cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የምዕመናን መረጃ መለዋወጫና ትምህርት መስጫ አውታር ነው፡፡

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
35 125
مشترکین
+5324 ساعت
+177 روز
+14430 روز
آرشیو پست ها
Photo unavailableShow in Telegram
🙏 8 3
Photo unavailableShow in Telegram
30👍 12
Photo unavailableShow in Telegram
👍 47 8🥰 4🤔 3
Photo unavailableShow in Telegram
25👍 13👏 3🥰 2🤔 2
ማኅበረ ቅዱሳን በተጨማሪ ማእከላት የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ከ ኢትዮጵያ የደም ባንክ ጋር በመተባበር ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሐ ግብር በ25 ማእከላት ማከናወኑ ይታወሳል። ይህ የደም  ልገሳ መርሐ ግብር ዛሬም በተለያዩ የማኅበሩ ማእከላት ላይ ቀጥሎ ውሏል። ሰቆጣ፣ባሌሮቤ፣ዲላ እና ወሊሶ ማእከላት በዛሬው ዕለት የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አባላትን እና ምእመናንን በማስተባበር የደም ልገሳ መርሐ ግብራትን አከናውነዋል። ከመንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ በተለያዩ የማኅበራዊ ኃላፊነቶች ላይ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ባከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር እጅግ በርካታ አባላት ተሳትፎ በማድረግ የብዙ ወገኖቻችንን ሕይወት መታደግ የሚችል ደም መለገስ ችለዋል።
نمایش همه...
48🙏 10👍 9👏 3
نمایش همه...
👍 15 15🥰 2
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እና ይህንን የመሳሰለ ፈተና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር እየሰደደ መምጣቱን በእጅጉ አሳስቦታል፤ ይህ የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው የመለያየት አዝማሚያ በጣም ሰፍቶ ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረሱ በፊት በትምህርት በምክርና በተግሣጽ ማረም እንዳለበት ቅዱስ ጳውሎስ ተገንዝቦአል፤ እሱ ራሱም በአካል በመካከላቸው ተገኝቶ ሊያስተካክላቸው ፈቃደኛ ነበረ፤ ነገር ግን እሱ በዚህ ጊዜ በሮም ውስጥ እስር ቤት ላይ ስለነበረ አልቻለም፤ የነበረው አማራጭ በጽሑፍ ማስተማርና መምከር ነውና፤ ይህንን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዘላቂው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነግረን ‹‹ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም፤ ፈተናውም ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ይከባታል፤ የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ፣ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው፤ ባዕዳውያን አይሁድ ጌታን ይዘው የገደሉ የውስጥ ሰው የሆነው ይሁዳ በሰጣቸው ምልክት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጣችን ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው፤ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል፤ በአጠቃላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን የፈተነ መለያየት በቤተ ክርስቲያናችንም ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን ነው፤ የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ወልደን፣ በሀብተ ክህነት ሹመን፣ በመዐርገ ምንኩስና አልቀን በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ያስቀመጥናቸው ሰዎች በውኑ ‹‹እርስ በርስዋ የምትለያይ ቤት… የሚለውን አምላካዊ አስተምህሮ እንዴት ዘነጉት? ወይስ ድሮውንም ሳያውቁት ነው ኃላፊነቱ የተሰጣቸው? ወይስ ደግሞ ሆን ብለው ቃሉን ቸል ብለውታል? ሁሉም ውሉደ ክህነት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል፤ በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም፡፡ ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም፤ አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማእከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል ተፈጽሞአል አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል፤ ስለዚህ ይህ ቅዱስ ጉባኤ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡ ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖስ አባላት! የማኅበረ ሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው፤ በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡ በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው፤ ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል፤ ከዚህ በተረፈ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ወሳኝና ወቅታዊ እንዲሁም ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ነገሮችን በማየት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በመጨረሻም ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ስም እናበስራለን ፡፡ መልካም ጉባኤ ያደርግልን! እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፩ ቀን !፻0፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
نمایش همه...
🙏 51👍 37 14🥰 1
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! - ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ - ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! እግዚአብሔር አምላካችን በቤተ ክርስቲያን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል ለዚህ ሲኖዶሳዊ ምልአተ ጉባኤ እንኳን በሰላም አደረሰን! ‹‹አስተብቊዓክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትበሉ ኵልክሙ አሐደ ቃለ ወአሐደ ነገረ ወትኩኑ ፍጹማነ ወኢትትፋለጡ ወሀልዉ በአሐዱ ምክር ወበአሐዱ ልብ፤ ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፣ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (፩ቆሮ ፩፥፲)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ ሰዎች ለመጻፍ ሲያስብ አንድ ዓቢይ ምክንያት እንዳለው ከመልእክቱ ይዘት መረዳት ይቻላል፤ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነትንና ሰላምን ፍቅርንና መተባበርን ከምትሰብከው ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር ወጥተው ብዙ ርቀት ሂደዋል፤ አንድነቱ፣ ኅብረቱ መረዳዳቱ መተጋገዙና መተባበሩ ከመካከላቸው ጠፍቶአል፤ ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንኳ የሀብታምና የድሀ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኗን አደጋ ላይ ጥሎአል፡፡
نمایش همه...
👍 27🙏 8 5
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል። ምንጭ: የኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
نمایش همه...
60👍 24🙏 10
፪. በቦታ ያለመርጋት (አጽንኦ በዓት) አለመኖር፡- ትልቁ የአንድ መናኝ ፈተና አጽንኦ በዓት ማለትም በዓትን አጽንቶ ወዲያ ወዲህ ሳይሉ ከቦታ ቦታ ከመዘዋወር ተቆጥቦ በገዳም መኖር አለመቻል ነው፡፡ የምንኩስና ጀማሪው አባ ጳውሊ ይሁን እንጅ መልክና ቁመና የሰጠው አባ እንጦንስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አባ አንጦንስ ከ፪፻፶፩-፫፻፶፮ ዓ.ም ለ፻፭ ዓመት የኖረ አባት ሲሆን በአባ እንጦንስ እንደ መነኮሰ የሚነገርለት ቅዱስ አትናቴዎስ ጽፎታል ተብሎ የሚታመነው የአባ እንጦንስን ታሪክ አባ እንጦንስ በ፹፭ የምናኔ ዓመታት ከበአቱ የወጣው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ይባላል፡፡ (ገድለ አባ እንጦንስ) አንድ ጊዜ በመክስምያኖስ ስደት የደረሰባቸውን ክርስቲያኖች ለማጽናናት በ፫፻፲፩ ዓ.ም ሲሆን ሁለተኛው አርዮሳውያን በአትናቴዎስ ላይ በተነሱ ጊዜ በ፫፻፴፰ ዓ.ም ለተመሳሳይ ዓላማ ወጥቷል፡፡ በሕንጻ መነኮሳትም ‹‹በአቱን ትቶ ከቦታው ውጭ የሚያድር መነኩሴ አይኑር›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ክፍ. ፪ ቁጥ ፭) ሕንጻ መነኮሳት በዚህ ሳይወሰን መነኮሳትን የሚያረክሱ አምስት ነገሮች ብሎ ከሚዘረዝራቸው አንዱ ‹‹ከቦታ ቦታ ከሀገር ሀገር መዘዋወር›› ነው ይላል፡፡ ‹‹በገዳም መኖር ማቅ መልበስ፣ በዝናር መታጠቅ ይገባል›› የሚል ሕግ ቢኖርም አሁን ያለው ችግር ከገዳም መውጣት ከገዳም ገዳም መዘዋወር አይደለም፤ እርሱስ ቢሆን በተሻለ ነበር፡፡(ፍት.መን. አንቀጽ ፲ ቁ ፫፻፶፯) ከገዳም ወደ ከተማ ከከተማም ወደሌላው ከተማ፣ ከሀገር ወደ ውጭ ሀገር ያለው የመነኮሳት ፍልሰትና እንቅስቃሴ እጅግ ከባድ ነው፡፡ ‹‹ለመነኩሴ ከተማ መግባት፣ አደባባይ ተቀምጦ መፍረድ፣ ምስክርነት ዋስነት አይገባውም፡፡ ለምውት ይህ ሁሉ ሥራው አይደለምና›› ተብሎ ቢጻፍም አሁን ላይ ብዙ ገዳማት ባዶ ናቸው፤ ጥቂቶቹም ጥቂት መነኮሳት ብቻ ይኖሩባቸዋል፤ መናንያኑ ከተሞችን ሞልተውታል፤ ግብረ ምነኩስናን የሚፈጽሙበት፣ ለአገልግሎት ለትሩፋት የሚፋጠኑበት ጊዜ የላቸውም፤ በጣም ከዓለማዊው ሰው ባነሰና በሚያስደነግጥ በዓለማዊ ሐሳብና ግብር ላይ ተጠምደው ይታያሉ፤ ያሰቡትን የሚያሳካ ፍላጎታቸውን የሚያረካ ነገር ሳያገኙ ሲቀሩ ባልተገባ አኳኋን ባልተገባ ቦታ የሚገኙ ወንጀል የሚሰሩ በርካታ መነኮሳት የታዩበት ዘመን ነው፡፡ (መ-ምዕዳን ገጽ ፻፶፪) ፫. በዚህ ዓለም ሐሳብ መሸነፍ፡- በገንዘብ ፍቅር መሸነፍ ሁሉን ትተው ፍጹም ይሆኑ ዘንድ የተከተሉ መነኮሳት ትተውት ከሄዱት ዓለም ተመልሰው ሀብትና ባለጸግነትን በመሻት ብዙዎች ወድቀዋል፡፡ አንድ መነኩሴ/መነኩሲት እንዲመንኑ የገፋቸው አምላካዊ ቃል ‹‹ሂደህ ገንዘብህን ሁሉ ሸጠህ ለነዳያን መጽውት፤ በሰማይም ድልብን ታከማቻለህ ና ተከተለኝ›› የሚለው ነው፡፡ (ማቴ.፲፱፥፳፩) አሁን ውሻ ወደ ትፋቱ እንዲመለስ ተፍተውት የሄዱትን ሀብት ፍለጋ ብዙዎች በገንዘብ ፍቅር ወድቀዋል፡፡ አርአያ ምንኩስናን ፈተና ላይ ጥለዋል፤ ስለሚነዱት መኪና ስለሚሰሩት ፎቅና ምድር፣ ስለሚያጌጡበት ወርቅና ብር የሚጨነቁ፣ ይህን ክፉ መሻታቸውን ለማሳካትም በየፍርድ ቤቱ በየመንግሥት ተቋማቱ ደጅ ተሰልፈው በክርክርና በንትርክ በአሕዛብ መድረክ ዳኝነት የሚፈልጉ ብዙ መነኮሳትን እንመለከታለን፡፡ በአንድ ወቅት የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ማኔጅመንትን ያጨናነቁ መነኮሳትና የደብር አለቆች መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ተሰራጭቶ ተመልክተናል፡፡ (መገናኛ ብዙኃናት) ይህ ብቻ ሳይሆን እነዚህ መነኮሳት በሕይወት ሲያልፉ የሚነሳው የወራሽነት መብት ጥያቄና ሙግት በራሱ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር የሚያዋርድ፣ ምእመናንን አንገት የሚያስደፋ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ በተራ መነኮሳት ሳይወሰን በአንዳድ ጳጳሳትም ዘንድ ይስተዋላል፡፡ በሥልጣን ፍቅር መውደቅ፡- የአንድ መናኝ (መነኩሴ) ሥልጣንን ሹመትን መሻት አንዱ የፈተናው ምንጭ እንደሆነና እንዲጠነቀቅ መጽሐፍ ይመክራል፡፡ ፍትሐ ነገስሥት እንዲህ ይላል፤ ‹‹የሹመት ፍቅር ሰይጣናዊ በሽታ ነውና በዚህ በሽታ ላይ የወደቀ ሰው ካህናትና ሹማምንት ሊሆኑ በሚገባቸው ላይ ቀናተኛ ይሆናል፡፡ ሰው ጠቅሶ ያነሳሳባቸዋል፡፡ በእነርሱ ሹመት ይተካ ዘንድ ሞታቸውን ይወዳል፡፡ ሹመቱ ባልሆነለት ጊዜ በርሱና በነርሱ ችግር ይፈጠራል፡፡ ከዚህ መጥፎ ፈቃድ ይራቅ እንጅ፡፡›› (ፍ.መ አ.፫፣ ቁ. ፫፻፹፭) ብዙ መነኮሳት በዛሬዋ ቤተ ክርስቲያናችን ተፈትነው የወደቁበት ፈተና ነው፡፡ አለቃ ለመሆን፣ ጸሐፊ ለመሆን፣ የመምሪያ ኃላፊ ወይም ሌላ ሥልጣን በመሻት ቦታቸውን ለመንጠቅ፣ በተሾሙት ፋንታ ለመሾም፣ በተቀቡት ቦታ ለመቀመጥ አባቶቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ለመወንጀል በዓለም ያሉ ተባባሪዎችን ለማግኘት የጠላት በር ሳይቀር ያንኳኳሉ፤ የተከበሩትን ያዋርዳሉ፤ በሐሰት ክስም ይከሷቸዋል ክፉዎችን ቀስቅሰው ያነሳሱባቸዋል፡፡ አሁን ደረጃውን ከፍ አድርጎ እስከ ጵጵስናም ደርሷል፡፡ መጽሐፍ ግን ‹‹ወኢያፍቅር ምንተኒ ዘዝንቱ ዓለም፤ የዚህን ዓለም ምንም ምን አይውደድ›› ነው የሚለው፡፡ (መጽሐፈ ምዕዳን ገጽ ፶፩) በሥጋ ምቾት መጠመድ፡- ብዙ መነኮሳት በሥጋዊ ምቾት ውስጥ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን እንዳንበላ፣ እንዳንጠጣ፣ እንዳንለብስ፣ እንዳናጌጥና እንዳይመቸን አይደለም የፈጠረን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አላፊ ጠፊ መሆናቸውን ተገንዝበን ሁሉንም በመጠን በአግባቡ በሥርዓት ብናደርገው በሚያልፈው ዓለም ውስጥ የተውነው ምቾት በማያልፈው ዓለም ውስጥ ዋጋ እንደሚያሰጠን በተለይ ለመነኮሳት ሲሆን የበለጠ መሆኑን በቀኖና መጻሕፍት ተጽፎ እናነባለን፡፡ እንኳንስ መነኮሳት የዚህን ዓለም ውበቱን ድምቀቱን፣ መብሉን መጠጡን ትተው የመነኑትን፣ ራሳቸውን በፈቃዳቸው ከሙታን ዓለም የቆጠሩትን ቀርቶ ሕዝባውያንም በሚበላ በሚጠጣ በሚለበስ ነገር ሁሉ በመጠን እንዲኖሩ ታዟል፡፡ ይሁንና አሁን ላይ ብዙዎች በሥጋ ምቾት በመብል መጠጥ ተጠልፈው ፈተና ብዝቶባቸው ለምእመናንም ለቤተ ክርስቲያንም ኃፍረት ሲሆኑ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ሕንጻ መነኮሳት ‹‹መነኩሴን ከሚያረክሱ ነገሮች አንዱ ከመጠን በላይ መብላትና መጠጣት ነው››ይላል፡፡ መጽሐፈ ምዕዳን ደግሞ ‹‹መነኩሴ የእንጦንስን የመቃርስን የቅዱሳንን ገድል ይመልከት፤ እንዲጸና ምግብ ይክፈል፡፡ አይምረጥ፤ የመጠጥንም ነገር የጽም ያህል ይጠጣ፡፡ ሥጋ አይብላ፤ ወይን ጠጅ አይጠጣ፡፡ ለመነኩሴ ምሳ የለውም፡፡ ዓመት እስከ ዓመት ጾም ነው እንጅ መነኩሴ ምሳውን ከበላ ሴት ከወንድ ጋራ አድራ በማኅፀኗ ልጅ እንዲፀነስ በሰውነቱ ሦስት ነገሮች ይፀነስበታል፡፡ ትዕቢት፣ ምንዝርነት፣ ቁጣ ይመጣበታል፤ ከዚህ በኋላ ሰይጣን ይሰለጥንበታል፤ ቆቡን ከመቅደድ፣ ዲቃላ ከመውለድ ያደርሰዋል፤ የንጽሕና መሣሪያ ከመብል መከልከል ነው›› ይላል፡። (ገጽ ፻፶፩) አሁን ሁሉም ነገር እየሆነ ነው፡፡ ብዙዎች በሆዳቸው ተገምግመዋል፤ በትዕቢትም፣ በቁጣም፣ በምንዝርነትም እየተፈተኑ ያሉበት ዘመን ነው፡፡ ይቆየን!
نمایش همه...
🙏 34 20👍 16🥰 3👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ›› ክፍል ሰባት ተወዳጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ! በክፍል ስድስት “ክብረ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ክብርና ሞገስ ያስገኘውን የቅድስና ፍሬና ያሳረፈውን አሻራ” አንስተን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ በዚህ በክፍል ሰባት ደግሞ ምንኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያጋጠመው ያለውን ተግዳሮት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ ቀደም ብለን እንደ ተመለከትነው ምንኩስና ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን፣ ከሰው ይልቅ የመላእክትን ግብር መምረጥ፣ ፍጹም ሆኖ ፍጹም የሆነችውን መንግሥት ለመውረስ ሁሉን ትቶ መመነን፣ ከሰው ከዓለም መለየት፣ በገዳም በአጽንዖ በአት፣ በግብረ ምንኩስና መወሰን መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ በዘመናችን ምንኩስና በዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ውስጥ ይገኛል፤ የተወሰኑ ችግሮችን ለማሳየት ያህል፡- ፩. የምንኩስና ሥርዓትን ተከትሎ አለመመንኮስ፡- በገዳም ሕግ አንድ መናኝ ሁሉንም ትቶ ወደ ገዳም ሲገባና “እመነኩሳለሁ” ሲል በገዳሙ ያለውን ሥርዓተ መነኮሳት መማርና መጠበቅ፣ የተቀመጠውን የአበው ሥርዓት ማክበር፣ በጉልበቱ እንጨት ሰብሮ፣ ውኃ ቀድቶ፣ ከብት ነድቶ፣ ቡኮ አብኩቶ፣ ዳቤ ጋግሮ በእርድና መነኮሳትን መርዳት ይገባዋል፡፡ ‹‹መነኮሳትን ሳይረዱ “እመነኩሳለሁ” ማለት ሳይበጡ መታገም ነው፡። ምክንያቱም ከሁሉም እርድና ይበልጣልና ከእርድና በኋላ ቢመነኩስ ይጠቅማል›› ይላል መጽሐፈ ምዕዳን፡፡ (ገጽ ፻፶) ይሁን እንጅ በአሁኑ ሰዓት የአመክሮ ጊዜ የሌላቸው ገዳማትን አበው መነኮሳትን በጉልበታቸው በእርድና ያላገለገሉ፣ የኋላ ታሪካቸውና የወደፊት ትልማቸው ያልተገመገመ፣ አንዳዶቹም የትና በማን እንደመነኮሱ የማይታወቁ፣ ተጠየቅ የሌለበት የምንኩስና ሥርዓት ቤተ ክርስቲያንን ፈትኗታል፡፡
نمایش همه...
👍 11 7
የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወኑ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ከ ኢትዮጵያ የደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሐ ግብር በአከናውኗል። ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም በተከናወነው የልገሳ መርሐ ግብር የማኅበሩ መዋቅሮች በሚገኙባቸው የተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ምእመናን እና የማኅበሩ አባላት ተሳታፊ ሆነውበታል። ማኅበረ ቅዱሳን ከመንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ በማኅበራዊ ኃላፊነቶች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ተሳትፎ የሚያደርግ ሲሆን ይህ የደም ልገሳ መርሐ ግብርም አንዱ ማሳያ መሆኑ በዕለቱ ተጠቁሟል። በደም ልገሳው ተሳታፊ የሆኑ የአባላት እንደገለጹት የማይተካውን የሰው ልጅ ሕይወት በሚተካው ደም መታደግ የሁሉም ማኅበረሰብ ኃላፊነት እንደሆነ ገልጸው ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል። በትናንትናው ዕለት በ25 ከተሞች ላይ የማኅበሩ የደም ልገሳ መርሐ ግብር መከናወኑ ማወቅ ተችሏል።
نمایش همه...
51👍 18🥰 3👏 2
በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት አገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል። ማኅበረ ቅዱሳን ከኢትዮጵያ የደም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐ ገብር በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየተከናወነ ይገኛል። አዲስ አበባ በሚገኘው የማኅበሩ ዋና ማእከል ጽ/ቤት በተከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ በርካታ ምእመናን ተገኝተው በመለገስ ላይ ይገኛሉ።
نمایش همه...
85👍 13🙏 4