwT#ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን#Mahiberekidusan Subscribe:

https://www.youtube.com/channel/UC2U27bED0bj7ONXPNmBEKmA

Telegram:

https://t.me/+5e0PniMWKnsyMWFh

11👍 6
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም፣ ቤተ ፋጌ በቀረበ ጊዜ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሁለቱን ሐዋርያት ወደ ቤተ ፋጌ ልኮ የታሰረች አህያ እንደሚያገኙና ፈትተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን ጥያቄ የሚጠይቅ ሰው ከመጣ ‹‹…ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ…›› አላቸው፤ (ማቴ.፳፩፥፫) ፈትታችሁ አምጡ ማለቱ ሕዝቡን ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈቱበት ጊዜ እንደ ደረሰ ሲያጠይቅ ነው፡፡ ዛሬ ዓለም በሥጋዊ ጥቅም በኃላፊ ደስታ ዓይነ ልቡናችንን ጋርዳ፣ ሥጋዊ ፈቃዳችን ከፈቃደ ነፍሳችን አይሎ በኃጢአት ማዕሰር ታስረናል፡፡ ጌታችን በትምህርቱ ‹‹…ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው፤ ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም…›› በማለት እንደገለጸው በበደላችን በኃጢአት ባርነት ቀንበር ሥር ወድቀን በዲያብሎስ ባርነት ታስረናል ፤ (ዮሐ.፰፥፴፬) ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን››፤ ከታሰርነበት የጥላቻ፣ የቂም፣ የዘረኝነት፣ የጎጠኝነት የኃጢአት ማሰሪያ ይፈታን ዘንድ ‹‹እባክህ አሁን አድነን!›› እንበለው፡፡   ‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- አይሁድ፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን የምስጋና ባለቤት ከሆነው ዘንድ በተሰጣቸው ኃላፊነት ምስጋና የባሕርይው የሆነን ፈጣሬ ዓለማት መድኅን ዓለም ክርስቶስን ማመስገን፣ አመስግነው መመስገን፣ ቅዱስ ስሙን ጠርተው መቀደስ ሲገባቸው በተቃራኒው ልባቸው በጥላቻና በቅናት ተመልቶ የሚያመሰግኑት ዝም ይሉ ዘንድ ጠየቁ፤ አንደበትን ለምስጋና የፈጠረ ጌታ ግን ‹‹እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ›› አላቸው፤ ምንም የሚሳነው የሌለ ጌታም ድንጋዮች ያመሰግኑት ዘንድ አደረገ፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵)   ጌታችን በትምህርቱ ‹‹ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ክፉም ስለሆነ ሥራው እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም›› በማለት እንደገለጸው የክፋት ሥራቸውን የሚገልጥ፣ ጨለማ አስተሳሰባቸውን የሚያበራ የብርሃን ጌታ ሲመጣ የእርሱ መገለጥና መመስገን እነርሱን የሚያሳንስ ስለመሰላቸው ተቃወሙ፡፡ ክህነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነና  የሰጣቸውም እርሱ እንደሆነ ማስተዋል ቢሳናቸው የራሱን ገንዘብ ምስጋናውን ለማስቀረት ፈለጉ፤ (ዮሐ.፫፥፳) ማድረግ የማይቻላቸውን ሊያስቀሩ ደፈሩ፤ ክፉዎች  የቅኖች ደግነት፣ የመልካሞች በጎ ሥራ፣ የትሑታን የተሰበረ መንፈስና  የአመስጋኞች ምስጋናቸው ይረብሻቸዋል፡፡ ልቡናቸውን ለጠላት ዲያብሎስ ማኅደር ስላደረጉ የቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ሲጠራና ምስጋናው ሲደመጥ ሰላም ይነሳቸዋል። ዲያብሎስ  እግዚአብሔር ሲመሰገን፣ ሰው ንስሐ ሲገባ፣ የምሥራቹ ወንጌል ሲነገር፣ ምእመናን በቤተ እግዚአብሔር ሲበዙ፣ ሰላም ሲሰፍን፣ ሰዎች ሲፋቀሩ አንድነት ሲጸና፣ ሕገ እግዚአብሔር ሲከበር፣ ክርስትና ሲሰፋ፣ በዓላት ሲከበሩ ማየትና መስማት አይሻም፤ የግብር ልጆቹን እያሰማራ መንፈሳዊውን ዓለም ያውካል፤ ሁሉም እንደ እርሱ ከፈጣሪው ተጣልቶ በክህደት እንዲኖር ይፈልጋሉ። ዓለም ሳይፈጠር ባሕርይው ባሕርይውን እያመሰገነ ምስጋናው ሳይቋረጥ የኖረውን ጌታችንን በእናታቸው እቅፍ ያሉ ሕፃናት፣ አዕባን (ድንጋዮች) “ለምን አመሰገኑት” ብለው የቅናት ጥያቄ እንደጠየቁት ማለት ነው።   ዛሬም በሥጋ ለባሹ የሰው ልጅ አድሮ “ለምን አመሰገናችሁ? ለምን አምልኮተ እግዚአብሔር ፈጸማችሁ” በማለት ምስጋናውን ሊያስቀር ይጥራል፤ ግን አይቻለውም! እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በስሙ እንዳያስተምሩ፣ ባስፈራሯቸውም ጊዜ  ‹‹… ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል…›› አሉ፡፡ (የሐ. ሥራ ፭፥፳፱) እኛም ልጆቻቸው የአሠረ ፍኖታቸው ተከታይ ነንና! ዛቻና ማስፈራራቱን ሳንፈራ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ  አሁን አድነን››  እንላለን፡፡ አመስግነን እንመሰገን፣ ቀድሰን እንቀደስ ዘንድ ከባለጋራችን ዲያብሎስ የተቃውሞ ዛቻና በትር እንዲታደገን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…መድኃኒት ሁነን›› ብለን እንዘምራለን፡፡   ዲያብሎስ በግብር ልጆቹ ልቡና አድሮ በግፍ በትር ሊሸነቁጠን በተስፋ መቁረጥ ገመድ አስሮናልና  ቅዱሳን በቃል ኪዳናቸው ይፈቱን ዘንድ ይልክልን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን›› እንበለው፤ በነቢዩ ዘካርያስ  አማካኝነት ‹‹…የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በይ፥ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል…›› በማለት በተናገረው ቃል መሠረት መምህረ ትሕትና የዓለም ጌታ መድኅን ክርስቶስ በአህያይቱና በውርንጭላይቱ  ዘባን ( ጀርባ) ተቀምጦ ሲመጣ  በኢየሩሳሌም የነበሩ ልብሳቸውን ከምድር አነጠፉ፤ (ዘካ.፱፥፱) “እንኳን ለአንተ ለተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባል” ሲሉ! ትሕትናን ከእርሱ በተግባር ተምረዋልና በትሕትና የለበሱትን ልብስ አውልቀው ከምድር አነጠፉ፤ በጥቂት የትሕትና ሥራቸው ዝቅ ካሉበት ከሰጠሙበት የበደል አዘቅት ከፍ ያደርጋቸውና ያከብራቸው  ዘንድ  ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…!›› በማለት ተማጸኑት፤ እኛም ከልቡናችን እልፍኝ በጎ ሥነ ምግባር ልብሳችንን አንጥፈን ይገባበት ዘንድ ‹‹በሰማይ ያለ መድኃኒት ናልን›› ብለን እንጋብዘው፡፡   በሆሣዕና በዓል ዕለት በምስጋናው ጊዜ ዘንባባን እንይዛለን፤ ጌታችን በአህያና በውርንጭላይቱ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ከልብሳቸው በተጨማሪ የዘንባባ ዝንጣፊም ይዘው ነበር፤ በብሉይ ኪዳን ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ወጡ፤ ዮዲት ወገኖቿን ሲያስጨንቅ ንጹሐንን በግፍ ሲገድል የነበረውን ሆሎፎርኒስ የተባለን ሰው ገድላ በተመለሰች ጊዜ ዘንባባን ይዘው ደስታቸውን ገልጠዋል፡፡ አንድም ይላሉ መተርጉማነ አበው ‹‹ዘንባባ እሾኻማ ነው፤ ትእምርተ ኃይል (መዊእ) አለህ›› ሲሉት አንድም ዘንባባን እሳት አይበላውም፤ ለብልቦ ይተወዋል፤ ባሕርይ አይመረመርም›› ሲሉ ነው፡፡ የሰላም አለቃ፣ ኃያል፣ ልዑል፣ ባሕርይው የማይመረመር አምላካችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት ይሆነን፣ ያድነን ዘንድ በሕጉ ተጉዘን፣ ትእዛዙን፣ አክብረን፣ በትሩፋት ሥራ አጊጠንና የምግባር ዘንባባን ይዘን ጠላት ዲያብሎስን ድል አድርገን ‹‹ሆሣዕና›› እንበለው፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል አድምታ ትርጓሜ ፳፩፥፰) ዝቅ ካልንበት ከፍ ያደርገን ዘንድ ከእግሩ በታች ራሳችንን እናዋርድ፤ ‹‹… በመጠን ኑሩ፤ ንቁም ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና …›› እንደተባለው፤ (፩ኛጴጥ. ፭፥፰) በአህያ ውርንጭላ ጀርባ ተቀምጦ ስለ እኛ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከፍ አድርጎናል፤ ዳግመኛ በኃጢአት ቀንበር ወድቀን በባርነት እንዳንያዝም በጾምና በጸሎት ልንተጋ ያስፈልጋል፡፡   ‹‹አምላካችን ሆይ! እባክህ አሁን አድነን!›› ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ! አሜን  
نمایش همه...
33👍 18🥰 5🙏 4👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
  ‹‹እባክህ አሁን አድነን!››   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹…ከእኔ ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና…››  በማለት  ትሕትናን በአንደበቱ ትምህርት ከማስተማሩ በተጓዳኝ በተግባር ሕይወቱም ተግብሮ ካሳየባቸው ዕለታት አንዱ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት ነው፤ (ማቴ.፲፩፥፳፱) ይህ ግሩም አምላክ በትሕትና ከተገለጠባቸው ዕለታት አንዱ የሆነው ድንቅ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሆሣዕና›› በመባል ይታወቃል፡፡ ሆሣዕና መተርጉማነ አበው በአንድምታቸው ‹‹ ሆሣዕና በአርያም በሰማይ ያለ መድኃኒት››  ብለው ተርጉመውልናል(ማቴ.፳፩፥፱ ወንጌል አንድምታ)  አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ደግሞ በመዝገበ ቃላታቸው ሆሣዕና ማለት ‹‹…እባክህ አሁን አድነን፤…መድኃኒት፣ መድኃኒት መሆን …›› በማለት ገልጸውታል፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፫፻፸፫)   ‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- ይህን የተማጽኖ ቃል የተናገሩት ጌታችን በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ ሕዝብ ናቸው፡፡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው፣ አንድም የወይራ ቅጠል እንዲሁም ልብሳቸውን ከምድር አንጥፈው ከልብ በመነጨ፣ ምስጋናቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያሉ ሆሣዕና በአርያም ‹‹…እባክህ አድነን…›› በማለት አመሰገኑት፡፡ የነቢየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት ትንቢት ተፈጽሞ በእናታቸው ጀርባ ያሉ የሚጠቡ ሕፃናት አመሰገኑ፤ ‹‹…ከሕፃናት ከሚጠቡ ልጆች አፍም ምስጋናን አዘጋጀህ…›› እንዲል፡፡ (መዝ.፰፥፪) 
نمایش همه...
👍 22 5👏 5🥰 2
ዝክረ ቅድስት እናት ኢሪን እና መንፈሳዊ የትርጉም ፊልም የምረቃት መርሐግብር ተከናወነ። በማኅበረ ቅዱሳን መዝሙር እና ኪነ ጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት የዘመናችን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቅድስት እናት ኢሪንን የሚዘክር መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካናውኗል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅድስቷን  የተጋድሎ ሕይወት እና ኦርቶዶክሳውያን ከሕይወቷ መማር የሚገባንን ትምህርት በተመለከተ መነሻ ጽሑፍ ቀርቧል። በዕለቱ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የማኅበሩ አባላት እና ምእመናም የተገኙ ሲሆን በእናት ኢሪን ዙሪያ የተዘጋጀው መንፈሳዊ ትርጉም ፊልም የምረቃትም ሥነ ሥርዓትም  ተከናውኗል። መንፈሳዊ ፊልሙ  በዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን የዩቲዪብ ቻናል ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። https://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905?si=2jTnKZXGAfEJWRi7
نمایش همه...
ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታዎቹ በመገኘት በተደረገው በዚህ የእጅ በእጅ ድጋፍ ርክክብ ወቅትም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ልዑካንና የማኅበረ ቅዱሳን ሽሬ እንደ ሥላሴ ማእከል ተወካዮች እንዲሁም የመንግሥት አካላት ተገኝተው ለተፈናቃዮች ድጋፉን አስረክበዋል። ይህ ድጋፍ በዚህ ዓመት በክልሉ ከተደረጉ ድጋፎች 2ኛ ዙር ድጋፍ ሲሆን በቀጣይ በአካባቢው በድርቅና ማኅበራዊ ቀውስ የተጎዱ ወገኖችን ኦርቶዶክሳዊነትንና ሰብአዊነትን መርሕ ባደረገ አግባብ ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ የሚሠራ ይሆናል። የማኅበረ ቅዱሳን #ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በ2016 ዓ.ም ባለፉት 7 የአገልግሎት ወራት ብቻ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃን አሞራ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሰቆጣና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተጎዱ የቅበት ኦርቶዶክሳዊያን፣ በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ መቐለ ኩሓ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና በትግራይ አጽቢ ወንበርታ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፎችን አድርሷል። በቀጣይ ጊዜያትም በድርቅ ለተጎዱ እንዲሁም በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረስ #ኑ ቸርነትን እናድርግ” በሚል መሪ ቃል እስከ ሚያዚያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ የማኅበራዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ስለሆነም የወገኖቻችንን ሕይዎት ለመታደግ ብሎም ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶችን ከፍልሰት ለመታደግ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል። ድጋፍ ለማድረግ፡- #በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡- 1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901 2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458 3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648 4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101 5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 6. በጎ ፈንድ ሚ https://www.gofundme.com/f/uerc8... 7. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
نمایش همه...
ኑ! የክቡራን ወገኖቻችንን ሕይወት እናትርፍ !!!, organized by Mahibere Kidusan

ኑ! የክቡራን ወገኖቻችንን ሕይወት እናትርፍ !!! +++ ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት 6 ዓመታት በሀገራችን ኢትዮጵያ እያጋጠመ ባለው ማኅ… Mahibere Kidusan needs your support for ኑ! የክቡራን ወገኖቻችንን ሕይወት እናትርፍ !!!

👍 9 7